Friday, October 4, 2013

አክራሪው ማኅበረ ቅዱሳን ‘አክራሪ አይደለሁም፤ አክራሪ ነው የሚል ማስረጃ ያቅርብብኝ’ አለ

አክራሪው ማኅበረ ቅዱሳን ‘አክራሪ አይደለሁም፤ አክራሪ ነው የሚል ማስረጃ ያቅርብብኝ’ አለ

ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፈጸማቸውና እየፈጸማቸው ባሉት ተግባራት በአክራሪነት የተፈረጀውና ቀድሞም ቢሆን በዚሁ ግብሩ የሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን በሐመር መጽሔት የነሐሴ 2005 እትም ርእሰ አንቀጽ ላይ “ክርስትና ‘አክራሪነት’ን የሚያበቅል ነገረ ሃይማኖታዊ መሠረት የለውም” በሚል ርእስ ባቀረበው ሐተታ አክራሪ አለመሆኑንና አክራሪ ነው የሚል ካለ ማስረጃ ሊያቀርብበት እንደሚገባ ገለጸ፡፡

ርእሰ አንቀጹ ክርስትና ከአክራሪነት ፈጽሞ የተለየ መንገድ መሆኑን በወርቃማ ቃላት ለመግለጽ የሞከረ ቢሆንም በገለጻው መሠረት እንኳን ማኅበረ ቅዱሳንን መፈተሽና እስካሁን የተጓዘበትን መንገድ መመርመር ከተቻለ ማኅበሩ እልም ያለ አክራሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በዚህም ማኅበረ ቅዱሳን የጻፈውን ያልኖረና የማይኖር፣ ንግግሩና ስራው ለየቅል የሆኑበት ስብስብ መሆኑን ራሱ በራሱ መስክሯል፡፡


ለማቅ አክራሪ የሚል ስም በመስጠት ቀዳሚ የሆኑት ራሳቸው ኦርቶዶክሳውያን ሲሆኑ ማህበሩ “ሃይማኖትን አስከብራለሁ” በሚል መነሻ በቤተክርስቲያን ከዚያ ቀደም በልማድ ሲሰራባቸው የነበሩትንና ዶግማ ያልሆኑትን ልዩ ልዩ የልማድ ትምህርቶችና ስርአቶች እንደዶግማ መታየት አለባቸው በሚል አስተሳሰብ በህዝቡ ውስጥ ለማስረጽ ሲታገል በነበረባቸው ጊዜያት ነበር ይህን ስም ያወጡለት፡፡ አንዱን እንኳን በማሳያነት ብናቀርብ በቤተክርስቲያኒቱ ከመስከረም 26 - ኅዳር 6 ያለው ወቅት ወርኀ ጽጌ (የአበባ ወቅት) በልማድም የጽጌ ጾም እየተባለ የሚጠራ ሲሆን ጾምነቱ የፈቃድ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመ ወዲህ ግን በግድ መጾም አለበት በሚል ወጣቶችን በመቀስቀስና ያለሲኖዶስ ዕውቅናም የቤተክርስቲያኒቱ አጽዋማት 7 ሆነው እያለ 8 ናቸው ሲል በሐመር ላይ በድፍረት ጽፏል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤም ከየት አመጣኸው በሚል እርማት እንዲሰጥበት በወቅቱ መመሪያ አስተላልፎለት ነበር፡፡ አክራሪው ማቅ ግን አልሰማም፡፡

በዚህና በሌሎችም ተመሳሳይ ሕገወጥ ድርጊቶቹ ቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ትርምስ እንደተፈጠረና ማቅ አዲስ እያሰረጸ ለነበረው አመለካከት እንቢኝ አሻፈረኝ ያሉትን ሁሉ በመናፍቅነትና በተሐድሶነት ሲፈርጅ እንደነበረና በዚህ ድርጊቱም እንደገፋበት ይታወቃል፡፡ ለዚህ እንዲረዳውም ሰላዮችን ጭምር በመመልመልና የሌላ እምነት ተከታይ መስለው እንዲቀርቡ በማሰልጠን ማኅበሩ የጠረጠራቸውን ሰዎች እንዲሰልሉ እስከማድረግና በዎክማን ቴፕ በማስቀረጽ መረጃ አገኘሁ ብሎ ለጳጳሳቱ በማቅረብ ክስ ይመሰርትባቸው ጀመር፡፡ በዚህ ረገድ ግዳይ የጣላቸው ከብዙዎቹ መካከል መምህር ጽጌ ስጦታውና መምህር ግርማ በቀለን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተለይ መምህር ግርማ በቀለን ለመወንጀል ወደእርሱ የላካቸው የማኅበሩ ሰላዮች ራሳቸውን የይሆዋ ምስክር አድርገው በመቅረብ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለክስ አመቻቹት፡፡

በእርግጥ የሰላዮቹን ማኅበረ ቅዱሳንነት ሳያውቅ መምህር ግርማ የሰጣቸው ትምህርት ማኅበረ ቅዱሳን የማያምንበትን እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነበር፡፡ ያን ከጥንት ጀምሮ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያናችንን እስከ ተጣባበት ጊዜ ድረስ ይሰበክና ይታመንበት የነበረውን ትምህርት ግን ማኅበሩ ለማሥረጽ በሚታገልለት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ለመተካትና ክርስቶስን ከመካከለኛነቱ ስፍራ ለማንሣት ታጥቆ ስለተነሣ መምህር ግርማን፣ መምህር ጽጌንና ሌሎችንም ከሰሰ፡፡ ከዚያም ጉዳዩ በሲኖዶስ እንዲታይ ተወስኖ ተከሳሾቹ መምህር ግርማና መምህር ጽጌ ቀርበው በክርስቶስ መካከለኛነት ዙሪያ ስላለውና ስለሌችም ጉዳዮች ትምህርት እውነተኛውን ነገር በመግለጥ ጳጳሳቱን ተከራክረው የረቱ ቢሆንም፣ የተሸነፉ ነገር ግን አልሸነፍ ባዮች የሆኑ አንዳንድ ጳጳሳት አሻፈረን ስላሉ እነ ግርማ ቢያሸንፏቸውም የተረቱት ይቅርታ መጠየቅ ሲገባቸው ፍርድ ተገልብጦ ለእነግርማ ቀኖና እንዲሰጣቸው ተወስኖ ወደ ደብረ ሊባኖስ ወረዱ፡፡ ነገር ግን የእነግርማን መርታት እንደ ትልቅ ሽንፈት የወሰደውና ቀኖናቸውን ጨርሰው ወደ ቦታቸው የሚመለሱ መሆናቸው ያነገበገበው ማኅበረ ቅዱሳን ነፍሰ ገዳይ አባላቱን ሱባኤ በመግባት ስም ደብረ ሊባኖስ እንዲከትቱ ካደረገ በኋላ እነግርማን እንደሰማዕቱ እስጢፋኖስ በድንጋይ አስወግሮ የሞቱ መስሎት በሞትና በሕይወት መካከል ትቷቸው ሄደ፡፡ ከዚህ የበለጠ አክራሪነትና አሸባሪነት ከወዴት ይገኛል? ሐመር ይህን የማኅበሩን ጉድ ሸፍኖ የራሱ ያልሆነውንና የክርስትና ጠባይ የሆነውን በኃይል ሳይሆን በፍቅር ወንጌልን የመስበክ መንፈሳዊ አካሄድ የእርሱም መመሪያ አስመስሎ እንዲያ ሲዛብር ስናይ “ኧረ ተው ማቅ የምትለው የክርስትና እንጂ የአንተ የነፍሰ ገዳዩ ጠባይ አይደለም” ብለናል፡፡

ማቅ የጆሆቫ ምስክሮች አስመስሎ ብቻ ሳይሆን ሙስሊም አድርጎ ወንጌል ወደሚሰብኩ የቤተክርስቲያን ልጆች ሰላዮቹን የላከበትና የተጋለጡበት ሁኔታም አለ፡፡ በአንድ ወቅት አንድ አገልጋይን አጥምዶ ለመጣል የሸረበው ዘዴ ግን በአይነቱ የተለየ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ሶስት አላማዎች ይዞ የተነሳ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ኢአማኒ (ሙስሊም) ነኝ የምትል ልጅ ልኮ እንዲያገለግላት ማድረግና ክርስቲያን የሆነች አስመስሎ እያስለፈለፉ ትምህርቱን መቅዳት እና ማስረጃ መሰብሰብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ልጅቱ በዝሙት እንድትጥለው ማድረግ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለቱ ካልተሳኩ ደግሞ በልጅትዋ አማካይነት በመድሃኒት ማሳበድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቸር ስለሆነ ግን አንዱም ወጥመድ ሳይሰምር ሃፍረትን ተከናንበውበታል፡፡(ይህ ታሪክ ራሱን የቻለ መጽሐፍ የሚወጣው ነው፡፡)

በሌላም ጊዜ አንድ ለአገልግሎት ወደ ክፍለ ሃገር የወጣን ወንድም ያረፈበት ሆቴል ድረስ ቆንጆ ሴት በመላክ አገልግለኝ በሚል ስም ካገኘችው በኋላ በዝሙት ልትጥለው ከፍተኛ ሙከራ ብታደርግም ልጁ ግን በአቋሙ በመጽናቱ በስተመጨረሻ በመጸጸት ይቅርታ ጠይቃው ይኸው አክራሪ ማኅበር ስለ እርሱ መጥፎ መጥፎ ነገር ነግሮ እንዳሳመናት እና በዝሙት እንድትጥለው እንዳግባቡዋት በከፍተኛ ጸጸት ነግራው ሄዳለች፡፡

በአዲስ አበባ ተክለ ሃይማኖት፣ በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በሃረር፣ በአዋሳ፣ በክብረ መንግስት፣ በአሰበ ተፈሪ፣ በሻሸመኔ፣ በጎንደር እና በሌሎችም ከተሞች ያስነሳው አመጽን የተመለከተ እና የሰማ ሰው ይህን ማኅበር ከአሸባሪ ሌላ ምን ስም ሊሰጠው ይችላል? ማኅበሩ በሀረር አካባቢ አልሸባብ ወደአዋሳ ታሊባን፣ ሻሸመኔ ቦካ ሀራም በመሃል ከተማ አልቃይዳ በሚል ስም እየተጠራ ያለው አካሄዱ ከእነዚህ አክራሪዎች አካሄድ የተለየ ስላልሆነ ነው፡፡

የማኅበሩ ልሳን ሐመር “ ‘አክራሪነት’ የሚተረጎመውም የራስን የሃይማኖት የበላይነት ለማስፈን ሲባል ሌላው የሃይማኖት ሐሳቡን እንዳይገልጥ፣ ተግባራዊ የአምልኮ ሥርዓቱን እንዳይፈጽም ማድረግ በኃይል ወይም በዐመፅ ቦታ ማሳጣት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡” ሲል አክራሪነትን አብራርቷል፡፡ ይህን ተግባር በመፈጸም በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነቱን ያሳየና ቀዳሚ የሆነ እንደማኅበረ ቅዱሳን ያለ ስብስብ አለ ማለት ግን አይቻልም፡፡ ከአዲስ አበባ ወጣ ባሉና በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች የሌሎች እምነት ተከታዮችን የአምልኮ ቦታ እንዳይኖራቸው፣ ሌላው ቀርቶ ወገናቸው በሞት ሲለይ በመቀበሪያ እጦት እንዲቸገሩ በማድረግ ብዙ ግፍ ሲፈጽም የኖረና አሁንም እየፈጸመ ያለ አክራሪ ቡድን ነው፡፡ ለዚህ እኩይ ድርጊቱ በመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ የማኅበሩ አባላት ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተለይ በፕሮቴስታንቶች ላይ ከፍተኛ ስደትና ሁከት ሲፈጽም ኖሯል፤ እየፈጸመም ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ሐመር ይህን የማኅበሩን መታወቂያ ደብቆ “በክርስትና ስም የሚፈጸሙ ወይም በታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ አሁን ‘አክራሪነት’ ያልነው ጠባይ የተንጸባረቀባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩ እንኳን በክርስትና ስም ልንቀበለው የምንችለው አይሆንም፡፡” ሲል ጨዋ ለመምሰል ሞክሯል፤ “እመት ስመኝ ለማያውቅሽ ታጠኝ” አሉ አለቃ ኪዳነ ወልድ፡፡ እኛ ደግሞ ለአፍህ እንዲህ በል እንጂ ይህን እየፈጸምክ ያለኸው አንተ ነህ እንላለን፡፡

ማቅ ይህ እኩይና አሸባሪ ግብሩ የተረሳለት መስሎት “ክርስትና ሰዎች የእምነት ሐሳባቸውን እንዳይገልጹ አይገድብም፡፡ ሌሎች በእምነቱ ላይ ያላቸውን ጥያቄ እንዳያቀርቡም አይከለክሉም፡፡ … በመግደል ሳይሆን በመሞት የብዙዎችን ነፍስ ለመታደግ የሚኖር ሃይማኖት በመሆኑ ነው” ሲል አሁንም የእርሱ ያልሆነውንና በተግባር የማያውቀውን የክርስትና ጠባይ የገለጸ ሲሆን፣ ራሱ ማቅ ግን በስም እንጂ ክርስቲያናዊ ማኅበር ስላልሆነ ለሃይማኖት በመቅናት ስም ያልመሰሉትን ለመግደል ካልሆነ በስተቀር በመሞት የብዙዎችን ነፍስ ለመታደግ ማንነቱ አይፈቅድለትም፡፡ ለዚህ ነው ከላይ የጠቀስናቸውን እነ መምህር ግርማ በቀለን የወገራቸው፡፡

ከዚያም በኋላ በማቅ የስለላ መረብ እየተጠመዱ ከቤተክርስቲያን በግፍ የተባረሩትን፣ ያስደበደባቸውን፣ ያስገደላቸውን፣ ከአገር ያስባረራቸውን ለስደት የዳረጋቸውን፣ አሁንም በአሸባሪ መዝገቡ ላይ ስማቸውን አስፍሮ አላስወጣ አላስገባ ያላቸውንና አጋጣሚ እየጠበቀላቸው የሚገኙትን ሁሉ ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ ይህን አክራሪነት የወለደውን እኩይ ተግባር ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው ማቅ ክርስቲያናዊ ምግባር ሊያደርገው የሚችለው? በፍጹም አይችልም፡፡ ለዚህም ነው የጻፈውና የሚሠራው ለየቅል ነው ያልነው፡፡ ማቅ ክርስትና አሸባሪነት የሌለው ሃይማኖት ነው የሚለው ትክክል ቢሆንም ማቅ የሚሠራው ግን በሽብር የተሞላ እኩይ ተግባር በመሆኑ እርሱ ክርስቲያን ሳይሆን ከክርስትና ውጪ ያለ ስብስብ ነው ቢባል ሳያስኬድ አይቀርም፡፡

ይህን በጠራራ ፀሐይ የሚፈጽመውንና በእርሱ አስተምህሮ መሰረት እንደሰማዕትነት የሚቆጥረውን የሽብር ድርጊት ወደጎን ትቶ “ማኅበሩ የቤተክርስቲያኒቱ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሠራ ከሰጠው ተግባራት ውስጥ ወደ ‘አክራሪነት’ አምባ ያስገባውን ወሰን አለፈ ያስባሉትን ነጥቦች ነቅሶ ማሳየት፣ እንዲህ የሚያስበሉ የተፈጸሙ ተግባራትንና ተግባራቱን ማኅበሩ ሓላፊነት ወስዶ የፈጸመው ተግባር መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ማቅረብ አግባብ ይሆናል፡፡” ሲል አለማፈሩ የሌባ አይነደረቅ አሰኝቶታል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማቅ አክራሪ መሆኑን፣ ስሙንና ግብሩን ጭምር ጠቅሰው ይፋ ከማድረጋቸው በፊት የማቅን አክራሪነት የቤተክርስቲያን ልጆች ጠንቀቀው ስለሚያውቁ ሰሚ ባያገኙም ማቅን በሃይማኖት አክራሪነት ሲከሱት ኖረዋል፡፡ በተለይም ቤተክርስቲያን የተመሠረተችበትን እውነተኛ ትምህርት በመቃወምና እንደኑፋቄ በመቁጠር በልማድ የገቡትንና በመጽሐፍ ቅዱስ ሲፈተሹ የስህተት ትምህርት ሆነው የተገኙትን ትምህርቶችን ለማስረጽ በመሞከር በተለይ ወጣቱን በዚህ አቅጣጫ አክራሪና ባዶ ቀናተኛ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁንም ቢሆን በዚህ ተግባሩ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ በቅርቡ አባ ዮናስ የተባሉ መነኩሴ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማቅ ኦርቶዶክስ ውስጥ የተቀበረ አክራሪ ፈንጂ መሆኑን ማጋለጣቸው እውነት እንጂ ሐሰት አይደለም፡፡ ማቅ አክራሪ የመሆኑ ጉዳይ ከቤተክርስቲያን ውጪም በመንጸባረቁ ምክንያት መንግሥት ጥርስ ውስጥ ገብቷል፡፡ ለዚህ ነው ጉዳዩ እጅግ አሳስቦት ሐመር በተባለው ልሳኑ ላይ እኔ አክራሪ አይደለሁም ሲል ራሱን ለመከላከል የሞከረው፡፡ የአክራሪነትን ባሕርያት በማስተንተን ንጹሕ መሆን የሚቻል ይመስል ማቅ በዚህ አቅጣጫ መድከሙ የሚገርም ነው፡፡ ስለዚህ ማቅ ራስህን አታታልል፤ ሌላውማ ነቅቶብሃል፡፡

ማቅ በአንድ በኩል አሸባሪ አይደለሁም ይበል እንጂ በአሁኑ ወቅት እንኳን እየሠራ ያለው ቤተክርስቲያንን የማሸበር ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን ክርስቶስን ማእከል አድርጋ እንድትንቀሳቀስና ተልእኮዋን እንድትፈጽም ሲተጉ የነበሩ ልጇችን ተሀድሶ መናፍቃን የሚል ስም እየሰጠ ሲያሳድዳቸው፣ ሲያወግዛቸውና ሲያስወግዛቸው እንደኖረ ይታወቃል፡፡ ለዚህም አንዳንድ ገበናቸውን የሸፈነላቸው የመሰላቸውን ጳጳሳት ከጎኑ በማሰለፍና የጉድ ሙዳይ ሆነው ሳለ እርሱ ግን “እንደእርሳቸው ያለ ቅዱስ የለም” እያለ በሚያስወራለቸውና በከንቱ ውዳሴ በጠለፋቸው ጳጳሳቱ በኩል በወርኀ ግንቦት የጅምላ ውግዘት እንዲተላለፍ አድርጓል፡፡ ይህም ቤተክርስቲያን ሰው እንደሌለባት ያሳየና የምትመራው በማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ያስመሰከረ ሐቅ ነው፡፡ ቁምነገሩ ማኅበሩ ከዚህ ምን አተረፈ? እንዳለው በጅምላው ውግዘት እርሱ “ተሐድሶ” የሚል ስም የሰጠው የእውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል ወይ? በፍጹም!!! እንዲያውም ከቀድሞው ይልቅ እጅግ እንደተጠናከረና ውስጥ ለውስጥ ይህ የተቀደሰና ለቤተክርስቲያን ትንሣኤን የሚያጎናጽፈው እንቅስቃሴ ሥር እየሰደደ እንደሆነ ነው ከየስፍራው የሚደርሰን መረጃ የሚያመለክተው፡፡

ማቅ በገንዘብ በሚደጉማቸውና እንዳሻው እያሽከረከረ የእርሱን አቋም ምንጭ ጠቅሰው ሳይሆን የራሳቸው አቋም አድርገው የጋዜጠኛነትን ስነምግባር በሚጻረር መልኩ ሲጽፉለትና “ተሐድሶ ተሐድሶ” ሲሉ በነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲያናፍሱት የነበረው ወሬም ከወሬነት አላለፈም፡፡ የቤተክርስቲያን ልጆች ግን ውስጥ ለውስጥ የክርስቶስን የማዳን ብሥራት የሆነውን ከምንም ጋር ያልተቀላቀለ ንጹሕ ወንጌል በመስበክ ብዙዎችን ከጨለማ ወደ ብርሃን እያፈለሱ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በመነሣትም ለማቅ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚናገሩት አንዳንድ የማቅ ሰዎች “በየመጽሔቱና ጋዜጣው የከፈትነው ዘመቻ ተሐድሶዎችን ከማስተዋወቅ ያለፈ ውጤት አላስገኘልንም፡፡ ከገጠር እስከ ከተማ ቀሳውስቱ ዲያቆናቱ፣ መሪጌቶቹ፣ መነኮሳቱ፣ ሰንበት ተማሪዎቹ ሁሉ የተሐድሶ መንፈስ እየገባባቸው ነው፡፡ ስለዚህ ስልታችንን መለወጥ አለብን፡፡ ተሐድሶዎች በኅቡእ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ እኛም የኅቡእ ሥራ መሥራት አለብን” እያሉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

የተጀመረውንና ቤተክርስቲያናችን መሠረቷን ክርስቶስን ማእከል አድርጋ ተልእኮዋን እንድትፈጽም የሚያደርጋትን እንቅስቃሴን ለመቀልበስ አንዱ ስልት አድርገው እየተንቀሳቀሱ ያሉት በቁጥጥራቸው ስር ያዋሏቸውን ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማነሣሣት ሰባክያነ ወንጌልን እንዲቃወሙና ተሐድሶ ናቸው በማለትም እንዲወነጅሉ የማድረግ ሥራ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አባላቶቻቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ነን እንዳይሉና ቀናእያን ምእመናን መስለው እንዲቀርቡ በማድረግና ለየአድባራቱና ገዳማቱ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ክስ በማቅረብ “እገሌ የተባለው ሰባኪ ወይም ዘማሪ ተሐድሶ ነው፤ እያስተማረን ያለውም የምንፍቅና ትምህርት ስለሆነ ይጣራልን” የሚል ጩኸት እንዲያሰሙ እያደረጉ ነው፡፡ ለዚህ እንዲረዳቸውም አባላቶቻቸውን በየሰበካ ጉባኤው ውስጥ በመሰግሰግ ክሱ እንዲጣራና የተከሰሰው ወገን በተሐድሶነት እንዲፈረጅ ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ከሁሉ የሚገርመው የቤተክርስቲያንን ትምህርት ለመመዘንና እገሌ መናፍቅ ነው ለማለት ማቅ ብቃቱ፣ መብቱስ አለው ወይ? “ማኅበሩ የቤተክርስቲያኒቱ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሠራ ከሰጠው ተግባራት ውስጥ ወደ ‘አክራሪነት’ አምባ ያስገባውን ወሰን አለፈ ያስባሉትን ነጥቦች ነቅሶ ማሳየት፣ እንዲህ የሚያስበሉ የተፈጸሙ ተግባራትንና ተግባራቱን ማኅበሩ ሓላፊነት ወስዶ የፈጸመው ተግባር መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ማቅረብ አግባብ ይሆናል፡፡” ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡ ማኅበሩ እኮ እኔ ከማመንው ውጪ የክርስትና ትምህርት የለም ባይ ነው፡፡ እርሱ ከሚያምነው ተረት ተረት ውጪ የሚያምን ደግሞ መናፍቅ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ አሸባሪነት ምን አለ?


እንደአንዳንድ ምንጮች ከሆነም ለጥቅምቱ ሲኖዶስ ሊወገዙ ይገባል ብሎ የሚያቀርባቸው አገልጋዮች መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን የሲኖዶሱ ብዙዎቹ አባላት ከዚህ ቀደም በማቅ ተመርተውና ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በፈጠሩት አለመግባባት እርሳቸውን የጎዱና ማቅን ያስደሰቱ መስሏቸው በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ጥቁር ነጥብ የጣለና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብ አሳፋሪ ውሳኔ አሳልፈው ሕግንና ሥርአትን ያልተከተለ ኢክርስቲያናዊ የጅምላ ውግዘት አስተላልፈዋል፡፡ ውጤቱ ለተወገዙት ይበልጥ ብርታትን በመስጠት በአገልግሎታቸው እንዲበረቱና አላማቸውን እንዲያስፋፉ ነው ያደረጋቸው፡፡ ስለዚህ እንደ ትናንቱ ዛሬም ሌላ ስሕተት እንዳይፈጽሙ ገማልያል ለሐዋርያት ከሳሾች የሰጠውን ምክር እንለግሳቸዋለን፡፡ “ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።” (የሐዋ. 5፥38-39)፡፡

47 comments:

 1. Kirstina Begiıts enji behbu aysebeKim. Maferiawoch.

  ReplyDelete
 2. እባካችሁ አትዋሹ ውሸት የዲያብሎስ ተግባር ነው ይህን በሬ ወለደ አይነት ውሸትናቤተክርስትያንዋ በመመርያ የምታስፈጸመውን ለምሳሌ ኦርቶዶክስ ያልሆነ ባኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ እንደማይቀበር እየታወቀ ማህበረ ቅዱሳን በቀብር ከልካይነት ብትወነጅሉ ዲያብሎስን የተሸከማችሁ እባቦች መሆናችሁን በግልጽ የሚያሰይ ነው። በህይወት እያሉ ያልተቀበልዋትን ቤ/ክ ያስከሬናቸው ማጠራቀሚያ ትሁን ማለት ነው? ማንን ነው ለማታለል የምትፈልጉት። ስህተትን በስህተት ማረም አይቻልም። ባማሩ ቃላት እርስ በርስ እየተቆለጳጰሳችሁ ቤ/ክርስትያንዋን የመናፍቃን መፈንጫ እንድታደርጉዋት ማንም ኤኢፈቅድላችሁም ሞኛችሁን ፈልጉ ለናንተ የውጭ እርዳታ ማግኛ ከበስተጀርባችሁ የተሸከማችሁትን ደባ በኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ላይ አታራግፉ። ማህበረ ቅዱሳን የናንተን ደባ ስላጋለጠና ስለሚዋጋችሁ ብቻ የጥላቻ ወሬ የምታወሩ ውሸታም መናፍቃን ናችሁ። ስለ ማህበረ ቅዱሳን የጻፋችሁት ይህ ሁሉ ጽሁፍ ውሸትና ተራ አሉባልታ ነው። አንባብያን አትታለሉ አስተውሉ

  ReplyDelete
 3. Initially I did not have any qualm with Maheber Kidusans. they have done some good things for the church. My problem got started when they went in to attacking some prominent priests for being "Thadesso" Apparent intimidation and harassments were typical feature of them. Once a unified youth choirs from LA, Houston, Dallas, Minneapolis and Denver got dismantled because of the leaders ambition to control Sunday Schools. Almost every church crisis in America had to do with this group.

  ReplyDelete
 4. አይሰለቻችሁም?ብቻ ካልጮሀችሁ ደሞዝ ማን ይከፍላችሗል?እናንተ በምታመጡት ፈተና ክርስቲያን ካልታገሰ የድል አክሊል ከየት ይገኛል? ስለዚህ የድል አክሊል አስገኝዎቻችን ሆይ እንወዳችሗለን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለዚህ የድል አክሊል አስገኝዎቻችን ሆይ እንወዳችሗለን።

   Delete
  2. ስለዚህ የድል አክሊል አስገኝዎቻችን ሆይ እንወዳችሗለን።

   Delete
 5. አይሰለቻችሁም?ብቻ ካልጮሀችሁ ደሞዝ ማን ይከፍላችሗል?እናንተ በምታመጡት ፈተና ክርስቲያን ካልታገሰ የድል አክሊል ከየት ይገኛል? ስለዚህ የድል አክሊል አስገኝዎቻችን ሆይ እንወዳችሗለን።

  ReplyDelete
 6. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ወካይና መገለጫ ናት፡፡ ስለዚህ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ተቀላቅሎና ተመሳስሎ መግባት እንደሌለ ሁሉ በዚህ ዓለም ያለችው ቤተ ክርስቲያንም የዚያ ወካይና መገለጫ ናትና የእርሷ ወገኖች ያልኾኑትን ትለያቸዋለች እንጂ፣ ጭፍን የምድራዊ መንግሥት ካድሬዎችና በመንግሥት የፀረ – አክራሪነት አጀንዳ ስም ስሑታኑ ከእነ ኑፋቄያቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልሰው እንዲገቡና የልዩ እምነት ፍላጎታቸው የኾነውን የቤተ ክርስቲያናችንን መዳከምና መከፈፋል እንዲያሳኩላቸው ‹‹የአስተምህሮ መቻቻል ዴሞክራሲ›› ከንቱ ፕሮፓጋንዳ እንደሚነዙት አንዳንድ ባለሥልጣናት በዝምታ ወይም በግዴለሽነት አታዝላቸውም!!!

  ReplyDelete
 7. Egziabeher yetkelewen Manem linkel ayechelem mk yalawekew sew yelemm lemehonu sreat lebtekeresteyan asebew new wey?? megeremew BEGERMN hager mk yemseraw sera meemnanen eyasademe kahenaten eyewenjele eyeksese yale endhihum tensehu belo kedeso yemayawk sew dero shanbel yenber ABRHAM belete lehekimena bemetut Abune KERLOS bemekinaw seyansherasherachew senbeto kisena yestugn belo serko kes hone biteyek gin andim eweket yelem zare Be GEREMEN hager kemisun ateleko Kobun defeto meskelun yezo ene kes negn eyale beslk mawejun ketelual sewn yemayafer EGZIABHEREN yemayefera Ye Mk meri aleka endenezhi ayenetu mehayem new zare betekereseteyanachenen eyasewenejele yalew mk westem teru lijoch alu maheberu endenezhi ayenetun mawegez alebet elalhu beterefe abaselamawoch bertu ewenetegnaw wengel yesebekal betekereseteyanachenem teketelalech teru zena yesemahut Zemarit Fantu Welde Yejemerechehu erk yebel yemeyasbel new bemiketelew sele Germen Besfiew Akerbalhu KeGermen Frankfurt Mareyam Betkersteyan ETAL......EGZIABHER ke Egna Gar New

  ReplyDelete
 8. Yo!!! I really want you to debate with MK face to face instead of veiling in this little screen.
  I always wonder to see every Tehadiso to reveal MK in whatever they do.

  ReplyDelete
 9. gosh! mahibere kidusan bertu egz/r eyeredachihu new. enezihin wushoch dehna adrgachihu yizachhual. megibiya mewuchachewn yemtawuqut enante nachihuna bertu

  ReplyDelete
 10. Lemehonu beye betekirstianu, senbet t/bet... Eyegebu egna yametanew adis timihirt kaltekebelachu bemalet yaschegerew 'yetahadisow budin' aydelemin? M.kidusan yebetekirstian astemihiro ayfales, yitebek bay new. Libona yisitachihu!

  ReplyDelete
 11. Lemehonu beye betekirstianu, senbet t/bet... Eyegebu egna yametanew adis timihirt kaltekebelachu bemalet yaschegerew 'yetahadisow budin' aydelemin? M.kidusan yebetekirstian astemihiro ayfales, yitebek bay new. Libona yisitachihu!

  ReplyDelete
 12. Keep doing good for our innocent people and exposing the work of the evil. God bless you for all your efforts to serve our church according the word of Almighty God.

  God bless Ethiopia
  Yours in the Love of our Lord
  Selam

  ReplyDelete
 13. መናፍቅን : መናፍቅ : ማለት: አሸባሪነት : አይደለም :: ከአንድ : ክርስቲያን
  የሚጠበቅ ተግባር ነው::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሁሌ የማይገባኝ ነገር ማን ነው መናፍቅ? ቅዱስ ጳውሎስ እኮ መናፍቅነትን ከሥጋ ስራዎች አንዱ ነው ይለዋል፡፡ለመሆኑ ዝሙትና መናፍቅነትን ፣ዘፈንና መናፍቅነትን ….. ማነው እንድናበላልጥ የፈቀደልን? መናፍቃን የተባሉትን የሚሳደብ ጻድቅ አንደበታችን መነው ዘፋኞች፣ሴሰኞች፣አመንዝራዎች፣ሰካራሞች….. ጋ ሲደርስ ይለጎማል?(ለነገሩ ለካ አነዚህ የኃይማኖት ህጸጽ አይደሉም መናፍቅነት የሀይማኖት ህጸጽ ነው እየተባልን ስንቴ ደነቆርን?)ብንረዳ ስድብም፣ዘፋኝነትም፣ዝሙትም እንደመናፍቅነት ከእግዚአብሔር መንግስት ያወጡናል፡፡

   Delete
  2. ዋው ለዛ ነዋ ያንተ አለቆች የዘፋኞች፣ሴሰኞች፣አመንዝራዎች፣ሰካራሞችን ነገር ይምገስፁት?i መሳቂያ ከመናፍቅነት በተጨማሪ ይህን ሁሉ አይደል እንዴ እናንተ መናፍቃንና ጴንጤዎች የምትሰሩት::

   Delete
 14. Thank you so much! It is so wonderful fact. But, Mak has to be understood.
  Thank you again!!!

  ReplyDelete
 15. zare genn amenku seytane hule geze endemewashe! arfo endemayetegna! enante yeawerewe wegenoche betemelesu yeshalachewal! eskemeche be MK eysabebachew hodachewen temolalachew! mecheresha ferdachewen medhenalem yekeflachewal endserachew!
  amlak wedkedmechew haymanot yemelsachew!

  ReplyDelete
 16. ሰበር ዜና
  ሌቦችና መናፍቆች ለጳጳሳት የሚከተለውን መልእክት አስተላለፉ፡፡
  “ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።”

  ReplyDelete
 17. What a heel is this,to be honest with you MK is the one they goon destroy
  Ethiopian church,they are cancer for that church &even for that country,are
  They Christians?not only for me the whole entire world get confused about
  Them.hey guys I am telling you the truth,stop &think about it what they did
  From the beginning until now?even it
  Might be the future,what is the difference between selafy Muslims and MK.they are in
  Different camp,but MK is under church.
  That is why no body figures out there cover UPS .we need stand &say them
  no,all there leaders are misleading,the members of that church,who is the real
  Orthodox?them,no way,even they don't
  deserve Christian name,they don't know what is Christianity?if they now it
  They goon stop their devilry ,if they are not guess how are they?

  ReplyDelete
  Replies
  1. do not you know that Meles is died? Let me tell you he is died. I understand from you writing you are not Christian like Meles but politician, of course a bad politician!

   Delete
 18. nothing to say every day u have blaming subject how is Christianity could expressed? this is the task of devil not Christine .

  ReplyDelete
 19. Open your eyes guys! I am neither Thadesso nor Mahibere Kidusan. There are a lot of these weird tales i hear in ETOC and they are all bunch of nonsense. I am sure the high priests are aware of them and afraid to denounce. Organized group like Mhibere Kidusans are hinderance for any valid changes. The Thadesso group should intensfy their effort to clear out and get the church in its correct path. Stop gathering the early lunatic Bahatawis's and monks' account as real ones. Our church has been damaged sigificantly by their irresponsible deeds. Should Mahibere Kidusan wish to save them, it can store them in its archives. Serious reformation is essential so our church be able to glow and lights up others. I am sick of these pseudo groups who called themeselves as the organization of saints patronizing us.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you sure that you are not Thadesso? so funny

   Delete
 20. menafekena weyane are the same, the aim of " menafeke
  " is to destroy orthodox, and the aim of weyane is to destroy Ethiopia. we love you MK . Keep the good work. " Tehadesu and menafekan becareful

  ReplyDelete
 21. is that true mk means mass killer

  ReplyDelete
  Replies
  1. Funny. I admire you for extracting this. Any way there are some good people in it who are victimized by the leaders of this organization. I was once belonged to the EPRP and believed in the leadership with out condition. You could put some parallels here.

   Delete
  2. Like tehadiso pente- TP means terrorist pente.

   Delete
 22. ዝንቱ ዲስኩር አልቦ ፕሮፊት

  ReplyDelete
 23. ውሸት መናፍቅ +ውሽት ተሃድሶ =ውሸት
  {መናፍቅ ተሐድሶ + ውሸታም}
  ( ተቺ ቀላዋጭ ጥቅመኛ)ሀሰተኛ

  ReplyDelete
 24. ዝንቱ ዲስኩር አልቦ ፕሮፊት
  This is an attempt by kokebe kotari debtera to discredit Thadesso. Nice try, but we got you!

  ReplyDelete
 25. "ማኅበሩ እኮ እኔ ከማመንው ውጪ የክርስትና ትምህርት የለም ባይ ነው፡፡ እርሱ ከሚያምነው ተረት ተረት ውጪ የሚያምን ደግሞ መናፍቅ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ አሸባሪነት ምን አለ?" Well said.

  ReplyDelete
 26. The discussion have brought some enlightenments. I say we all owe a debt of gratitude to Aba Selama. There are a lot of fixings to do in our church. The Pharisees consumed their time crying over culture and traditions being violated. They were constant critiques of Jesus who eventually became the cheer leaders for his cruxfication. We could draw some lessons here. .

  ReplyDelete
 27. እናንተ እያወራቹህ ያላችሁት አክራሪነት እና መንግስት እያለው ያለው አክራሪነት ፈፅሞ አይገናኝም እናንተ የፃፈችሁትን ነገር መማህበሩ በፈፅም እንካ በመንግስት ደረጃ አክራሪ አያሰኘውም በቻላቹህ እና መረጃ ካላቹህ ከ ፖለቲካ ፓርቲዎች ግንኝነት ካለው ብታብሩሩ ጥሩ ነበር!

  ReplyDelete
 28. ዝንቱ ዲስኩር አልቦ ፕሮፊት! በጣም ደስ ይላል ልዘርዝረው

  ዝንቱ ዲስኩር አልቦ ተስፋ
  ዝንቱ ዲስኩር አልቦ ጽደቅ
  ዝንቱ ዲስኩር አልቦ እንጀራ
  ዝንቱ ዲስኩር………………

  ReplyDelete
  Replies
  1. The above gibberish was an attempt of Debtera to confuse you. As a debtera who claimed he would tell you your future by counting the stars above you. I say back off Satan!!!!

   Delete
 29. Ene Mahebere kidusan yemesrachewen anidaned negeroche balidegefem ,Minafekan Bibet kirsteyan enidyekberu tiklikelu ymeliw gen Manenitachehun ymegiletse yemiselignal.

  ReplyDelete
 30. አይ ፍራንክፈርቶች የምትይዙት የምትጨብጡት ጠፋችሁ አይደል? ስታሳዝኑ በአውደ ምህረቱም በመናፍቅ ብሎጋችሁም እንዲሁ ሰውን ስትኮንኑ ትኖሩ አታፍሩም አንድ ቀን ተንስኡ ሳይል ያላችሁት ማን ያስተማረውን እናንተ እንደሆናችሁ እንኳን ለሰው ልትሆኑ ለራሳችሁም ዕውቀታችሁ እስከ ምን እንደሆነ ታውቁታላችሁ መቼም ቀሚሳችሁን ለብሳችሁ ስትንጎማለሉ ከእናንተ በላይ አዋቂ የሌለ ታስመስላላችሁ መቼም ይህ የዋህ ምእመን የእውነተኛ አባትነት ትርጉሙ እስኪገባው ድረስ ምን ይደረግ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ አሉ እባካችሁ ዝም ብላችሁ የሰው ስም አታንሱ ልቦና ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 31. እናንት የሰይጣን ትጋት ማሳያዎች። ልቡና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 32. ማህበረ ቅዱሳን እራስ ምታት ሆነባችሁ.......

  ReplyDelete
 33. ስለዚህ የድል አክሊል አስገኝዎቻችን ሆይ እንወዳችሗለን።

  ReplyDelete
 34. don't worry. we know every thing well.

  ReplyDelete
 35. ማቅ ያገር አሸባሪ ከሆነ ተሸባሪው ለምን ያንቀላፋል (አንድ ሰው ባውደ ምሕረቱ እንዳለ ሲያጥወለውለው ለጓደኛው አንተ ወንድሜ እንትን እንትን አለብኝ ይለዋል ። እንዴ እንትን እስቲልብህ
  ትጠብቀዋለህ ውጣ አለው ይባላል አሁንም መጻጻፉ ብቻ ዋጋ አያሰጥም መመከት እንጂ

  ReplyDelete
 36. መቼ ወደልብህ ተመልሰህ አክራሪነትህን፥ እኔ ብቻ የወንጌል አዋቂ ነኝ ባይነትህን ትተህ የሚመስል ነገር ለመፃፍ ፍላጎትም ሆነ ተነሳሽነት የለህም። ደሞዝህን ነዋ የምታጣው።
  አንተ የጴንጤ ቅጥረኛና ተላላኪ እኔ ያልኩት ነገር ብቻ ነው ትክክል፤ የላኪዎቼን የጴንጤን አስተምህሮ ካልተቀበላችሁ ራሴን ደብቄና ተደብቄ ስበጠብጣችሁ እኖራለሁ ባይ አክራሪ ካልተባለ? ተላላኪ ካልተባለ ምን ሊባል ነው? በምንፍቅናና በጥቅም ደንዝዘኸልና ከያዘህ “የወባ ዛር የሚያድን ምህረቱን ያምጣልህ።” ተሃድሶ ተብዬ የጴንጤ ተላላኪዎች እንደው ትንሽ እምነት አለን ካላችሁ የማፍያ ስራችሁን አቁማችሁ ቤተ ክርስቲያኗን ካላደስን ከሚል አክራሪነታችሁ ተላቃችሁ ከሚመስሏችሁ ጋር ተሰብስባችሁ የራሳችሁን “ሃይማኖት” ማቋቋም ወይም ወደ አሰማሪዎቻችሁ መሄድ እየቻላችሁ ከወንጌሉ ቃል ጋር እየተላተማችሁ በአክራሪነት ከኛ ወዲያ የወንጌል አዋቂ የለም እያሉ መታበይ ግብዝነት ብቻ ነው።ተሃድሶዎች በየትኛውም ዌብ ሳይቶቻችሁ ሆነ በነ ሙሉጋኔን ፅሁፍ ብታቅራሩ የምትፈጥሩት ግራ ማጋባት የዛሬ አመት ወደመቀመቅ ወርዶባችኋል። የታጠቃችሁት “የበቀልና የእልህ መንፈስም” እስኪያጠፋችሁ ድረስ አይለቃችሁምና በምርቃና ክሰሱ፣ የወንድሞችንም ስም አጥፉ፥ ዋሹ።ደስ የሚለው ግን ምንም የምትፈጥሩት ነገር ግን የለም።

  እንደ ወሃቢያም በጀታችሁን ከውጪ ድርጅቶች እየተቀበላችሁ የጴንጤ አክራሪነትን ለማስፋፋት የምታደርጉትን ጥረት መክሸፉ አይቀርምና ብዙ አትደሰት።ተነቅቷል።

  ReplyDelete
 37. Yweshet abate dyablos now enantm yesuljoj nachu miknyatum friyacy wshet nowna kurt Abatachu tmeslalacu

  ReplyDelete
 38. Yweshet abate dyablos now enantm yesuljoj nachu miknyatum friyacy wshet nowna kurt Abatachu tmeslalacu

  ReplyDelete