Wednesday, June 12, 2013

አዲሱ የዶክተር አባ ገ/ሥላሴ ጥበቡ መጽሐፍ፦ ሲኖዶሳዊ ጉዞ በኦርቶዶክሳዊ ቀኖና ሲመዘን

 
(ከክንፈ ገብርኤል - ሲያትል)

«ሲኖዶሳዊ ጉዞ በኦርቶዶክሳዊ ቀኖና ሲመዘን» በሚል ርእስ በ2013 ዓ.ም ታትሞ ለንባብ የበቃው የዶክተር አባ ገ/ ሥላሴ መጽሐፍ በቅርቡ በተካሄደው የውጭው ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ከአንዳንድ የሲኖዶሱ አባላት ተቃውሞ እንደደረሰበት፤ መጽሐፉንም ለማገድ ኮሚቴ እንደተቋቋመ እንዲሁም በከተማችን ያሉ ጳጳስ መጽሐፉ እንደተወገዘ አድርገው እንደተናገሩ  ከአንድ ወዳጄ ሰማሁና ለማንበብ ወሰንኩ። ብዙ ጊዜ ተቃውሞ የሚገጥመው ነገር ቁም ነገር እንዳለው ስለሚሰማኝ ትኩረቴን ይስበዋል።እውነትም ቁም ነገር አገኘሁበትና  ለአንባቢያን ለማካፈል ወሰንኩ።
  
ጸሐፊው አንዳንድ የቤ/ክርስቲያን አስተዳደራዊ የስሕተት መንገዶች የሚሏቸውን አካሄዶች አጋልጠዋል። የጥንት ኦርቶዶክሳውያን አባቶች በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ይመሩበት የነበረውን የቤተ ክርስቲያን መመሪያ አጭርና ግልጽ በሆነ መንገድ ግልጥልጥ አድርገው አቅርበውታል። ከጊዜ በኋላ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የፖለቲከኞች መንጠላጠያ መድረክ መሆኗንና የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ከነገሥታት ጋር በመቀማጠል ክብሯን አሳልፈው መስጠታቸውን፤ የክርስቶስን ተልእኮ ወደ ኋላ ትተው የነገሥታቱን ተልእኮ ማገልገል መጀመራቸውን የገለጡ ሲሆን፣ ዛሬ ላይ የሚገኙ ጳጳሳትም ከጥንቱ በባሰ ሁኔታ ያለ ይሉኝታ ከፖለቲከኞች ጉያ ሄደው መለጠፋቸውን አጥብቀው ኮንነዋል። የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የሁሉም መጠለያ ከአድልዎ እና ከምድራዊ ሥርዓት ነጻ ሆና ሁሉንም በእኩልነት ማገልገል እንደሆነ ትኩረት ሰጥተው ያብራራሉ። ሁሉንም በየቦታው ማስኬድ ሲገባ ፖለቲካን እና ሃይማኖትን መደበላለቅ ጤና የሚሰጥ እንዳልሆነም ያስረዳሉ።
 
 ሦስቱን የቤተ ክርስቲያን የሥልጣን (የክህነት)ማዓርጋት ማለትም የጵጵስናን፣ የቅስናን እና የዲቁናን አላማቸውን አሰጣጣቸውን እና አገልግሎታቸውን በተገቢው መንገድ አብራርተውታል። ዛሬ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ለበላይ አካል አለመታዘዝ ሥርዓተ አልበኝነት ነግሦ የሚታየው፣ ሦስቱን የቤተ ክርስቲያን መዓርጋት አለመረዳት ሲሆን የመዓርጋቱ ክብርም እጅግ ተዋርዶ እንደሚታይ ይጠቁማሉ። ሦስቱ የክህነት መዓርጋት የቤተ ክርስቲያንን ሰላም አንድነት ለመጠበቅ በጌታና በሐዋርያቱ የተሠሩ ሥራቶች መሆናቸውንም አክለው ይናገራሉ። ጸሐፊው ይህንን እውነት ከተቀበረበት ቆፍረው በማውጣት በጥናት መልክ አቅርበዋል።  አባ ገብረ ስላሴ እንደገለጡት ክህነት ለኃላፊነት ለሚበቃ ሰው የሚሰጥ ትልቅ ሸክም ነው። ክህነት ማንም የፈለገ ሁሉ የሚከፋፈለው የዘኬ ቤት ዳቦ አይደለም። መጽሐፉን አስተውሎ ላነበበው ሰው ብዙ ጉዳችንን የሚያጋልጥ ነው።  

እውነት ነው፦ ዲቁና፥ ቅስና፥ ጵጵስና የሚሰጠው የሃይማኖትን ምሥጢር ላወቀ፣ በአእምሮው ለበሰለ፤ አንድ ሴት ብቻ ላገባና ልጆቹን በሥርዓት የሚያሳድግ፤ ኑሮው በመልካም ለተመሰከረለት ነበር ድሮ። 1ጢሞ 3፥1-35፤ ፍትሐ ነገሥቱም ያላገባ እና እድሜው ከ25 ዓመት በታች ለሆነ ዲቁና እንዳይሰጥ ይከለክላል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግን ገና ተወልዶ ከጀርባ ሳይወርድ ዲቁና ይሰጠዋል። ከዚያም ምንም ሃይማኖታዊ እውቀት ሳይኖረው የቅዳሴ ተስጥኦ ስለጮኸ ብቻ ቅስና ይሰጠዋል። እናም የሃይማኖት አባት ተብሎ በሰው ትከሻ ላይ ይወድቃል። ዛሬ ዛሬማ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሁሉ እንደ ሁለተኛ ዲግሪ በርቀት የሚስወዱት ተራ ሰርተፊኬት ሆኗል። አንዳድ ጳጳሳትም ለልጆቻቸው ክህነት በመስጠት ከባለ ሀብቶች ጋር የሚወዳጁበት እጅ መንሻ ሆኗል። ቤተ ክርስቲያን በክህነት አሰጣጥ ላይ ተሐድሶ ወይንም ለውጥ ማድረግ እንደሚገባትና ወደ ጥንቱ ስርዓት መመለስ እንዳለባት እንድናስተውል ያደርገናል ብዬ አስባለሁ።

መጽሐፉ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው አገር ባለው ሲኖዶስ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ጥሩ ያልሆኑ አሰራሮችን ይተቻል። ጸሐፊው መጠጊያ የማመቻቸት ጉዳይ ሳይሆን የእውነት እና የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያስጨነቃቸው ይመስላሉ።

በአገር ውስጥ ያለው ሲንዶስ በጥንታዊው ቀኖና ሲመዘን አፍራሽና ሕገ ወጥ እንደሆነ ለማሳመን ይሞክራሉ።  ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን ከመጽሐፋቸው ላይ ቀንጭቤ አቅርቤአለሁ።

«ቤተ ክርስቲያንን ለስደት የዳረጋት ፓትርያርክ እያለ ሌላ ፓትርያርክ እንዲሾም ያደረገው የወያኔ መንግሥት ፖለቲካ ነው። ፖለቲካ የወያኔ ኢሕአዴግን መንግሥት የተጠጉትንም እንኳ የወሰኑትን ውሳኔ በሥራ ላይ እንዳያውሉት እያስቸገረ ሲሆን ያለ መንግሥት ፈቃድ ውሳኔያቸውን በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ነጻነት የላቸውም። ይህ ሊስተባበል የማይችል ሐቅ ነው። በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ መድረክ በሕግ የታወቁ ተቃዋሚና ተወዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅቶችን በነጻ ለማሳተፍ የማይሻ መንግሥት መሆኑ በገሀድ ታውቋል። ሁኔታው ይህ ከሆነ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የመብት ጥሰት የተካሄደው በመንግሥት አስተባባሪነት ነው የሚለውን ክስ የሚያስተባብል ማንም የለም። አፈጻጸሙም ሲታይ  መንግሥት ከሚፈቅደው ውጭ ሲኖዶሱ በራሱ ፈቃድ መሥራትም መንቀሳቀስም አይችልም። እንግዳውስ ቀኖናውን የጣሰውም ያስጣሰውም መንግሥት ነውና ይህን ችግር ለመፍታት እና የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናዊ መብት ለማስከበር የመንግሥት ፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የሌለበት ፍጹም ነጻነት ያስፈልጋል»  ገጽ 163

የውጭውን ሲኖዶስ በተቹበት አንቀጽ ደግሞ፦  

«የእኛን ልዩ የሚያደርገው ከሦስቱም ቡድኖች ውስጥ የግል ባሕርያቸውን እንደ ሕግ የሚጠቀሙ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን እንመራለን ብለው ግራ ማጋባታቸው ነው። ባሉበት የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ እንኳ ኅብረት የሌላቸው ሰዎች የማያምኑበትን መንፈሳዊ ተቋም መምራት እንዴት ይችላሉ? የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ችግር ከሌሎቹ ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ቀጥሎ የተመለከቱት ይገኙበታል።» ካሉ በኋላ «አንደኛ ፖለቲከኞች ቤተ ክርስቲያንን ለሕዝብ መሰብሰቢያ ጥቅም ይፈልጓታል። በአንጻሩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ቀኖናዊ ሕግ እንዳትመራ በአመክንዮ ላይ የተመሠረተ አጀንዳም እንዳታራምድ ቀፍድዶ በመያዝ በተለያየ መንገድ ይቃወሟታል። ለዚህም ቀደም ሲል የነበረውን ማኅበረ ቤተ ክርስቲያን ዘተዋሕዶና የአሁኑን የሲኖዶስ ድጋፍ ሰጭ ኮሚቴ ብለው ራሳቸውን የሰየሙት ግለሰቦች መመልከት በቂ ነው። አባቶች እኒህን ዓይነት ግለሰቦች ይዘው የሚያደርጉትን ተግባር በማስተዋል ለተመለከተው አዲስ አበባዎቹ በወታደር ኃይል ይብለጧቸው እንጂ በሌላው ተግባራቸው ግን አይተናነሱም።» በማለት የሚያውቁትን እውነት ይተነትናሉ።

«ክህነታዊ አገልግሎትን ለቶፈኝነት አሳልፎ በመስጠትም የተወሰኑ ስደተኛ አባቶችንም የሚበልጣቸው አልተገኘም። አንዳድ የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ ኃላፊዎች በየሄዱበት ቀኖናዊ ሕግን ከሚከተሉ ይልቅ የኃይል ሚዛንን ይመለከታሉ --- ጳጳስ እንኳን የቤተ ክርስቲያን ራስ እግርም መሆን አይችልም ከማለታቸውም በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራስ ቦርድና የቦርድ ሊቀ መንበር ነው በማለት የሚመልሱት መልስ ለቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቁሜያለሁ ማለታቸውን በገሀድ መሻራቸውን ያሳያል። በአንጻሩ ለቤተ ክርስቲያን እድገትና አንድነት አብረዋቸው ከሚሠሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይልቅ የንግድና የግል ፖለቲካ አራማጅ ብልጣ ብልጦች ሐሳብ ይበልጥብኛል ብለው ትናንት ሲያወግዙት የነበረውን ዓላማ ሰዎቹ ስለተለዋወጡ ብቻ ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለግለሰቦች ስሜት ሥልጣናቸውን አሳልፈው ሲሰጡ ማየት በትዝብት ጉዳዩን ከመመልከት ውጭ ሌላ ሊባል የሚችል ነገር የለም----» በማለት በውጭውም ሲኖዶስ የተበላሹ አሰራሮች እንዳሉ ይጠቁማሉ።

ባጠቃላይ መጽሐፉ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለሚገደው ሁሉ እጅግ ጠቃሚ የመወያያ ሀሳቦችን ይዞ ይገኛልና አንባብያን ገዝተው እንዲያነቡ እጋብዛለሁ።  አንዳንድ አባቶች እንደተቃወሙት ሰማሁ እንጂ ምክንያታቸው ግን ምን እንደሆነ የደረሰኝ መረጃ አልነበረም።  ምናልባት ከላይ ቀንጭቤ ያቀረብዃቸው የመጽሐፉ ትችቶች አንዳንድ ሰዎችን አስቀይሞ ሊሆን እንደሚችል ገምቻለሁ። ታዲያ መጽሐፉን ለማገድ መሞከርን ምን አመጣው?  

15 comments:

 1. ወንጌል ከዚህ አለም ልክስክስ ፖለቲካ በላይ የከበረ እንደሆነ ለሃገራችን ፖለቲከኞች ማን በነገራቼው!

  ReplyDelete
 2. ሐዋርያው ጳውሎስ በወንጌል አላፍርም አለ፡፡ አንድ አይሁዳዊ ሰው በሮም ለሚኖሩ የዘመኑ ስልጡኖች መልእክት ሲልክ አቅምን አለማወቅ ይመስላል፡፡ መልእክቱ ግን የዘላለሙ ጌታ የክርስቶስ ነው፡፡ ከአንዲት ገጠራማ የኢየሩሳሌም መንደር በወቅቱ ገናና ወደ ነበረች ወደ ሮም ከተማ ደብዳቤ መጻፍ የሚያሳፍር ይመስላል፡፡ መልእክቱ ግን ሰማያዊ ነው፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ በወንጌል አላፈረም፡፡ ወንጌል ዘመን የማይሽረው፣ ሥልጣኔ የማይቀይረው የእግዚአብሔር ብሥራት ነው፡፡ ወንጌል ለሁሉም ሰው የሚሆን የምሥራች ነው፡፡ ወንጌል የማያስፈልገው ትልቅ ሰው የለም፡፡ ያለ ወንጌልም ትልቅነት አይኖርም፡፡

  በዚህ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ዘመን፣ በዚህ የፍልስፍናና የሥነ ልቡና ዘመን፣ በዚህ ስለ ግዙፋዊ ኃይል በሚወራበት የኒውክለር ዘመን፣ በዚህ በተራቀቀና በመጠቀ ሰዎችን ጨረቃን በረገጡበት ዘመን፣ በዚህ የሰው የአስተሳሰብ ችሎታ ተመነደገ ተብሎ በተወደሰበት ዘመን፣ ወንጌል ሞኝነት፣ በአደባባይ ሊያቀርቧት የምታሳፍር ትመስል ይሆናል፡፡ ስለ ማቴሪያሊዝም በሚሰበክበት ዘመን ወንጌል ተጨባጭ አትመስልም፡፡ ስለ ዘመናዊነት በሚወራበት ዘመን ወንጌል ጊዜ ያለፈባት የሞኞች መጽናኛ ትመስላለች፡፡ ዓለም ስለ ካፒታሊዝም በሚወራበት ዘመን በበረት በፍጹም ድህነት ስለ ተወለደው ጌታ መናገር ሞኝነት ይመስላል፡፡ በዚህ የኃይል ዘመን መስቀል ተሸክሞ ስለ ሞተው ኢየሱስ መናገር ያሸማቅቀን ይሆናል፡፡ የዓለም ጥበብ ሁሉ እየከሰረ ሲመጣ ወንጌል ግን እያበበ ይመጣል፡፡ ወንጌል ብቻውን ደረቅ ነው ብለን በፍልስፍናና በዘመናዊነት ቅብ ብንቀባው ደረቅ የሆነው እውነት ብቻ ያድናል፡፡ ሐሰት ምንም ቢዋብ ነፍስን አያረካትም፡፡ ዘመናዊነትም ወረት ስለሆነ ደስታው አይቆይም፡፡ “ክረምትና እመጫት ሲጠሉት ያጠግባል” እንዳሉ እንደ ክረምት አብቃይዋ፣ እንደ እመጫት ወላዷ ወንጌል ሲጠሏት ታጠግባለች፡፡

  አንድ አረጋዊ ወንጌልን አወቁ፣ መሰከሩ፣ ሰው ሁሉ አበዱ አላቸው፡፡ እርሳቸው ግን በጀርባቸው ላይ፡- “የኢየሱስ ሞኝ ነኝ” ብለው በመጻፍ ከተማ ለከተማ መዞር ጀመሩ፡፡ አዎ የኢየሱስ ሞኝ መሆን ይሻላል፡፡ እግዚአብሔር የለም ብለው የለፈፉ ዛሬ የሉም፡፡ እግዚአብሔር ሞቷል ያሉ እነ ኒቼ እነርሱ ሞቱ፡፡ በልዕልናቸው ተመክተው ክደው ያስካዱ እነ ሶቭየት ኅብረት ዛሬ ተበትነዋል፡፡ እግዚአብሔር የለም ብለው የሰበኩ ካድሬዎች ዛሬ ቆራቢና ሰባኪ ሆነዋል፡፡ ሞኝነት የመሰለው ወንጌል ግን ዛሬም አለ፣ ወደፊትም ይኖራል፡ ታላቁ ሞኝነት!!

  ReplyDelete
 3. - ታላቁ ሞኝነት ደግሞ ይህ የወንጌል ክብር ከአስተዋዮችን ጥበበኖች መሰወሩ ነው- ታላቁ ጥበብ ደግሞ ለአላዋቂዎችን ምናምንቴዎች መገለጡ ነው ሉቃ 10፣21-24 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና።ሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን
  ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ
  ሆኖአልና።ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ
  ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ። ወደ ደቀ መዛሙርቱም ዘወር ብሎ
  ለብቻቸው። የምታዩትን የሚያዩ ዓይኖች ብፁዓን ናቸው። እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት
  ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ»።

  ReplyDelete
 4. ሂስና ምክር አስፈላጊዎች ናቸውና የተደከመበት ሊነበብ ይገባል።

  ReplyDelete
 5. I have not seen the book, but from the title of your article what turned me off right away is the distortion on his title "Dr. Abba". The book cover has his name as "Abba Gebre Selassie Tibebu" and then in parenthesis "Mamre & Drm Candidate". If he is a candidate he has not earned it yet. Why do abesha people like to give titles that they have not officially earned? That is called lying and deceiving.

  ReplyDelete
 6. መጽሐፉ ለጊዜው በገምጋሚ ኮሚቴው ታይቶ አስፈላጊው እስኪወሰን ድረስ በሲኖዶሱ ሥር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይሸጥ በጉባኤው ተወስኗል። የቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅም ይህንን ውሳኔ ለአብያተ ክርስቲያናቱና ለጸሐፊ ለአባ ገብረሥላሴ እንዲጽፉ ተነግሮአቸዋል። የመጻፍም ሆነ የመናገር ነጻነት ባለበት በምድረ አሜሪካ ይህ ውሳኔ መወሰኑ እኔ በጣም ከብዶኛል። ወደፊት ለየት ያለ አስተሳሰብ የሚገኝበትን መንገድ ያጣብባል። ጸሐፊዎች የተሰማቸውንና ይጠቅማል ያሉትን እንዲጽፉ ሊበረታቱ ይገባል። ያንን የሚቃወም ካለ ደግሞ እንዲሁ መጻፍ ይኖርበታል ብየ አምናለሁ። አሁን ግን ይህ ቅዱስ ሲኖዶስ በጉባኤው የወሰነው ነገር እንዴት ነው የሚሆነው?

  ReplyDelete
 7. Is it possible to get the book? Thank you.

  ReplyDelete
 8. endete yarge ngre xYEtadseme YEbalal enkon haymanot yesewe ergena yetadesal

  ReplyDelete
 9. የሚገርመው ባለፈው ሲኖዶሱ ሲሰበሰብ ይህ መፅሐፍ እንዲገመገም በሊቃውንት ጉባዔ እንዲታይ ታዘዘ እንጅ ሰውየው ይህንን በመጻፋቸው አልተወገዙም፦ እረ እባካችሁ ይሄ ውግዘት የሚባለው ነገር በቃ ዝም ብሎ ቀላል ነው ማለት ነው????? ለማንኛውም የሲያትሉ ጳጳስ ዝም ብለው በሲኖዶስ ያልተባለውን ከሚለፈልፉ የራሳቸውን ቆሻሻ አስተዳደር ቢያስተካክሉ ይመረጣል። መድሐኔዓለም ክርስቶስ ልቦና ይስጣቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabhare yistelegne ewnetegna sewe newot ene begubaew lay nebrkugne

   Delete
  2. Egziabhare yistelegne ewnetegna sewe newot ene begubaew lay nebrkugne

   Delete
 10. Metazeze ka senefe mesewate yebeletale!!! Keriseteyane ka hege belaye new yetem yehune yetem la betekeriseteyane abatuch betazeze

  ReplyDelete
 11. http://qirchat.blogspot.com/

  ReplyDelete
 12. why is this people act like they are a good monk?
  http://qirchat.blogspot.com/2013/06/blog-post_15.html?showComment=1371321761180#c2296196387189991692

  ReplyDelete
 13. Seriously, Why do you call this person a doctor when he himself declares that he is a doctoral candidate. If you do not know what a candidate means, it may mean that he was/is enrolled in a doctorate program and passed a comprehensive exam. Please do not distort facts. I know he is capable of becoming one, but let's refrain from using that name for people who have not earned it yet, including honorary doctorate recipients. It is only in Ethiopia that we are using names like Engineer and doctor for honorary degree recipients, and so on....

  ReplyDelete