Monday, September 30, 2013

ከሰማይ ወረደ በተባለው መስቀል ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አባ እስጢፋኖስ ቃለመጠይቅ ሰጡ


ለሚያየው ምድራዊ የሆነውና በላዩ ላይ የሚገኘው የስነ ስቅለት ምስል ኦርቶዶክሳዊ ትውፊት የተከተለ አይደለም እየተባለ በመተቸት ላይ ያለው የገላንጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት የመጋቤ ሐዲስ ፍስሀ መስቀልን በተመለከተ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ መስከረም 18/2006 ዓ.ም. ከታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ አደረጉ፡፡ ሊቀጳጳሱ እንዳሉት ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ከወደቀበት መሬት ያነሡትና ወደቤተክርስቲያን እንዲገባ ያደረጉት እርሳቸው መሆናቸውን ገልጸው፣ “በወቅቱ ከመሬቱ ላይ እንዲነሳ እነርሱ (መስቀሉ ወረደ ያሉት ክፍሎች) ብዙም ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ እዚያው ላይ እያለ ቤተክርስቲያን እንዲሠራለት ነው የፈለጉት፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያን የሚሰራለት ከሆነም መስቀሉ መሬት ላይ ሆኖ አይደለም የሚቆፈረውና የግድ ወደ መቅደሱ መግባት አለበት አልናቸው፡፡” ብለዋል፡፡ ሲጀመርም “መስቀል ከሰማይ ወረደ” የተባለውን ድርሰት በድጋሚ የደረሱት (የመጀመሪያዎቹ ደራሲዎች ደብረሊባኖሶች ናቸው) እንዲህ ያለ ትርፍ ለማግኘት እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም እዚያው ጎረቤታቸው ታቦቷ ሕንጻ ካልተሠራልኝ አልገባ አለች ተብሎ ሕንጻ እንደተሠራላት እኛም በዚህ መንገድ ሕንጻ ማስገንባት እንችላለን በሚል ስሌት ይህን እንዳደረጉ መገመት አይከብድም፡፡


ጋዜጠኞቹ “መስቀሉ ሲነሣ ብርሃናማና የሚያቃጥል ነበረ፣ ብዙ ተአምራቶችም ታይተዋል በእርግጥ እነዚህ ነገሮች ነበሩ?” ሲሉ ላቀረቡላቸው ጥያቄም ሲመልሱ “ያቃጥል ነበር የሚለው እንደው የሚያቃጥል ቢሆን ኖሮ መቼ እናነሳው ነበር? አናነሳውም፡፡ እኔ እንደዛ መስሎኝ ነበር የሄድኩት እንጂ መነኮሳቱ ማንሳት ይችሉ ነበር፡፡ የሚያቃጥል ነበረ የሚያበራ ነበረ ምናልባት ጨለማ ሲሆን ታይቶ ይሆናል እንጂ እኛ ምንም አላየንም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አክለውም “በመሠረቱ መስቀሉ ያቃጥላል፤ ይፋጃል የሚባለው ሐሰት ነው፡፡ መስቀል ይፈውሳል እንጂ አያቃጥልም” ብለዋል፡፡

እዚህ ላይ አንድ ሀቅ መገለጥ አለበት፡፡ ነገሩ እውነት ከሆነ እግዚአብሔር ይህን “ተአምር” የሠራው ለምንድነው? ክብሩን ለመግለጥና ሕዝቡን ሊባርክ ነው ወይስ ሕዝቡን ሊቀጣ? ሕዝቡን ሊባርክ ከሆነ ማቃጠልና መፋጀት የሚባል ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ለቅጣት ከሆነ ግን አዎን ሊፋጅና ሊያቃጥል ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕነታቸው “ሐሰት ነው” ያሉት፡፡ ይሁን እንጂ በመስቀሉም ይሁን በሌላ መንገድ የሚፈውሰው ፈዋሹ እግዚአብሔር እንጂ ቁስ የሆነው መስቀል አይደለም፡፡   

አባ እስጢፋኖስ እንደዚህ አይነት ነገሮች ሲከሰቱ ችግሮች የሚፈጠሩበትን ምክንያት ሲያብራሩም “ቤተክህነት እውቅና ሳይሰጠው ቀድሞ ሕዝቡ እውቅና ይሰጠዋል፡፡ እኔ ሄጄ በነበረ ጊዜ ስለመስቀሉ አስተያየት ብሰጥ ኖሮ ምን አይነት ትርምስ ይፈጠር እንደነበር ትገነዘቡታላችሁ ብዬ አምናለሁ” ብለዋል፡፡ እውነት ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችን ትልቁ ችግር ቤተክርስቲያኗ በአስተምህሮዋና በሕጓ መሠረት ነገሮችን ሳትመረምር ሕዝቡ የተቀበለውንና እውቅና የሰጠውን ነገር በሲኖዶስ ሳታስወስን እያጸደቀች መጓዟ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ሲጫኑባት የኖሩት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርአቶችና ትምህርቶች በሲኖዶስ እውቅና የተሰጣቸው ሳይሆኑ አንዳንድ ነገሥታትና ሕዝቡ በጉልበትና በዕውቀት ላይ ባልተመሠረተ ባዶ ቅናት እውቅና የሰጧቸው ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ብዙ ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የደብረ ሊባኖሱ “ከሰማይ ወረደ” የተባለው መስቀል ብፁዕነታቸው እንዳሉት ሲኖዶስ ዕውቅና የሰጠው ነው ወይስ የገዳሙ መነኮሳት ያቀረቡለትን ድርሰት ሕዝቡ ተቀብሎ ዕውቅና የሰጠው ነው? ምላሹ ግልጽ ነው፡፡ ሲኖዶስ ጉዳዩን መርምሮ እውቅና የሰጠው ሳይሆን ሕዝቡ የሰጠውን ዕውቅና አጽድቆ ተከታይ ነው የሆነው፡፡ መሪ ሳይሆን ተከታይ የሆነ ሲኖዶስ ባለበት ሁኔታ ከዚህ የበለጠ አይጠበቅም፡፡ አሁን እየተባለ ካለው አንጻር ግን ሲኖዶሱ እንዲህ ባሉ ነገሮች ላይ የመሪነቱን ሚና ከተጫወተና በተገቢው መንገድ ማጣራት አድርጎ ስሕተትን ስሕተት፣ እውነትን እውነት ማለት ከጀመረ ቤተክርስቲያኗ ተስፋ አላት ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ በነካ እጃችሁ የደብረ ሊባኖሱንም “ከሰማይ የወረደ መስቀል” አብራችሁ እንድታዩት ሐሳብ እናቀርባለን፡፡

እርግጥ እንዲህ ያለ አስተያየት መስጠትና ይህ መስተካከል አለበት ሲባል “መናፍቅ ተሐድሶ” የሚል ስም እንደሚያሰጥ ግልጽ ነው፡፡ አባ ኦጢፋኖስ “እኔ ሄጄ በነበረ ጊዜ ስለመስቀሉ አስተያየት ብሰጥ ኖሮ ምን አይነት ትርምስ ይፈጠር እንደነበር ትገነዘቡታላችሁ ብዬ አምናለሁ” ብለዋል፡፡ እውነት ነው ካዩትና ካስተዋሉት ተነሥተው ሐሳብ ቢሰጡ የነመጋቤ ሀዲስ ፍስሀን ህልም ማጨናገፍ ስለሚሆን እርስዎ “ትርምስ” ቢሉትም “ፀረ መስቀል እና መናፍቅ ጳጳስ” ይባሉ ነበርና እንኳንም በግልዎ አስተያየት ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡

ሊቀጳጳሱ አክለው እንደተናገሩት ሕዝቡ “እውነት ነው” እና “አይደለም ሐሰት ነው” በሚሉ ሁለት ጎራዎች የተከፈለ ቢሆንም፣ በመስቀሉ ዙሪያ ተወያይቶ ሲኖዶሱ ውሳኔ ስለሚሰጥ ሕዝቡ በያለበት ሆኖ በትዕግሥት እንዲጠብቅ አስገንዝበዋል፡፡ ጉዳዩ እየተጣራ ሲሆን መስቀል ወረደ ባዮቹ ከምን ተነሥተው እንዲህ እንዳሉ ማጣራት እንደሚደረግና “ውሸት ሆኖ ከተገኘ ሰዎቹ ተጠያቂ ሊሆኑበት ይችላል” ብለዋል፡፡ ይህ ተገቢና ለሌሎችም ተመሳሳይ ድርጊት ለሚፈጽሙ ሐሳውያን ትልቅ ትምህርት የሚሰጥና የቅዱስ ሲኖዶስን ተደማጭነትና የመሪነት ሚናም ከፍ የሚያደርግ ነው፡፡ ነገር ግን ሲኖዶስ አሁን የተከሠተውን ብቻ ሳይሆን ወደኋላ መለስ ብሎ ብዙ ነገሮችን ሊመረመርና የተሳሳቱ አስተምህሮዎችንና ሥርአቶችን ሊያስተካክል ይገባል፡፡ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ሁሉ እውነት ላይሆን ይችላልና፡፡

አባ እስጢፋኖስ በሰጡት ምላሽ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚያስነሡ ሁለት ነጥቦች ያሉ ይመስለናል፡፡ አንደኛው የመስቀሉ ከሰማይ መውረድ አለመውረድ ባልተጣራበት ሁኔታ የዚህ መስቀል ፎቶ መቸብቸቡ ስሕተት የለውም ማለታቸው ነው፡፡ በትክክል ከሰማይ መውረዱ ያልተጣራውን መስቀል ከሰማይ እንደወረደ ተቆጥሮ እንዲቸበቸብ ማድረግ ሙስና አይሆንምን? ሕዝብን ማሳሳትስ አይሆንምን? ነው ወይስ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ነው ነገሩ? ይህ ትክክል ነው ብሎ ማመን ያስቸግራል፡፡

ሁለተኛው በመስቀሉ ላይ ከተነሣው ጥያቄ አንዱ የኦርቶዶክስ አይደለም የሚል ነው፡፡ አባ እስጢፋኖስ ይህን በተመለከተ ሲመልሱ “ለነገሩ መስቀል መስቀል ነው፡፡ ይሄ የእገሌ ያ የእገሌ ነው የሚባል አይደለም” በማለታቸው እውነት መስክረዋል፡፡ መስቀል የክርስቲያኖች ሁሉ አርማና የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያሳስብ ምልክት ነውና፡፡ ይሁን እንጂ “መስቀሉ ላይ የሥነ ስቅለት ምስል አለበት፡፡ ይሄ አሣሣል የእኛ የኦርቶዶክሳውያን አይደለም የሚለውን የሲኖዶስ ውሳኔ የሚያረጋግጠው ይሆናል፡፡” የተባለው ግን ሌሎች ጥያቄዎችን ያስነሣል፡፡ መስቀሉ ከሰማይ ላለመውረዱ አንዱ ማስረጃ የኦርቶዶክስን ትውፊት ተከትሎ ያልተቀረጸ ምስል መሆኑ ነው የሚል አንድምታም አለው፡፡ እግዚአብሔር አላደረገውም እንጂ ይህን መስቀል ከሰማይ ልኮት ቢሆን “አይ ይህ በትውፊታችን መሠረት የተሠራ ምስል አይደለምና አንቀበልም” ብላችሁ ልትጥሉት ነው ማለት ነው? ደግሞስ እነመጋቤ ሀዲስ የሚያገኙትን የአመፅ ትርፍ እንጂ የቤተክርስቲያኒቱ ትውፊት ሳያሳስባቸው ቀርቶ በሌሎች ትውፊት መሠረት የተሠራውን ምስል የያዘውን መስቀል “ከሰማይ ወረደ” አሉን እንጂ በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት የተሠራ ምስል ቢሆን ኖሮ፣ መስቀሉ ከሰማይ ለመውረዱ አንዱ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ ነበር ማለት ነው? ምንም ይሁን ምን የእኛ ትውፊት እኮ እዚሁ አገር በቀል እንጂ ሰማያዊ አይደለም፡፡ የሚሠራውም በእኛ ዘንድ ለእኛ ብቻ እንጂ በሰማይ የጸደቀ አይደለም፡፡ ስለዚህ ባይወርድም እንኳ የመስቀሉን “ከሰማይ መውረድ” ትክክለኛነት በእኛ ትውፊታዊ የምስል አቀራረጽ ለመመዘን ማሰብ ከመነሻው ስህተት ነው፡፡ አሁንም ሲኖዶሱ በማጣራቱ ሂደት በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ጉዳዩን ሊመረመርና እንደአስፈላጊነቱም ሳይንሳዊ ማጣራትም እንዲደረግ መፍቀድ አለበት፡፡

   


9 comments:

 1. May the grace of God be on this bishop. His Eminence astonished me stressing the importance of not believing on all what people said and was imperative to wait and hear from the Church what its finding was. The Church needs to charge up and filter out all thse dubious man made stories. I have these problems of believing some gedels and tamers were truely Devine related. To me they were fabricated by some ill advised monks and priests. It was all my parayer that one day our church do away with these and go the right direction.

  ReplyDelete
 2. ሰሞኑን በተለያዩ የማህበረሰብ ገጾች መናፍቃን የኦርቶዶክስን አኩሪ ታሪኮች እና ጽኑ እምነት ለማጣጣል ዘመቻ መያያዛቸውን ሳይ ይህ የአባቶች ተረት ትዝ አለኝ፡-

  ..... አንድ ጦጣ የሰው ማሳ ገብታ ስታጠፋ ገበሬው ያገኛትና የያዘውን ገጀራ ሲወረውርባት ጅራቷ ላይ በማረፉ ጅራቷ ተቀንጥሶ መሬት ሲቀር እሷ ግን ቀሪ አካሏን ይዛ እግሬ አውጭኝ ትላለች፡፡ ጦጣዋ ወደ ባልደረቦቿ ከመቀላቀሏ በፊት ጅራቷ ቆራጣ በመሆኗ የማን ተቆርጦ የማን ይተርፋል የሚል የምቀኝነት ሐሳብ አስባ፡ አንድም ጅራተ ቆራጣነቷ ምልክት ሆኖ ገበሬው ተከታትሎ እንዳይዛት በመስጋት የተንኮል ስብከት አዘጋጀች….
  …እንዳይታይባት በተቆረጠው ጅራቷ ላይ በመቀመጥ ከፊት ለፊት በተፈጥሮ የሚመስሏትን ቢጤዎቿን እንዲሰበሰቡ በማድረግ ስለጅራት መጥፎነት መስበክ ጀመረች ‹‹ይህ ጅራት የሚባል የተረገመ አካል በላይችን ላይ እንደጥገኛ ተንጠልጥሎ እንሩጥ ስንል አያስሮጠን እናምልጥ ስንል አያስመልጠን የበላነውን እየተሻማ እንዲሁ ሲያንገላታን ይኖራል ለምን አናስወግደውም?›› ብላ የማስመሰል ስብከቷን ስታወርድባቸው የተደገሰላቸውን ያላወቁ ቢጤዎቿ ነገሩን አምነው ተቀበሏትና ወደርሷ በመቅረብ ጅራታቸውን እየዞሩ አስረከቧት፡፡ እሷም ገምዳ ገምዳ ከከረከመችላቸው በኋላ በመካከላቸው ተቀላቅላ ተሰወረች አሉ፡፡

  *****ፊት የትም ሲያውደለድሉ መቆረጥ፣ኋላ ደግሞ የራስ እኩያ ለማድረግ ማስቆረጥን ልብ ይሏል፡፡ ዛሬም እየሆነ ያለው የሄው ነው*****

  መስቀል አያስፈልግም፣ታቦት አያስፈልግም ፣ቤተመቅደስ አያሰፈልግም፣መስቀል ክብር አይገባውም ፣ቅዱሳን አያስፈልጉም….ወዘተ እያሉን ሊያሞኙን የሚሞክሩ ጅራተ ቆራጦች ታሪክ አልባዎች የእኛን ቤተ መቅደስ ከእነሱ ኦና /ባዶ/ አዳራሽ ጋር ለማመሳሰል ነውና ወገኔ የሆንክ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጅ ሆይ፣ ነቅተህ ሃይማኖትህን ከነስርአቱ ጠብቅ፡፡ እኛ ቆራጣ ታሪክ የለንም፡፡

  መልካም የመስቀል በዓል ይሁንልን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. *****ፊት የትም ሲያውደለድሉ መቆረጥ፣ኋላ ደግሞ የራስ እኩያ ለማድረግ ማስቆረጥን ልብ ይሏል፡፡ ዛሬም እየሆነ ያለው የሄው ነው*****

   መስቀል አያስፈልግም፣ታቦት አያስፈልግም ፣ቤተመቅደስ አያሰፈልግም፣መስቀል ክብር አይገባውም ፣ቅዱሳን አያስፈልጉም….ወዘተ እያሉን ሊያሞኙን የሚሞክሩ ጅራተ ቆራጦች ታሪክ አልባዎች የእኛን ቤተ መቅደስ ከእነሱ ኦና /ባዶ/ አዳራሽ ጋር ለማመሳሰል ነውና ወገኔ የሆንክ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጅ ሆይ፣ ነቅተህ ሃይማኖትህን ከነስርአቱ ጠብቅ፡፡ እኛ ቆራጣ ታሪክ የለንም፡፡

   Delete
 3. ሰሞኑን በተለያዩ የማህበረሰብ ገጾች መናፍቃን የኦርቶዶክስን አኩሪ ታሪኮች እና ጽኑ እምነት ለማጣጣል ዘመቻ መያያዛቸውን ሳይ ይህ የአባቶች ተረት ትዝ አለኝ፡-

  ..... አንድ ጦጣ የሰው ማሳ ገብታ ስታጠፋ ገበሬው ያገኛትና የያዘውን ገጀራ ሲወረውርባት ጅራቷ ላይ በማረፉ ጅራቷ ተቀንጥሶ መሬት ሲቀር እሷ ግን ቀሪ አካሏን ይዛ እግሬ አውጭኝ ትላለች፡፡ ጦጣዋ ወደ ባልደረቦቿ ከመቀላቀሏ በፊት ጅራቷ ቆራጣ በመሆኗ የማን ተቆርጦ የማን ይተርፋል የሚል የምቀኝነት ሐሳብ አስባ፡ አንድም ጅራተ ቆራጣነቷ ምልክት ሆኖ ገበሬው ተከታትሎ እንዳይዛት በመስጋት የተንኮል ስብከት አዘጋጀች….
  …እንዳይታይባት በተቆረጠው ጅራቷ ላይ በመቀመጥ ከፊት ለፊት በተፈጥሮ የሚመስሏትን ቢጤዎቿን እንዲሰበሰቡ በማድረግ ስለጅራት መጥፎነት መስበክ ጀመረች ‹‹ይህ ጅራት የሚባል የተረገመ አካል በላይችን ላይ እንደጥገኛ ተንጠልጥሎ እንሩጥ ስንል አያስሮጠን እናምልጥ ስንል አያስመልጠን የበላነውን እየተሻማ እንዲሁ ሲያንገላታን ይኖራል ለምን አናስወግደውም?›› ብላ የማስመሰል ስብከቷን ስታወርድባቸው የተደገሰላቸውን ያላወቁ ቢጤዎቿ ነገሩን አምነው ተቀበሏትና ወደርሷ በመቅረብ ጅራታቸውን እየዞሩ አስረከቧት፡፡ እሷም ገምዳ ገምዳ ከከረከመችላቸው በኋላ በመካከላቸው ተቀላቅላ ተሰወረች አሉ፡፡

  *****ፊት የትም ሲያውደለድሉ መቆረጥ፣ኋላ ደግሞ የራስ እኩያ ለማድረግ ማስቆረጥን ልብ ይሏል፡፡ ዛሬም እየሆነ ያለው የሄው ነው*****

  መስቀል አያስፈልግም፣ታቦት አያስፈልግም ፣ቤተመቅደስ አያሰፈልግም፣መስቀል ክብር አይገባውም ፣ቅዱሳን አያስፈልጉም….ወዘተ እያሉን ሊያሞኙን የሚሞክሩ ጅራተ ቆራጦች ታሪክ አልባዎች የእኛን ቤተ መቅደስ ከእነሱ ኦና /ባዶ/ አዳራሽ ጋር ለማመሳሰል ነውና ወገኔ የሆንክ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጅ ሆይ፣ ነቅተህ ሃይማኖትህን ከነስርአቱ ጠብቅ፡፡ እኛ ቆራጣ ታሪክ የለንም፡፡

  መልካም የመስቀል በዓል ይሁንልን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በዚህ ቃለመጠይቅ እጅግ ነው የማመሰግንዎ፡፡ እግዚአብሔር እንደእርስዎ ደፍረው የሚናገሩና ስህተቶችን የሚያርሙ አባቶችን ያብዛልን፡፡ አባት ማለት እንዲህ ደፍሮ የሚናገር ነው እንጂ ከሰው አልጣላም በሚል ተሸብቦ በዝምታ ሐሰትን የሚደግፍ አይደለም፡፡

   Delete
 4. This is a crime against Orthodox Christians. Should put the guys in jail.
  Ain't nothing but a crab. What ever they smoked had to do with this nonsense. I felt sorry for those victimized by this hoax. Ironically the people you have trusted delivered you to evil.We all ought to pray that God deliver us from evil.

  ReplyDelete
 5. Some of us are really opssesed with thesse ludicrous attacks of Thadesso, Menafeke etc, but our church is moving one step ahead and two steps backward. Now a days the church has to start and denounce all these man made Voodo tales. The way things running now have attributed for many to abandon our church. The exodus to the protestant church is at alarming fequency. We need to stop the bleeding and quit blaming one another. In the long history of our church there is this bad habbit of taking any monk"s and bahatwi's account as the devine one. Often this does not sink in to the mind of inqusitive young members. The church needs to set a strategy at least to stop the defection.

  ReplyDelete
 6. Salvation begins with oneself. One needs to clean himself before he or she acuses other. Now relegion particularly ETOC is a race to judge someone. I t is becoming fasionable rather than practicing the dos of christians. The church suffers all these crisis from the synods to Senbet Temehertbets. Judgement is God's only. Ranting He is Thadesso or he is Mahibere kidusan leave you nothing. The grace of God keeps its distance away from you. Embrace Love!

  ReplyDelete
 7. what is going on in this church leaders, so embarrassing for our church in this century kind of untrue miracle happened. every body running for lovely money instead of save sinner life. please do not cheat in the of Our God. it doesn't take you any where and not blessing............

  ReplyDelete