Thursday, June 13, 2013

በሙስና ላይ የተከፈተው ዘመቻ ተሐድሶን በማንቀሳቀስ ማቅን በማስታገስ ስብከተ ወንጌልን በማጠናከር ቢጀመር

ላይፍ መጽሔት በግንቦት 2005 ዓ.ም እትሙ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ ወዲህ  በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በተለይም ሙስናን በተመለከተ ለውጥ ለማምጣት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን  ዘግቧል፡፡ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ መጽሄቱ እንደዘገበው ፓትርያርኩ በእጅ መንሻነት የተበረከተላቸውን የወርቅ መስቀል እንዲመለስ ማድረጋቸው ይጠቀሳል ብሏል፡፡ “አቡኑን እንኳን ደስ ያለዎት በማለት ታማኝነታቸውን ለማሳየት የተወሰኑ የቤተክርስቲያንና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ገንዘብ በማዋጣት የወርቅ መስቀሉን በመግዛት ወደ ፓትርያርኩ ይመጣሉ፡፡ መስቀሉ በአስተዳዳሪዎቹ ደሞዝ እንደማይሸፈን የጠረጠሩት ፓትርያርኩ ለመሆኑ ይህንን መስቀል የገዛችሁበት ገንዘብ ከየት ተገኘ በማለት ይጠይቃሉ፡፡ መልሱ ቀላልና ግልጽ ነበር፡፡ አስታዳዳሪዎቹ እጅ መንሻ ለማቅረብ የሚያስተዳድሩትን ቤተክርስቲያን ካዝና ገልብጠዋል፡፡ ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለ ነገር የተለመደ በመሆኑ አስተዳዳሪዎቹ በአሁኑ ፓትርያርክ አቋም ተደንቀዋል፡፡ አቡኑ እንዲህ ዓይነት ነገር ማንም እንዳያደርግ በማስጠንቀቅ መስቀሉ ለቤተክርስቲያን ገቢ እንዲደረግ አዘዋል፡፡” (ላይፍ ገጽ 21)፡፡

በእርግጥ እንደተባለው ፓትርያርኩ የወሰዱት እርምጃ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሙስና ግንባር ላይ የተሰለፉትን የደብር አስተዳዳሪዎችን ፊት ለፊት በማሳፈር ድርጊታቸውን መኮነናቸውና እንዲህ ዓይነት ስራ ደግመው እንዳይሰሩ ማስጠንቀቃቸው ትልቅ ተግባራዊ ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ አጓጉል ልማዶችን ማፍረስ እንደሚቻል የፓትርያርኩ እርምጃ ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡ ስለዚህ በልማድ የሚሰራባቸውን በርካታ አጓጉል ልማዶችንና አሰራሮችን ይዞ ከመቀጠል ይልቅ በሚያሳምን መንገድ ማፍረስና ቤተክርስቲያንን በወንጌል እውነት ማደስ ይቻላል፡፡
  
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል ሲባል እንደዚህ ያሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶችና ልምምዶችን ልታስተካክል ይገባታል ማለት ነው እንጂ ሌላ ሀሳብ የለውም፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም በሙስና ላይ እየወሰዱ ያለው የማስተካከያ እርምጃ ስሙ ተሐድሶ ነው፡፡ ተሐድሶ እንዳይባል ግን ማቅ ይህን የከበረና ቤተክርስቲያን ስትጠራውና ስትሰራበት የነበረውን ስም መናፍቃን የሚል ዘርፍ አበጅቶለትና “ተሐድሶ-መናፍቃን”፣ “ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ” ወዘተ እያለ ቀንድና ጭራ ካበቀለለት በኋላ ተሐድሶ ተጠላ ሌላ አላማ ያለው ተደርጎም ተወሰደ፡፡

ቅዱስነታቸው ባለፈው ለትንሣኤ በዓል እስመ ሐደሰ ለነ ፍኖተ ጽድቅ ወሕይወት ንቅረብ እንከ በልበ ጽድቅ” የሕይወትና የእውነት መንገድን አድሶልናልና ከእንግዲህ በቅን ልቡና ወደ እርሱ እንቅረብ” (ዕብ. 10፡19) በሚል መሪ ጥቅስ ባስተላለፉት ቃለ ቡራኬ “ያረጀው ነገር ሁሉ በክርስቶስ ደም ተቀድሶና ነጽቶ ሐዲስ ሆኖአል፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሠርቶ የሚያሠራ የመልካም ነገር ሁሉ አርአያና መሪ እንደመሆኑ መጠን አዲሱን መንገድ ከፍቶ እንድንጓዝ ሲያደርግ እኛም በሐዲስ መንፈስ በሐዲስ ሕይወት ልንመላለስበት እንጂ እንደገና ወደአረጀውና ወደአፈጀው ሕይወት ተመልሰን ልንዘፈቅ አይደለም፡፡ አዲስ ሕይወት ማለት እግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ መድኃኒት እንዲኾን በላከው በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ድኅነትን ማግኘት ነው፤ ምንም ዐይነት አማራጭ የማይገኝለትን ይህን የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ የሰው ዘር ሁሉ ተቀዳሚ ሥራው አድርጎ ሊቀበለው ይገባል፤ በዚህ በኩል ካልሆነ ሌላ የምንድንበት መንገድ የምናመልጥበት ዐውድ ፈጽሞ የለምና፡፡” ማለታቸው ይታወሳል፡፡
አክለውም የሚያድነው እምነት በሥራ የሚገለጽ መሆኑን ሲያስረዱ “በቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ እንደተቀመጠው የክርስትና ሃይማኖት በመልካም ሥነ ምግባር ገዝፎ የሚታይ ሃይማኖት እንጂ በእምነት ብቻ ተደብቆ የሚኖርበት ሃይማኖት አይደለም፤ በርቀት ያለችው ነፍሳችን በግዙፉ ሥጋ ሆና በምትሠራው ሥራ አማካይነት በአካላችን ውስጥ እንዳለች እንደምናውቅ ሁሉ አንድ ክርስቲያንም መልካም ሥራን አብዝቶ ሲሠራ በሥራ ገላጭነት ሃይማኖቱ ገዝፎ በጉልሕ ይታያል፡፡ በመሆኑም በክርስትና ሕይወት ሃይማኖትና ሥነ ምግባር እንደ ነፍስና ሥጋ ተዋሕደው በአንድነት ሲኖሩ ሕይወተ ነፍስን እንደሚያጎናጽፉ ልብ ብሎ ማስተዋል ይገባል፡፡” ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ሙስናን ለማጥፋት የፀረ ሙስና አቢይ ኮሚቴ ማቋቋም ብቻውን የቤተክርስቲያኗን የሙስና ችግር አይፈታም፡፡ ዘራፊዎቹ ሌላ የዝርፊያ መንገድ ያበጃሉና፡፡ የቤተክርስቲያኗ መሰረታዊ ችግር ሙስና አይደለም፡፡ ችግሯ መንፈሳዊ ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወደ ሰው ልማድና ወግ መዞሯ፡፡ ሙስና የዚህ መሰረታዊ ችግሯ መገለጫ እንጂ መሠረታዊ ችግሯ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ተሐድሶው ከመሰረታዊ ችግሯ ሊጀመር ይገባል፡፡ ይኸውም ከላይ በተጠቀሰው የቅዱስነታቸው ቃለ ቡራኬ ውስጥ የተላለፈው የወንጌል መልእክት ለተከታዮቿ ሁሉ በግልጥነት ሊሰበክላቸው ይገባል እንዲህ ተብሎ “አዲስ ሕይወት ማለት እግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ መድኃኒት እንዲሆን በላከው በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ድኅነትን ማግኘት ነው፤ ምንም ዐይነት አማራጭ የማይገኝለትን ይህን የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ የሰው ዘር ሁሉ ተቀዳሚ ሥራው አድርጎ ሊቀበለው ይገባል፤ በዚህ በኩል ካልሆነ ሌላ የምንድንበት መንገድ የምናመልጥበት ዐውድ ፈጽሞ የለምና፡፡” ቤተክርስቲያኗ በዚህ ረገድ መሠረታዊ ችግሯን መፍታት ብትችል ሙስና ብቻ ሳይሆን ሌሎቹም ችግሮች ሁሉ ሊቀረፉና ስሟንና ግብሯን ልታድስ ትችላለች፡፡ ስለዚህ መድኃኒቷ ወንጌል ነው፡፡ በወንጌል ስም ሌላ ሌላውን ሳይሆን የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ ልትሰብክ ይገባታል፡፡   

ፓትርያርኩ በቅርቡ ከዜና ቤተክርስቲያን መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቤተክርስቲያን ትልቅ ትኩረት ልትሰጥ የሚገባትና ትልቅን በጀት መመደብ ያለባት ለስብከተ ወንጌል መሆኑን መናገራቸው ትልቅ ነገር ነው፡፡ ጥያቄና መልሱ እነሆ
ዜና ቤተክርስቲያን “ከቤተ ክርስቲያናችን ቁልፍ ስራዎች አንዱ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴው የሚፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ይህን የቤተ ክርስቲያኗን ቀዳሚ ሥራ የሆነውን ተልእኮ ለማጠናከር ቤተክርስቲያኒቱ ምን ማድረግ አለባት?”
ቅዱስ ፓትርያርክ “እንደ እኔ እምነት ትልቁን በጀት መመደብ ያለባት ለስብከተ ወንጌል ሥራ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ቤተክርስቲያናችን ከሁሉም አኃት አብያተ ክርስቲያናት የበለጠ ተከታይ ምእመናን አሏት፡፡ በቅድሚያ ያሉንን ምእመናን በእምነታቸው በእውቀታቸው እንዲጠነክሩ ማስተማር ያስፈልጋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ያላመኑትን ለማስተማር ወጣቱን ትውልድ በሚገባ ለመያዝ የተጠናከረ የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ያስፈልጋል፡፡ ይህን ወደተግባር ለመለወጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ትልቅ ሃላፊነት አለበት፡፡ በአጠቃላይ ስብከተ ወንጌል መምሪያው በሰለጠነ የሠው ሀይልና በበጀት ሊጠናከር ይገባዋል፡፡” (ዜና ቤተክርስቲያን ገጽ 9)፡፡

እውነት ነው የተባሉት ነገሮች ሁሉ ያስፈልጋሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ትልቁን በጀት መመደብ ያለባት ለስብከተ ወንጌል ነው፡፡ በጀት መመደብ ብቻውን ግን ምንም አይፈይድም፡፡ በዋናነት ቤተክርስቲያን ብዙ ዋጋ ከፍላ ያስተማረቻቸው የመንፈሳውያን ኮሌጆች ደቀ መዛሙርት እየተማሩ ወደሌሎች ተቋማት መፍለሳቸው ስብከተ ወንጌልን ያዳክመዋል፡፡ የሚፈልሱት ለምንድነው? ተብሎም መጠየቅ አለበት፡፡ አንዱ ጥያቄ በቂ ደመወዝ ስለማያገኙና በነጻነት እንዳያገለግሉ ዋስትና ስለማይሰጣቸው ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ አለቦታው እየገባ ልፈትፍት የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ መናፍቃን እያለ ስማቸውን ስለሚያጠፋው አላሰራ ስለሚላቸውና በልዩ ልዩ መንገድ ጫና እየፈጠረ ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ዛሬ በየደብሩ ተሐድሶ ናቸው እያለ በልዩ ልዩ ዘዴ እየሰለላቸው እየከሰሳቸውና እያስባረራቸው ያሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ እነዚህ ጉዳዮች እልባት ባላገኙበት ሁኔታ ስብከተ ወንጌል ሊስፋፋ አይችልም፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ለእነዚህ ጉዳዮች መፍትሄ መስጠት አለባት፡፡

መናገር ከሚቻለው በላይ ቤተክርስቲያኗ በሙስናዊ አሰራር ተተብትባለች፡፡ ጉዳዩ መንፈሳዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል፡፡ ከምንም በላይ ግን መድኃኒቱ ወንጌልና ወንጌል ብቻ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው አዲስ ሕይወት ማለት እግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ መድኃኒት እንዲሆን በላከው በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ድኅነትን ማግኘት ነው፤ ምንም ዐይነት አማራጭ የማይገኝለትን ይህን የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ የሰው ዘር ሁሉ ተቀዳሚ ሥራው አድርጎ ሊቀበለው ይገባል፤ በዚህ በኩል ካልሆነ ሌላ የምንድንበት መንገድ የምናመልጥበት ዐውድ ፈጽሞ የለምና፡፡” እንዳሉት ወንጌል በግልጥነት ይሰበክ፡፡ የቤተክህነት የአመራር ቦታ ወንጌልን በተረዱና መልካም የሕይወት ምስክርነትና መንፈሳዊነት ባላቸው አገልጋዮች ይያዝ፡፡ ፀረ ወንጌል የሆኑ እንደማህበረ ቅዱሳን ያሉ ስብስቦች አደብ እንዲገዙ ይደረግ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለችግሮቿ መፍትሄ የምታገኘው ያኔ ይሆናል፡፡  

28 comments:

 1. ወዳጄ በሙስና ላይ የተከፈተው ዘመቻማ ተሐድሶን በማባረር: በመመንጠር ይካሄዳል:: ወዴት ጠጋ ጠጋ ነው? የሌባ አይን አውጣ አሉ:: ደፋር::

  ReplyDelete
  Replies
  1. thanks, no more time for tehadiso's

   Delete
  2. Eko syen aweta becha

   Delete
 2. hhahha, ayeeeeee, you have no hope, no hope. protestants have no room to disturb hereafter.

  ReplyDelete
 3. haven't you heard that the patriarch also urged MK and other true servants to combat 'tehadiso menafkan' as soon as he came to power. ቅዱስ ፓትርያርኩም በሙስና ላይ እየወሰዱ ያለው የማስተካከያ እርምጃ ስሙ ተሐድሶ ነው .don 't distract your hidden objective, such tehadisos is loved by true orthodoxies, the tehadiso that you want but in fact in your dream is a different one ---protestantism tehadiso. which the patriarch and others stand to eliminate it. over all, you are not prohibited to dream, wish something, keep on it...

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቆች መቼ ይሆን እውነትን ከማጣመም የምታርፉት? ፓትርያርኩ ያስተላለፉት መልእክትም ሆነ በሙስና ላይ የተከፈተው ዘመቻ ተሀድሶ አይደለም ልትሉ ነው? እናንተ ለስልታችሁ ስትሉ ፕሮቴስታንታዊ አላችሁት እንጂ ተሐድሶ እግዚአብሔራዊ ነው፡፡ ተሐድሶ የሚያስነሣው እግዚአብሔር ነው፣ እግዚአብሔር ምንጊዜም የተበላሸ ነገር በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ ሲመለከት ዝም አይልም ባሮቹን አስነሥቶ እንዲታደሱ ይጠራል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ እውነትን አታጣሙ፡፡ ይልቁን ሌላ መንገድ ሳትፈልጉ ፓትርያርኩ እንዳሉት በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ መዳንንም ውረሱ፣ እምነታችሁንም በእውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምግባር ግለጡት፡፡

   Delete
 4. ለቤተ ክርስቲያን ሰዎች ርማት(ተሐድሶ)ይሰጣቸው ከተባለ ካንገት ሳይሆን ካንጀት የሆነ ጸሎት
  አስፈላጊ ሆኖ ይስተዋላል። ምክንያቱም በክፋት (በኀጢአት)ሽርብ ገመድ የተተበተበ ትውልድ ቢንቅፉትም
  ምስጋናው ቢያመሰግኑትም ነቀፋው ነውና በምክር ወይም በብትር አይመለስም፡፤ ሥርዋ ለኃጢአት አፍቅሮ ንዋይ ወይሬስይዎ ለጽድቀ እግዚአብሔር ተግባረ(ሐ/ጳውሎስ የኀጢአት ሁሉ ምንጭ በገንዘብ ፍቅር
  መነደፍና የግዜርን ቃል መናገጃ (መነገጃ)አደረጉት እንደተባለው በዚህ ዓመት ፳፻፭(2005)
  በኢየሩሳሌም የትንሣኤ በዓል ሲከበር በ50 ዓመታት ውስጥ ያልታየ ያልተሰማና ያልተስተዋለ ክሥተት
  ተከሠተ ይሄውም መንፈሳውያን ነን ባዮችና ሥጋውያን ነጋዲዎች ጎራ ለይተው በመተናነቅ ከፍተኛ
  አምባጓሮ(ረብሻ) ሲፈጥሩ ተስተውሏል። ይህም ድርጊት በቅንነት ካራቱ መዓዝን ለጽድቅ ብለው
  የመጡ ምእመናንን ሳያስደንቅ አልቀረም፤ እንዴት ዕኮ ለምን ዕኮ የጽድቅ የሰላም ሀገር ተብሎ ባዕድ
  ይመስል በዘመድ ይህ ነገር ይፈጸማል በማለት፤ እናም አስመሳይ ጻድቃን ከመሠረቱ እስከጉልላቱ
  ስለተቆራኙት ከልብ የሆነ ጸሎትና ጾም ያስፈልጋል ወዝንቱ ዘመድ ኢይወጽእ ይህ ዓይነቱ ቁርኝት
  አደገኛ ነውና ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማዕ

  ReplyDelete
 5. These "Mahibre Kidusans" are modern time pharisees of Ethiopia who advance radicalism beyond the limit. They zeallously tried to persecute fellow orthodoxians who have diffrent view.Real obstacles for the church.

  ReplyDelete
 6. Yegna Stupid ntekula!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 7. tehidso is growing day to day . thank you

  ReplyDelete
 8. The shining moments for Tahedeso. Talibans are busted and are running nuts.

  ReplyDelete
 9. I leave a comment when I especially enjoy a article
  on a site or if I have something to valuable to contribute to the
  conversation. Usually it is caused by the fire communicated in the post I browsed.
  And after this article "በሙስና ላይ የተከፈተው ዘመቻ ተሐድሶን በማንቀሳቀስ ማቅን በማስታገስ ስብከተ ወንጌልን በማጠናከር ቢጀመር".
  I was excited enough to post a commenta response ;) I do have a few questions for you if
  it's okay. Is it just me or does it look as if like some of the responses appear like they are written by brain dead people? :-P And, if you are writing at other online social sites, I would like to follow you. Would you make a list all of all your shared pages like your twitter feed, Facebook page or linkedin profile?

  My site; http://www.iamsport.org/pg/blog/pike1owl/read/16531239/a-guide-to-pilates

  ReplyDelete
 10. Write more, thats all I have to say. Literally, it seems as though
  you relied on the video to make your point.
  You definitely know what youre talking about, why throw away your
  intelligence on just posting videos to your
  site when you could be giving us something informative to read?


  My web site voyance gratuite

  ReplyDelete
 11. Heya i am for the first time here. I came across this
  board and I find It truly useful & it helped me out much.
  I'm hoping to give something back and aid others like you aided me.

  My website - tarot de Marseille

  ReplyDelete
 12. Gena ye Tehadiso meaza etekiristianachinin yawudewal. Gena enibezalen!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. you all tehadso protestant&your supporter are stupidddddddddddddd

  ReplyDelete
 14. Seriously there are a lot to weed out from our church. Scrape out some of the stories that do not go parallel with other sister oriental churchs. I am pretty sure some bishops agree with this, but lack courage to stand up and defend the truth.One should ask questions why so many defected to the protestant church @ alarming frequency? The answer is is pretty simple.Much emphasis is on gedeles and on tamers rather on the Haimanot.

  ReplyDelete
 15. Memihir Yilima Chernet Addis Abeba HagereSibket Wana Sira Asikiyaj ehonachew Tesema Abune Esitsifanos Ahun Melkam Aderegu

  ReplyDelete
 16. wore alekebachiu, aselichiwoch.

  ReplyDelete
 17. all the time i used to read smaller articles that as well clear their motive,
  and that is also happening with this paragraph which I am reading at this time.


  Feel free to visit my website :: voyance par telephone

  ReplyDelete
 18. Love this blog. God bless you all!!!!!!!!!!! comabt modern time phareeses!

  ReplyDelete
 19. እኔኝ የሚገርሙኝ 1: ጸረ ተሃድሶ ነን ባዮቸ ሁሉ እናታቸዉ አንድ ነች። ስድብ: አሁንም ስድብ: ነዉ የሚቀናቸዉ። ቤተክረስቲያናችን አየተከተለችዉ ያለችዉ አካሄድ ለፕሮቴስታንቶች መመልመያ መድረከ መሆንዋን የማያይ እዉር ብቻ ነዉ። ይልቁንም ባህልና ባዕደ አምልኮ የተቀላቀለበትን አሰራርዋን ትታ ሁላችንንም በወንጌል መሰረትነት የሚያስማማንን ብትሰራ የት በደረሰች:
  2: ሌላዉ የሚገረመኝ የወንጌል እዉነት ሁሉ የፕሮቴስታንቶቸ ከሆነ ልክ ናቸዉ ማለት ስለሆነ ልንነቅፋቸዉ አይገባም። ፕሮቴስታንት የሚለዉን ነገር እንደማሰፈራሪያ መጠቀም ከንቱ ልፋት ነዉ። ወደዉስጣችን በመመልከት ስህተታችንን ማረም ነዉ የሚጠቅመዉ።
  ክርስቲያን ነኝ የምትል አንድ አሳዛኝ ነገር ለህሊናህ ላቅርብና ላቁም። የጌቶች ጌታ የሆነዉ መድሃኒያለም ገቢ አያስገባም ተበሎ በቀጨኔ መድሃኒያለም ገብርኤል ቤተክርስቲያን አልተሰራም? ደግሞሰ በየአድባራቱ መድሃኔዓለም ደባል ታቦት እየተባለ በመድሃኒታችን ሲሾፍ አንጀታችሁ እንዴት ቻለላችሁ? እንደገና እስቲ ልጠይቅ: ከታህሳሰ ገብርኤልና ከየትኛዉም የመድሃኔአለም በዓል የሚደምቀዉ የትኛዉ ነዉ? በዓመት ሁለት ጊዜ በገብርኤል ቀን የዓመተ ፈቃድ እየተወሰደ ሥራ እየተዘጋ አይደለምን? ይህስ ከገናና ከፋሲካ ጋር እኩል ለማድረግ አይደለምን? ብዙ አሰቃቂ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል: የማይጨክነዉን ጌታ እንዲጨክን አታድርጉት። ገብርኤለ ራሱ ይህንን የሚያስቀስፍ ነገር እያየ ዝም ማለቱ ያሳዝናል: በሱ ስም ለሰይጣነ አሰራር ዕድል መስጠቱም የሚያስገርመ ነዉ: ወንድሞችና እህቶች: የመዳን ቀን አሁን ነዉ ተበላል:እምነትንና ፖለቲካን ለዩ። ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

  ReplyDelete
 20. Fekre, good point. Well spoken. It is imperative to have all out reformation to emancipate our church from all these practices.Stand up for the truth if you love our Tewhido Church. Please do'nt get intimidated by these paper tigers(MK). If Thadeso is for change we go with Thadeso. May God bless you Fekre and thank you for your insight.

  ReplyDelete
 21. Alawaki sami............... yilekelikal alu.... amilak yeabatochachinin zemen kemelesema teterarigo medefat yalebet yenanite shefit new........ yebetkirsitiyan yebibit esat honachihu yemitakosiluwat yetehadiso yebekur lijoch............

  ReplyDelete
  Replies
  1. የትኛዉ ነዉ ሸፍጡ? ዉሸት ተናግሬ ከሆነ ዉሸት ነዉ ማለት ነዉ እንጂ እርግማንን ምን አመጣዉ? ዘፈኑ ሲያልቅበት በቀረርቶ የገባበትን አዝማሪ መሆን ነዉ ወይስ እዉነቱን አምኖ ለቤተክርስቲያናችን መዳን መሥራት ነዉ የሚሻለዉ? ወንጌልን እንደጦር እየፈራችሁ አታነቡትም። ያሳስተናል ብላችሁ መንፈስ ቅዱስን ትሳዳባላችሁ። ይህ ደግም ይቅርታ የሌለዉ መሆኑን ብታነቡት ትረዱ ነበር።ስለዚህም ተጠያቂዎች ናችሁ። አሁንም ልድገመዉ ጸረ ተሃድሶ ነን ባዮች ሁሉ አንተን/አንቺን ጨምሮ እናታቸዉ አንድ ነች። ስድብ: አሁንም ስድብ: ነዉ የሚቀናችሁ። ከዚያም በላይ ካህኑን መስቀል መቀማት ዘማሪዉን ማይክሮፎን መቀማት በጠረባ "ጠራርጎ መድፋት" ዓይነተኛ ሙያችሁ ነዉ። የፀረ ወንጌል አባታችሁ የሚያስተምራችሁ ንሰሐና ቅድስናን ሳይሆን ይህንኑ መሆኑ ያሳዝናል።

   Delete
 22. May our God and our Mother the Imaculate bless Thadeso!!

  ReplyDelete