Thursday, July 18, 2013

“ነገረ ድኅነት በአሚነ አበው” የተሰኘው የዲያቆን አግዛቸው ተፈራ መጽሐፍ ተመረቀ

ከዲያቆን ዘመድኩን
ነገረ ድኅነት በአሚነ አበው በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የድኅነትን ነገር አባቶች ባስተማሩት መንገድ የሚተነትነው መጽሀፍ ባለፈው እሁድ ሰኔ 30/2005 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት ላይ በርካታ እንግዶች በተገኙበት ተመረቀ፡፡
ደራሲው ምዕራፍ አንድን የመዳን እውቀት ምንጭ በሚል ርዕስ የጀመረው ሲሆን ይህን የመዳን እውቀት ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን በመግለጽ በስፋት አብራርቷል፡፡ ጸሀፊው ሀሳቡን በማጠናከርም እንዲህ ሲል ጽፏል፡፡
“በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተገኙ መጻህፍት ሁሉ በልማድ “ቅዱሳት መጻህፍት” ተብለው ሲጠሩ እንሰማለን፡፡ “ቅዱሳት” የሚለው ቅጽል ግን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ከተጻፉት ከብሉያትና ከሀዲሳት መጻህፍት ውጪ ለሌሎች መጻህፍት ሁሉ የሚስማማና ሊቀጸል የሚገባ አይደለም፡፡ ከጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ አትናቴዎስ ለንጉስ ቆስጠንጢኖስ ልጅ ለዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ በጻፈው ትእዛዝ ላይ እንዲህ ብሏል፤ “የሚበልጠውም ትእዛዝ በኦሪት በነቢያት በወንጌል በሐዋርያት ቃል እናምን ዘንድ ነው። ንጉሥ ሆይ! ለነፍስህ መድሀኒት ይሆኑህ ዘንድ እግዚአብሔር ሊገልፅልህ የወደዳቸው መጻህፍት እኚህ ናቸው፡፡” (ሃይማኖተ አበው 1986 ገጽ 89፡90) በማለት ሰው ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተሰጠው መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
“በእግዚአብሔር ዘንድ ከሰዎች ድህነት የበለጠ ዋና ጉዳይ የለም (ህዝ. 18፡23፡32፤ 33፡11፤ ዮሐ. 3፡16-17፤ 1ጢሞ. 2፡3)፡፡ በሰውም ዘንድ ትልቁ ጥያቄ እንዴት ነው የምድነው? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዋና አላማ ለሰው ባዘጋጀው ድህነት በኩል ሁሉን በክርስቶስ መጠቅለል በመሆኑ (ኤፌ. 1፡10) እግዚአብሔር የድህነት ትምህርት በቃሉ ውስጥ እንዲሰፍር ያደረገው በግልፅና ሰዎች ሁሉ ሊረዱት በሚችሉት መንገድ ነው፡፡” (ገፅ 14)
እንዲህ ያለውን አገለለጽ በቅዱሳት መጽሐፍት እና በአባቶች ምስክርነት እያስደገፈ የሚቀጥለው ጸሐፊው ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ የሚሸጋገረው ስለ ሰው አወዳደቅ በማንሳት ነው፡፡ ይህንን ሀሳብ እያብራራም እንዲህ ይላል
“በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረው ሰው በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ልጅን የወለደው በራሱ መልክና ምሳሌ ነው (ዘፍ. 5፡3)፡፡ ይህም የአዳም ዘር የሆነ ሁሉ በኃጢአት የተበከለ ማንነትን (ጥንተ አብሶን) ወርሶ መወለዱንና በኃጢአት ምክንያት የእግዚአብሔር ክብር ከሰው ሁሉ መጉደሉን (ሮሜ 3፡23) ያመለክታል፡፡” (ገጽ 18)
በቀጣዩ ምዕራፍ ላይም የእግዚአብሔርን ጽድቅና ምህረት እንዲህ ሲል ያብራራል፦ “መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ጻድቅ ፈራጅ መሆኑን ይናገራል፡፡ በሌላም በኩል እግዚአብሔር መሃሪና ይቅር ባይ መሆኑን ይመሰክራል፡፡ የእግዚአብሔር ባሕሪያት እርስ በርስ የተያያዙና የማይቃረኑ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅና መሃሪ አምላክ ነው (መዝ. 112፡4 ፤ 115፡5)፡፡ የዙፋኑ መሰረቶችም ጽድቅና ፍርድ ናቸው፡፡ ምሕረትና እውነትም በፊቱ ይሄዳሉ፡፡
“እግዚአብሔር ጻድቅ ነው ሲባል ትክክለኛ ነው፣ እውነተኛ ነው፣ ሐቀኛ ነው፣ ፊት አይቶ አያደላም፣ በርሱ ዘንድ ዐመፃ የለም፣ በትክክል ይፈርዳል ማለት ነው (መዝ. 92፡15)፡፡ መሃሪ ነው ሲባልም በጥቅሉ ለኃጢአተኞች የማይገባቸውን ምሕረት ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ይህም “ምሕረትም የሌላትን እምራለሁ ” በሚለው ቃሉ ይታወቃል (ሆሴ 2፡25፤ ሮሜ 9፡16፤ 11፡30-31)፡፡ (ገጽ 30)
የእግዚአብሔርን ጽድቅና ምሕረት የሚያብራራው ይህ ምዕራፍ ስለእውነተኛው የእርቅ መንገድም እንዲህ ሲል ይገልጣል፡፡
እውነተኛው የመታረቂያ መንገድ እግዚአብሔር ያዘጋጀውና ክርስቶስ በሊቀ ካህናትነቱ በሰማያዊቱ መቅደስ ውስጥ አንድ ጊዜ ባቀረበው ደሙ አማካኝነት የተከናወነው የእግዚአብሔርና የሰው እርቅ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ በጥላው አገልግሎት በታየው የመታረቂያ መንገድ አምሳል ራሱን ስለ ኃጢአት መስዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረብ እግዚአብሔርንና ሰውን አስታርቋል፡፡ ሰውም ይህንን እርቅ በመቀበል በክርስቶስ በኩል ብቻ ወደ እግዚአብሔር ሊቀርብ ይችላል፡፡” (ገጽ 36)
በዚህ መልኩ የሚቀጥለው መጽሀፉ በምዕራፍ ስምንት ላይ የወቅቱ አወዛጋቢ ርዕስ እየሆነ የመጣውን ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ላይ ድርሻ አላት ወይስ የላትም የሚለውን ጥያቄ በዚህ መልኩ የአባቶችን ትምህርት እና የመጽሀፍ ቅዱስን እውነት ተደግፎ ያብራራል፡፡ የድንግል ማርያምን ትክክለኛ ስፍራ እንዲህ ሲል በማብራራት ይጀምራል “እግዚአብሔር አለምን ለማዳን በወደደ ጊዜ አንድያ ልጁን የላከውና ሰው ሆኖ እንዲወለድ ያደረገው ከሴቶች መካከል ከተባረከችው ከድንግል ማርያም ነው (ሉቃ. 1፡28)፡፡ እርሷን ለዚህ ታላቅ ክብር የመረጣት እግዚአብሔር ነው፡፡ ድንግል ማርያም በመልአኩ በገብርኤል በኩል የመጣላትን የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠር (ሉቃ. 1፡18) በእምነት በመቀበል ታዛለች፡፡ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝም ትልቅ አብነታችን ናት፡፡ መልአኩ በመንፈስ ቅዱስ ግብር (ማቴ. 1፡20) የሚከናወነውን የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር ባስረዳትና ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ በነገራት ጊዜ “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” በማለት ለእግዚአብሔር ቃል ፍጹም ታዛዥ መሆኗን አሳየች፡፡ “ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት” ተብሎም ስለ እምነቷ ታላቅነት ተመሰከረላት (ሉቃ. 1፡35-38፡45)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችን የአምላካችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት በመሆኗና እግዚአብሔር በእርሷ ታላቅ ስራን በመስራቱ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ስትል መስክራለች (ሉቃ. 1፡48)፡፡”
ጸሃፊው አክሎም ድንግል ማርያም በነገረ ድህነት ውስጥ ድርሻ አላት በማለት በሰሜን አሜሪካ ኑፋቄውን እየዘራና ብዙዎችን እያሳተ ከሚገኘው ከአንዱዓለም ዳግማዊ መጽሀፍ ጠቅሶ ሞግቶታል፡፡ “የቤተ ክርስቲያኗን አቋም የሚያንጸባርቅ ነው ማለት ባይቻልም አንዳንድ ግለሰቦች እያሰራጩት ያለው ትምህርት ከመጽሀፍ ቅዱስ እውነት የራቀ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ “ወላዲተ አምላክ በነገረ ድህነት” የተሰኘ መጽሐፍ ከርእሱ ጀምሮ በተደጋጋሚ ማርያም በክርስቶስ የአድህኖት ስራ ውስጥ ተሳትፎ እንዳላት ይናገራል፡፡ ለዚህ የሚያቀርበው ማስረጃ ግን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታ ኢየሱስን መውለዷን ብቻ ነው። ለምሳሌ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፦በመሰረቱ የእግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ሰው የመሆኑ ምሥጢር እኛን ለማዳን መሆኑ ከታወቀና ከታመነ ከማሕጸነ ድንግል እስከ ቀራንዮ አደባባይ የተደረገው የድህነተ አለም ጉዞ ሁሉ የተከናወነው በእርሷ ባሕሪ ስለ ሆነ ይህ አምላካዊ የቸርነት ስራ ወላዲተ አምላክ በነገረ ድህነት ውስጥ ያላትን ሱታፌ (ተሳታፊነት) በጉልሕ ያሳያል ያስገነዝባል (አንዱዓለም 1998፣ ገጽ 80)፡፡       
“ሰውን በማዳን ሥራ ውስጥ ድርሻ ያላቸው አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ብቻ ናቸው፡፡ አብ ዓለምን እንዲሁ በመውደድና ለማዳን አንድያ ልጁን አሳልፎ በመስጠት ወልድ ደግሞ ሰው ሆኖ ስለ ሰው በመሞት መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ይህን የእግዚአብሔር አብ ፍቅርና የእግዚአብሔር ወልድ ቤዛነት ለሰው በመግለጽና እንዲያምኑ በማድረግ ተሳታፊ ነው፡፡ መዳናችን የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው ማለት ነው (ኤፌ. 1፡3-14)፡፡ ከዚህ በቀር በማዳን ስራ ውስጥ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ላይ ሌላ አራተኛ ባለ ድርሻ አካል መጨመር ትልቅ ስሕተት ነው የሚሆነው፡፡” (ገጽ 97)
በመጽሀፉ ምረቃ ላይ ይህ ክፍል የተነበበ ሲሆን በዚህ ክፍል የተጠቀሰው አንድ ገጠመኝ  ብዙዎቹን የምረቃውን ታዳሚዎች ፈገግ አሰኝቷል፡፡ “አንድ ሰባኪ ‘ኢየሱስ የተሰቀለው ከማርያም በነሳው ስጋ ነውና የኢየሱስ ስጋ የማርያም ስጋ ነው’ እያለ ሰብኮ ከአጠናቀቀ በኋላ ወደመቀመጫው ይመለስና ከአንድ ሊቅ አጠገብ ይቀመጣል፡፡ ሊቁም ሰባኪውን ቈነጠጡት፡፡በዚህ ጊዜ ሰባኪው ‘ምነው አባታችን? ምን አጠፋሁ?’ ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም ‘አሁን ይህ ቁንጥጫ አንተን ነው ወይስ እናትህን ነው የተሰማት?’ አሉት” (ገጽ 99)
እንዲህ ያለው ማብራሪያ በቅን ልቦና ከመንገድ የወጡትን ወገኖች ለማንቃት እና ከስህተት አሰራርም ለመመለስ ይረዳል፡፡ እውነትን በእልህ ለማጽደቅ እና እውነትን በእውነትነቱ ለመቀበል ለማይፈልጉ ወገኖችም የማይዋሹት ህሊናቸው ለእውነቱ እንዲገዛ እና ውሎ አድሮም ለእውነት ባርያዎች እንጂ ጠላቶች እንዳይሆኑ ሊያነቃቸው ይችላል ተብሎ ይታመናል፡፡
ነገረ ድህነት በአሚነ አበው መጽሀፍ በተመረቀ ዕለት ጸሃፊው እንደተናገረው ይህ መጽሐፍ የዘመናት ምጡ የነበረ እና ከሁሉም መጽሐፎቹ ከፍ ያለ ሥፍራ የሚሠጠው ነው፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ ኢየሱስ ለኃጢአታችን ሥርየት ሲል የከፈለውን ዋጋ እና ያሳየንን ፍቅር የሚወዳደር ሌላ ቁም ነገር የለምና ነው ብሏል፡፡
በምረቃው ቦታ ላይ የተገኙት አንድ አርታዒ በመጽሐፉ ላይ ያላቸውን አስተያየት ሲያቀርቡ “ማንኛውንም መጽሐፍ የምመለከተው አንድ አርታዒ እንድን መጽሐፍ በሚገመግምበት ጊዜ ሊጠይቀው የሚገባውን ‘ጸሀፊው የሚጽፈውን ነገር አውቆታል ወይ?’ የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ በመጠየቅ ነው፡፡ ከዚህ ጥያቄ በመነሳትም ነገረ ድህነት በአሚነ አበውን ስገመግመው ደጋግሜ ላነባቸው ከወሰንኩዋቸው ጥቂት መጽሐፍት መካከል አንዱ እና ዋነኛው አድርጌ ነው የወሰድኩት፡፡ ጸሀፊው ሀሳቡን በአግባቡ ከመግለጽ ውጭ ማንንም ወገን አይነቅፍም፡፡ ትችት በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ ትችቱን የሚያቀርበውም በአግባቡ የጽነ ጽሁፍ ሕግን በጠበቀ መንገድ እና ከበቂ ምክንያት ጋር ነው፡፡ እንዲህ ያለውን መጽሐፍ ለማንበብ መብቃት መታደል ነው፡፡” በማለት የተናገሩ ሲሆን ያነሱትን ሀሳቦች በበቂ ምክንያት በማስደገፍ እና ከመጽሐፉ በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡
ሌላኛው አስተያየት ሰጪም ነገረ ድህነት በኛም ቤት በሌላኛውም ቤት የትርጉም እና የአላማ መዛባት የደረሰበት እውነት መሆኑን አስረድተው፣ ሌሎች የአዳኙን ነገረ መስቀል እና የዳኑበትን እውነት ለምድራዊ ብልጽግና መድረሻ አድርገው እንደሚቆጥሩት እና ስለእኔ የሞትክልኝ በማለት እየዘመሩ የተንጣለለ ቪላ ላይ እየኖሩ መሆናቸውን የሚያሳዩ እንዳሉ እና እንደእነዚህ ላሉት ጌታ የሚመጣ እስከማይመስላቸው ድረስ የመዳናቸውን እውነት ምድራዊ አድርገውት እየቀሩ መሆኑን ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በእኛ ቤተክርስቲያን ያለውን ሁኔታ ሲያስረዱ “በእኛ ቤት ያለው ሁኔታ ደግሞ ወደ ሌላ አቅጣጫ የሄደ እና በአንዱ ጌታ የተፈጸመውን ማዳን ለብዙዎች በማደላደል በብዙ አዳኞች ታቅፎ በመቀመጥ የመዳንን እውነት እና የመዳኛውን መንገድ ሙሉ በሙሉ ያጣመመ ነው” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ አስተያየት ሰጪው ከእነዚህ እውነቶች በመነሳትም ነገረ ድኅነት በአሚነ አበውን “.. ወደ ግራ ወደ ቀኝም ሳይል እውነቱን በእውነትነቱ ብቻ ያቀረበ ድንቅ መጽሐፍ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ስለ ጸሀፊውም “ምንም እንኳ ራሱ ጸሀፊው ክርስቶስ ኢየሱስ ለእርሱ የከፈለው የማዳን ስራ የሚያምን እና የሚቀበል ሰው እንደመሆኑ የራሱ የሆኑ አስተያየቶች ቢኖሩትም ከእራሱ አስተያየት ይልቅ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ ዙሪያ የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉትን ጽሁፍ እና ማስረጃ ብቻ  ማካተቱ እና ከእነርሱም ተነስቶ ትንታኔ መስጠቱ የሚያስመሰግነው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እኔም እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቴ እና የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንደሚጠማ ሰው ከመጽሐፉ በርካታ ቁም ነገሮችን አግኝቼበታለሁ፡፡ የሩቆቹም የቅርቦቹም የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስተማሩት ትምህርት በመጽሀፉ ውስጥ የመገኘቱ ጉዳይ ቤተክርስቲያን ደፋሮች ከነስህተት ትምህርታቸው እየፈነጩባት ከገዛ አባቶችዋ የተቀበለችውን እውነት አዳፍና መቅረትዋ በታላቅ ሀዘን እንድተክዝ አድርጎኛል፡፡
የተቀበረ መክለት በሚል ርእስ የተጻፈውን የደራሲውን የመጀመሪያ መጽሐፍ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን እንደሚያስታውሱት እምነቴ ነው፡፡ ነገረ ድህነት በአሚነ አበው ያ የተቀበረው መክሊት ምን እንደሆነ በጉልህ የታየበት እና በማያሻማም ሁኔታ ስመ ጥሩዎቹ የቤተክርስቲያን አባቶች ባስተማሩት መንገድ ተቆፍሮ የወጣበት መጽሀፍ ነው፡፡ ደራሲው ከተቀበረ መክሊት በተጨማሪ ጥላና አካል፣ የለውጥ ያለህ እና አልተሳሳትንምን? የሚሉ መጻህፍቶችን ለህዝበ ክርስቲያን ያበረከተ ሲሆን አሁን ደግሞ ነገረ ድህነት በአሚነ አበውን አበርክቷል፡፡  
ጸሀፊው መጽሀፉን ሲጨርስ የማጠቃለያ ሀሳቡን ማሳረጊያ የሚል ርዕስ ሰጥቶታል፡፡ በማጠቃለያው ላይ ቃሉ ራሱ ይናገር በሚል ይመስላል ምንም አይነት ሀተታ አላቀረበም፡፡ ማሳረጊያው እንዲህ የሚል ነው፡፡
“ምንተ እግበር ከመ እድኀን እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” የወህኒ ጠባቂ)
“እመን በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወተሐዩ አንተ ወኵሉ ቤትከ፡፡  በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተሰዎችህ ትድናላችሁ” (የሐዋርያት ስራ 16፡30፡31)
ለሰው ልጆች ዘለዓለማዊ ጥያቄ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሆነ ዘለዓለማዊ መልስ፡፡
እርስዎስ ይድኑ ዘንድ ምን ማድረግ የሚገባዎት ይመስልዎታል?

34 comments:

 1. pe pe pe lik endih new ke protestant thihufoch lekakimo yametawn asatemena ante degimo mastewokia tenagerh huletachihum yeand santim hulet gestawoch nachihu-protestants behig amlak " betekirisitianachin" atbelu

  ReplyDelete
 2. የመናፈቁ መፅሐፍ ተመረቀ በል እንጂ የ ዲያቆን አትበል ::አጨበርባሪ መናፍቅ ሁላ

  ReplyDelete
  Replies
  1. nufakie ye getan be lela mete kate new

   Delete
 3. I think it's Great so how to get this book? we need to buy it....we have to right? Thank you !

  ReplyDelete
 4. D\Agezachew Geta Tsegawen Tabezaleh, Yegtan ewnet yemgeletu bezeh meder derome kebere yelachew yeheche alem lekehadi nat le'asemesay ane ede anet yaleutu gen hagerachew besemay newena kebeder keberen atetebekum, tebarek, le'lochachu demo menafek malet min endehon yekdemuten yemetekreseteyan metsehafet anebebu 318 lekawen yetsafuten ahun menafek manew? masetewalen yesetachu.

  ReplyDelete
 5. wow!wow!wow!bilenal.amilak yasinesah wud wendime mechereshahin yasamirilh.yenigid metsehaf bebezabet zemen yeewinet meleekit siweta sewim amilakm desi yilewal.gin adera adera adera timikihit honobih befetena endatiwedik tseliy.geta yirdah.silemititsifachew metsahifit hulu lak yale akibirot alegn.letesadabiwoch lib yisitachew.antem tseliytilachew.ayzoh.yeageligilot wendimih negn.

  ReplyDelete
 6. breaking news! this book will be available in the shops of all orthodox churches including MK shops. piftttttttttttttttt hahhaahha. the Protestant's 'teret teret' is same old story- insulting our Lord and God Jesus Christ and his Saints for the past 50 years. nothing more nothing less.who bothers with your void nufake?

  ReplyDelete
 7. ፀሓፊው የትኛው ቤቴክርስትያን ነው የምያገለግለው ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ያገለግላል። የማንን ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግል ትፈልጋለህ?

   Delete
  2. yemakin betekirstiyan meslot yihonal

   Delete
 8. ዉረድ ከ እመቤቴ ዉረድ ከ እመቤቴ

  ReplyDelete
 9. Should you disagree with Decon Agezachew, bring your points on why you disagree.His points are interesting and valid. You do not have to board on smear and cursing wagon.A lot of our youth are defecting to the protestant church because of lack of clarity.We need more like the decons to enlighten our Orthodoxians. The more you learn the better unerstanding you have. The Fetha Negest has it in simpler and easy way, but seldom is used as a reference in daily teachings. This is the time of enlightenment. We all need to dig and learn more about our church. This undoubtly will stop the exodus to the protestant church. Last but not least I thank Aba Selama for this blog. Bless you all!

  ReplyDelete
  Replies
  1. The Anonymous above is wonder full comment, God bless u more.

   Delete
 10. i cant say anything, just the grace of God and the power of holy sprite be with him and with u.

  ReplyDelete
 11. Aynachew laltekefte mk nene bayoch menme slemaygebachew, enesu ye-misetuten ye-denkoro asteyayet manem yawkalena, enante ewunetegnawun ye-Egziabehearen wongel kemenagerna kemastemar atekotebu adera. Aba Selama Tebareku. Wongelu yegebawu kerestiyan hulu yiwedachehual. We Love you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ye-denkoro" asteyayet
   አቤት ሌላ ሰው ደንቆሮ ቢላችሁ ጥቅስ ለመጥቀስ ስትሮጡ::
   በነገራችን ላይ በትክክል ራስህን ገልፀህበታል::

   Delete
 12. God bless you brother,it is one of the best.

  ReplyDelete
 13. መናፍቁ አግዛቸው የአባ ሰላማ፣ የጮራና የሌሎች ምንፍቅና አሰራጭ መፅሃፎች ደራሲ እንኳን ፃፍክ። አዲሱን ስህተትህን ደሞ አይተን እንማርበታለን። ከጴንጤዎቹ ጋር ያለህን ግንኙነት እንገመግምበታለን።

  ግን ግን ዜናውን ስትዘግቡ አንተ ወይም ፅጊቱ ምርቃታችሁ በህልማችሁ ካልሆነ፤
  የት ተካሄደ?
  እነማን ነበሩ?
  አርታኢው ስም የለውም ወይስ ፖስተር ሆነባችሁ?
  አስተያየት የሰጡት ስም የላቸውም?
  አሁንም ነገሮችን በጨለማ ለምን ማድረግ ያስፈልጋል? እሱ እንደሆን አንዴ ተወግዟል። አርታኢውም ሆነ ተጋባዠ ካመናችሁበት ምን ያስደብቃችኋል? እስኪ የራስ ክንብንባችሁን፣ የበግ ለምዳችሁን አውልቁ።

  ReplyDelete
 14. መናፍቁ አግዛቸው የአባ ሰላማ፣ የጮራና የሌሎች ምንፍቅና አሰራጭ መፅሃፎች ደራሲ እንኳን ፃፍክ። አዲሱን ስህተትህን ደሞ አይተን እንማርበታለን። ከጴንጤዎቹ ጋር ያለህን ግንኙነት እንገመግምበታለን።

  ግን ግን ዜናውን ስትዘግቡ አንተ ወይም ፅጊቱ ምርቃታችሁ በህልማችሁ ካልሆነ፤
  የት ተካሄደ?
  እነማን ነበሩ?
  አርታኢው ስም የለውም ወይስ ፖስተር ሆነባችሁ?
  አስተያየት የሰጡት ስም የላቸውም?
  አሁንም ነገሮችን በጨለማ ለምን ማድረግ ያስፈልጋል? እሱ እንደሆን አንዴ ተወግዟል። አርታኢውም ሆነ ተጋባዠ ካመናችሁበት ምን ያስደብቃችኋል? እስኪ የራስ ክንብንባችሁን፣ የበግ ለምዳችሁን አውልቁ።

  ReplyDelete
 15. The shining moments for our church! Now we will start looking things in perspective to the actual teaching of the true Ethiopian Tewahido and the Oriental sister churches. Like many I congratulate Aba Selama on opening the highway to Discovery Tewahido. God Bless you all!

  ReplyDelete
 16. እግዚአብሄር አብዝቶ
  ይባርክህ የእውነት ጌታ በተለየህለት እውነት ያጽናህ ተባረክ። (www.michaelyemane.blogspot.com)

  ReplyDelete
 17. እግዚአብሄር አብዝቶ
  ይባርክህ የእውነት ጌታ በተለየህለት እውነት ያጽናህ ተባረክ። (www.michaelyemane.blogspot.com)

  ReplyDelete
 18. ጸሓፊው ደክሞ ጽፎታልና ሊደነቅና የኅሊና ድጋፍ ሊሰጠው ይገባል እኛም ባንል ሥራው ይገልጸዋል
  ዳሩ ግን የሰው ልጆች ተሽቀዳድመው ወደነቀፋ መግባታቸውና መናፍቅ ወዘተ ማለታቸው በስንዴው
  መካከል እንክርዳድ መዝራት ይሆንባቸዋል ሰላውዲውና አሳባቂው የግብር አባታቸው ጸላዔ ሠናይ
  ለነቀፋ የቆመ በመሆኑ ነቃፊዎቹም ግብራቸው ያው ነው (ሊቃውንትንና ሥራቸውን መንቀፍ)አርፈው ቢነግዱ ይሻላቸው ነበር

  ReplyDelete
 19. "መናፍቁ አግዛቸው የአባ ሰላማ፣ የጮራና የሌሎች ምንፍቅና አሰራጭ መፅሃፎች ደራሲ እንኳን ፃፍክ። አዲሱን ስህተትህን ደሞ አይተን እንማርበታለን። ከጴንጤዎቹ ጋር ያለህን ግንኙነት እንገመግምበታለን" Who ever comments this a victim of "MK" propaganda. I urge every one to pray for this lost sheep so he will come to his senses.
  As for "MK" I say it is the oasis of ጸላዔ ሠናይs. You can not get away with what ever you say now a days. People are getting brighter and smarter.

  ReplyDelete
  Replies
  1. dude,Thank you. However, i don't need your pente pary. Pray for yourself. You are a victim of Gay pentes from America. so start thinking about what you doing. As you said "You can not get away with what ever you say now a days. People are getting brighter and smarter." so, prepare to be questioned.

   ግን ግን ዜናውን ስትዘግቡ አንተ ወይም ፅጊቱ ምርቃታችሁ በህልማችሁ ካልሆነ፤
   የት ተካሄደ?
   እነማን ነበሩ?
   አርታኢው ስም የለውም ወይስ ፖስተር ሆነባችሁ?
   አስተያየት የሰጡት ስም የላቸውም?
   አሁንም ነገሮችን በጨለማ ለምን ማድረግ ያስፈልጋል? እሱ እንደሆን አንዴ ተወግዟል። አርታኢውም ሆነ ተጋባዠ ካመናችሁበት ምን ያስደብቃችኋል? እስኪ የራስ ክንብንባችሁን፣ የበግ ለምዳችሁን አውልቁ።

   Delete
 20. ooo Getare sebarek yebetekreseteyan tensea deresalenea leb be'haset temola leka geta bezu demek legoch aleut. Elias ene becha kerehu bale Gize 7000 le'beal yalesegedu ale endale leka geta yelamen hasab yemataderegu, ye'mk haseben yemiyaferesu, ye'protestaten hasab yemayekebelu yegetan ewenet yemigletu ewenetegochu bezu le'geta yekereulet alu. Ye'Abereham ableki tebarek wodimi geta yebarekeh tesgawen tabezaleh, Ebakeachu besemay lemekeber lemedan yemetwodu hulu mesehafun anebemu keteret wetu haseten kewenet leyu tetekemubt. nekefeaw yekerena bemanebebena bemamen danu. Geta huluen leyaden metal yehenene ewenet tekebeleuna kemot danu.

  ReplyDelete
 21. ጎበዝ ታምረ እገሌ እየተባለ በየገዳሙ የተደረተ ጸረ ክርስትና ተረት ለምዳችሁ እዉነተኛዉ ወንጌል ሲገለጥ ቢተናነቃችሁ አይደንቀንም፤ የግብር አባታችሁ የወንጌል ጠላት ስለሆነ ነዉ፡፡ ዲያቆኑ “ሰባ ስምንት ነፍስ የገደለው ሰው ለጥቂት ወደ ሲኦል ሊገባሲል ማርያም አማላደችው፤ እግዚአብሔርም መፍረዱን ትቶ ሚካኤልን በማርያም ስም የተሰጠውን ውሃና ሰባ ስምንቱን ነፍሳት መዝንልኝ አለው፤ ነፍሳት እየከበዱ ውሃው እየቀለለ መሄዱን ያየችው ማርያም ሮጥ ብላ በውሃው ላይ ጥላዋን ጣለችበት በዚህ ጊዜ ከማርያም ጥላ የተነሳ ውሃው ክብደት በማሳየቱ ነፍሰ በላው ወደ ገነት ተዛወረ”:: የሚለዉን ተረታችሁን ባለመቀበሉ መናፍቅ ከተባለ እናንተ ምን ልትባሉ ነዉ? ለማንኛዉም አዉነተኛ ክርስቲያን ይመርቃል እንጅ አይረግምም፡፡ አግዛቸዉንም እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንክን ይባርክልህ ብዬሃለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አረ ምነው! ወንድሜ የማታውቀውን ባትዘባርቅ፤መልካም ነው፤፤አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል፤፤ ባታምንበትም አይሰደብም፤፤ እግዚአብሔር ልቦና ይስጥህ!!፤፤ እመ አምላክ ዐይነልቦናህ ታብራልህ!!!፤፤

   Delete
 22. ጎበዝ ታምረ እገሌ እየተባለ በየገዳሙ የተደረተ ጸረ ክርስትና ተረት ለምዳችሁ እዉነተኛዉ ወንጌል ሲገለጥ ቢተናነቃችሁ አይደንቀንም፤ የግብር አባታችሁ የወንጌል ጠላት ስለሆነ ነዉ፡፡ ዲያቆኑ “ሰባ ስምንት ነፍስ የገደለው ሰው ለጥቂት ወደ ሲኦል ሊገባሲል ማርያም አማላደችው፤ እግዚአብሔርም መፍረዱን ትቶ ሚካኤልን በማርያም ስም የተሰጠውን ውሃና ሰባ ስምንቱን ነፍሳት መዝንልኝ አለው፤ ነፍሳት እየከበዱ ውሃው እየቀለለ መሄዱን ያየችው ማርያም ሮጥ ብላ በውሃው ላይ ጥላዋን ጣለችበት በዚህ ጊዜ ከማርያም ጥላ የተነሳ ውሃው ክብደት በማሳየቱ ነፍሰ በላው ወደ ገነት ተዛወረ”:: የሚለዉን ተረታችሁን ባለመቀበሉ መናፍቅ ከተባለ እናንተ ምን ልትባሉ ነዉ? ለማንኛዉም አዉነተኛ ክርስቲያን ይመርቃል እንጅ አይረግምም፡፡ አግዛቸዉንም እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንክን ይባርክልህ ብዬሃለሁ፡፡

  ReplyDelete
 23. “በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተገኙ መጻህፍት ሁሉ በልማድ “ቅዱሳት መጻህፍት” ተብለው ሲጠሩ እንሰማለን፡፡ “ቅዱሳት” የሚለው ቅጽል ግን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ከተጻፉት ከብሉያትና ከሀዲሳት መጻህፍት ውጪ ለሌሎች መጻህፍት ሁሉ የሚስማማና ሊቀጸል የሚገባ አይደለም፡፡ ከጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ አትናቴዎስ ለንጉስ ቆስጠንጢኖስ ልጅ ለዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ በጻፈው ትእዛዝ ላይ እንዲህ ብሏል፤ “የሚበልጠውም ትእዛዝ በኦሪት በነቢያት በወንጌል በሐዋርያት ቃል እናምን ዘንድ ነው። ንጉሥ ሆይ! ለነፍስህ መድሀኒት ይሆኑህ ዘንድ እግዚአብሔር ሊገልፅልህ የወደዳቸው መጻህፍት እኚህ ናቸው፡፡” (ሃይማኖተ አበው 1986 ገጽ 89፡90) በማለት ሰው ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተሰጠው መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

  ReplyDelete
 24. ቤተ ክርስቲያንም ተሐድሶ ያስፈልጋታል፤ ተሐድሶ እጅግ በጣም ከሚያስፈጋቸው ተቋማት መካከል የእግዚአብሔር ቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ናት። በዓለም ውስጥ ከዓለም ተለይታ የምትኖር የጌታ ቤት በመሆኗ በየጊዜው እራሷን ማየት፤ በጌታ ቃል ሕይወቷን መመርመር ይኖርባታል። ይህች ቤት በዚህ ሰይጣን በሚገዛው ክፉ ዓለም ውስጥ የምትኖር ስለሆነ የዓለም ርኩሰት ሊገኝባት ይችላል፤ የዓለም ፍልስፍና ወይም ርእዮተ ዓለም ገብቶባት ሊሆን ይችላል፤ የስይጣን አሠራር እና እውነት የሚመስል የአጋንንት ትምህርት ሾልኮ ገብቶ ሊሆን ይችላል፤ ጥንቆላ እና መተት ሰማያዊ ታምራት መስለው ተቀላቅለው ሊገኙ ይቻላሉ፤ ሥጋዊነት፣ ዓለማዊነት፣ ገንዘብን መወደድ፣ ሥልጣንና ሹመት ፍለጋ፣ ስግብግብነት፣ ሞልተውባት ሊሆን ይችላል፤ ጥላቻ፣ ስድብና እርግማን፤ የርስ በርስ መነካከስ፣ ዘርኝነት፣ ስንፍና፣ ሊኖር ይችላል፤ እራይ አልባ ሆና ስኬት ርቋት ሊሆን ይችላል፤ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲገኙ ነገር ተገለባብጧል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን ወደ ዓለም ገብታ ዓለምን መቀደስ ሲገባት፡ ዓለም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ርኩሰቷን ፈጽማለች ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያንን ከዓለም መለየት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሰን እያየነው ተሐድሶ አያስፈልገንም ማለት የሚያስገርም ነው።

  ReplyDelete
 25. የት? መቼ? እነማን? የሚለውን ማቅረብ አስፈላጊነቱ አልታየኝምና እንኳንም ዲያቆን ዘመድኩን በእለቱ በመርሐ ግብሩ ላይ ዝግጅት ያቀረቡትንና ቦታውን አልጠቀስክ፡፡ የማቅ ሰዎች ይህን ቢያውቁ እነእገሌም ተገኝተዋል በሚል መናፍቅ ለማለት አፋቸውንና ብእራቸውን ያሾላሉ እንጂ የሚለወጥ ነገር የለም፡፡ የማቅ ሰዎች በዜናው ይዘት ላይ ሳይሆን የተለመደውን የስም ማጥፋት አሉባልታቸውን ከማናፈስ ያለፈ ስራ የላቸውም ስለዚህ እነርሱም ያውሩ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተሐድሶም ይፋጠናል እንጂ አይደናቀፍም፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ተሐድሶ እየተፋጠነ ያለው እንደውም ማቅ ለቤተክርስቲያን ቆሜያለሁ እያለ ባለበት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህ ማቆችና ርዝራዦቻቸው ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ እንዳትገኙ ተጠንቀቁ፡፡ ዲያቆን አግዛቸው እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝመው ድንቅ መጽሐፍ ጽፈሃል፡፡ ደግሞም ማቅ ካሳተመው የሊቀ ጉባኤ አበራ መጽሐፍ እና ከቤተክርስቲያን መጻሕፍት ላይ የጠቀስካቸው አስገራሚ እውነቶች ዛሬም የቤተክርስቲያን ልጅ ለመሆንህ ምስክሮች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ha ha ha! Funny. ዶሮን ሲያታልሏት አሉ። ያልተከሰተን ዜና በምርቃና እየፃፉ መለጠፍ ዜና ከተባለ ይመችህ።ዜና ብሎ የፃፈው እኮ እንደ ኢቲቪ ዜና አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚለው እዚህም የፃፈው እኮ ዝባዝንኬ ነው።

   Delete
  2. Ha ha ha! Funny. ዶሮን ሲያታልሏት አሉ። ያልተከሰተን ዜና በምርቃና እየፃፉ መለጠፍ ዜና ከተባለ ይመችህ።ዜና ብሎ የፃፈው እኮ እንደ ኢቲቪ ዜና አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚለው እዚህም የፃፈው እኮ ዝባዝንኬ ነው።

   Delete