Monday, September 16, 2013

እፎኑ መስቀል ዘደብረ ሊባኖስ ጽርሑ
ወረድኩ እምነ ሰማይ ይቤለነ ናሁ
እንዘ ነአምሮ ለሊነ ከመ ሊቀ ጸረብት አቡሁ
ትርጓሜ፦
ቤቱ ደብረ ሊባኖስ የሆነው መስቀል
አባቱ (ጠራቢው) የአናጺዎች አለቃ መሆኑን ስናውቅ
እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?

“ ‘ከሰማይ ወረደ’ ተብሎ በጳጳሳት የተጐበኘው መስቀል ለህዝብ ይታያል” ይህ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ርእሰ ዜና ነው፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ በመስከረም 4/2006 ዓ.ም. እትሙ በፊት ገጹ ካስነበባቸው ዜናዎች መካከል ዋና አድርጎ ያቀረበው “ ‘ከሰማይ ወረደ’ ተብሎ በጳጳሳት የተጎበኘው መስቀል ለህዝብ ይታያል” በሚል ርእሰ ዜና የቀረበው ዜና አንዱ ነው፡፡   

መስቀሉ “ከሰማይ ወረደ” የተባለው ከ5 ዓመታት በፊት አቃቂ ውስጥ በተተከለው የገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲሆን ነገሩ ሆነ የተባለውም ነሐሴ 23/2005 ዓ.ም. ለ24 አጥቢያ ሌሊት ላይ ነው፡፡ ወረደ ለተባለው መስቀል የዓይን እማኝ ነኝ ያሉት ደግሞ መጋቤ ሐዲስ ፍስሐ የተባሉ ሰው መሆናቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ መጋቤ ሐዲሱ መስቀሉ በኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት ተጠቅልሎ ከሰማይ በዝግታ እየተገለባበጠ ሲወርድና መሬት ላይ ሲያርፍ በአይኔ በብረቱ አይቻለሁ ማለታቸውን የዘገበው ጋዜጣ፣ ጊዜው ከሌሊቱ በ9 ሰዓት ገደማ መሆኑን መናገራቸውን ጠቅሷል፡፡ የመስቀሉን መውረድ ለማየት የቻሉትም ሌሊት በቤተክርስቲያን ውስጥ ከነበረው ማሕሌት ላይ ነፋስ ለመቀበል በወጡ ጊዜ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ በወቅቱ ቤተልሔሙ የተቃጠለ መስሏቸው ሲጮኹ ሰምተው ከመጡ አገልጋዮች መካከል አንዱ ወጣት አገልጋይ አያለሁ ብሎ ሲቀርብ “አንዳች ነገር አስፈንጥሮ መሬት ላይ እንደጣለውና ምላሱ ተጎልጉሎ እንደወጣ፣ ለአራት ቀናትም ራሱን ስቶ ከቆየ በኋላ መስቀሉ ከወደቀበት መሬት ላይ ተነሥቶ ወደቤተክርስቲያን በአጀብ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ መንቃቱንና አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ወጣቱም ተጠይቆ መስቀሉን ሊያነሳው ሲል “አንዳች ህጻን ልጅ የመሰለ ነገር” ጎትቶ መሬት ላይ እንደጣለውና ከዚያ በኋላ ራሱን እንደ ሳተ ተናግሯል ብለዋል መጋቤ ሀዲስ ፍስሀ፡፡

“ከሰማይ ወረደ” የተባለውን መስቀል የአካባቢው ነዋሪዎች ሲወርድ እንዳላዩና ወደቤተክርስቲያን ሲገባ ወርቃማ ብርሃን እንደነበረው ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ ነሐሴ 27/2005 በበርካታ ጳጳሳትና ምእመናን አጀብ ወደቤተክርስቲያን እንደገባና መስከረም 19/2006 ዓ.ም. ለሕዝብ እይታ ለማቅረብ ቀጠሮ መያዙን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡

በመስከረም ወር ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የመስቀል በዓል መሆኑ ይታወቃል፡፡ “ከሰማይ ወረደ” የተባለው መስቀል ለእይታ የሚበቃው ደግሞ ከበዓሉ መከበር ሁለት ቀናት በኋላ ነው፡፡ “መስቀሉ ወረደ” የተባለበት ሌሊት ደግሞ ነሐሴ 23 ለ24 አጥቢያ ነውና፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም በደብረ ሊባኖስ ገዳም “መስቀል ወርዶላቸዋል” የተባሉት የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው በዓል ነው፡፡ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ትተን እነዚህን ግጥምጥሞሾች ስናስብ የ “መስቀል ከሰማይ ወረደ” አዲስ ትእይንት አለመሆኑንና ከዚህ ቀደም የተተወነ፣ በፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ ላይ ሳይቀር አባ ተክለ ሃይማኖት የተባሉት ገጸ ባህርይ ሲያጭበረብሩበት የነበረና በእውነተኛ ፍቅር የታመመችውን ሰብለ ወንጌልንም በተመሳሳይ መንገድ ጋኔን ተቆራኝቷት ነው በሚል ሲነግዱበትና ሲያተርፉበት የነበረ የገሃዱ ዓለም እውነተኛ ገጽታ መሆኑን እንረዳለን፡፡

ሊቃውንቶቻችን ይህችን የቤታችንን የተለመደች የማጭበርበሪያ ስልት የትመጣዋን ስለሚያወቁና ለአንዳንድ ዕውቅና ላላገኙ አድባራትና ገዳማት ዝና መሸመቻና ከፍተኛ ገቢ ማጋበሻ በር አድርገው አድርገው እንደሚጠቀሙባት ቀድመው ስለተረዱ በተለይ ደብረ ሊባኖስ ላይ ለአባ ተክሌ “ከሰማይ መስቀል ወረደላቸው” የተሰኘውን ልቦለድ ከላይ በርእሱ ላይ በተጠቀሰው ቅኔ ውሸት ነው ብለው ተችተውት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለግል ጥቅማቸው የቆሙና በተአምር ስም ለመነገድ ታጥቀው የተነሱ የቤታችን አጭበርባሪዎች ከመርካቶ የገዙትን “made in china” የሆነውን መስቀል ከሰማይ ወረደ ለማለት ምንም አላቅማሙም፡፡ ነገር ግን ዛሬም ያን ጠንካራ ምስጢር ያዘለ የአባቶችን ቅኔ እንጠቅስባቸዋለን፡፡ 
እፎኑ መስቀል ዘደብረ ሊባኖስ ጽርሑ
ወረድኩ እምነ ሰማይ ይቤለነ ናሁ
እንዘ ነአምሮ ለሊለ ከመ ሊቀ ጸረብት አቡሁ
ትርጓሜ፦
ቤቱ ደብረ ሊባኖስ የሆነው መስቀል
አባቱ (ጠራቢው) የአናጺዎች አለቃ መሆኑን ስናውቅ
እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?

ይህን የሰሞኑ የፌስቡኩን የወሬ ገበያ ያደራውንና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ምንም ሳያቅማማ ዋና ዜናው አድርጎ የዘግበውን ከ“ሰማይ የወረደ መስቀል” ድራማ ከነግጥምጥሞሹ ስናስበው ከዚህ ቀደም ደብረ ሊባኖስ ላይ ተደርሶ ለሕዝብ የተሠራጨውን፣ በሊቃውንቱ ቅኔ የተራከሰውን ነገር ግን ብዙዎች እውነት መስሏቸው ያመኑትን የፈጠራ ወሬ ነው ያስታወሰን፡፡

እውን እግዚአብሔር እንዲህ ያደርጋል? ይህን ጥያቄ ለማቅረብ ድፍረት የሰጠን የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ አላማና አሠራር የገለጸው እውነት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም የሚለው እውነተኛ ቃል አለቦታው እየተጠቀሰ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ለማይችሉ ሰዎች መሸሻ እንደሚሆናቸው ብንገነዘብም፣ ይህን ድራማ በዚህ ጥቅስ ለመሸፈን መሞከር የሚቻል አይመስለንም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ይህን ሊያደርግ የሚችልበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ እግዚአብሔር “በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።” (ኤፌ. 1፥9-10)፡፡ ታዲያ ለምን ብሎ ከሰማይ ቤት መስቀል ይልካል? ደግሞስ በሰማይ ቤት የመስቀል ፋብሪካ አለወይ? ወዘተርፈ የሚሉ ጥያቄዎች ለቀልድ ሳይሆን ከምር ይቀርባሉ፡፡

ከሰማይ እንዲህ ያለ ነገር ወረደ ተብሎ ሲነገር የምናውቀው በአምልኮተ ባዕድ መንደር እንጂ በቤተ ክርስቲያን አልነበረም፡፡ ስለ አርጤምስ በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈው አርጤምስ የተባለችው እንስት “አምላክ” ጣዖትዋ ከሰማይ ወረደ ተብሎ ይታመን እንደ ነበረና ይህን ወሬ ያስፋፋውም ብር ሰሪ የነበረውና ለአርጤምስ ቤተ መቅደስ ምስሎች በብር እየሠራ ለአንጥረኞች እጅግ ትርፍ ያገኝ የነበረው ድሜጥሮስ ነው (የሐዋ. 19፥24-35)፡፡  ዛሬም በእርሱ መንገድ የዐመፅ ትርፍ ለማጋበስ የሚከጅሉ ድሜጥሮሶች “መስቀል ከሰማይ ወረደ” “ታቦቷ ህንጻ ካልተገነባልኝ ንቅንቅ አልልም አላች” ወዘተ… ቢሉ ሊደንቀን አይገባም፡፡ ያው እነድሜጥሮስ የወጠኑት አቋራጭ መክበሪያ ዘዴያቸው ነው፡፡ ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ግን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ ለማይረባ አእምሮ ተላለፎ የተሰጠ ሰው ካልሆነ በቀር ይህን እውነት ብሎ የሚቀበል ክርስቲያን ይኖራል ብለን አናስብም፡፡

ለእኛ የመስቀል ቅርጽ የተሰቀውን ክርስቶስን የሚያሳስበን አርማ እንጂ በራሱ ምንም አይደለም፡፡ መስቀል የምንለውም የክርስቶስን መከራና ሞት እንጂ እኛ የሰራነውንና የክርስቶስ መስቀል የሚል ስያሜ የሠጠነውን የተመሳቀለ እንጨት ሁሉ አይደለም፡፡ እርሱማ የእኛ እጅ ስራ ነው፡፡ ክርስቶሰ የተሰቀለበት እንጨትም ቢሆን ከዚህ ያለፈ አገልግሎት የለውም፡፡ ዋናው የተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ እርሱ የተሰቀለበት መስቀል አይደለምና፡፡ ክርስቶስን ትቶ የተሰቀለበትን ማምለክ ትልቅ አላዋቂነት ነው፡፡ ስለዚህ በመስቀል ወረደ ስም ምእመናንን ለማወናበድ የሚሞክሩትን ሁሉ ተዉ! ይህ ነገር ከእግዚአብሔር አይደለም እንላቸዋለን፡፡

ከሁሉ የሚገርመው ይህን አሳፋሪና አንገት አስደፊ የአጭበርባሪዎች የፈጠራ ወሬ አዲስ አድማስ እንደዜና መዘገቡ ነው፡፡ ጋዜጣው ዓለማዊ እንደመሆኑ መጠን ይህን ሃይማኖት ለበስ  የአፈጮሌዎች የፈጠራ ወሬ መዘገቡ ብዙዎችን ያነጋገረ ሲሆን፣ ራሱንም ትልቅ ትዝብት ላይ ጥሏል፡፡ ጋዜጣው ከማቅ ተጽእኖ ነጻ ያልሆነ ጋዜጣ መሆኑን በዚህና ከዚህ ቀደም በሚያወጣቸው ቤተክህነት ነክ ዜናዎች ሁሉ በግልጽ አስመስክሯል፡፡ ጋዜጣው ምንም እንኳን ወሬው የብዙዎችን ትኩረት ይስባል በሚል እሳቤ ዜና አድርጎ ያወጣው ቢሆንም፣ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ አየን ካሉት ብቻ ሳይሆን ከሚመለከታቸውና ከሌሎችም የሃይማኖት ሰዎች መጠየቅ ነበረበት የሚል እምነት አለን፡፡ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ግን የሃይማኖት ምንጮቹ የማቅ አባላት ናቸውና መጋቤ ሀዲስን ጠቅሶ እንደ ጻፈው የእነርሱ መገኘት ለመስቀሉ ከሰማይ መውረድ ማረጋገጫ ይመስል የማህበረ ቅዱሳን አባላት በስፍራው ተገኝተው መመልከታቸውን ነው የነገረን፡፡ አዲስ አድማሶች ትዝብት ላይ እንዳትወድቁ እባካችሁ ወሬ ምረጡ፣ ሚዛናዊነቱን ለመጠበቅ ተገቢ ሰዎችን አነጋግሩ፤ ከማቅ የቀረበላችሁን ሁሉ እንደወረደ ብቻ ከዘገባችሁት ያው ሌላው የማቅ ልሳን መሆናችሁ ነው፡፡

41 comments:

 1. ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ይህን ሊያደርግ የሚችልበት ምንም ምክንያት የለውም፡ ታዲያ ለምን ብሎ ከሰማይ ቤት መስቀል ይልካል? ደግሞስ በሰማይ ቤት የመስቀል ፋብሪካ አለወይ? ወዘተርፈ የሚሉ ጥያቄዎች ለቀልድ ሳይሆን ከምር ይቀርባሉ፡፡ le eliyas kesemay masero werdoletal endenanite ababal semay bet shekila sira ale ende?lelaw min yahil erigitegna neh egizabeher yihin ayadergim yemitilew?egizabeher yimiserawin anite new yemitiwesinilet? lelaw be hawaritat sira lay ye kidus paulosin libis eyekedadedu yiwesidu neber adagu geta eyale lemin cherik felegu? asitewil

  ReplyDelete
 2. በቦታው የሆነውን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ይኸ ሁሉ ቲያትር ‹‹ባሕታዊ›› ነኝ ባዩ ገንዘብ ለማግበስበስ ከካህናቱ ጋር የፈጠረው ሤራ መሆኑን ራሱም ሆነ አብረው የተሰለፉትም ያውቁታል፡፡ ለመሆኑ ብርሃኑ የታየው ፎቶ ላነሳውና አብሬ አይቸዋለሁ ለሚለው ሰው፣ ብርሃኑ ከሄደ በኋላ መስቀሉ አልነሳ አለ የሚለው ቲያትር እንዴት እንደተጠናቀቀ፣ ‹‹ባሕታዊ›› ነኝ ባዩ እንዴት እንዳቀናበረው እዚያ ያላችሁ ካህናት አታውቁትም? ካህናቱ አልነሳልን አለ ያላችሁትን መስቀል ያነሳውና የያዘው ዲያቆኑ አልነበር???… ማፈሪያዎች ናችሁ፡፡ በፎቶ የምታሳዩት ወርቅማ ቅብ ያለው ዘመናዊ መስቀል ነው… ተነሳ ተብሎ የታየው ደግሞ የእንጨት መስቀል ነው… ታዲያ ማምታታቱ ለምን ይሆን? ይህን ያልተረዳ ሕዝብ ገፈፋችሁት…. ዘራፊዎች፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለማያምን ሁሉም ከባድ እና ጭንቅ ነዉ! በልዎ ለእግዚኣብሔር ግሩም ግብርከ!

   Delete
 3. MESKEL WERD KE-MALET MELA'EK WERD BILUN ENAMIN NEBER. AHUNES WESHET BEZA . BESEMAY MELAE'KET ENJI MESKEL YELEM. JUST COMMON SENSE. THANK YOU!

  ReplyDelete

 4. የማቴዎስ ወንጌል
  12፥39
  እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።

  ReplyDelete
 5. for protestant menafkan, there is no miracle , they don't believe in god's miracle why? because they don't know the bible they carry.their father ( the devil ) always make them to hesitate every truth. in the true churches of Ethiopia, Egypt and sirya our god, Jesus always reveals his miracle with many aspects/signs.what do we say about the appearance of virgin Mary in Egypt some years ago where millions of people around the world were rushing to visit?? it was widely disseminated/broadcasted by international media (bbc, cnn..etc) it was fact. so what do say about this, was it not the miracle of god? menafk should be ashamed of their beliefs/void religion

  ReplyDelete
 6. leboooooooooooooooo meskel sinesa mechem tikatelalachihu

  ReplyDelete
 7. yewerdelin legna tadia enanten min asdenegetachihu,kalayehu alaminim kehone hidina kaldaseskut bileh temuaget, wei tamnaleh wey degmo tasaminaleh. neger gin eza atdersim ergitegna negn gena meskelun endayeh bewustih yalewu diabilose tekatelku eyale endemichoh amnalehu. bezihim sewu hullu yemskelun hail yimeleketal

  ReplyDelete
 8. bet ayhud Ykirstos sew mehon alamenum neber

  ReplyDelete
 9. kmenafik mene yetebekal. gene tekatelalachu!!!

  ReplyDelete
 10. We don't Expect from you Faith, because you are Protestant(You protest for every thing). But we believe that Nothing is impossible for the Almighty God.

  G/Hiwot From Tigray

  ReplyDelete
 11. We know every moment who is playing this dirty game behind the name of Eotc. Arabs tried blood and death to destroy they failed with big shame. Egypt, Europ and the west tried all failed. When all Africans fall under Islam invassion Eotc as a religion and as a leader resist the invassion. So mnay challenging sucrifice eotc entertain with successful victory. No matter what Eotc will continue. Funny abaselam.org Don't you know marxisiest and leniniest fall under the grave. So what kind of change u gona bring to our change. What is about attacking saints and holy fathers? Because they are black or what? Abaselama.org u r out of touch. If you have the power of God come out public like saint and holy Paul by doing practically not hiding under an online .Sometimes some simple minded with simple idea simple sentance by simple person personal or private problem tthose who sick suffer by spritual demon try to associate our church .sorry for u I hope may God jesus christ forgive u.. Who cares We know in the last dayes this all betrial and attacking saints and even God to happen. EOTC IS FOUNDED BY GOD NOT BY HOPE OF FLESH, BLOOD AND MATERIALS. ACT 8:26....... Read it. Abaselama.org is one of the most simple blog try to get recognition by any means of personal or private matters. Is that the way we fulfiled the mission of of Gaspol of God?

  ReplyDelete
 12. ፈረንጅ መጥቶ ካልባረከው ለእናንተ ሁሉም ነገር ተረት ተረት ነውና ፈረንጅ ሀገር እስኪወርድ ጠብቃችሁ ዘግቡ እዛ ደግሞ ችግሩ ጥይት ብቻ ነው እያወረደ ያለው ምን ይደረግ <> የወረደው መስቀል ለኛ ለምናምነው ፍቅር ለእናንተ ደግሞ ሞኝነት ወይም ተረት ተረት ነው መፅሀፍ ቅዱሱም ነገ ተረት ተረት ነው ካሉዋችሁ እርሱንም ትክዳላችሁ ይቅር ይባላችሁ መቼም post አታደርጉት ካነበባችሁት ይበቃል

  ReplyDelete
 13. አይሁዶች ጌታን ...አባቱ እንጨት ጠራቢዉ ዮሴፍ አይደለም እንዴ ...እያሉ እውነተኛውን ጌታን እንዳልተቀበሉ ሁሉ የዘመናችን ተረፈ አይሁድ ጌታ ታምራቱን በተለያየ መልኩ ሲገልፅ ያማከራቸው ይመስል አፋቸውን ሞልተው እግዚአብሄር ከሰማይ መስቀል የሚያወርድበት ምክንያት የለም ሰማይ ቤት ብረት ቀጥቃጭ አለ እንዴ? በማለት ይሳለቃሉ አረ ለመሆኑ በየትኛው ብቃታችን ነው ለእግዚአብሄር በዚህ ዘመን ይህን ያደርጋል ይሄን አደርግም እያልን የስራ መመሪያ የምናወጣለት ሌላው ለአብርሀም ከሰማይ በግ ወርዶለታል ሰማይ ቤት በግ እርቢ አለ እንዴ እንደናንተ አባባል እባካችሁ በየትኛውም ጊዜ የፈለገውን ማድረግ እንደሚችልእመኑ

  ReplyDelete
 14. Ewunetun E/r yegeltseltselen Amen !

  ReplyDelete
 15. tebareke geta abzeto tsegawen yesetehe.

  ReplyDelete
 16. ኦርቴጋ እኮ እንደዚህ አይነት የቶም ኤንድ ጄሪ የካርቱን ፊልም ትወዳለች ልማዷ ነው፡፡በዳመና ላይ ማሪያም ታየች፣በጨረቃ ላይ ማሪያም ታየች፣በተራራ ላይ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ መብረቅ ለቀቁ፣ ምናምን ምናምን ምናምን . . . . . . ይልቅ ከሰማይ የወረደ ምናምን እያላችሁ የህንድ ፊልም ከምትሰሩ ጌታ የሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ለፍርድ ሳይመጣባችሁ በጊዜ ንስሃ ብትገቡ ይሻላችኋል፡፡

  ReplyDelete
 17. ይህንን ይመልቱ http://orthodoxnegn.blogspot.com/

  ReplyDelete
 18. ከሰማይ ወረደ!
  ደግሞ ምን ወረደ ብላችህ እንዳትገረሙ ሁሉኑም በትግስት ካነበባችሁ ትደርሱበታላቸሁ፡፡ በመፅሃፍ ቅዱሳችን ከሳማይ መቅሰፍት፤ እሳት ፤ መና፤ መልአክት፤ ከሁሉም በላይ ከሰማይ የወረደውና በክበር በደመና ወደሰማይ ያረገው ጌታ እየሱስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በሃገራችን በሬ ወለደ የኑፋቄ አስተምህሮተች ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ ፀረ ወንጌል እየሆነ መጥቷል፡፡ ሰዎችን ላማሳት እዚህ ጋር ከሰማይ እንትን ወረደ እያሉ ሰውን ስለሚያስቱ መናፍቃን ትንሽ ለማለት ወደድኩኝ፡፡ ነገርዬው ምን መሰላችሁ ከጥቂት ቀናት በፊት እዚሁ መዲናችን ገላን ገብረኤል በተባለ ቦታ ከሰማይ መስቀል ወረደ በማት አዳሜ ወደዚያ ተመመ፡፡ እኔም ወደ ተጠቀሰው ቦታ ሄጄ ባላይም የተካረየሁበት ቤት ልጅ ስእሉን( ፎቶውን) አሳየኝ፡፡
  እኔም አመንክ ወይ ስለው ታዲያስ አለኝ! ለመሆኑ መቼና እዴት ወረደ ማንስ አየው ሲወርድ አልኩት እሱም መልስ የለውም፡፡ እናትየውም ቀጠለች ይህ የአምላክ ስራ ነው፡፡ መድሃንያም ወረደ አለች( መስቀሉን!)፡፡ ይገረማል! ለመሆኑ ጌታ እየሱስ ወረደ ቢሏቸው አንድም ሰው ዝር የሚል የለም፡፡ ሰዎች የክርስቶስ ቀንደኛ ጠላትና ተዋጊ ሆነው ሳሉ ስለክርስቶስ መስቀል ሲከራከሩና ክብር ሲሰጡ ይገርመኛል፡፡ አያክብሩ እያኩኝ አይደለም፡፡ ግን ለመስቀሉ ጌታ ምናለ ቅድሚያ ቢሰጡ፡፡ መዳን በማንም የለም! በማንም ከራሱ ከክርስቶስ በስተቀር፡፡
  ለመሆኑ ከሰማይ መስቀል ወረደ ማለት ለምን አስፈለገ? ምናልባት ልትንታንዬ ትክክለኛ መለስ ማስቀመጥ ባልችልም ሁልት ምክንያት ማስቀመጥ እችላለሁኝ፡፡ የመጀመሪያው ታሪካዊ ዳራው ሲሆን ከጥንት ጀምሮ እዚህ ቦታ ፀበል ፈለቀ፤ እዚህ ቦታ እንትን ወረደ፤ እዚህ ቦታ እንትን ታየ እተባለ ሰውን ማሳትና በሬ ወለደ አካሄድ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በ 14ኛው ክፍለዘመን የኑፋቄና የክህደት አባት የሆነው ዘረያቆበ በዚህች ሃገር የተከለው መርዝ ዛሬም ሰውን ቀስፎ ይዟል፡፡ ዛሬም መርዙ ሰውን ይጎዳል፡፡ በዚህ ንጉስ ዘመን ከሳማይ የመስቀል ብረሃን ወረደ ተብሎነበር፡፡ አሁን ደብረ ብርሃን ያን ጊዜ ደበረ ኤባ ትባል በነበረችው ከተማ ላይ ከሰማይ የእሳት መስቀል በራ ወይም ታየ ተብሎ ከተመዋ ደብረ ብረሃን ተባለች፡፡ ይች ከተማ ዛሬም የምትታወቀው በወረደባት መስቀል ሳይሆን በሰይጣናው ተግባሯ ነው፡፡ የዘረያቆብ መንፈስና ልክፍት ያለቀቃቸው ሰዎች ዘሬም ሊያሞኙን መስቀል ወረደ ይሉናል፡፡ ሌላው ተረት ደግሞ አለ ቅዱስ ጊዮርጊስ( በሱ ገድል ላይ እንደሰፈረው) ከሰማይ ጌታ እየሱሰ የተሰቀለበትን መስቀል በፈረስ እየጎተተ ወደምድር አመጣ ይሉና፡፡ ዛሬስ ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል በማ በኩል ወረደ፡፡ ጌታ ማስተዋልይስጣቸው፡፡ ክር ለመስቀሉ ጌታ ለሆነው ለአባታችንና አምካች ጌታ እየሱስ ይሁን፡፡
  ሌላው መስቀል ከሰማይ ወረደ የተባለበት አብይ ምክንያት ደገሞ አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ብርቱ ተቀናቃኝ የሆነው ተዋህዶ የተባው አስተሳሰብ ነው፡፡ በተዋህዶዎች አመለካከት ኦርቶዶክስ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክል አለመሆኑን ደግሞ የሞያረጋግጥላቸው ቅዱ ኤልያስ ከአርያም መውረዱ ነው፡፡ ስለሆነም ለተዋህዶዋውያን ኤልያስ ከሰማይ “ከወረደ” ለኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ከሰማይ “መስቀል” ወረደ”፡፡ ከሰማይ ምንም ሊወርድ ይችልል እኛ ግን በሰማይ ላይ እዲህ እንደተባለው “ አሁን ወደሰማይ እንዲህ ሲወጣ ያያችሁት እንዲሁ ይወርዳል” የተባለውን ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ደግሞም እንዲህ ተብሏል ሰይጣን ከሰማይ እሳትን የማውረድ ስልጣን ተሰጥቶታል ሰዎችን ለማሳት፡፡
  ጌታ ሆይ እኔስ የአነተን መውረድ እንጂ ሰለሌላ መውረድ ግድ የለኝም፡፡
  ጌታ ይባርካችሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዛሬስ ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል በማ በኩል ወረደ፡፡

   በኢትዮጵያ ባንዲራ ተጠቅልሎ ነዋ! ቂቂቂቂቂ!

   Delete
 19. ከሰማይ ወረደ!
  ደግሞ ምን ወረደ ብላችህ እንዳትገረሙ ሁሉኑም በትግስት ካነበባችሁ ትደርሱበታላቸሁ፡፡ በመፅሃፍ ቅዱሳችን ከሳማይ መቅሰፍት፤ እሳት ፤ መና፤ መልአክት፤ ከሁሉም በላይ ከሰማይ የወረደውና በክበር በደመና ወደሰማይ ያረገው ጌታ እየሱስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በሃገራችን በሬ ወለደ የኑፋቄ አስተምህሮተች ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ ፀረ ወንጌል እየሆነ መጥቷል፡፡ ሰዎችን ላማሳት እዚህ ጋር ከሰማይ እንትን ወረደ እያሉ ሰውን ስለሚያስቱ መናፍቃን ትንሽ ለማለት ወደድኩኝ፡፡ ነገርዬው ምን መሰላችሁ ከጥቂት ቀናት በፊት እዚሁ መዲናችን ገላን ገብረኤል በተባለ ቦታ ከሰማይ መስቀል ወረደ በማት አዳሜ ወደዚያ ተመመ፡፡ እኔም ወደ ተጠቀሰው ቦታ ሄጄ ባላይም የተካረየሁበት ቤት ልጅ ስእሉን( ፎቶውን) አሳየኝ፡፡
  እኔም አመንክ ወይ ስለው ታዲያስ አለኝ! ለመሆኑ መቼና እዴት ወረደ ማንስ አየው ሲወርድ አልኩት እሱም መልስ የለውም፡፡ እናትየውም ቀጠለች ይህ የአምላክ ስራ ነው፡፡ መድሃንያም ወረደ አለች( መስቀሉን!)፡፡ ይገረማል! ለመሆኑ ጌታ እየሱስ ወረደ ቢሏቸው አንድም ሰው ዝር የሚል የለም፡፡ ሰዎች የክርስቶስ ቀንደኛ ጠላትና ተዋጊ ሆነው ሳሉ ስለክርስቶስ መስቀል ሲከራከሩና ክብር ሲሰጡ ይገርመኛል፡፡ አያክብሩ እያኩኝ አይደለም፡፡ ግን ለመስቀሉ ጌታ ምናለ ቅድሚያ ቢሰጡ፡፡ መዳን በማንም የለም! በማንም ከራሱ ከክርስቶስ በስተቀር፡፡
  ለመሆኑ ከሰማይ መስቀል ወረደ ማለት ለምን አስፈለገ? ምናልባት ልትንታንዬ ትክክለኛ መለስ ማስቀመጥ ባልችልም ሁልት ምክንያት ማስቀመጥ እችላለሁኝ፡፡ የመጀመሪያው ታሪካዊ ዳራው ሲሆን ከጥንት ጀምሮ እዚህ ቦታ ፀበል ፈለቀ፤ እዚህ ቦታ እንትን ወረደ፤ እዚህ ቦታ እንትን ታየ እተባለ ሰውን ማሳትና በሬ ወለደ አካሄድ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በ 14ኛው ክፍለዘመን የኑፋቄና የክህደት አባት የሆነው ዘረያቆበ በዚህች ሃገር የተከለው መርዝ ዛሬም ሰውን ቀስፎ ይዟል፡፡ ዛሬም መርዙ ሰውን ይጎዳል፡፡ በዚህ ንጉስ ዘመን ከሳማይ የመስቀል ብረሃን ወረደ ተብሎነበር፡፡ አሁን ደብረ ብርሃን ያን ጊዜ ደበረ ኤባ ትባል በነበረችው ከተማ ላይ ከሰማይ የእሳት መስቀል በራ ወይም ታየ ተብሎ ከተመዋ ደብረ ብረሃን ተባለች፡፡ ይች ከተማ ዛሬም የምትታወቀው በወረደባት መስቀል ሳይሆን በሰይጣናው ተግባሯ ነው፡፡ የዘረያቆብ መንፈስና ልክፍት ያለቀቃቸው ሰዎች ዘሬም ሊያሞኙን መስቀል ወረደ ይሉናል፡፡ ሌላው ተረት ደግሞ አለ ቅዱስ ጊዮርጊስ( በሱ ገድል ላይ እንደሰፈረው) ከሰማይ ጌታ እየሱሰ የተሰቀለበትን መስቀል በፈረስ እየጎተተ ወደምድር አመጣ ይሉና፡፡ ዛሬስ ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል በማ በኩል ወረደ፡፡ ጌታ ማስተዋልይስጣቸው፡፡ ክር ለመስቀሉ ጌታ ለሆነው ለአባታችንና አምካች ጌታ እየሱስ ይሁን፡፡
  ሌላው መስቀል ከሰማይ ወረደ የተባለበት አብይ ምክንያት ደገሞ አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ብርቱ ተቀናቃኝ የሆነው ተዋህዶ የተባው አስተሳሰብ ነው፡፡ በተዋህዶዎች አመለካከት ኦርቶዶክስ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክል አለመሆኑን ደግሞ የሞያረጋግጥላቸው ቅዱ ኤልያስ ከአርያም መውረዱ ነው፡፡ ስለሆነም ለተዋህዶዋውያን ኤልያስ ከሰማይ “ከወረደ” ለኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ከሰማይ “መስቀል” ወረደ”፡፡ ከሰማይ ምንም ሊወርድ ይችልል እኛ ግን በሰማይ ላይ እዲህ እንደተባለው “ አሁን ወደሰማይ እንዲህ ሲወጣ ያያችሁት እንዲሁ ይወርዳል” የተባለውን ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ደግሞም እንዲህ ተብሏል ሰይጣን ከሰማይ እሳትን የማውረድ ስልጣን ተሰጥቶታል ሰዎችን ለማሳት፡፡
  ጌታ ሆይ እኔስ የአነተን መውረድ እንጂ ሰለሌላ መውረድ ግድ የለኝም፡፡
  ጌታ ይባርካችሁ፡፡

  ReplyDelete
 20. woy gize...werede ketebalew belay ewinet new bilo yemiyamin menoru yasafiral.....seyitan birhan lebiso besemay bimeta man werede yibal yihon? mechem sew yemesikelun kirts enji bemesikelu yetegeletewin yekiristos fikir lemayet alemetadelu yasazinal.geta yirdachihu....seyitan gena bizuwochn lemasasat bizu neger yasayal....!kesemay keweredew geta beker lela yeminayew neger yelem!

  ReplyDelete
 21. This is factless shame designed by mk gangster. The're is no way to approve any cross manufacturers found in up stairs. Ethiopian law must be protect the citizen such kind of fabricated news on behalf of faith. If it is real we need evidence from astrologiCal science.

  ReplyDelete
 22. አጭበርባረሪ ሌቦች ማኅበረ ሰይጣናት

  ReplyDelete
 23. ይሄንን ድረ ገጽ ገብቸ አይቸው አላውቅም ነበረ ግን ዛሬ እንደ አጋጣሚ ስከፍት በጣም የድፍረት የተሞላበት የእነ በጋሻው እና የእነ ጽጌ ስጦታው ቡድን ይህችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በለመደ አፋችሁ ትሳደቡ ጀመረ፡፡ ምን ታደርጉ አወቅናችሁ በደንብ አድርገን ፡ እናነተ የተረገማችሁ ምን አይነት ንግግር ነው የምትናገሩት ሰው በቃ ዝም ብሎ ያወራል በጣም ነው የምትገርሙት ሰይጣን ልባችሁን ስለደፈነው ትንሽ እንኳን አታስተውሉም ስትጽፉ ፡፡ የእነማን ቡድን እንደሆነ ስለምናውቃችሁ ምንም አንልም ግን አንድ ነገር ማለት ይቻላል ፡ ቅ/ጳውሎስ በጻፋው መልዕክቱ ላይ እንዳታስተውሉ "ምን አዚም አደረገባችሁ"? ነው ያለው አይደል? እንደው በእግዚአብሄር ስራ ደግሞ ገብታችሁ "እግዚአብሄር ከሰማይ መስቀል የሚያወርድበት ምንም ምክንያት የለም " ብላችሁ ማውራት ጀመራችሁ፡ በሉ እናነተ መኖሪያችሁ ከዚህ ከእኛ ጋር አይደለም ወደ እነ ልበ አምላክ ዳዊት ሂዱ፡፡ እናንተ የአምላክን ልቦና ታውቁ የለ? እስኪ ሁልጊዜም እኛ የምንለው ልቦናችሁ ተመልሶ እውነትን አውቃችሁ ተረድታችሁ ወደ ቀደመችው መንገድ እንድትመለሱ እግዚአብሄር ይርዳችሁ ነው መቸስ ምን ይባላል ሌላ መቸም ይሄንን አስተያት እንደማታወጡት እያወኩ ነው የጻፍኩት ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ጽፌ ስላላወጣችሁልኝ ነው ግን የዛሬውን አውጡት.

  ReplyDelete
 24. እግዚአብሄር ይባርክህ!

  ReplyDelete
 25. በመስቀሉ ጀርባ ላይ ያለው የቻይንኛ ጽሑፍ ምናልባት ጌጥ መስሎአችሁ ከሆነ ለመስከረም 19ኙ ፉገራ ሌላ ቀይራችሁ ብታሳዩ ድራማው ሊሳካ ይችላል፡፡ ማኅበረቅዱሳን ደግሞ ‹‹ማቅ›› ወደመሰለ ዜናና ማምታታት መውረዱ በጣም ያሳዝናል፡፡

  ReplyDelete
 26. ወይ ጉድ ከ ጰንጤ ዘር ደግሞ እምነት ሊገኝ!!!! ጥርጥሩ ለማን ሊሆን? ስሙ ይመርሆ ሃበ ግብሩ ተብሎ የለ ፕሮቴስታንት ማለት ተጠራጣሪ ነዉ ይህን ስም ይዛችሁ ብታምኑ ነበር የሚገርመዉ። ደግሞ በተኣምራት ልታምኑ አረ ጨርሶ እማይታሰብ። ታድያ ከዚህ ብሎግ ምን ሊጠበቅ ኖሯል። እምታምኑባቸዉ ነጮች እምያወሩት ስለሳይንስ ቤተክርስትያናችን ምታወራዉ ስለ እምነት እንዴት ልንገናኝ እንችላለን? እናንተ በጥርጥራችሁ እኛ በእምነታችን አለን ይልቅ እዚህ ብሎግ ያለማወቅ እያጨበጨብን ያለን ወገኖች ካለን እንወቅባቸዉ እንዴ እነዚህ ዓላማቸዉ ዓለሙን በጥርጥር ሞልተዉ እግዚኣብሔር የለም እንዲልላቸዉ ነዉ ። ይህ ግሞ ለኛ ዓዲስ ነገር ኣይደለም እኛ ግን ለእግዚኣብሔር የሚሳነዉ ነገር የለም በሚለዉ የመልኣኩ ትምህርት እናምናለን ለእምነታችንም ሳይንሳዊ ማረጋገጫ ኣያስፈልገንም። (በደምብ ኣንብቡት ላይጥማችሁ ስለሚችል ፖስት አደረጋችሁት ኣላደረገችሁት ብዙም አልገረምም) ሐጎስ ነኝ ከመቐለ

  ReplyDelete
 27. We just have to stop putting down those who are skeptical. Now Bete Khenet itself have not said anything and should be blamed
  for its unspoken doubts. We are told that the physical evidence is in the church yet no other news group have come and elaborate on such high Devine deeds, except Admas. I personaly think this thing has happened, but I also accuse Bete Khnet for its lack of clarity on many things that have left people apart. The church has allowed man made fictions contaminate true miracles and the skepticism is understandable. This has to stop. We get in to this labeling games as one is Thadesso or Menafeke, one is Kebat or whatever all are attributed by Bete Khenets inability to function right.Biased Mhibere Kidusans sometimes assume the role of Bete Khnets and deservice the church by inflicting divisions among the church members. We have more youth departed our church to THE PENTA COSTAL due to the group unwise campange against so called thdesso. God wants us to inherit love from Jesus so we all have a peaceful lasting closeur to our disputs.We neget this cardinal teaching of Jesus and become a prey to Satan now a days. Though I am proud of the Ethiopian Orthodox Church as one of the oldest one, we tend sometimes to forget that Jesus has come to all races in the world. We act clanish towards other christians using The Geez and Yared standard scale. Where does the church stand as to spreading the Gospel for the world? Some 1000+ years old church could have at least convert a lot in Sudan and Kenya leave alone Africa. Missionaries easily took over when they get the opporunity. It is imperative that The church needs some change in strategy. It is insignificant wheather you use Piano or masinqo, wheather you use Gez or latin.The church needs to expand its intenational family members by teaching the Gospel in simple easy way in which people can understand.
  I congratulate Aba Selama on bring it on this web for
  all have a chance to speak .

  God bless Ethioia and ETOC!

  ReplyDelete
 28. This thing might truely be happened or could be an account from a person who suffered mental lunancy or a deliberate act to scum money . Therefore it was justfied to generate some hard core questions for some good answers. Based on one of the anonymous above the whole thing seems like a hoax. I believe in miracles and in exalting God evey time. Having said this I could not put up with some fabricated, ill intended story which set doubts on the real miracles.

  ReplyDelete
 29. Eleeleleeeee enkuan legan weredelin leminaminew enante kehadiwoch.

  ReplyDelete
 30. Abaselama.org u looks like countryside barteder. Yetelashache wore prostitute somebody say this that ............religious person is who pray other failer not exajurated. U tell us how the apostle make a difference from those high priests weül those come by doing practicall work not hiding an online they come face to face not hiding the skirt of their mom. Come on God is the same yesterday today and forever show us ur spirite Gods power . Do not worry about him or her as far as u believe God but the problem is there is no one . He fail or stand is for his God why abaselama acting like the rich man prayer ....thank u God I am not like this tax collecter I fast two times a week....... .... This is not christainity at all that is why these billions people have zero 0 saints holy fathers. U classify urself the side of those who shake the foundtion belives by the power of holy spirit where is urs baby sold out hodu amilaku who tried to creat follower by lie and lie and lie........

  ReplyDelete

 31. In the Name of the Father, the Son and Holy Sprit One GOD
  I do not expect you to believe in this . Because, this is God's Plan to return the stolen sheep by you and your Lutheran brethren to EOTC.

  Your Lord and Savior Jesus Christ, Kings of Kings the Beginning and Last ,we thank for what you did to strengthen our faith. How,ever, these people are not ready to repent. Please Our Lord, I beg you to do for these people what you did for St Paul!

  Amen

  ReplyDelete
 32. አባ ሰላማዎች ለምትጽፉት ነገር ኃላፊነት መውሰድ ለምን ትፈራላችሁ? ለምን ስማችሁን አናውቀውም? እውነት ካላችሁ ለምን ትፈራላችሁ? ተደብቃችሁ የትልቁንም የትንሹንም ስም ከምታጠፉ ወይም ሰውን ጥርጣሪ ውስጥ ከምትከቱ ለምን እውነት የምትሉትን በስማችሁ አትጽፉትም? እውነት ማንንም አይፈራም። ተከታይ ይኑረኝ አይኑረኝ ብሎም አይጨነቅም። ስለዚህ ጽሑፍ ስትጽፉ የጸሓፊውን ስምም አስቀምጡ የኤዲቶሪያል ኮሚቴም ካላችሁ እንወቃቸው። ሁሉንም ነገር አሳውቁን እንጂ። ካልሆነ ግን በእምነታችን ላይ ስሙን እየጠራችሁ አትቀልዱ። በእምነቱ ላይ የሚጫወቱትን ከመደገፍ በስተቀር ሌላ ነገር አታመጡም።

  ReplyDelete
 33. please excuse my limited knowledge of the bible, but I remembered that I came across the words of God that we all ought to be vigilant not to fell in the hoggish scheme of Satan. Many falsely would rise as they would be Jesus's followers and victimized us by deception. My question would be how would we see the above phenomenon? A Devine one or a hoax? Please be advised my intention was not to ridicule or antagonize certain groups, but seeking an honest view of my brothers and sisters of the Tewahido Church. Bless U all. Thank you!

  ReplyDelete
 34. Lete Tseone , from DallasSeptember 23, 2013 at 8:05 PM

  GeberHiwot Teru belehal Egziabher Yesteh Enezhe tehadesowech men yemyelute ale kehadiwoch. Yebelubeten mosebe sebariowch Nachew. Legna Teleke tamer new Enamnalen Enezeh degmo senogose tesedual eyalu yemiatelelu yebetekristian kahdiwoch nacheu Egziabhere selam honene yalem kristianoch hulu miniakel weshatamoch endehonacheu badebady yemenagerebet geze eruk ayhonem. Lezeh HULU TETEYAKI ABA HABTE ( aba Meleke Tsedic Nachew LIBEYEBELU ABATACHIN. BUCHLOCH DEGEMO END DIKON ANDUALEM DAGMAWI YEBETEKRISITIAN DELALA. GENZEB BAYBET YEMIANAFA. HIYEWOT BEGENZEB YTELEWOTE WESHETAKM. eGIABHER mastewal Yesten.

  ReplyDelete
 35. At anonymous sep 28/20133 1:44 AM

  ስማ እኛ ኢየሱስ የሚባል አምላክ እንጂ የሱስ አምላክ ተገዥዎች አይደለንም፡፡ ለማንኛዉም ጋኒን ላለበት ሰዉ መስቀል ከጦር በላይ እንደሚያስፈራዉ እናዉቃለን ስለዚህ እንዲህ የሚራወጠዉ በዉስጥህ ያለዉ ጋኒን ነዉና ወደ ቤ/ን አባቶች ብትመጣ የሱስ አምላክን ስም ሳይሆን የ ጌታ እየሱስን ስም ጠርተዉ ጌታ እየሱስ እኛን ከሰይጣን እስራት ለመፍታት ደሙን ባፈሰሰነት መስቀል ዳሰዉ ይፈዉሱሃል፡፡

  ReplyDelete
 36. lemehonu enante eneman nachehu bebetekirstian lay endih yale yedefret kal yemetenageru tamere maryam lay alanebebachehuma geta yenatun betemekdes sisera amd ena menber kesemay endemeta atawkum? enante yegeta tekawamiwoch nachehu serachehun geta esgiagaletew deres keledu yejachehun yesetachehual minem alachehu minem Egziabher yechin alem kalemenor wedemenor yameta amlak selehone legna kesemay meskel biyawedelen minem ayesanewum yehe legna lemenamnew yemedan milket sihon lenante lemetetefut demo mognenet new. selezih yemetenageruten yedefret negeger akumut geta lesanachehun kemezegatu befit neseha gebu hailun endehone atekedut engdih betenadedum yemayhon neger betenagerum minem atametu eshi.

  ReplyDelete
 37. መኑመ እንከ ለበግዐ ይሥሐቅ አቡሁ፡
  እስመ ንብል አምነ ሰማይ ወረደ ለሊሁ፡
  ወመኑ የአምር ነገረ መሰቀል ከማሁ፡፡
  ይሆናልም አይሆንምም ማለት አይቻልም፡

  ReplyDelete