Friday, August 30, 2013

ቤተክህነት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን አንደኛ ዓመት የመታሰቢያ ሥነሥርዓትን ማደብዘዙ ብዙዎችን አሳዝኗል

ቤተክህነት የዛሬ ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያን እንደ ደሃ ፍታት አደብዝዞት መዋሉ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ የቅዱስነታቸው የሙት ዓመት መታሰቢያ ባለፈው ነሐሴ 10/2005 ዓ.ም ሲከበር በቤተከህነት በኩል ምንም አይነት ዝግጅት እንዳልተደረገበትና ምንም አይነት ትኩረት እንዳልተሰጠው በዕለቱ የታየው ዝግጅት በቂ ምስክር ነው፡፡ ለዚህም በዋናነት ተጠያቂው ጠቅላይ ቤተክህነቱ ነው፡፡ ክብር ለሚገባው ክብርን መስጠት ሲገባ የቤተክርስቲያኗ መሪ የነበሩትን የቅዱስነታቸውን መታሰቢያ ማደብዘዝ ለምን አስፈለገ? የሚለው በብዙ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ መታሰቢያቸው የመገናኛ ብዙኃንን ሽፋን በተገቢው መንገድ አላገኘም፡፡ ይህም ለዝግጅቱ ከተሰጠው አናሳ ትኩረት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሪፖርተር ጋዜጣ ግን ሽፋን ሰጥቶታል፡፡ የቅዱስነታቸው የመታሰቢያ ሥነሥርአት ሰፊ የሚዲያ ሽፋን የተነፈገው ምናልባት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙታመት መታሰቢያ ከፍተኛ ትኩረት ስለተሰጠው ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን “ባለቤቱ ያቃለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም” እንደሚባለው ቤተክህነቱ ቸል ያለውን ሌላው እንዴት ሊያተኩርበት ይችላል የሚለው ብዙዎች የተስማሙበት ነጥብ ሆኗል፡፡
 
ቅዱስነታቸው በፕትርክና ዘመናቸው ለቤተክርስቲያኒቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ለመሆናቸው ሥራዎቻቸውና ለቤተክርስቲያኗ በዓለምአቀፍ ደረጃ ያስገኙት እውቅና በቂ ምስክሮች ናቸው፡፡ እነዚህን በአይን የሚታዩ በእጅ የሚዳሰሱ የስራ ውጤቶችን መካድ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ሰው እንደመሆናቸው ያጠፉትም ይኖራል፡፡ ይሁንና እኒህን ታላቅ አባት ካንቀላፉ በኋላ መታሰቢያቸውን በተገቢው መንገድ አለማክበር ለቤተክህነቱ ክብር ሳይሆን ትልቅ ውርደት ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን ፓትርያርክ ማትያስ ተጠያቂ ናቸው፡፡ ፓትርያርክ ማትያስ ገና ከመነሻቸው አቡነ ጳውሎስ ያደርጉ የነበረውን አብዛኛውን ነገር አላደርግም በሚል የእርሳቸውን ሥራና በዘመናቸው ያደረጉትን ብዙ ነገር መቃወማቸውንና ማክፋፋታቸውን ገልጸዋል፡፡ ለምሳሌ ነጭ ልብስ አልለብስም ብለዋል፡፡ ነጭ ልብስ መልበስ በአቡነ ጳውሎስ አልተጀመረም፡፡ ከእርሳቸው በፊት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ለብሰዋል፡፡ ነገር ግን አቡነ ማትያስ በጥቁሩ ልብስ ምን ሠሩበት ነው ጥያቄው፡፡ ተቃውሞ ብቻውን ተግባር ሊሆን አይችልም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፓትርያርክ ማትያስ በየበዓሉ ቃለ ምእዳን ከማሰማት ያለፈ ምን እያደረጉ እንደሆነ እንኳን ለመናገር በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡ የቤተክርስቲያኗ ችግሮች እየተወሳሰቡ በመጡበት ሁኔታ እዚህ ግባ የሚባል አመራርና ወሳኝ እርምጃ ሲወስዱ አልታየም፡፡ ስለዚህ ብዙዎች የአቡነ ጳውሎስን ዘመን እያመሰገኑና ማትያስን በጳውሎስ እየመዘኑ ይገኛሉ፡፡  

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ካረፉ አንድ ዓመት ያለፈ ሲሆን በጀት ተመድቦለት ለተቋራጭ የተሰጠው ሐውልታቸው ግን እስካሁን አልተሰራም፡፡ “የአይጥ ምስክር ድንቢጥ” እንዲሉ ቤተክህነቱ ያደበዘዘውን የመታሰቢያ ስነሥርዓታቸውን እጅግ አደብዝዞ የዘገበው ሐራ ዘተዋህዶ፣ ለሐውልቱ አመለሰራት ተጠያቂ አድርጎ ያቀረበው ተቋራጩን ሲሆን እንደምንጮቻችን ከሆነ ግን የሐውልቱን ስራ ቤተክህነቱ ትኩረት አልሰጠውም አልተከታተለውም፤ ከዚህ የተነሣ ነው በተቋራጩ በኩል መዘግየት የታየው ይላሉ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን መንደር ደግሞ ሐውልታቸው ያልተሰራው በኃጢአታቸው ምክንያት የቅዱስነታቸው አስከሬን በተዘጋጀለት ስፍራ ማረፍ ስላልቻለና መሬት ከድቶት ወደመሬት ሰርጎ ስለገባ ነው የሚል ወሬ ይናፈስ እንደነበር ምንጮች የተናገሩ ሲሆን አንዳንድ የዚህ ተረት ሰለባ የሆኑ ምዕመናን በእለቱ ተገኝተው ነገሩ ውሸት መሆኑን ለማረጋገጥ መቻላቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

የቅዱስነታቸው መታሰቢያ እንዲደበዝዝ የተደረገው ከጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተላለፈውንና በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ጸሎተ ፍትሀት እንዲደረግ መልእክት ይተላለፍ ዘንድ የሚያዘውን ደብዳቤ ማህበረ ቅዱሳን ያዝበት የጀመረው የአባ እስጢፋኖስ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አፍኖ ስለያዘው ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ የተነሳ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት በዕለቱ ጸሎተ ፍትሀት አልተደረገላቸውም ይላሉ ምንጮቻችን፡፡ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተደረገው ስነስርአት ላይ የተገኙትና ከተሾሙ ጊዜ ጀምሮ ቤተክህነቱን መምራት ያልቻሉት፣ የቅድስት ስላሴ ኮሌጅን ችግር እንኳን መፍታት ተስኗቸው ለወዳጃቸው ለአባ ጢሞቴዎስ አድልተው ኮሌጁ ይዘጋ የሚል ደብዳቤ ጽፈው የነበሩት በኋላም በሲኖዶስ ውሳኔ ደብዳቤያቸው የተሻረባቸው ፓትርያርክ ማትያስ ጥቂት ጳጳሳትን አስከትለው ከልብ ያላሰቡበትን የአቡነ ጳውሎስን የሙት ዓመት መታሰቢያ ለማክበር የተገኙ ቢሆንም ከአንገት በላይ የሆነ ጸሎትና ቡራኬ ማድረጋቸው ለመታሰቢያው የሰጡትን ስፍራ ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል፡፡

በስፍራው የተገኙ የአይን ምስክሮች እንደገለጹት ከሆነ በቤተክህነቱም ሆነ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኩል የቅዱስነታቸውን መታሰቢያ ለማክበር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተደረገ ዝግጅት አልነበረም፡፡ መካነ መቃብራቸው በቆርቆሮ የታጠረ ከመሆኑ በቀር ለመታሰቢያ ስነስርአቱ ዝግጁ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ቤተክህነቱ ሊያደበዝዘው የሞከረውን መታሰቢያ የቅዱስነታቸው የመንፈስ ልጅ የሆኑት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እንዲደምቅ አድርገውታል ተብሏል፡፡ ይኸውም የቅዱስነታቸውን ትልቅ ፎቶ የያዘና “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል” የሚለው ጥቅስ በተጻፈበት ትልቅ ባነር የሸፈኑት ሲሆን፣ ድንኳንም አስተክለው መታሰቢያቸው ደመቅ እንዲል የተቻላቸውን አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም የቅዱስነታቸው ፎቶ የታተመበትን ቲሸርት ለአንዳንዶች ማደላቸው ታውቋል፡፡ እንደ ወ/ሮ እጅጋየሁ ሁሉ ሌሎች ወዳጅ ዘመዶቻቸውም በርካታ የአበባ ጉንጉኖችን መካነ መቃብራቸው በታጠረበት ቆርቆሮ ሥር አስቀምጠዋል፡፡

ይህን ሁኔታ የተመለከቱና ዝግጅቱን ለማድመቅ የቻሉት ወ/ሮ እጅጋየሁ መሆናቸውን ያወቁ አንዳንድ ጳጳሳት በመገረም “እኚህ ሴት እኮ ወረት የማያውቁ እውነተኛ ወዳጅና የቤተ ክርስቲያን ሰው ናቸው፡፡ አሁን ማን ይሙት እንዲህ የሚያደርግ ማነው? እኛ የረሳናቸውን አባታችንን ሞተውም አልረሷቸውም፡፡” ሲሉ ለወ/ሮ እጅጋየሁ ስራ አድናቆታቸውን ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡

የቅዱስነታቸው የአቡነ ጳውሎስን ሙት አመት በተገቢው ሁኔታ ማክበር ጥቅሙ ለራስ ክብሩም ለቤተክርስቲያን ነበር፡፡ ከቁማቸው ይልቅ በሞታቸው የቤተክርስቲያን ታላቅ ባለውለታ መሆናቸው እየታወቀ የመጣው አቡነ ጳውሎስ በቅርቡ በሥላሴ ኮሌጅ የተከሰተውን ችግር አስመልከቶ የወቅቱ ፓትርያርክ ያሳዩትን ቸልተኝነትና ተማሪዎችንም ለማነጋገር አለመፈለጋቸውና ችግሩን ለመፍታት የወሰደው ጊዜ ሲታሰብ፣ ብዙዎችን አቡነ ጳውሎስ ቢኖሩ ኖሮ እንዴት ባለ ጥበብ ችግሩን በፈቱት እንዲሉ አስገድዷል፡፡ በተማሪዎቹ ምረቃ ዕለትም በአደባባይ ለአቡነ ጳውሎስ ምስጋና ሲቀርብ ተማሪዎቹ ያደረጉት ረዘም ያለ ጭብጨባ ይህንን የሚያረጋግጥ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም የቅዱስነታቸውን አንደኛ ዓመት መታሰቢያን በተመለከተ አንዳንድ የደብር አለቆች በራስ ተነሳሽነት ካደረጉት በቀር በሃገረ ስብከት ደረጃ ምንም አይነት መመሪያ አለመተላለፉ ማቅ ከዚህ በፊት ከሞቱ 100 ዓመት ያለፋቸውን ሰዎች ጨምሮ የቤተክርስቲያን አባቶች ይወገዙልን ማለቱን እያስታወሰን፣ በቆሙት ላይ ብቻ ሳይሆን በሙት ላይ እንኳ ሥር የሰደደው ቂም በቀሉ ምን እንደሚመስል በተግባር ያሳየናል፡፡

ደግነቱ ፍርድ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር እጅ ሆነ እንጂ የማቅ አመራሮች እድሉን ቢያገኙማ በምክንያት ሳይሆን በጥላቻ የሚመራው አእምሮአቸው ስንቱን ቅዱሳን ወደ ሲኦል ይዶሏቸው እንደነበር መገመት አይከብድም፡፡ በአንድ ወቅት አንድ የማህበሩ የጎንደር ማዕከል ኃላፊ የነበረ ሰው ከወንድሞች ጋር ሲወያይ ለሚያነሳው ሀሳብ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳብና ጥቅስ እየጠቀሱ ቢያሳፍሩት፣ “እኛን ያስቸገሩን እኮ የጳውሎስ መልዕክታት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገብተው መገኘታቸው ነው፡፡ እንደ እሱ ያስቸገረን እና ለማኅበሩ አላማ እንቅፋት የሆነ የለም፡፡ ምን አለ አባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስ እንደገና ይጠረዝ ብለው የጳውሎስን መልዕክታት ባስወጧቸውና ባሳረፉን” በማለት እንኳን የዚህን ዘመን ሰዎች ቀር ሺህ ዓመታትን ተሻግረው በነበሩና ለቤተክርስቲያን አዕማድ በሆኑ ቅዱሳን አባቶች ላይ ማኅበሩ ያለውን ጥላቻ አስረድቷል፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ሙት ወቅሰው ደንጋይ ነክሰው የአቡነ ጳውሎስ ስም በበጎ እንዳይነሳ ቢጥሩ ምን ይገርማል?

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሙት ዓመት ፍትሀተ ጸሎት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን፣ በየአድባራቱና በየገዳማቱም ጸሎተ ፍትሀት እንዲደረግ ታዝዞ የነበረ ሲሆን ማቅ የሚያዝበት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ግን መልእክቱን እንዳላስተላለፈና በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብቻ ሥነሥርአቱ እንደተደረገ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲህ ማድረግ ታላቅ ነኝ ከምትለው ቤተክርስቲያን አይጠበቅም፡፡ እየተደረገ ያለው የቂም በቀል መንገድ ተራ የሕፃናት ጨዋታ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ በምን አይነት መሪዎች እጅ ላይ እንደወደቀችም ትልቅ ማሳያ ሆኗል፡፡

20 comments:

 1. በቅዱሳን ስም በአቡነ ሰላማ ስም መናፍቃን መነገድ አይችሉም፡፡ ቅዱሳን ሲዘከሩ የተለያየ ነገር እያላችሁ ስታክፋፉ የምትታዩት እናንተ ናችሁ፡፡ መናፍቃንን እንደፈለጋቸው እንዲፈነጩ እድሉን የከፈቱ አንዱ አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡ ህገወጥ ሰባክያንና ዘማርያንን ማውገዝ ትተው ስርዓት አልባ ያደረጉ፡፡ ከውስጥጉዳያቸው ይልቅ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዘዳንት በመባላቸው የቤተክርስቲያንዋን ጥቅም አሳልፈው ለውጭ ቅጥረኞች የሰጡ፤ በቤተክርስቲያንዋ ዙሪያ በላተኛ ያበዙበት የውም ማጅራት መቺና ቀማኛ ከነዚህ ውስጥ እጅጋየሁ አንድዋ ነች ጳጳሳትን እንኩዋን እስከመዝለፍ እንድትደርስ ያደረጉ የቤተክርስቲያንን ጥቅም ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል መሪ እንድትሆን ያደረጉ ፤ አሁን አደረገች የምትሉት ነገር ቢኖር ከቤተክርስቲያን በዘረፈችው ወይም ባዘረፉዋት ብር ነው፡፡ ከሁሉም ማዘን የሚገባትም እስዋ ነች ለምን ቢሉ ጥቅምዋ ቀርቶባታልና፤ ሌሎችን ለማማለል ብትሮጥም አይደንቅም፡፡
  የቅዱሳንን ክብረ በዓል ተቃውማችሁ እንደፈለጋችሁ እንድትሆኑ በር ከፍተውላችሁ የነበሩት ሙት ዓመት ይታሰብ ማለታችሁ ይደንቃል፡፡ ክብረ በዓል ሲሆን ሲቀድሱ ምዕመኑ በጥምቀትና ጊዜ እንደሚመለከታቸው ሙሉ ነጭም ባይሆን የሚለብሱት አይነት የትኛውም ፓትርያሪክ ለብሶዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የካቶሊክ አቀንቃኝ ናቸው፡፡ ቤተክርስቲንዋ አበቃላት በተባለ ሰዓት የሞቱ በመሆኑ ቤተክርስቲያንዋ ከውድቀት እንድትድን እግዚአብሔር ያደረገው ነው፡፡ አቡነ ማትያስ ሲመጡ ደግሞ መልካም ነገር እግዚአብሔር እንደሚያደርግ ተጠብቆአል እንደታሰበውም እየሆነ ነው፡፡ የተሃድሶ አቀንቃኞች እርር ድብን በሉ እንጂ በአቡነ ማትያስ ጊዜ መንገድ አይኖራችሁም፡፡ ለዚህም ነው በሳቸው ላይ ተቃውሞ የምታነሱት፡፡ ፓትርያርኩ ከተሾሙ ጥቂት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያደረጉት ነገር ቤተክርስቲያንዋን በትክክለኛው መንገድ እንድትሄድ የሚያደርጋትን ነገር ስለሆነ የኛ ሰው አልተሸመም በሚል በሳቸው ላይ መናገር ተገቢ አይደለም፡፡
  በቅዱሳን ስም በአቡነ ሰላማ ስም መናፍቃን መነገድ አይችሉም፡፡ ቅዱሳን ሲዘከሩ የተለያየ ነገር እያላችሁ ስታክፋፉ የምትታዩት እናንተ ናችሁ፡፡ መናፍቃንን እንደፈለጋቸው እንዲፈነጩ እድሉን የከፈቱ አንዱ አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡ ህገወጥ ሰባክያንና ዘማርያንን ማውገዝ ትተው ስርዓት አልባ ያደረጉ፡፡ ከውስጥጉዳያቸው ይልቅ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዘዳንት በመባላቸው የቤተክርስቲያንዋን ጥቅም አሳልፈው ለውጭ ቅጥረኞች የሰጡ፤ በቤተክርስቲያንዋ ዙሪያ በላተኛ ያበዙበት የውም ማጅራት መቺና ቀማኛ ከነዚህ ውስጥ እጅጋየሁ አንድዋ ነች ጳጳሳትን እንኩዋን እስከመዝለፍ እንድትደርስ ያደረጉ የቤተክርስቲያንን ጥቅም ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል መሪ እንድትሆን ያደረጉ ፤ አሁን አደረገች የምትሉት ነገር ቢኖር ከቤተክርስቲያን በዘረፈችው ወይም ባዘረፉዋት ብር ነው፡፡ ከሁሉም ማዘን የሚገባትም እስዋ ነች ለምን ቢሉ ጥቅምዋ ቀርቶባታልና፤ ሌሎችን ለማማለል ብትሮጥም አይደንቅም፡፡
  የቅዱሳንን ክብረ በዓል ተቃውማችሁ እንደፈለጋችሁ እንድትሆኑ በር ከፍተውላችሁ የነበሩት ሙት ዓመት ይታሰብ ማለታችሁ ይደንቃል፡፡ ክብረ በዓል ሲሆን ሲቀድሱ ምዕመኑ በጥምቀትና ጊዜ እንደሚመለከታቸው ሙሉ ነጭም ባይሆን የሚለብሱት አይነት የትኛውም ፓትርያሪክ ለብሶዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የካቶሊክ አቀንቃኝ ናቸው፡፡ ቤተክርስቲንዋ አበቃላት በተባለ ሰዓት የሞቱ በመሆኑ ቤተክርስቲያንዋ ከውድቀት እንድትድን እግዚአብሔር ያደረገው ነው፡፡ አቡነ ማትያስ ሲመጡ ደግሞ መልካም ነገር እግዚአብሔር እንደሚያደርግ ተጠብቆአል እንደታሰበውም እየሆነ ነው፡፡ የተሃድሶ አቀንቃኞች እርር ድብን በሉ እንጂ በአቡነ ማትያስ ጊዜ መንገድ አይኖራችሁም፡፡ ለዚህም ነው በሳቸው ላይ ተቃውሞ የምታነሱት፡፡ ፓትርያርኩ ከተሾሙ ጥቂት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያደረጉት ነገር ቤተክርስቲያንዋን በትክክለኛው መንገድ እንድትሄድ የሚያደርጋትን ነገር ስለሆነ የኛ ሰው አልተሸመም በሚል በሳቸው ላይ መናገር ተገቢ አይደለም፡፡


  ReplyDelete
  Replies
  1. Oh My God, what kind of person are u? u have big mouth, u will see Geta kereb newu ayineh eyaye Geta ymiwdachew Aba Pawulos betam talak abat neberu. Shame on u . afehen kefteh e-christiyanawi neger besachew lay setenager kelay wagahen tagegnaleh. keman gar endmetederader alawekehem wondeme, fered YGetachen engi yante ayidelem. Egziabeher yiker yibeleh.

   Delete
 2. KIMJAMA kenat belay yelem azaje kebe angoc nachu

  ReplyDelete
 3. abaselama Chomitiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiiii!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! With out Insulting MK U don't have any thing. KOBEROOOOOOOOOOOOOO

  ReplyDelete
 4. የነገረ ሰሪ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ ታውቃችሁ ግን እንዲህ ተቆርቋሪ መስላችሁ ቤተ ክርስቲያንን ስታሳድዱ?

  ReplyDelete
 5. Beftihat mamen jemerachihu endie? Ashikabach hula!.....

  ReplyDelete
 6. I thought I was reading Dejeselam for a little while. What was the relevance of writing the low profile anniversary of the passing away of both leaders? The wind of hypocrisy blew through Aba Selam. Our Prime Minister was not an orthodox Christian, in fact He did not believe in God yet he was memorized as a Tewahido Christian. His funeral and the processions was carried by higher ranking bishops. Then the question why should have surfaced for a good answer, but did not. The late Patriarch's legacy was marred by lots of criticisms, perhaps the church wanted to play low to give it a closure.Anyway I do not see the significance of writing the above article.

  ReplyDelete
 7. በአንድ ወቅት አንድ የማህበሩ የጎንደር ማዕከል ኃላፊ የነበረ ሰው ከወንድሞች ጋር ሲወያይ ለሚያነሳው ሀሳብ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳብና ጥቅስ እየጠቀሱ ቢያሳፍሩት፣ “እኛን ያስቸገሩን እኮ የጳውሎስ መልዕክታት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገብተው መገኘታቸው ነው፡፡ እንደ እሱ ያስቸገረን እና ለማኅበሩ አላማ እንቅፋት የሆነ የለም፡፡ ምን አለ አባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስ እንደገና ይጠረዝ ብለው የጳውሎስን መልዕክታት ባስወጧቸውና ባሳረፉን” በማለት እንኳን የዚህን ዘመን ሰዎች ቀር ሺህ ዓመታትን ተሻግረው በነበሩና ለቤተክርስቲያን አዕማድ በሆኑ ቅዱሳን አባቶች ላይ ማኅበሩ ያለውን ጥላቻ አስረድቷል፡፡

  ReplyDelete
 8. sorry 4 mk if they do suck kind of thing i do really sorry

  ReplyDelete
 9. Shame, Shame, Shame on you bete kehedet. Woradoch, deros ke-mk na kewushet askema lebash haymanot yelesh leba gar mene yitebekal...
  But, God is Great all the time.!!!!!

  ReplyDelete
 10. That is ok. Bc he was not doing good for our church particularely in mk. His cousin Abazelebanose in Atlanta suffering from Aids. YOU abaselama fuck you bc you hate mk for nothing. I am glade to be as MK. FUCK MYOUUUUUUUUUUU, ][]

  ReplyDelete
 11. Feyel wediya Kizimzimwediya!!! Mahibere Kidusan wediYa YeAsddis Ababa Hageresibket Wediya Min agenagnachew??? Yemotutin Nefisachewun yimarilin. Enaniten Gin yasitagisilin Lemin bitilu Kekumum Kemutum Litatalun betekristiyanachinim Litaswekisu Titataralachohuna. Kidus michael "Amlak Yigesitsi" endale Amlak Yigesitsachihu.

  ReplyDelete
 12. ena aragabi hula, enante eko atafrum bherawi beal yihun tilu yihonal kkkkkkkkkk aye tehadiso?????????????? hulet milas hula!!!!

  ReplyDelete
 13. መቸ ነዉ እዉነት ምትናገሩ;እዲያዉስ እናንተ ቅዱሳን መታሰቢያ አያስፈልጋቸዉም አደል ምትሉ;ድንግልማርያምን ተክለሀይማኖተን.አባህርያቆስን…………….የምታጥላሉ ስለ አቡነ ጳዉሎሰ ምንም እንደማያገባቸሁ አይምሮ ያለዉ ሁሉ ይገነዘባልልል፡፡ምነዉ በከንቱ ደከማችሁ፡አይ አለመታደል፡

  ReplyDelete
 14. you have tried your best to express your hatred view againist MK, nothing else!

  ReplyDelete
  Replies
  1. THE SAME THING IS HAPPENING IN DILLA ORTHODOX CHURCH.
   I WISH GOD HELP US TO CALL THE NAME JESUS WITH FULL CONFIDENCE.

   Delete
 15. egziabher wagachune yikfelachihu
  ADIS ABEBA HEGERE SIBKET BBALE 2MISTOCH PAPASNA MAHEBER KIDUSAN EYETEMARA XDEBARATUNE ENDEMESGIDE yEBITBETNA POLETIKA MENAHARYA LEMADERGE 2 BIROWOCE BENta TESTITOT YALKIRA\YE BAHEGRE SIBKETU EYESERA NEWE ,YESLIK yEMBERAT ENEKANE AYKEFLIM

  ReplyDelete
 16. The anonymous above emphatically stressed that this blog's intention was to discrediting Mahibere Kidusan. Cautiously I disagree. I am not an individual who gets in to serious Haimanot arguements and issues. I simply practice the simple dos and don'ts of the Tewahido norms. I knew nothing of Mahebere Kidusans until about eight years ago. It was when The Houston Medhanealem add a new deacon to its preaching priest squad. Then Deacon now probably a priest told us that he came to Houston in defiance to Mhibere Kidusan secretly. He was suppose to go to Atlanta to check and harass Memhier Luel Khal of Saint Mary Church Atlanta. He said that his trip and boarding expenses werefully covered by this organization, had he gone to Georgia, but he got lucky for one father had helped him facilitating this trip to Houston Secretly. A few of us asked what Mahibre Kidusan was? and he replied going against certain kahenats they disliked and hate. Their practice and deeds had surged fear of them even in Bete Khnets. A few years ago the same guy married a diehard Mhibere Kidusan member and her influence had plaid a significant role in switching him back.

  ReplyDelete
 17. ኦርቶዶክስም ሆነ መንፈሳዊ መሆን መቼም ከአምላክ የሚሰጥ ትልቅ ስጦታ ነው ይህን አልታደላችሁም አሁንስ የምትሰሩትን የማታቁ እብድ መሰላችሁኝ በፍጹም የምትናገሩትን የምትጽፉትንም አታቁም አረ ተው ለመናፍቃን ነው የምትጽፉት ይባል ግን አንባቢያችሁን መናቅ እኮ ነው አሁን እናንተ በቤተክርስቲያን ስርዓት አናምንም እያላችሁ እንደገና ይከበር ትላላችሁ ሰውየው በርግጥ በመሞታችሁ ተጐጂ ናችሁ ግን ጌታ ልብ ይስጣችሁ የሰሩት ኃጢያት ብዙ ቢሆንም የአቡኑንም ነፍስ ይማር ግን የህን ብሎግ የምታዘጋጅ ምስኪን እራስህን ለስነልቦና ሀኪም አሳይ በእውነት ዝም ብለህ ትዘላብዳለህና በርግጥ እናንተ ጋር መዳን የለም ቢያድልህ ወደኛው ሆነክ በጸበሉ በእምነቱ መዳን ነበር ምስኪን፡፡

  ReplyDelete