Friday, August 16, 2013

ማኅበረ ቅዱሳን በውስጥ ችግር መታመሱ የአደባባይ ምስጢር እየሆነ ነው ታማኝ የተባሉ አገልጋዮቹን እያባረረና እነርሱም እየከዱት ይገኛሉ

ማኅበረ ቅዱሳን በውስጥ ችግሮቹ እየታመሰ መሆኑን ከማኅበሩ አካባቢ ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ላለፉት ዓመታት አቡነ ጳውሎስን መቃወምን ትልቅ አጀንዳው አድርጎ ሲሰራ የነበረው ማቅ ከእርሳቸው ዕረፍት በኋላ ድምጹ ብዙም እየተሰማ አለመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ለተቃውሞው አብረው የነበሩት የማቅ ዋና ዋና ሰዎችም ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ በራሳቸው የቤት ስራ መጠመዳቸው አልቀረም፡፡ ልዩነታቸውም እየጎላ በመምጣቱ በተለያየ ክፍል የሚሰሩ የማኅበሩ ቁልፍ ሰራተኞች እየተባረሩና አንዳንዶችም ለመልቀቅ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ስንታዘብ ቆይተናል፡፡
በዋናነት ልዩነቶች እየተፈጠሩ የመጡት በዋልድባው ጉዳይ ሲሆን፣ በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት እየሠራ ያለውን የወልቃይት ጠገዴ የስኳር ልማት ፕሮጀክትን ለማደናቀፍና ለፖለቲካ ፍጆታ በማዋል ገቢ ለማሰባሰብ አንዳንድ የማቅ ሰዎች ሲያራግቡትና ጉዳዩን የተለየ አቅጣጫ እንዲይዝ ሲያደርጉት እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ማቅ በእርሱ በኩል ፕሮጀክቱን የተመለከተ ጥናት አድርጎ ሪፖርት እንዲያቀርብ እድሉ ተሰጥቶት በነበረ ጊዜ ሶስት አባላት ያሉት የጋዜጠኞች ቡድን ወደስፍራው ልኮ የነበረ ሲሆን የማቅ የጎንደር ንኡስ ማእከል በጊዜው ከቡድኑ አባላት አንዱ ሆኖ የመጣውን ባያብል ሙላቱን ለምን እርሱን ይዛችሁት መጣችሁ? ማለታቸው ታውቋል፡፡ ሆኖም በማጣራቱ ሂደት ባያብልም ተሳትፎ ቡድኑ ተገቢውን ማጣራት ካደረገና ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ ሪፖርቱን አዘጋጅቶ በማኅበሩ የሌሊት ስብሰባ ላይ አመራሮቹ ባሉበት ገለጻ አድርገው የነበረ ሲሆን፣ ገለጻውን ተከትሎ ለሁለት ተከፍለዋል፡፡
በዚሁ መሰረት የቀድሞው የማኅበሩ ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ ዋና ጸሐፊው ሙሉጌታ ሃይለ ማርያም ያሉበት ቡድን በሪፖርቱ ውስጥ ፕሮጀክቱ ምንም ጉዳት የለውም የሚል ሐሳብ እንዲካተት አድርገው ነበር፡፡ በሌላ በኩል አባይነህ ካሴ፣ ጌታቸው በቀለ፣ ብርሃኑ አድማስ ያሉበት ቡድን ደግሞ ፕሮጀክቱ ሆን ተብሎ ገዳሙን ለመንካት የሚሰራ መሆኑን የሚጠቁም አረፍተ ነገር እንደወረደ መካተት አለበት በሚል ይቃወማሉ፡፡ ወይይቱ በዚሁ ሁኔታ ላይ እንዳለ የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ሰው ይህን ውይይት ውጭ አውጥቶ ላለመናገር እንማማል ሲል ሐሳብ አቅርቦ ተማምለው የነበረ ቢሆንም በዚያው ሌሊት ወሬው በደጀ ሰላም ድረገጽ ላይ ወጥቶ ተገኘ፡፡
የመጨረሻውን ሪፖርት በማኅበሩ ድረገጽ ላይ ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ በነበሩ ጊዜ ፕሮጀክቱ እንዲያውም ገዳማውያኑን እንደሚጠቅም የሚያስረዳ አንቀጽ እነ ዶ/ር ሙሉጌታ አስገብተው የነበረ ሲሆን እነርሱ ዘወር ሲሉ በእነአባይነህ ካሴ የሚመራው ቡድን አንቀጹን ለውጦ ወዲያው በማኅበሩ ድረገጽ ላይ አየር ላይ አዋለው፡፡ በጊዜው የአንቀጹ መለወጥና ሳይካተት አየር ላይ መዋሉ ለአባይነህ ካሴ ከማህበሩ መባረር ምክንያት እንደሆነ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ በዚሁ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ የሚታወቀው ሀራ ዘተዋህዶ የተሰኘው አዲስ ብሎግም የአባይነህን ከማቅ የመታገድ ወሬ ይዞ በመውጣት ራሱን አስተዋወቀበት፡፡
የዋልድባውን ፕሮጀክት ለማጣራት ወደስፍራው ከሄዱት መካከል አንዱ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው በቀለ በሌሊቱ ስብሰባ ላይ ከማኅበሩ አመራር ከፍተኛ ተግሳጽ ደርሶበት በዚያው ሌሊት ከማኅበሩ ወጥቶ እንደቀረ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ የዳንኤል ክብረት ደቀመዝሙር መሆኑ የሚነገርለት ጌታቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ማኅበሩን ሰለቸኝ ደከምኝ ሳይል ያገለገለና በርካታ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅ ልሳኖች በሐመር በስምአ ጽድቅና በሐመረ ተዋህዶ ያቀረበ ትጉ ሰራተኛ እንደነበረ ይነገርለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ከማህበሩ ለቆ በሙያው አዲስ ጉዳይ በሚባልና እነዳንኤል ክብረት ያዙበታል በሚባለው መጽሔት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጌታቸውን የሚያውቁት የማኅበሩ አባላት በጌታቸው ከማቅ መልቀቅ በማኅበሩ አመራር ላይ ጥያቄ እያነሱ እንደሚገኙና የማኅበሩ አመራር በአክራሪው ብሄረተኛ በብርሃኑ አድማስ ሀገር ልጆች እየተሞላ መሆኑ እያነጋገረ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡    
በማኅበሩ ውስጥ ለተፈጠረው ክፍፍል አንዱ ማሳያ የሚሆነው በማኅበሩ ልሳኖች ላይ የሚሠሩ እንደ ጌታቸው በቀለ ያሉ ጋዜጠኞች ከስራ የመልቀቃቸው ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማኅበሩ በተለይ በጽሑፍ ስራና በጋዜጠኝነት ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን አባላቱንና ሰራተኞቹን በተሐድሶነት ይጠርጥር ወይም ምን እንደነካው ባይታወቅም እያሰናበተ ይገኛል፡፡ አንዳንዶችም ማኅበሩን ለመልቀቅ አኮብኩበው እንደሚገኙ እየተነገረ ነው፡፡ የስምአ ጽድቅ ዋና አዘጋጅ የነበረውና በእንቁ መጽሔት ላይ ፖለቲካዊ ይዘት ያለውና የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ክፉኛ እያብጠለጠለ በመጻፍ የሚታወቀው ታደሰ ወርቁም እንደዚሁ ከማቅ የተሰናበተ መሆኑ ሲታወቅ ከማቅ ጋር ንክኪ ባለው በጎልጎታ አስጎብኚ የጉዞ ወኪል በጋይድነት ተቀጥሮ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ድርጅት አማካይነትም ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮው የፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም መጓዙ ታውቋል፡፡ በማኅበሩ ውስጥ ቢሆን ኖሮ ይህን እድል እንደማያገኝ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ በተመሳሳይም የማኅበሩ አካሄድ ያልጣማቸው ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይንም ከስምአ ጽድቅ አዘጋጅነታቸው ለመልቀቅ እያኮበኮቡ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጎርጎርዮስ አጸደ ሕጻናት ይሠራ የነበረውና በቲዎሎጂ ዲግሪ ያለው ቀሲስ ጥላሁን ከወራት በፊት ከማኅበሩ ለመውጣት መልቀቂያ አስገብቶ የነበረ ሲሆን ሀሳቡን ቀይሮ ልመለስ ቢል አንዴ እወጣለሁ ብለሃል ዳግም መግባት አትችልም ተብሎ የተሰናበተ ሲሆን፣ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኝ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከማኅበሩ የተሰናበተውና ብእሩን በማኅበሩ ላይ ያሾለው ታደሰ ወርቁ ባለፈው ሳምንት በወጣው ፋክት በተሰኘው መጽሔት ላይ “በቄሳራውያን መዳፍ ሥር ያለ አስኬማ” በሚል ርእስ በጻፈው ጽሑፍ ማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ጳውሎስን ይዋጉልኛል ብሎ በተለያየ አቅጣጫ “ከእናንተ ጋር ነኝ እናንተም ከእኔ ጋር ሁኑ” እያለ ሲያንቆለጳጵሳቸው የነበሩትን ጳጳሳት “ቄብ ጳጳሳት” ሲል ክፉኛ ተሳልቆባቸዋል፡፡ ይህን የተመለከተ በተለይም በማኅበሩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ካቀረበው ትችት ጥቂቱንና ሌሎች የተነሡ ጉዳዮችን በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን፡፡

30 comments:

 1. wow mk like epyptians people fight each other. That is the fruit of opposing Gospel. B

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁንስ እጅ እጅ አላችሁ ያለ ማኀበረ ቅዱሳን ሌላ አታውቁም የምታወሩት ሁሉ የወረደ ድሮስ ከመናፍቅ ምን ፍሬ ሊገኝ የቆጥ የማገሩን ትቀባጥራላችሁ፡፡ እንደ ፍልስጣ ዘወትር ነገር ትከትባላችሁ፡፡

   Delete
  2. You don't know the meaning of Gospel. Are saying the same thing for 9/11 terrorist attack on America ppl.

   Delete
 2. Do you think you gonna be in Heaven talking about MK day and night? You are one of false Gossipers. You end will be...

  ReplyDelete
 3. What is wrong with you? Why don't you do your job. Live Maheber Kidusan alone. What ever they do they are always right. Don't comment any body. this blog is false WESHETEM THADESO NACHEHU. We don't believe you. All you are liers.

  ReplyDelete
 4. Yih blog yetehadiso sayhon yeprotestant new. minalbat tehadiso tinishim bihon orthodoxawinet yinorew yihonal yemil eminet silalegn. tehadiso malet endezih blog tshuf kehone gin menafiknet bicha sayhon astseyafi new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. @ Meaza, Wedaje, Endaymeslih Tehadiso Adgo Adgo Protestant Endemihon Atiterater Lemin bitil Ye Protestant Akahed Yeteleyaye sim bemwutat Mekefafelin Mabizat New. Kastewalkewu Diro Protestant Yilut yeneberewu Yekudusan Amalajinet, Teamur, Gedil wezete Yinekfu neber Ahun Yebet Sirawun Letehdiso Setewual. Ena Tehadiso(Abba Selemawoch)Ye protestant Lijoch nachew Beminim le Tewahido Aykerbum. G/Hiwot ...Adigrat

   Delete
 5. Thank you Aba Selama blog for your blessed statement about the truth. We are all children of Orthodox church but MK members are against of the truth bible, Lord Jesus Chris and church reformation from traditional to truth of bible life. Our church members instead of knowing regarding of Our God Jesus Chris covered by not biblical orders.MK members are stand of money not for orthodox church growing fruits, Every day attacking children God who what know about Lord Jesus our savior. Some our Church choirs are pay a lot of money every month for MK luxury. MK still attack our church children and spiritual fathers. we are absolutely disagreed with those peoples collecting their money for MK. I like thank you Aba Selama blong for providing us about this bad Satan (MK) group. Believe or not God is a winner without doubt. Thanks to our God our generations are know regarding right and wrong. MK do not shade our sight with your wrong philosophy. Please believe in truth spiritual change not your selfish order. your so far from the lord Jesus and our generation .....we will stand for truth spiritual change.

  ReplyDelete
 6. One common denominator between some Pentes and Mahibere Kidusans is both believe that they have gotten in to the Kngdom of God prior the Judgment Day.Both turned me off. I do not know much about Pente, but they love patronizing you as if you do not know about your God. That make me sick as well. As for Mahibere Kidusan one can write 1000 pages. They have taken the executive and policing work of the Ethiopian Orthodox Church without a mandate. The church is losing its young generation because of the sickening interference of these guys despite their claim that they are the vanguard elites of the church. No body stand up and told them they would not put up with their nonsense until now. They got carried away with this, until Thadesso came in telling them enough is enough! Bless their heart!


  ReplyDelete
 7. who cares!!! Mahebere kidusan is not combination of one or ten person where as a combination of more than 25,000 peoples so don't think about the less amount pls. Egziabeher maheberachenene metenakerachenene yetebeke


  ReplyDelete
 8. who cares!!! Mahebere kidusan is not combination of one ore ten person where as a combination of more than 25,000 peoples so dont think about the less amunt pls. gziabeher maheberachenene metenakerachenene yetebeke

  ReplyDelete
 9. ''metekakat slehone '' hahhahhaa

  ReplyDelete
 10. lemehonu wana alamachen betekrstiyanen ende abun selama betamagnet magelgel new belachehu yekefetachehut blog besdebena, bekinat magelgel new ende?

  ReplyDelete
 11. No joke. MKS need to get in socked with the Holy Water to get them out of their fantasy world. Those of you in Sunday School, please do not get ripped off by these self gratifying Pseudo Orthodox Christians.

  ReplyDelete
  Replies
  1. dude, do you believe in holy water? That's amazing. really. Good for you. just out of curiosity which pente org you going believe in holy water?

   Delete
 12. We like thahadiso{spiritual changes)because our eyes shaded by wrong written in Merkato shop. no body controlled all those wrong books came from merkato street. That why Tehadisoo is crucial for truth spiritual change. Our holy bible is different than any books and must stand for God message not for wrong peoples interest and luxury. we all watching daily church movement in this generations.every church members are disagreed with MK and leaders. Aba Selama great job for you guys providing the truth of church. i like to encourage your blog continue for blessed and truth spiritual offers on daily work. Let us stand with Tehadiso (good spiritual changes). The truth never hide.!!!!!!

  ReplyDelete
 13. Why you guys doesn't post my comments. My friends telling me the same thing.

  ReplyDelete
 14. It is pitiful that you thought I went to Pente Church. Yes I believe in Holy Water,I go to Baheta Le mariam Ethiopian Tewhido Church. Mahibere Kidusans myopic view of other Tewhido brothers and sisiters warrants socking with Holy Water perferably Entoto's Kidane Mehiret. Just for your curiosity Dude!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dude, you just showed us your myopic view. you are CONFUSED!!!

   Delete
 15. እኔ የሚገርመኝ የምታወሩትን የምንቀበል ይመስላችሁዋልን፡፡ እናንተ የምትሉዋቸው ሁሉ አሁንም ከማህበሩ ጋር ናቸው፡፡ አገልግሎታቸውን እያበረከቱ ነው፡፡ ማንም ደግሞ በነጻነት እንዲያገለግል እንጂ በግዴታ አይደለም፡፡ በግላቸው ለመስራት ያሰቡት ስራ ኖሮ የማህበሩንም ደርበው መስራት አዳጋች ከሆነባቸው ስራውን ከሚበድሉ መልቀቃቸው ተገቢ ነው፡፡ እናንተ ግን እንደ ክፉ ታዩታላችሁ፡፡ ስምዖን አረጋዊ እነሆ ባርያህን አሰናብት እንዳለ ማንም ስራን ከሚበድል ቢሰናበት ይደገፋል፡፡ ስለዚህ መጥፎነት የለውም፡፡ የእናንተ ወሬ ግን አላማው ምን እንደሆነ አይገባኝም፡፡ ማህበሩ የተወሰኑ ሰዎች ሳይሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውቅና የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ያለው በመሆኑ የመላው ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል ሁሉ ማህበር ነው፡፡
  ደግሞኮ ስለ ገዳም ታወራላችሁ ማህበሩ የወሰደውን አቁዋም ሰምተናል፡፡ በምንም መልኩ ገዳሙን በተወሰነ እንደሚነካ እንደውም መጠኑን በመግለጥም ጭምር አብያተ ክርስቲያናት እንደሚፈርሱ ከገዳማውያኑ ጋር መወያየት እንደሚያስፈልግ ጠቁሞ ነው ያለፈው፡፡ ከአመት በላይ የተወሰደን አቁዋም እንደ አዲስ ማራገብ ያውም በማይገባ አካሄድ ተገቢ አይደለም፡፡ በዚህ ደግሞ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡፡ ለወሬ የለውም ፍሬ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Gosh Nigerilign Ema. Lenegeru Enezih Tehadisowoch Min yadrigu bileh new? Sile genet Ayasibu Sile hodachewu Enji, Ye Protestant Erdata Eskale Dires Mewasheachewu Aker, Semi Gin Yelem!!

   Delete
  2. Stupid, Dros mene yigebahena tekebelaleh. Defen kele. ms.

   Delete
 16. አሁንስ እጅ እጅ አላችሁ ያለ ማኀበረ ቅዱሳን ሌላ አታውቁም የምታወሩት ሁሉ የወረደ ድሮስ ከመናፍቅ ምን ፍሬ ሊገኝ የቆጥ የማገሩን ትቀባጥራላችሁ፡፡ እንደ ፍልስጣ ዘወትር ነገር ትከትባላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 17. ቆይ እናንተ መጨረሻችሁ ምን እንደ ሆነ እኮ አገር ያወቃል ለምን ትለፈልፋላችሁ ?

  ReplyDelete
 18. This is not the begining for Eotc. Not a big deal Eotc has good experience . U can track wayback the past how eotc challange demonic activivties you are not really smarter than the fifth grade. Do you think we do not know you? Nothing surprise us even an online jihad big lie taking some sentence from some books and twist the idea. Really, «lij enatuan mit asetemarechat» our brothers and sisters these wolf if they get a chance, they will prescuted u like their decivers brainwashed masters today

  ReplyDelete
 19. A prostitute style war of words. Take anything, chance, and oppertunity, weither it could be someone personal failer or something elseto fight eotc. We know that we are waiting for this. The kingdom of God is not how this simple mind corput

  ReplyDelete
 20. I do not blame u because Eotc beat the hell up physically and emotionally . Egypt in the 1874& 1876 with the europe, west and bunch of Arabs said 1000% eotc must convert to islam but with this two significient battles those proud banch of egyptions lost. We have somany history og facts even this an online full of lie . Experience is the best. Weither u act like us or your father accuser satan we know you deaft is not an option. One person Personal failer could not meant the whole . Yes some of us r very weak sinner.

  ReplyDelete
 21. ልፋ ያለው በህልሙ ክብደት ይሸከማል አሉ!

  ማህበረ ቅዱሳን ብላችሁ ልባችሁ ወለቀ! ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንደተባለ ማህበሩን ከፍሬው እናውቀዋለን። የእናንተንም ፍሬ እናውቃለን። አላማችሁ ወንጌል መስበክ ከሆነ ወንጌሉ የት አለ? በእርግጥ ማህበሩ ስራ አላሰራ አላችሁ አይደል? ልፋ ያለው በህልሙ ክብደት ይሸከማል እንዲሉ በቅዠት ዓለም ተውጣችሁ አስሬ ማህበረ ቅዱሳን ትላላችሁ። ልፋ ያለው በህልሙም ክብደት ይሸከማልና እናንተ ለፋችሁ ማህበረ ቅዱሳን ግን ስራውን እየሰራ ነው።


  የእናንተ ፍሬ ምንድን ነው?

  የማህበረ ቅዱሳን ፍሬ ይህ ነው፦

  ገዳማትን አጠናከረ
  የተዘጉ ቤተክ ተከፈቱ
  የወጣቱን እውቀት ለቤተክርስቲያን አደረገ።

  እናት ቤተክርስቲያን ሆይ ከልብ እንወድሻለን!

  ReplyDelete