Saturday, August 3, 2013

በአሰበ ተፈሪ የሆነውና እየሆነ ያለው ምንድን ነው?

ሐራ ዘተዋህዶ አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ አይነት ሐሰተኛ ወሬ ማስነበቡን ተከትሎ ከስፍራው የደረሰን ጽሁፍ እንደሚሳየው ሀራ እውነታውን ገልብጦ የዘገበ መሆኑን ነው፡፡ መቼም ከሀራ ከዚህ የተሻለ ነገር አይጠበቅም፡፡ ሲጀመር አላማው እውነት ማቅረብ ሳይሆን እውንትን በማዛባትና ሀሰትን እውነት አስመስሎ በማቅረብ ማቅ አለአግባብ ለመበልጸግና በቤተክርስቲያን ተቆርቋሪነት ስም ቤተክርስቲያንን የመዝረፍ ተግባሩን እንዲቀጥልበት ሽፋን መስጠት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሌሎችን ስም አክፍቶ ማቅረብን እንደ አንድ ስልት እየተጠቀመበት ነው፡፡

ባለፈው ጽሑፍ ላይ ለማሳየት እንደሞከርነው የማቅ ሰዎች ከእነርሱ ጋር በሀሳብና በአካሄድ የተለየውን ሰው ሁሉ ከእኔ ጋር የሐሳብ ልዩነት ነው ያለው ነው ከማለት ይልቅ “ተሐድሶ መናፍቅ ነው” ማለት ይቀናቸዋል፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ አሰበ ተፈሪ ላይ ከማኅበረ ናታኒም ጋር የተፈጠረውን አለመግባባትም ከማቅ ጋር የተፈጠረ አለመግባባት ሳይሆን ተሐድሶ መናፍቅነት ነው ማለታቸው ይኸው ክፉ ጠባያቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ምን ያህል እየጎዳ እንዳለ ያመለክታል፡፡ ሰሞኑን ሐራ ዘተዋህዶ ብሎግ አሰበ ተፈሪን በተመለከተ የሰቀለው ጽሑፍ እንኳን ሌሎችን ሊያሳምን ይቅርና የራሱን አንባቢዎችንም ግራ ያጋባ መሆኑን ብሎጉ ላይ ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ይቻላል፡፡ በአሰበ ተፈሪ በትክክል የሆነውና እየሆነ ያለው ምንድነው ለሚል ጠያቂ ከመሪጌታ የሻውወርቅ የደረሰን ጽሁፍ ምላሽ ይሰጣልና እንዲያነቡት እንጋብዛለን፡፡


በእጅ አዙር የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር መቆጣጠር የሚፈልገዉ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ጥርቅሙ ማህበረ ቅዱሳን በአሰበ ተፈሪ ድብቅ ሴራዉ ተጋለጠ

ከመሪጌታ የሻውወርቅ

ሐራ ዘተዋህዶ በተባለዉ የማህበረ ቅዱሳን መርዝ መርጫ ድረ ገጽ ላይ በምእራብ ሐረርጌ በአሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ዉስጥ ከእሁድ ሰንበት ቅዳሴ በኋላ ምእመኑና ማህበረ ካህናቱ የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫን ለማከናወን በሐገረ ስብከቱ ተይዞ የነበረዉን ፕሮግራም ሰንበት ት/ቤት አባላት ነን ከሚሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የማህበረ ቅዱሳን አመራሮችና በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦች የተፈጠረዉን ከኦርቶዶክሳዊ አማኝ ስነምግባር ዉጪ የሆነዉን ሁከት እንደለመደዉ ማህበሩ በአንድ የማህበረ ናታኒም የተሰራ ተንኮል እንደሆነና ከዚሁም ጋር የሐገረ ስብከቱን ስራ አስኪያጅና ጸሀፊ ለመወንጀል የታሰበበት ጽሁፍ አስነበበን፡፡

ያሳዝናል እድሜ ልኩን እንደ ግብር አባቶቹ ጸሐፍት ፈሪሳዊያን /ቤተ አይሁድ/ ለጥፋት የተቋቋመ ማህበር፡፡ መቼ ይሆን እዉነቱን እዉነት ሐሰቱን ሐሰት የሚለዉ? አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሐፍት ፈሪሳዊያን ተይዞ ሊቀ ካህን ሐና ዘንድ በቀረበ ጊዜ አንድ ነገር ተከሰተ፡፡ ይሄዉም ሊቀ ካህኑ ሐና ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀዉ፡፡ አምላካዊ መልሱ “በግልጥ ለአለም ተናገርኩ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በቤተ መቅደስና በምኩራቦች በግልጽ አስተማርኩኝ በስዉርም ምንም አልተናገርኩም፡፡ ስለምን ትጠይቀኛለህ? የሰሙትን ጠይቅ እነርሱ እኔ የተናገርኩትን ያዉቃሉ” አለዉ፡፡ በዚህ ግዜ ግን አንድ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ የሊቀ ካህኑ ሎሌ የነበረ አገልጋይ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን እንዲህ አይነቱን መልስ ለሊቀ ካህኑ ትመልሳለህ ብሎ ጌታን በጥፊ መታዉ፡፡ እጅግ የሚገርመዉ አምላካዊ መልሱ ነዉ፡፡ ኢየሱስም መልሶ “ክፉ ተናግሬ እንደሆንሁ ስለ ክፉ መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ አለዉ፡፡” የዮሀንስ መንጌል ምእራፍ 18፡19-23፡፡

ይህንን ጥቅስ የወሰድኩበት አንድ ምክንያት አለኝ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን እንደ ምሰሶ ደግፎ ይዞ እንደቆመ ራሱን ይቆጥራል፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ መንፈሳዊ ማህበር ለቤተክርስቲያኒቱ እንደማያስፈልግ ያዉጃል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር በሙሉ የእርሱ ሐሳብ አራማጆች በሆኑ አባላቱ ብቻ መቆጣጠር ለእርሱ ህልዉና አማራጭ የሌለዉ መፍትሄ እንደሆነ ከወሰነም ቆይቶአል፡፡ እርሱ ከሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እንደምትጠፋ ከወሰነም ሰንብቶአል፡፡ ስለዚህ በዚህ ሰይጣናዊ ምክር የተተበተበ ማህበር በመሆኑ ጌታን በጥፊ እንደመታዉ ሎሌ አንድም ቀን ክፉዉን ክፉ መልካሙን መልካም ብሎ ሳይመሰክር እድሜ ልኩን የአለቃዉ የዲያብሎስ ሎሌ ሆኖ የቤተክርስቲያን ልጆችን ሲከስ ዘመን እያለፈበት መጣ፡፡ ያሳዝናል እንዲህ ሆኖ ለፍርድ መቀመጥ! እግዚአብሔር ከዚህ እርግማን ይሰዉረን፡፡ አሜን!!!

በአሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ቤ/ክ የተፈጠረዉ እዉነት ግን ይሄ ነዉ፡፡

 1. የሁለቱ ደብር ሰበካ ጉባኤ ማለትም የቅድስት ልደታ ለማርያምና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ሰበካ ጉባኤ አባላት የአገልግሎት ግዜዉ ያበቃ በመሆኑ በሀገረ ስብከቱ አማካይነት አዲስ የሰበካ ጉባኤ አመራር ቃለ አዋዲዉ በሚያዘዉ መሰረት ማስመረጥ የሚገባ በመሆኑ ሰበካዉ አጠቃላይ ሪፖርቱን እንዲያቀርብና ማህበረ ምእመናኑ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲመርጡ ተደረገ፡፡ በዚህ ጊዜ ማህበረ ምእመኑ ከዚህ በፊት ለቤተክርስቲያኒቱ ልማትና ወንጌል አገልግሎት እጅግ የሚፋጠኑና የሚተጉ ተወካዮቻቸዉን በአስመራጭ ኮሚቴነት መረጡ፡፡ በዚህ ያልተደሰተዉና ከዚህ በፊት ለረጅም አመታት የራሱን አባላት የሰበካ ጉባኤና ሰንበት ትምህርት ቤት አመራር አድርጎ የቆየዉ ማህበረ ቅዱሳን አንዳንድ አባላቶቹ በእለቱ ተቃዉሞ ሊያነሱ የሞከሩ ቢሆንም የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች ካህናቱና ማህበረ ምእመኑ በያዙት ጽኑ አቋም ምርጫዉ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡ ይሁን እንጂ እድሜ ልኩን በክስ የኖረዉ ማህበረ ቅዱሳን የሐሰት ክሱን ይዞ ሀገረ ስብከትም የሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንባቆም ጋ ቢሄድ ተቀባይነት በማጣቱ የሰበካ ጉባኤዉ ምርጫ ሂደት አዲስ ከተሰራችዉ ቤተክርስቲያኒቱ ምረቃ በኋላ እንዲከናወን ተወስኖ አበቃ፡፡

 2. ይሁን እንጂ እስከ ሊቀ ጳጳሱ ድረስ ቅሬታዉን አቅርቦ የሐሰት ክሱ ተሰሚነት ያጣዉ ይሄዉ የጸሀፍት ፈሪሳዊያን ስብስብ እንደ ግብር አባቶቹ የምርጫዉን እለት ጠብቆ ሁከት መፍጠርና ቤተክርስቲያኒቱን ማወክ እንደ መፍትሄ ሐሳብ ይዞ በ21/11/2005 እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ የራሱ አባላት የሆኑትንና የእርሱ ደጋፊ የሆኑ ነገር ግን የሰንበት ትምርት ቤት አባላት ያልሆኑትን የመዝሙር ዩኒፎርም በማስለበስና ከበሮ በማስመታት የምርጫ ሂደቱ ሊከናወን ሲል ረብሻ አስነሱ፡፡ የህግ አካልም፣ ህዝበ ክርስቲያኑም፣ ማህበረ ካህናቱም ቢለምናቸዉ እንቢ በማለት ሁካታ በመፍጠር የምርጫ ሂደቱ በእለቱ እንዳይከናወን መሰናክል ከመፍጠርም አልፈዉ የሐገረ ስብከት ሰራተኛ የሆኑ አንድ አባት ላይ የድብደባ ወንጀልም ፈጽመዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ እንደ እንሰሳዋ ተረት እኔ ካልሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ያለዉ ማህበረ ቅዱሳን እንኳን ታላላቆች የቤተክርስቲያን አባቶችን ለጸጥታ የመጡ የፖሊስ አካላትንም ሊያከብር አልቻለም፡፡ ራሱን ከቤተክርስቲያንም ከመንግስት ህግም በላይ አድርጎ ስለሚቆጥር፡፡

 3. የማህበሩ ሁካታ በዚሁ ሁኔታ የተጠናቀቀ ቢሆንም ሐገረ ስብከቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ እልህ አስጨራሽና ለትእግሰቱ የመጨረሻ የሆነዉን ምክርና ዉይይት ከዚህ ማህበር አባላት ነን ከሚሉ ጋር ያደረገ ቢሆንም ከዚህ በላይ ማህበሩና የሰንበት ትምህርት ቤቱ አመራር ነን የሚሉ ማህበረ ቅዱሳኖች ቤተክርስቲያኒቱን እያወከ መቀጠል የለበትም በማለት ድሬደዋ ከተማ ከሚገኙት ከሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንባቆም፣ ከህግ አካላትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመመካከር አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወሰድ አድርጎአል፡፡ ይህ እርምጃ ማህበረ ካህናቱን ምእመናኑን እጅግ ያስደሰተ እርምጃም ሆኖ ተገኝቶአል፡፡ በዚሁ መሰረትም ደግሞ ይህ እርምጃ ትክክለኛ አካሄድ እንጂ እነርሱ እንደሚሉት ሐገረ ስብከቱ ከማህበረ ናታኒም ጋር ተቀናጅቶ ያደረገዉ አይደለም፡፡

 4. የሐይማኖት አበዉ ርዝራዥ አባላት የተጠራቀሙበት ነዉ ያሉት ማህበረ ናታኒም ያሉት ማህበር የተቋቋመዉ በ2003ዓ/ም ብጹእ አቡነ ማቴዎስ አሁን የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ሆነዉ እያገለገሉ ያሉት አባት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት የቅድሰት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከ19 አመት በላይ ሳትሰራ ስትጓተት ቆይታ በእነዚህ ወጣቶች ተነሳሽነት በአንድ የወንጌል አገልግሎት ጉባኤ በማዘጋጀት ከ600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በመሰብሰብና ከዚያም በኋላ በተደረጉ ከፍተኛ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ከ2,500,000.00 (ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በማሰባሰብ ለ19 አመታት የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊ የሆነዉ ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጥቂት አመራር አባላት በከፍተኛ ምዝበራና ብክነት ሲያጓትቱት የቆየዉን ህንጻ ቤ/ክ ስራ በሁለት አመት ዉስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ያደረገ ማህበር በመሆኑና በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በጎ ፍቃድ የተቋቋመ ማህበር እንጂ ማ/ቅ እንደሚለዉ የመናፍቃን ጥርቅም አይደለም፡፡ አሁን ግዜ ያጥራል እንጂ ማህበረ ናታኒምና ማህበረ ጽዮን በቅንጅት በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየሰሩ ያሉትን መንፈሳዊ አገልግሎት መዘርዘር የሚቻል ነበር፡፡ ነገር ግን ዉዳሴ ከንቱ ስለሚሆን አልፈነዋል፡፡

 5. አቶ ታረቀኝ በቀለ ለቤ/ክ የቁርጥ ቀን ፈጥኖ ደራሽ ልጅ እንጂ እንደ እነርሱ /ማህበረ ቅዱሳን/ ለአባቶች የማይታዘዝ፣ ወላጆቹ የሚሉትን የማይሰማ፣ ህግን የማከብር አይደለም፡፡ የሐገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ሊቀ ብርሀናት ከሀሊ በቃሉ እና የሐገረ ስብከቱ ጸሐፊ ሊቀ ህሩያን ደረጀ ብርሀኑ በማህበረ ካህናቱ በማህበረ ምእመኑ እጅግ የተወደዱ ለቤ/ክ ጥቅም የቆሙ ለሰዉ ልጅ መዳን የሚጨነቁ የቤ/ክ ዶግማና ቀኖና እንዳይደፈር የሚሰሩ አባቶች እንጂ በማህበር ወይም በሰዉ ሐሳብ የሚመሩ አባቶች አይደሉም፡፡ ነገር ግን ማህበሩ ለእርሱ ዉሸት ያልተባበሩትን እድሜ ልኩን የሀሰት ታፔላ ሲለጥፍ የኖረ በመሆኑ ስለእነርሱ መልካም ነገር እንዲናገር መጠበቅ ከዝንብ ማርን እንደመጠበቅ ነዉ፡፡

 6. ስለዚህም ማህበረ ቅዱሳን እስከ መቼ እንደ ቀበሮዋ የበግ ለምድ ለብሰህ ትኖራለህ፡፡ አንተ ከተቋቋምክ ጀምሮ ከ7,000,000 (ሰባት ሚሊዮን) ኦርቶዶክስ አማኞች በአንተ ክስና ተንኮል በመናፍቃን እንደተበሉ አልሰማህም፡፡ አሁን ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ ስታይ አይንህ ለምን ደም ይለብሳል፡፡ በአንድ ሐጥእ መመለስ በሰማይ መላእክት ዘንድ ደስታ ከሆነ በወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ከተናደድክ ግብርህ እንደ ስምህ ከቅዱሳን ጋር ሳይሆን የሰዉን ልጅ መጥፋት ከሚመኘዉ ከዲያብሎስ ጋር ነዉ፡፡ ስለዚህ ያ የአንተ ክፉ ዘመን አብቅቶአል፡፡ ቤተክርስቲያናችን ብሩህ ዘመን በእዉነተኛዉ እረኛ በክርስቶስ የተበሰረላትን እየጠበቀች በመሆኑ አንተ ከዚህ በኋላ በቤ/ክ ስፍራ የለህም፡፡ ስፍራህ አሁን እየኖርከዉ እየተለማመድከዉ ባለዉ ድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ ነዉ፡፡ ግን ግዜ አለህ ንስሀ ለመግባት ምክንያቱም የክርስትና አላማ ሰዉን ማዳን ነዉ፡፡ እግዚአብሔር የሚያድነዉ ሰዉን ነዉ እናንተ የጠላችሁት ደግሞ ሰዉን ነው፡፡ ስለዚህ “የጠቢብ አይኑ በራሱ ነዉ” ስለሚል ጠቢቡ ሰለሞን ወደራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን እዩ ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ አሜን!!!

29 comments:

 1. The best, of the best Information and truth, article.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You Anto Menafik,do you have evidence for 7,000,000 (ሰባት ሚሊዮን),600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር),2,500,000.00 (ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር)? or plse do not pretend as if you are atrue christian. We know you are a thief, who is living in our church. Please do not insult MK as you coudn't deserve to insult them. manete Kelfares!

   Delete
 2. ምነው ስለቀደሙሕ ተናደድህ እንዴ አይ ማቅ ቀደም ቀረ በእንጨት መጫወት ስንት አመት ቀለድህ በቅዱሳንና በእመቤታችን ሥም
  በመነገድ። የደደብና የወሮበላ ጥርቅም፣ የቤተክርስቲያናችን ሸቃጭና ለዋጭ ነጋዴ፣ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ስም ማጭበርበርህንና፣
  ክርስቲያኖችን ማሳደድህን የብርሃን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃንን የፈጠረ አንተ በጨለማ የምትዶልተውን እያየ እድሜ ለንስሃ ሲሰጥህ ጊዜ የማያይ መስሎህ ክፉ ስራህ ጣመህና ቀጠልክ፣ አሁን ግን በቃ አለ እግዚአብሔር ጅራፉን አንስቶአል፡ ክፉ ስራህም
  በብርሃኑ እየተገለጠ ነው። ባለብህ ጭፍን ጥላቻና ከህዝበ ክርስቲያኑ በቤተክርስቲያን ሥም በምትዘርፈው ገንዘብ ልብህ አብጦ እንዲህ
  እንደፉለልክ አትቀርም። ገንዘቡም፡ አንተም፣ አለቃህ ዲያብሎስም ተያይዛችሁ እሳት። አይንህ እያየ አንተ የምታሳድዳቸው
  የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ምርጥ ልጆች ከጌታችንና ከመድሐኒታችን ጋር እያበቡ ሲሄዱ በቅናት እንደ ይሁዳ እራስህን ትሰቅላለህ።
  ምክንያቱም በሐሰት ጌታውን ለ ብ ር አሳልፎ እንደሰጠው ህሊናው ያውቅ ነበርና እናንተም እንደዚሁ ናችሁ። ሰውና ሰው እንዲጣላና በደሙ የመሰረታትን ቤተክርስቲያን እናንተ ለማፍረስ ስትሩሩጡ ሲያይ ጌታችን በጣም ያዝናል ግን አትችሉም፣ እመቤታችንንም
  ቢሆን ማታለል አትችሉም። አረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይቻላል የናንተ ነገር ብቻ ------ፍቅር\እግዚአብሔር\ ይቅር ይበላችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Amlak yesidib Afachihun Sayikotir Enditimelesu yadirigachihu. Yehenini Yahil Sedib Kesatinael /Luscifer Kalihone beker Menfesawi ageligilot Enesetalen kemil Endalihone Manin yiredawal. Motina Hiwot Banid Lay Lehedu ayichilum Huletum Tekaraniwoch Nachewuna. Enanite Tesadabiwoch Manim hunu man Lib Yistachihu. Kesemayawiw kekidus Michael Yetemarnew Amlak Yigesitseh maletin newuna Yesedib afin Amlakg Yigesitsew Amen.

   Delete
  2. አይ የመናፍቅ/የጴንጤ ድድብና! እስኪ የራስህን ቃላቶች ልጠቀም። መቼም ቅር አይልህም አይደል? ስድቡም የራስህ ስለሆነ ቻለው። አትገበዝ።

   ምነው ጴንጤው፥ ማቅ ስለቀደሙሕ፣ ስለመነጠሩህ፥ ሚስጥርህን ስለሚደርሱበት፥ ጨለማህን ስለገለጡት፥ ተኩላነትህን ስላሳወቁ ተናደድህ እንዴ? አይ የተሃድሶ መናፍቃን ነገር። ድሮ ቀረ በእንጨት መጫወት ስንት አመት ቀለድህ። እቅድህ ሁሉ አብሮ ከአባ ጳውሎስ ጋር ተቀበረ። ስትፈልግ በኢየሱስ ስም
   በመነገድ፤ ስትፈልግ በአባ ጳውሎስ ስም ስትነግድ፦( አንዱ ነጋዴ የወንጌል ሸቃጭ ቤተ ጳውሎስ እያለ ዌብ ሳይት ሲከፍት፤ ሌላኛው ነጋዴ የወንጌል ሸቃጭ ሃውልት ሲያሰራና እግዚአብሔር አትበሉ ሲል፤) ቆየህ። የደደብና የወሮበላ ጥርቅም፣ የቤተክርስቲያናችን ሸቃጭና ለዋጭ ነጋዴ፣ ተኩላ ጴንጤ ሆነህ ሳለ፥ ሁለት ደሞዝ እየተከፈለህ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ስም ማጭበርበርህንና፣
   ክርስቲያኖችን ማሳደድህን አቁም። እውነተኛ እምነት አለኝ ካልክ መሰሎችህ አዳራሽ ሄደህ ጨፍር። በጨለማ አትመላለስ። የብርሃን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃንን የፈጠረ አንተ በጨለማ የምትዶልተውን እያየ ( ስንት በድብቅ የዶለታችሁት ማስረጃና ቪዲዮ ነው የወጣው ) እድሜ ለንስሃ ሲሰጥህ ጊዜ የማያይ መስሎህ ክፉ ስራህ ጣመህና ቀጠልክ፣ አሁን ግን በቃ አለ እግዚአብሔር ጅራፉን አንስቶአል፡ ክፉ ስራህም
   በብርሃኑ እየተገለጠ ነው። ባለብህ ጭፍን ጥላቻና ከህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያን በምትዘርፈው ገንዘብ ልብህ አብጦ እንዲህ
   እንደፉለልክ አትቀርም። ገንዘቡም፡ አንተም፣ አለቃህ ዲያብሎስም ተያይዛችሁ እሳት። አይንህ እያየ አንተ- የጨለማ/ተሃድሶ ጴንጤና የሙስና አባላት- የምታሳድዳቸው
   የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ምርጥ ልጆች ከጌታችንና ከመድሐኒታችን ጋር እያበቡ ሲሄዱ በቅናት እንደ ይሁዳ እራስህን ትሰቅላለህ። ይሁዳ ጌታን በ፴ ብር እንደሸጠ አንተም ቤተ ክርስቲያኒቱን በብር ሸጠሃታል።
   ይሁዳ ቢያንስ በሐሰት ጌታውን ለ ብ ር አሳልፎ እንደሰጠው ህሊናው ያውቅ ነበርና ተፀፀተ። እናንተም ግን ህሊና የላችሁም። የደደብና የወሮበላ ጥርቅም ናችሁ። ሰውና ሰው እንዲጣላና በደሙ የመሰረታትን ቤተክርስቲያን እናንተ ለማፍረስ ስትሩሩጡ ሲያይ ጌታችን በጣም ያዝናል። እናንተ ግን ከገንዘብ ውጪ ሃይማኖትም ሆነ እምነት የሚባል የላችሁምና ማንንም ማታለል አትችሉም። ፍሬያችሁ ያስታውቃል። አረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይቻላል የናንተ ነገር ብቻ ------እግዚአብሔርን አታውቁትም እንጂ እሱ ፍቅር\እግዚአብሔር\ ይቅር ይበላችሁ። ልቦና ይስጣችሁ። ከጨለማው ከተደበቃችሁበት ያውጣችሁ።

   Delete
  3. kuletegnaw asteyayet copy cat. aye mk/ms/ Copy Cat kikikikikikikikik.

   Delete
  4. አይ የኔ መሃይም ጴንጤ አንብበህ የመረዳት ችግር አለብህ ማለት ነው:: እንጂ "አይ የመናፍቅ/የጴንጤ ድድብና! እስኪ የራስህን ቃላቶች ልጠቀም። መቼም ቅር አይልህም አይደል? ስድቡም የራስህ ስለሆነ ቻለው። አትገበዝ።" ይላል እኮ:: አንብበህ ተረዳ:: መሳቂያ ሃሃሃሃሃሃሃ

   Delete
  5. wustihe eyawekewu afeh gne alereta ale. yasazenal, bacheru kefu alamachehu sletawekebachehu betam tenadachal, ayzohe feteneh neseha geba Amlak mehari newu. yesafkewun hulu anbebewalehu ymaytekem selehon trash/delete/ adregewalehu. lewedfitu gne copy madrege bhege yasketalna, copy ataderege eshi?
   Egziabeher yibarkeh.

   Delete
  6. ግብዙ ጴንጤ በመጨረሻ በመከራ ገባህ አይደል? እኔም እኮ እያልኩ ያለሁት ይሄንን ነው። what you wrote was a trash, but I didn't delete it. Rather wrote the same word you wrote and you felt it's trash - your words. That was my aim.
   በህግማ የሚያስጠይቅ ስንት ነገር አለ መሰለህ።
   ለማንኛውም እንኳን ዘግይቶም ቢሆን ፅሁፍህ ቆሻሻ እንደሆነ ገባህ።
   ተመስገን።

   Delete
 3. Replies
  1. Tehadiso pente and you are stupids!

   Delete
  2. በነዋይ ፍቅር የሰከረው ማቅ መቀመቅ ይውረድና በቅዱሳንና በእመቤታችን ሥም በቤተክርስቲያናችህን የሚነግደው አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥራ መቀማት ፈልጎ እንደ ሳጥናኤል እየዞረና እያገሳ እኔ ሁሉን አዋቂ ነኝ፣ ከኔ በላይ ለቤተክርስቲያን የቆመ የለም በማለት ውዥንብሩን አየነዛ ይገኛል። የአንድን ሰው እምነት የሚለካውና የሚመረምረው ቅዱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የቤተክርስቲያናችንን ብርቱ ሰባኬ ወንጌላዊያንና ሊቃውንት ወንድሞቻችንን መናፍቅና ሌላም ሌላም ስም በመስጠት ከህዝበ ክርስቲያ ጋር ማጣላት፣ ማቃቃር፣ እምነት ማሳጣትና ማባላትን ሲኪያሂድ የቆየ ሲሆን፤ ይህ የሳጥናኤል ሥራው ለትንሽ ጊዜ የሠራለት መሆኑን አየና ይህንኑ የሰይጣን ስራውን ተያያዘው። ደስ የሚለው ነገር ግን ጌታችን ሁልጊዜም አሸናፊ በመሆኑ የጠላት ወሬውን እያጋለጠ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው። ግን ጌታችን እድሜ ለንስሃ ስለሰጣቸውና ስለታገሳቸው፣ ትክክል የሰሩ መሰላቸው። እንኩአን ኃያሉ ጌታ፣ ህዝበ ክርስቲያኑም አሁን ተንኮላቸውን አውቆ ተቀባይነት ካጡ አመታት አስቆጥሩአል። የወንድሞች ከሳሽ ማቅም እያፈረ ስለመጣ ሌላ ግድግዳ መጫር ጀምሩአል፡ እግዚአብሔር ደግሞ የራሱ የሆኑትን እሱ ያውቃልና ምስማር ሲመቱት እንደሚጠብቀው
   ሁሉ ልጆቹን ከመቸውም በበለጠ እያፅናና በድል እየመራቸው ይገኛል። ክብር ለአምላካችንን ይሁን። ሰይጣንና የሰይጣኑ ማህበር ወደ ተዘጋጀለት እንጦሮጦስ እየወረደ ይገኛል። በማቅ የተገፉት የቤተክርስቲያናችን ወንድሞችና ህዝበ ክርስቲያኖች ግን እያበቡ
   ነው። መድሐኒያለም ክርስቶስ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን።

   Delete
 4. አይ መናፍቃን ምን ይሻላችኃል ሁል ግዜ ማሐበረ ቅዱሳንን መክሰስ ብቻ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ናችሁ ተዋህዶን ተዋት ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዴት ወዴት እባክህ? ማቅ ሌላ! ተዋህዶ ሌላ!!

   Delete
  2. እረ ተው ወይኔ አላወኩም እኮ እስቲ ንገረኝ ?

   Delete
 5. abba huket! When are you open your mouth for peace,love, unity, repentance,and so forth. You have been designed and produced to be the tool of Devil.Wey alemetadel!? By any standard you are truly the slaves of yetifat lij.Please grow up,kids.

  ReplyDelete
 6. Asbe Teferi MK tiru sira eyesra new malet new? good

  ReplyDelete
 7. Guys, you have to know about Seyitan. Seyitan never sleep all his life. mahibere kidusans means like seyitan and never sleep all there life.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Derom Egziabeher Lemetegnat Alasebasebenim. Seytan Eskale Dires Yebetekristiyan Lijoch Litegnu Ayigebam. Seytan ende Esist Melkun Eyekeyayere Bimetam Bemenfes Kidus Hailna Gelachinet siraw Eyetegalete Eskiwared Dires MK Ayitegnam. Lemetegnat Almeseretinewum. Bezih Meder Metegnat Endemayigeba Getachin "Niqu Siga dekama new Menfes gin Tezegajitalech" Degimom "Tegitachihu Tseliyu" balew Yitawokal.

   Delete
  2. Leselot eko newu tegu yetebale. mk gne sewun behaset lemekses enkelef yelewum ende seytan.

   Delete
 8. ማቅ ማለት ንፋስ የገፋው ደመና ዝናብ የሌለበት ባዶ ማህበር ነው። ድሮ ህዝቡ በመንፈሳዊ ህይወቱ ጥንካረ ስላለበረው እጅግ ብዙ ገንዘብ በቅዱሳን ስም ይዘርፍ ነበር።አሁን ግን ህዝበ ከርስትያኑ እጅግ የጠነከረ በመሆን ማታለል ስላቃተው ሁሉ ተሃድስ መናፊቅ እያለ የወንድሞችንና የአባቶችን ስም ያጠፋል። ምክንያቱም እንደ ቀድሞ ማታለል አልቻለም።ማቅ የድፍረት ድፍረቱ እርሱ ማህበር የማደግፉትን ሊቃነ ጳጳሳት እና ጳጳሳት ሳይቀሩ ተሀድሶ መናፍቅ እያለ አባቶች የሚዳደብ ከፉ መንፈስ ነው።ወጌነ ይበቃል ከእንግድህ ማን ለአንተ ግብሩን የሚገብር የለም።NO more to play stupid game.,,,,,

  ReplyDelete
 9. Mk is not faith, it just a group of some gangsters.we know them who they are.Orthodox Tewahedo faith and MK is not the same.it is very big difference. May be our Sunday school (Mezemeran) need to carefully understand Orthodox and MK. because those Sunday school members paying money to MK from 10 dollars of one to MK..........that is to stupid.......we are disagree with Mezemeran.,,,,,

  ReplyDelete
  Replies
  1. They know every thing better than you.

   Delete
 10. mk is not tewahedo. it is sytanic

  ReplyDelete
 11. Mk behedebet hulu ya seytan tewekayi huno mebetibet naw siraw!wedegn akebabim(Arsi Negele)andi kegn gar la betekristiyan lewat yematitega ihit andi mk yehone boy friend yeza agalatalahu tahadiso ale iyalech balawan lemasideset iyatarech ignan behaset iyekesesechan naw ina ayzowachu asebe teferiwochi

  ReplyDelete
 12. በነዋይ ፍቅር የሰከረው ማቅ መቀመቅ ይውረድና በቅዱሳንና በእመቤታችን ሥም በቤተክርስቲያናችህን የሚነግደው አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥራ መቀማት ፈልጎ እንደ ሳጥናኤል እየዞረና እያገሳ እኔ ሁሉን አዋቂ ነኝ፣ ከኔ በላይ ለቤተክርስቲያን የቆመ የለም በማለት ውዥንብሩን አየነዛ ይገኛል። የአንድን ሰው እምነት የሚለካውና የሚመረምረው ቅዱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የቤተክርስቲያናችንን ብርቱ ሰባኬ ወንጌላዊያንና ሊቃውንት ወንድሞቻችንን መናፍቅና ሌላም ሌላም ስም በመስጠት ከህዝበ ክርስቲያ ጋር ማጣላት፣ ማቃቃር፣ እምነት ማሳጣትና ማባላትን ሲኪያሂድ የቆየ ሲሆን፤ ይህ የሳጥናኤል ሥራው ለትንሽ ጊዜ የሠራለት መሆኑን አየና ይህንኑ የሰይጣን ስራውን ተያያዘው። ደስ የሚለው ነገር ግን ጌታችን ሁልጊዜም አሸናፊ በመሆኑ የጠላት ወሬውን እያጋለጠ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው። ግን ጌታችን እድሜ ለንስሃ ስለሰጣቸውና ስለታገሳቸው፣ ትክክል የሰሩ መሰላቸው። እንኩአን ኃያሉ ጌታ፣ ህዝበ ክርስቲያኑም አሁን ተንኮላቸውን አውቆ ተቀባይነት ካጡ አመታት አስቆጥሩአል። የወንድሞች ከሳሽ ማቅም እያፈረ ስለመጣ ሌላ ግድግዳ መጫር ጀምሩአል፡ እግዚአብሔር ደግሞ የራሱ የሆኑትን እሱ ያውቃልና ምስማር ሲመቱት እንደሚጠብቀው

  ReplyDelete
 13. Let us pray to get the true answer. In the last 20 years the number of our church followers reduced dramatically. Some groups are against the truth stated in the bible and the others are not systematic and organized to absorb the shock. The Asebe Teferi St. Marry church is a model in terms of organizing different individuals from different profession to contribute to the construction of the church. The construction of the church was delayed for about two decades. It is well known how it was delayed. The church followers need truth, truth and truth. The truth is clearly stated in the holy bible. When ever we use unreligious and uncivilized words we open a hole for our enemy (Devil) to destabilize the church. Why we are trying to judge on other? Congratulations those of you contributed for the construction of St Marry church in Asebe Teferi.

  ReplyDelete
 14. "ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥"

  2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:1-4"ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"

  2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:13-14

  ReplyDelete
 15. አይ መሪ…….

  ReplyDelete