Saturday, July 6, 2013

በነጻነት አገር ነጻነት አጣን

 
ውድ አባ ሰላማዎች ይህችን መልእክት በካሊፎርንያ ግዛት በሳን ሆዜ ከተማ ለሚገኙ ምዕምናን አስነብቡልኝ። 
ታዛብ ከሳንሆዜ ካሊፎርኒያ
 
 በዚህ ዘመን ያለን ኢትዮጵያዊያን በአጠቃላይ የባሕሪያችን ጽመት ጎልቶ የወጣበትና እርስ በራሳችን ተቻችለን የማንኖር አስቸጋሪ ሰዎች መሆናችን የታየበት መጥፎ አጋጣሚ ቢሆንም በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ በተለይ ብዙ ወንድሞች “ማኅበረ ሰይጣን” ብለው የሰየሙት ድርጅት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረው ትርምስ በቃላት ሊገለጽ የሚችል አይደለም። ጳጳሳት በገንዘብ ተገዝተው ክብራቸውን አዋርደዋል፤ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ሰዎችም ለይቶላቸው የማኅበሩ አገልጋይ ሆነው ተቀጥረዋል። ለእውነት የቆሙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተሰደዋል፤ ወይም አፋቸውን ለጉመው ተቀምጠዋል። ቤተ ክርስቲያንችን በርካታ ልጆቿን አጥታለች። ማኅበሩን ያልተቀበለ ወይም ለማኅበሩ እውቅና ያልሰጠ ኦርቶዶክሳዊነቱን ይነጠቃል። መናፍቅ የሚል ታርጋ ይለጠፍለታል። ችግሩ አሁንም መቋጫ አልተገኘለትም። በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው አጠቃላይ ውድመት ወደፊት በጥናት የሚረጋገጥ ይሆናል።  
ለልዩ ተልዕኮ እያሰለጠኑና ለማኅበሩ ታማኝነታቸውን የሚያረጋግጡበት የቃል ኪዳን ምልክት በአንገታቸው ላይ እያጠለቁ የሚልኳቸው የክርስትና መንፈስና ኢትዮጵያዊ ለዛ የሌላቸው ወጣቶች በየቦታው በሚፈጥሩት ሁከትና ሽብር የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ታውኳል። በየቤተ ክርስቲያኑ ጤናማ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም።

በሳን ሆዜ ከተማ አሁን ያሉት አብያተ ክርስቲያናት 4 ሲሆኑ ከመጀመሪያ የነበሩት ሁለት ብቻ ናቸው። አሁን ደብረ ይባቤ ቅዱስ ገብርኤል የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ከራማ ቅዱስ ገብርኤል ሲከፈል ምክንያቱ የዚህ ማኅበር አባላት ነበሩ። እንደሚታወቀው በሰሜን አሜሪካ አንዱን ቤተ ክርስቲያን ጣኦት ሌላውን ታቦት እያደረጉ የሕዝቡን ሥነ-ልቡና መረበሽና ቤተ ክርቲያንን ከሁለት መክፈል የማኅበሩ አባላት የሰለጠኑበት ሙያቸው ነው። አዲስ ነገር ፈጥሬ እያወራሁ ከሆነ የደረሰባችሁ ምስክሮች ናችሁ። በገብርኤል ላይ ሌላ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከከፈቱም በኋላ በዚህ አልረኩም። የአዲሱ ቤተ ክርስቲያን አካሄድ እነርሱ እንደፈለጉት ሊሆንላቸው ስላልቻለ፣ ከፍተኛ ትርምስ ፈጥረው ከእነርሱ ተከፍሎ ሌላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እንድትከፈት ምክንያት ሆኑ። የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን መቀጠል አልቻለችም። ከተወሰን የአገልግሎት ጊዜ በኋላ የማኅበሩ አባላት በሚፈጥሩት ጫና ምዕመናንኑ ተበታተኑ። ከኪዳነ ምሕረት መበተን በኋላ በርካታ ኦርቶዶክሳዊያን እረኛ አጥተው የት እንደደረሱ አይታወቅም።

አንድ ቤተ ክርስቲያን ሲከፈል በምዕመናን አእምሮ የሚፈጠረው የሥነ-ልቡና ሁከት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጅ ከመጀመሪያውም አዲስ ቤተ ክርስቲያን መክፈት ያስፈለገው በልዩ መጥፎ አጋጣሚ ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ምዕመናን እንዳይበታተኑ ታስቦ ሳይሆን፣ የማኅበሩን የግል ዓላማ ለማሳካት ስለነበር በሁለተኛው ክፍፍል የተበተኑን ምዕማናን ለማሰባሰብ የተደረገ ጥረት አልነበረም። ከመሳቅና ከመዘባበት አልፎ። ከዚህ በኋላ ዓላማቸው ማኅበሩ የነገሠበት ብቸኛ ቤተ ክርስቲያን መመሥረት ስለነበር ለዚህ የሚረዷቸውን አባ ኅሩይ የሚባሉ አሁን አዲስ አበባ ሄደው እያተራመሱ ያሉትን መነኩሴ ቀጠሩ። አባ ኅሩይ ጥላቻን በማስፋፋትና ምዕመናንን በመከፋፈል የእነሩሱን ዓላማ ለማስፈጸም የሚመቹ ቢሆንም የመነኩሴው ገንዘብ ወዳድነትና ሰውን እርስ በራሱ የማጋጨት ልዩ ባሕርይ የእነርሱንም አንድነት የሚጎዳ ስለሆነ ቤታቸውን ዘግተው አውጥተው አባረሯቸው። አሁን አስተዳዳሪዎችና አድራጊ ፈጣሪዎች የማኅበሩ አባላት በመሆናቸው በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በየዕለቱ የሚፈጥሩት ትርምስ ከእነርሱ አልፎ የአካባቢውን ሰላምና አንድነት እያደፈረሰ ነው። ከላይ እንደገለጽኩት የዕነርሱ ዓላማ በአካባቢው ማኅበሩ የነገሠበት የእነርሱ ቤተ ክርስቲያን ብቻ እንዲኖር ነው። ከዚህ አንጻር በጎረቤት ያሉ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በአገልግሎት እንዳይተባበሩ እንቅፋት መፍጠር ብቻ ሳይሆን፣ የጎረቤት አብያተ ክርስቲያናትን ህልውና የሚጎዳ የጠባጫሪነት ተግባር እየፈጠሩ ሰላማቸውን ማወክ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆኗል።

ከዚህ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለረዥም ጊዜ ተባብሮ በማገልገል የምትታወቀው ከቀደምት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ የሆነችው የማርያም ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነበረች። ይህም የኅብረት አገልግሎት በብዙ አባቶች ድጋፍና ምክር ታግዞ ነው እንጅ እንከን ሳይኖርበት አልነበረም። ሆኖም በቅርቡ የማኅበሩ አባላት በፈጠሩት ችግር ሆኖ ተብሎ ገብርኤል ላይ ተደራቢ የማርያም ታቦት እንድትገባና ማሪያሞች በሚቀድሱበት በቅዳሜ ቀን ገብርኤልም ላይ እንዲቀደስ በማድረግ ምዕመናኑ እንዲከፋፈሉና አብያተ ክርስቲያናቱም እንዲለያዩ አድርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የእኛ በሚሉት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነደደው የነገር እሳት ሳይበርድ፣ ምዕመናን እየተተራመሱ፣ እነርሱ ግን መኪና የሌላቸውን የሚያጓጉዝና ስም በማጥፋት የሰለጠነ ሠራዊት አሰማርተው ሰፈር ለሰፈር በመዞር ከደብረ ይባቤ ቅዱስ ገብርኤል ውጭ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት የመናፍቃን ናቸው፤ አትሂዱ እኛ ራይድ እንሰጣችኋለን እያሉ የሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን መቀማት ወይም ምዕመናን ሂደው እንዳይገለገሉ ጫና ማሳደር ትልቁ የጥፋት ተልዕኳቸው ነው።

ለዓመታት ዝም ብለን ተመለከትን። የጥፋት ተልዕኮው የሚቆም አይደለም። ግን እስከ መቸ? መቸም ይህ ሁሉ ሩጫ የክርስቶስንና የቅዱሳን ሐዋርያትን ዓላማ ለማሳካት እንዳልሆነ ማንም በቀላሉ የሚገነዘበው እውነት ነው። ስለዚህ በዚህ ጽሑፍ የማይቻለውን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ልመና ወደ ፈጣሪ ለማቅረብ ወይም እነዚህ ለዕኩይ ዓላማ የተሰለፉ የማኅበሩ አባላት ተጸጽተውና ንስሐ ገብተው ክርስቲያናዊ ሕይዎት እንዲኖሩ ለማግባባት አይደለም። ይህ በተሞክሮ እስከዛሬ አልሠራም። መልእክቴ ለምዕመናን ነው። አንድነት እንጅ መለያየት ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝባችን አይበጅም። በፖለቲካም ሆነ በሃይማኖት የዕድገት መለኪያው ሰላምና አንድነት ነው እንጅ በርካታ ሚሊዮን ዶላር በባንክ ማካበት አይደለም። አንዱ ሌላውን የሚኮንንበት ዘመን ይብቃ፤ ለጥላቻችን ገደብ ይኑረው። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳ ሥራ የሚሠሩትን ለይታችሁ በማወቅ ራሳችሁን ነጻ አውጡ። የእናንተ ነጻነት የሁላችንም ነጻነት ነውና።  

ልዑል አምላክ ለሁላችንም ማስተዋልን ያድለን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ጸንታ ለዘለዓለም ትኑር፤ አሜን
ከታዛቢ

35 comments:

 1. Seriously these guys have gone a little too far. They need to getting stop. They have been pocking their noses in church buisness. Who give them the mandate to call some one Thadesso
  GELEMELLE? I share Tazaby's frusration, but draw some lessons from other churches like Saint Mary Church of Atlanta, Kidus Michael of Dallas, Saint Mary of Irving Texas. They have erected impermeable wall against these Taliban. MK agent and his spouse @ Houston Medhanealem tried through the youth choirs but failed. The board drastic action have saved the church from these agents and phrases and enjoyed worshiping God peacefully.

  ReplyDelete
 2. አሜን ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ይጐብኛት

  ReplyDelete
 3. wow wow wow good job and Lord God bless you brothers. This is the true and with out any doubt ...........This church right know the losing their members due to selfish MK. Our San Jose Debre Yibabe Gabreil church members use to stronger peoples, know no more. The church members number are going decreasing so fast. why? why? because they don't obey Senodos and Hagere Sebket.........The good things is so many opportunity or church in our area to join and pray to our Lord God.

  ReplyDelete
 4. የሳን ሆዜ ደብረ ይባቤ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ብዙ ችግር ጉድ ያለበት ቦታ ሆኖዋል። የአማኙ ቁጥርም በጣም እጅግ ቀንሶዋል።ምክንያቱም ለስም የፓትርያርኩን ስም በቅዳሴ ግዜ ህዝቡን ለማታለል ይጠራሉ ዳሩ ግን የኢትዮጵያን ቅዱስ ስኖዶስ የማይቀበሉ ናቸው።እውነቱ ይህ ነው
  1. አቡነ ፓዉሎስ ስሞቱ ፍታታቸው በዚህ ቤተ ክርስቲያን እንዳይፈታ ተከለከለ።
  2.በአውደ ምህረቱ ላይ ይፈታ ብለው የተናገሩት የደብሩ አስተዳዳር በተንኮል ከሥልጣናቸው እንደነሱ ተደረጉ። በዉሸት ግን ስራ ሰለበዛባቸው ነው ተባለ

  3.አሁን በቅዳሴ ግዜ የአዲሱ ፓትርያርክ ስም ይጠራሉ። ነገር ግን ስለ መሾማቸው ደብዳቤ ስላልደረሰን በአውደ ምህረት ላይ አንናገርም በማለት ይናገራል።ሁለት እርስ በርሱ የሚቃረን አስመሳይ ጉዞ። ጉድ ጉድ ነው ህዝበ ክርስቲያኑን ለማታለል የሚደረገው ተንኮል። ጉድ ነው።
  4. የጎጃም ተወላጆች እና የወሎ ተወላጆች አገልጋዮች እየተፋተጉ ናቸው ይገረማል። ኤረ የባሰወን አታምጣ እንበል
  5.አንዱ ዲያቆን የወሎ ተወላጅ የሆነው አዲሱ አስተዳዳር ሆነው ለተሾሙት አባት(የወሎ ተወላጅ} እንዲህ በመላት በዐዉደ ምህረቱ ላይ ደስታውን ገልጾ ነበር። አሁን ገና ትክክለኛ አባት አገኘን በማለት የጎጃሙ ተወላጅ የሆኑትን የቀዱሙት አባት ግን ጥሩ አለመሆናቸው በመወረፊ ተናገረ። ኤረ ገና ብዙ ጉድ እየተፈፀመ ነው ወደፊት በመረጃ የተደገፈ እናቀርባልን።


  ReplyDelete
 5. "Mahebere Kidusans" are the replica of the Medieval Spanish Inquisitors. They believed that they had some power vested on them to harass and to intimidate the true Tewahido clergies and lejoch. They will go down my friends! because they are loosing it now.

  ReplyDelete
 6. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ጸንታ ለዘለዓለም ትኑር፤ አሜን::
  But aba selama website is "yemenafikan new"

  ReplyDelete
 7. ሽብር ፈጣሪዎች(የበግ ቆዳ ያንከረፈፉ)በዘመናችን እውነተኛውን መንጋ ለማስበርገግ
  የገበሬ አስደንግጥ ሤራ በመሸረብና በመጐንጐን በውጭ በውስጥ ሽር ጉድ ሲሉ
  ይስተዋላሉ በፈጣሪ ሥልጣን ገብተው እኛ እንፍረድ ወደማለቱም ተቃርበዋል። ይህም
  ለመጥፊያቸው የዋዜማ ዋዜማ ነው የስልምና አክራሪዎች በባድ ላይ የጠነሰሱት በራሳቸው
  ዘመድ ላይ የመከራ ገፈት እየሆነ ይታያል በመሆኑም ለተጠቀሰው ማኅብር አባልና
  ተከታይ ባልሆንሁ የሚባልበት ዘመን የራቀ አይሆንም በጎቹ ግን በተኩላዎቹ ምክንያት
  ከቤተ ክርስቲያን መገለል አይገባቸውም።

  ReplyDelete
 8. ሽብር ፈጣሪዎች(የበግ ቆዳ ያንከረፈፉ)በዘመናችን እውነተኛውን መንጋ ለማስበርገግ
  የገበሬ አስደንግጥ ሤራ በመሸረብና በመጐንጐን በውጭ በውስጥ ሽር ጉድ ሲሉ
  ይስተዋላሉ በፈጣሪ ሥልጣን ገብተው እኛ እንፍረድ ወደማለቱም ተቃርበዋል። ይህም
  ለመጥፊያቸው የዋዜማ ዋዜማ ነው የስልምና አክራሪዎች በባድ ላይ የጠነሰሱት በራሳቸው
  ዘመድ ላይ የመከራ ገፈት እየሆነ ይታያል በመሆኑም ለተጠቀሰው ማኅብር አባልና
  ተከታይ ባልሆንሁ የሚባልበት ዘመን የራቀ አይሆንም በጎቹ ግን በተኩላዎቹ ምክንያት
  ከቤተ ክርስቲያን መገለል አይገባቸውም።

  ReplyDelete
 9. God bless you !!!

  ReplyDelete
 10. ''Let him who does wrong continue to do wrong; let him who is vile continue to be vile; let him who does right continue to do right; and let him who is holy continue to be holy.'' (Rev 22:11)

  Brother! lets keep doing our own part and God is faithful to keep his promise for His faithful children.

  God bless you

  Selam

  ReplyDelete
 11. እነ ሙሉጋኔን ደሞ በእንዲህ አይነት ስም መጥፋት መጣችሁ? አይ የጋኔን መጫወቺያ!

  ReplyDelete
 12. Tiru Tizebet nwu. Mekefafel sayehon 1 mehon yeshalenal lehulachin'm Ergit yemahiberu abalat aberochewu yaletegazewun Tarega yeletefubetal....meweyayet yesefelgal ....Tazabiwu adderes yetewuna weyem behon menged bakababiwu yalen enwuyayebet elalehu .
  fetehanegest
  san jose

  ReplyDelete
 13. Betam Yigermal Yasazinal Yihe Cheger Behulum Bota Yale New Leka Hmmmm Ene Beminorebet Be Germen Frankfurt Mk Abalat kehonut dikunaw sayegebachew minunim tensehu sayechelu diyakon yibas belew wetader ena majerat mechi yenberu sew ayawekeneim belew kihenetun achbereberw agegnetewal gin andim ken kedesewena agelgelew ayawekum yibas belew betekersteyanin eyekefafelu meemenun eyaweku kahenun eyesdebu gena yalegebachew tikit meemenan asketelew biguazum alekenachewem hizebe kiresteyanum nekitobachewal kalarefum ermeja yiwesedebachewall wendemoche belela gize betshuf elkelachewalew betekiresteyan enzhin 1 litel yasefelegal

  ReplyDelete
 14. ante bemar yetelewesh merz man new yelakeh meche new ebakih leametat zim yalachihut? ma/kidusan gena lebetekirstian yitagelal min tihonu yilk nisha gibu

  ReplyDelete
 15. you have the right to exercise your OWN religion at your OWN worship area; you do not have the right to dump your 'rubbish belief practices' on another worship areas to which you do not belong. that is the difference which you want to confuse readers. today we encountered a problem by protestant extremists that need to dump their rubbish western traditions on the Ethiopian orthodox doctrine as a part of neo- colonialism. the neo colonialists use several disclosed and undisclosed means to achieve their objectives, among other things, deploying some slaves/tehadisos who are recruited from inside and paid large amount of money for the mission.but, everybody seem to be aware of this devil thinking and is fighting against it. with the help of GOD, JUSES, WE CAN WIN

  ReplyDelete
 16. ጸሓፊው ይህን መልዕክት ስታስተላልፍ አንድም ቤተ ክርስቲያንን በትክክል ባለማወቅ ወይም በጎጥ አለበለዚያም በማይጠቅምህ አጉል ጥላቻ የተዋጥክ ትመስላለህና በመጀመሪያ ራስህን በትክክል መመርመር ስትጀምር እውነቱን ስለምታገኘው እዚይ ላይ በርታ። ለመሆኑ አንተ የምትኖርበት አካባቢ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አፍራሽ ካህናት የሉም ብለህ ታምናለህ? ይህንንም በቅጡ ተመልከተው። መቼም እውነትን ለማየት ከእግዚአብሔር ነውና ይህንንም ተለማመደው። በስድብ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቓሪ መምሰል ያልሆነ ግምት ላይ ይጥልሃልና እንዲሁ መጻፍ ስለፈልግክ ብቻ አዋቂነትን አይገልጽም ስልዚህ ጊዜህን በከንቱ አታጥፋ።

  ReplyDelete
 17. Tehadiso protestants, we know what you want. you will never succeed .but devil will never stop fighting our church, we feel sorry for those who are serving the devil .

  ReplyDelete
 18. Tehadiso protestants we know what you are dreaming but you will never succeed. Pls don't be slaves for the devil

  ReplyDelete
 19. Some are realy pathetic when they criticize the writer. He wrote exactly what had happened in many churchs aswell.
  I did not know what this so called MK were up to? They acted up like the were butlers in Heaven. Enough Said!
  Glory to our Medhanealem!

  ReplyDelete
 20. The person who wrote this article is clearly jealous and has no idea what is really going on at Gabriel church. I know the church for long time, and I have never seen such marvelous service every Sunday like any other place in the USA. The priests and the people who serve this church are true Ethiopian Orthodox Church followers and I am amazed with their energy and passion for their belief everyday. Whoever wrote this article is a true enemy of the church and will be exposed his or her true face when time comes up. Other than that, we know that this church has many enemies from the beginning, and we all know they all fell in their face, and the church still survived and blossomed through the years

  ReplyDelete
 21. You guys who follow" Mahebere Kidusan" are like those who followed Reverend Jim Jones and David Korosh of Texas. We all ought to pray for you so you will come to your senses. Bless your heart!

  ReplyDelete
 22. The person who wrote this article wasn't jealous without any doubt, but he wrote the truth of what is going on the that church by Mk supporters.our church members must understand how Mk members playing the game in our community.Honestly today this church is on crisis. All church members are quietly watching the MK game...........
  God bless our church and members.....

  ReplyDelete
 23. ታዛቢ ከሳንሆዜJuly 14, 2013 at 10:09 PM

  ጳውሎስ ኞኞን የስፖንጅ ፍራሽ ደም ይመጣል አሉ ቢሉት ይህ የሳር ፍራሽ ነጋዴዎች ወሬ ነው አለ! ይህ በውኑ የሰላማዊ ሰው አስተያየት ትዝብት አይደለም። እኔም ጸሃፊውን ታዝቤዋለሁ። እናንተም ብትሆኑ በአባ ሰላማ ስም እባካችሁ የሰላም ወሬ አውሩ። በፍጹም የአባ ሰላማ ልጆችም ሰላማውያንም አትመስሉም። ስሙን እና ለጭንብልነት ፎቶዎቻቸውን ለጠፋችሁ እንጅ እናንተ የአባ መልኬ ልጆች ብቻ ናችሁ። የአባ መልኬና ደቀ መዝሙራቱ ቅንቀና ዜማውና ቀኝቱ በደንብ ይታወቃል። ይህ ለእናንተ አገልግሎት ቢመስልም ይህ ብሎግ የመናፍቃን ዋሻ መሆኑ እሙንና ግልጽ ነው። ሌላው ታዛቢ ነኝ ከሳንሆዜ

  ReplyDelete
 24. for God sack leave us aloneJuly 14, 2013 at 10:47 PM

  first of all thanks God! secondly it make us even stronger than ever. Yes, you guys should have Feared because the biggest Event coming up next month for Sunday School IN San Jose Debre Yibab Kulbe Gebrial from all over the United States. the distraction you guys trying to make it doesn't last a week....honestly talking i just laugh by reading this article because it seems like kids playing with a fire... we are not strong enough but our strength is only God that is why every Evil have fear for us because we have a SON of Saint Virgin Marry that is all nothing else.... i feel sorry who ever wrote this article Holly God have Marcy On You and YOUR family!!! My God keep us Strong and let evil continue talking about us because we are the winers Son we don't distract by any of these because we have more work to do... DINIGLE Atleyen Amen!!!

  ReplyDelete
 25. አፍ ሲያመልጥ እራስ ሲመለጥ አይታወቀም አሉ እሰኪ ማስተዋሉን ያድለን።

  ReplyDelete
 26. አፍ ሲያመልጥ እራስ ሲመለጥ አይታወቀም አሉ እሰኪ ማስተዋሉን ያድለን።

  ReplyDelete
 27. ጎበዝ የምንናገረው የሰማይን አምላክ በመፍራት ቢሆን መልካም ነው የሀሰት ጦር በቤተክርስቲያን ላይ መስበቅ ተገቢ አይደለም ቤተክርስቲያኑን በቅርብ ስለማቀው ለስም ማጥፋታችሁ ሎቱ ስብሃት ብዬላችኋለሁ የምትሉት አንድም ፍሬ የለውም ቤተክርስቲያን ድሮም ነበረች ዛሬም አለች ወደፊትም ትኖራለች የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አንድ ሲሆኑ ያየነው ሳን ሆዜ ነው በመልካም ነገር ደስተኛ ያልሆነ ዲያቢሎስ ብቻ ነው እግዚአብሄር ማስተዋሉን ይስጣችሁ፡;


  ReplyDelete
 28. አንድ ወንድም የጻፉቱ ጽሁፉ በሚቀጥለው ወር የአንድነት ሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ በሳን ሆዜ ደብረ ይባቤ ይደረጋል ብለዋል። ለመሆኑ በዚህ ቤተ ክርስቲያን የምደረገው የማህበረ ቅዱሳን ጉባኤ መሆኑን በግልጥ ልነግሩን ይሞክራሉ። ለዚህ ለማቅ ማደረጃ እንድሆን ህዝቡን ገንዘብ እንድያዋጡ እያስጨነቁ አይደለም? ህዝቡ ደግሞ ምን እያለ ነው ለመሆኑ? ሕዝቡማ እኛ ሞርገጅ መክፈል አቅቶናል እየሉ እያማረሩ ናቸው።እንድያውም ቦርዱ ከህዝበ ክርስቲያኑ የተበደረውን $80,000.00 Dollars የተበደረውን መክፈል አልቻለም። አበዳርዎች ደግሞ ያበደርነውን ገንዘባችን መልሱልን እያሉ አይደለምን? ወንድማችን ይህን ርፓርት ቦርዱ ለህዝቡ አቅርቦ ነበር። ታድያ በዚህ በምቀጥለው ወር መጨረሻ የሚደረገው የማቅ ጉባኤ በሳን ሆዜ ደብረ ይባቤ የሚካሄደው ለቤተ ከርስቲያናችን ምን ጥቅም ይሰጣል? ባዶ ባዶ የማቅ ክስ ማደበር ካልሆነ በቀር። እዉነቱ ይህ ነው። የጠላትነት ወሬ አይደለም። ማንም ሰው ሙሉ መብት አለው እስክ የደበሩን ቦርድ ደውላችሁ ጠይቁ ያለውን ችግር ገልጥ በማድረግ ያቀርቡላችዋል። ማቆች ለማደናገር አትሞክሩ እኛም ነቅተናል ,,,,,ወደፊት ስለ የማቅ ጉባኤ በደንብ እናቀርባለን።  ...................

  ReplyDelete
 29. Guru n aseteyate nwu

  ReplyDelete
 30. Where is Abune Fanuel and Dn Hailegiorgis? They did'nt show up at north america diocis yearly meeting at seattle?

  ReplyDelete
 31. ችግሩ ያለው መርካቶ ማቅ እያላችሁ የምትተቹ መናፍቃን ቸግር አለ የምትሉት እሩቁ ፕላኔት ፕሉቶ ላይ ነው። እናንተ እንደምትሉት ማህበረ ቅዱሳን በሁሉም ቦታዎች ላይ ባሉ አብያተክርስትያናት ስሙን የሚያስጠሩ ሰዎች ካሉት ይህ ማህበር በሁሉም አብያተ ክርስትያናት ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሰዎች ሁሉ የሚፈልጉት የሚንከባከቡት ማህበር ነው ማለት ነው። የትችታችሁ ሌላው ገጽታ የሚያሳየው ይህንን ነው። እኔ የማህበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም የሚቀርቡ አስተያየቶችን ስመለከት ግን ጸበል መጠመቅ የሚያስፈልጋችሁ የማህበረ ቅዱሳን ጥላ እንኩዋን ባጠገባችሁ ካለፈ መጡብን ብላችሁ በርግጋችሁ ብዕር የምታነሱ ወይም አፋችሁን ለነገር የምትከፍቱ በርካታ ህሙማን እንዳላችሁ ለመገንዘብ ችያለሁ። እውነቱ ግን እንደ እስስት መልካቸውን የሚቀያይሩ የውስጥ መናፍቃን እና ባሉባልታ የሚፈቱ ደካማ ግለሰቦች እንዲሁም ለውስጥ መናፍቃኑ አፍ ማሳመርያ የሆኑ ሙሰኞችና ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞ በቤተክርስትያን የተሸሸጉ ፖለቲከኞች ናቸው የቤተክርስትያንን ችግሮች መሆናቸውን ነው የሚያሳየው። አንባብያን አትወናበዱ ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ ዝም ብላችሁ በሃይማኖታችሁ ጽኑ በወሬ አትፈቱ። በሰዎች መካከል ጥርጥር የሚፈጥር ራሱ መናፍቅ ነው።

  ReplyDelete
 32. I know MK for many years.Here is my observation:

  1) Are they trying to serve the church of Jesus Christ? For Sure!

  2)Are they perfect in their services? No.

  3)Do I expect them to be perfect as servant of God. Yes, but I let anyone who never sins to throw stones at MK.

  4) Are they fighting the good fight against church enemies? Of course!

  5) Are they helping the church by all means? O Yes!

  I work with them for the interest of our church, though I have some reservation about them. I agree with MK on the big picture even if I have some minor issues.

  MY wish and advise to MK is: to become more stronger to serve our Lord Jesus Christ everyday. As a christian, I know that those people who throw stones against our Lord 2000 years ago, their evil sprite still exist and do the same thing to MK or our church as they did to our Lord Jesus Christ the Savior, but MK will be the winner as usual because of Our Lord.

  Lastly, I recommend MK to have a more realistic and strategic understanding on some church canon law to accommodate to this generation concerns. I know that MK understand and knows church canon laws can be improved by Holy Synod to enable the church responsive to the generational change. So, MK and its members needs encourage our church fathers to able to make any necessary church's canon law that can able to spreed gospel all over the world to all human races. If MK have any issues on my minor reservation, it has to go back and refer a research paper that presented by Kesis Eshetu on 1990 or 1991 at Betekhinet Hall entitled "Betekrestian be 2000 amet or Church in Years 2000". Even if I have some minor differences with MK, I still work with them and help them as much as I can and pray for them as a true member of EOTC. God Bless MK, its members and services. Jesus Christ, our Lord and savor, may give you(MK) more wisdom and power to serve Him and His Church.

  Jesus Christ is Lord of Lord Kings of King.

  ReplyDelete
 33. I know MK for many years.Here is my observation:

  1) Are they trying to serve the church of Jesus Christ? For Sure!

  2)Are they perfect in their services? No.

  3)Do I expect them to be perfect as servant of God. Yes, but I let anyone who never sins to throw stones at MK.

  4) Are they fighting the good fight against church enemies? Of course!

  5) Are they helping the church by all means? O Yes!

  I work with them for the interest of our church, though I have some reservation about them. I agree with MK on the big picture even if I have some minor issues.

  MY wish and advise to MK is: to become more stronger to serve our Lord Jesus Christ everyday. As a christian, I know that those people who throw stones against our Lord 2000 years ago, their evil sprite still exist and do the same thing to MK or our church as they did to our Lord Jesus Christ the Savior, but MK will be the winner as usual because of Our Lord.

  Lastly, I recommend MK to have a more realistic and strategic understanding on some church canon law to accommodate to this generation concerns. I know that MK understand and knows church canon laws can be improved by Holy Synod to enable the church responsive to the generational change. So, MK and its members needs encourage our church fathers to able to make any necessary church's canon law that can able to spreed gospel all over the world to all human races. If MK have any issues on my minor reservation, it has to go back and refer a research paper that presented by Kesis Eshetu on 1990 or 1991 at Betekhinet Hall entitled "Betekrestian be 2000 amet or Church in Years 2000". Even if I have some minor differences with MK, I still work with them and help them as much as I can and pray for them as a true member of EOTC. God Bless MK, its members and services. Jesus Christ, our Lord and savor, may give you(MK) more wisdom and power to serve Him and His Church.

  Jesus Christ is Lord of Lord Kings of King.

  ReplyDelete