Monday, June 10, 2013

የደቂቀ እስጢፋኖስ ገዳማት በሊባኖስ ተገኙ

ለብዙ ምእት ዓመታት ታሪካቸው ተቀብሮ የኖረውና በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ አማካይነት ከመቃብሩ እንዲወጣና ትንሣኤን እንዲያገኝ የተደረጉትና በአንድ ጥራዝ የታተሙት የአባ እስጢፋኖስና የተከታዮቻቸው የገድል መጻሕፍት  ማለትም ገድለ አባ እስጢፋኖስ፣ ገድለ አበው ወአኀው፣ ገድለ አባ አበከረዙንና ገድለ አባ ዕዝራ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትልቅ መነቃቃትን እየፈጠሩ ይገኛል፡፡ አንዳንዶች ደቂቀ እስጢፋኖስን ሌላ ዓላማ የነበራቸው እንጂ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች አይደሉም ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው ግን የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሩቅ ሳንሄድ በገድላቸው የተንጸባረቁት ተሐድሶአዊ ሐሳቦችና በእነርሱ ላይ ስደት ካወጀባቸው ከአፄ ዘርአ ያዕቆብ በኩል የተሰጣቸው ስምና ከተጻፈባቸውና ከተነገረባቸው ውንጀላ መረዳት ይቻላል፡፡
የደቂቀ እስጢፋኖስ ገድላት ተርጓሚው ፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌም “ታሪካቸውን እዚህ የማቀርበው አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው (ደቂቀ እስጢፋኖስ) የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የማትቀበላቸው እንዲያውም የተወገዙ አድርጋ የምታያቸው በዐሥራ ዐምስተኛው ምእት ዓመት ያበቡ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች ናቸው፡፡ አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠው ሥርዓት (Establishment) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ አእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥኦ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው” (ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ፣ ገጽ 23)፡፡
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከምናገኛቸው የደቂቀ እስጢፋኖስ አገልግሎቶች መካከል አንዱ በእምነታቸው ምክንያት ሲሰደዱ በየተሰደዱበት ወንጌልን መስበካቸውና ክርስትናን ማስፋፋታቸው፣ በየደረሱበት አብያተ ክርስቲያናትን መትከላቸው ነው፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የተወሰነ ብቻ እንዳልነበረ በቅርቡ ይፋ ከተደረገው ጥናት መረዳት ተችሏል፤ በቅርቡ የተሰማው ዜና ደቂቀ እስጢፋኖስ በተሰደዱበት በሊባኖስ አሻራቸው መገኘቱን ያመለክታል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ለንባብ ያበቃው የዜናው ሙሉ ዘገባ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያውያን 15ኛው ክፍለ ዘመን ገዳማት በሊባኖስ ተገኙ
ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ የግንቦት 25/2005 ዓ.ም. እትም
በሄኖክ ያሬድ
·        በዋሻው የተገኙት የግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ማረጋገጫ ሆነዋል
·        ሰዎቹ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ናቸው
·        ወደ ሊባኖስ የሄዱት በወንጌል መልዕክተኝነት ነው
ኢትዮጵያውያን መነኮሳት 15ኛው ክፍለ ዘመን በሊባኖስ ቀዲሻ ሸለቆ (Holy Valley) ይገለገሉባቸው የነበሩ አራት ገዳማት ከግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ጋር ተገኙ፡፡
ኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲና ካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል ግንቦት 20 ቀን 2005 .. በጋራ ባዘጋጁት የግእዝና የሱርስጥ (የሶርያ ቋንቋ) ጥናቶች ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ጥናታቸውን ያቀረቡት አብዶ በድዊ፣ በገዳማቱ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ጽሑፍና የቅዱሳንና የመስቀል ሥዕሎች መገኘታቸው ገዳማቱ የኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ያሳያሉ ብለዋል፡፡ 
‹‹አሕባሽ›› የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን መነኮሳት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንና 15ኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ሊባኖስ ተራራዎች በተለያዩ አጥቢያዎች የኖሩ ናቸው፡፡ ገዳማቱም ማር ያዕቆብ በኢሕደን (Ehden) ማር ጊዮርጊስ በሐድቺት (Hadchite) ዴር ኤል ፍራዲስ እና ማር አስያ ናቸው፡፡
ጂኢአርኤስኤል የተሰኘ የጥናት ቡድን ..አ. 1991 የግእዝ የድንጋይ ላይ ጽሑፍና የተለያዩ መንፈሳዊ ሥዕሎች ማግኘቱን ሊባኖሳዊው አብዶ በድዊ ተናግረዋል፡፡ 
መነኮሳቱ በደብረ ሊባኖስ እንዴት ሊገኙ እንደቻሉ የተለያዩ መላምቶች እንዳሉ ያወሱት አጥኚው፣ አንዱ በእምነት የሚመስሏቸውን የግብፅ ኮፕቲኮችን የወንጌል መልዕክተኛነትን ለማገዝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ 
መነኮሳቱ ሊባኖስ ተራራ (ደብረ ሊባኖስ) የደረሱት 1470 እና 1488 መካከል መሆኑን በሥፍራው የነበሩትን የማሮናይት እምነት ተከታዮችን በስብከታቸው ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መለወጣቸው ይነገራል፡፡ ከነዚህም አንዱ በኋላ ላይ የያዕቆባውያን ፓትርያርክ የሆኑት የብቆፋው ኖኅ (Nouh of Bqoufa) ይገኙበታል፡፡ 
በአካባቢው አጠራር ኢትዮጵያውያንን ለመጥራት በሚጠቀሙበት አሕባሽ የሚጠሩት ኢትዮጵያውያን 15ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከደረሰባቸው ጥቃት የሸሹ ደቂቀ እስጢፋኖስ መሆናቸውን ተመራማሪዎች እንደደረሱበት አብዶ በድዊ ተናግረዋል፡፡ 
‹‹በርካቶች እንደሚያምኑት፣ ከነዚህም መካከል ኢቫ ዊታኮውስኪ (Eva Witakowsky) እንደሚሉት መነኮሳቱ ደቂቀ እስጢፋኖስ ናቸው፡፡ በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ወገኖቻቸው ከደረሰባቸው ፍጅት አምልጠው ኢየሩሳሌም፣ ቆጵሮስ፣ ሊባኖስ፣ ሶርያና አርመን ድረስም የተሰደዱ ናቸው፡፡ ሊባኖስ እንደደረሱ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል በተለያዩ አጥቢያዎች ቀዲሻ (ቅዱስ) ብለው በሰየሙት ቦታ መኖር ጀምረዋል፡፡›› 
የግድግዳ ላይ ሥዕሎችና የግእዝ ጽሑፍ ከሱርስት ቋንቋ ጽሑፍ ጋር የተገኙት በማር አስያ፣ ማር ጊዮርጊስና ማር ዮሃና ገዳማት መሆኑን ያወሱት አቅራቢው፣ ከተገኙት ሥዕሎች አንዱ የፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምስል ላሊበላ ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ካለው ጋር ይመሳሰላል ብለዋል፡፡ በማር ሙሳ አልሐበሺ ያለውም ጋይንት ቤተልሔም (ደቡብ ጎንደር) ካለው ጋር ተመሳስሎ እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡ 
የግእዝ ጽሑፉ ከፊሉ የጠፋ ሲሆን፣ ያሉትን የግእዝ ቃላት የቋንቋው ፕሮፌሰሮች ባደረጉት ጥናት ኃይለ ቃሉ ጸሎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹መሐረነ እስከ ለዓለመ ዓለም አሜን›› (ለዓለም እስከ ዘለዓለም ማረን አሜን) ይላል፡፡ 
በጉዳዩ ላይ ቀጣይ ጥናት እንደሚደረግበትም አብዶ በድዊ ሳይናገሩ አላለፉም፡፡
አስኮ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል ከግንቦት 19-22 2005 .. ድረስ በተካሄደው የግእዝና የሱርስጥ ጥናቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ከኢትዮጵያ ሌላ ከሩቅ ምሥራቅ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የመጡ ምሁራን 25 ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡  


16 comments:

 1. eshi demo bezih metachihu? I thought You didn't believe in Gedlat and Teamrat. wechew gud, ere atizelabidu. wey mamen new weyy metew new.

  ReplyDelete
 2. The document revealed that Atse Zereyakob's palace priests who enjoyed the special treatments were in constant feud with Deqike Estifanos for they were more to rever king Zeriakob to Jesus. Aba Estifanoses asserted that they worshiped only Jesus Christ while the respect for Saint Mary could not even be equiated with the creator leave alone with the king. The palace priests intentionaly misguided Atse Zereiakob whom he had a strong passion for Mother Mercy that Deqike Estifanos were anti St. Mary. The king later swore to perish them. May find some astonishing facts from the documents. Thank you Aba Selama for bring it on. The road to weed ot all obscure tales and rveal the true Orthodox history

  ReplyDelete
 3. አይ ተሃድሶ ዘመድ ለማግኘት የማታደርጉት ጥረት የለም:: እናንተ ከመሰረት ስባት በስተቀር ኢትዮጵያ ውስጥ ጀማሪ የላችሁም። እሱም ኪሱን አስብቶ ነው የሞተው። በቅርቡ በፕሮፌሰር ጌታቸው የተተረጎመው [ፕ/ር ሳይተረጉሙት በፊት እኮ እናንተ ፈጥራችሁ ስንት ነገር ስትፅፉ ነበር። እግዚአብሄር ይስጥልን ፕ/ር] የደቂቀ እስጢፋኖስና የተከታዮቹ ታሪክ ትክክለኛ ከሆነና የነሱን ታሪክ ብቻ ተቀብለን ካነበብነው እንኳን ከእናንተ በብዙ ይለያሉ::
  ከልዩነታችሁ መካከል
  • እነርሱ መነኮሳት የነበሩ በትርህምት የሚኖሩ ነበሩ እናንተ ምንኩስናን ትቃወማላችሁ
  • እነርሱ በመልካም ስራ የሚያምኑ በሃይማኖት ጸንተው በሃይማኖትም ለመኖር የሚታገሉ ነበሩ እናንተ መልካም ስራ ለጽድቅ ዋጋ የለውም የምትሉ ናችሁ
  • እነርሱ አዲስ የመሰላቸውን ነገር /ለማርያም መስገድን/ አንቀበልም ቢሉም ጳጳሱ ባስተማራቸው ጊዜ የተረዱና ለድንግል ማርያም ስግደትን ያቀረቡ ናቸው በአንጻሩ እናንተ እንደማታደርጉ የታወቀ ነው::
  • እነርሱ አባቶቻቸው ያስተማሯቸውን ለመጠበቅ የተጉ ናቸው እናንተ ደግሞ ፈረንጂ የነገራችሁንና ለማድረግ
  • እነርሱ በድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት የሚያምኑ የሚማጸኑ እንደነበር ተጽፏል እናንተ ይህንን እንደ ፌዝ እንደምትቆጥሩት ዌብሳይታችሁ አሳይታናለች ሌላም ብዙ መጨመር ይቻላል::


  በተጨማሪ እንዲህ አንደሚልስ ታውቃለህ:: "በዛ ላይ አንደ ሌሎቹ ሁሉ የቅዱስ ኤፍሬምን ውዳሴ ማርያም እና የቅዱስ ያሬድን አንቀጸ ብርሃን ይደግሙ ነበረ:: [እነ ደቂቀ እስጢፋ] እነዚህ ሁለት ድርሰቶች እመቤታችንን የሚያደንቁና የሚያመሰግኑ:በየአንቀጹ 'ሰአሊነ ቅድስት' (ቅድስት ሆይ: ኃጢያታችንን ይቅር እንዲለን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ አማልጅን) የሚል ንባብ ያለባቸው ናቸው::ጳጳሱም ለቅድስት ድንግል ማርያም ብትሰግዱ ስህተት አይሆንባቹም ብለዋቸው አብረው መስገዳቸውን መስክረዋል::" ገጽ 30

  አንተ አሁን ገድለ እስጢፋኖስ ተቀብለህ ታምረ ማርያምን ለማቃለል ትሞክራለህ? ነው ወይስ አጼ ዘርዓ ያዕቆብን ይሰድብልኛል ብለህ ነው? ገድለ እስጢፋኖስም እኮ አስከሬናቸውን ፈወሰ ይላል:: አመንከው????? እና እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነው እስከችግሩ ነው የምንቀበለው:: አንተ ካልተመቸህ ከቤተክርስቲያናችን ውልቅ በልልን:: ጌታ እውነተኛ ይወዳልና ነገሮችን ከእውነት ጀምር::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you.
   እነዚህ የሀሰት ልጆች የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ለጥፋታቸዉ ምክንያት ለመስጠት እግዚአብሔር ይሁናቸዉ

   Delete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማልን። አንጀቴን አራስከው።

   Delete
 4. What can I say? I have a word to say(Hidden Treasure)These three Revival,renewal and reformation are Golden Words of Ethiopian Real Saints.One of them was the Great fifteenth century
  Real Person who worships The Most High in Exile in
  Lebanon.As Qumranites did in western part of Dead sea two thousand Years ago.Aba Selama has to continue this Enlightening Hidden History as much as possible.Thank you for that.

  ReplyDelete
 5. What can I say? I have a word to say(Hidden Treasure)These three Revival,renewal and reformation are Golden Words of Ethiopian Real Saints.One of them was the Great fifteenth century
  Real Person who worships The Most High in Exile in
  Lebanon.As Qumranites did in western part of Dead sea two thousand Years ago.Aba Selama has to continue this Enlightening Hidden History as much as possible.Thank you for that.

  ReplyDelete
 6. ምን ማረጋገጫ አግኝታችኹ ነው የ ደቂቀ እስጢፋኖስ ነው የምትሉት ? ዝምብሎ አንስቶ አልሆነ ቦታ መመረግ አይሆንም ? እባካችሁ ያልሆነ ውዥንብር አትፍጠሩ ከ ሀገር ወጪ የሚገኙትን ገዳማት ሁሉ በዚ መልክ ልትሰይሙት ይሆን ? ተባረው ሳይሆን እግዜያብኤር በመራቸው ቦታ እየዞሩ ገዳም እንደሚገደሙ እና ወንጌል እንደሚሰብኩም አንርሳ እንጂ እባካችሁ የተዋህዶን ታሪክ አናፋልስ ::

  ReplyDelete
 7. ምን ማረጋገጫ አግኝታችኹ ነው የ ደቂቀ እስጢፋኖስ ነው የምትሉት ? ዝምብሎ አንስቶ አልሆነ ቦታ መመረግ አይሆንም ? እባካችሁ ያልሆነ ውዥንብር አትፍጠሩ ከ ሀገር ወጪ የሚገኙትን ገዳማት ሁሉ በዚ መልክ ልትሰይሙት ይሆን ? ተባረው ሳይሆን እግዜያብኤር በመራቸው ቦታ እየዞሩ ገዳም እንደሚገደሙ እና ወንጌል እንደሚሰብኩም አንርሳ እንጂ እባካችሁ የተዋህዶን ታሪክ አናፋልስ ::

  ReplyDelete
 8. it may help for the reformation of the church

  ReplyDelete
 9. These monks that were in Lebanos were orthodox not as you claim protestants. They have accepted monastic life and were monks. Even they converted those who belief in two nature of Christ one united nature of Christ.

  ReplyDelete
 10. Good Job Aba Selama! Stubborns and victims of MK are running nuts . The true Tewahiodo is shining now. I praise God for discovering this blog.It has cleared some of the man made confussions from the Tewhido. As for MK they are very close to insert Daniel Kibret's in the bible. Would love Dr. Getachew, Proffessor Mesfin and others like them write on this blog.

  ReplyDelete

 11. To:- yeኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲና ካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል

  Bravo! Work hard! You are the hope that Christianity and civilization may flourish in this country once again. Bravo the Ethiopian Catholic church! Go forward.

  Rescue the Christianity of this country from the hands of nationalists and extremist reformists. The Blessed John Paul II said, "Faith and reason are like two wings on which the human spirit rises to contemplation of truth; and God has placed in the human heart a desire to know the truth". Because of our former ecclesiastical rulers, the Copts, Ethiopian Christianity has been cut off from the rest of the world. The Egyptians had been filling us with distorted information. Thanks to 20th century technological advancement and all the ecumenical movements, now, any person who searches for the truth easily finds out that we have the same faith and the same sacraments. Despite historical prejudices, stereotypes and misunderstandings, throughout history, the Ethiopian church- both in faith and sacraments- has remained part of the One Catholic Apostolic Church of Christ which the Apostles served in. It is amazing to see how the Lord preserved our Orthodox faith and Catholic church, despite our stereotypes that we have been holding against each other. May His name be praised!

  This country needs the revival of the Catholic (universal) spirit of Christianity so that Christianity may be relieved from the burden of the national flag and the disgusting mingling of national politics with the faith as well as from the sectarianism of the so called "protestant" movements.

  God bless you! God bless you! Go forward! May the Lord be with you.

  May the Holy Mother pray for you to revitalize Christianity in Ethiopia from its fossilized state.

  We are One!

  ReplyDelete
 12. The discussion really sparks enlightenments. Ain't wrong with our Tewhido Haimanot, but it has suffered substantial set back from the man made gedels. Some of the writings in Tamere Mariam needs serious visitation. This is just my view. I am neither "MaQue nor Thadesso" but a simple Tewhido Orthodoxian.

  ReplyDelete
 13. አንዳንድ ትምህርት የገባቸው አስተማሪዎች ካፍ የሚወጣው እንጂ ወደ አፍ የሚገባው ሰውን አያረክሰውም እያሉ ማብራሪያ ሲሰጡ ተቀብሎ ማሰላሰል ሲገባ አንዳንድ ቀላማጆች(የወንድሞች ከሳሽ የተነፈሰባቸው) ይኽ ዕኮ መናፍቅ ነው የተናገረውን ሰሙ በማለት በመገናኛ ብዙኃን ወንድሞቻቸውን ለማሳጣት እንደ ኤልዛቤል አንገታቸውን እያሰገጉ በየመስኮቱ ብቅ ይላሉ። ይህ አለመማራቸውን እና ቀላማጅነታቸውን እንጂ የውነተኛውን አስተማሪ መናፍቅነት አያመላክትም ከምእመናን ፊት ቀርቦ ቃለ ወንጌል በማስተማር ፈንታ በተፈጥሮ ወንድሙን ካሃዲ መናፍቅ ማለት ይሉኝታ ከማጣት ባሻገር
  ትዝብት ላይ ይጥላል ከመድረክ ላይ እንደቆመ አንት ምንድነህ ቢሉት አይን ፍጥጥ እንጂ
  መልስ የለውም በመሆኑም ሰባክያን ነን የምትሉ ሁሉ አማኞች እንዳይታዘቧችሁ ሌላውን ከመንቀፍ
  ራሳችሁን ከመደገፍ ብትመለሱ ንሥሓ ነው (እስመ ኩሉ ዘአልዐለ ርእሶ የኀሥር)ራስ ወዳጅ ወንድም አዋራጅ አወዳደቁ አያምርም ይላልና ሰሚዎቹም ሊጠነቀቁ ይገባል።

  ReplyDelete
 14. አሁንም ዋናው ጉዳይ ጨርሶ እንዳይረሳ ፍሬ ነገሩን ባጭሩ ለማስታወስ በአሥራ አምስተኛው ምዕተ-ዓመት አባ እስጢፋኖስ የሚባሉ መነኩሴ ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም ለምንም መስገድ ተገቢ አይደለም የሚል እምነት ይዘው ተነሡና ብዙ አባሎችን አፈሩ፤ ይህ የሆነው በአውሮፓም ገና ሉተር የሚባለው የፕሮቴስታንተት መሪ ከመነሣቱ ከሠላሳ ዓመት ግድም ቀድሞ ነው፤ ከተለመደው የተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ልማድ በመውጣቱ ደቂቀ እስጢፋኖስ በሚባሉት የአባ እስጢፋኖስና ተከታዮች የደረሰባቸውን መከራና ስቃይ የሚገልጸውን ገድላቸውን ዶር. ጌታቸው ኃይሌ ከግዕዝ ወደአማርኛ ተርጉሞ በአሜሪካ አሳትሞት ነበር፤ አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ኒቨርሲቲ አማካይነት አሳትሞታል፤ የስብሰባው ዋና ርዕስ በዚህ መጽሓፍ የተገለጸው የደቂቀ እስጢፋኖስ አበሳና መከራ፣ ሞት ነበር፤ በዕለቱ ከተናገርሁት ውስጥ የሚከተለውን ብያለሁ፤–

  ‹‹እነዚያ ሟቾችና ገዳዮች ለኛ ዛሬ ለምንኖረው ምን የሚያዛልቀን ትምህርት አስተምረውናል? የአቅመ-ቢሶቹ የደቂቀ እስጢፋኖስ ስቃይና ሞት ያስተማረን ነገር አለ? የጉልበተኞቹ ማሰር፣ ማሰር ሲሰለቻቸው ምላስና አፍንጫ መቁረጥ፣ ምላስና አፍንጫ መቁረጥ ሲሰለቻቸው እግርና እጅ መቁረጥ፣ እግርና እጅ መቁረጥ ሲሰለቻቸው መግረፍ፣ መግረፍ ሲሰለቻቸው መግደል አስተምሮናል? ይህ ትምህርት የዛሬ ስድስት መቶ ዓመት ግድም ከነበረው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የተሻልን ሰዎች፣ የተሻልን ኢትዮጵያውያን አድርጎናል? ከታሪካችን ብንማር ነው በአሥራ ስድስተኛው ምዕተ ዓመት ደግሞ በክርስቲያንና በእስላም መሀከል አሥራ አምስት ዓመታት ያህል የፈጀ መተላለቅ የተደረገው? በአሥራ ሰባተኛው ምዕተ-ዓመትስ በካቶሊኮችና በኦርቶዶክሶች መሀከል የተፈጸመውስ ግፍና ስቃይ? ለዛሬውስ የኑሮ ሥርዓታችን ምርኩዝ የሚሆነን ከታሪካችን የተማርነው ነገር አለ?http://mesfinwoldemariam.wordpress.com/page/11/

  ReplyDelete