Wednesday, June 26, 2013

ሐረርን የሚበጠብጡ አባ አብርሃምና ግብረ አበሮቻቸው ናቸው

ሐረርን የሚበጠብጡ አባ አብርሃምና ግብረ አበሮቻቸው ናቸው
ለሐራ ዘተዋሕዶ ሐሰተኛ ዘገባ የተሰጠ ትክክለኛ ምላሽ
ክፍል ሁለት
ታዛቢ ከሐረር
 አስመሳዩ ጳጳስ አብርሃምና ጉዱ
አባ አብርሃም ብዙ ጉዶች ያሉበት ሰው መሆኑን ከዚህ ቀደም “የጉድ ሙዳይ” በሚል ስም ማንነቱ ሲገለጽ መኖሩ የሚታወስ ነው፡፡ በእርግጥም ሰውዬው የጉድ ሙዳይ ነው፡፡ ከባሕር ዳር እስከ አዲስ አበባ ራጉኤል፣ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ አሁንም በሐረር ብዙ ጉዶች ያሉበት የጉድ ሙዳይ ነው፡፡ የጵጵስና ልብስ የለበሰውና በማንነቱ ግን ነውረኛ የሆነው አባ አብርሃም ምሥራቅ ሐረርጌ ከተመደበበት ጊዜ አንስቶ ከሰራቸው ኢክርስቲያናዊ ስራዎች መካከል አንዳንዶቹን ለመጥቀስ እንሞክራለን፡፡
1.    ዘረኛ ነው
አባ አብርሃም ወደሀገረ ስብከታችን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ 98% የሚሆኑትን ከምስራቅ ጎጃም የሆኑትን የወንዙን ልጆች ሲጠቅም ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ፦
·        አቡነ ማርቆስ በስነ ምግባር ብልሹነቱ ያባረሩትንና መሰሉን “መነኩሴ” ከደብረ ማርቆስ በማስመጣት በሌለበትና ባልሰራበት ከታህሳስ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ እንዲከፈለው አድርጓል፡፡ መነኩሴው  ሀገሩን የረገጠው ግን ጥር 9/2005 ዓ.ም. ነበር፡፡
·        ቄስ ፋሲል አጥናፉ የተባለውንና ለዘረኛ አላማው ዋነኛ አቀንቃኝ የሆነውን ሰው፣ አካሉ ብቻ ሳይሆን ልቡም የጎበጠበት ጊዜው አሸናፊ የተባለው ሰው አቅራቢው ሆኖ የቅርሳ ቅርስ መምሪያ ሃላፊ ተደርጓል፡፡ ይህም የሆነው ለቦታው የሚመጥኑትን የዲግሪ ምሩቅ የሆኑትን መምህር ባዩን ከሚሰሩበት የቅርሳ ቅርስ መምሪያ ያለ ምንም ምክንያት ለፋሲል ሲባል በማፈናቀልና ከሀገረ ስብከቱ ወደ ወረዳ በማዛወር ነው፡፡ አባ አብርሃም ፋሲል አጥናፉን የቅርሳ ቅርስ ክፍል ማድረጉ አላረካ ቢለው፣ ከዚያ አንሥቶ የጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ የነበሩትን በኩረ ትጉሃን በላይሁን ሞልቶትን በተመሳሳይ ሁኔታ በማባረር ፋሲል አጥናፉን የሀገረ ስብከቱ ገንዘብ ያዥ በማድረግ ሾሞታል፡፡ ይህም የሆነው የኪዳነ ምህረትን ገንዘብ ያለተቀናቃኝ ለመዝረፍ እንዲያመቸውና በተጠናወተው የዘረኛነት ልክፍት ምክንያት ነው፡፡
·        በቄስ ፋሲል አጥናፉ ቦታ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ጊዜ በነጭ ወረቀት ገንዘብ እየሰበሰበ ምዝበራ በመፈጸሙ እና በሥነ ምግባር ብልሹነት ከነበረበት ከጉርሱም ራጉኤል አስተዳዳሪነት ለቅጣትና ማስተማሪያ ወደ ቀርሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተራ ሰራተኛነት እንዲዛወር የተወሰነበትን “ቄስ” ነጻነት የተባለውን ነውረኛ ወደሐረር ደብረ ገነት መድሀኔ ዓለም ቤተክርስቲያን በስብከተ ወንጌል መድቦታል፡፡ ይህም የሆነው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አልቀበልም እያለ እንቢታውን ቢገልጽ አስተዳዳሪውን ነጥሎ በመጥራት ከስራ ከማባርርህ ተቀበል ብሎ በማስፈራራት ነው፡፡ በደብሩ እድገት ማግኘት ያለባቸው ብዙ ካህናትና ዲያቆናት እያሉ እንዲህ ያለውን ሰው ለዚያውም በስብከተ ወንጌል መመደቡ አባ አብርሃም ምን ያህል የዘቀጠና ብጤዎቹን የሚሰበስብ ዘረኛ ሰው መሆኑን ያሳያል፡፡
·        ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ውስጥ በጌታ ጾም ሰአታት በመቆም አገልግሎት እየፈጸመ ሳለ በደብሩ አስተዳዳሪ በመቋሚያ ድብደባ የደረሰበት ዲ/ኅሩይ በደል ተፈጸመብኝ ፍትሕ ይሰጠኝ ብሎ ለ“አባ” አብርሃም አቤቱታውን ቢያቀርብ ሰይጣናዊ ምግባር ያለው አባ አብርሃም ግን የካቴድራሉን አስተዳዳሪ ዲያቆኑን አግድና የሀገሬ ልጅ የሆነውን ዲ/ጌትነትን ከመድኃኔ ዓለም ይምጣልኝ ብለህ ጠይቅ በማለት ዘረኛነት የተሞላውን ቀጭን ትእዛዝ በስልክ አስተላልፎ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል፡፡
·        ከደ/ሣ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከዲቁና ወደ ሀገረ ስበከት ሂሳብ ሹምነት በተዛወረ አገልጋይ ቦታ በጽዳት አገልግሎት እየሰራ ያለ ዲያቆን እያለ አባ አብርሃም ግን ዲ/ለይኩን የተባለ ዲያቆን ቀጥሯል፡፡ በአጠቃላይ ከዚህ በላይ የተገለጸው አባ አብርሃም ግለሰቦችን በማባረርና በመግፋት ከፈጸማቸው በደሎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ መረጃዎቹ እውነተኛ ለመሆናቸው በተጠቀሱት ቦታዎች ቀርቦ መጠየቅና መረዳት ይቻላል፡፡

2.   ሙሰኛነቱን በተመለከተ
በሚግርምና በሚደንቅ ሁኔታ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ ዋነኛው ሙሰኛ አባ አብርሃም ነው፡፡ ከፈጸማቸው የሙስና ተግባሮች መካከል በጥቂቱ እነሆ
·        የግሉ መኪና ቁልፍ ቢጠፋበት ለቤተ ክህነቱ ጉዳይ ለስራ ስንቀሳቀስ ነው የጠፋብኝ በሚል ምክንያት ከ10,000 ብር በላይ ውዝግብ ከተፈጠረባት ከኪዳነ ምህረት ገቢ ላይ ወስዷል፡፡
·        ለመንበረ ጵጵስናው እድሳት በሚል ሰበብ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ አሁንም ከኪዳነ ምህረት ገቢ ላይ መዝብሯል፡፡
·        በአበል ስም ከሀገረ ስብከቱ ጽህፈት ቤት እና ከቁሉቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከስድስት ሺህ ብር በላይ በየወሩ ይወስዳል፡፡
·        በካህናት ማሰልጠኛ ስም ከጠቅላይ ቤተክህነት የሚለቀቀው በጀት መድረሻው አይታወቅም፡፡
·        “ቄስ” ፋሲል አጥናፉ ሲቀጠር ማግኘት የነበረበትን መነሻ በጀት ሳይሆን ከመድረሻውም በላይ እንዲከፈለው ሲደረግ መደበኛ ስራው ሆኖ ሳለ 800 ብር አበልም እንዲወጣለትም ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያንም 700 ብር በአጠቃላይ ከጣራ በላይ ከሚከፈለው ደሞዝ ውጪ ስንት የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች በየገጠሩ በ600 እና በ700 ብር እየተንገላቱ በአበል ስም ከ1500 ብር በላይ እንዲከፈለው አድርጓል፡፡
·        ልጆቹንና ሚስቱን አባሮ ለጎዳና የዳረገውንና በአጠቃላይ ለክህነት የማይበቃውን ቄስ ዮሐንስ የተባለውን የሀገረ ስብከቱ ልማት ክፍል ሰራተኛ የሆነውን የኪዳነ ምህረት ገበዝ በማለት በዘረኛነት መንፈስና ለሚመዘብረው ገንዘብና ስእለት እንዲያመቸው 600 ብር አበል እንዲወጣለት  አድርጓል፡፡
·        የማያጥንና ክርስትና ለማንሣት እንኳን ሞያ የሌለው በዘመናዊውም ትምህርት የ9ኛ ክፍል ሽፍታ የሆነውን ስራ አስኪያጅም በአበል ስም ከቁሉቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ2000 ብር በላይ ይወስዳል፡፡
·        ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አባቱን በሕይወት እንዳሉ አድርጎ ሥልጣኑን አለአግባብ በመጠቀም ደሞዛቸውን እየወሰደ እንደሚገኝ ተደርሶበት በጠቅላይ ቤተክህነት ተከሶ የነበረው የሀገረ ስብከቱ ሂሳብ ሹም ኢያሱ የተባለውን ያለ ዕውቀቱና ያለችሎታው ቦታውን ከመያዝ አልፎ “አባ” አብርሃም ለምዝበራው እንዲመቸው ከኪዳነ ምህረት ገቢ ላይ 600 ብር አበል እንዲወጣለት አድርጓል፡፡

3.   ነውረኛነቱን በተመለከተ
መጽሐፍ ቅዱስ ክብራቸው በነውራቸው ሆዳቸው አምላካቸው ከሚላቸው አንዱ የሆነው “አባ” አብርሃም ከመጋረጃ ወይም ከቆብ ጀርባ ያለውን ታሪኩን ስንመለከት አመንዝራ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡ ሳይጠራ ለገንዘብና ለስልጣን ሲል በገባበት የምንኩስና ሕይወት መኖር ያቃተው፣ ወትሮውንም ዱርዬ የሚለው ስም የማይገለጸው ነውረኛ ነው፡፡ እንዴት እንሾመዋለን የሚል መቃወሚያ ቀርቦበት የነበረው “አባ” አብርሃም ከሹመት በኋላም “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” እንዲሉ ሀረር ከመጣ በኋላም የቀደመ ምግባሩን በግልጽ ቀጥሎበታል፡፡ ለዚሁም እንደማሳያ፦
·        የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ንብረት ክፍል የነበረችውን ቅምጡን፣ የደብሩ ዲያቆናት ከ500-900 ብር እየተከፈላቸው ከሚሰሩት መደበኛ ስራቸው ውጪ በነጻ እንዲሰሩ ተገደው ሲሰሩት የነበረውን የጸበል ገቢ ሰብሳቢነት ስራ ላይ በመቅጠር የ1200 ብር ተከፋይ አድርጓታል፡፡
·        ቀድሞ ፖሊስ እንደ ነበረ የሚነገረውና በየት በኩል ዲያቆን እንደ ሆነ በማይታወቀው አመንዝራው ሾፌሩ በኩል የተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰንበት ተማሪ የነበረችውን ቤዛ የተባለች ልጅ መጀመሪያ ሰራተኛ በሚል ስም ካስገባት በኋላ እንደ ገና ኤንጂኦ ስራ አስገባኋት በማለት ሲኤምሲ በሚገኘው ቤቱ መስቀመጡ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ታዲያ ይህ ዘረኛ ሙሰኛና ነውረኛ “ጳጳስ” መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ሙስናን ለማጥፋት በቅዱስ ሲኖዶስ ተመረጥኩ እያለ ማውራት ጀምሯል፡፡ የሚያውቁትማ ሙስናን ለማስፋፋት ነው የተመረጠው እያሉ ነው፡፡ ምነው ሰው ጠፍቶ ነው ሙሰኛው አባ አብርሃም የፀረ ሙስና አቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተደረገው? ቤተክርስቲያናችን ከድጡ ወደ ማጡ እየገባች ለመሆኑ የአባ አብርሃም ሹመት ያሳያል፡፡ ለመሆኑ ከእሾህ በለስ ይለቀማልን?

13 comments:

 1. wey gud yigermal

  ReplyDelete
 2. መቸም ውሸታችሁ ተነግሮ አያልቅም መቸ እውነት እንደምትናገሩ እግዚአብሔር ይወቀው ውሸት 1. አቡነ ማርቆስ በስነ ምግባር ያባረሩትን መንኩሴ ያላችሁት ወጣቱ አዛውንቱ አይነኩብንም እያለ የዋሻው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ማህበረ ምዕመናን አቡነ ማርኮስን አንፈልግም እያለ መንኩሴውን ግን ማንም እንዳይነካቸው ብሎ ህዝቡ ባንድነት ተነስቶ ሳለ መነኩሴው በራሳቸው ፈቃድ የአቡነ ማርቆስን ጥላቻ በመሳቀቅ ጥለው ሄደዋል ደግሞ እኛ ምስክር ነን ፡ዋሻው ቅዱስ ሚካኤልን የመሰለ ካቴድራል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያሰሩ ጠንካራ አባት ናቸው፡፡ ከፈለጋችሁ ወጣት የሰነበት ት/ቤት አባላትን በዚያው ያሉትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት የሆኑትን የማህብረ ቅዱሳንን አባላት ጠይቋቸው መችም ማህበረ ቅዱሳን ሲነሳ የያዛችሁ የበርሃ ዛር ያስጎራችኋል አይዟችሁ ቻል አድርጉት ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቸም ውሸታችሁ ተነግሮ አያልቅም መቸ እውነት እንደምትናገሩ እግዚአብሔር ይወቀው ውሸት::በዚያው ያሉትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት የሆኑትን የማህብረ ቅዱሳንን አባላት ጠይቋቸው መችም ማህበረ ቅዱሳን ሲነሳ የያዛችሁ የበርሃ ዛር ያስጎራችኋል አይዟችሁ ቻል አድርጉ you said thrue and thrue,

   Delete
 3. መቸም ውሸታችሁ ተነግሮ አያልቅም መቸ እውነት እንደምትናገሩ እግዚአብሔር ይወቀው ውሸት 1. አቡነ ማርቆስ በስነ ምግባር ያባረሩትን መንኩሴ ያላችሁት ወጣቱ አዛውንቱ አይነኩብንም እያለ የዋሻው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ማህበረ ምዕመናን አቡነ ማርኮስን አንፈልግም እያለ መንኩሴውን ግን ማንም እንዳይነካቸው ብሎ ህዝቡ ባንድነት ተነስቶ ሳለ መነኩሴው በራሳቸው ፈቃድ የአቡነ ማርቆስን ጥላቻ በመሳቀቅ ጥለው ሄደዋል ደግሞ እኛ ምስክር ነን ፡ዋሻው ቅዱስ ሚካኤልን የመሰለ ካቴድራል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያሰሩ ጠንካራ አባት ናቸው፡፡ ከፈለጋችሁ ወጣት የሰነበት ት/ቤት አባላትን በዚያው ያሉትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት የሆኑትን የማህብረ ቅዱሳንን አባላት ጠይቋቸው መችም ማህበረ ቅዱሳን ሲነሳ የያዛችሁ የበርሃ ዛር ያስጎራችኋል አይዟችሁ ቻል አድርጉት ፡፡

  ReplyDelete
 4. አውደ ምህረት ከዚህ በፊት ስለ አባ አብርሃም እንዲህ ጽፋ ነበር
  አባ አብርሃም ኢየሱስ አያዋጣም አሉ!!

  በሀረር ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሦስት ቀናት የቆየ እጅግ ደማቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሂዶ ነበር። በወንጌል ወዳድነቱ የሚታወቀው የሐረር ህዝብ በሶስቱ ቀን ጉባዔ በከፍተኛ ሁኔታ የተገኘ ሲሆን በጉባኤው ሰዓት የክልሉ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ አብርሃም አገልጋዮቹን ጠርተው “…ይሔ ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉት የሚያዋጣችሁ አይመስለኝም። ብትተዉት ይሻላል።” በማለት ተናገሩ።
  የአባ አብርሃም የጉድ ሙዳይ በከፈቱት ቁጥር በውስጡ የተደበቀ ነገር እየወጣበት ከማስደነቅ አልፎ ማሳዘን ከማዛዘንም አልፎ ማስደንገጥ ጀምሯል። ይህ ንግግራቸው ሰውየው በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያላቸው አጀንዳ ምንድን ነው? አሰኝቷል። ህሊናቸውን ተጠቅመው የሚያደርጉት ነገር እንደሌለ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከሰጣቸው ተልዕኮ ውጭም ሌላ አጀንዳ እንደማይታያቸው ያሳየው እንዲህ ያለው ንግግራቸው ከወንጌሉ እውነት ውጭ መስማት በማይፈልገው የሐረር ሕዝብ ፊት እንዲፈጸም በማዘዛቸው ትዕዛዛቸው ሳይሳካለት ቀርቷል። ከዛም በኃላ ደግሞ የደብሩን አስተዳዳሪ ጠርተው “…ይሄ ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉትን የማያዋጣ ጉዞ መቸ ነው የምትተዉት?...” ሲሉ ለመውቀስ ሞክረዋል።

  ስለ ጽድቅ ስለ ኃጢአትና ስለ ፍርድ አለምን ይወቅሳል የተባለው የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ እንዳያገኛቸው ከመንፈስ ቅዱስ የሆኑ መልዕክቶችን በመግፋት የሚታወቁት አባ አብርሃም ካፈርኩ አይመልሰኝ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማያዋጣቸው ደጋግመው መናገር ይዘዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ካላዋጣ የሚያዋጣው ማን ይሆን? ማኅበረ ቅዱሳን? ወይስ በቆብ ተሸሽገው ቆብ ገልጠው የሚገቡት አባ አብርሃም?
  ለነገሩ ክርስቶስ የመጠላቱ ሚስጢር ገብቶናል። ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “…ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤” ብሎ በጻፈው የእውነት ቃል እንደሚያረጋግጥልን ብርሃን የሆነውን ጌታችንን ስሙን መጥራት ራሱን ለጨለማ ሀሳብ ላስገዛ ሰው ይከብዳል። አባ አብርሃም እውነታቸውን ነው ክርስቶስ ብርሃን ነው። የጨለማን ሥራ ያስወግዳል። በጨለማ ስራ ለመኖር የሚፈልግ ግን የብርሃንን መልዕክት መሰማት አይፈልግም። እሳቸውም ካሉበት ቦታና ድርጊት አንጻር ስለ ብርሃን ጌታ መስማት አይፈልጉም። ነገሩ በአንድ ወቅት አንድ ጸሀፊ “ኃጢአትም ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስም ከኃጢአት ይጠብቃል።” እንዳለው ሆኖባቸው ነው።
  አባ አብርሃምን በምን እንምንከተላቸው ግራ ገብቶናል። ከሃይማኖት ሃይማኖት የላቸው። ከምግባር ምግባር የላቸው። ከአስተዳደር ችሎታ የአስተዳደር ችሎታ የላቸው። ከእውነት እውነት የላቸው። ከህዝብ ፍቅር ራሳቸውን ካስገዙላቸው የማቅ ሰዎች ውጭ የሚወዳቸው የለ። በገንዘብ ፍቅር በሴት ፍቅር በሥልጣን ፍቅር… የተያዙ ሰው ናቸው። የሞነኮሱ ለት ስርዓተ ግንዘት የተፈጸመላቸው ለዓለም እና ለምኞቱ እንዲሞቱ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ነገሮች ሞተው ለአለማዊ ነገሮች ህያውነትን ለማግኘት ሳይሆን አይቀርም። ምን… ችግር እኮ ነው እነ ደብተራ አስቻለው የማይሰሩት የለ!!
  ከሁሉ ከሁሉ የከፈፋው ጉድና ጉድለታቸው ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እንዲህ አድርገው መጥላታቸው ነው። ይህ ተግባራቸው እጅግ የሚያሳዝንና ሰውየው በመዳናቸው ጉዳይና በመንግስተ ሰማያት ተስፋ ቆረጡ እንዴ? ያሰኘ ነው። አሁን ያሉበትም ሁኔታ እነደ ሥጋዊ ሰው እንኳ በማንነታቸውና በጤንነታቸው የሚያስመካ አይደለም እና የጌታችን የኢየሱስ ክርቶስም ደም ከኃጢአት ሁሉ ነፃ እንደሚያወጣቸው አውቀውና አምነው ንስሐ በመግባት ፊታቸውን ወደ እርሱ ዘንበል ቢያደርጉ የተሻለ ነው እንላለን።
  ብቸኛ የድኅነት አማራጭ መሆኑን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሙላት ያረጋገጠውን ክርስቶስ አያዋጣም ማለትን እንኳን እሱን አገለግላለሁ የሚል ጳጳስ ምዕመንም ሊናገረው የማይገባ ክህደት ነው። ለክብሩ የማይደራደረው ጌታን እያመለክን እኛም ብንሆን ለክብራችን መደራደር አይገባንም። ሚሥጢር ገላጩ ጌታ በመንፈሳዊነት ካባ ኃጢአት ሲያደባ ምን እንደሚመስል ተራ በተራ እያሳየን ነው። አባ አብርሃምን የተንጠለጠሉበት ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው የሸንበቆ ዛፍ ከምንም አያስጥሎትም እና ወደ እውነተኛው እና አስተማማኙ የወይን ግንድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲጠጉና ከዘላለም ጥፋት እንዲመለሱ በአደራ ጭምር እናሳስባለን።

  ReplyDelete
 5. tesfa mekuret yhin yanagiral. ayferedibachum

  ReplyDelete
 6. wow, thank you guys for great and wonderful info. please continue update us regarding our church racist leaders to know what the doing every day ........

  ReplyDelete
 7. ergetegna negn metefiyachu dersoal yabatun hafret yegelete....

  ReplyDelete
 8. እኔስ አልገባህ ያለኝ ነገር፣ ለምንድን ነው የጐንደር ቄስ በጐጃም ቄስ ያመጸው?

  ReplyDelete
 9. https://silverdam.wordpress.com/2013/06/24/photo-pastor-and-choir-mistress-caught-having-sex-inside-church/

  ReplyDelete
 10. መቼም አንዳንድ ህሊና ለሌላቸዉ ሰዎችና እንደ አባታቸዉ እንደ ዳቢሎስ የሃሰት አባት የሆኑትን ሰዎችን መተዉ እንጂ መልስ መስጠት አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን አንዳንድ ግዜ ግድ ይልና በዝርዝር መግለጽ ባያስፈልግም አንድ ነገር እንድንል ህሊናችን ያስገድደናል

  ብጹዕ አቡነ አብርሃም እዚህ ሰሜን አሜሪካ በነበሩበት ግዜ ባዬሁት የአገልግሎት ትጋታቸዉና ላመኑበት ነገር በጽናት የሚቆሙ አባት ነበሩ ለራሳቸዉ ምቾት እንኩን አይጨነቁም አንተ እንደምትለዉም ዘረኛም አይደሉም የሁሉም አባት ነበሩ ካህናት እንኩን ለአገልግሎት ሲጠሩ የኮኔክሽን በረራ ካለዉ ቅር በሚልባቸዉ በአሜሪካን ሃገር እርሳቸዉ ለአገልግሎት የህዝብ ትራንስፖርት ሳይቀር እየተጠቀሙ ረጅም መንገድ ሲጘዙ ቅር የማይሰኙ አባት ነበሩ

  እረ እንዳዉ እዉነት እንነጋር በዚች ምድር ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ የምንኖረዉ እግዚአብሔርን እንፍራ እንዲህ ያለ የሀሰት ወሬ በማራባታችን ምን ይሆን የምናገኘዉ እባካችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱና በጎ የሆነዉን ነገር እንስራ

  ፀሃፊዉንም ከእንደዚህ ካለዉ የሀሰት አባት ከሆነዉ ከዳቢሎስ ቁራኝነት ያላቅህ
  አሜን

  ReplyDelete
 11. ዋሻው ቅዱስ ሚካኤልን የመሰለ ካቴድራል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያሰሩ ጠንካራ አባት ናቸው፡፡ ከፈለጋችሁ ወጣት የሰነበት ት/ቤት አባላትን በዚያው ያሉትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት የሆኑትን የማህብረ ቅዱሳንን አባላት ጠይቋቸው መችም ማህበረ ቅዱሳን ሲነሳ የያዛችሁ የበርሃ ዛር ያስጎራችኋል አይዟችሁ ቻል አድርጉት ፡፡

  ReplyDelete