Friday, July 5, 2013

ተሐድሶ እና የፓትርያርክ ለውጥ

ተሐድሶ የእግዚአብሔር ሐሣብ መሆኑ በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡ ፀረ ተሐድሶ የሆኑት እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉት “ፕሮቴስታንታዊ” የሚል ዘርፍ አበጅተውለት ቢያጣጥሉትም፣ የቤተክህነት ምንደኞችም “መናፍቃን” ከሚል ቃል ጋር አዛርፈው ለማስጠላት ቢሞክሩም ተሐድሶ ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ሐሣብ ላይ ለሚነሣው የሰው ሐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላፈነገጠውና በኑፋቄ አረም ለተዋጠው የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ስርአት፣ አስተዳደራዊ ጉድለት ሁሉ ተሐድሶ ያስፈልጋል፡፡ ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኗ ቃሉን ስትጠቀም የምትታየው በተገቢው ጊዜና ሁኔታ ሳይሆን አንድ ፓትርያርክ በሞት ወይም በፖለቲካ ምክንያት መንበሩን ሲተው ወይም ሲታገድ ብቻ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በራሷ ፓትርያርክ መመራት ከጀመረችበት ጊዜ አንሥቶ “ተሐድሶ” የሚቀነቀነው በዋናነት አንድ ፓትርያርክ በሞት ሲለይና ሌላው ሲተካ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ ከብዙ ምእተ ዓመታት ትግል በኋላ የራሷን ፓትርያርክ በሾመች ጊዜ ማለትም በ1951 ዓ.ም ሁኔታው የቤተክርስቲያን መታደስ እንደተባለ በዚያ ዘመን የተጻፉ ጽሑፎች ይመሰክራሉ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የወንጌልን እውነት የተረዱ ስለመሆናቸውና ቤተክርስቲያንን ወደ መንፈሳዊ ተሐድሶ ለማምጣት ያደረጉት ጥረት ስለ መኖሩ ግን መናገር የሚቻል አይደለም፡፡ በዘመናቸው የተወሰዱ አንዳንድ የተሐድሶ እርምጃዎች መኖራቸው ባይካድም ያን ያህል ለውጥ አምጥተዋል ማለት አይቻልም፡፡ ለዚያም ነው አቡነ ቴዎፍሎስ በእርሳቸው እግር ተተክተው ፓትርያርክ ሲሆኑ ለቤተክርስቲያን ተሐድሶን ያመጣሉ ተብሎ ብዙ የተባለላቸው፡፡ በተለይም በተሾሙ ጊዜ የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የተሰኘው የመንግስት ጋዜጣ እንዲህ ሲል ዘግቦ ነበር፤ “የሌሎች አገሮች አብያተ ክርስቲያኖች እንደ ታደሱ ሁሉ የእኛም እንደ ዘመኑ መራመድ ይኖርባታል። የአሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች አስተሳሰብና የሃያኛው ክፍለ ዘመን ፍልስፍና በጣም የተራራቀና የተለያየ ስለ ሆነ ሊያሳምን በሚችል በአዲስ ዘዴ መቅረቡ የተሻለ ውጤት ያስገኛል። ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ይህን ሁሉ በማመዛዘን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ፣ በአሠራር፣ በአስተሳሰብና በአፈጻጸም የታደሰችና የዘመኑን ሥርአት የተከተለች እንደሚያደርጓት ከፍተኛ ኀላፊነት ይጠብቃቸዋል” (የሚያዝያ 2/1963 እትምን ይመልከቱ)፡፡

በእርግጥም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ብዙ የተሐድሶ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ በአይን የሚታዩና በእጅ የሚዳሰሱ በርካታ የለውጥ ሥራዎችንም ሰርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ደርግ አድኃሪ ብሎ ከንጉሡ ጋር በመፈረጅና ለቤተክርስቲያኗ ተሐድሶ እንደሚያስፈልግ በማወጅ “የተሐድሶ ጉባኤ” የሚል ስብስብ ቤተክህነት ውስጥ አቋቁሞ እርሳቸውን አስወገደ፡፡ በእርሳቸው እግር የተተኩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በተሾሙ ጊዜም ይኸው የፈረደበት ተሐድሶ እንደገና መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አንዳንድ ጽሑፎች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ በ1971 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ያጸደቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ ስለ ስብከተ ወንጌል በሚናገረው በክፍል ሁለት በተራ ቁጥር 1 ላይ "በቤተ ክህነት በኩል ያለው አስተዳደር በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመራና ተሐድሶ የሚታይበት እንዲሆን ያስፈልጋል" ብሏል (ትንሣኤ መጽሄት ቁጥር 20 የካቲት 1971 .ም ገጽ 14)፡፡

ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በአገር ቤት በነበሩበት የፓትርያርክነት ዓመታት ስለተሐድሶ የተነገረ የጎላ ነገር ባይኖርም፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኖሩበት ስርአተ መንግስት ሥር ስለ ነበሩ ከዚያው የቀጠለ ሁኔታ ነው የታየው ማለት ይቻላል፡፡

አቡነ መርቆሬዎስ ከስልጣን እንዲወርዱ ከተደረገና አቡነ ጳውሎስ በቦታቸው ሲተኩ እንዲሁ ተሐድሶ፣ ተሐድሶ ተብሎ ነበር፡፡ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 28 ቀን 1984 ዓ.ም ባደረገችው ፓትርያርካዊ ምርጫ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በካህናትና በምእመናን ከፍተኛ ድምጽ ተመርጠዋል፡፡ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የተሐድሶ መሠረት በጣሉበት ወቅት የመጀመሪያው ተመራጭ አባትና የተሐድሶውን መሠረት የመጣሉን ተግባር ከቅዱስነታቸው ጋር አብረው ያከናወኑ ሐዋርያ ስለ ነበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የተሐድሶ ተግባርን በብፁዕነታቸው ዘመነ ሲመት እንደሚቀጥል ስለ ተገመተ የምርጫው ዜና በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ያስተጋባውን ልባዊ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ተመራጭ ቃል አይገኝም፡፡ … በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የተሐድሶ መሠረት እንደ ገና ለመጣል ‘ኢትዮጵያ ታበጽሕ አደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር’ በተባለው መሠረት ዘወትር ለጸሎት የተዘረጉት የመላ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እጆች አላፈሩም፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ቀድሞ በትሩፋታቸው የሚያውቃቸውንና በተጋድሎአቸውም ወቅት ለአንድ አፍታም ያልተለያቸውን ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጳውሎስን ከስደት ጠርቷል፡፡ … ስለዚህ ‘ፀሓይ ሳለ እሩጥ አባት ሳለ አጊጥ’ እንዲሉ … ራስን በንስሓ አስተካክሎ ለትምህርተ ወንጌል ታጥቆ መነሣትና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ መዘጋጀት የብፁዓን አባቶች የመላው ካህናትና ምእመናን ወቅታዊ ግዴታ ነው” (፭ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ልዩ እትም 1984 ገጽ 3-4)።

በአባ ማትያስ የፕትርክና ዘመንም ተሐድሶ በሌሎች አገባቦች ወይም በተለዋጭ ስሙ “ለውጥ” ተብሎ እየተጠራና እየታወጀ ይገኛል፡፡ ይህም እንደ ተለመደው የቀደሙትን ፓትርያርክ የአባ ጳውሎስን ስራዎች ለማኮስመንና ለየት ብሎ ለመታየት በመሞከር የተጀመረ ቢመስልም አባ ማትያስ እውነተኛ ተሐድሶ በቤተክርስቲያኗ እንዲመጣ ለማድረግ ይሰራሉ ወይ የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ምክንያቱም በአሜሪካ ሳሉ አንዳንድ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ የስሕተት ትምህርቶች በግድ ኦርቶዶክሳዊ ናቸው ብለው ሲካሰሱ እንደነበር ከቀሲስ አስተርአየ ጋር የገቡበት እሰጥ አገባ እንኳ ምስክር ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊው ትምህርት ማርያም የከበረችና ጌታ እናቱ ትሆን ዘንድ የመረጣት ብትሆንም የሰው ዘር በመሆኗ ያለጥንተ አብሶ አልተወለደችም፤ ከእርሷ የተወለደው ጌታ ግን በመንፈስ ቅዱስ ግብር ስለ ተፀነሰና ስለተወለደ ጥንተ አብሶ ሳያገኘው ቅዱስ ሆኖ ያለኃጢአት ተወልዷል የሚል ነው፡፡ አባ ማትያስ ግን ይህን የኖረ ንጹሕ ትምህርት ነበር ሲቃወሙና ቀሲስ አስተርአየን እስከ ማገድ ደርሰው የነበረው፡፡ ሆኖም ሰሞኑን በሙስና ላይ የከፈቱት የተሐድሶ አዋጅ በራሱ መልካም ቢሆንም ብቻውን ግን የቤተክርስቲያንን ተሐድሶ ሊያመጣ ፈጽሞ የሚችል አለመሆኑ ስታለም የተፈታ ነው፡፡

ቤተክርስቲያን በፓትርያርክ ለውጥ ሰሞን ያለፈውን ለማንኳሰስና አሁን የመጣውን ለማወደስ በሚል ብቻ ተሐድሶ ተሐድሶ ማለት የለባትም፡፡ የቤተክርስቲያኗ ችግር ከመሠረቱ ሊታይ ይገባል፡፡ አሁን ለምትገኝበት ችግር የዳረጋት በዋናነት የአስተምህሮዋ መበረዝ ነው፡፡ የእምነት መግለጫዋ በሆነው በጸሎተ ሃይማኖት ላይ በልዩ ልዩ መንገድ የተጨመሩትና ጸሎተ ሃይማኖትን ያስረሱ በርካታ የስህተት ትምህርቶች የሞሉባት ቤተክርስቲያን ሆናለች፡፡ ይህ እየታወቀ ግን “እምነታችን ምንም ችግር የለበትም ችግራችን አስተዳደራዊ ነው” እየተባለ ነው፡፡ በመጀመሪያ ተሐድሶው መጀመር ያለበት ከቤተክርስቲያኗ መሠረታዊ ችግር ከአስተምህሮዋ ነው፡፡

የቀናው ትምህርት የሕይወት ለውጥን ሊያመጣ የሚችልና ፈሪሃ እግዚአብሔርን በሰዎች ልብ የሚያነግስ ነው፡፡ ለዚህም ወንጌል ከሌላ ትምህርት ጋር ሳይቀየጥ በግጽነት ሊሰበክ ሰዎች ኃጢአተኛ መሆናቸውን ሊያውቁ፣ መድኃኒቱም ስለኃጢአታቸው የሞተውና ዕዳቸውን የከፈለው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ሊያምኑ አምነውም በእርሱ ሊኖሩ ይገባል፡፡ አሁን ያለው ትምህርት ግን በዚህ የወንጌል እውነት ላይ ሙስናን የሚፈጽም ነው፡፡ በተለይም ማኅበረ ቅዱሳን እጅግ የሚያቀነቅነው ክርስቶስን ሳይሆን ቅዱሳንን የመስበክ አካሄድ በክርስቶስ የአዳኝነት ትምህርት ላይ ሙስናን መፈጸም ነው የሚሆነው፡፡ መዳን የሚገኘው በክርስቶስ ሆኖ እያለ በቅዱሳን በኩልም መዳን ይገኛል ብሎ ከመስበክ የከፋ ሙስናዊ ትምህርት የለም፡፡ ከዚህ የተነሳም ሰዉ በብቸኛነት በሚያድነው በክርስቶስ ቤዛነት አምኖ እንዳይድንና የጌታን ፈቃድ እየፈጸመ እንዳይኖር እንዳሻህ ብትሆንም እንኳን በቅዱሳን ምልጃ ትድናለህ እየተባለ መሰበኩ፣ በዚህ ትምህርት አንጻር ምግባሩ ከሙስና ያልራቀ ትውልድን ነው ያፈራው፡፡

የአዋልድ መጻሕፍት ስብከት ሰውን ንዝህላል እንደሚያደርግ ከቀድሞ ጀምሮ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በተረጎሙት የደቂቀ እስጢፋኖስ ገድል ላይ እንደተጠቀሰው ደቂቀ እስጢፋኖስ በመጀመሪያ አጼ ዘርአ ያዕቆብ የላከላቸውን ተአምረ ማርያም ወደቤተክርስቲያናቸው አላስገቡትም ነበር፡፡ “የተኣምረ ማርያምን ቅጂ ለደቂቀ እስጢፋኖስ ገዳምም ልኮ እንደ ነበረና ከቤተ ክርስቲያናቸው ሥርአት እንዳላስገቡት ምንጫቸው ይመሰክራል፡፡” ለማስገባት ያልፈለጉበት ምክንያትም የደቂቀ እስጢፋኖስ ተከታዮች ጭምቶችና በእግዚአብሔር መንገድ ለመጓዝ የሚፈልጉ ስለሆኑና በተኣምረ ማርያም ላይ ግን “ታላላቅ ኃጢአቶችን የሠሩ ብዙዎች ኃጢአተኞችን እንዳዳነቻቸው የእመቤታችንን በ፪ መንገድ ድንግል ቅድስት ማርያም ወላዲተ አምላክን ተአምር ሲሰሙ እነሱም ጻማቸውንና ገድላቸውን ትተው ንዝሕላሎች ይሆናሉ፡፡” የሚል ነው (ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ ገጽ 26)፡፡ እንደ ጌታ ፈቃድ ከመኖር ይልቅ እንደራስ ፈቃድ በመኖር በቅዱሳን ምልጃ መዳን ይገኛል ከማለት የበለጠ በእምነት ላይ የሚፈጸም ሙስና ከቶ ከየት ይገኝ ይሆን? ተሐድሶ ለፓትርያርክ ለውጥ የሚቀነቀን የአንድ ሰሞን ወሬ ማጠፈጫ ሳይሆን ሁልጊዜም ልንኖርበት የሚገባ የንስሀ ሕይወት ነው፡፡

12 comments:

 1. ትን ኢሳ. 1፡9፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። ታዲያ የቀረልን ዘር ምን ይሆን ከእመቤታችን ውጪ ምንም የለም፡፡ ለዛም ነው እመቤታችን በመድሃኒቴ ያለችው ለምን ቢሉም ከ ጥንተ አብሶ ነጻ አድረጎዋታልና፡፡ ስለዚህ መናፍቃን እናንተ የዘመኑ 666 መንፈስ የተጠናወታችሁ ተሃድሶ የምትሉት በእመቤታችን ላይ የምትዳፈሩት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖስ ምናምን ትላላችሁ ለመሆኑ የትኛውን ሰው እንደምትሉ አይገባንም በምናባችሁ የፈጠራችሁዋቸው ካልሆነ በስተቀር፡፡ እንኩዋን እናንተ የምትሉዋቸው ከሃዲዎች አይደሉም ንጉስ የነበሩት ሱስኒዎስ እንኩዋን በክህደታቸው በንግስና እንዲቆዩ አልተደረጉም፡፡ በምንም ይሁን በምን የቅዱሳንና የእመቤታችን ምልጃ የእግዚአብሔር ቸርነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን አጽንቶ ያኖርልናል፡፡ የናንተ መተራመስ በመጨረሻው ዘመን ብዙዎች በስሙ የሚመጡበት ብዙዎች የሚስቱበት የሚክዱበት ስለሆነ አይደንቀንም፡፡ ማቴ. 24፡23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤
  24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።
  25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
  አስቀድሞ ስለነገረን ተዋህዶም ተጠንቅቃ የምትሄደው ለዛ ነው፡፡
  ትን ኢሳ. 1፡9፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። ታዲያ የቀረልን ዘር ምን ይሆን ከእመቤታችን ውጪ ምንም የለም፡፡ ለዛም ነው እመቤታችን በመድሃኒቴ ያለችው ለምን ቢሉም ከ ጥንተ አብሶ ነጻ አድረጎዋታልና፡፡ ስለዚህ መናፍቃን እናንተ የዘመኑ 666 መንፈስ የተጠናወታችሁ ተሃድሶ የምትሉት በእመቤታችን ላይ የምትዳፈሩት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖስ ምናምን ትላላችሁ ለመሆኑ የትኛውን ሰው እንደምትሉ አይገባንም በምናባችሁ የፈጠራችሁዋቸው ካልሆነ በስተቀር፡፡ እንኩዋን እናንተ የምትሉዋቸው ከሃዲዎች አይደሉም ንጉስ የነበሩት ሱስኒዎስ እንኩዋን በክህደታቸው በንግስና እንዲቆዩ አልተደረጉም፡፡ በምንም ይሁን በምን የቅዱሳንና የእመቤታችን ምልጃ የእግዚአብሔር ቸርነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን አጽንቶ ያኖርልናል፡፡ የናንተ መተራመስ በመጨረሻው ዘመን ብዙዎች በስሙ የሚመጡበት ብዙዎች የሚስቱበት የሚክዱበት ስለሆነ አይደንቀንም፡፡ ማቴ. 24፡23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤
  24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።
  25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
  አስቀድሞ ስለነገረን ተዋህዶም ተጠንቅቃ የምትሄደው ለዛ ነው፡፡


  ReplyDelete
  Replies
  1. tiru mels setehal wendmei yekdusan chernetna mlja kantegara yhun

   Delete
 2. wedet wedet. mamush lela photow lela. Teenate Tehadisonet eko kezih yetelee mehonu hager yaweqew Tsehay yemoqew new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. @AnonymousJuly 5, 2013 at 1:00 PM
   If don't know about Deqiqe Estifanos Why you say "እናንተ የምትሉዋቸው ከሃዲዎች" ??? I am sorry.

   ደቂቀ እስጢፋኖስ እውነተኞች መናንያን ሲሆኑ ሰው በላው ድብ ጸር(ዘርዓ ያዕቆብ) ግን ለክብሩ ሲል በሚዘገንን ስቃይ አስጨፈጨፋቸው በረከተታቸው ይርብን፡፡ለቅድስት ድንግል የነበራቸው ክብርማ ሰዓሊ ለነ በማለት እና አብዛኞቹ ገዳሞቻቸው በስሟ በመገደም ነበር የሚገልፁት፡፡ ለበለጠ መረጃ ግን የትግራይ ገዳማት ውስጥ ያሉገድሎቻውን ማንበብ ይቻላል፡፡
   "አባ ሰላማዎች" እና ሌሎች ቢጽ-ሐሳውያን ሊሆኑላቸው እንደሚፈልጉት ግን አልነበሩም፡፡

   @ "Abaselama"
   We EOTC childeren need great reformation in our beloved church but we don't have any problem in belife(Dogma/ Doctrine) to borrow from modern colonization theory of wetern(Protestantism).Protestantism is not relegion but poletics of "throwing away ur identity and becoming Western".


   Delete
 3. kale-hiyiweti yasemalini,!!!!!!!! stegawi yibizalachihu.

  ReplyDelete
 4. Keep Dreaming MK will continue in Strength.

  ReplyDelete
 5. I think you have two choices:
  1. Defend your idea (MK) by emphasizing the facts and revealing the truth that
  appeared on this subject (Tehadiso). But, not go around with same teret.
  2. Accept the truth and turn around to the Lord whom presented this truth through
  His people (in your mind your enemy).

  I will pray for you to come up with the truth of the Gospel.

  Thank you!!!

  ReplyDelete
 6. Wey Gud! Krystianoch mechie new ersbersachin bemayreba ena keaemrowachin belay yehone neger lay mecceqacceq ena yenie theory kalhone mochie egegnalehu maletn ttiten yetetteranletn yekrstosn memotna meneseat bersum bekul tsdq megegnetuwan yemnmesekrew? Yemanachinm theological explanations alemn aladenem:: Alemn yadanew Eyesus bcha new:: Egnam yetazeznew ersu Eyesus ereft, selam, fqr endehone endnmesekr new:: Egna ers bers bemebettabet gizieyachinn slemnattefa yhew alemu be kfuw teyzo ybaznal:: Gita hoy! Mastewaln stten gizie enedayameltten.
  Amen!

  ReplyDelete
 7. Please do not be blind open your eyes and heart Jesus Christ will guide you to the truth. Only Jesus is the way not Mary. When is some of the Ethiopian orthodox understand that the truth of the Gospel. Orthodoxy is not going to take to heaven nor Mary.

  ReplyDelete
 8. MK is not truth Gospel followers.

  ReplyDelete
 9. it is geart cammenst abaselam . tankyou for your information.

  ReplyDelete
 10. yemogn zefen hulgize munaye alu merzachihun bmar lemelwos titralachuhu gin ayisakalachihum

  ReplyDelete