Thursday, June 6, 2013

ሰሚ ያጣው የጉጂ ቦረና ሃገረ ስብከት ምእመናን አቤቱታ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ

ምእመናኑ ለጥያቄያቸው ምላሽ ካላገኘ አብያተ ክርስቲያናቱን በገለልተኛ
አስተዳደር ለማስተዳደር እንደሚገደዱ አስታውቀዋል
“በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንደሚባለው ማኅበረ ቅዱሳን እያመሳቸው ካሉ አህጉረ ስብከቶች አንዱ የሆነው የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት በጥቂት የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎችና ከእነርሱ ጋር ትስስር በፈጠሩት አባ ገብርኤልና በቤተክህነት ሥራ አስኪያጆች ምክንያት ከአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ጀምሮ እስካሁን ድረስ እየታመሰ ይገኛል፡፡ ምእመናኑ “ከጉጂ ቦረና ሊቀ ጳጳስ ጀምሮም ስራ አስኪያጁና አንዳንድ የወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጆች ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለአንድ ማኅበር ህልውና የሚደክሙ መሆናቸውን” ቢገልጹም፣ ለአቤቱታቸው እየተሰጣቸው ያለው ምላሽ አታካችና ተስፋ አስቆራጭ እየሆነባቸው ስለመጣ ግንቦት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. በጻፉት ማመልከቻ በመንግስት በኩል በተደረገው ማጣራትና በቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ መሠረት ጥያቄያቸው የማይመለስ ከሆነና ገለልተኛ ሊቀ ጳጳስ ካልተመደበላቸው ሥር የሰደደው ችግራቸው እስኪቀረፍ ድረስ ሁኔታውን በቅርብ ለሚከታተለው ለመንግስት አሳውቀው አብያተ ክርስቲያናቱን በገለልተኛነት ለማስተዳደር የሚገደዱ መሆኑን አሳወቁ፡፡ ለሲኖዶሱ አስደንጋጭ የሆነው አቤቱታም ይኸው መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ምእመናን ተወካዮች በደብዳቤያቸው እንደገለጹት አባ ገብርኤል ሙሰኞችን፣ የብዙዎች እንባ ያለባቸውንና የችግሩ ዋና አካላት የሆኑ ግለሰቦችን በመሾምና እድገት በመስጠት ችግሩን እያባባሱት የሚገኙ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ግለሰቦቹ ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለማቅ የቆሙ መሆናቸውንም አጋልጠዋል፡፡ አመልካቾቹ ወደዚህ ውሳኔ ያደረሳቸው ሲኖዶሱ በተደጋጋሚ ላቀረቡት አቤቱታ ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ እነ ተስፋዬ በሸፍጥ ለማደናቀፍ የሞከሩትን የማጣራት ሂደት የመንግስት አካለት በራሳቸው አጣርተው መፍትሔ አቅርበው ባለበት ሁኔታ ያን ወደ ጎን ትቶ ሌላ የቤተ ክህነት አጣሪ ኮሚቴ ለመሰየም መንቀሳቀሱ መሆኑ በአቤቱታው ተመልክቷል፡፡  ይህን ድርጊትም “በጣም አሳዛኝና በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የተንቀሳቀሰውን መንግስትንም መናቅ ነው፡፡” ሲሉ የገለጹ ሲሆን “በተደጋጋሚ ለብቻው ሄዶ ውጤት ያላመጣውን የቤተ ክህነት አጣሪ ኮሚቴ መልሶ መላክም ሰቆቃችንን ማራዘም ነው፡፡” ሲሉ አማረዋል፡፡ የቤተ ክህነቱ አጣሪዎች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ሁሉ “አሁንስ ብቻቸውን ቢመጡ ፍርድ እንደማያጣምሙ ምን ዋስትና አለን? አጀንዳቸው እውነቱ ከሆነ ለምን ከመንግስት ጋር መሥራቱ አስፈራቸው?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

እንደሚታወሰው በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ጉዳዩን እንዲያጣሩ ከቤተክህነትና ከመንግስት በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የፌደራል ጉዳዮች ያሉበት ኮሚቴ የማጣራቱን ሥራ እያከናወነ የነበረ ሲሆን፣ የአቡነ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት ሲሰማ ግን ጉዳዩ መቆሙን ጠቁመዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በቤተ ክህነቱ በኩል ከኮሚቴው አባላት ተሰናባቹ ተስፋዬ ውብሸት “አቡነ ጳውሎስ ከሞቱልንማ ማኅበረ ቅዱሳንን ማን ይነካዋል?” በሚል ራሱንና ሌሎችን የቤተክህነት የኮሚቴ አባላት ወደኋላ በመጎተት የተዋቀረው ኮሚቴ ስራ እንዲጓተት ማድረጉ ታውቋል፡፡ ከመንግስት በኩል የኮሚቴው አባላት ስራችንን እንቀጥል ቢሉም ተሰናባቹ ተስፋዬ ግን ፈቃደኛ ሊሆን ባለመቻሉና በልዩ ልዩ ምክንያት ወደኋላ በማፈግፈጉ በመንግስት በኩል የማጣራቱ ሂደት ቀጥሎ በአሁኑ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ሪፖርት መቅረቡ ተሰምቷል፡፡ በሪፖርቱ መሠረት የችግሩ አካላት የሆኑት አመራሮች ተነስተው ገለልተኛ አመራሮች ቢቀመጡ መፍትሄ እንደሚገኝ ተጠቁሟል ተብሏል፡፡ መንግሥት በጉዳዩ አጣሪ ሆኖ እንዲገባ የተደረገው በቤተክህነቱ አጣሪዎች በኩል ምንም መፍትሔ መቅረብ ስላልቻለና ችግሩ እየተባባሰ ስለመጣ፣ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ምእመናን እስከዛሬ በጻፏቸው ማመልከቻዎች ለመንግስት አካላት በግልባጭ እያሳወቁ ስለመጡና ጉዳዩ ከአካባቢው ጸጥታ ጋር ስለሚገናኝ መሆኑ ታውቋል፡፡

  


11 comments:

 1. መንፈሳዊ አስተዳዳሪዎች ቶሎ መስማት ካልጀምርን እና ላስተዳደር አፋጣኝ መፍትኄ
  ማምጣት ካልቻልን ፤ ችግሩ የችግሩ መንሥኤና መፍትኄው እየረቀቀ እየተደበቀ ይመጣና
  ዕንቈቅልሽ ሆኖ ቀጣይ የሆነ መለያየትን ያመጣል አስቀድሞ እንደታየ We have to
  be wise how to see things in the church.

  ReplyDelete
 2. YAsazenal!! hezbe eyalekese esemeche?

  ReplyDelete
 3. That's fake. Whose stamp is that? If that is a formal stamp the identity of the writer should be explicit. That's an indication for a hidden agenda.

  ReplyDelete
 4. lib Enkirt Yimegnal Alu kkkkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 5. ይህ የሚያሳዬዉ ቤተክርስቲያናችንን ለማመስ ምን ያህል እንደሄዳችሁና በዉጩ አለም እንዳለዉ ለሆዱ አዳሪ የቤተክርስቲያን አስተዳደር በየቦታዉ ለመፍጠር የምታደርጉት ጥረት አካል ነዉ

  መቼ ይሆን ከቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን አንስታችሁ ለነፍሳችሁ የምትተጉት በየቦታዉ ጽድቅ ሳይሆን ስልጣን የሚሻ ቡድን አየፈጠራችሁ መሄድ የምታቆሙት

  እረ እባካችሁ እግዚአብሔርም ፍሩ

  ReplyDelete
 6. Yihe ye Mahibre kidusan sira sayihon yenante ye tehadisowochu sira new. yilikunis Memire zinabu hulet mist emdalewuna, ye huletegna mistun lij Kibremengist sillase bete kiristiyan be merigeta Lisanework amakagnimet kirisitina masnesatun lemin atigeltsutim. Egna Ye Guji akababi sewoch alamachihun hulu awkenal demo yegosachinin sim astekakilachihu tsafu. DEDEBOCH egna GUJI enji GOJI ayidelem simachin.

  ReplyDelete
 7. so sorry for gugi borena church

  ReplyDelete
 8. ሊቃነ ጳጳሳት እና የየሀገረስብከቱ ሥራ አስኪያጆች ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ 7ሚሊዮን የኦርቶዶክስ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን ሲለውጡ እንቅልፋቸውን ሲለጥጡ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ጨርሶ በማሾፍ የአስተዳደሩን ሁሉ ነገር ራሳቸውንም ጭምር ለማኅበረቅዱሳን በመስጠት በቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ ናቸው፡፡ የቦረና ሀገረ ስብከት ብቻ ሳይሆን፣ ሀዋሳ ፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ሐረር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ሌሎችም ከተሞች ያሉ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የሲኖዶስን የግፍ አገዛዝ በመቃወም ነጻ ቤተክርስቲያናትን ለመመሥረትና ገለልተኛ አስተዳደር ለመመሥረት መዘጋጀታቸውን ልብ ልንል ይገባል፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኝ ለመባል የግድ የአቡነ ገብርኤልን፣ የአቡነ አብርሃምን ወይም የአቡነ ሉቃስንና የመሳሰሉትን የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪዎችን ቡራኬ መጠበቅ ግድ ላይል ይችላል፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡

  ReplyDelete
 9. Who the hell is "mahibre Kidusans"? Are they over the Synod? where ever they go they incite problems. Churchs in America turned them off in search of peace. Dallas, DC, Atlanta, LA, Houston and many cities perhps Europe and Australia too. Who gave them the mandate to jude and police others? Who is this Decon Daniel who spins the members to the Tewahido Jahad. We got to stop them and search the true Tewhido teachings.

  ReplyDelete
 10. MAY GOD BLESS THIS BLOG! AMEN!!!! I HAD THIS VIEW ABOUT TAHDESSO THAT IT WAS ANTI TEWAHIDO. DARN WRONG I WAS! I LET MYSELF BRAIN WASHED BY SOME MEMBERS OF MK IN OUR SUNDAY SCHOOL.

  ReplyDelete
 11. ማኅበራት ነን እያሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንት የሚያቃልሉ ከዚያም አልፈው ለማሳደድ
  ሙከራ የሚያደርጉ ከለት ወደለት እየጨመሩ በመሄድ ላይ ናቸው። ይባስ ብለው በየደረሱበት የሽብር ሥራ በመተግበር ላይ ይገኛሉ እንደነዚህ የመሳሰሉ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ተቆቋሪዎች ሳይሆኑ
  ተቀርቃሪዎች ናቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ከኔ ጋር የማይሆን ይበትናል እንዳለው የሰውን አንድ ሐሳብ
  ወደ ብዙ ለመበታተን ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች አይዶሉም ራዕ ዮ.2.2-3
  ሳይሆኑ ነን የሚሉ በጥባጮች(መሀውካን)ናቸው ይለናል ማሥታገሻውን ያውርድላቸው!

  ReplyDelete