Tuesday, June 4, 2013

ሲኖዶሱ አባ ኤዎስጣቴዎስ ላይ ውሳኔ አሳለፈ፤ የእስክንድርን ቢሮ አጠፈ፤ አለቦታው የተቀመጠውን ተስፋዬ ውብሸትን ከምክትል ስራ አስኪያጅነቱ አነሣ

Read in PDF

ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው ስብሰባ በወሲብ ቅሌት ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ የተባረሩት አባ ኤዎስጣቴዎስ ወደአገር ቤት ተመለስውና በሲኖዶስ ፊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ እንዲያስረዱ ካልሆነ ግን እንዲወገዙ ውሳኔ ማሳለፉ ተነገረ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው አባ ኤዎስጣቴዎስ ስለፈጸሙት የወሲብ ቅሌት ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ በውጭ በሚገኘው ሀገረ ስብከት በኩል በደብዳቤ ለቤተክርስቲያኗ ስለ ተጻፈ መሆኑ ታውቋል፡፡ ውሳኔው ለሌሎቹም አስተማሪ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን እንዲህ ተጽዕኖ ሊፈጥር የሚችል ደብዳቤ ካልተጻፈስ በቀር በሴት ጉዳይ የሚታሙና ሚስት አግብተው ጭምር እንደተቀመጡ በስፋት የሚወራባቸው ጳጳሳት ላይጠይቁ ነወይ? የሚል ጥያቄን አጭሯል፡፡ አባ ኤዎስጣቴዎስ በዚህ ውሳኔ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገቡ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም አባው በአቡነ ጳውሎስ ዘመን አሜሪካ ተልከው በዚያው የቀሩ በመሆናቸውና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልገኝም ወደአገር ቤትም አልመለስም ብለው መወሰናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ጥገኝነት ጠይቀው ይሁን ወይም አይሁን ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም፡፡ የግንቦቱ ሲኖዶስ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ አባ ኤዎስጣቴዎስ ተመልሰው እንዲመጡና ስለተከሰሱበት ጉዳይ እንዲያስረዱ መወሰኑ ትልቅ አጣብቂኝ እንደሚሆንባቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ወደአገር ቤት መመለስ ለእርሳቸው ትልቅ ሽንፈት እንደሚሆን ሲጠበቅ አለመምጣትም ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋል፡፡ የመጀመሪያው መወገዝ ሲሆን፣ ሁለተኛ ሊሆን የሚችለው በተመሳሳይ ጥፋት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደተደረጉትና “አሜሪካን ረግሜያት ነው የመጣሁት ፊቴን ወደእርሷ አላዞርም” እያሉ እንደሚያስወሩት አባ ሳሙኤል አይነት እጣ እንደሚጠብቃቸው የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ አባ ኤዎስጣቴዎስ የቱን ይመርጡ ይሆን? የሚለውን አብረን የምንከታተል ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሐራና መሰሎቿ ይህን ትልቅ ዜና እንዳልሰማ ሆነው አልፈዉታል መሰል በጉዳዩ ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡
በሌላም በኩል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተብሎ የተከፈተውና አቶ እስክንድር በአንድ በኩል የአመጽ ትርፍ ሲያጋብስበት በሌላ በኩል የማቅን ተልእኮ ሲያስፈጽምበት የነበረው መምሪያ እንዲታጠፍ ተወስኗል፡፡ በቅርቡ እስክንድርና ተስፋዬ ውብሸት በ“መጽሔት እናሳትማለን” ስም ስፖንሰር ሁኑን ብለው ለአድባራት የበተኑት ደብዳቤ በሌላ ደብዳቤ የተሻረ መሆኑ ሲታወቅ፣ ከጥቂት አድባራተወና ከአንዳንድ የንግድ ተቋማት ማስታወቂያና ባገኙት ገንዘብ ዜና ቤተክርስቲያን የተሰኘ መጽሔት በቀለምና ደረጃውን በጠበቀ ወረቀት ያሳተሙ ሲሆን፣ ተስፋዬ ውብሸት  “ለተጠናከረ የህዝብ ግንኙነት ሥራ በጋራ እንረባረብ” በሚል ርእስ በስሙ በወጣው ጽሁፍ የግብር ወንድሙን የእስክንድርን መምሪያ አንቆለጳጵሶ የጻፈለት ቢሆንም፣ ሲኖዶሱ ግን ለጥሪው ምላሽ ባለመስጠት መምሪያው እንዲታጠፍ ወስኗል፡፡ ተስፋዬንም ከምክትል ሥራአስኪያጅነቱ አንሥቷል፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳን የሁለቱ ሰዎች መነሳት ትልቅ ክፍተት እንደሚፈጥርባቸው የሚጠበቅ ሲሆን፣ እስክንድር ጥቅሙን ለማስከበር የማቅን አላማ ከማስፈጸም ወደኋላ ብሎ የማያውቅ መሆኑ ሲታወቅ በተጠቀሰው መጽሔት ላይ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ካቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተለው ይገኛል፡፡
“ቅዱስነትዎ በተለያዩ አጋጣሚዎች አጋጥሞዎት ከሆነ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም አህጉረ ስብከት የህገ ወጥ ሰባክያን፣ ዘማርያንና የጉዞ ማኅበራት ቁጥር እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ለመስበክ ፈቃድ  ያልተሰጣቸውና በሞያው በቂ እውቀት ያልያዙ ሰዎች መተላለፍ የሌለበት መልእክት ለምእመናን ያስተላልፋሉ፤ ዘማርያንም እንደዚሁ በሊቃውንት ያልተመረመሩና የዜማ ስርአታቸውን ያልጠበቁ መዝሙሮችን በየዓውደ ምሕረቱ ይሸጣሉ፡፡ የጉዞ ማኅበራት ጉዳይም ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህን ህገ ወጦች መስመር ለማስያዝ ቅዱስነትዎ የሚያስተላልፉት አባታዊ መልእክት ካለ”

ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲመልሱ “እንደ እውነቱ ከሆነ ቤተክርስቲያንዋ ሳታውቀው የሚንቀሳቀስ አካል መኖር የለበትም፡፡ የሚጎበኙት፣ የሚታዩት ገዳማትና ቅርሳ ቅርሶች የቤተክርስቲያንዋ ናቸው፡፡ ስለዚህ ንብረቶቿ በራሷ ሰዎች መሪነት ወይም መብትና ፈቃድ በሰጠቻቸው ሕጋዊ አካላት ካልሆነ በስተቀር በሌላ መከናወን የለበትም፡፡ በእርግጥ እዚህ ላይ የእኛም ድክመት አለበት፡፡ ስለሆነም ለወደፊቱ ቤተክርስቲያናችን ቅርሶቿንና መብቷን ለማስጠበቅ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡”  (ገጽ 9)

ልብ ይበሉ! እስክንድር ብዙ የለፈፈው ማቅ “ሕገወጥ” ስላላቸው ሰባክያንና ዘማርያን ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ደግሞ ትኩረት የሰጡት ለቅርሶችና ገዳማት ነው፡፡ ወይ አለመገናኘት! ለሁሉም ቻዎ ቻዎ ተስፋዬና እስክንድር! 

9 comments:


 1. ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተመርጠዋል፤ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ኾነው ተሠይመዋል

  ReplyDelete
 2. ሃሜተኛዋ ፅጌ የሃይለ ሰይጣን የጭን ገረድ አንሸቺስ የአቡነ ሉቃስንና የአቡነ ማቴዎስን መሾም ምነው እንዳላየ አለፍሽ። ገልቱ ሃሜተኛ።

  ReplyDelete
 3. የሰውን ሃጢያት ለመዘርዘር ጊዜ ጣጣላችሁ ምነው ፓትርያሪኩ ስለ ሙስናና በዘመድና አድሎ ስለሚሰሩት ነገሮች የተናገሩትን በትንታኔ አላቀረባችሁም፡፡ የሲኖዶስ ስራ አስኪያጅና ጸሀፊ መመረጣቸውን ምነው አለመዘገባችሁ ለናንተ ስለማይጠቅማችሁ ነው፡፡ የሰዎችን ሚስጥር በመናገር መንግስተ ሰማያት የሚገባ ቢኖር እናንተን የሚቀድም የለም ሲኦል ለመግባትም እየፈጠናችሁ እንደሆነ እያወቃችሁ፡፡የሰውን ሃጢያት ለመዘርዘር ጊዜ ጣጣላችሁ ምነው ፓትርያሪኩ ስለ ሙስናና በዘመድና አድሎ ስለሚሰሩት ነገሮች የተናገሩትን በትንታኔ አላቀረባችሁም፡፡ የሲኖዶስ ስራ አስኪያጅና ጸሀፊ መመረጣቸውን ምነው አለመዘገባችሁ ለናንተ ስለማይጠቅማችሁ ነው፡፡ የሰዎችን ሚስጥር በመናገር መንግስተ ሰማያት የሚገባ ቢኖር እናንተን የሚቀድም የለም ሲኦል ለመግባትም እየፈጠናችሁ እንደሆነ እያወቃችሁ፡፡

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማ እናመሰግናለን በርቱ ወንድሜ ማቅ የደበቀውን እውነት ስላወጡት ተበሳጨህ እንዴ?

  ReplyDelete
 5. Given the investigative report posted by Aynalem Gizaw of Jerusalem regarding Patriarch Matias' past, particularly his relations with ladies in Jerusalem and Washington DC, what moral authority would the New Patriarch have to pursue Aba Ewsttatewos' case to a just conclusion? This is a very important question, as whether or not the Patriarch has repented for his publicly acknowleged tresspasses remain unknown.

  ReplyDelete

 6. Anonymous June 4,2013 at 10:49 pm, Please repent what you said about Kidusnetachew is totally immoral and wrong I don't think you ever seen him, or known him, he is human being like me and you blood and flesh, he might did mistakes but not adultery, the way you mention or any, so please ask forgiveness from almighty God. We know him for almost 24 years and never seen or heard such thing about him of curse lot of women serve our fathers mostly abroad, that does not mean anything than showing how our women loves our church since apostles time.

  ReplyDelete
  Replies
  1. why women have to serve them ? why not men? the only way to get women around them is to do adultery. Men can do cooking and other house hold stuff too. Ethiopian women are raped and forced to be used by them and said nothing. You Ethiopian sisters, mothers, and daughters you have to respect yourself by saying no and stopping them from doing this to you.

   Delete
  2. It is good if your know him for the past 24 years. Yes I will say you are right only if your were with him for 24 hours a day for the last 24 years. All of them have a greater opportunity to do adultery than any other regular man. Because, women are around them all the time to do cooking, cleaning and even getting closer to them when women are there to make their beds. Please stop saying you know him for 24 years.

   Delete
 7. የምትጽፉት ነገር በጣም ያሳዝናል!
  ምነው ቢቀርባችሁስ!ምንም ቁምነገር ለሌለው ነገር ጊዜ ማባከን
  እኔ ግን ሁለተኛ የናንተ ጽሁፍ ላለመማንበብ ወስኛለሁ

  ReplyDelete