Monday, July 22, 2013

የተሐድሶ እንቅሥቃሴና አስፈላጊነቱ

ተሓድሶ ማለት የፈረሰውን መጠገን ያዘመመውን ማቅናት የቆሸሸውን ማጽዳት ማለት ነው። አንድ ቤት እድሜው ሲረዝም ሊያዘም ወይም ውበቱ ሊጠፋ ይችላል። እንዲህ ዓይነቱን ቤት፤ ያለውን ይዘትና ቅርጽ ሳይለይቅ እንደገና ማደስ፤ መጠገን፤ ማሳመር ማደስ ይባላል። እያንዳዱ ፍጥረት ተሃድሶ የሚያስፍልገው ሆኖ ነው የተፈጠረው። ግኡዝ አካል [ማቴሪያልም] ይታደሳል፤ ለምሳሌ ብረት ሲዝግ ወደ እሳት አስገብተው ሲጠራርቡት ብረትነቱን ሳይለቅ አዲስ ይሆናል። ኅብረተ ሰብእ፣ ማህበር፣ መንግስት የመሳሰሉት የሰው ልጅ የጋራ ግንኙነቶችም እንደ ጊዘው ሁኔታ ይታደሳሉ። የማይታደስ ነገር ጨርሶ ከመጥፋት አይድንም። የማይታደሰው አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
  ቤተ ክርስቲያንም ተሐድሶ ያስፈልጋታል፤ ተሐድሶ እጅግ በጣም ከሚያስፈጋቸው ተቋማት መካከል የእግዚአብሔር ቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ናት። በዓለም ውስጥ ከዓለም ተለይታ የምትኖር የጌታ ቤት በመሆኗ በየጊዜው እራሷን ማየት፤ በጌታ ቃል ሕይወቷን መመርመር ይኖርባታል። ይህች ቤት በዚህ ሰይጣን በሚገዛው ክፉ ዓለም ውስጥ የምትኖር ስለሆነ የዓለም ርኩሰት ሊገኝባት ይችላል፤ የዓለም ፍልስፍና ወይም ርእዮተ ዓለም ገብቶባት ሊሆን ይችላል፤ የስይጣን አሠራር እና እውነት የሚመስል የአጋንንት ትምህርት ሾልኮ ገብቶ ሊሆን ይችላል፤ ጥንቆላ እና መተት ሰማያዊ ታምራት መስለው ተቀላቅለው ሊገኙ ይቻላሉ፤ ሥጋዊነት፣ ዓለማዊነት፣ ገንዘብን መወደድ፣ ሥልጣንና ሹመት ፍለጋ፣ ስግብግብነት፣ ሞልተውባት ሊሆን ይችላል፤ ጥላቻ፣ ስድብና እርግማን፤ የርስ በርስ መነካከስ፣ ዘርኝነት፣ ስንፍና፣ ሊኖር ይችላል፤ እራይ አልባ ሆና ስኬት ርቋት ሊሆን ይችላል፤ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲገኙ ነገር ተገለባብጧል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን ወደ ዓለም ገብታ ዓለምን መቀደስ ሲገባት፡ ዓለም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ርኩሰቷን ፈጽማለች ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያንን ከዓለም መለየት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሰን እያየነው ተሐድሶ አያስፈልገንም ማለት የሚያስገርም ነው።
 አምልኮ ሊኖር ይችላል፤ ሥራት ባግባቡ ሊፈጸም ይችላል፤ ይህ ግን ቤተ ክርስቲያን ሰላም መሆኗን የሚያሳይ ዓይደለም። የተለመደ ነገር ማድረግ ለሰው ቀላል ነውና ሁሉም ሲደረግ ልናይ እንችላለን፤ እውነቱን ስንመለከተው ግን ቤተ ክርስቲያን ከሞላባት እድፍ የተነሣ ወደ ፊት መራመድ አለመቻሏ ነው። የእግዚአብሔር ቃል  ነውር የሌለበትና ንጹሕ አምልኮ የሚለው ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እና ባልቴቶችን በመከራቸው መጠየቅ፤ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ እራስን መጠበቅ ነው። ያዕ 127 ቤተ ክርስቲያን በዓለም ከሚገኝ እድፍ እራሷን እየጠበቀች ዓይደለም። በዓለም ውስጥ የሚገኙ ከንቱ ነገሮች ሁሉ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገኛሉ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሌለ ኃጢአት ምንም የለም። የእግዚአብሔር ጠላቶች የሚፈጽሙት በደል ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል። ተሐድሶ በሁለት አቅጣጫ የሚደረግ ነው።
1 የሕይወት ተሐድሶ
 የሕይወት ተሐድሶ እያንዳዱ ሰው በግሉ የሚፈጽመው ተግባር ነው። ይህም ንስሐ መግባት፣ ኃጢአትን መናዘዝና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ መውጣት ማለት ነው፤ ኃጢአትን የሚያደርግ የኃጢአት ባሪያ ነውና ከማነኛውም ኃጢአት ነጻ መውጣት ተሐድሶ ይባላል። በሐዲስ ኪዳን የተሐድሶ እሳትን በምድር ላይ ያቀጣጠለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ተሐድሶን ለሕይወታችን ሊሰጠን ይፈልጋል። "ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛል ለታሠሩት መፈታትን ለእውሮች ማየትን እሰብክ ዘንድ የተጠቁትን ነጻ አወጣ ዘንድ፤ የተወደደችውን የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛልይላል። ሉቃ 419 ተሐድሶ ማለት ከእስራት መፈታት፤ እንደገና ማየት፤ ከተጠቃንበት የዲያብሎስ መውጊያ ከኃጢት፤ አርነት መውጣት ማለት ነው።
  እግዚአብሔር ለቅድስና ጠርቶናል፤ ከዓለም እንድንለይና ወደ ዓለም እንድንገባ ልኮናል። የተሐድሶ ዋና ዓላማው ቅድስናን ለማምጣት ነው። የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ከመነሣታችን በፊት የሕይወት መታደስ ያስፈልገናል። ያለ ቅድስና ምንም ነገር ማከናወን አይቻልም። በብሉይ ኪዳን ታዋቂ የተሐድሶ መሪዎች እዝራ እና ነህምያ ነበሩ። የኢየሩሳሌምን ቅጥር ለመሥራት ከመነሣታቸው በፊት ኃጢአታቸውን በመናዘዝ የሕይወት መታደስን አግኝተዋል። ሥራ የሚሠራው በእግዚአብሔር ሞገስ ነውና ሞገስን አግኝተዋል።
"አምላካችንም ዓይናችንን ያበራ ዘንድ በባርነት ሳለን ጥቂት የሕይወት መታደስ ይሰጠን ዘንድ ለጥቂት ጊዜ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ሞገስ ተሰጥቶናልይላል እዝ 98 ዛሬም እኛ የሕይወት መታደስ ያስፈልገናል። ዋናው የተሐድሶ እንቅሥቃሴ አለማ ይኸው ነው።
 2  ትምህርታዊ ተሐድሶ፤
የእግዚአብሔር ቃል ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ጸንቶ የሚኖር የሕይወት ቃል ነው። ይህ የእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ይገኛል። መንፈስ ቅዱስ በሰዎች አድሮ ስለተናገረው እና ስለጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ዘመናት በተለያዩ ሰዎች የተጻፈ ሲሆን ሐሳቡ አንድ ነው። በተለያየ ቋንቋ በተራራቀ ጊዜ ተጽፎ የሐሳብ ግጭት የሌለበት ድንቅ መጽሐፍ ነው። ዓለም አቀፉ መጽሐፍ ቅዱስ 66 ሲሆን በኦርቶዶክስና በካቶሊክ ግን የተለያየ ቁጥር አለው። ይህን ጉዳይ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። "እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነውእንደተባለ ሮሜ 1017 እምነታችን እና ተግባራችን አምልኮአችን፣ ጸሎታችን ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት። ይህን የምንለው የእግዚአብሔር ቃል ያልሆነ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል ተደርጎ ዘወትር የሚሰበክ የስሕተት ትምህርት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ስለሚገኝ ነው። ዘጠና ከመቶ የሚሆነው የቤተ ክርስቲያናችን ሕዝብ የዚህ የስሕተት ትምህርት ተከታይ ነው። በዚህ የስሕተት ትምህርት ምክንያት የሕዝቡ ሕይወት በሚከተሉት ውድቀቶች ውስጥ ይታያል።
ሴተኛ አዳሪው፤ ወንደኛ አዳሪው የቤተ ክርስቲያናችን አባል ነው። በሀገሪቱ ተንሰራፍቶ የሚገኘው ባዕድ አምላኪ ጠንቋዩ፣ መተተኛው፣ ደብተራው፣ ሟርተኛው ሁሉ የቤተ ክርስቲያናችን አባል ነው። ሌባው ሀገሪቱን በዘርኝነት በሙስና እና በቅሚያ እያመሰ ያለው በአብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን አባል ነው። በጥላቻ በበቀለንኝነት እርስ በርስ ለመገዳደል እየተጠባበቀ ያለው ከወጣት እስከ ሽማግሌ ያለው ትውልድ በአባዛኛ የቤተ ክርስቲያናችን አባል ነው። በልመና እና በሥራ ፈትነት በማታለል ሥራ ተሰማርቶ የሚገኘው በአብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን አባል ነው። ክርስቲያን ነኝ ለሃይማኖቴ ቀናተኛ ነኝ የሚለው ክፍል ደግሞ የሚያመልከውን የማያውቅ ወደ ተለያዩ ነፍሳት የሚጸልይ መናፍሳታዊ ታምራትን የሚከተል ለምስል እና ለስእል የሚሰግድ የፕሮፓጋንዳ ስብከቶችን የሚቀበል አስቸጋሪ ክፍል ነው። ለዚህ ዋና ምልክቱ ሃይማኖቴ ለሚለው ባዕድ ነገር ሲንበረከክ ከመኖር ውጭ የጌታን ሥጋ እና ደም ለመቀበል ዝግጁ አለመሆኑ ነው። ሕዝባችን የመናፍስታዊ ታምራቶች ተከታይ እንጂ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ዝግጁ አይደለም።
  ከዚህ በላይ ያየነውን ጎምዛዛ ፍሬ በሀገሪቱ ላይ ያፈራው ሁልጊዜ እየተዘራ ያለው የስሕተት ትምህርት ነው። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዳለ ጌታ ሕዝባችን ትክክለኛ እምነት የሌለው መሆኑን ለማወቅ ክርክር ሳያስፈልግ ፍሬውን ማየት ነው። ትክክለኛ እምነት ትክክለኛ ሥራ ያስገኛል እምነት ያለ ሥራ የሞተ ነው እንደተባለ ደብተራዎቻችን የሚሰብኩት የሞተ እምነት አገሪቱን በሙታን ሞልቷታል። የግብጽን ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የጌታን ሥጋና ደም የማይቀበል አማኝ የለም። የጌታ ሥጋና ደም ቀርቦ ተቀባይ አጥቶ የሚመለስበት ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ቢኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት። ይህ የስሕተት ትምህርቱ ውጤት ነው።
ለምሳሌ፤  ሰባ ስምንት ነፍስ የገደለው ሰው እግዚአብሔርን ክዶ ማርያምን በማመኑ የዘላለም ሕይወት አገኘ የሚለው ትምህርት እንደ እራሱ እንደ ሰውየው ነፍሰ ገዳይ የሆነ ትምህርት ነው። ሰውየው ነፍሰ ገዳይ ነበረ ታሪኩም እስከዛሬ እየገደለ ነው፣ እሱ በጁ ከገደላቸው ይልቅ ታሪኩ የገደላቸው ወገኖችችን በዝተዋል። ሰውየው ለጥቂት ወደ ሲኦል ሊገባ ሲል ማርያም አማላደችው እግዚአብሔርም መፍረዱን ትቶ ሚካኤልን በማርያም ስም የተሰጠውን ውሃና ሰባ ስምንቱን ነፍሳት መዝንልኝ አለው፤ ነፍሳት እየከበዱ ውሃው እየቀለለ መሄዱን ያየችው ማርያም ሮጥ ብላ በውሃው ላይ ጥላዋን ጣለችበት በዚህ ጊዜ ከማርያም ጥላ የተነሳ ውሃው ክብደት በማሳየቱ ነፍሰ በላው ወደ ገነት ተዛወረ በማለት ይተርካል። በሰማይም ሙስና አለ እንዴ? ያሰኛል። ይህን የሙስና ትምህርት ጸረ ሙስና ኮምሽን ቢያውቀው ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊያስከስስ የሚችል ነው። እንደዚህ ዓይነቱ ትምህርት ነው ሚዛን  የሚያዛባ ትውልድን የፈጠረው። ስለዚህ ይህንና ይህን የመሳስሉ ትምህርቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር አደገኛ ግጭት ውስጥ ስለሚገኙ መጠረግ እና መቃጠል ይገባቸውል፤ ትምህርታዊ ተሐድሶ ማለት ይህ ነው። በእግዚአብሔር ቃል የተመራ ተሐድሶ ያስፈልገናል። በዚህ አጋጣሚ በተለያየ ማህበር ተደራጅተው የተሐድሶ እንቅሥቃሴውን እያቀጣጠሉ ያሉት ውድ ኦርቶዶክሳውያን ታሪክ የማይረሳቸው የኢትዮጵያ ባለውለታዎች ናቸው። ተራራ መስሎ አይነኬ የሆነውን የዘመናት እዳችንን ከላያችን ላይ አንከባለው ወደ ጌታ ብርሃን ዘወር እንድንል የረዱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው።  ታሪካቸውንም ወደፊት በመጽሐፍ አዘጋጅቶ ለትውልድ ማስተላለፍ አስፈላጊ ነው።
ተስፋ ነኝ  

9 comments:

 1. 1. በመጀመሪያ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስር ላሉ ምዕመናን አትጨነቁ ይህ የቤተክርስቲያንዋ ሥራ ነው፡፡ እናንተ አንደኛችሁን ለምን ዶግማና ቀኖና አውጥታችሁ በዚህ ተመሩ አትሉዋትም፡፡ በመጀመሪያ እራሳችሁን ከገባችሁበት አዝቅት አውጡ፡፡ ሁኔታችሁ ሁሉ እንደ ፈሪሳውያን ሆነ፡፡ እኔን አዳምጡኝ ስትደመጡ ባዶ ልፍለፋ፡፡ እስቲ እናንተ ንሰሃ ግቡ አርፋችሁ ተቀመጡ፡፡ በባዶ አትጩሁ፡፡ የሌላውን ሰው አትዩ፡፡ለምን እንደምትጮሁ ታውቃላችሁ ባዶ ስለሆናችሁ ነው፡፡ የራስዋ ሲያርባት የሰው ታማስላለች አይሁንባችሁ፡፡ ለጅብ ለመስጠት የምትሮጡ ባንዶች አርፋችሁ ተቀመጡ፡፡
  2. ንጉስ ሰሎሞን እግዚአብሔርን ትቶ ወደ ጣኦት ፊቱን ቢያዞር ስለአባትህ ስለ ዳዊት ስል መንግስትህን አንተ ባለህበት ዘመን አልከፍልብህም ዙፋንህንም አላሳጣህም አለው፡፡ ለካስ ከንጉስ ዳዊት ጋር እግዚአብሔር ባለው ግንኙነት ልጁ ሊድን ችሎዋል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር አሰራር ነው ልንቃወም አንችልም፡፡ ይሄንጊዜ እናንተ ብትሆኑ እግዚአብሔር ያዳላል እንዴ ትሉ ነበረ፡፡
  3. በማቴ. 10. 41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
  42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።
  ከዚህ በላይ ቃል ኪዳን ምን አለ፡፡ ዋጋው አይጠፋበትም በቃ አራት ነጥብ፡፡ እናንተ የእመቤታችን ስም ለምን ተጠራ ስለሆነ ገና ለዘለዓለም ትጠራታለች፡፡ ምነው እናንተ አንድ ሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን አጥላልቶ የሚያወጣውን ጸሐፊ አስር ጊዜ አይደል እንዴ የምታወድስት ስሙንም የምታነሱት፡፡ ስለቃሉ የታመነ አምላክ ባደረገ ጌታ ሙስናን አስፋፋ ልትሉት ነው፡፡ የናንተ ችግር በስጋ ስላላችሁ ነው፡፡ በመጀመሪያ መንፈሳዊ ሁኑ፡፡ ቀስ ብላችሁ ለምን ጌታ በመስቀል ላይ ያለውን ቁዋንጃ ቆራጭ ስንት ወንጀል የሰራውን ሌባ ገዳይ ለምን እንዴት ማረው ሳትሉ አትቀሩም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዚህ መልስ ሰጪ የወንጌልን ቃላትና ትዕዛዛት ለምን ለሙታን ቅዱሳን እንደሚሰጥ አይገባኝም። እነሱ እኮ ተጋድሎአቸዉን ጨርሰዉ በጌታ ዘንድ ናቸዉ። ስለዚህም በነሱ ስም የሚደረግ ነገር አይፈልጉም። በተሰጣቸዉ ጸጋ የሚፈለግባቸዉን ጨርሰዉ የድል አክሊል ተቀዳጅተዋል። በዚህ በተሳሳተ ትምህርት ብዙ የተዋህዶ ልጆች እየተወዛገቡ ነዉ። ጉዳዩ ግልጽ ሆኖ እያለ ለምን ሊገባን እንዳልቻለ ይገርመኛል። ጌታ የተናገረዉ ሁሌም እያገለገሉተ ስላሉት ነዉ። እነዚህ አገልጋዮች ወንጌልን ለማስፋፋት ከኛ የሚጠብቁት ብዙ ድጋፍ አለ። እነሱም ነብያት ቅዱሳን ጻድቃን ተብለዉ ነዉ የሚጠሩት። እንክዋን እነሱ ይህ ቅጽል ለኛም በቸርነቱ ተሰጥቶናል ስ።ለዚህም በሕይወት ስለሌሉት አገልጋዮች የታዘዘ አይደለምና ቢስተካከል እላለሁ።

   Delete
 2. Wow! I did not know Thadesso was like this. I thought it meant being Pente. We got to do away with a lot of misinformation out there. Well written and to the points. Congratulations! God bless you. I found this blog by accident and was lucky.
  Thanks!

  ReplyDelete
 3. The first guy who commented on this is pitiful. He threw the ball @ the writer with no substance. The writer did not write this to blemish our Mother Mercy. The writer intention was to stress the importance of Thadesso for todays Ethiopian Tewahido Church. Yes there are a lot of mystifications that are contradicting the dogma. Therefore, reformation is not an option it is a necessity. Our mother The Immaculate Saint Mary cheers Thdesso and Tesfa.

  ReplyDelete
 4. Hod siyawuq doro mata

  ReplyDelete
 5. the first thing you must know , no one can understand teaching of the holy church unless he is part of the church,the body of Christ. which is nourished by her Master. If you remember what St. Athansious said about arians,heretics, we believe in order to understand,but they want to understand in order to believe. I think it is better for you to examine your way .

  ReplyDelete
 6. AnonymousJuly 23, 2013 at 5:05 AM yeayet meseker debet.negerun ewenet lemasemesel erasacehu tesefalachu aydel?ewnetegaw metehaf 66 new kemalet lela men penta net ale."bemoralem behayemanotem bemegebarem yegosekelachu nacehu>long live mkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk.

  ReplyDelete
 7. Tesfa, God Bless you for ever, Kale hiwot yasemalen. Tebarek!!!

  ReplyDelete