Monday, October 21, 2013

የ32ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቀቀ የአቋም መግለጫው ማኅበረ ቅዱሳን ሒሳቡን በቤተክህነት ሞዴላሞዴል እንዲሠራ ያዛል


ባለፈው ሳምንት ሲካሄድ የሰነበተው የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ቅዳሜ ጥቅምት 09/2006 ዓ.ም. ከሰዓት በፊት ተጠናቀቀ፡፡ በአቋም መግለጫው ላይ ከተነሡት ነጥቦች አንዱ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳንን የተመለከተ ሲሆን፣ የአቋም መግለጫውም የሚከተለው ነው፡፡
“ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉት ማእከላትና የግንኙነት ጣቢያዎች በየሀገረ ስብከቱ እያበረከተ ያለው ሁለንተናዊ ልማት ጉባኤው ከየሪፖርቱ በማወቁ አገልግሎቱን ተቀብሎታል። ከዚህ አንጻር እየሰራበት ያለውን የገቢና የወጪ ሂሳብ በቤቱ የቁጥጥር ሥርዓት እያስመረመረ የቤቱን ሞዴላሞዴሎች እየተገለገለ ማዕከልንም በመጠበቅ የቤተክርስቲያንን መብትና ሃብት ሃይማኖትና ሥርዓት እንዲጠብቅ መልካም ምሳሌ እየሆነ አገልግሎቱን በጥበብ እንዲቀጥል ጉባኤው ያስገነዝባል። ከዚህም ጋር ማኅበሩ አቅጣጫ ያልጠበቀ አሰራር እንዳይታይበት በቅዱስ ሲኖዶስ የማስተካከያ መመሪያ እንዲሰጠው ጉባኤው ያሳስባል።”
ከዚህ የአቋም መግለጫ መረዳት እንደሚቻለው በስብሰባው ላይ ማኅበሩ ሂሳቡን ባለማስመርምሩ ትችት ተሰንዝሮበት የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ የማኅበሩ ተወካይ የነበረው አባልም “ቤተ ክህነቱ የተመሰከረለት የሂሳብ አያያዝ የሌለው በመሆኑ ነው ለቤተክህነቱ የማናስመረምረው” ሲል ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ያለውን ንቀት አሳይቶ ስለነበር እየሰራበት ያለውን የገቢና የወጪ ሂሳብ በቤቱ የቁጥጥር ሥርዓት እያስመረመረ የቤቱን ሞዴላሞዴሎች እየተገለገለ” ሥራውን እንዲያከናውን መመሪያ ተሰጥቶታል፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበሩ ይህን በቀላሉ ይተገብረዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ከዚህ ቀደምም ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር ያጋጨው ይኸው “ሒሳብህን አስመርምር” የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡ ማኅበሩ ግን ጥያቄውን በአዎንታዊ መንገድ ከመቀበል ይልቅ ወደመቃወምና አባ ሠረቀን ወደመክሰስ ነው የሄደው፡፡ ይሁን እንጂ ወትሮም ቢሆን ሕገወጥ ሆኖ መቀጠል ስለማይቻል፣ ያንጊዜ ለተነሳበት የሂሳብህን አስመርምር ጥያቄ ሌላ መልክ በመስጠት ሊያልፈው ቢሞክርም ጥያቄው አሁንም መነሣቱ፣ በዚህ ስብሰባ ላይ በከፍተኛ ድጋፍ ውሳኔው መተላለፉና በአቋም መግለጫ መጠቀሱ ለማኅበሩ ትልቅ ሽንፈት ነው የሚሆንበት፡፡ ማኅበሩ የገንዘብ አቅሙን ከዚህ በበለጠ ለማጠናከርና ጡንቻውን ለማፈርጠም ከሚያደርገው እንቅስቃሴና ቤተክርስቲያን ውስጥ “ተሐድሶ መናፍቃን” በሚላቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ለሚፈጽማቸው ጥቃቶች ማካሄጃና ለሌሎቹም ሕገወጥ ድርጊቶቹ ከሚያወጣቸው ወጪዎች አንጻር በቤተክህነት ሞዴላሞዴሎች እንዲጠቀም መደረጉ በቤተ ክርስቲያን ስም እየሰበሰበ ያለውን ገንዘብ ለራሱ ድብቅ ዓላማ ሳይሆን መልሶ ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንዲያውል ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል። 
   
ይህ ጉዳይ ማኅበሩ በተለያየ አጋጣሚ ለሽብር ስራ እና ለግል መጠቀሚያ የሚያውላቸውን ገንዘብ የአወጣጥ ሂደት የመግታት አቅም ያለው በመሆኑ በማኅበሩ አመራር ዘንድ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም። ከአባ ሠረቀብርሃን ጀምሮ ሂሰባችሁ በታወቀ መንገድ ይንቀሳቀስ የሚሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን የተለያየ ስም በመፈረጅ ባለ በሌለ ሃይሉ ያሳድድበት የነበረው ዋነኛ ጉዳይ ይኸው ሂሳብ አወጣጣህ ህጋዊ ሂደት ይኑረው የሚለው ጉዳይ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ከዚህ እና መሰል ስጋዊ አመለካከቱ በመነሳትም ማኅበሩ ይህን ውሳኔ በጸጋ ከመቀበል ይልቅ ውሳኔው እንዲወሰን ያደረጉና ያስወሰኑ የሚላቸውን ግለሰቦች ለማጥፋት በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀሱ እና ውሰኔውንም ላለመተግበር ማንገራገሩ የማይቅር መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ። በባያብል አማካይነት እንኳን በደቡብ-ምዕራብ ሸዋ ሥራ አስኪያጅ ላይ የተሞከረው በመኪና ገጭቶ የመግደል ሙከራ ለዚህ አንዱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡
ሌላው ነጥብ ከደቡብ-ምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት የቀረበበትን ችግር ፈጣሪነቱን የተመለከተ ሪፖርት በመቃወም ባልተለመደ ሁኔታ ስብሰባ ረግጦ በመውጣቱ ምክንያት በማኅበሩ ላይ ለተወሰደው አቋም ሌላ መነሻ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ይመስላል “ማዕከልንም በመጠበቅ የቤተክርስቲያንን መብትና ሃብት ሃይማኖትና ሥርዓት እንዲጠብቅ መልካም ምሳሌ እየሆነ አገልግሎቱን በጥበብ እንዲቀጥል ጉባኤው ያስገነዝባል።” የተባለው፡፡ ይህም ነጥብ የሚያሳየው ማኅበሩ በሚሰራው ስራ መልካም ምሳሌነት የጎደለው መሆኑን ነው፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን ማእከል አለመጠበቅና በየደረሰበት ራስ ለመሆን መሞከሩ ቀድሞ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር ያጋጨው የነበረው ጉዳይ አሁን ላይ አድጎ በየሀገረ ስብከቱ ከቤተክህነት ሃላፊዎችና አመራሮች ጋር ያላትመው ይዟል፡፡ በቀጣይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ማኅበሩ ሊያደርግ የሚገባውን ሁሉ በብልሀትና በጥበብ ካላደረገና በማንአለብኝት እንዳሻኝ እሆናለሁ ቢል የእድሜ ገመዱን በራሱ የሚበጥስ መሆኑን የአቋም መግለጫው ያስረዳል ይላሉ ተንታኞች፡፡
በመጨረሻም የአቋም መግለጫው ማኅበሩ አቅጣጫ የመሳት ነገር እንደታየበት የጠቈመበት ሁኔታ አለ፡፡ “ከዚህም ጋር ማኅበሩ አቅጣጫ ያልጠበቀ አሰራር እንዳይታይበት በቅዱስ ሲኖዶስ የማስተካከያ መመሪያ እንዲሰጠው ጉባኤው ያሳስባል። ማኅበሩ አቅጣጫ የሳተው በምን ጉዳይ ነው ቢባል በዋናነት ላይ ላዩን ሃይማኖተኛ ወይም መንፈሳዊ ማኅበር ነኝ እያለ ውስጥ ውስጡን በሚያራምደው ፖለቲካዊ አቋምና በሚታይበት የአክራሪነት ዝንባሌ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ለማቅ ትልቅ ሽንፈትን ያጎናጸፉ ክስተቶች ናቸው፡፡ በዚህ ቤተክህነቱን ተቆጣጥሬዋለሁ ብሎ በሚያምንበት ወቅት እንዲህ ያለውን ውሳኔ ማስተናገዱ ለማኅበሩ ቀኑ እየጨለመ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ውሳኔውን ለማለዘብና ጉዳዩ ወደ ሲኖዶስ ቀርቦ እንዲወሰንበት ቀርቦ የነበረውን ሐሳብ በአሁኑ ወቅት ከማቅ ጋር ዓይንና ናጫ የሆኑት አባ ጢሞቴዎስ በጽኑ በመቃወም እዚህ ሁሉም የሲኖዶስ አባል ባለበት የታየ ጉዳይ በመሆኑ ይኸው ውሳኔ እንዲጸና ያቀረቡት ሐሳብ በደማቅ ጭብጨባ ተደግፎ ውሳኔው እንዲጸና ተደርጓል፡፡ ምናልባት እንዲህ ባይሆን ኖሮ ማቅ እንደለመደው የሲኖዶስ አባላትን ለመጠምዘዝ ጥረት ሊያደርግ ይችል ይሆናል የሚሉ ግምቶች አሉ፡፡ 
በሌላም በኩል የማኅበረ ቅዱሳንን ክፉ አሠራርና አካሄድ በመቃወም ከጸኑት አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በስብሰባው መዝጊያ ዕለት ለመናገር ጠይቀው ወደመድረኩ ከሄዱ በኋላ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራአስኪያጅና የጉባኤው ሰብሳቢ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጊዜ የለም በሚል ምክንያት እንዳይነጋሩ የከለከሏቸው ሲሆን፣ በመጨረሽ ላይ የተናገሩት ፓትርያርኩ ግን በንግግራቸው መካከል ከዚህ ጋር የተያያዘ ትችት በጠቅላይ ስራ አስኪያጁ ላይ ሰንዝረዋል፡፡ ፓትርያርኩ እንዳሉት እንዲህ ዓይነቱ ልማድ (ሰው እንዳይናገር ማፈን) ጥሩ አለመሆኑን ጠቅሰው፣ “ሰው ኅሊናው እንዳይናገር ከታፈነ ክፉ ነገር ነው የሚያስበው፡፡ ምክንያቱም ያ በህሊናው የተሰበሰበውን ነገር ካላወጣው ወደክፉ ነገር ይሄዳል፤ ክፉ ነገር ያስባል፡፡ ሲሆን ሲሆን ያ የተነገረው ሁሉ ሊፈጸም ይችላል፡፡ ካልተፈጸመ ደግሞ at least ቢያንስ ተናግሮታል፡፡ ከህሊናው ወጥቷል፡፡ ስለዚህ ይነፍስለታል፡፡ … የህሊና ነጻነት እግዚአብሔር የሰጠን ሲሆን ሰው ሁሉ ነጻነት ያላት ህሊና በሕይወቱ አሳድሮበታል፡፡ ያቺ እግዚአብሔር የሰጠን የነጻነት ህሊና መታፈን የለባትም፡፡ መውጣት አለባት መናገር አለብን፡፡”  ብለዋል፡፡

ከጉባኤው ጋር የተያያዘ ሌላ ዘገባ አለን በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን፡፡

15 comments:

 1. የቤተክርስቲያንን መብትና ሃብት ሃይማኖትና ሥርዓት እንዲጠብቅ መልካም ምሳሌ እየሆነ አገልግሎቱን በጥበብ እንዲቀጥል ይህ ማለት እናንተን እየተዋጋ እንዲቀጥል ማለት ነው ድንቅ የአቋም መግለጫ ነው፡፡ እናንት ማፈሪያዎች እንግዲህ ምን ትሆኑ?

  ReplyDelete
 2. endhe new enji. txs

  ReplyDelete
 3. What's wrong with this if MK uses Betekihnet reciepts instead of their own. I couldn't see any strange thing. But, you the writer of this article pls don't pretend as if orthodox follower. As I can understand "ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉት ማእከላትና የግንኙነት ጣቢያዎች በየሀገረ ስብከቱ እያበረከተ ያለው ሁለንተናዊ ልማት ጉባኤው ከየሪፖርቱ በማወቁ አገልግሎቱን ተቀብሎታል።" this is more than enough to show how the general assembly accepted the service of MK. You guys are just accusing MK with out any tangible evidence. If you see it from spirtual point of view their service is the most necessary for the current church specially preventing you guys (tehadiso) from altering the base of our fathers religion.
  I would simply say "ሲያሳድዷችሁና ሲነቅፏችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ፡፡ ማቴ 5፡11" . Please MK members and supporters don't be confused with anti-orthodox writers.
  God bless our laity and Ethiopia!

  ReplyDelete
 4. This is a positive sign. Hopfully the red army type approch will stop by MK leaders now. By the way, today's Sunday School Choirs came to exist through a hard struggle of his Emmenence Abune Melketsedek,then Leque Seltanat Habtemariam. He was balmed for allowing females to join the choir as it was believed a reformation of Orthodox ( Sete tekedese malet newe). .Just making a point for ardent opponent of Thadesso.

  ReplyDelete
 5. the Almighty God had done thies on His time.and the prayer of ouf beloved fathers and brotheres are now heard.we love you Mahberekidusan but we hate your evil act.

  ReplyDelete
 6. Doro betalem Terewan.Yale MK yemtawekut neger yelemen??????Why dont u report the whole Gubae?Tasazenalachehu.Egziabeher Ayene llebonacheun yekfetlachehu.

  ReplyDelete
 7. “ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉት ማእከላትና የግንኙነት ጣቢያዎች በየሀገረ ስብከቱ እያበረከተ ያለው ሁለንተናዊ ልማት ጉባኤው ከየሪፖርቱ በማወቁ አገልግሎቱን ተቀብሎታል።
  yes that's very true. keep moving forward mk!

  ReplyDelete
 8. WERDETEN ENDE YELEBESACHEU. AMESEGOCH.TEMELEU NESEHA GEBU. BERE WOLED ATEBELU. ATWASU. WE LOVE , WE DIE, WE TRUST MAHEBERE KIDUSAN. MEFENDAT TCHLALACHEU.

  ReplyDelete
 9. ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉት ማእከላትና የግንኙነት ጣቢያዎች በየሀገረ ስብከቱ እያበረከተ ያለው ሁለንተናዊ ልማት ጉባኤው ከየሪፖርቱ በማወቁ አገልግሎቱን ተቀብሎታል። ከዚህ አንጻር እየሰራበት ያለውን የገቢና የወጪ ሂሳብ በቤቱ የቁጥጥር ሥርዓት እያስመረመረ የቤቱን ሞዴላሞዴሎች እየተገለገለ ማዕከልንም በመጠበቅ የቤተክርስቲያንን መብትና ሃብት ሃይማኖትና ሥርዓት እንዲጠብቅ መልካም ምሳሌ እየሆነ አገልግሎቱን በጥበብ እንዲቀጥል ጉባኤው ያስገነዝባል። ከዚህም ጋር ማኅበሩ አቅጣጫ ያልጠበቀ አሰራር እንዳይታይበት በቅዱስ ሲኖዶስ የማስተካከያ መመሪያ እንዲሰጠው ጉባኤው ያሳስባል። ያልገባኝ ግን አሁን በሞዴላ ሞዴል መጠቀሙ ይሄ ድል ነው ለናንተ ምነው ወንድሞቻችሁ መናፍቃን የዲያብሎስ ልጆች በየሀገረ ስብከቱ የሰሩትን ሥራ አባቶች ያገሪቡትን አላቀረባችሁ አሁን ማን የሙት እናንተ መንፈሳዊ ናችሁ ምንፍቅና ምን ያህል የከፋ መጥፎ እንደሆነ እያየሁ ያለሁት በናንተ ነው ማፈሪያ የሞዴላ ሞዴል መዘገብ ምንድ ነው ለምን ወደ በረታች አትመለሱም ምንም አልተሳካላችሁም ያንን የመናፍቃን ብር መብላት ብቻ ሙቶች ናችሁ ነፍስ ይማር ብለናል

  ReplyDelete
 10. ብዙ ጊዜ ጽሑፋችሁን እመለከታለሁ አብዛኛውን ጊዜ ስመለከተው ግን አንድን ማኅበር በመቃወም በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ም ብዥታን ለመፍጠር ሆን ብሎ በፕላን የሚካሄድ ለመሆኑ ምንም አጠራጣሪ አይደለም። የአብዛኛው አቀራረብ በእነውተኛነቱ ሚዛን ሲታይ ግን በጣም ዝቅተኛ ነው። ያቀረባችሁት ዘገባ በራሱ ግራ የተጋባና የአጻጻፍ እውቀት ያነሰው ነው። ለወደፊት ግን ውሸትም እንኳ ቢሆን በተስተካከለ አማርኛ ብትጽፉት ለጊዜውም ቢሆን ምንም ለማያውቅ ሰው እውነት ስለሚመስል በዚህ አስተያየቴ እንኳ ልተባበራችሁ። በአላችሁበት ሁኔታ ግን ብዙ ቁም ነገር ለማለት አይቻልምና።

  ReplyDelete
 11. ቅሉ ዱባ ጣለ አቤት ዉሸት
  እባብ በእግሩ ሄደ አቤት ዉሸት
  በሬ ጥጃ ወለደ አቤት ዉሸት
  አባሰላማ እዉነት ተናገረ አቤት ዉሸት
  ማህበረ ቅዱሳን ስብሰባ ረግጦ ወጣ አቤት ዉሸት
  ማህበረ ቅዱሳን አከረረ አቤት ዉሸት

  ReplyDelete
 12. ቅሉ ዱባ ጣለ አቤት ዉሸት
  እባብ በእግሩ ሄደ አቤት ዉሸት
  በሬ ጥጃ ወለደ አቤት ዉሸት
  አባሰላማ እዉነት ተናገረ አቤት ዉሸት
  ማህበረ ቅዱሳን ስብሰባ ረግጦ ወጣ አቤት ዉሸት
  ማህበረ ቅዱሳን አከረረ አቤት ዉሸት

  ReplyDelete
 13. ቅሉ ዱባ ጣለ አቤት ዉሸት
  እባብ በእግሩ ሄደ አቤት ዉሸት
  በሬ ጥጃ ወለደ አቤት ዉሸት
  አባሰላማ እዉነት ተናገረ አቤት ዉሸት
  ማህበረ ቅዱሳን ስብሰባ ረግጦ ወጣ አቤት ዉሸት
  ማህበረ ቅዱሳን አከረረ አቤት ዉሸት

  ReplyDelete
 14. Kenantes ETV yeshalal

  ReplyDelete