Wednesday, August 7, 2013

የወ/ሮ ዘውዴ የዋዜማ ድግስ መርሀግብር ሲገመገም


ባለፈው ማቋ ዘውዴ አንዳንድ የማቅ ምርኮኛ የሆኑ የቅድስት ሥላሴ ተማሪዎችን ግብዣ ጠርታ እንደነበር ዘግበን ነበር፡፡ እንደተባለውም ማቋ ዘውዴ እሁድ ሀምሌ 21/2005 ኣ.ም ሰሜን ገበያ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ያዘጋጀችው ግብዣ ጥሪው ከቀኑ 6 ሰዓት የነበረ ሲሆን ለዘውዴ ደቀመዛሙርቱን የመማረክ ተልእኮ የሰጣት የማቅ አባላት በሰዓቱ ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ ከምርኮኞቹ ደቀመዛሙርት አንዳንዶቹም በተለይም አራት መነኮሳትና ጥቂቶቹ ደቀመዛሙርትም ቀደም ብሎ የተሰጣቸውን ቲሸርት ለብሰው ነበር ወደ ስፍራው የደረሱት፡፡ ሌሎቹ ግን በጣም ዘግይተው ነበር የመጡት፡፡ በእነርሱ መዘግየት ምክንያት በ6 ሰዓት የመጡት የማቅ አባላት ማቋ ዘውዴ ካዘጋጀችው ቡፌ በልተው መሄዳቸው ታውቋል፡፡

በእለቱ ሰባኪ ሆነው የተሰየሙት ከተማሪዎች አንዱ አባ ክንፈ “እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” በሚል ርእስ በስብከት ስም ከምንም ጋር ያልተገናኘና ማቆች ዘወትር መስበክና መስማት የሚፈልጉትን ዲስኩር ነበር ያሰሙት፡፡ በዲስኩራቸው “ኢየሱስ ኢየሱስ አትበሉ እርሱ የሚገኘው እናቱ ባለችበት እንጂ እርሷ በሌለችበት አይገኝም” ሲሉ ጆሯቸው የጠገበውንና እንደሞኝ ዘፈን በማቅ መንደር ዘወትር የሚቀነቀነውን ፀረ ኢየሱስ ዲስኩር አሰምተዋል፡፡ በወንጌል እንደተገለጸው ማርያም ኢየሱስ ባለበት የተገኘችው በቃና ዘገሊላው ሰርግ ላይ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ ያን አንድ ጊዜ ብቻ የተከናወነውን ድርጊት ለኢየሱስ መገኘት ሁሌ እንደ መስፈርት አድርጎ ማስቀመጥ ከየት የመጣ ፈሊጥ ይሆን? መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሁለት ወይም ሶስት በስሜ ባላችሁበት በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” አለ እንጂ እናቴ ባለችበት ብቻ ነው የምገኘው አላለም፡፡ ደግሞስ እናቱ በመካከላችን እንዴት ልትገኝ ትችላለች? እርሷ በቦታ የተወሰነች ፍጡር ደግሞም በአጸደ ነፍስ የምትገኝ እንጂ እንጂ እንደ አምላክ በስፍራ ሁሉ የምትገኝ ፈጣሪ አይደለችም እኮ፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ እንደአባ ክንፈ ካሉ “ጨዋ” መነኮሳት አንደበት የሚሰማ የድፍረት ንግግር ነው፡፡

አባ ክንፈ መች በዚህ ያበቁና ለመብላትና በበሉበት ለመጮህ የመጡ እንደመሆናቸው ወንጌል እሰብካለሁ ብለው እንዳልተነሱ ዘውዴን ወደማሞገስ ነበር የዞሩት፡፡ አባ ክንፈ “በሱነም ለኤልያስ ያቺን ሴት እንዳስቀመጠለት እኛን ለማዳን አንቺንም በአዲሱ ገበያ አስቀመጠልን” ሲሉ ራሳቸውን እንደ ኤልያስ ማቋን ዘውዴን ደግሞ በሱነማይቱ ሴት መስለው አቅርበዋል፡፡ ዘውዴ በግርግሩ ሰሞን ለተማሪዎቹ የዋለችውን “ውለታም” ከመጠን በላይ አጋነነው አቅርበዋል፡፡ እርሷንም የተማሪዎች አዳኝ ሲሉ ሲጠሯት ቅንጣት ያህል አልቆረቆራቸውም፡፡   

ከስብከት ቀጥሎ ለዘውዴ ሥላሴ ቅኔ የተበረከተላት ሲሆን ቅኔው የሚከተለው ነው

ዝክረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ

እስመ ገብረት ለነ ወለተ ኢየሱስ ገሊላ

ዘውእቱ እግዚአብሔር እምኩሎን አልአላ

እምነ መንሱት ዘበማእከላ

ወኢንክል በምንት ናስተማስላ

እስመ ዛቲ ዘኃይለ ሥላሴ አልዓላ

ሲተረጎም፦

ከብዙ ሴቶች ይልቅ እግዚአብሄር በገሊላ (በአዲሱ ገበያ)

ከፍ ከፍ ያደረጋት ወለተ ኢየሱስ (ዘውዴ)

የአብ የወልድ ጰራቅሊጦስ የተባለ የመንፈስ ቅዱስን ዝክር አድርጋልናለችና

ኃይለ ሥላሴ (ባለቤቷ) በመካከሏ ካለው ችግር ሁሉ ከለላ ይሁናት

እርሷን (ዘውዴን) በምንም ልንመስላት አንችልም፡፡

እርሷ የኃይለ ሥላሴ (የባለቤቷ) ማር ወለላ ናትና፡፡ እንደማለት ነው

 

በዕለቱ አስመሳይና “ውሃ ጠባሽ” ሆነው የቆዩት አባ ክንፈ “እኔ ለወ/ሮ ዘውዴ በተማሪዎች ፊት የሚገባትን ሰጠኋት እንጂ ምንም ስለሆነች አይደለም” ማለታቸው የተሰማ ሲሆን፣ ይህን ያሉት በበሉበት መጮሃቸውና ለዘውዴ ከሚገባት በላይ ውዳሴ ከንቱን ማዝነባቸው ህሊናቸውን ጭምር ስለከነከናቸው እንደሆነ ያስታውቅባቸው ነበር፡፡

እንግዶቿን ቲሸርት አልብሳ እርሷ ግን የአበሻ ልብስ ለብሳ የተቀበለቻቸው ዘውዴ በእለቱ በፊቷ ላይ ደስታ አይታይባትም ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በምስጢር ተይዞ የነበረው የዋዜማ ድግሷ አባ ሰላማ ብሎግ ላይ ቀድሞ ሰለወጣ ነው ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ አባ ሳሙኤል የተባሉ ሌላ መነኩሴም ዋና መስለው ለመታየት ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ዝግጅቱ በቪዲዮ የተቀረጸ ሲሆን ለማቅ ሪፖርት ሆኖ እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡ ወ/ሮ ዘውዴም ተርጉሜያለሁ ያለችውንና አልሸጥ ያላትን መጽሐፍ “ቅዱስ ፖሊካርፐስ”ን ለተመራቂዎች በሙሉና በችግሩ ጊዜ ለተማሪዎቹ ምግብ በማብሰልና በማቅረብ ለተሳተፉ፣ በዚህ ዓመት ለማይመረቁ ደቀመዛሙርት ሁሉ ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡    

 

   

 

27 comments:

 1. Aye mkna meselochu maferiyawoch.kikikikiki......

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዮሐንስ ራእይ
   2፥9
   መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
   3፥11
   እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
   13፥1
   አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
   13፥5
   ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

   Delete
 2. ወሬኛ መናፍቅ።

  ReplyDelete

 3. ይቺ የማቅ ባልቴት ብላ ብላ ደግሞ ለራስዎ ቅኔ ማስዘረፍ ጀመረች ለነገሩ የማቅ ሐይማኖት ራሱ ሰውኛ አይደል እስዋንም ጥቅት ቆይተው ቅድስት ያስብልዋት ይሆናል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ታይቷችሁ ይሆናል ይገርማችኋል እንኳን እርሷን እመቤታችንን እየሰደባችሁ ስለሆነ አይደንቅም፡፡ ልጅቱ ራስዋን ልትደብቅ ብትል በእናንተ ላይ ያደረው ሰይጣን ማንነቷን ለማጋለጥ የሚሞክረው መፍጨርጨር ነው፡፡ ለማንኛውም ከአጋንንትና ከማደሪያዎቹ የሚገኘው ስድብ ነውና ትንቢትም ተነግሮላችኋል ስለዚህ ማን እንደሆናችሁ ከፍሬአችሁ ይታወቃል፡፡ ግን በእመቤታችን ላይ የምትከፍቱት የስድብ አፍ ግን መሞት አይቀር አሁን ሁሉንም ነገር የሚያሠራችሁ አብሯችሁ ያለው አጋንንት ያን ጊዜ አብራችሁ ገሃነመ እሳት ስትወረወሩ ወዮ ወዮ ወዮ ንስሐ ተው ግቡ፡፡


   የዮሐንስ ራእይ
   2፥9
   መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
   3፥11
   እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
   13፥1
   አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
   13፥5
   ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።
   17፥3
   በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።

   Delete

  2. ወደ ሮሜ ሰዎች 16
   1
   በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ፤

   2
   ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።

   Delete

  3. ወደ ሮሜ ሰዎች 16
   1
   በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ፤

   2
   ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።

   Delete
  4. 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5

   9
   ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፥ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤
   10
   ልጆችን በማሳደግ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።

   Delete
  5. ማህበረ ቅዱሳን እስከ መቼ እንደ ቀበሮዋ የበግ ለምድ ለብሰህ ትኖራለህ፡፡ አንተ ከተቋቋምክ ጀምሮ ከ7000000(ሰባት ሚሊዮን) ኦርቶዶክስ አማኞች በአንተ ክስና ተንኮል በመናፍቃን እንደተበሉ አልሰማህም፡፡ አሁን ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ ስታይ አይንህ ለምን ደም ይለብሳል፡፡ በአንድ ሐጥእ መመለስ በሰማይ መላእክት ዘንድ ደስታ ከሆነ በወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ከተናደድክ ግብርህ እንደ ስምህ ከቅዱሳን ጋር ሳይሆን የሰዉን ልጅ መጥፋት ከሚመኘዉ ከዲያብሎስ ጋር ነዉ፡፡ ስለዚህ ያ የአንተ ክፉ ዘመን አብቅቶአል፡፡ ፤ቤተክርስቲያናችን ብሩህ ዘመን በእዉነተኛዉ እረኛ በክርስቶስ የተበሰረላትን እየጠበቀች በመሆኑ አንተ ከዚህ በሁዋላ በቤ/ክ ስፍራ የለህም፡፡ ስፍራህ አሁን እየኖርከዉ እየተለማመድከዉ ባለዉ ድቅድቅ ጨለማ ነዉ፡፡ ግን ግዜ አለህ ንስሀ ለመግባት ምክንያቱም የክርስትና ማእከሉ ሰዉ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር የሚያድነዉ ሰዉን ነዉ እናንተ የጠላችሁት ደግሞ ሰዉን፡፡ ስለዚህ #የጠቢብ አይኑ በራሱ ነዉ$ ስለሚል ጠቢቡ ሰለሞን ወደራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን እዩ ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ አሜን!!!

   Delete
 4. አስገራሚ ነው፡፡ ወይዘሮ ዘውዴ የማቅን መንጋ ከምታደልብ፣ ነዳያንን ብታበላ ምናለበት? ከፍ ካለም ወላጅ ያጡ ሕፃናትን ብትረዳበት፤ ብታስተምርበትስ? የፅድቅ መንገድ ማቆችን ቲ ሸርት ማልበስ ሆነ? አይ አለማወቅ ! ! !

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዮሐንስ ራእይ
   2፥9
   መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
   3፥11
   እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
   13፥1
   አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
   13፥5
   ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

   Delete
 5. Aye enanete melkam yadereg Hulu Maheber Kidusan New blachehu Erasachehune Eyageletachehu mehonachehune tawkalachehu. ENANET YEMARIAM YEMAHBER KIDUSAN BICHA SIYHONE YEMARMAM TELATOCH CHIMER MEHONACHEHU BEMETADERGUST,BEMETSIFUT HULU ERASACHEHUN YEMETANKU YETELEYACHEHU YEWESHET AGNENTOCH NACHEHUNA NESEHA GEBU. MENEM TEKETAY ATAGEGNUME TESFA KURETU.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ጅሎ መልካም የሰራ ማኅበረ ቅዱሳን ነው ማን አለ? የት አነበብክ? ማቅማ መልካም እንደማይሰራ የታወቀ ነው፡፡ ባልቴትዋ እኮ እራስዋን ለማክበር ደከመች እንጂ ለመልካም ስራ አልደከመችም ይህም ባስዘረፈችው ቅኔ ይታወቃል፡፡ መልካም የምንሰራ ሰዎች ነን ብለህ በማመን ለራስህ የጅል መጽናናት አትስጥ!!!!

   Delete
  2. የዮሐንስ ራእይ
   2፥9
   መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
   3፥11
   እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
   13፥1
   አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
   13፥5
   ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

   Delete
 6. እፎ ወድቀ እምሰማይ ኮከበ ጽባሕ ዘይሠርቅ ሶበ ይገውህ
  ሲገሰግስ አድሮ ማለዳ ወራሪ የሚሰድ ( የክህደትን አደጋ የሚጥል ዘላለም እንዴት ወደቀ ( ጠፋ)
  ወአንተሰ ትቤ በልብከ አዓርግ ውስተ ሰማይ
  አንተ መናፍቁ በልብህ ( ክህደት በተሞላዉ የልቦና ትህቢትህ ሁሉም ክእጀ በታች ናቸው ብልህ ነበር
  ይህዜሰኬ ትፀድፍ ውስተ ሲኦል ወትወርድ ውስተ ማዕምቅቲሃ ለምድር
  አንተ ሆይ ዛሬ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ሞት መቃብር ትወርዳልህ
  ነገሩ እንዲህ ነዉ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጡ ሲያድርበት ሁሌ የሚያስብዉ ቀና ነገር ነው በተልይም ደግሞ እግዚአብሔር ካሳ ለከፈለለት ሰው ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡ በሰው ልጆች ማግኘትና መደሰት የሚከፋው እንደተፈጠረ የሳተው ዲያበሎስ ነው፡፡
  ዲያብሎስ ማለትም ነድ፤ ፈታዊ ማለት ነው፡ ምክኒያቱም ነድ እሳት (ትኩሳት) እየሆነ የሰው ልጆችን በሙሉ በመከራ የኑሮ እሳት ውስጥ እስከ ዕለተ ዓርብ ድረስ ሲያስጨንቅና ሲገዛ የነበር ጠላት በመስቀል አንዴ ወደቀ ክብር ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን እና ዛሬ ግን ጠላታችን ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆነ መቸም ቢሆን ጥርስ በሌለዉ ድድ ይበላል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡
  መናፍቁ ዘላለም ዲያቆን ብየ እንዳልጠራህ ምንም የለህም ምክንያቱም ዲያቆን ብትሆን ኖሮ የረከሰ ነገር ከአንደበትህ ባልወጣም ነበር አንተ በክ የጥፋት ልጅ ዲያብሎስ በዕለተ ዓርብ ጥርሱ ሁሉ ወልቆ ድዱ እንደ ቀረ አንተም ዛሬ ትልቁ መንጋጋህ አባ ጤሞቴዎስ እና ትንንሽ ጥርሶችህ አጋፋሪዎችህ እንዲሁም የጥፋት ብሮችህ ወልቀው ሲያልቁብህ ድድህ ብቻውን አጥንት የሚቆረጥም መስሎህ ከሆነ ድል የተነሳው ሰይጣን አያታልልህ፡፡
  አንተ ከዚህ በኋላ ወደ ልብህ ተመለስ እስከ ዛሬ ዲያብሎስ ሲያሽከረክርህ ቆይቶ ነበር አሁን ግን እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ሊስጥህ ሲፈልግ እልከኛ አትሁን ይህ አሁን የተመለከትከው የቅጣቱ መጀመሪያ ነው፡፡ መቸም የፈርዖንን ታሪክ ባታውቀዉም አንብበኸው ይሆናል አሁንም የጥፋትህ ኤርትራ ባህር እንዳስጥምህ ቶሎ ብልህ ንስሐ ግባ እውነት እልሃለሁ የመምጫው ሰዓት አይታወቅምና ትግተህ ጸልይ ምን አልባት የወለቁት ጥርሶችህ ይተኩልህ እነደሆን ማን ያውቃል፡፡
  ለዘመናት ለኮሌጁ እንደ ዲያብሎስ ትኩሳት ሆነኸው ነበር አሁን ግን ጊዜው አልቆብሃል አተሸወድ
  ለዛሬዉ ሃይ ልብልህ ብየ ነው ወደፊት ግን በደንብ እንተዋወቅና የወለቁ ጥርሶችህ እንደገና ከማህፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደህ የልጅነት ጥርሶችህን በወንጌል እንዲገጠሙ እናደርጋልን፡፡
  አይ ኑሮ ዘልዛላው
  ቴልጌልቴልፌልሶር ነኝ

  ReplyDelete
 7. Abet Geta Eyesus Be semeh yemideregewun erkuset hulu yematetagesebet qen saymeta mehret adergelachewu

  ReplyDelete
 8. <>ale liqu aba hryaqose.<> balfew zemen yenberew zare degmo yemisemaw endet yeteqarene new.getachn besbketu yemechereshaw zemen endemikefana awrew wedemadryaw afun eskikeft dres mekera yhonal ale bewnet asferi zemen new kemebetachn/kemaderyaw/ lay yetekefetw afh/mouth/ legna mezegaja yemihon tru melkt alewna nseha engebalen.

  ReplyDelete
 9. were selechen hametachihu nefsachinin aschenekat ebakacchihu ewunetegnoch kehonachihu wongel sibeku.............................ebakachihu telemenu

  ReplyDelete
 10. ይበል ብለናል ለማንኝውም ማቅን ላላ አድርጋችሁ ወንጌሉን ተበቅ እድርጉልን: ያ ማለት ግን ነፍሰ ገዳዩን ማህበር በጋራ አንዋጋ ለማለት አለመሆኑን ተረዱኝ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. 13፥1
   አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
   13፥5
   ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

   Delete


  2. የዮሐንስ ራእይ

   13፥1
   አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
   13፥5
   ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

   Delete

  3. 1፥18-19
   ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤

   Delete
  4. አላተዋልክም እንዴ ወንድሜ ዮሃንስ ላይ ያለው እኮ አሁን ቤተክርስቲያንንና ክርስቲያኖችን የሚያተራምሰው እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው አስመሳዩ ሳጥናኤል እኮ ነው። አይነ ልቦናችንን ይክፈትልንና በተንኮሉ ካወረን ማህበር እንጠንቀቅ።

   Delete
 11. ማህበረ ቅዱሳን እስከ መቼ እንደ ቀበሮዋ የበግ ለምድ ለብሰህ ትኖራለህ፡፡ አንተ ከተቋቋምክ ጀምሮ ከ7000000(ሰባት ሚሊዮን) ኦርቶዶክስ አማኞች በአንተ ክስና ተንኮል በመናፍቃን እንደተበሉ አልሰማህም፡፡ አሁን ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ ስታይ አይንህ ለምን ደም ይለብሳል፡፡ በአንድ ሐጥእ መመለስ በሰማይ መላእክት ዘንድ ደስታ ከሆነ በወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ከተናደድክ ግብርህ እንደ ስምህ ከቅዱሳን ጋር ሳይሆን የሰዉን ልጅ መጥፋት ከሚመኘዉ ከዲያብሎስ ጋር ነዉ፡፡ ስለዚህ ያ የአንተ ክፉ ዘመን አብቅቶአል፡፡ ፤ቤተክርስቲያናችን ብሩህ ዘመን በእዉነተኛዉ እረኛ በክርስቶስ የተበሰረላትን እየጠበቀች በመሆኑ አንተ ከዚህ በሁዋላ በቤ/ክ ስፍራ የለህም፡፡ ስፍራህ አሁን እየኖርከዉ እየተለማመድከዉ ባለዉ ድቅድቅ ጨለማ ነዉ፡፡ ግን ግዜ አለህ ንስሀ ለመግባት ምክንያቱም የክርስትና ማእከሉ ሰዉ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር የሚያድነዉ ሰዉን ነዉ እናንተ የጠላችሁት ደግሞ ሰዉን፡፡ ስለዚህ #የጠቢብ አይኑ በራሱ ነዉ$ ስለሚል ጠቢቡ ሰለሞን ወደራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን እዩ ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ አሜን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Stupid! Don't you know that MK is the backbone of EOTC? And it is after the establishment of Mk that millions of people are back from other religions and are being baptisized.

   Delete
 12. which is new?Didn't you understand that MK is leading the Church since its regles(Metedaderia Denb) have been passed by the Holy Sinod?It has already started its work,leading the Church.Where were you?aren't you looking the leadership of MK in the Church?you can't collapse this leadreship which has been given by Almighty God,not by human being.Egziabher yatamerewun 'sew' aylew yetebalew lezih new.MK sew liaqomew ayichelem.

  ReplyDelete
 13. ምን አይነቶች ናችሁ እናተ ደግሞ፡፡ ወላዲት አምላክ ባለችበት ቦታ ሁሉ እግዝአብሔር መንፈስ ቅድስ አለ በእግዝአብሔር መንፈስ ቅድስ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ ብሎ መመስከር ይቻላል፡፡ በመንፈስ ቅድስ ደግም አብ አንድዬ ልጅን እንደላከው መናገር ያቻላል፡፡ አንድ ናቸው እና፡፡ ወላዲት አምላክ ባለችበት ቦታ እግዝአብሔር መንፈስ ቅድስ አለ፡፡ በመንፈስ ቅድስ ደግሞ በእየሱስ ስም እና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅድስ ስም ማጥመቅ ልይነት የለውም፡፡ በሐዋርያት ጉባዬ እመቤታችን ነበረች፡፡

  ReplyDelete