Monday, November 11, 2013

በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ 37ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ

 • ብጹእ አቡነ ዮሴፍን ከምክትል ጸሐፊነት አንሥቷል

በመጀመሪያው የስብሰባ ቀን በዳላስ ያልተሳካው ቀሲስ መልዓኩ ባወቀን ከጸሐፊነት የማውረድ ጅማሬ በዚህ ጉባኤ ተፈጽሟል። አስቀድሞ በእጩነት ተይዞ የነበረውን ዲያቆን አንዱዓለም ግማዊን በቀሲስ መልአኩ ቦታ ተክቷል። በእለቱ እንዲናገር እድል የተሰጠው ዲ/ አንዷለም "አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሲኖዶስ ሥር ይገኛሉ እነርሱን ለመከላከል ጠንክሬ እሠራለሁ» በተለይም አዳዲስ የሚከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት በጸረ ማርያሞች የተሞሉ ናቸው ብሏል።

 በሁለተኛው ቀን የታየው ቅዱስ ፓትርያርኩ ለኦክላንድ መካነ ሰላም ኢየሱስ፣ እንዲሁም በ ዋሽንግተን ዲሲ ለብጹእ አቡነ ሳሙኤል የጻፏውቸው ደብዳቤዎችና አዲስ የተገዛው የቅዱስነታቸው ቤት ጉዳይ ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ ለኦክላንድ ኢየሱስ እውቅና የሰጡበት ደብዳቤ፣ እንዲሁም ለብጹእ አቡነ ሳሙኤል ለፍርድ ቤት የጻፉት ምሥክርነት ጉባኤው እንዲሽራቸው ተጠይቆ በዶ/ አባ ገ/ ሥላሴ ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ዶ/ አባ ገብረ ሥላሴ ፓትርያርኩ በሌሉበት የፓትርያርኩን ውሳኔ መሻር ሕገ ወጥነት ነው ብለው ተከራክረዋል። ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ለኦክላንድ ኢየሱስ በፓትርያርኩ የተሰጠውን እውቅና ሲቃወሙ መቆየታቸው ይታወሳል።ከቤተ ክርስቲያኑ ተውክሎ የመጣው ግለ ሰብ ለምን አቡነ መለከ ጼዴቅን ትታችሁ ወደ ፓትርያርኩ ሄዳችሁ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ አቡነ መልከ ጼዴቅ አውግዘው ስላባረሩን ሌላ አባት ፍለጋ ሄድን እንጂ እራሰቸውን ባለማክበር አይደለም ብሏል። ለምን ይቅርታ አትጠይቁም ? ለሚለው ጥያቄ ይቅርታ መጠየቅ አይከብደንም ነገር ግን የተበደልን እኛ ነን ቀርበን እንነጋገርና በደል ከተገኘብን እናደርገዋለን የበደሉን እርሳቸው ሆነው ከተገኙ ደግሞ ይቅርታ ይጠይቁናል በማለት መልሷል። ሽማግሌዎች ነገሩን ከፍጻሜ እንዲያደርሱ ውሳኔ ተላልፏል። በተመሳሳይ መልኩ ብጹእ አቡነ ሳሙኤል እራሳቸው ካቋቋሙት ከዲሲ ቅዱስ ገብርኤል በዶ/ ነጋ መባረራቸውን በመቃወም ክስ መሥርተዋል። ዶ/ ነጋ አቡነ ሳሙኤል የገብርኤል ቤ/ክር ኀላፊ አለመሆናቸውን የሚገለጥ ደብዳቤ ከአቡነ መልከ ጼዴቅ ለፍርድ ቤት በማጻፉ ቅዱስ ፓትርያርኩ ደግሞ የአቡነ መልከ ጼዴቅን ደብዳቤ የሚሽር ሌላ ደብዳቤ ለፍርድ ቤት ጽፈው ነበር። ይህ ደብዳቤ ነው ጉባኤው እንዲሽረው ታስቦ የነበረው። ይህም በዶክተር አባ ገ/ ሥላሴ ታጋይነት ሳይሆን ቀርቷል። በአባ ጽጌ ደገፋው የቀረበው ሪፖርት ፓትርያርኩ እኛ ሳናውቅ ከአትላንታ ወደ ዲሲ ለምን ተወሰዱ ? የማያገባቸው ሰዎች ቤቱን ሊያዝዙበት አይችሉም የሚል ሐሳብ ያለው ነበር። ፓትርያርኩ እየታመሙ ስለሆነ ባስቸኳይ እረፍት እንዲያገኙና ህክምናቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ሲባል በቤተ ሰባቸው አማካኝነት በክብር ወደ ቤታቸው ገብተዋል። ይህም የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስቆጣ መሆን የለበትም የሚል ምላሽ ተሰጥቶበታል።


  ብጹእ አቡነ ዮሐንስ በተሰጣቸው ኀላፊነት መሠረት የፈለገ ሕይወት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ሪፖርት አቅርበዋል። የዳላስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ኀላፊዎችንና ካህናትን አነጋግረው ቤተ ክርስቲያን ቢከፈት ተቃውሞ የለንም ነገር ግን ከኛ ራቅ ቢሉ የተሻለ ነው የሚል አስተያየት መስጠታቸውን፣ እንዲሁም የፈለገ ሕይወት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ኀላፊዎችን አነጋግረው ከሚካኤል ጋር ምንም ችግር እንደሌላባቸው ሕጋቸውም ተቀባይነት ያለው መሆኑንና ቢፈቀድላቸው መልካም ነው የሚል ሪፖርት አቅርበዋል። የዜና ምንጫችን እንደገለጸው የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንደሚቃወም አድርጎ ሲያስወራ የነበረው ዲያቆን አንዷለም ብድግ ብሎ አቡነ ዮሐንስና እርሱ የተገናኙበትን ቀን ረግሟል። «የዳላስ ጳጳስ እንዲሆኑ የመረጥሁዎት እኔ ነበርሁ ይህን ሐሳብ ያመጣሁበት ቀን የተረገመ ይሁን» ብሏል። በዚህ ጊዜ አባቶች አንገታቸውን ደፍተው ታይተዋል፣ በሁለቱ ጉንጮቹ ላይ እንባውን እያንዠቅዠቀ "ይህ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሲኖዶስ መካተት የለበትም አስተማሪው መምህር ተከስተ ለስእል አይሰገድም እያለ ያስተምራል‚ በማለት የይወገዝልኝ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኢየሱስ ቤተ/ ክርስቲያን ወደ ሲኖዶሱ ከመጣ የሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን ከሲንዶሱ አወጣዋለሁ በማለት ዝቷል። ማስረጃህ ምንድን ነው? ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ ማስረጃ የለኝም ነገር ግን ከነርሱ ሲማር የነበረ ሰው ከነርሱ ተለይቶ ወጥቶ አሁን የሚካኤል የቦርድ አባል የሆነ ነግሮኛል፣ አሁንም ወደ እኛ ለመምጣት የሚፈልግ የሚደውልልኝ ሰው አለ እርሱን ለመመለስ እያነጋገርሁ ነው ብሏል። ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴ ግን ተከስተ ከኔ ጋር ሲኖር ጥሩ አስተማሪ ነበር ምንም አግኝቸበት አላውቅም የኔ ሰንበት ተማሪዎች ግን ከኔ ከተለየ በኋላ ከሰውታል ብለዋል። አቡነ ዮሐንስም ሦስት አራት ጊዜ ትምህርቱን አዳምጨዋለሁ ምንም እንከን አላገኘሁበትም በማለት መሥክረዋል። የክሱ ጉዳይ በዝምታ እና በመገረም ያለፈ ሲሆን ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ የአቡነ ዮሐንስን ውሳኔ ይጠበቅ በማለት ታልፋል።

የዶ/ አባ ገብረ ሥላሴ መጽሐፍ አንዱና አነጋጋሪው አጀንዳ ነበር። መጽሐፉ በአቡነ መልከ ጼዴቅ ይቃጠል የሚል አስተያየት ተሰጥቶበት ነበር። ብጹእ አቡነ ኤልያስ ግን የእግዚአሔር ስም ያለበት መጽሐፍ ነውና አይቃጠልም ብለዋል። ይቃጠል የሚለው ሐሳብ እየበረታ ሲመጣ  አንድ አባት «ይህ መጽሐፍ የርስዎ ስም አለበት ለምን ይቃጠላል?» የሚል አስተያየት በመስጠታቸው መጽሐፉ ከቃጠሎ አምልጦ እንዳይሰራጭ እግዳ ይጣልበት በሚለው ተደምድሟል። በዚህ የረጅም ጊዜ ክርክር ዶ/ አባ ገ/ ሥላሴን በኃይል የተሳደቡ ካህናት ነበሩ። እራሳቸው ግን በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ምንም ሳይናገሩ በትግሥት በማሳለፋቸው ክብርና አድናቆትን አግኝተዋል።

ቀጥሎ የታየው የመምህር ልኡለ ቃል ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ነበር። መምህር ልኡለ ቃል ወደ ሲያትል እንደሚዛወር ገልጦ በስያትል በሚገኘው በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይቀበሉት እንደሆነ ጠይቆ እንደማይቀበሉት ስለተገለጠለት የራሱን ቤተ ክርስቲያን እንዲከፍት በሲኖዶሱ ተፈቅዶለታል። መምህር ልኡለ ቃል በዘመናችን እጅግ ከተገፉና በጽናት ከቆሙ የቤተ ክርስትያናችን ልጆች አንዱ ነው። ሲኖዶሱ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲከፍት በመፍቀድ ትክክለኛ ፍትሕ ሰጥቷል።

በመጨረሻም ሲኖዶሱ ብጹእ አቡነ ዮሰፍን ከምክትል ጸሐፊነት በማውረድ መላከ ገነት ገዝኻኝን በቦታቸው ተክቷል። በአትላንታ በተደረገው  ሰበር ስብሰባ ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ ይውረዱልኝ የሚል አቤቱታ ማቅረባቸውን፣ እርሳቸውም ኀላፊነቱን እንደማይፈልጉ ይቅርብኝ ብለው እንደነበር፣ ፓትርያርኩ ግን አይሆንም ሥራዎትን ዝም ብለው ይሥሩ በማለት መወሰናቸውን ዘግበን ነበር። በዚህ ጉባኤ የፓትርያርኩን አለመኖር እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የተጀመረው ሐሳብ ፍጻሜ አግኝቷል።


በጠቅላላው የነአቡነ ዮሴፍ፣ የአባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ የቀሲስ መላኩ፥ የአባ ሀብተ ማርያም፣ የቄስ ጌታቸው በሲኖዶሱ አለመገኘት፣ የማህበረ ቅዱሳን ቡድን እንደሆነ የሚጠረጠረው የነዲያቆን አንዷለም ቡድን በርካታ ጎሎችን ለማስቆጠር አስችሎታል። ጎል ጠባቂው ዶ/ አባ ገብረ ሥላሴ ብቻቸውን በመሆናቸው በርካታ ጎሎችን ለማዳን አልቻሉም፣ የመሐል ተከላካዩ ቅዱስ ፓትርያርኩ ባለመገኝታቸውም ጨዋታው ተበላሽቷል በማለት መረጃውን የሰጡን አባት ቀልደዋል።       

25 comments:

 1. menafik silemotu zemedochih lemin altsafikim?

  ReplyDelete
 2. ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት በሌላቸው ፈሪሳውያን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየወደቀች ይመስለኛል

  ReplyDelete
  Replies
  1. በእዉነት በትክክል ቤተክርስቲያንን የምታውቅ የቤተክርስቲያን ሰዉ ነህ? ማኅበረ ቅዱሳንን ታውቀዋለህ? ነገረ ሥራህ አላማረኝም……. የጥፋት መልእክተኛ እንዳትሆን?

   Delete
 3. ትልቅ ተስፋ የጣልንበት የሕጋዊው ሲኖዶስ አንድነት አሳሳቢ ነውና መጠበቅ ይገባናል፡፡ በጸሎትና በምክር የምንተጋበት ጊዜ ነው፡፡ አሊያ ቤ/ክ ማስተዛዘኛም ታጣለች፡፡

  ReplyDelete
 4. Dn andulem is real a messenger of mk he has a plan to destruct or destroy holy synod in U.S.A

  ReplyDelete
  Replies
  1. "It is not holy synod." it is holy stone." This synod is anti gospel and politicians working with Ginbot 7 and ESAT. አቡነ ዮሴፍ፣ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ ቀሲስ መላኩ፥ አባ ሀብተ ማርያም፣ መምህር ተከስተ they can't work and spread the word of God with this synod.

   Delete
 5. አቤት ውሸት። መቸም የእግዚአብሔርን ስም እየጠራችሁ ለምን እንደምትዋሹ አይገባንም። እውነቱ አይገለጥም ብላችሁ አስባችሁ ነው? ወይስ አንባቢያን እውነቱን ለማወቅ ጥረት አያደርጉም ብላችሁ?
  ቅዱስነታቸው የጻፏቸው ደብዳቤዎችም እንዲነሱ ተወስኗል። በእርግጥ ነው አባ ገብረሥላሴ ተቃውመው ነበር ሆኖም ግን አልተሳካላቸውም። በዳላስ የተከፈተው አዲስ ቤተ ክርስቲያንም እውቅና እንዳይሰጠው ተወስኗል። ኧረ እባካችሁ ነገ የሚገለጥን ነገር ደፍራችሁ አታውሩ። አቡነ ዮሴፍም በሌላ ሰው ተተክተው ሳይሆን የምክትል ጸሐፊነት ቦታ አያስፈልግም ተብሎ ነው የተወሰነው። እውነቱን እናስተምራለን ብላችሁ ያልሆነ ነገር መጻፍ ተገቢ አይደለም። "ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚያይ እግዚአብሔር አለ" እንደሚባለው ፈሪሀ እግዚአብሔር ሊኖረን ይገባል። አንባቢዎቻችሁንና ደጋፊዎቻችሁን ሳይቀር ታሳዝናላችሁ። መልካም የሆነውን ወይም ስለ እውነት በመጻፍ ልታስተምሩን ትችሉ ነበር።

  ReplyDelete
 6. እኔ እኮ ተሃድሶ ከአባ ጳውሎስ ጋር ብቻ የተቀበረች መስሎኝ ነበር። የዚህንማ ማን አስቦት። አሁን ግን የዚህም እየተቀበራችሁ ነው። አባ መልኬ ስህተቶዎትን ለማረም የሚያደርጉት ጥረት ምስጋና ያስፈልገዋል። ተሃድሶ መንጠላጠያ እያጣች ነው። ሙሉጋኔን ይሰማኻል?

  ReplyDelete
 7. Yihem ale leka, Fetari sirawin eyesera Emebirhan wileta eyewalech newina zim bilo mayet yishalal. Yemiweraw lela, yemitsafew lela, yetewesenew wisane lela. Lemaniganwim Fetari mechereshawin yasayen. Ayy kentunet, ayy dikam, endew kentu melfat. Chirash demo "LiuleKal" Seattle limeta new? Ahun new mefrat alu. Selam yenebere betekirstian lirebish new mallet new?! Yehonu lijoch shirr gudd silu ayichalehu. Endewim Aba weldeTinsae alubet yibalal. Gudd new, gena yebase yimetal leka. Fetari yitebiken. Demo bilachihu bilachihu Seattlem litibetebitu new?! ene yemigermegn, enaten amigne sanebb koyiche, leka enantem ende-Mahibere Kidusan betbach nachihu! Belu belu tewut, dirom sew siyamnut keseytan yiwedajal yibal yele.

  ReplyDelete
 8. እረ አባሰላማዎች አሁንስ አበዛችሁት!!!! ወላዲትን!
  ግን ለምን ይህን ያህል ይዋሻል ? ነገሩ በእናንተ ሳይሆን በወሬ አቀባዩ ነው የማፍረው፣ የማዝነው! እራሳችሁን እማ እንዲህ አድርጋችሁ አታዋርዱ! እውነቱ እኮ አሁን ይወጣል!

  ReplyDelete
 9. ምነው ዲያቆን እንደው አርፈህ ዝምብትል እንደቁራ ከመጮህ አልፈህ ፓትራያርክና ጳጳስ ማዘዝና መዝለፍ ገባህ። ለሁሉም ጊዜ አለው ብላለች ቀበሮ። እግዚአብሔርን መቀለጃ እንዳደረከው መጨረሻህን ያሳምርልህ። ዲያቆን ጳጳሳትን የሚያዝበትና አፍ የሚያስይዝበት ዘመን ደረሰን፤ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን ሁላችንም ተንበርከከን እንጸልይ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሜን፤ ይኸ የክርስቶስ ተከታዮች ነን የምንል ክርስቲያኖች በሙሉ ዋነኛ ስራ ሊሆን ይገባል! እለት እለት ጉልበታችን ከመሬት አይለይ! ኢየሱስ በመስቀል እዳችንን ባይከፍልና ዘላለማዊ ሕይወት ባይሰጠን ኖሮ እኛም ሁላችን እንደቁራ በመጮህ ሕዝቡን ሁሉ ባደነቆርን ነበር። እንደእስራኤል በአለም ዙሪያ ተበተን እግዚአብሔር ፈቅዶ እንደእስራኤል ወደአገራችን እስኪመልሰን ፊቱን ከእኛ እንዳያዞር የእግዚአብሔር ነን የምንል ሁሉ ክፉዎቹ እንዳያስቱን እባካችሁ አጥብቀን ወደ እግዚአብሔር እንጩህ እናልቅስ፤ መሐሪ ነውና ለስሙ ብሎ ቢምረን።

   Delete
 10. መቼም ከመጀመሪያውም እነአባ መልከ ጼዴቅ ስለ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስበውም ተጨንቀውም አያውቁም ይህ ምንም አዲስ ነገር የለውም። ስብስቡ ከገዛኽኝ በስተቀር የአንድ ጎሳ ጥርቅም መሆኑ እንኳ ምን ዓይነት ትርጉም እንደሚሰጥ ለማየት ቀላል ነው። ስለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን የዘር ፖለቲካ ስብስብ ስለሆነ አንድም የቤተ ክርስቲያን ስሜት የለውም። አንዱዓለምም ቢሆን ምንም ጊዜም ጉዞው ከጥቅም ጋር የተያያዘ ስለሆነ የዳላስ ሚካኤልን ማጣት ምንም ሳይሠራ ከሚይጋብሰው ገቢ መለየት ስለሆነ የሞትና የሽረት ትግል ሆኖበት ነው እንጂ ይህን ያህል የማኅበረ ቅዱሳን አባልነት ደረጃ የሚያደርሰውም ግብር ያለውም አይደለም በዚህ አትሳሳቱ።

  ReplyDelete
 11. እውነቱ ይነገር አባ ሰላማ የአባ ገብረ ስላሴ ከሆነ ልክናቹህ ካልሆነ ደግሞ ምንጭቹህ አባ ገብረ ስላሴ ከሆኑ ይቅርባቹህ እሳቸው የሰሙትን ሳይሆን ያሰቡትን ይናገራሉና እባካቹህ አባ ገብረ ስላሴ አይስኩል የት እንደተማሩ ጠይቁልኝ 37ኛ ሳይሆን 38ኛ ነው የሲኖዶሱ ገባዔ 15 ውሳኔዎቸ አሳልፏል ሁሉም እጅግ አስፈላጊዮቸ ነበሩ ሰውን ለማስደሰት የተወሰነ የለም

  ReplyDelete
 12. Abaselama, you are the peace maker to go our church in correct direction. You are hero in the church because providing public to truth and fact about eotc followers. The interest group debt era and terrist MK still playing game on the followers. There is no way in this day to listen cross come up to down that passed in Fewodal gov. Eprdf made great to reach goal freedom of religion in Ethiopia. Not any more time to listen gojam debteta. Please do not call mk in single name. Real name is Terror creator mk that danger in East Africa. Called them Ashbary. Erget kale women called him in nick name ergtelkkulla formerly program leader in Sunday school now he made$5000 dollar a month. He never pay tax in GA.


  ReplyDelete
 13. ውሸትእውነት ቢሆን ሁሉም ይሆን ነበር

  ReplyDelete
 14. ከዚህ የስብሰባ መንፈስ ተነስተን በውጪ ሲኖዶስ አለ የሚባለውን ዲስኩር ስንገመግም በእውነት ቀልድ ነው። ዲያቆናትና ቀሳውስት፣ አውደልዳይ መነኮሳት የሚያምሱት፤ ጳጳሳት ተብዬዎች የሚሸምቁበትና መንፈሳዊነት ያልጎበኘው ስብስብ በእውነት ታላቂቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የምወክል ነኝ ሊል በፍጹም አይችልም። ምንም ባላጋራ ቢነሳባትና የደከመች ብትመስልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቅና ሰፊ ናት። የብዙ ምሁራንና አዋቂዎችም ስብስብ ናት እንጂ የማንም ጋጠወጥ ዲያቆን ተብዬ ሁሉ የሚፈነጭባት አይደለችም። ስለዚህ እነ አባ መልከ ጼዴቅም ይሁኑ ዲያ- ዘላለም ዐረፍተ ዘመን በሞት እስኪወስዳችሁድረስ ሲኖዶስ ነን የሚለውን ቀልድ ትታችሁ ያገኛችሁትን ሰው እየሰበካችሁና የተሰጣችሁን እየበላችሁ ኑሩ። በግሌ ቤተ ክርስቲያናችን ከአቡነ ቴዎፍሎስ ሞት በኋላ ግርማ ሞገስ ያለውና በሕዝብ ፊት የከበረ ሲኖዶስ አላየሁም። ከፓትርያርክም መናኝ መሆኑ የተመሰከረላቸው ከአቡነ ተክለሃይማኖት ማንም አልነበረም። አራት ነጥብ።

  ReplyDelete
 15. aba melek is one of tehadoso

  ReplyDelete
 16. yeker yebelacu abaselamawech

  ReplyDelete
 17. Thank you Aba selama. we proud you guys, for you are doing wonderful spiritual sacrificed for truth by sharing to every body who concerned abour our church unit. MK is playing the game by trying to destroy unit of the church congregations. it doesn't matter the exile or in Ethiopian synods members must stand for truth of church. let leave a side our political problem and come together for church unit to fight MK (Satan group) . Mk is playing the game own business by big bucks or money to our church leaders. how long do we have to sleep? why do not wake up ? our church leaders are doing good business with MK. ...................

  ReplyDelete
 18. አይ አባ ሰላማ መምህር ብታጡ መምህረ ተከስተ አላችሁ …ናሽቪል እያለም አንድ ቀን ተማርን ሳንል ጌታ ነቀለልን የሚገርመው ቀሲስ ታደስ መናፍቅ ሰለሆነ መናፍቅ እንዲያስተምር ጋበዘው የናሽቪል ህዝብ መቼም ንቃተ ሂሊና የላችሁም ንቁ ከመናፍቅ ጎራ ውጡ ቀሲስ ታደስ ተከስተ መናፍቅ እንደሆነ እያውቀ ህዝቡን ወደ መናፍቅ ለመውስደ እሱን አመጣ ቀሲሱም ቢሆን ክህነቴን አለፈልግም ጸበል አያድንም ብሎ ሲናገር የነበረ ቄስ ነው ሰው እንዴት አይኑ አይከፈትለትም የናሽቪል ህዝብ ሆይ ንቃ!!!!

  ReplyDelete
 19. aye andualem selase kolejen acelemehe degmo yeamericawen sinodos letachelem new?

  ReplyDelete
 20. There is only one Holy Synod that is in Addis Ababa, Ethiopia. Our Father who temporarily separated from the mother church should should ash the Holy Synod to reinstate them in their mother church. Deacon Andualem who was supposed to accomplish this novel cause in deeded up joining the disaffected Fathers and he came face to face with Tehadiso! On the cementary of Tehadiso the is affected Father will be reinstated in their Mother Church.
  Amen

  ReplyDelete
 21. Abet!!!!!! egziabher yeker yebelachu. beegziabher sm lekbrachu ena lehodachu kemitnoru mn alebet egziabherin fertachu haymanotachuhun sebkachu btalfu?

  ReplyDelete
 22. የኢትዮጲያዊነት አንዱ ከሌላው ህብረተሰብ ለየት የሚያደርገን የነበረው ባህላችን ያስተማረን መከባበርን ነው። ትንሽ ትልቅን ማክበር። በጣም የሚያሳዝነው “ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች” አሉ የድሮሰዎች። ትልቆች አባቶችን፣ ሃይማኖታችን እስካሁን ያቆዩት፣ ተሰደውም በሰው አገር ቅድስት ቤተክርስትያንን እያገለገሉ አሉ፣ አባቶችን የምትሳደቡና የምታዋርዱ ግለሰቦች ስለተሳደባችሁ እናንተ ለኦርቶዶክስ ተቆርቋሪ አያደርጋችሁም ወይም ትክክል ናችሁ ማለት አይደለም። መጀመሪያ እያንዳንዳችሁ እራሳችሁን በኦርቶድክስነታችሁ ለቤተክርስቲያን መጠናክር ምን አድርጋችኋል? ምንያህል የኦርቶዶክስን ሃይማኖትን በጥልቅ ታውቃላችሁ? እግዚአብሔርን የሚያውቅና የሚያከብር ሰውን: አባቶችን “መሳደብ አላዋቂነት ነው።” ለመሆኑ እናንተ የምትሉት እውነት ሌላው የሚለው ውሸት ብለን የምናስብ ይመስላችኋል ድሮ ቀረ በዚህ ሰዓትና ዘመን ሁሉም እውነቱን: ለመረዳት: ያጠናል: ይመራመራል :ይደርስበታል:: አሉባልታና ስም ማጥፋት ማንንም አይጠቅም ጊዜያችሁን ወደእግዚአብሄር ቤት የሚያቀርባችሁን፣ ለመልካም ስራ ስሩበት:: አንድ ስው ሲያጠፋ አንድ ክፍለሃገር አትሳደቡ አንድ ሰው ሙሉ ክፍለሀገር አይወክልም፡ አስተሳስባችሁን አታጥቡት፡ የሰው ወሬ ተከትላችሁ እውነቱን ሳታውቁ ለውሳኔና ለስድብ አትቸኩሉ።
  እግዚአብሔር ኢትዮጵያና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን። አሜን።

  ReplyDelete