Sunday, July 21, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ትግል አባ ጢሞቴዎስን ከቦታቸው በማስነሳት ተጠናቀቀ፡፡

ከአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ጀምሮ ያሉባቸው አስተዳደራዊ ችግሮች እንዲቃለሉ ሲጠይቁ የቆዩትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኮሌጁ አስተዳደር ጋር የከረረ ጠብ ውስጥ የገቡት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በአባ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና ፈጽሞ ያልጠበቁት “ኮሌጁ ተዘግቷል” የሚል ምላሽ ማግኘታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለተጻፈባቸው ህግና ስርአትን ያልተከተለና አባ ጢሞቴዎስን ለማስደሰት በሚል ብቻ በተጻፈባቸው ደብዳቤ ሳይደናገጡ ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለው ባሉበት በአሁኑ ጊዜ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እያገኙ የሚመጡ ለመሆናቸው ፍንጭ ያገኙበት አጋጣሚ መፈጠሩን ማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ መሠረት በዛሬው የስብሰባ ውሎ ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩን “ኮሌጅ የመዝጋት ስልጣን የለዎትም” በማለት የወሰዱት እርምጃ ከህግ ውጪ መሆኑን የነገራቸው ሲሆን፣ የኮሌጁን መምህራን ጠርቶ ያነጋገረ መሆኑም ታውቋል፡፡ መምህራኑም ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸው ፈተና ሊወስዱና ሊመረቁም እንደሚገባ ተናግረዋል ተብሏል፡፡ በዚሁ መሠረት እንዲፈጸምም ቋሚ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን “ምርቃት የለም” እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩትን አባ ጢሞቴዎስንና ግብረአበሮቻቸውን ከቦታቸው ላይ በማንሳት ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ፣ እንዲፈተኑና እንዲመረቁ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ይሁን እንጂ ከመምህራኑ በኩል የቀረበው አስተያየት ያበሳጫቸው አባ ጢሞቴዎስ መምህራኑን “ሌባ ሁሉ” ሲሉ መሳደባቸው ተሰምቷል፡፡ የሀይል ሚዛኑ አባ ጢሞቴዎስን እየከዳቸው መሆኑን የተረዱት አባ ማትያስም ወዳጃቸውን አባ ጢሞቴዎስን ከድተዋቸዋል፡፡ ከቦታቸው እንዲነሱ በተወሰነው ውሳኔም ተስማምተዋል ተብሏል፡፡ የኮሌጁን ተማሪዎች አስመልክቶ የተላለፈውን ውሳኔ እንዲያስፈጽሙና የበላይ ኀላፊ እንዲሆኑ ንቡረ እድ ኤልያስ ተመድበዋል፡፡

ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ ስብሰባ የተቀመጠው ቋሚ ሲኖዶስ የተማሪዎቹ ጥያቄ ተገቢነት ያለው በመሆኑ ተቀብሎ ከሊቀ ጳጳሱ ጀምሮ መ/ር ዘላለምና ፍስሀ ጽዮንን እንደሚያነሣ እየተጠበቀ ባለበት በዚህ ወቅት የማቅ እንባ ጠባቂ የሆነችው ሀራ ዘተዋህዶ ግን የማቅ ቀኝ እጅ የሆነውን ፍስሀ ጽዮንን ተማሪዎቹ አጥብቀው እየተቃወሙ ባሉበት ሁኔታ እየካበችና ዘላለምን እየናደች መዘገቧን ቀጥላለች፡፡ ወዳጃቸውን አባ ጢሞቴዎስን ለማስደሰት ኮሌጁ ይዘጋ ያሉትን አባ ማትያስን በጉዳዩ ላይ ተጠያቂ አለማድረጓም ፓትርያርኩ በአሁኑ ጊዜ ከማቅ ጋር በጫጉላ ሽርሽር ላይ በመሆናቸው ላለመረበሽ ነው ይላሉ ምንጮቻችን በስላቅ፡፡ ለእዚህ አንዱ ማሳያ በቅርቡ ፓትርያርኩ ቋሚ ሲኖዶስ ላይ ቀርበው “ማኅበረ ቅዱሳን የአንድ ሆስፒታል ዲዛይን ሰርቶልኛልና ሲኖዶሱ ያጽድቅልኝና ስራው ይጀመር” ሲሉ ጠይቀው የነበረ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ሆኖም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ዲዛይን ቢሰራም ዝም ተብሎ ይሰራ ማለት አይቻልም፡፡ ገንዘቡ ከየት ይመጣል? ይህ ውይይትና በቂ ጥናት የሚጠይቅ ስራ ነው ማለቱና ፓትርያርኩ ገና በተሾሙ ማግስት ለስማቸው ማስጠሪያ ሆስፒታል ይገንባልኝ ማለታቸው ትልቅ ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ ወዳጆቻቸውን በመክዳትና ጊዜያዊ ጥቅማቸውን በማስላት ሲቃወሟቸው የነበሩትን በማቅረብ እያሳዩ ያለው አቋም ምን እንደሆነ ስራቸውን ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑት ፓትርያርክ ማትያስ ከማቅ ጋር የጀመሩት አዲስ ፍቅር ብዙዎችን ግራ ያጋባ ሆኗል፡፡ የማቅ ዋና ዋና ሰዎችም ምሽቱን ከፓትርያርኩ ጋር እንደሚያሳልፉና ፓትርያርኩ የሚወዱትን የፈረንሳይ ወይን ጭነው በመግባት በወይን እያስደሰቱ ሊሰሩ የሚፈልጉትን ሁሉ እንደሚያሰሯቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ በቅርቡ እንኳ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤልን ከቦታው ያስነሱት የማቅ ሰዎች መሆናቸውንና መምሀር ዳንኤል ማቅ አለአግባብ በቤተክርስቲያን ስም ይሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ከምንጩ እንዲደርቅ በማድረግ በጥቅሙ ላይ ስለቆመ ያንን ለመበቀል እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል (ዝርዝሩን በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን)፡፡ 

አስቀድሞ የራሱን ጳጳስ ለማስቀመጥ ከፍተኛ በጀት መድቦ ሲንቀሳቀስና አባ ማትያስን ከመንግስት ጋር በማገናኘት ሲያጣጥላቸው እንዳልነበርና በአስተዳደር በኩል ዳተኛ መሆናቸውን በሀራ በኩል ሲነግረን እንዳልነበር ዛሬ ግን ዳተኛነታቸውን በተመለከተ ትንፍሽ አልል ብሏል፡፡ ለቤተ ክህነቱ አስተዳደር እንግዳ በመሆናቸው ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ተብሎ በሰፊው የተነገረላቸውና ከተሾሙ ጀምሮ በቤተክህነት ውስጥ እየደረሱ ላሉት ልዩ ልዩ ችግሮች መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ችግሮችን እየከመሯቸው የሚገኙት ፓትርያርክ ማትያስ ምን እየሰሩ እንደሚገኙ እንኳን ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ከተሾሙ ጊዜ ጀምሮ የቀረበላቸውን የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችን ጉዳይ ጆሮ ዳባ ብለው የቆዩ ፓትርያርክ ማትያስ ዛሬ ግን የግዳቸውን ኮሌጁ ይዘጋ ሲሉ የጻፉትን ህገወጥ ደብዳቤያቸውን መቅደድና ተማሪዎቹ እንዲመረቁ ውሳኔ ማሳለፍ ወዳጃቸውን አባ ጢሞቴዎስንም መክዳት ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከማቅ ጋር ያወዳጃቸው ምን ይሆን? ምን ያህልስ ይዘልቁ ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡

አባ ማትያስ የቅድስት ስላሴን ኮሌጅ ጉዳይ አስመልክቶ እያሳዩት ያለው ዳተኛነት አቡነ ጳውሎስ ለኮሌጁ ይሰጡ ከነበረው ከፍተኛ ትኩረት ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የምድር ያህል ርቀት እንዳለው መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኮሌጁ ውስጥ ችግር በተፈጠረ ጊዜ ሁሉ ፈጥነው በኮሌጁ በመገኘት ወይም ተማሪዎቹን አስጠርቶ በማነጋገር ውጥረቱን አርግበው በመመለስ በተማሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት እንደነበራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አባ ማትያስ ግን የተማሪዎቹን ድምፅ እንኳን ለመስማት ፈቃደኛ ባለመሆን ጭምር “እኔ የሁሉም አባት ነኝ፤ ሁሉንም ያለአድልዎ በእኩል አስተናግዳለሁ” ሲሉ ከጥቂት ወራት በፊት የገቡትን ቃል በተግባር ማሳየት ተስኗቸው ታይቷል፡፡ እንኳን  ችግሮችን ለመፍታት ተሰልፈው ወደቤተክህነት የመጡትን ተማሪዎች ሌላው ቢቀር ሰው እንኳን መድበው ጥያቄያቸውን ሊሰሙ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ ይህም ሁኔታ ከሌሎች የውስጥ ችግሮች ጋር ተደማምሮ የስልጣን ዘመናቸውን ፈታኝ ያደርገዋል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ እርሳቸው ግን ማቅን ከያዝኩ ማንም አይነካኝ ያሉ ይመስላል፡፡

8 comments:

 1. Pop Mathias : he is old p/c leave him alone !

  ReplyDelete
 2. ፅጊቱ ንዴቷን አስነካችው::

  ReplyDelete
 3. hhaahha aba matyas is not comfortable for distributing your nufake unlike aba poulos. you have no hope.

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር እንደ ሰዉ አድሎዋ ፍርድ የማይሰጥ ደግ ጌታ ነው። አባ ማትያስ ግን በአደባባይ የተሰጣቸው የእግዚአብሄር ታላቅ ክብር ዝቅ በማድረግ ለሰው ክብር በማለት ያደረጉት ልበ ደንዳናናት ህዝቡን እንዳሳዘነው እያየን ነው። አዲስ የጀመሩት ከማቅ ጋር ያለው ፍቅር ምናልባትም ምስጥራቸውን ዘርፈው ነገ በአደባባይ እንዳይበትኑባቸው ብጠነቀቁ ይበጃቸዋል። ለኮሌጁ ተማርዎች አንኳን እግዚአብሔር አምላክ በጥቅቱም ብሆን ድምጸችሁን ሰማችሁ አንላለን

  ReplyDelete
 5. aba selamawoch..... tut nekashoch.........nachihu.......yesirachihun ......yistachihu...

  ReplyDelete
 6. ይህ ድኅረ ገጽ እጅግ ተመስጋኝ ይሆናል ምክንያት ችግሩን መንሥኤውን እና መፍትኄውን አቀናብሮ ያቀርባልና ነው። እውነት ችግር ፈጣሪው ጳጳስ ካስተዳደሩ
  ተወግደው ከሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ ነፍስ ዘርቶበታልና በዚያው ሐቅ እንዲቀጥል ይበረታታል።(እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ያድሯል)ነውና በተረፈ ሥልጣንን ለማሰንበት
  በሰዎች መመካት ከድጡ ወደማጡ ነው (ወይከውን መንግሥት ለእግዚአብሔር)
  ሥልጣን ለእግዜር እንጂ በሰው ትክሻ የሚከናወን አይዶለምና ሐቅን ያዙ ከእርሱ ጋር
  ተጓዙ!

  ReplyDelete
 7. Abune Matiyas ewnetegna menekos nachew...tehadiso gudu fela libona yistachihu

  ReplyDelete
 8. ውስጥ አዋቂ__ሰላም ሰላማዎች በቅድሚያ መቸኮል ጥሩ አይደለም ታላቁ አባት ፓትርያርክ አባ ማትያስ ከሚታወቁበት ዋናው መገለጫ ባህርያቸው አድልዎ ለእግዚአብሄር ውስጣቸው ስላለ ቅድሚያ ለቅድስት ቤ/ን ሲሰጡ እንጂ ለሰው ሲሰጡ ሰምተን አናውቅም ምናልባትም ላለው እውነታ ቅድሚያ ሰጥተው ይሆናል ያም ሆነ ይህ ፓትርያርክ አባ ማትያስ ለተዋህዶ ሃይማኖታችን በሰው ወይም እንደ ሰው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የተሰጡን ታላቅ መንፈሳዊ አባት ሰለሆኑ ብንጠቀምባቸው መልካም ነው ። ከላይ አንድ መናፍቅ ለሰጠው አስተያየት መመለስ ግድ ይለኟል በአደባባይ የተሰጣቸውን የእግዚአብሄርን ክብር ካልክና ከእግዚአብሄር መሆኑን ካወክ ፓትርያሪኩን ሳይሆን የቀባቸውን መንፈስ ቅዱስ እንደዘለፍክ ልታውቅ ይገባል ቅዱስ መጽሃፍ ካነበብክ የተሳደበ በንስሃ ይሰረይለታል መንፈስ ቅዱስን የተሳደበ ግን አይሰረይለትም ይላልና ስለዚህ ተሳስተሃልና ንስሃ ግ።

  ReplyDelete