Sunday, June 23, 2013

ሐረርን የሚበጠብጡ አባ አብርሃምና ግብረ አበሮቻቸው ናቸው

ሐረርን የሚበጠብጡ አባ አብርሃምና ግብረ አበሮቻቸው ናቸው
ለሐራ ዘተዋሕዶ ሐሰተኛ ዘገባ የተሰጠ ትክክለኛ ምላሽ
ክፍል አንድ
ታዛቢ ከሐረር
ሰሞኑን ሐራ ዘተዋህዶ የተሰኘው የማቅ አንድ አንጃ ድረገጽ በሀገረ ስብከታችን በአባ አብርሃምና በግብረ አበሮቹ እየተፈጸመብን ያለውን የዐመጽ ሥራ ጽድቅ አስመስሎና ሸፍኖ እውነተኞቹን ሐሰተኛ ሐሰተኞቹን ደግሞ እውነተኛ ለማስመሰል የሞከረበት የሐሰት ዘገባ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ ሐራ “የተሐድሶ መናፍቃንና ጥቅመኞቻቸው የሐረር ///ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ከሀ/ስብከቱ አስተዳደር ለመለየት እየቀሰቀሱ ነው” በሚል ርእስ ጁን 15/2013 እና ጁን 18/2013 ደግሞ “ከሓላፊነቱ የታገደውአባጳውሎስ ከበደ ከአስተዳዳሪነቱ ተነሣ” በሚሉ ርእስ የጻፈው የሐሰት ዘገባ ከእውነታው ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ የደብሩን ካህናትና ምእመናንም በእጅጉ ያሳዘነ ነው፡፡ እርግጥ ከማቅና ከነፍስ አባቱ ከአባ አብርሃም ከግብር አበሮቻቸውም ከዚህ የተሻለ ነገር አንጠብቅም፡፡ ሆኖም እውነቱ መገለጡ ስለማይቀር ከዚህ ቀጥሎ በተዛባ መንገድ ለቀረቡት ሀሰተኛ ዘገባዎች ተራ አሉባልታዎችን ትተን እውነተኛውን ነገር ለማቅረብ ተገደናል፡፡

1.    ሀገረ ስብከቱ የደ////ቤ/ክ/ሰ/ት የጌቴሰማኒ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያንን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲያስተዳድር እንደነበር እና ከእርሱ የሚያገኘውንም ገቢ መ/ጽዮን አባ ጳውሎስ ከበደ እና ሌሎች ምእመናን ሲዘርፉት እንደነበር ተደርጐ ተገልጦአል፡፡
የጌቴ ሰሚኒ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከተተከለችበት ጊዜ አንስቶ እስካአሁንም ድረስ እየተዳደረች ያለችው በሀገረ ስብከቱ ሲሆን ከቤተክርስቲያን የሚገኘውንም ገቢ የሚቆጣጠረው ሀገረ ስብከቱ ነው፡፡ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን እና ካህናት የሚያውቁት የኪዳነምህረት ሙዳየ ምፅዋት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች የኪስ ቦርሣ መሆኑን ነው፡፡ የደብሩ ሰንበት ተማሪዎችና ካህናቱ ግን “ይህ መሆን የለበትም ሀገረ ስብከት ከአጥቢያ ቤ/ክ ከመቶ ሃያ ፐርሰንት ይሰበስባል እንጂ አንዱን አጥቢያ በግሉ ይዞ ሙዳየ ምፅዋት እየቆጠረ ለራሱ ማድረግ የለበትም፡፡ በቃለ ዓዋዲው አንቀፅ 40 ቁጥር 5 ላይ የተደነገገውም እንዲሁ ነው” በማለት ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ አቤቱታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ ሰሚ ግን አላገኙም፡፡

እንዲያውም የጥቅሙ ዋና ተጋሪዎች የሆኑት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች “አርፋችሁ ተቀመጡ አለበለዚያ በየገጠሩ እንደጨው እንበትናች`ለን” በማለት እያስፈራሩ ጉዳዩ ዛሬ ላይ ደርሶአል፡፡ ሆኖም ለመጨረሻ ጊዜ ካህናቱና የደብሩ ስንበት ትምህርት ቤት አቋም በመውሰድ “የቅድስት ኪዳነምህረት ቤ/ክ የምትገኘው አጥቢያችን ላይ ነው፤ ፅላቱም የሄደው ከደብራችን ነው፤ አሁን ደግሞ አንድ አጥቢያ ሆና ትቋቋም ከተባለ የአጥቢያችንን ምእመናን ሙሉ በሙሉ ስለሚወስድ ደብራችን ሊዘጋ ይችላል፡፡ ስለዚህ ለዘመናት ስንጠይቀው የነበረው አስተዳደሩ በእኛ ስር ይሁን ለሚለው ጥያቄያችን መልስ ይሰጠን” በማለት በተፃፈው ደብዳቤ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ቢጠየቁም መልሳቸው እንቢታ በመሆኑ ለ12 ዓመታት ለሀገረ ስብከቱ የፃፋቸውን ደብዳቤዎች በማያያዝ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት አቤቱታቸውን ሊያቀርቡ ችለዋል፡፡

በመሠረቱ የእንገንጠል ጥያቄው መቅረብ ያለበት ከአጥቢያው ምእመናን ነበር፡፡ ነገር ግን የኪዳነ ምህረት ቤ/ክንን በደ/ሣ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ ሰ/ጉ እንድትተዳደር ከፈቀድን “የድራፍት መጠጫ ምንጫችን ይደርቅብናል” ያሉት አንዳንድ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች “የይገባኛል ጥያቄውን እየመራ ያለው አስተዳዳሪው መታገድ አለበት” በማለት በቀን 14/9/05 በቅዱስ ፓትርያርክ የተሾሙትን አባት ከቤተክርስቲያን ህግና ሥርዓት ውጪ በሥራ አስኪያጅ ፊርማ ሊያግዷቸው ችለዋል፡፡ ሐራ እንደ ወሻከተችው የደብሩ አስተዳዳሪ ከመታገዳቸው በፊት ሙዳየ ምፅዋቶች እና ፅ/ቤቶች እንዲታሸጉ መገለፁ ፍፁም ከእውነት የራቀ የሐሰት ዘገባ ነው፡፡ አባ ጳውሎስ ከበደ የታገዱት በቀን 14/9/2005 ሲሆን ሙዳየ ምፅዋቱ የታሸገው ደግሞ በቀን 16/9/2005 ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ የማይታለፍ እውነተኛ መረጃ አግኝተናል፤ ይኸውም አስተዳዳሪው እንዲታገዱ፤ ሙዳየ ምፅዋቶች እና ፅ/ቤቶች እንዲታሸጉ፣ የደብሩ ካህናት እና ልዩ ልዩ ሠራተኞች ከነቤተሰቦቻቸው በርሃብ አለንጋ እንዲጠበሱ በዚህም ምክንያት የቤ/ክ አገልግሎት እንዲቋረጥ ከጀርባ ሆኖ በስልክ መመሪያ ይሰጥ የነበረው የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ነበር፤ ምክንያቱም በአካል በቦታው አልነበረማ፡፡ አባት ማለት እንዲህ ነው? ልጆቹን በረሐብ የሚቀጣ? ቤተ ክርስቲያንን የሚዘጋ?

2.   360,000 ብር በግለሰቦች እጅ ተቀምጦ እንደተገኘ እና 60,000 ብር ለሞንታርቦ መግዥያ ተብሎ ሳይገዛ ተረስቶ እንደ ተበላ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ በአንዲት ምዕመናን ላይ በፈፀሙት ስህተት በፍርድ ከመወሰድ ለማዳን  መቃብር ቤት ውስጥ እንደተገኘና ሀገረ ስብከቱ ምዝበራን ለመከላከል የማሸግ እርምጃ እንደወሰድ ተደርጐ ተገልጦአል፡፡

ልብ በሉ አባ አብርሐም አንዲት ምዕመን እያለ የሚጠራት እኮ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነች፡፡ የእርሱ የውሸት ማዳበሪያ ስለሆነች አማኝ ተባለች፡፡ የእርሱን የዘረኝነት እና የዱርዬነት አካሄድ የሚነቅፉትን እውነተኛ አባት ደግሞ መናፍቅ ይላል፡፡

ጉዳዩም እንዲህ ነው፤ የተጠቀሰችው ሴት ሃይማኖትዋን ከመለወጧ በፊት በደብሩ ውስጥ የመቃብር ቤት አሰርታ ነበር፡፡ ታዲያ እምነቴን ብለውጥም መቃብር ቤቱን ልጠቀምበት እችላለሁ ብላ ክስ መሠረተች፡፡ ከብዙ ክርክር በ`ላ ከ80,000 ብር በላይ ግምት እንዲከፈላት በፍርድ ቤት ተወሰነላት፡፡ ደብሩም ወደ ፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለቱ ውሳኔው እስኪታወቅ በቀድሞ ውሳኔ መሠረት ሴትየዋ ገንዘብን እንዳትወስድ ማድረግ ተችሎአል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የቀድሞውን ውሳኔ ውድቅ በማድረጉ ከ80,000 ብር በላይ ለማዳን ተችሎአል፡፡ እንግዲህ ይህ የሚያሸልም ሥራ ነው እንደ ክስ ሆኖ የቀረበው፡፡ ደግሞም ይህ ክስ የተጀመረው 1986 ዓ.ም. ሲሆን የማሸግ እርምጃው የተወሰደው ደግሞ በ2005 ዓ.ም. ነው፡፡ ብሩ በባንክ ነበር፡፡ እንደዚያ ካልሆነማ ለባንክ ቤት የደብሩን ገንዘብ ለማገድ ማገጃ የፃፉት ለሌለ ገንዘብ ነው ያሰኛል፡፡

በጣም የሚገርመው ደግሞ ለሞንታርቦ መግዣ ተብሎ የተበላ 60,000 ብር እንዳለ መነገሩ ነው፡፡ ለመሆኑ ሞንታርቦ የተገዛው መቼ ነው? ላለፉት አራት ዓመታት እየተገለገሉበት ያሉትን ሞንታርቦ ሀገረ ስብከቱ ገንዘብ ተቀብሎበት ይሆን እንዴ? ሞንታርቦ የተገዛው በ2001 ዓ.ም. ሲሆን ለደብሩ ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ የሚያስገርምው ነገርገረ ስብከቱ የማሸግ እርምጃ የወሰደው ምዝበራን ለመከላከል እና ለጥንቃቄ ነው መባሉ ነው፡፡ ከዲቁናቸው ጀምሮ ሙዳየ ምፅዋት በመገልበጥ ምዝበራን የሕይወታቸው ዋና ክፍያ ያደረጉት እነሱ አይደሉም እንዴ? ነገር ግን ሀገረ ስብከቱ የደብሩን አስተዳዳሪ በሕገወጥ መንገድ አግደንሃል አሉአቸው፡፡ ካህናቱና ሕዝቡ ደግሞ “እገዳው ሕገወጥ ነው፡፡ እርስዎ የተሾሙት በቅዱስ ፓትርያርኩ ሲሆን ሃይማኖታዊም ሆኖ አለማዊ ፊደል ባልቆጠረ ሥራ አስኪያጅ ሊታገዱ አይችሉም፡፡ ይልቁንም ጉዳዩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት ተይዞ እያለ የበላይ ውሳኔ ሳይታወቅ አስተዳዳሪውን ማገዳቸው ለመንበረ ፓትርያርክ ያላቸውን ንቀት እና እምቢተኝነት ነው የሚያሳየው፡፡ ስለዚህ ከበላይ አካል ውሣኔ እስኪመጣ ድረስ ያስተዳድሩ” በማለት ወሰኑ፡፡ ሀገረ ስብከቱ ደግሞ አስተዳዳሪው ከዚህ የማይወጡ ከሆነ የባንክ ገንዘብ ቢታገድ ሙዳየ ምፅዋቶች እና ፅ/ቤቶች ቢታሸጉ፣ ለካህናት እና ልዩ ልዩ ሠራተኞች ደሞዝ መክፈል ስለማይችሉ ካህናት ደግሞ ኑሮአቸው ከእጅ ወደ አፍ ስለሆነ የሚበሉት ሲያጡ ይሰደዳሉ ወይም ከእኛ ጋር ይሰለፋሉ ያኔ የጀመርነውን ዘረኛ ተግባራችንን በማስፋፋት ሥራችንን እንሠራለን፡፡ የኪዳነምህረት ሙዳየ ምፅዋትም የኪሣችን ቦርሣ እንደሆነ ይቀጥላል ብለው ነበር፡፡

ነገር ግን የደብሩ ምዕመናን ለወሰዱት ጥንቃቄ የተሞላበት ሕጋዊ እርምጃ ሙዳየ ምፅዋቶች እና ፅ/ቤቶቹ ከ20 ቀናት መታሸግ በኋላ ተከፍተው ከሙዳየ ምፅዋት የተገኘውም ብር በሞዴል 30 ገብቶ ካህናትን ህጋዊ መስመሩን በጠበቀ መልኩ በፔሮል እየፈረሙ ደሞዛቸውን ወስደዋል፡፡ ይሄ ነው እንግዲህ ምዝበራ ተካሂዶአል እየተባለ በአባ አብርሃም እና ቤተክርስቲያንን በሚበዘበዙ፣ እንደ መዥገር ተጣብቀው የምዕመናንን ደምም በሚመጡ ጀሌዎቻቸው የሚነገረው፡፡ እኛን የሚገርመን ምእመናን ተርፏቸው ሳይሆን ፆማቸውን እያደሩ ከእለት ጉርሣቸው ቀንሰው ለእግዚአብሔር ክብር የሚወረውሩትን ሳንቲም አጠራቅመው እነሱ ጮማ ሲቆርጡ እና በቢራ ሲራጩ አለማፈራቸው ነው፡፡
3.   መ/ጽ አባ ጳውሎስ ከበደ ለአዳር መርሃግብር እና ለጸሎት የሚጠቀሙበት ኮንዴሚንየም ቤት እንዳለ እና ምንፍቅናን እያስፋፉ እንደሆነ፤ ለተወገዙ መምህራንና ዘማሪያን መድረኩን አሳልፈው እንደሰጡ ተዘግቦአል፡፡
ለመሆኑ አባ ጳውሎስ ከበደ እን£ን ሌሊት ይቅር እና ቀን እን£ን ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ይወጣሉ ወይ? እርሳቸውን የሐረር ካህናትና ምዕመናን የሚያውቋቸው በተገለጠ ማንነታቸው ትክክለኛ መነኩሴና ከበአታቸው የማይወጡ አባት መሆናቸውን ነው፡፡

ሌላው አስገራሚ ነገር በሐሰት እንዳስወሩባቸው አባ ጳውሎስ መናፍቅ ከሆኑና አላማቸው ቤተክርስቲያንን ማፍረስ ከሆነ ለምን ሕገ ቤተክርስቲያን ይጠበቅ ቃለ አዋዲው ይከበር እያሉ ይከራከራሉ? ለምንስ በደብሩ ውስጥ እናንተ “ሕገወጥ እያላችሁ የምትተቹትን የልማት ሥራ እራሳቸውን ሰውተው ሰሩ? ደግሞስ በደብሩ ይዞታ ላይ የሚገኘውን የእንስሳት መኖ ጠዋት እና ማታ በመቆፈር እና ውሃ በማጠጣት ለምን ይደክማሉ? ለምንስ ለምንኩስና ሕይወት ራሳቸውን አስገዙ? ደግሞስ ባለ ኮንዴሚንየምዋ ሴት በስም ለምን አልተጠቀሰችም? ነገሩ ፍጹም ውሸት በመሆኑ አይደለምን?

የሚገርመው አንድ ጊዜ የተጠቀሙበትን ስልት ለዘመናት ሊጠቀሙበት መሞከራቸው ነው፡፡ መቼም ሕዝቡ ለሃይማኖቱ ቀናኢ ነው እና የሕዝቡን ድጋፍ ለማግኘትና ማህበረ ቅዱሳን የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋልን ተብሎ አባ ጳውሎስ ላይ ‘መናፍቅ ተሐድሶ” የሚለውን ስም እንስጣቸው ተብሎ ታፔላው እንደተለጠፈባቸው ግልፅ ነው፡፡

ለመሆኑ የትኛውን በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘ መምህር እና ዘማሪ ነው በቤተክርስቲያን መድረክ እንዲያገለግል የፈቀዱለት? ማኅበረ ቅዱሳን በእንጀራዬ ገቡ ለእኔ አይታዘዙም በሚል በሃይማኖት ሰበብ “ይወገዙልን” ያላቸውን ሁሉ ሲኖዶስ እንዳላወገዘ ግልጽ ነው፡፡ ምንአልባት ቅዱስ ፓትርያርክ ከሚመራው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውጪ አባ አብርሃም ራሱ በፓትርያርክነት የሚመራው ሲኖዶስ ይኖረው ይሆን እንዴ? ወይም የማህበረ ቅዱሳንን ስብሰባ ከሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ እያለ የሚጠራ ይህ መናፍቅነት ነው፡፡ ምክንያቱም አሥራት እና በኩራት ከሚያወጡለት የራሱ አባላት ውጪ ማህበሩ ለየትኛውም የቤተክርስቲያን ሊቅ ወይም መምህር እውቅና ሰጥቶ አያውቅም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስንም አይወክልም፡፡

አባ አብርሃም “ጳጳስ” ሆኖ ወደሀገረ ስብከቱ ከመጣ በኋላ ምን ሠራ? የእርሱን ማንነት በተመለከተ በቀጣዩ ክፍል አቀርብላችኋለሁ፡፡

ታዛቢ ከሐረር


25 comments:

 1. ታድሶ ተመታች:: አመማት:: ማልቀስም ጀመረች::

  ReplyDelete
 2. so sad, when we will get the right leader for our church. Those church leaders (bishops) are running their private business. what kind of spiritual responsibility do we expect? They are so stupid, sorry to say this word. I felt bad. Aba Abraham is so racist, we know him more than anybody. thanks for ጌቴ ሰሚኒ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን congregations. Be united to remove Aba Abraham from that area. The Grace of God be with you all .....

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ማታዉቀዉ ነገር የምታወራ ትመስላለህ

   ተሃድሶ መናፍቃን ስራቸዉ ስለተመታ የሞት የሽረት ትግል እያደረጉ ነዉ
   አንዱ መንገዳቸዉ ደግሞ ይህን ዘመቻ የግለሰቦች ጠብ ማስመሰል ነዉ
   የራሄል እንባ ተሰምታል እስከዛሬ ሀረር ላይ የሚደረገዉ የመናፍቃን ግፍ ማብቃት አለበት ከእግዚአብሔር ጋር ሁሉም ለቤቱ ይተጋል
   አባ አብርሃም እንደሆነ ለእዉነተ ፊታቸዉን አይመልሱም ለእዉነት የቀመዉ ጋር አብረዉ ይቆማሉ

   Delete
 3. ታዛቢው ከሐረር በእውነቱ እረስህን ታዝበሃል፡፡ ለመሆኑ አንተም ወገንተግነት አለብህ ሐራን ወቀስክ እንጂ አንተ እንደ ታዛቢ አልቀረብክም፡፡ ጳጳሱን አንተ ማለትህ መነኩሴውን አንቱ ማለትህ በምንም መስፈርት ምንፍቅና ነው፡፡ አንተ አይደለህም አንቱነትን የሰጠኸው ስለዚህ መግፈፍም አትችልም፡፡ ቢያንስ ሐራ በምንም ይሁን አንተ የገለጥከውን ነገር ነካክታለች ድርጊቱ በምንም መንገድ መከናወኑን መግለጥህ ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ለሰው አትቁም ለቤተክርስቲያን ቁም፡፡ ትክክለኛ ክርስቲያን ከሆንክ የሰውን ገመና መናገር ሃጢያት መሆኑን ትረዳ ነበር፡፡ በጸሎት ብትተጋ ስንቱን ታድን ነበር ግን ባዶ የሆነ ነገር ሁሉ ይጮሃልና እንደዛ ነህ፡፡ ከዚህ በሁዋላ ባወራህ ቁጥር በራስህ ላይ ሃጢያትን እየጨመርክ እንደሆነ ተገንዘብ፡፡ ከውጪ በምትሰማው አትወሰድ አሁንም ጸልይ እንጂ አትናገር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሐራስ መነኩሴውን አንተ ማለትዋን አላነበበብክምን? መነኩሴውን ሐራ አንተ በማለትዋ ማቅን መናፍቅ ለማለት ድፍረት አለህን? ሐራን እንደዛ ለማለት ከደፈርክ ርድህ ትክክል ነው ለማለት ባልችልም ሚዛናዊነትህን አከብራለሁ፡፡ አለበለዚያ ግን የውሾን ነገር ያነሳ ብለን ----- ብለን እናፍሀለን

   Delete
  2. ስማ እንጂ የመነኩሴ ትንሽ አለው ወይ? ሀራ ትክክለኛውን መነኩሴ አባ ጳውሎስን አንተ ሲል አንተስ እርሱን ለመተቸት ምነው አልደፈርህም አንተም ወግነተኛ ነህ፡፡ ስለዚህ በቅድሚያ በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፡፡

   Delete
 4. betam enamesegenalene

  ReplyDelete
 5. ይሀ ክፉ መነኩሴ ለምን ይበጠብጠናል? አብርሃም የሚባል ባለዛር ማነው ሀረር ያመጣብን እግዚአብሔር ይንቀለው አቦ?

  ReplyDelete
 6. አሁን ማን እንደሆናቹ በአባ ሰላማ በኩል ስትመጡ እወቅን

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባ ሰላማ ትክክለኛ ብሎግ ናት፡፡ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያለው እግር ተሸፋፍኖ እንዳይቀመጥና ቤተክርስቲያናችንን እንዳይገድላት እንስተካከል የምትል የሁላችንም ብሎግ ናት፡፡ እንደ እናንተ ከአንድ ወገን ብቻ ወግና ሐሰት የምታራግብ አይደለችም፡፡ ስለዚህ እባክህን ሰውን ባቀረበው ሐሳብ እንጂ ሐሳቡን ባቀረበበት ሚዲያ አትለካ፡፡ ይህ የሚያሳየው ገና እንጭጭ መሆንህን ነው፡፡ ለመሆኑ የእናንተ ሐራ ይህ ጽሑፍ ቢላክላት ታወጣው ነበር? በፍጹም አታወጣውም፡፡ ታዲያ እውነቱ ተቀብሮ ይቅር ወይ? አባ ሰላማ እኮ እንዲህ ላለው ጊዜ መተንፈሻችን ናት፡፡

   Delete
  2. ታማኝ ክርስቲያን ነኝJune 26, 2013 at 6:23 AM

   አንተስ የት አነበብከዉ ከአባ ሰላማ አይደለም አንተስ በማን በኩል እየመለስክለተ ነዉ ይህንን ስል ስድብን በምንም መልኩ አልደግፍም አባ ሰላማ ላይ የሚወጡት እዉነቶችን እነዚህ ባለጌ ተሰዳቢዎች ሊሸፍኑት አይገባም

   Delete
 7. ምነው ይህ የጎጃም ቄስ ባለትዳሩን አባ አብርሃምን ጵጵስናውን ገፋችሁ አታባርሩትም?

  ReplyDelete
 8. አውደ ምህረት ከዚህ በፊት ስለ አባ አብርሃም እንዲህ ጽፋ ነበር
  አባ አብርሃም ኢየሱስ አያዋጣም አሉ!!

  በሀረር ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሦስት ቀናት የቆየ እጅግ ደማቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሂዶ ነበር። በወንጌል ወዳድነቱ የሚታወቀው የሐረር ህዝብ በሶስቱ ቀን ጉባዔ በከፍተኛ ሁኔታ የተገኘ ሲሆን በጉባኤው ሰዓት የክልሉ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ አብርሃም አገልጋዮቹን ጠርተው “…ይሔ ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉት የሚያዋጣችሁ አይመስለኝም። ብትተዉት ይሻላል።” በማለት ተናገሩ።
  የአባ አብርሃም የጉድ ሙዳይ በከፈቱት ቁጥር በውስጡ የተደበቀ ነገር እየወጣበት ከማስደነቅ አልፎ ማሳዘን ከማዛዘንም አልፎ ማስደንገጥ ጀምሯል። ይህ ንግግራቸው ሰውየው በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያላቸው አጀንዳ ምንድን ነው? አሰኝቷል። ህሊናቸውን ተጠቅመው የሚያደርጉት ነገር እንደሌለ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከሰጣቸው ተልዕኮ ውጭም ሌላ አጀንዳ እንደማይታያቸው ያሳየው እንዲህ ያለው ንግግራቸው ከወንጌሉ እውነት ውጭ መስማት በማይፈልገው የሐረር ሕዝብ ፊት እንዲፈጸም በማዘዛቸው ትዕዛዛቸው ሳይሳካለት ቀርቷል። ከዛም በኃላ ደግሞ የደብሩን አስተዳዳሪ ጠርተው “…ይሄ ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉትን የማያዋጣ ጉዞ መቸ ነው የምትተዉት?...” ሲሉ ለመውቀስ ሞክረዋል።

  ስለ ጽድቅ ስለ ኃጢአትና ስለ ፍርድ አለምን ይወቅሳል የተባለው የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ እንዳያገኛቸው ከመንፈስ ቅዱስ የሆኑ መልዕክቶችን በመግፋት የሚታወቁት አባ አብርሃም ካፈርኩ አይመልሰኝ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማያዋጣቸው ደጋግመው መናገር ይዘዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ካላዋጣ የሚያዋጣው ማን ይሆን? ማኅበረ ቅዱሳን? ወይስ በቆብ ተሸሽገው ቆብ ገልጠው የሚገቡት አባ አብርሃም?
  ለነገሩ ክርስቶስ የመጠላቱ ሚስጢር ገብቶናል። ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “…ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤” ብሎ በጻፈው የእውነት ቃል እንደሚያረጋግጥልን ብርሃን የሆነውን ጌታችንን ስሙን መጥራት ራሱን ለጨለማ ሀሳብ ላስገዛ ሰው ይከብዳል። አባ አብርሃም እውነታቸውን ነው ክርስቶስ ብርሃን ነው። የጨለማን ሥራ ያስወግዳል። በጨለማ ስራ ለመኖር የሚፈልግ ግን የብርሃንን መልዕክት መሰማት አይፈልግም። እሳቸውም ካሉበት ቦታና ድርጊት አንጻር ስለ ብርሃን ጌታ መስማት አይፈልጉም። ነገሩ በአንድ ወቅት አንድ ጸሀፊ “ኃጢአትም ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስም ከኃጢአት ይጠብቃል።” እንዳለው ሆኖባቸው ነው።
  አባ አብርሃምን በምን እንምንከተላቸው ግራ ገብቶናል። ከሃይማኖት ሃይማኖት የላቸው። ከምግባር ምግባር የላቸው። ከአስተዳደር ችሎታ የአስተዳደር ችሎታ የላቸው። ከእውነት እውነት የላቸው። ከህዝብ ፍቅር ራሳቸውን ካስገዙላቸው የማቅ ሰዎች ውጭ የሚወዳቸው የለ። በገንዘብ ፍቅር በሴት ፍቅር በሥልጣን ፍቅር… የተያዙ ሰው ናቸው። የሞነኮሱ ለት ስርዓተ ግንዘት የተፈጸመላቸው ለዓለም እና ለምኞቱ እንዲሞቱ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ነገሮች ሞተው ለአለማዊ ነገሮች ህያውነትን ለማግኘት ሳይሆን አይቀርም። ምን… ችግር እኮ ነው እነ ደብተራ አስቻለው የማይሰሩት የለ!!
  ከሁሉ ከሁሉ የከፈፋው ጉድና ጉድለታቸው ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እንዲህ አድርገው መጥላታቸው ነው። ይህ ተግባራቸው እጅግ የሚያሳዝንና ሰውየው በመዳናቸው ጉዳይና በመንግስተ ሰማያት ተስፋ ቆረጡ እንዴ? ያሰኘ ነው። አሁን ያሉበትም ሁኔታ እነደ ሥጋዊ ሰው እንኳ በማንነታቸውና በጤንነታቸው የሚያስመካ አይደለም እና የጌታችን የኢየሱስ ክርቶስም ደም ከኃጢአት ሁሉ ነፃ እንደሚያወጣቸው አውቀውና አምነው ንስሐ በመግባት ፊታቸውን ወደ እርሱ ዘንበል ቢያደርጉ የተሻለ ነው እንላለን።
  ብቸኛ የድኅነት አማራጭ መሆኑን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሙላት ያረጋገጠውን ክርስቶስ አያዋጣም ማለትን እንኳን እሱን አገለግላለሁ የሚል ጳጳስ ምዕመንም ሊናገረው የማይገባ ክህደት ነው። ለክብሩ የማይደራደረው ጌታን እያመለክን እኛም ብንሆን ለክብራችን መደራደር አይገባንም። ሚሥጢር ገላጩ ጌታ በመንፈሳዊነት ካባ ኃጢአት ሲያደባ ምን እንደሚመስል ተራ በተራ እያሳየን ነው። አባ አብርሃምን የተንጠለጠሉበት ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው የሸንበቆ ዛፍ ከምንም አያስጥሎትም እና ወደ እውነተኛው እና አስተማማኙ የወይን ግንድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲጠጉና ከዘላለም ጥፋት እንዲመለሱ በአደራ ጭምር እናሳስባለን።

  ReplyDelete
 9. ስሟን ይተውልን


  ያቺን ደጀ ሰላም ያቺን የኛን ጓዳ
  ይፃፃፋል አሉ ሊያፈርሳት እንግዳ
  ንገሩት ንገሩት ስሟን ይተውልን
  ለዘለፋ ርዕስ አታድርጋት በሉልን
  ያን ተዋጊ በሬ በሉት መንጋ አትበትን
  የእቅፏን ልጆች በክፉ አትፈትን
  ውረድ ከጀርባዋ በቃ አትድረስባት
  እኛ እንጎራረስ ፍቅርን እንብላባት

  (ዘፍቅርተ 2002)

  ReplyDelete
 10. ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
  እኛን የመውደድህ የዘላለም እትራት
  የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
  የጲላጦስ ግርፊያ የሔሮድስ ካባ
  ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍና እምባ
  ላንተ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን ደስታ
  መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
  ጅራፍና ቡጢ ምራቅና ሀሞት
  ለዓይን ደስ የማይል የህመም ሰውነት
  በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
  እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
  የመዳን አለኝታ የዘላለም እትራት
  ውዴን ያላያችሁ እኔ ልንገራችሁ
  ፍቅሩን ላሳያችሁ ድምጹን ላሰማችሁ
  ምራቅ ተቀብቷል
  መከራ ተቀብሏል
  ኃጢአት ተሸክሟል
  በቆንዳላው መሀል የደም ጎርፍ ይፈሳል
  የፍቅር ንጉሥ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
  ውዴን ያላያችሁ እኔ ላሳያችሁ
  ዓይኑ ፍቅር ያለቅሳል
  ጎኑ ደም ይረጫል
  ጽህሙ ተነጭቷል
  ልብሱ ሜዳ ወድቋል
  በቃሉም ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
  በፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
  ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
  እኛን የመውደዱ የዘላለም እትራት
  ለእርሱ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን መድኃኒት!!!

  ReplyDelete
 11. መስቀል ነው ይከብዳል
  ይወጣል ይወርዳል
  ላብ አይደለም ደም ነው
  በጨርቋ የቀረው
  የእኔንም ልብ እንካ
  እንደ ቬሮኒካ
  በላዩ ላይ ይቅር
  የታተመ ፍቅር

  ReplyDelete
 12. ፋሲካ

  በሚያስፈራው ሌሊት ጩኸት ሲበረታ
  ግብጽ ተሸበረች ጌታ በኩሯን መታ
  ሞት መግባት አልቻለም ወደ እስራኤል ቤት
  ታትሞ ስላየ የደም ምልክት
  ደጃቸውን ዘግተው ፋሲካ አደረጉ
  በደም ተከልለው ሌሊቱን አነጉ
  ባሕሩን ተሻግረው ከነዓን ሲገቡም
  የልጅ ልጆቻቸው ፋሲካን አልረሱም
  ይህ ሥርዓት አልፎ የእግዚአብሔር በግ መጣ
  ሰውን የገዛውን የሞት ኃይል ሊቀጣ
  የሰው ፍቅር ስቦት ከሰማያት ወርዶ
  ጠላትን ረታው ፋሲካችን ታርዶ


  በመስቀል ተሰቅሎ ስለሆነ ቤዛ
  ወገኖቹን ዋጅቶ በራሱ ደም ገዛ
  ንጉሡ እንዲገባ ደጆች አይዘጉም
  ሌሊቱ አልፏልና የሚያሰጋን የለም
  የሕይወታችን ጉበን በደም ታጥሯልና
  ሞት እያየ አለፈን ኃይሉን አጥቷልና
  ለምሕረት በሚጮኸው የደሙ ምልክት
  ባሕሩን ከፍለን አልፈን እንገባለን ገነት
  የዘላለም አምላክ የምስጋና ጌታ
  ምርኮን የማረከ ማኅተሙን የፈታ
  ሞትን ድል የነሳው የናዝሬቱ ኢየሱስ
  በዙፋኑ ያለው የአርያም ንጉሥ
  ከፍ ከፍ ይበል ይድረሰው ምስጋና
  መከራን ታግሶ ለእኛ ታርዷልና
  ፋሲካን ስናደርግ ኖረን በእድሜ ጸጋ
  ክርስቶስ ፋሲካ መሆኑን አንዘንጋ፡፡

  ReplyDelete
 13. ከባሕሩ ዳር ሕመሜን ትቼ
  አልጋዬን ባዝል ድኜ በርትቼ
  በሰንበት ዳነ ማረው ብላችሁ
  ያዳነው ይሙት ለምን አላችሁ?

  ክንድህን እጠፍ የሚልህ ማነው?
  ማዳንህን ተው የሚልህ ማነው?
  ቢከፋቸውም አሳዳጆቼ
  እስከአሁን አለሁ ባንተ ጸንቼ

  ReplyDelete
 14. ሠራተኞች አብዛ
  ዘመኔ በከንቱ በጣም እየሮጠ
  በክፉዎች ወሬ ልቤ እየቀለጠ
  ሕይወቴ በጅምር እንዳይቀር ፈረቼ
  በረሃውን አለፍኩ ድምፅህን ሰምቼ
  ይናፍቃል ልቤ የቃልህን ወተት
  ደግም ተሠረቼ እንድተከልበት
  በሰፊው መከርህ ያሰማራሃቸው
  ጥቂት ሠራተኞች ምሥራች ተናግረው
  ወደ አንተ እንዲያደርሷት ነፍሴ ፈልጋቸው
  በመንገድ አስቀሯት ጥቅም አጣልቷቸው
  መልካሙን ምስራች ተግተው የሚያወሩ
  የተናገሩትን በሕይወት የሚኖሩ
  ለእውነት የሚቆሙ ሠራተኞች አብዛ
  እንዳይቀር ትውልዱ እረግፎ እንደጤዛ
  ዘኁ 13-15፣ ማቴ 9፡35-38፣1ጴጥ 25፡1-3

  ReplyDelete
 15. denkoro menafik

  ReplyDelete
 16. yihich kifu yemmitinnager milas and qen meqorexua layqer zare tilefelifalech!

  ReplyDelete
 17. ውስጥ አዋቂ᎗ በጣም ያሳዝናል ጭራሽ የጕድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ጸረ ሙስና ውስጥ ገቡ ከድጡ ወደ ማጡ አባቶች አላማችሁ አልገባንም የፓትርያሪኩ ጅማሮ ሰውን ሁሉ አስደምሞት ሳለ ነገር አበላሻችሁ የፓትርሪርኩን የስራ ዘመናቸውን ለማበላሸት ይመስልባችኋል አስቡበት ድመት አይጥ ጠባቂ ስትሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ይቆየን።

  ReplyDelete
 18. Geta Hoy Zemenachenen Ades

  ReplyDelete
 19. kerstena mewaded , mefeqaqer,memkaker enji mesdadeb ayidelem. feraj ersu egzihabher becha new.

  ReplyDelete