Tuesday, September 3, 2013

የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃምና በኢየሱስ ስም ላይ የከፈተው ዘመቻ

(አናኒመስ ከሐረር)
አሁን የምነግራችሁ የምሥራች ሳይሆን መርዶ ነው፡፡ በተለይ ለእኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች አንገት የሚያስደፋ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ ሐረርን ለማህበረ ቅዱሳን ለማስከበር ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ሐረር የመጣው የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሐም ተልዕኮውን ለመፈፀም ደፋ ቀና ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ለስራዬ እንቅፋት ናቸው ያላቸውንና የቤተክርስቲያን እንጂ የማህበር አገልጋይ አንሆንም ያሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች እያደነ ከቤተስርቲያን ማፈናቀሉን ቀጥሎበታል፡፡

የደ/ሣ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ የተነሡት ቃለአዋዲ ባለማክበራቸው መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በ22-10-2005 ዓ.ም. የየአድባራቱን ሰበካ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤት፣ ስብከተ ወንጌልና ልማት ኮሚቴ አባላትን ሰብስቦ ውይይት መሰል የማስፈራሪያ መልእክት ያስተላለፈው የጉድ ሙዳዩ ከአንድ ስብሳቢ “የሚካኤል አስተዳዳሪ ለምን ተነሳ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ እንዲህ አለ፡፡ “ሰውየው ኢየሱስ ኢየሱስ ማለት ያበዛል፡፡ ከአንዴም ሁለቴ ጠርቼ ነገርኩት፡፡ ኢየሱስ የሚሉት አምላክነቱን እና አዳኝነቱን ያልተረዱት ናቸው፡፡ ኢየሱስ የሚለው ስም ማንነቱን አይገልፅም፤ ክብሩን ያንሰዋል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ኢየሱስ አትበል አልኩት፡፡ እሱ ግን ሰዓታቱ፣ ኪዳኑ፣ ቅዳሴው ሁሉ እኮ ኢየሱስ ኢየሱስ ነው የሚለው እያለ ሊከራከረኝ ሞከረ…” በማለት መልስ ሲሰጥ ንቀት በተሞላበት እና ኢየሱስ የሚለውን ስም በማጥላላት ነበር፡፡” አለ፡፡

ኢየሱስ የሚለው ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የተነገረው በቅዱስ ገብርኤል ቢሆንም ስሙ የወጣው ግን ፍፅምት በሆነች በአንዲት የስላሴ ፍቃድ (በባሕርይ አባቱ በአብ ፍቃድ በራሱ በወልድ ፍቃድ፣ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ) ነው፡፡ አምላካችን እንዴት እራሱን በትክክል መግለጥ የማይችል ክብሩን የሚያዋርድ ስም ለራሱ አወጣ ይባላል? ይህን ምን እንበለው? ስሞቹ ሁሉ ክብሩን፣ ሥልጣኑን፣ ሀይሉን እና ህላዌውን በትክክል የሚገልጡ ናቸው፡፡ ስሞቹን ያወጡለትም ሰዎች ሳይሆኑ እራሱ ነው፡፡ ስሜ ይህ ነው እያለ የነገረን፡፡ በመጻሕፍትም “በዚህም ምክንያት ደግሞ ያለልክ ከፍ ከፍ አደረገው፡፡ ከስምም ሁሉ በላይ  ያለውን ስም ሰጠው፡፡ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው” (ፊል. 2፥9-11) በማለት ኢየሱስ የሚለው መድኃኒት ስም የወጣው በእግዚአብሔር እንደሆነ እና ከስም ሁሉ በላይ የሚበልጥ ስም መሆኑን መስክሮአል፡፡

በሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ውስጥ ሐዋርያት ኢየሱስ የሚለውን ስም 352 ጊዜ ጠቅሰውታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በማለትም 174 ጊዜ ጠቅሰውታል፡፡ ክርስቶስ የሚለውን ስም ደግሞ 519 ጊዜ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡  ይህም የሆነበት ምክንያት በተለይ ከቤተ አይሁድ ለሆኑት፦
1.      ኢየሱስ እሱ በነቢያት ትንቢት የተነገረለት፣ ሱባኤ የተቆጠረለት፣ በተስፋ ስንጠብቀው የነበረው ክርስቶስ (መሲሁ) ነው ለማለት ሲሆን፣
2.     እናንተ ሰቅላችሁ የገደላችሁት ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል፡፡ አሁን ባባቱ ቀኝ በጌትነቱ በፀጋው ዙፋን ተቀምጦአል (ሐዋ. 2፥36) ለማለት ነው እንጂ ኢየሱስ የሚለው ስም መድኀኔ ዓለምን የመግለጥ አቅም ስለሌለው ክብሩንም ስለሚያዋርደው አይደለም፡፡
ኢየሱስ የሚለው ስም የተዋህዶ ስሙ ስለሆነ ሰውነቱንም አምላክነቱንም በእኩል መጠን የሚገልጥ የተፀውኦ ስሙ ነው፡፡ “ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ” ብለን ስንጠራው በእኛ ህይወት ውስጥ ያለውን ቦታ የባቤትነት ድርሻ ለመግለጥ እንጂ፣ ለእርሱ ክብርን ልንጨምርለት አይደለም፡፡ እኔ “ጌታዬ አምላኬ መድኀኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ” ብዬ ስጠራው ኢየሱስ እርሱ ጌታዬም አምላኬም መድኀኒቴም መሆኑን እየመሰከርኩ ነው እንጂ፣ መልአከ ፀሐይ መልአከ ገነት ወዘተ. እንደሚሉት ተግባር አልባ የማዕርግ ስሞች ለስሙ ድጋፍ ሰጪ የአክብሮት ቃላትን እየደረደርኩ አይደለም፡፡ ስሙ ብቻውን መጠራት የሚችል ወይም መቆም የሚችል ሙሉ እና  ጉድለት የሌለበት ስም ነው፡፡

ሌላው እኔን የገረመኝ ነገር ቅዱስ ገብርኤል እና እናቱ ድንግል ማርያም እንዲሁም ሐዋርያት ኢየሱስ ኢየሱስ እያሉ መጥራታቸው አምላክነቱን እና አዳኝነቱን ባለማወቃቸው ነው እንዴ? “እኛስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ አምነናል፤ አውቀንማል” (ዮሐ. 6፥69) ያለው ጴጥሮስ አይደለም እንዴ? “መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” የሐዋ. (4፥12) በማለት ሽባውን የተረተረው ኢየሱስ የሚለው ስም መሆኑን በሸንጎ ፊት የመሰከረው? የኀጢአት ሥርየት የሚገኘው በስሙ መሆኑን ለጉድ ሙዳይ ማን በነገረው! “በስሙ ንስሃና የኀጢአት ሥርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአህዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲህ ተፅፏል፡፡”  (ሉቃ. 24፥47)

በሌላ ቦታስልጆች ሆይ ኀጢያታችሁ ስለስሙ ተሰርዮላኋልና እፅፍላችኋለሁ” (1ዮሐ. 2፥12) አይደል እንዴ የሚለው? ፍርድስ የሚያስከትለው በስሙ ባለማመን መሆኑን ሰምቶ ያውቅ ይሆን?በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ ማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል” (ዮሐ. 3፥18) ተብሎ ተፅፏል፡፡ በርግጥ “እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል?” ይላል (ሮሜ 10፥14)፡፡ ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል እንዳይችል (1ቆሮ. 12፥3) የተረጋገጠ በመሆኑ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም በአደባባይ የገለጠው የልቡን እምነትና ማንነቱን ነው፡፡ እኔን የገረመኝ ስሙ ሲጠራ እንደ ሰይጣን መበርገጉ አይደለም፡፡ ስሙን የሚጠሩትን ማሳደዱም አልደነቀኝም፡፡ ሁሉም እንደአባቱ ነውና የሚኖረው፡፡ የጌታን ስም የሚጠሩት እንደአባታቸው እንደ ክርስቶስ ይሰደዳሉ፡፡ አባ አብርሃምም የአባቱን የዲያብሎስን ሥራ (የጌታን ስም የሚጠሩትን ማሳደድ) ነው እና እየሰራ ያለው፡፡

የሚገርመው አዲስ አበባ የሚገኙትን ቤቶቹን የሠራው፣ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የፈጀችውን ዘመናዊ መኪና የገዛው፣ እንደ እንግሊዝ ክለብ ተጨዋቾች አይነት የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖረው በኢየሱስ ስም ከድሆች በሚሰበሰብ ሣንቲም መሆኑን አለማወቁ ነው፡፡ “ከሥጋው ጿሚ ነኝ ከመረቁ አውጡልኝ” የሚለው አባባል መቼም አይሠራም፡፡ በስሙ ፈውስ ነው እንጂ ንግድ አልተፈቀደም፡፡

የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሐም በውጪ ሲያዩት እውነተኛ እረኛ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም በልቡ ያልተሸከመውን የኢየሱስን መስቀል በእጁ ይዞአል፡፡ የእሾህ አክሊል ምሳሌ የሆነውን አስኬማም ደፍቷል፡፡ ቀሚሱም እንዲሁ ለአለም የሞትኩኝ ነኝ እያለ ይሰብካል፡፡ ውስጡ ግን የአለም ወዳጅ፣ የኢየሱስ ስም ጠላት፣ ስሙን የሚጠሩትንም የሚያጠቃ ነጣቂ ተኩላ ነው፡፡ ለመሆኑም የቤተ ክርስቲያን መሠረት (1ቆሮ. 3፥11) ማነው? ኢየሱስ አይደለምን? የማእዘን ድንጋዩስ ማነው? ኢየሱስ አይደለምን? (ኤፌ. 2፥20)፡፡ የቤተክርስቲያን ራስስ ማነው? ኢየሱስ አይደለምን? (ቆላ. 1፥18)፡፡ ታዲያ ስለእርሷ ሲል (ዘበእንቲኣሃ ለቤተክርስቲያን እንዲል) በጦር በተወጋላት በጅራፍ በተገረፈላት በመስቀል ላይ በተቸነከረላት እና መራራውን የመስቀል ሞት በሞተላት ቤተክርስቲያን ስሙ ያልተጠራ በየት ይጠራ? የኢየሱስን ስም በቤተ ክርስቲያን እንዳይጠራ እየከለከለ በየቅዳሴው እና በየኪዳኑ መሐል የራሱ ስም እንዲጠራ ደጋግሞ ጥብቅ መመሪያ መስጠትስ ምን አይነት መንፈስ ነው?

የኢየሱስ ስም እንዳይጠራና በዚህ ስም እንዳያስተምሩ ሐዋርያትን ያዝዙ የነበሩትና ያስፈራሩ የነበሩት የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ነበሩ እንጂ ጳጳሳት ይሆናሉ ተብሎ አይጠበቅም ነበር (የሐዋ. 4፥17፤ 5፥28)፡፡ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሐም ግን ተረፈ አይሁድ ፀረ ኢየሱስ መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ አስመስክሯል፡፡ ከዚህ ቀደምም ኢየሱስ ኢየሡስ አትበሉ ብሎ ከአዲስ አበባ የመጡ ሰባክያንን ከልክሎ ነበር፡፡ እነርሱ ግን ኢየሱስን በስብከታቸውም በዝማሬያቸውም አክብረውት ነው የተመለሱት፡፡
ለካ አባ ጳውሎስ የጣሱት መመሪያ የኢየሱስን ስም አትጥራ ተብለው ስሙን መጥራታቸው እና ስለ ስሙ ክብር ከአባ አብርሐም ጋር መከራከራቸው ነው፡፡ ለካ ስለ ስሙ ከቤተክርስቲያን መገፋትም አለ፡፡ በክርስቶስ ስም አሥራቱን በኩራቱን እየሰበሰቡ የቤቱ ጌታ ግን ስሙ እንዳይጠራ በትጋት የሚቆጣጠሩ የጉድ ሙዳዩና ጀሌዎቹ ቤተክርስቲያንን እያዋረዷት ስለሆነ የተዋሕዶ ልጆች ልንነቃ ይገባል፡፡  
ሌለው የሚገርመው ደግሞ አስተዳዳሪው አባ ጳውሎስ የሚነሱት በእኔ ሳይሆን ከእኔ በፊት በነበሩ አባቶች፣ አሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ወሳኝ አካል ስለሆኑ በእነሱ ነው፡፡ በተለይም ብፅዕ አቡነ ያሬድ በአቀረቡት ክስ ነው በማለት ለተሰብሳቢው መግለጡ አስገርሞናል፡፡

          በግል ቀርቦ ለሚጠይቀው ደግሞሸዋዎች ቢሞቱም ቂማቸው ስለማይበሰብስ ሰውዬውን ያስነሱት እነሱ ናቸው” እያለ ያወራል፡፡ ነገር ግን ይህን ማመን አይቻልም፡፡ ከአሁን በፊት የነበሩ አባቶችን ብንመለከት ለምሳሌ ብፁእ አቡነ ቀሌምናጦስ በቆዩባቸው ዓመታት በአጥቢያዎች ውስጥ እንኳን ፀብ የሚጨስ የጥዋፍ ክር አልነበረም፡፡ ለዚህ ተቀይረው ሲሄዱ በተዘጋጀው የአሸኛኘት ፕሮግራም ላይ የነበረውን ሁኔታ ማስታወስ በቂ ነው፡፡ አባ አብርሃም ግን እንኳን 4 ዓመት 4 ወር ሥራ ሳይሰራ ጠብ እና ጥላቻ ብቻ ነው በከተማው መዝራት የጀመረው፡፡ ሌሎች አባቶችም ቢሆኑ በካህናት በሰንበት ትምህርት ቤት በምእመናን እንደተወደዱ ወደሌላ ሀገረ ስብከት ምክንያት በሰላምና በፍቅር ነው የተሸኙት፡፡ የጉድ ሙዳዩ፣ ጉድ አያልቅበት እደ ሰይጣን አባ አብርሃም ግን ሰውን ከሰው ለማጋጨት ሲጥር ተስተውሏል፡፡

የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም ሆይ የመውጊያውን ብርት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃልና እባክህን ኢየሱስ የሚለውን ስም ከመጥላትና ስሙን የሚጠሩትን ከማሳደድ ተመለስ፡፡

30 comments:

 1. You look funny. Please try to imagine your readers before starting to write. I think God send him Harar to clean HIS house. As long as we know Aba Abrahm, he is a man of action... He always stands with the Truth! I think he is a father that we need at this time.

  Good luck man... you are straggling with God, not with aba Abreham or yebetekrtian lejoch!

  ReplyDelete
 2. weyenea abeat amlak hoy men lay dersen ahun enzieh nachew abatoch yeterachewen yemayaweku lenegeru aba abereham mechea be amlak teri hone hoadam teraw yehew hodun yemolala ayi anchi beatekereseteyan yemotelesh AMLAK GETA EYESUS KERESETOS YETADEGESH alemetadel;;;;;;;;;

  ReplyDelete
 3. ይህን የኦርቶዶክስ ማፊያ ጳጳስ ምነው ድስቱን ቀምተው ቢያባርሩት?

  ReplyDelete
 4. በርግጥ ይህ ብሎግ በመኖሩ ‹‹ ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው›› /ራእ 13፤ 5/ ተብሎ የተነገረለት አውሬው ሥራውን እያበረታ መሆኑን እናያለን፡፡ በማያቋርጠው የሐሰትና የጠብ ፤ የስድብና የስም ማጥፋት እንዲሁም የኑፋቄና የክህደት ጽሑፎቻችሁም ‹‹ እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ ›› /ራእ 12 ፤ 15/ የተባለውን አውሬው በገቢር የሚያሳይባችሁ የክሕደትና የኑፋቄ የአውሬው የትፋት ወንዞች መሆናችሁን ታረጋግጡልናላችሁ፡፡ ነገር ግን ‹‹ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው ›› /ራእ 12 ፤16/ ተብሎ እንደተጻፈው ምድር ቤተ ክርስቲያን የእናንተን የክህደት መርዝ ታሰርገዋለች

  ReplyDelete
 5. በርግጥ ይህ ብሎግ በመኖሩ ‹‹ ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው›› /ራእ 13፤ 5/ ተብሎ የተነገረለት አውሬው ሥራውን እያበረታ መሆኑን እናያለን፡፡ በማያቋርጠው የሐሰትና የጠብ ፤ የስድብና የስም ማጥፋት እንዲሁም የኑፋቄና የክህደት ጽሑፎቻችሁም ‹‹ እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ ›› /ራእ 12 ፤ 15/ የተባለውን አውሬው በገቢር የሚያሳይባችሁ የክሕደትና የኑፋቄ የአውሬው የትፋት ወንዞች መሆናችሁን ታረጋግጡልናላችሁ፡፡ ነገር ግን ‹‹ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው ›› /ራእ 12 ፤16/ ተብሎ እንደተጻፈው ምድር ቤተ ክርስቲያን የእናንተን የክህደት መርዝ ታሰርገዋለች

  ReplyDelete
 6. አቤት!!! ያች ሀረር ምን አይነት ታምረኛ ምድር ነች በኢየሱስ ስም ስንቱን ስንቱን ከባድ የመከራ ዘመናት ትገፋለች? እኔኮ በጣም የሚገርመኝ እንዴት ያለ እራሱን ለኢየሱስ የሰጠ ሕዝብ የሚኖርባት ወንጌል በነጻነት የሚሰበክባት በተመሳሳይ መልኩም የውስጥ ጠንካራ ጠላት የሚያስጨንቃት ብቸኛ ምድር መሆኗ ነው:: አረ እባካችሁ የመዳን ጠላቶች: ምናለ ለዚያ በመዳኑ ለታመነ ህዝብ ፋታ ብትሰጡት ገንዘባችሁን ክብራችሁን እንደሆነ አልከለከላችሁ: አረ ተውት ባመነበት ይዘምር ስለሚያምንበት ይማር: ፍላጎታችሁ ባመጣባችሁ ሀጢአት እያስፈራራ የእቅዱ ማስፈጸሚያ ላደረጋችሁ ነፍሰ ገዳይ ድርጅት ደስታ ብላችሁ እውነትን በማሳደድ እስከመቼ? የመውጊያውን ብርት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃልና እባክህን ኢየሱስ የሚለውን ስም ከመጥላትና ስሙን የሚጠሩትን ከማሳደድ ተቆጠቡ:አምላክ ልብ ይስጣችሁ::

  ReplyDelete
 7. አቤት!!! ያች ሀረር ምን አይነት ታምረኛ ምድር ነች በኢየሱስ ስም ስንቱን ስንቱን ከባድ የመከራ ዘመናት ትገፋለች? እኔኮ በጣም የሚገርመኝ እንዴት ያለ እራሱን ለኢየሱስ የሰጠ ሕዝብ የሚኖርባት ወንጌል በነጻነት የሚሰበክባት በተመሳሳይ መልኩም የውስጥ ጠንካራ ጠላት የሚያስጨንቃት ብቸኛ ምድር መሆኗ ነው:: አረ እባካችሁ የመዳን ጠላቶች: ምናለ ለዚያ በመዳኑ ለታመነ ህዝብ ፋታ ብትሰጡት ገንዘባችሁን ክብራችሁን እንደሆነ አልከለከላችሁ: አረ ተውት ባመነበት ይዘምር ስለሚያምንበት ይማር: ፍላጎታችሁ ባመጣባችሁ ሀጢአት እያስፈራራ የእቅዱ ማስፈጸሚያ ላደረጋችሁ ነፍሰ ገዳይ ድርጅት ደስታ ብላችሁ እውነትን በማሳደድ እስከመቼ? የመውጊያውን ብርት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃልና እባክህን ኢየሱስ የሚለውን ስም ከመጥላትና ስሙን የሚጠሩትን ከማሳደድ ተቆጠቡ:አምላክ ልብ ይስጣችሁ::

  ReplyDelete
 8. man feraj aderegeh.tilik sewn ante malet ewnet ciristna newn ? ykir ybelih.

  ReplyDelete
 9. መንፈስ ቅዱስ በትክክል እየተለያችሁ እንደመጣ በየጊዜው የምታወጧቸው የፅርፈት ፅሑፎች በቂ ማስረጃ ናቸው፡፡ አሁንስ በጣም እያሳዘናችሁኝ መጣችሁ መቸም ወዳችሁ አይመስለኝም ያደረባችሁ ክፉ መንፈስ ካልተሳደባችሁ እረፍት ስለሚነሳችሁ ይመስለኛል፡፡ አሁን እንዲያው ራሷ ኢየሱስ በሆነነው ቤተክርስቲያን ውስጥ ጳጳሱ አቡነ አብርሐም የኢየሱስ ስም እንዳይጠራ ከለከሉ ብላችሁ ብታወሩ አርግጠኛ ነኝ እንኳን ሰው ሰይጣን ራሱ አያምናችሁም
  እባካችሁ ልብ ግዙ ጠፍታችሁ እንዳተቀሩ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳቸሁ

  ReplyDelete
 10. እዉነት ተደብቆ አይቀርም። እግዚአብሄር በግዜውና በሰዓቱ ያጋልጠዋል። የማቅ ጳጳሳት ገንዘብ ያሰከራቸው የዘመኑ ይሁዳዎችና ናቸው። ጥቁር ልብስና ቆብ የመንግሰተ ሰማያት መግቢያ መስፈርት አይደለም ይልቁን ሰውን በጥቅም ለማስደሰት ከመሮጥ በንስሐ ሕይወት ተመልሰው እግዚያብሔርን ደስ ብያሰኙ ይሻላቸዋል።በእግዚአብሔር ስም እየነገዱ እራስን ለምድራዊ ጥቅም መሸጥ የቆም ሞት ነው። የህይወት ያሉ ግን በቁም ሞታኖች ከመሆን እግዝአብሔር ያውጣን/////////

  ReplyDelete
 11. አባ ሰላማዎች የሰጣችሁት አስተያየት እውነት ቢሆንም አቀራረባችሁ ኢትዮጵያዊነት አክብሮት የተላሰበሰ አይደለም።ክፉ ሰዎች እንዴት እናንተን መልሰው ያስቷችኋል።ያሳዝናል እኒህ አባት እኮ ሊስቱ ይችላሉ ግን የሚያሳዝነው ስተው እናንተን በንግግርና በጽሑፍ ማሳታቸው ነው!የሚገርመው ነገር ክፉዎች በተለሱብኝ ጊዜ በአንደበቴ እንዳስት አንደበቴን ጠብቅ የሚለውን የመዝሙረኛውን ቃል ለምን ረሳችሁት?በባህላችን እኮ በአክብሮት ተናግሮ መገሰጽ ይቻላል ትክክል ያልሆነውን ትክክል አይደለም ማለት ይቻላል።<ንጉሥ ሆይ ሺ ዓመት ንገስ ግን ላቆምከው የወርቅ ምስል አንሰግድም ማለትን ማን ይከለክለናል?ወደድንም ጠላንም ጳጳስ ናቸው ተሾመዋል እግዚአብሔር የሾመውን ማዋረድ እግዚአብሔርን ማሳዘን ነው።ምንም ዓይነት ጥፋት ቢያጠፉ ሥልጣናቸውን መጋፋት አይቻልም ነገር ግን ስህተታቸውን በትህትና ማስረዳት ማንም አያግደንም!ሰላም ሁኑ!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete

 12. mulushewa September 5, 2013 at 3:32 pm Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ላለፉት ሀያ ምናምን አመታት ከስሙ ይልቅ ስራው የገነነ የኢኦተቤክ አጋዥ ሆኖ ቆይቱአል አሁንም እንዲቀጥል ምኞቴ ነው. ሆኖም አሁን አሁን ከስራው ይልቅ ስሙ መግነኑ እና አንዳንድ ነገሮቹ አልተመቹም. በተለይ
  1.ሁለት አይነት የሚዲያ አጠቃቀም-ይፋዊ እና ይፋዊ ያልሆነ(ደጀሰላም፣አንድ አድርገን፣ሀራ ተዋህዶ). በተለይ ይፋ ያልሆኑቱ አርአያ የሚሆኑ በህይወት ያሉና የሌሉ አባቶችን ህይወት ከመተረክ ይልቅ ባንድ ወገን ቆመው ለማህበሩ አስጊ ናቸው ባሉዋቸው ሁሉ በጭፍን ይተኩሳሉ. በነዚህ ሚዲያዎች የቤ/ክ አመራሮች ኢላማ በመደረጋቸው የማህበሩን አባላት እንደልጅ አቅርቦ መምከሩንና መገሰጹን ትተው ስማቸው እንዳይጠፋ በመፍራት ብቻ እያዩ ዕንዳላዩ እየሆኑ ነው.ማህበሩ በስሙ ከመፈራት ይልቅ በስራው ለመወደድ ብዙ ይስራ በ..ተ..ለ..ይ በማህበረ ካህናት ዘንድ ማህበሩ የሚታይበት የጥርጣሬ አይን
  2.ተገቢ ያልሆነ ቡድናዊ መዋቅር-በአሁን ሰአት ሰ/ጉባኤና ሰ/ት/ቤቶች ተጠሪነታቸው ለአጥቢያ አብ/ክርስቲያናት ሳይሆን ለማህበሩ የሆነ ይመስላል.በዚህም አጥቢያውን ዘለው የኦዲት ሪፖርት የምናቀርበው ለማህበሩ ነው የሚሉ ሰ/ት/ቤቶችን ማየት ከለመድን ቆየን
  3.ፖለቲካ- መንግስት ኢኦተቤክንን ካለፉት ስርኣቶች ጋር ለመደመር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መቃወም ፖለቲካ ካልተባለ በቀር በሀገር ውስጥ ያለው የማህበሩ እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን ከፖለቲካ የጸዳ ይመስለኛል.ባህር ማዶ ያለው የማህበሩ ክንፍ ግን ያጠራጥራል.ይህን ደግሞ የማህበሩን የአሜሪካ እንቅስቃሴ ሲያsተጋባ የቆየው ደጀሰላም በተደጋጋሚ ከሚያወጣቸው ገዥውን ፓርቲ የሚወቅሱና አንዳንዴም ቢሆን ተቃዋሚን የሚወግኑ በኢሳት እስከመጠቀስ የደረሱ ዘገባዎች መረዳት ይቻላል
  4.ካህናትን እንደጥቅመኛ ፈርጆ ራስን ብቸኛ የቤ/ክ ተቆርቁዋሪ ማድረግ-ይህ አቁዋም በተለይ በተራ አባላት ላይ ስር እየሰደደ መጥቱዋል. እኔ(እኛ) ብቻ የሚሉ ደግሞ በሀገራችን ምን ያህል ጥፋት(ሽብር) እንደሰሩ ታሪክ ምስክር ነው.ስለዚህ ስለአቦይ ስብሃት፣ስለአባ ዮናስ፣ስለሚኒስቴሩ እና ስለመንግስት ከማውራታችን በፊት ንግግራቸውን አጢነን ራሳችንን እንመርምር.ማን ተናገረ ሳይሆን ምን ተናገረ የሚለው ላይ እናተኩር.የለበለዚያ ያው የፈረደበት የፍረጃ አዙሪት ውስጥ መውደቃችን ነው.
  5.በሰ/ት/ቤቶች አመራር አካባቢ ያሉትን የስነ-ምግባር ችግሮች ለመቅረፍ አለመሞከርና መተካካትን አለማበረታታት-የማህበሩ ዲሞልራሳዊ የውስጥ አሰራርና የአመራር መተካካት ሂደት ምርጥ የሚባል ቢሆንም ይህ ልምድ ለሰ/ት/ቤቶች ባለመትረፉ 20 እና 30 አመታት ከክፍል ክፍል ሲዘዋወሩ ቆይተው በስንት ትግል የሚወርዱ የሰ/ት/ቤት አባላት ጉዳይ ሽብር ባይሆንም ሼም ነው
  6.ካህን መርጦ መሳለም-የማህበሩ አባላት የሲኖዶስን ውሳኔ ሳይጠብቁ ካህናትን በየሰበብ አስባቡ እየፈረጁ መርጦ መሳለም ፋሽን ኁኗል.አስተውሉ ከማህበሩ ኔትወርክ አንጻር በዚህ መልኩ የተፈረጀ ካህን በማህበረ ምእመናኑ ምን ያህል ሊገለል እንደሚችል.
  7.ከመንግስት የተቀራረበ የመሰለውን ሁሉ መፈረጅ-አንዱ መንግስት ማህበሩን እንዲጠራጠር የሚያደርገው ምክንያት ይህ ይመስለኛል.ይህ ደግሞ በአቡነ ጳውሎስ፣በአባሰረቀ፣በንቡረዕድ፣በዲ/ባያብል፣በዲ/ዳንኤል ታይቱዋል.ቢታረም!!!

  ReplyDelete
  Replies

  1. ስምህ ባይጠቀስም ስለ አስተያየትህ አንድ አንድ ነገር ማለትን ፈለኩ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም ግን ምንፍቅና በበዛበት ጊዜ ቤተክርስቲያንን መታደግ በተለይ ወጣቱን ቤተክርስቲያኑን እንዲውቅ በማድረግ እረገድ ቤተክርስቲንን ያለምንም ክፍያ ማገልገል ቀላል አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ትልቁ ችግር የነጻ አገልግሎት ልስጥ ስትል የሚከፈላቸው አገልጋዮች ስራ የሚያጡ እየመሰላቸው ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የተወሰኑ ለገንዘብ ያደሩ እንደ ይሁዳ ያሉ ቤተክርስቲያናቸውን አሳልፈው ሲሰጡ ይታያል፡፡ በተለይ ከመናፍቃን ጋር በመሆን ከስርዓት ውጪ ሆኖ መንቀሳቀስ፡፡ መናፍቃንን ሰርገው እንዲገቡ ከማድረግም በላይ የነሱየሆነውን ነገር አሹልከው የማስገባት ነገር ሲታወቅባቸው ማህበሩ ነው ስሜን የሚያጠፋው የገታን ስም ስለጠራሁ ነው ይላሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ጌታን ኢየሱስ ብላ ከመሰየም አልፋ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ የአማልክት አምላክ በማለት ትጠራዋለች፡፡ ከመናፍቃን ጎራ አዳራሻቸው ሳይቀር የሚሄዱትን ከሃዲና አገልጋይ ነን ባዮችን ማጋለጥ ቤተክርስቲያንን መታደግ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ይሁዳም ያልታወቀበት እየመሰለው ጌታን አሳልፎ እስከመስጠት አደረሰው፡፡ አሁንም የውስጥ ጠላትህን ሳይደራጅ በማስረጃ አስደግፈህ ማቅረቡ ምንፍቅናን ከቤተክርስቲያንዋ ማጥፋት ነውና፡፡
   1. ማህበረ ቅዱሳን ስራውን ሲሰራ ተቀማጭ ሰው ብዙ ሊያወራ ይችላል፡፡ ማህበሩ ሃይማኖታዊ ግዴታውን ሲወጣ ቁጭ ብሎ የሚያወራው ደግሞ አግንኖ ሊያወራ ይችላል፡፡ ስለዚህ አውሪውን መጠየቅ ነው፡፡ ማህበሩ ግን ስለሚሰራው ስራ በተለያየ ሁኔታ ለአባላቱ ማሳወቅ ግዴታው ነው፡፡ ይህንን የሚያይ ሊያደንቅና ሊያወራ ይችላል፡፡ ችግሩ ከአውሪው ነው፡፡
   2. ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ባላት መዋቅር ተጠናክራ አገልግሎት እንድትሰጥ ምኞቱና ትልሙ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የማህበሩ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኦርቶዶክስ ነኝ ባይ ስራ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ማህበሩ ውስጥ ያሉ በተለያየ ሙያ ያሉ በመሆናቸው ለቤተክርስቲያን ሙያዊ እገዛ ማድረጋቸው ስልጠና ቢሰጡ ለመዋቅሩ እገዛ ቢያደርጉ ችግር የለውም፡፡ ሰበካ ጉባኤ ነኝ ግን አይሉም በነሱም ሆነው አይወስኑም፡፡
   3. ማንኛውም ሰውም ሆነ ሚዲያ ወይም ቡድን እንዲሁም መንግስት አንድን አባባል ለራሱ እንደመሰለው አድርጎ ሊወስደው ይችላል፡፡ የውጪው ሚዲያ ማህበሩን ስላነሳ ፖለቲካ ውስጥ ገብተዋል ብሎ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ የማህበሩ ያልሆኑ ዌብ ሳይቶችንም ከማህበሩ ጋር ማገናኘት ተገቢ አይደለም፡፡ ማህበሩ እንዲፈርስ የሚፈልግ የማህበሩ እንዲመስል እያወደሰ መንግስትን እየነቀፈ ቢጽፍ የማህበሩ ነው ሊያስብልና ማህበሩ ላይ መንግስት አይኑን እንዲያደርግ ሊያደርግ ይችላል፡፡
   ስምህ ባይጠቀስም ስለ አስተያየትህ አንድ አንድ ነገር ማለትን ፈለኩ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም ግን ምንፍቅና በበዛበት ጊዜ ቤተክርስቲያንን መታደግ በተለይ ወጣቱን ቤተክርስቲያኑን እንዲውቅ በማድረግ እረገድ ቤተክርስቲንን ያለምንም ክፍያ ማገልገል ቀላል አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ትልቁ ችግር የነጻ አገልግሎት ልስጥ ስትል የሚከፈላቸው አገልጋዮች ስራ የሚያጡ እየመሰላቸው ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የተወሰኑ ለገንዘብ ያደሩ እንደ ይሁዳ ያሉ ቤተክርስቲያናቸውን አሳልፈው ሲሰጡ ይታያል፡፡ በተለይ ከመናፍቃን ጋር በመሆን ከስርዓት ውጪ ሆኖ መንቀሳቀስ፡፡ መናፍቃንን ሰርገው እንዲገቡ ከማድረግም በላይ የነሱየሆነውን ነገር አሹልከው የማስገባት ነገር ሲታወቅባቸው ማህበሩ ነው ስሜን የሚያጠፋው የገታን ስም ስለጠራሁ ነው ይላሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ጌታን ኢየሱስ ብላ ከመሰየም አልፋ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ የአማልክት አምላክ በማለት ትጠራዋለች፡፡ ከመናፍቃን ጎራ አዳራሻቸው ሳይቀር የሚሄዱትን ከሃዲና አገልጋይ ነን ባዮችን ማጋለጥ ቤተክርስቲያንን መታደግ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ይሁዳም ያልታወቀበት እየመሰለው ጌታን አሳልፎ እስከመስጠት አደረሰው፡፡ አሁንም የውስጥ ጠላትህን ሳይደራጅ በማስረጃ አስደግፈህ ማቅረቡ ምንፍቅናን ከቤተክርስቲያንዋ ማጥፋት ነውና፡፡
   1. ማህበረ ቅዱሳን ስራውን ሲሰራ ተቀማጭ ሰው ብዙ ሊያወራ ይችላል፡፡ ማህበሩ ሃይማኖታዊ ግዴታውን ሲወጣ ቁጭ ብሎ የሚያወራው ደግሞ አግንኖ ሊያወራ ይችላል፡፡ ስለዚህ አውሪውን መጠየቅ ነው፡፡ ማህበሩ ግን ስለሚሰራው ስራ በተለያየ ሁኔታ ለአባላቱ ማሳወቅ ግዴታው ነው፡፡ ይህንን የሚያይ ሊያደንቅና ሊያወራ ይችላል፡፡ ችግሩ ከአውሪው ነው፡፡
   2. ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ባላት መዋቅር ተጠናክራ አገልግሎት እንድትሰጥ ምኞቱና ትልሙ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የማህበሩ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኦርቶዶክስ ነኝ ባይ ስራ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ማህበሩ ውስጥ ያሉ በተለያየ ሙያ ያሉ በመሆናቸው ለቤተክርስቲያን ሙያዊ እገዛ ማድረጋቸው ስልጠና ቢሰጡ ለመዋቅሩ እገዛ ቢያደርጉ ችግር የለውም፡፡ ሰበካ ጉባኤ ነኝ ግን አይሉም በነሱም ሆነው አይወስኑም፡፡
   3. ማንኛውም ሰውም ሆነ ሚዲያ ወይም ቡድን እንዲሁም መንግስት አንድን አባባል ለራሱ እንደመሰለው አድርጎ ሊወስደው ይችላል፡፡ የውጪው ሚዲያ ማህበሩን ስላነሳ ፖለቲካ ውስጥ ገብተዋል ብሎ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ የማህበሩ ያልሆኑ ዌብ ሳይቶችንም ከማህበሩ ጋር ማገናኘት ተገቢ አይደለም፡፡ ማህበሩ እንዲፈርስ የሚፈልግ የማህበሩ እንዲመስል እያወደሰ መንግስትን እየነቀፈ ቢጽፍ የማህበሩ ነው ሊያስብልና ማህበሩ ላይ መንግስት አይኑን እንዲያደርግ ሊያደርግ ይችላል፡፡


   Delete
  2. 4. ማሰብ ያለብን ማህበሩ ቀድሞም በአይን የሚታይ ማስረጃ በመያዝ እንጂ በደፈናው ካህናትን የሚወነጅል አይደለም፡፡ በአሁን ሰዓት በብዛት የኛን ካህናት ድክመት ስለሚረዱ እንደ ይሁዳ በብር ስለሚደልሉዋቸውና አንድ አንዱ በቀላሉ ስለሚሸነፍ ከአዋዋላቸው አካሄዳቸው አሰራራቸው አስተምህሮታቸው ንግግራቸው በሙሉ ወደ መናፍቃኑ በመወሰዱ ሊመከሩ ቢሞከር እምቢ አሻፈረኝ በማለታቸው በጥፋታቸው በመቀጠላቸው ከቤተክርስቲን ይልቅ ለመናፍቃን ዘብ ስለሚቆሙ መለየት ስላለባቸው ለዚህም ማህበሩ መረጃ በማቅረቡ ሰው ደግሞ ማህበሩ የሚያደርገውን የመረጃ ማቅረበ ሳይሆን አሁንም በሰው ውስጥ መናፍቃን በማህበሩ ላይ የሚያቀርቡትን ክስና ካህኑን የሚደግፉ ሰዎች በሚያቀርቡት ወሬ አንድ አንዱ ማህበሩን እንደ መጥፎ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በዛው ቢቀጥሉ ምን እንደሚመጣና ቤተክርስቲያን ምን ያክል ትበረዝና ትጠፋ እንደነበር ማሰብ የግድ ነው፡፡
   5. በተፈጥሮዋችን እኛ አንድ ሰው ጥሩ ከሰራ እድሜውን ሙሉ ቢሰራ ደስ ይለናል፡፡ ለምሳሌ የሰበካ ጉባኤን ብንወስድ አንድ ሰው ሁለት ጊዜ በተከታታይ መመረጥ ይችላል፡፡ ከዛ በሁዋላ ለመመረጥ ቢፈልግ በሶስተኛው ምርጫ መውጣትና ከዛ ቀጥሎ ባለው ደግሞ እንደገና መመረጥ እንደሚችል ይናገራል፡፡ ይህ ሰው ግን በሌሎች የቤተክርስቲን አገልግሎት ውስጥ አይግባ ብሎ አይከለከልም፡፡ ስለዚህ ከመናገር በፊት ህጉን ማወቅ የግድ ነው፡፡
   6. ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንደሚባለው አንድ አንድ የምንፍቅና ችግር ያለባቸው ክህነት አለን የሚሉ የማህበሩን ልጆች ማቅረብ አይፈልጉም፡፡ ማህበሩም ኑና በጸሎት ክፈቱልን በማህበራችን መርሃ ግብር ላይ ተገኙልን ቢሉዋቸው አያደርጉትም ይህንንም በተደጋጋሚ ሲያደርጉት ሊያስተውሉት ይችላሉ ስለዚህ ምን አይነት ግንኑነት እንዲኖራቸው ይፈለጋል፡፡ የንስሃ አባቱ እየፈለጋቸው ባይጎበኙት ደጋግሞ በመጠየቅ መተውና መለወጥ መብቱ ነው፡፡
   7. የይሁዳ አይነት መረጃን ለሌላ አሳልፎ የሚሰጥ የለም አይኖርም ማለት አይቻልም፡፡ ማናም ምንም ይበል መንግስትም ምንም ያስብ ማህበሩ መንፈሳዊ ነገር ነው የሚሰራው የተማረ የሰው ሃይል ስላለበት መንግስት ነገ ስለሚሆነው ስለሚጠራጠር ማህበሩን ሁሌም መነዝነዙን አያቆምም፡፡ መንግስት ውስጥ ደግሞ ለፖለቲካ የሚያድሩ ካድሬዎች፤ መናፍቃን ሌሎችም ስለሚኖሩበት ለነዚህ ደግሞ ማህበሩ የእግር እሳት ነው የሚሆንባቸው፡፡ የግብጽ ኦፕት ቤተክርስቲያንን ብንመለከት ገዳማቸው ውስጥ እንኩዋን የተማሩ ሰዎች ነው ያሉባቸው መንግስትም የተማረ የሰውሃይል እንዳላት ስለሚያውቅ ይጠብቃቸዋል፡፡
   ስለዚህ ኦርቶዶክስ ነን የምንል ሁሉ በየሄድንበት ሁሉ ስለማህበሩ የሚወራውን ክፉ ነገር ሁሉ በመገንዘብ ባንደነብር ባንቀበል መናፍቃን በማህበሩ ላይ ኦርቶዶክስ ሆነው የኛንም አገልጋዮች በመያዝ የሚከፍቱትን ስም የማጥፋት ዘመቻ ባንቀበል እላለሁ፡፡
   4. ማሰብ ያለብን ማህበሩ ቀድሞም በአይን የሚታይ ማስረጃ በመያዝ እንጂ በደፈናው ካህናትን የሚወነጅል አይደለም፡፡ በአሁን ሰዓት በብዛት የኛን ካህናት ድክመት ስለሚረዱ እንደ ይሁዳ በብር ስለሚደልሉዋቸውና አንድ አንዱ በቀላሉ ስለሚሸነፍ ከአዋዋላቸው አካሄዳቸው አሰራራቸው አስተምህሮታቸው ንግግራቸው በሙሉ ወደ መናፍቃኑ በመወሰዱ ሊመከሩ ቢሞከር እምቢ አሻፈረኝ በማለታቸው በጥፋታቸው በመቀጠላቸው ከቤተክርስቲን ይልቅ ለመናፍቃን ዘብ ስለሚቆሙ መለየት ስላለባቸው ለዚህም ማህበሩ መረጃ በማቅረቡ ሰው ደግሞ ማህበሩ የሚያደርገውን የመረጃ ማቅረበ ሳይሆን አሁንም በሰው ውስጥ መናፍቃን በማህበሩ ላይ የሚያቀርቡትን ክስና ካህኑን የሚደግፉ ሰዎች በሚያቀርቡት ወሬ አንድ አንዱ ማህበሩን እንደ መጥፎ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በዛው ቢቀጥሉ ምን እንደሚመጣና ቤተክርስቲያን ምን ያክል ትበረዝና ትጠፋ እንደነበር ማሰብ የግድ ነው፡፡
   5. በተፈጥሮዋችን እኛ አንድ ሰው ጥሩ ከሰራ እድሜውን ሙሉ ቢሰራ ደስ ይለናል፡፡ ለምሳሌ የሰበካ ጉባኤን ብንወስድ አንድ ሰው ሁለት ጊዜ በተከታታይ መመረጥ ይችላል፡፡ ከዛ በሁዋላ ለመመረጥ ቢፈልግ በሶስተኛው ምርጫ መውጣትና ከዛ ቀጥሎ ባለው ደግሞ እንደገና መመረጥ እንደሚችል ይናገራል፡፡ ይህ ሰው ግን በሌሎች የቤተክርስቲን አገልግሎት ውስጥ አይግባ ብሎ አይከለከልም፡፡ ስለዚህ ከመናገር በፊት ህጉን ማወቅ የግድ ነው፡፡
   6. ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንደሚባለው አንድ አንድ የምንፍቅና ችግር ያለባቸው ክህነት አለን የሚሉ የማህበሩን ልጆች ማቅረብ አይፈልጉም፡፡ ማህበሩም ኑና በጸሎት ክፈቱልን በማህበራችን መርሃ ግብር ላይ ተገኙልን ቢሉዋቸው አያደርጉትም ይህንንም በተደጋጋሚ ሲያደርጉት ሊያስተውሉት ይችላሉ ስለዚህ ምን አይነት ግንኑነት እንዲኖራቸው ይፈለጋል፡፡ የንስሃ አባቱ እየፈለጋቸው ባይጎበኙት ደጋግሞ በመጠየቅ መተውና መለወጥ መብቱ ነው፡፡
   7. የይሁዳ አይነት መረጃን ለሌላ አሳልፎ የሚሰጥ የለም አይኖርም ማለት አይቻልም፡፡ ማናም ምንም ይበል መንግስትም ምንም ያስብ ማህበሩ መንፈሳዊ ነገር ነው የሚሰራው የተማረ የሰው ሃይል ስላለበት መንግስት ነገ ስለሚሆነው ስለሚጠራጠር ማህበሩን ሁሌም መነዝነዙን አያቆምም፡፡ መንግስት ውስጥ ደግሞ ለፖለቲካ የሚያድሩ ካድሬዎች፤ መናፍቃን ሌሎችም ስለሚኖሩበት ለነዚህ ደግሞ ማህበሩ የእግር እሳት ነው የሚሆንባቸው፡፡ የግብጽ ኦፕት ቤተክርስቲያንን ብንመለከት ገዳማቸው ውስጥ እንኩዋን የተማሩ ሰዎች ነው ያሉባቸው መንግስትም የተማረ የሰውሃይል እንዳላት ስለሚያውቅ ይጠብቃቸዋል፡፡
   ስለዚህ ኦርቶዶክስ ነን የምንል ሁሉ በየሄድንበት ሁሉ ስለማህበሩ የሚወራውን ክፉ ነገር ሁሉ በመገንዘብ ባንደነብር ባንቀበል መናፍቃን በማህበሩ ላይ ኦርቶዶክስ ሆነው የኛንም አገልጋዮች በመያዝ የሚከፍቱትን ስም የማጥፋት ዘመቻ ባንቀበል እላለሁ፡፡

   Delete
 13. aba selama ewunet miskrie yihunina bedenbi www chun eketatelalehu ahun ahun eyaferkubachehu new. balefew bawetachut tihufachew yewengiel memihru aba kale tidk (ato kale tidk) endinager bilachu neber ahunis sile kale tidk min melis tisetu yihon kkkkkkkkkkk abune yosfe ke tehafinetachew alitenesum bilachu neber tadiya abune michale mahitemun endirekebu madreg keyet yemeta new tewut tewut gudachin ebietachin yihunina yihn werie yemiyakebilachu wendmie kessis tixztaw samuhel new gin nigerut yalitetara weri ayingerachu ersu endihon businessun eyesera new gobez endiet bezih birr wengel esebikalehu emil jegina yihunina gin anbabi endayasatat aba selama nigerut tikikilun yigerachu awukalehu endematawetut eniem enditawetut aliteyikachum yichin yegud muday emitlew neger eyanim silemineka lekale tidk man
  babaye neger situ.

  ReplyDelete
 14. በስሙ መመካከር እና መፈቃቀር ሲገባ፤ በስም ምክንያት ወንዝ እየተሻገሩ ስም እየጠሩ
  የጥላቻውን አጥር ማስፋት ያጋንንት አካሄድ ይሆናል በመጨረሻም የግራ የቀኙ መሠረት
  ይናወጣል ሞኛሞኞች የሚመኩበት ጣራውና ግድግዳውም ይናዳል በሥራ እንጂ በስም
  ሰማያዊ ሀብት አይገኝም (ወይፈድዮ ለኩሉ በከመ ምግባሩ)በመሠረቱ ወኩሉ ዘጸውዐ
  ስመ እግዚአብሔር ይድኅን ይላልና ይህ የተባለው ባደጋ ጊዜ ነው በመሆኑም ያሁኑ ትውልድ ቀይ መሥመር አልፎ ወዳልሆነ አቅጣጫ ስለገባ አደጋ ላይ ነውና በስም ከመጣላት በስሙ ካደጋ ለመውጣት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል ዳሩ ግን
  ተመክሮ ልብ ተፍቆ ጥርስ አይሆንምና ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ

  ReplyDelete
 15. lebetekirstianitu tilik tifat new

  ReplyDelete
 16. Well, we learn from our God and lord Jesus christ is truth not sin. No one is perfect we all are sinners.

  ReplyDelete
 17. I am glad I did not c the slogan «yes we can yes we can» change believe in. All those tried to destroy eotc by blood and death even one of our leader Atse syseneyous the father of fasil to modernize his militry power, he promised the spain and portugal thee Ethiopians all must converted to catholic. He murdered somany innocents but the dream became nightmare eotc is still walking around the glob professtionally. We have somany account that made eotc. The spirit of God only can change not even this dirty unholy abaselama blog. All those lie video from type of you we everyday watch it. In the last days we know the dragon have power to speak blasphemy words. Change is not negative, those dyanamic holy and saint paul came with evidance the power of holly sprit but abaselama funded and empoerd by those who fought eotc . Abaselama blog God forgive you God forgive ur lie. Among the ten comandments do not lie do not false witness your friend. This law destroys ur soul every minute when ever ur courapted mind start jihad filty nasty emotions. Who cares what u or ur masters said God is the fighter we will c as those bloody hand lost control you the same went through

  ReplyDelete
 18. Who is this writing ?I don't believe

  ReplyDelete
 19. ገላትያ፥ምዕራፍ፡6።1-6
  1፤ወንድሞች፡ሆይ፥ሰው፡በማናቸውም፡በደል፡ስንኳ፡ቢገኝ፥መንፈሳውያን፡የኾናችኹ፡እናንተ፡እንደዚህ፡ያለውን ፡ሰው፡በየውሀት፡መንፈስ፡አቅኑት፤አንተ፡ደግሞ፡እንዳትፈተን፡ራስኽን፡ጠብቅ።
  2፤ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡የአንዱን፡ሸክም፡ይሸከም፡እንዲሁም፡የክርስቶስን፡ሕግ፡ፈጽሙ።
  3፤አንዱ፡ምንም፡ሳይኾን፡ምንም፡የኾነ፡ቢመስለው፡ራሱን፡ያታልላልና።
  4፤ነገር፡ግን፥እያንዳንዱ፡የገዛ፡ራሱን፡ሥራ፡ይፈትን፥ከዚያም፡በዃላ፡ስለሌላው፡ሰው፡ያልኾነ፡ስለ፡ራሱ፡ብ ቻ፡የሚመካበትን፡ያገኛል፤
  5፤እያንዳንዱ፡የገዛ፡ራሱን፡ሸክም፡ሊሸከም፡ነውና።
  6፤ነገር፡ግን፥ቃሉን፡የሚማር፡ከሚያስተምረው፡ጋራ፡መልካምን፡ነገር፡ዅሉ፡ይከፋፈል።

  ReplyDelete
 20. ኤፌሶን፥ምዕራፍ፡4።30-32
  30፤ለቤዛም፡ቀን፡የታተማችኹበትን፡ቅዱሱን፡የእግዚአብሔርን፡መንፈስ፡አታሳዝኑ።
  31፤መራርነትና፡ንዴት፡ቍጣም፡ጩኸትም፡መሳደብም፡ዅሉ፡ከክፋት፡ዅሉ፡ጋራ፡ከእናንተ፡ዘንድ፡ይወገድ።
  32፤ርስ፡በርሳችኹም፡ቸሮችና፡ርኅሩኆች፡ኹኑ፥እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡በክርስቶስ፡ይቅር፡እንዳላችኹ፡ይቅር፡ ተባባሉ።

  ReplyDelete
 21. የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡6።14-15
  14፤ለሰዎች፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡ብትሉ፥የሰማዩ፡አባታችኹ፡እናንተን፡ደግሞ፡ይቅር፡ይላችዃልና፤
  15፤ለሰዎች፡ግን፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡ባትሉ፥አባታችኹም፡ኀጢአታችኹን፡ይቅር፡አይላችኹም።

  ReplyDelete
 22. 1ኛ፡ዮሐንስ፥ምዕራፍ፡2።9-11
  9፤በብርሃን፡አለኹ፡የሚል፡ወንድሙንም፡የሚጠላ፡እስከ፡አኹን፡በጨለማ፡አለ።
  10፤ወንድሙንም፡የሚወድ፡በብርሃን፡ይኖራል፡ማሰናከያም፡የለበትም፤
  11፤ወንድሙን፡የሚጠላ፡ግን፡በጨለማ፡አለ፥በጨለማም፡ይመላለሳል፥የሚኼድበትንም፡አያውቅም፥ጨለማው፡ዐይኖቹ ን፡አሳውሮታልና።

  ReplyDelete
 23. መዝሙር፡33፡12-14
  12፤ሕይወትን፡የሚፈቅድ፡ሰው፡ማን፡ነው፧በጎንም፡ዘመን፡ለማየት፡የሚወድ፧
  13፤አንደበትኽን፡ከክፉ፡ከልክል፥ከንፈሮችኽም፡ሽንገላን፡እንዳይናገሩ።
  14፤ከክፉ፡ሽሽ፡መልካምንም፡አድርግ፤ሰላምን፡ሻ፥ተከተላትም።

  ReplyDelete
 24. 1ኛ፡ጴጥሮስ፥ምዕራፍ፡3።10-17
  10፤ሕይወትን፡ሊወድ፡መልካሞችንም፡ቀኖች፡ሊያይ፡የሚፈልግ፡ሰው፥ምላሱን፡ከክፉ፡ከንፈሮቹንም፡ተንኰልን፡ከ መናገር፡ይከልክል፤
  11፤ከክፉ፡ፈቀቅ፡ይበል፥መልካምንም፡ያድርግ፥ሰላምን፡ይሻ፡ይከተለውም፤
  12፤የጌታ፡ዐይኖች፡ወደ፡ጻድቃን፡ናቸውና፥ዦሮዎቹም፡ለጸሎታቸው፡ተከፍተዋል፥የጌታ፡ፊት፡ግን፡ክፉ፡ነገርን ፡በሚያደርጉ፡ላይ፡ነው።
  13፤በጎንም፡ለማድረግ፡ብትቀኑ፡የሚያስጨንቃችኹ፡ማን፡ነው፧
  14፤ነገር፡ግን፥ስለ፡ጽድቅ፡እንኳ፡መከራን፡ብትቀበሉ፡ብፁዓን፡ናችኹ።ማስፈራራታቸውንም፡አትፍሩ፡አትናወጡ ም፥
  15፤ዳሩ፡ግን፡ጌታን፡ርሱም፡ክርስቶስ፡በልባችኹ፡ቀድሱት።በእናንተ፡ስላለ፡ተስፋ፡ምክንያትን፡ለሚጠይቋችኹ ፡ዅሉ፡መልስ፡ለመስጠት፡ዘወትር፡የተዘጋጃችኹ፡ኹኑ፥ነገር፡ግን፥በየዋህነትና፡በፍርሀት፡ይኹን።
  16፤በክርስቶስ፡ያለውን፡መልካሙን፡ኑሯችኹን፡የሚሳደቡ፡ሰዎች፡ክፉን፡እንደምታደርጉ፡በሚያሙበት፡ነገር፡እ ንዲያፍሩ፡በጎ፡ኅሊና፡ይኑራችኹ።
  17፤የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡እንዲህ፡ቢኾን፥ክፉ፡ስለ፡ማድረግ፡ሳይኾን፡በጎ፡ስለ፡ማድረግ፡መከራን፡ብትቀበሉ ፡ይሻላችዃልና።
  _

  ReplyDelete
 25. ያዕቆብ፥ምዕራፍ፡4።11-12
  11፤ወንድሞች፡ሆይ፥ርስ፡በርሳችኹ፡አትተማሙ።ወንድሙን፡የሚያማ፡በወንድሙም፡የሚፈርድ፡ሕግን፡ያማል፡በሕግ ም፡ይፈርዳል፤በሕግም፡ብትፈርድ፡ፈራጅ፡ነኽ፡እንጂ፡ሕግን፡አድራጊ፡አይደለኽም።
  12፤ሕግን፡የሚሰጥና፡የሚፈርድ፡አንድ፡ነው፤ርሱም፡ሊያድን፡ሊያጠፋም፡የሚችል፡ነው፤በሌላው፡ግን፡የምትፈር ድ፡አንተ፡ማን፡ነኽ፧

  ReplyDelete
 26. 1ኛ፡ጴጥሮስ፥ምዕራፍ፡3።9-11
  9፤ክፉን፡በክፉ፡ፈንታ፡ወይም፡ስድብን፡በስድብ፡ፈንታ፡አትመልሱ፥በዚህ፡ፈንታ፡ባርኩ፡እንጂ፤በረከትን፡ልት ወርሱ፡ለዚህ፡ተጠርታችዃልና።
  10፤ሕይወትን፡ሊወድ፡መልካሞችንም፡ቀኖች፡ሊያይ፡የሚፈልግ፡ሰው፥ምላሱን፡ከክፉ፡ከንፈሮቹንም፡ተንኰልን፡ከ መናገር፡ይከልክል፤
  11፤ከክፉ፡ፈቀቅ፡ይበል፥መልካምንም፡ያድርግ፥ሰላምን፡ይሻ፡ይከተለውም፤

  ReplyDelete
 27. what happend to you? you have to believe.

  ReplyDelete
 28. The Holy spirit only points toward Jesus Christ!

  ReplyDelete