Sunday, October 27, 2013

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሆይ ከእንቅልፍ የምትነቂበት ሰዓት አሁን ነው

ሰሞኑን በተካሄደው 32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ “የሃይማኖት መቻቻል” በሚል ርእስ በተካሄደው አንድ ውይይት ላይ፣ አንዳንድ ጳጳሳት ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በስብሰባው ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከመጡ ባለሥልጣናት ጋራ ባደረጉት ውይይት፣ በሃይማኖት ጉዳይ በተለያዩ ክልሎች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተጽእኖ በመግለጽ የመንግስትን ባለሥልጣናትን መውቀሳቸው ትክክለኛ የአባትነት ሚናቸውን እንዲጫወቱ ያደረገ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ የሃይማኖት አባቶች እንደ ሃይማኖት አባትነታቸው ጥፋት ሲፈጸም በተገቢው መንገድ ፊት ለፊት መናገራቸውና የመንግሥት ባለሥልጣናትን መውቀሳቸውና መገሠጻቸው ተገቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ወቀሳውን ተቀብለው እንደ ሕዝብ አገልጋይነታቸው በአንዳንድ ክልሎች ውስጥ በቤተክርስቲያኒቱ አማኞች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ሊያስተካክሉ ይገባል፡፡ እንዲህ ካልሆነ የሃይማኖት መቻቻል የሚለው ነገር ፍሬ ቢስ ይሆናል፡፡ ውጤቱም የከፋ ነው የሚሆነው፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንዱ ሪፖርት የቀረበበት መንገድ ትክክል መስሎ አይሰማንም፡፡ ለምሳሌ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ለአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ተጽእኖ አሳድረውብኛል በሚል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትን የከሰሰው “መናፍቃን” በሚል ስም ነው፡፡ ይህ አቀራረብ ትምክሕተኛነት የተጠናወተው፣ ራስን ከፍ ሌላውን ዝቅ በማድረግ የቀረበና እንደ ስድብ የሚቆጠር በመሆኑ በሕግ ፊት ሊያስጠይቅ ይችላል፡፡ ስለዚህ በልማድና የኦርቶዶክስ የበላይነት ሰፍኖ በቆየባቸው ዘመናት እንደ ነበረው ቀለል አድርገን የምናየውና ሌላውን የምንነቅፍበትን ያረጀና ያፈጀ ስድብ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ መንጸባረቁ ቤተክርስቲያኒቱ አሁንም ድረስ ሌሎች ሃይማኖቶችን እንደ ሃይማኖት ለመቀበል ፍላጎት የሌላት ያስመስላል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለው አቀራረብ በዚህ ዘመን ስለማይሠራ፣ በሃይማኖቶች መካከል መከባበርና መቀባበል እንዳይኖርም እንቅፋት ስለሚሆን ቤተክርስቲያኗ ይህን ልማድ መተው ይገባታል፡፡ ሌሎችን በሚጠሩበት ስም መጥራት መጀመር አለባት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሌሎቹን አብያተ ክርስቲያናት “መናፍቃን” እና ሌላም ስድብ አከል ስም በመስጠት ያለስማቸው መጥራት ሙሉ ለሙሉ ማቆም አለባት፡፡ ራሳቸውን በሚጠሩበትና በሚታወቁበት ስም ልትጠራቸው ይገባል፡፡
በጥቅሉ ሲታይ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በደል እየደረሰ ያለው በአንዳንድ ሙስሊሞች በሚበዙባቸው ክልሎች በሙስሊም ባለሥልጣናት በኩል የሚደርስ ተጽእኖ ሲሆን፣ በሌሎቹ ፕሮቴስታንቶች በሚበዙባቸው ክልሎች ደግሞ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በሆኑ ባለሥልጣናት በኩል የሚደርስ ተጽእኖ እንዳለም ይነገራል፡፡ እነዚህ ተግባራት ከመንግስት ባለስልጣናት የማይጠበቁ ናቸው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት ሁሉንም ዜጋ በእኩል የማገልገል ግዴታ አለባቸው እንጂ በእምነት ለሚመስሏቸው ብቻ በማድላት በእምነት በማይመስሏቸው ላይ ተጽእኖ ማሳደር የለባቸውም፡፡ በምሥራቅ፣ በምእራብና በደቡብ ኢትዮጵያ አንዳንድ ስፍራዎች እየሆነ ያለው ግን የአድልዎ አሰራር መሆኑንና የኦርቶዶክስ አማኞች ላይ ጫና እየተፈጠረ መሆኑን ከየክልሎቹ የቀረበው ሪፖርትና የጳጳሳቱም ወቀሳ ያመለክታል፡፡ ስለዚህ መንግስት የባለሥልጣናቱን ተገቢ ያልሆነ ተግባር ማስቆምና ዜጎችን ሁሉ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲያስተዳድሩ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ ወይም ባለሥልጣን ሃይማኖት ሊኖረው የሚችል ቢሆንም ያን በግሉ ሊያካሂድ ይችላል እንጂ የመንግስትን ሥልጣን ሃይማኖቱን ለማራመድ የሚጠቀምበት ከሆነ መንግሥትና ሃይማኖት ዛሬም አልተለያዩም ያሰኛል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ባለሥልጣናት በተለይም በክልልና በወረዳ የሚገኙ ሃይማኖትና ፖለቲካን ከመደበላለቅ ተግባር እንዲቆጠቡና የሁሉንም ዜጋ ሃይማኖት አክብረው የሁሉንም መብት በእኩልነት ማክበርና ጥበቃ ማድረግ አለባቸው፡፡ ካልሆነ ግን አሁን በሃይማኖቶች መካከል እየታየ ያለው ሁኔታ ወደአላስፈላጊ ሁኔታ ሊያመራ ይችላል፡፡ መንግሥትም በየስፍራው የሾማቸውን ሹሞች ለሕገ መንግሥቱ ታማኞች እንዲሆኑ የራሱን የቤት ሥራ በጊዜው መሥራት ካልቻለ የሚፈጠረውን ችግር ለመፍታት ብቁ ስለማይሆን አገሪቱን ወደማትወጣው ቀውስ ውስጥ ሊያስገባት ይችላል፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ በተጠቀሱት ክፍሎች አሁን እየታየ ያለው ሁኔታ እንዲህ ይሁን እንጂ በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ደግሞ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች የሆኑ ባለስልጣናት በሌሎቹ እምነቶች በተለይም በፕሮቴስታንቶች ላይ ተመሳሳይ ጫና እንደሚያሳድሩባቸው ሲናገሩ ይሰማል፡፡ እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ ልዩ ልዩ ስደቶች ይታወጁባቸዋል፡፡ በጸሎት ቤታቸው ላይ የድንጋይ ናዳ ይወርዳል፤ የሞተ ወገናቸው እንዳይቀበር ክልከላ ይደረጋል፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው እንዲቀብሩ ይገደዳሉ፤ ይህም ተገቢ አይደለም፡፡ በሰሜኑ ክፍል ከኦርቶዶክስ ውጪ ማንም ሊኖር አይገባም የሚል አይነት አመለካከት ያላቸው የሃይማኖቱ መሪዎችና ምእመናን እንዳሉም አይካድም፡፡
ቀደም ሲል ጀምሮ ከኦርቶዶክስና ከሙስሊም በቀር ሌላ ሃይማኖት መኖር የለበትም የሚሉ ኦርቶዶክሳውያን ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ ለእነርሱ ጠላቶች ሆነው የተነሡባቸው በአንዳንድ አስተምህሮ፣ ባህልና ልማድ ካልሆነ በቀር በብዙ የክርስትና እሴቶች የሚመስሏቸው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እምነት ተከታዮች ሳይሆኑ ከሙስሊም ክፍል የሆኑ አክራሪዎች ናቸው፡፡ በልዩ ልዩ ጊዜያት በተለይ በኦሮሚያ ክልል በጅማና በአርሲ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ በርካታ አገልጋዮችና ምእመናን ታርደዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ የጥፋት ድርጊት በፕሮቴስታንቶች ላይም ተፈጽሟል፡፡ ይህ ሁሉ አንዱ ሌላውን አጥፍቶ በኢትዮጵያ ላይ እርሱ ብቻ የበላይ ለመሆን በሚያደርገው ጥረት የተነሣ ይመስላል፡፡ ይህ ግን በኢትዮጵያ የሚቻል አይሆንም፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክና አሁን ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ መመልከትም ይገባል፡፡
ለቤተክርስቲያን ከእኔ በላይ ላሳር የሚለው ማኅበረ ቅዱሳንም የወንጌልን እውነት ባልተረዱ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ላለማጣት ሲል የሚያቀነቅነውን “ተሐድሶ መናፍቃን” የሚለውን ነጠላ ዜማ መለወጥ አለበት፡፡ እርሱ ተሐድሶ የሚላቸው ክፍሎች ቤተ ክርስቲያን ወደእውነተኛ የወንጌል መሠረት እንድትመለስ የሚተጉ እንጂ አፍራሾቿ ወይም እርሱ እንደሚያስወራው ቤተክርስቲያንን ለፕሮቴስታንቶች አሳልፈው ለመስጠት ሰርገው የገቡ አፅራረ ቤተክርስቲያን አይደሉም፡፡ ስለዚህ በወገን ላይ ያልተገባ ዘመቻ ከፍቶ ጥይት ከማባከን ይልቅ በሙስሊም አክራሪዎች በኩል በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተቃጣውን አደጋ በተለይ በየገጠሩ ሕዝበ ክርስቲያኑንና አገልጋዮችን በጥቅማ ጥቅም የማስለም መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ለመግታት ሰፊ ጥረት ሊያደርግ ይገባል፡፡ ይህ የሚሆነው ሰይፍ በመምዘዝ ሳይሆን ወንጌልን በመስበክና ሕዝበ ክርስቲያኑን ከልማዳዊ ክርስትና ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና በማሸጋገር ነው፡፡ አሊያ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማትቋቋመው ችግር ውስጥ መግባቷ አይቀርም፡፡ ለዚህ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን ከተቃጣባት አደጋ ለመታደግ የሚጋደሉትን ወገኖች በማሳደድና ቤተክርስቲያኒቱን ለማጥፋት ከሚዶልቱት ጋር በማበር እየተሄደበት ያለው መንገድ የቤተክርስቲያኒቱን ጥፋት የሚያቃርብ ነው የሚሆነው፡፡
በሌሎቹ የኦርቶዶክስ ተጽእኖ በስፋት በማይታይባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች በኦርቶዶክሶች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና በአንድ በኩል በሰሜኑ ክፍል በእነርሱ ላይ ለሚደርሰው ጫና የሚሰጥ የመልስ ምት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ ይህም ቢሆን የተገፋውን ወገን ለሌላ ጫና የሚያነሳሳ ተግባር ይሆናል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ የሁሉም ሀገር እስከ ሆነች ድረስ የየሃይማኖቱ ተከታዮች ተከባብረውና ተቀባብለው ለመኖር የራሳቸውን እምነት በሰላማዊ መንገድና በፍቅር እንዲሰብኩና እንዲያስፋፉ መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡
በመላው ሀገሪቱ ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ የተሾሙ የመንግሥት አካላት መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ሽፋን አድርገው ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት አካል የሆኑባቸውን የሃይማኖት ተቋማት በሌሎች ሃይማቶች ላይ ወንጀል ሲፈጽሙ የሚሰጡትን ሽፋንና ማስተባባያ እንዲያቆሙ ግልጽ የሆነ ተጠያቂነት ያለበት እርምጃ ሊወስድ፣ እንደአስፈላጊነቱ ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ አመራር እንዲሆኑ ሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት አለበት፡፡ የሃይማኖት ተቋማትም በመንግሥት ሹሞች ተመክተው በየጊዜው በሌሎች ሃይማኖቶች ላይ ከሚፈጽሙት ሕገወጥ ድርጊት ሊቆጠቡ ይገባል፡፡
የአክራሪ እስልምና ኃይል የመንግሥት ሥልጣንንና የሌሎች ሃይማኖቶችን መብት በኃይል ለመቆጣጠር የተነሣ በመሆኑ አቋሙ በአስተምህሮውና በፈጸማቸው የወንጀል ድርጊቶች የተገለጠ በመሆኑ፣ በዋናነት መንግሥት ጉዳዩን ለሥልጣኑ ሲል ብቻ ሳይሆን ለዜጎች መብት መከበር ሲል በቅርበት ሊከታተለው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን የሙስሊሞች መኖሪያ ብቻ ለማድረግ የተጀመረው የአክራሪዎች ትግል ከወዲሁ መገታት አለበት፡፡ በዚህ ረገድ በአሁኑ ጊዜ ዋና ተጎጂ እየሆነች ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለሆነች መብቷን ለማስከበር ከምንጊዜውም በላይ ልትንቀሳቀስ ይገባታል፡፡ በየጊዜው በኃይል እንዲሰልሙ የሚደረጉ ምእመናን በዝተዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም በስደትና በጭንቀት ላይ ይገኛሉ፤ በሕንጻዎቿ ላይ እሳት በአገልጋዮቿና በምእመናኗ ላይ ደግሞ ሰይፍ ተቃጥቷል፡፡
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም በኃይል ለሚደረግ አስገዳጅ ተጽእኖ እጁን መስጠት የለበትም፡፡ ችግሮች እንዲፈቱና ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ሆና እንድትቀጥል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ በመተባበር መሥራት አለበት፡፡ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በሕገ መንግሥቱ ለሰፈሩ ድንጋጌዎች፣ መብቶችና ግዴታዎች መከበር፣ ለሃይማኖት ነጻነትና እኩልነትም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸው፡፡20 comments:

 1. It has been a while since the church got out of sync. Pitiful incident @ Debre Tsion Mariam in London is a typical example. Ambitious priest and his supporters vehemently undermine the members rights to choose and administer their church end up closing the church. The crux of the problem is Aba Girma. In order to restore peace this monk has to go so the majority would worship their God under their preferred priest. All reasons given by this monk have nothing to do with the cannon or dogma of the church. It was a deliberate attempt to confuse people.

  ReplyDelete
 2. amantiin ortodoksii yoomiyyuu kan biroo irratti ol aantummaa agarsiisee hin beeku! haa tau malee warri ilaacha kana qaban waa jiraniif (kan akka piroteestaantii) kun yoomiyyuu hin tau hin dadhabina! Abera

  ReplyDelete
 3. we will keep on calling the protestant wolfs as ' menafkan' forever!!!!!! we call the protestant cadres( hailemeriam, aba dulla.....menafkan) for ever.this name never ever changed. it is the right and perfect name to describe their identity.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you know that the feresy call Jesus christ of nazareth and his disciples " menafikan" ?(read bible ,Acts 24:5-6,and 14-15) so any one who is following Jesus christ in truth and in the spirit has been offended for the last 2000 years.because every thing our lord Jesus christ said is true. Please read too Luke 6:22 -23 God bless you all.

   Delete

 4. “መናፍቃን” በሚል ስም
  በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ መንጸባረቁ ቤተክርስቲያኒቱ አሁንም ድረስ ሌሎች ሃይማኖቶችን እንደ ሃይማኖት ለመቀበል ፍላጎት የሌላት ያስመስላል
  አዎ በቤተክርስቲያናችን መናፍቅ ማለት የኦርኦዶክስ ሀይማኖትን የማያምን ተጠራጣሪ ማለት ነው ሌሎች ሀይማኖቶች በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰበኩ ቀጥተኛ ሀይማኖቶች ናቸው ብለን ስለማናምን ና ዘመን አመጣሽ/አለማዊነትን የተላበሱ ስለሆኑ ምንፍቅና አለባቸው እንላለን ይህ ስድብ ከመስለህ ወደ ቤትክርስቲያንህ መመለስ ካልመሰለ ኦርቶዶክስን ለቀቅ አድርገህ ምንፍቅናህን ማመን መከተል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please do not give up your salvation ,by not reading the Bible ,i am sure if you read you will know who really the true Christian. be a christian not someone who have a religion only GBU.

   Delete
 5. ahun Gena manintachihu Tawek enant MENAFIKAN Ye Sitan LIgoch

  ReplyDelete
 6. you are also “መናፍቃን”

  ReplyDelete
 7. Aba Selama, You are the best web based information provider in Eotc history but and if you focus is only in mk and holy synod. Here in GA we have been suffered from fake Eotc mafiya priest. As I told you before St Michael Ethiopian Orthodox Kesis Efrem church is lawless and the supper role model of corruption. The fake naive priest Merkebu Hailu the wanted. Tax disputed criminal steal money with the church with his girl friend who has responsible for cashers that assigned by Merkebu. This gang did not write and. Speak basic English. He is working in farmers market as butcher. We have several problems in Atlanta eotc please send. Investigator journalist to inform this dam issue to the public. One of Zetwahido.

  ReplyDelete
 8. NIKI NIKI NIKI!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 9. ahun le yelachu beka menafk nen belu kkkkkkkkk

  ReplyDelete
 10. what a big joker you are? what is the problem calling protestants as 'menafkan' as there is no shame calling a spade is a spade.call them 'wongelawian'???? hahhahhahhhaa. parallel lines do not intersect each other. they are rather 'wonjelawian' bro. do not fool yourself they even do not oppose by this name b/c they know that they are menafkan. as long as they do not stop stealing our sheep , i want to add even one indicative name called 'tequla menafkan'

  ReplyDelete
 11. anchi menafik ahun maninetishin hodish sayreget awetash limin erasishin honesh atikerbim aba selama minamin lemin tiyalesh just say i'm from tehadiso beka geta eko arsinj mekad sil yefiyel lemd libes malet aydelem haymanotegna degmo achberbari aydelem lemanignawim endih satikebagri tawkobish neber ahun gin bedenb berasish lay mesekersh

  ReplyDelete
 12. አይ እናንተ "መናፍቃን" መባላቹ አንገበገባቹ አይደል።

  ReplyDelete
 13. Why you care about ethiopa orthodox tewahedo church you are not part of this church TEKULA

  ReplyDelete
 14. lemsafik tokorquary
  asmesayoch

  ReplyDelete
 15. genfelo weta manenetachu...tekula

  ReplyDelete
 16. All comment on the above is stupid. because u don't understand what they
  are trying to say. look other country's all religion is respect each other, so they live in peace, and no fighting who is great or who is less than great. How ever we have to have confidence what we are, that way we don't have to call names which is not their name. I think that way we can be good for our self and God. Judgement is for God only only only.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ደደቦ ታዲያ የሰው ሃይማኖት ማክበር ካወክ በቤተክርስቲያናችን ካልጨፈርኩባት ምን አስባለህ? ወደ ጴንጤዎችህ ጋር አትሄድም? ደደብ ለማውራት እንጂ ለመስማትና ለመረዳት ያልታደልክ መሃይም።

   Delete
 17. Aba Selama, We love u. no matter what always u stand with z truth. Those who doesn't know the truth are trying to discourage ur blog, but please stick with the truth and Holy God. u are the best, don't discourage by devil mk. and EWUR followers comment. Thank u . God Bless .

  ReplyDelete