Thursday, November 7, 2013

ማኅበረ ቅዱሳንንና አባ እስጢፋኖስን ምን አፋቀራቸው


ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ስም የሚነግድ ስብስብ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚያስብ አለመሆኑን ከዚህ ቀደም በማስረጃ ላይ ተመሥርተው በቀረቡ የተለያዩ ጽሑፎች ተመልክቷል፡፡ ዛሬም ቢሆን ማኅበሩ ጥቅሙ እስካልተነካበት ወይም እስከ ተጠበቀለት ድረስ ዐመፅን ጽድቅ፣ ጽድቅን ዐመፅ፣ እውነትን ሐሰት ሐሰትን እውነት፣ ሌባውን ታማኝ ታማኙን ሌባ ከማለት አይመለስም፤ ይህን በተግባር እያስመሰከረም ነው፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ አባ እስጢፋ በተለይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጰስ ሆነው ከተሾሙ በኋላ እያደረሱ ያለውን አስተዳደራዊ በደልና እያስፋፉ ያለውን ሙስና ከመኮነን ይልቅ በማበረታታቱ ሥራ መጠመዱ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ማኅበሩ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ከእርሳቸው ጋር በፍቅር የወደቀበት የፍቅር ጊዜው በመሆኑ ነው፡፡

እርግጥ ቤተክህነት ውስጥ በጥቅም የሚለካ እንጂ እውነተኛም ዘላቂም የሚባል ፍቅር እንደሌለ ከማንም ስውር አይደለም፡፡ አባ እስጢፋኖስና ማቅ በፍቅር እፍ ያሉትም ማቅ አገር ያወቀውንና ፀሐይ የሞቀውን የአባ እስጢፋኖስን ገበና ሊሸፍን፣ እርሳቸውም በበኩላቸው ማቅ ዘወትር የሚያልመውን ቤተክርስቲያንን የመቆጣጠር ህልሙን በማሳካቱ ሂደት ሊረዱትና በቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቅሙ እንዲከበርለት ሊያደርጉለት “በዓይን ቋንቋ” ዓይነት ስለተግባቡ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በቤተክህነት ታሪክ ባልተለመደ መልኩ የማቅ ሰዎች ካህናቱን አሰልጣኞች ሆነው የተሰየሙበት ሁኔታ ታይቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም ማቅ ቤተክርስቲያንን እንዳሻው ለማድረግ እንዲያመቸው “የለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናት” ወዘተርፈ በሚሉ ከንግግር ባላለፉ መደለያዎች እርሱ ቤተክርስቲያኒቱን በተዘዋዋሪ ሳይሆን በቀጥታ በቁጥጥሩ ስር የሚያውልበትን በር ወለል አድርገው ከፍተውለታል፡፡ ከዚህ የተነሣ ማቅ ለአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ካህናት በለውጥ ስም መተዳደሪያ ደንብ እስከማርቀቅና በየአድባራቱ እንዲሠራጭ እስከማድረግ ያደረገ ሲሆን፣ ይህም የብዙዎችን ቁጣ በከፍተኛ ደረጃ መቀስቀሱ ታውቋል፡፡


በማቅ ሰዎች ብዙ የተባለለት “የለውጥ አመራሩና ፀረ ሙስና የተባለው አካል” በትክክል ቢሠራ ኖሮ ለቤተክርስቲያን እጅግ እንደሚጠቅም ይታመናል፡፡ እኛም ይበል ባልነው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የሚያሳዝነው የለውጥ አመራር የተባለው ከዚያ በተቃራኒ የሙሰኞች መሸሸጊያና ንጹሃንን ማጥቂያ እየሆነ መምጣቱ ነው፡፡ ምክንያቱም የለውጥ አመራር የተባለው ስብስብ ባሕርዩ ይህን ለማድረግ ስለማይፈቅድለት ስለለውጥና ሙስናን ስለመዋጋት እየለፈፈ በተግባር ግን ሙስናን የሚያስፋፋና መጥፎ አስተዳደርን የሚያሰፍን ሆኗል፡፡ ታዲያ ማቅ ስለአመራሩ በጎነት ብቻ ከሚነግረን ብዙዎች ሮሮ የሚያሰሙት ከግፍና ከበደል መብዛት የተነሳ መሆኑን እንዴት ያጣዋል? ለምንስ የእነርሱን ጩኸት በአፅራረ ቤተክርስቲያንነት ይፈርጀዋል? 
ማቅ ጥቅሙን ብቻ እንጂ ስለሌላው ደንታ እንደሌለው ከዚህ ተግባሩ መረዳት ይቻላል፡፡ የጥቅም በር ስለተከፈተለት ብቻ በአባ እስጢፋ እየደረሰ ያለውን ግልጽ ዘረፋና የሰፈነውን መጥፎ አስተዳደር መልካም አስተዳደር አድርጎ ለመሳል ይሞክራል፡፡ አባ እስጢፋ በንቡረ እድ ገብረ ማርያም ተወጥኖ የነበረውንና ዘራፊዎችን እንቅልፍ የነሣውን የሙዳየ ምጽዋት በሕጋዊ መንገድ የመቁጠር የለውጥ አሰራርን በመቅልበስና ድራሹን ለማጥፋት ወደር ያልተገኘለትን ሙስና በመፈጸምና በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም የማቅ ደጋፊና አቀንቃኝ ናቸው እየተባሉ ቢታሙም በብዙ ደብሮች ውስጥ ይካሄድ የነበረውን የሙዳየ ምጽዋት ግልበጣና የገንዘብ ዝርፊያውን ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን መካድ አይቻልም፡፡ ግሩም ውጤትም ታይቶ ነበር፡፡ በአንዳንድ ደብሮች ውስጥ የተጀመረው ግልጽነት ያለው አሰራር እስካሁንም የቀጠለ ቢሆንም፣ ያን የተዘረጋ መልካም አሠራር አባ እስጢፋ ሰብረው ለመግባት ሙከራ እያደረጉ ሲሆን ቀላል እንዳልሆነላቸው ይነገራል፡፡ ሰብረው እንዲገቡ ለማድረግ በአሁን ጊዜ ዘራፊዎቹ እየተጠቀሙ ያለው ስልት ለአባ እስጢፋ የሁለት እሁድ የመድረክ ገቢ ለጅማ ፕሮጀክት መልቀቅ ነው፡፡

በቅርቡ ከሥራ አስኪያጅነታቸው በለቀቁት መጋቤ ሐዲስ ይልማ ምትክ አባ ገብረ ማርያም ቢገቡ ጥሩ ይሆን ነበር የሚል ወሬ መናፈሱን ተከትሎ አባ እስጢፋ የተጀመረው ብልሹ አሠራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማሰብ ይመስላል “ሞቼ ነው ቆሜ” በማለት ፊታቸውን ወደሌላ አዙረዋል፡፡ የማቅ ሰዎችና እንደሀራ ያሉ ብሎጎች በንቡረእድ ገብረ ማርያም ለተሠራው ውጤታማ ስራ አቡነ ጳውሎስን ለመውቀሻ እንደምክንያት ካልጠቀሱት በቀር ተገቢውን ዋጋ አልሰጡትም፡፡ በጎ ጅምሩን በየሚዲያው ማበረታታት ሲገባ ያን ሲያበረታቱ አልታየም፡፡ ስለዚህ ማቅ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለጥቅሙ የቆመ ስብስብ መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል፡፡ ንቡረ እድ ከሥራ አስኪያጅነት ሲነሱ ድምፁን አለማሰማቱና በአዲሱና አብዝቶ በሚያወራለት የለውጥ አመራር ውስጥ እንዲካተቱ አለማድረጉ ማኅበሩ ከአመፅ እንጂ ከእውነትና ጽድቅ የራቀ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ዛሬ በስም እንጂ በተግባር የሌለው የለውጥ አመራር እየፈጸመ ያለውን ሙስናና ብልሹ አሠራር ከመኮነን ይልቅ ጥሩ ጅምር አድርገው ማቅረባቸው አባ እስጢፋና ደላሎቻቸው በብዙዎች ላይ እያደረሱት ያለውን በደል እንደ ትልቅ ለውጥ እንዲታይ ማድረግ ነው የሚሆነው፡፡ የዝርፊያው ተቋዳሽ የሆኑቱ ይህን መጥፎ አስተዳደር እያሞጋገሱ ቢገኙም፣ ያለጥፋታቸው የደላሎቹንና የአባ እስጢፋ ኪስ በአመፅ ትርፍ ለመሙላት በዝውውር መስኮቱ በግፍ እየተሸጡና እየተለወጡ የሚገኙት አገልጋዮች ሮሮና ብሶት ግን ሰሚ አጥቶ ጭራሹኑ እንደአፅራረ ቤተክርስቲያን እንዲታዩ እያደረገ ነው፡፡

ሕዝበ ክርስቲያኑ ሳይቀር መጥፎ ሥነ ምግባራቸውን ተመልክቶ ይነሡልን የሚላቸውን አስተዳዳሪዎች አይነሱም በማለት አባ እስጢፋ የሚከላከሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህ መቼም “በደረቁ” የሚሆን አይደለም፡፡ ለምሳሌ የጠሮ ሥላሴ አለቃ አባ ነአኩቶ በሚያሳዩት የሥነምግባር ችግር ይኸውም መነኩሴ ነኝ ካሉ በኋላ ከሴቶች ጋር ያላቸው ያፈጠጠ ጾታዊ ግንኙነት፣ በአውደ ምህረት ላይ በቤተክርስቲያን ስም የተለመነውን ገንዘብ ወደራሳቸው ኪስ በግልጽ የሚጨምሩ መሆናቸውና ሲጠየቁም፣ “እኔ የለመንኩትን ለማንም አልሰጥም” የሚል ምላሽ በመስጠት የሚዘርፉ መሆናቸውን ሕዝቡም ካህናቱም በግልጽ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን ከቦታቸው እንዲነሱ ግፊት ሲደረግባቸው፣ ሲዘርፉ ከኖሩት ላይ 50 ሺህ ብር “ቆንጥረው” ለአባ እስጢፋ በመስጠታቸው “በአለህበት እርጋ” ተብለዋል፡፡ አባ ነአኩቶን መጠጥ ቤት አግኝተው “ምነው ይህን ሁሉ ሰው ማባረር ጥሩ ነወይ?” ብለው ሲጠይቋቸው “ማን ምን ያመጣል? ለአባ እስጢፋኖስ እኮ 50 ሺህ ብር ሰጥቻቸዋለሁ” ማለታቸውን በጆሯቸው የሰሙ መስክረዋል፡፡ አባ እስጢፋ ጠሮ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ድረስ በመገኘት “ከአንድ ጎጆ ላይ 3 ሳር ቢመዘዝ ጎጆው ያፈሳል ወይ?” ብለው ሕዝቡን በመጠየቅና “አያፈስም” በማለት አባ ነአኩቶን ባሉበት እንዲረጉና ያሻቸውን እንዲያደርጉ ፈቃድ ሲሰጧቸው፣ “የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት የጥቂቶች መጠቀሚያ ሊሆን አይገባም” ያሉትን ደግሞ “የሚመዘዙት ግን ይመዘዛሉ” በማለት ማስፈራራታቸው ተሰምቷል፡፡

የአባ እስጢፋ ሚስትና ዕቅብት በሚገኙበት በኡራኤል ቤተክርስቲያን ደግሞ ሰሞኑን ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት እንዲሁም የቤተክህነት ታዛቢዎችም ባልተገኙበት አኳኋን በ170 ሺህ ብር ቤት እንገነባለን ብለው “ጌታቸውን” አባ እስጢፋን የተማመኑት እነ ወ/ሮ መና ያለአንዳች ሕጋዊ ጨረታ 80 ሺህ ብር ቀብድ ከፍለዋል፡፡ የደብሩ ቁጥጥር ግን ይህ ለምን ይሆናል? ሕግንና ሥርዓትን የተከተለ አይደለም በማለት ይቃወማል፡፡ በዚህ ጊዜ በሙስናው ውስጥ እጃቸውን የነከሩት ዕቅብት መናና የደብሩ አለቃ “ፀረ ሙስና” አቋም ያሳየውን ቁጥጥሩን “ፀረ ልማት ነህ” በማለት ሊያሸማቅቁት ሞክረዋል፡፡ እርሱም ታዲያ ፀረ ልማት ከሆንሁ ለምን አታስቀይሩኝም ብሏቸዋል ነው የሚባለው፡፡ ባለው አሰራር መሰረት ጧፍ እንኳን የሚሸጥ ከሆነ በግልጽ ጨረታና የሀገረ ስብከቱ ታዛቢዎች በተገኙበት ነበር የሚከናወነው፡፡ አሁን ግን “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ ታሳድራለች” እንደሚባለው አባ እስጢፋን በመተማመንና መናም በዕቅብትነታቸው በማስፈራራት ያለከልካይ ሕገወጥ ሥራዎችን እየሰሩ ቤተክርስቲያንን በማራቆት ላይ ይገኛሉ፡፡ ታዲያ ይህን ነው ማቅ የለውጥ አሠራር  እያለ የሚያሞካሸው?

ሌላውና ብዙዎችን እያሳዘነ የሚገኘው አባ እስጢፋ በድብቅ ያደረጁት ሰራተኛ ቀያሪ ወይም አዘዋዋሪ ቡድን ነው፡፡ በዚህ በኩል በዋናነት ስሙ የሚነሳው የቦሌ መድሃኔ ዓለም ጸሐፊ የሆነው ሰለሞን በቀለ ነው፡፡ ሰለሞን የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አንተም አብረህ ዝረፍ እንደሚባለው ከመጣው ሥራ አስኪያጅ ጋር ተግባብቶና ተመሳስሎ በመስራት የሚታወቅና በተለይ በአሁኑ ወቅት በሰራተኛ ዝውውሩ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሚሠሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ዝውውር ከተፈጸመባቸው ሰራተኞች መካከል ከቦሌ ማርያም ፀሀፊ ቁጥጥርና አለቃ ደሞዛቸው ተቀንሶ እንዲቀየሩ የተደረገ ሲሆን ፀሀፊው በአየር ላይ ተንሳፋፊ እንደሆነ ነው፡፡ መካኒሳ አቦ ፀሀፊ እያለ በላዩ ላይ ሰው የተመደበበት ሲሆን ለእርሱ ግን ደብዳቤ አልደረሰውም ነው የተባለው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከቦሌ መድሃኔ ዓለም፣ ከጠሮ ስላሴ (ይመዘዛሉ የተባሉት ሳሮች መሆናቸው ነው) ወዘተርፈ የቅያሬ ሰለባ ከሆኑት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እነዚህና ሌሎቹም ባለፈው አርብ ግንቦት 22/2006 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ሀገረስብከትን አጨናንቀው ያረፈዱ ሲሆን አቤቱታቸውም እድገት ይሰጠን ለማለት ሳይሆን በጥቅምት ወር ላይ አባ እስጢፋ ቅያሬ ቀርቷል ብለው በአደባባይ የነገሩንን ለውጠው ደላሎቻቸውና ቀያሪዎቻቸው ሕግና መንግሥት ባለበት አገር ላይ ጉቦ በልተው ከእንጀራችን አፈናቅለውናል የሚል ነው፡፡ ነገር ግን አባ እስጢፋኖስ በፊትለፊት የሚናገሩትና ከመጋረጃ በስተጀርባ የሚሰሩት የተለያዩ በመሆናቸው ሊያናግሯቸው እንኳን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጉቦ ሰጥተው የተዛወሩት ስማቸው ፔሮል እንዲነክስና ከዚያ በኋላ ከሳሽ ተከሳሽ ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ቢጓተት የእነርሱ ጉዳይ ባለመሆኑ ለዚህ ጊዜ ለመግዛት እንደሆነ ብዙዎች ጠርጥረዋል፡፡ ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አንድም ወደቦታው የተመለሰና አቤቱታው የተሰማ ሰራተኛ የለም፡፡ በሕግ አምላክ ማለት ይህን ጊዜ ነው፡፡
  
አሁን ትልቁ ጥያቄ  ዝውውር ፈጻሚ ቡድን በስውር ማቋቋም ለምን አስፈለገ? የሚለው ነው፣ ጥያቄው በጉልህ መነሳትና ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ትልቅ የሙስና በር ሆኖ የቆየው ሰራተኞችን ያለአንዳች ምክንያት ከአንዱ ደብር ወደሌላው ደብር፣ ከአንዱ ሥራ ወደሌላው ስራ ግልጽነት በጎደለው አሰራር የማዛወሩ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ሕገወጥ ክፍል ውስጥ ለመሸጉ አዘዋዋሪዎች፣ ደላሎችና ጉቦ አቀባባዮች ይህ ዳጎስ ያለ ገቢ የሚያገኙበት የስራ መስክ ሆኖላቸዋል፡፡ ጉቦ ሰጥተው የሚዛወሩትን የሚጠቅም፣ ያለአንዳች በደል ከቦታቸው ደሞዛቸውን ቀንሰው የሚዛወሩትን የሚጎዳ ተግባርም ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ላይ አንድ ደንብ ካልወጣ፣ አባ እስጢፋም በዚህ ብልሹ አሰራራቸው ከቀጠሉና ሕግ ባለበት አገር እየተደረገ ያለው ህገወጥ ዝውውር በሕግ እንዲቆም ካልተደረገ ቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ምስቅልቅል ያስከትላል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰራተኞች አስፈቅደው ዕረፍት ለመውጣትና ወደክፍለ ሀገር ሄደው ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅም ሆነ ጉዳያቸውን ለመከወን እንኳን ድፍረት ያጡበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም አስፈቅደው ከሥራቸው ዘወር ሲሉ ስራቸው ለሌላ የሚሰጥበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነውና፡፡ በዚህ መንገድ አስፈቅደው ወጥተው የቀሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እንኳን ዘወር ብለው በቦታቸው ላይ እየሰሩም በላያቸው ላይ ሰው የሚመደብባቸውና በአየር ላይ የሚንሳፈፉ እየበረከቱ ነው፡፡ ስለዚህ የሚመለከተው አካል እንዲህ ያለውን አሰራር በማፍረስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕግንና መልካም አስተዳደርን ማስፈን አለበት፡፡ ዝውውር በዘፈቀደና በጉቦ የሚከናወንበትን አሰራር በመለወጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበትን ሥርዓት መዘርጋት ለነገ የማይባል ሥራ ነው፡፡

በአጠቃላይ በቤተክርስቲያኗ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚታየው ሁኔታ ከቀደመችው እስራኤል ውድቀት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ በሙስናና በብልሹ አስተዳደር የላሸቁ መሪዎቿ ወደልባቸው ይመለሱና ንስሐ ይገቡ ዘንድ፣ ጥለውትና ለሌላው ላልደከመበት ትተውት ለሚሄዱት ገንዘብ ብለው በወንድማቸውና በወገናቸው ላይ መጨከን የለባቸውም፡፡ ስለዚህ እየሰሩ ያለውን ግፍ በመጠቆም በድርጊታቸው የብዙዎች ሕይወት እየተመሰቃቀለ መሆኑን እንዲያስቡና ፍትሕንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንዲነሳሱ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት እናሰማቸዋለን፡፡
ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ። ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ። አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ ከዚህም ጋር። እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ። ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌምም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።” (ሚክያስ 3፥9-12)

በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው። ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል። እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው ክፋትን አያደርግም ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።” (ሶፎንያስ 3፥3-5)

አዎን “እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው ክፋትን አያደርግም ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።”
      
15 comments:

 1. Hey You,

  You talk!
  MK work!

  Check this out, Tewahedo iPad Apps, What did you do??? just talking gossips, right? Libona yistih.
  http://www.mkus.org/Default.aspx?tabid=36&ctl=Details&mid=371&ItemID=559

  ReplyDelete
 2. I'm NOT a member of MK but I wish to pose a polite query to Abba Selama: you know that our church is faced with huge challenges from non-Christians, internal disunity, waste, gross corruption, inadequate evangelization, weak care for our monasteries including the lack of maintenance of our historic legacy: our monastery in Jerusalem, church schools ("Abennet"), etc. etc. In the face of all this challenge: you prefer to use all your energy and precious time to besmirch MK. Is this a Christian thing to do? Don't you think that the Almighty is looking at the evil you're undertaking instead of having an open dialogue with MK and resolve your conflict with it in a peaceful and Christian manner?

  ReplyDelete
 3. arife zegeba new. berche aba selama

  ReplyDelete
 4. የቤተክህነቱ የለውጥ አመራር መዋቅር፣ መንግስት BPR እያለ የሚጠራት አይነት ናት፤
  ምን ሆነ መሰላችሁ…………..መንግስት BPR አስጠንቶ ወደ ትግበራ ሲያመራ የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች እንደምንም ተሽሎክልከው በፌድራል መስሪያ ቤቶች ውስጥ አመራሩን ያዙ እና የራሳቸውን ሰው ዋና ዋና ቦታ ላይ ደለደሉት……..ግን ምን ያደርጋል የማ/ቅዱሳን ሰዎች ወያኔን ያራሩጡታል እንጂ አይቀድሙትም………..ወያኔ BPR ላይ መቀደሙን ሲያረጋግጥ ወዲያውኑ በየክልሉ የሚገኙ የፌድራል መንግስት መስሪያ ቤቶች/ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ / በአካባቢው ተወላጆች እንዲመራ አደረገ እና የማህበረ ቅዱሳንን ሰዎች አየር ላይ አንሳፈፋቸው ፡፡
  እኔም ወያኔን እሰይ ደግ አደረክ፣ እደግ ተመንደግ ብዬዋለሁ፤ ምክንያቱም በየትኛውም ቦታ ላይ የሚሰራ የመንግስት የልማት ስራ የአካባቢውን ሰዎች መጥቀም ይኖርበታል፡፡ ኦሮሚያ ፣ ደቡብ እና ሱማሌ…..ወዘተ ላይ በሚሰራ የልማት ስራ ተጠቃሚዎቹ ጎጃምና ጎንደር ብቻ የሚሆኑት በየትኛው የሂሳብ ስሌት ነው
  ማህበረ ቅዱሳን ግን አቅም ስላጣ ነው እንጂ፤ የማ/ቅዱሳን ህልም ከዛሬ 100 ዐመታት በፊት አጼ ሚኒሊክ የሰሩትን የግፍ ስራ መድገም ነው፡፡……….በፍጹም አይሳካም፡፡
  ለማህበረ ቅዱሳን ሰዎች ማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት በአንድ ወቅት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተናገርኩትን በመድገም ነው………”እኔ በደሜ የሲዳማ ብሔረሰብ አባል ፤ በዜግነቴ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ “፡፡
  ለእነዚያ ትምክህተኞች ለሆኑት የማህበረ ቅዱሳን በጎች የአቶ ሽፈራው ንግግር ትልቅ መልዕክት አለው፡፡
  ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መቆጣጠር፣ ሀገሪቱን መቆጣጠር ነው በሚል የተሳሳተ ስሌት መነኮሳቱንና ካህናቱን አታስቸግሩ፣ አርፋችሁ ተቀመጡ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዘረኛ ጴንጤ። አሁን እኮ አንተም ሃይማኖት አለኝ ትላለህ። ዘረኛ የዲያብሎስ መፈንጫ።

   Delete
 5. Do you read what you are writing? The post prior to it says that MK is on the verge of going down and now with the speed of light you are saying that MK is going to control the whole Process of the church.
  Are you out of mind?
  YOU are a day dreamer and worthless.
  May God help you to soften your hatred!

  ReplyDelete
 6. መልካሙን ዜና የምተሰሙን ከቶ መቼ ነዉ? ሁሌ መከራ፣ ውድቀት፣ ሀዘን፣ አመጽ . . . እኒህ እንዲህ በአደባባይ የምታዋርዷቸዉና ሥማቸዉን የምታጠፏቸዉ አባቶችና ማኅበራት አንዳች በጎ ነገር የሌላቸዉ ሆኖ ነዉ? የማናዉቃቸዉ ቢሆን እንዴት እንጠላቸዉ ነበር ደግነቱ ማንነታቸዉን መልካም ሥራቸዉን እና ለቤተክርስቲያ የሚፈጽሙትን ተጋድሎ ስለምናዉቀዉ በእናንተ አሉቧልታ አንረበሽም፡፡ ደግሞም ከአማናዊቷ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወገን ካልሆነ እንደናንተ ካለ አዉቆ አጥፊ አካል መልካም ምስክርነት ሥለማይጠበቅ የምታወሩት ሁሉ አያስደንቅም፡፡ ለእነርሱ ግን እወቁት ይህን የእናትን የጥፋት ዘመቻ ከቁብ ሳይቆጥሩ የሚፈጽሙት አገልግሎት በራሱ ሰማእትነት ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 7. Serious question to a concerning party. Does the church realy have to be managed by priests? All these things we see in our church are the result of ambitious priests craving for wealth and fortunes. Urban monk like Aba Girma of London is typical example.

  ReplyDelete
 8. ምን አለፋችሁ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መነኮሳቱና ጰጰስን የሚሉቱ ድስት ተሸካሚዎቹ ቤተ ክርስቲያኒቱን ባፍ ጢሟ ይደፏታል። አድመኝነት፤ ተንኮልና ሴራ፤ ዘረኝነት፤ ጉቦ፤ ውሸትና ማጭበርበር፤ ማስመሰል፤ ዝሙትና ስካር፤ ጥላቻና በቀል የሌለበት የቤተ ክርስቲያን ስፍራ የለም። ወንጌል የለም። ተረትና ልምድ፤ ባህልና ወግ ሃይማኖት ሆኗል። እውነት መናገር ወንጀል ነው። የደመወዝ ቅጥረኛ እንጂ እምነትና ከአማኝ የሚጠበቅ ስነ ምግባር የለም። በአጠቃላይ ፈሪሃ እግዚአብሔር ጠፍቷል። በእውነት መቅደሱን የረከሱ ሰዎች ተቆጣጥረውታል። ቤተ ክርስቲያን «ኢካቦድ» ከምትባልበት ሰዓት ላይ ደርሳለች። የታቦተ ጽዮን በፍልስጤማውያን እጅ መውደቅ መነሻው ይኼው የመቅደሱ ሰዎች ርክስና ውጤት ነበር። ወደድንም ጠላንም፤ አመንም አላመንም ርኩሰት በመቅደሱ ደጃፍ ነውር መሆኑ እስከቀጠለ ድረስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን «ኢካቦድ» በደጅ ነው። አሁንም እየሆነ ነው። ሲኖዶስ በሉት ማቅ ሁሉም «ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ በልቡ ግን ከእኔ ርቋል» የተባለው ቃል ውጤቶች ናቸው።

  ReplyDelete
 9. ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ!!
  ጌታ ኢየሱስ በውርንጭላ ተጭኖ ኢየሩሳሌም ሲገባ ካህናት፤ጸሐፍት ፈሪሳውያን ከራሳቸው አለፈው ሕዝቡን እንዳያመሰግን
  ዝም አደረጉት ጌታ ግን መናገር አፍ ያልከፈቱ ሕጻናትና እና መናግር የማይችሉት ግኡዛነን ነገሮች አፋቸው ከፍተው እነዲያመሰግኑት አደረገ!!
  የዚህ ብሎግ ጸሀፊዎች ግዑዛን አይደላችሁም ግን ሕጻናት ናችሁ የቤተክርስቲያኒትዋ ብጹዕ የሚለውን አባትነት ከተቀበሉ በኃላ በፍቅረ ነዋይ እና በፍቅረ ብእሲት ከተጠመዱበት መረብ ያልወጡ እንደ እነ አባ እስጢፋኖስ በመሳሰሉት አመንዝራ አባቶች ቤተክርስቲያኒትዋ አደጋ ላይ ነች የምትጠፋውም ሕዝቡን ለማታለል እነሱ እንደሚሉት በሌላው እምነት ተከታዮች ሳየሆን በእነሱ እንደሚሆን መጠራጠር አያስፈልግም፡፡
  በማስረጃ እንየው አባ እስጢፋኖስ ሽማግሌው / ባህታዊውን ፓትርያርክ / በማታለል አዲስ አበባ ሲገቡ ያልተማረ ሰው አያፍርምና በማስፈራራት በአንድ ቀን ስብሰባ 1.6ሚልዬን ብር መዋጮ እንዲሰጠቻው የአድባራቱና ገዳማቱ አስተዳዳሪዎችን በግልምጫና በማስፈራረት እንደፈረስ በማሽካካትም ጭምር ሲጠይቁ ለገንዘብ ፍቅር ያላቸው አቋም የሚያውቁ አድባራት አስተዳዳሪዎችም የገንዘብ አቅማቸው እንከኳ ከሚመለከታው ሳይመክሩ እኔ 100 ሲህ እኔ 20ሺህ እኔ ኮምፕዩተር እኔ ምርጥ የቆንጆ ሴት መቀመጫ አቅርባለሁ በማለት በገቡት ቃል መሰረት ከ1.6 ሚልዮን ቃል ገብተው ከዚህ ውስጥ ጥቂት ገንዘቦች ማረጋጋጫ ባይኖርም ባንክ ገቡ ቢባልም የበለጠውን ግን ቀን ተቀን ከቢሮአቸው በማይለዩትና ከሳቸው በፊት ፍርድ በሚሰጡት ደላላዎቻቸው አማካኝነት ገንዘቡ ወደ እሳቸው ባንክ እንዲገባ ሲደረግ ተገዝተው የመጡት እቃዎችም ለምሳሌ ከመድሀኔዓም ሕዙናን መሰከይ የመጣው ዘመናዊ ላፕቶፕና ምርጥ የሴት ወንበር ለራሳቸው ተቀብለው ወስደዋል፡፡
  በቅጥርና ዝውውርም በተመለተ እሳቸው እገሌን ቅጠር እገሌን አዛውር እያሉ ብሩን እራሳቸው ለጂማ እያሉ / በልጅ አመካኝቶ ይበላል አንጉቶ / እየተቀበሉ በፐርሰንት የሰው ሃይል አስተዳደሩን የድሮ ውሽማቸው ልጅ የሆነው ዮናስ ፍቅረን / ገንዘብ ተቀብሎ የመቅጠርና የማዛወር ልምድ ያለው አደራዳሪው የማደጎ ልጅ ቀሲስ ዳዊት ያሬድን ፤ ደፋሩ አቀራራቢ መልከ መልካሙ ወጣጥ ጫት ቃሚው ታዴዎስ እና ሆደ ሰፊው መምህር ይልማ ቸርነትን በማደራጀት ከተማዋን እጥብ አድርገዋታል አንድ ሥራ ላይ 2 ሰዎች ይመደባሉ 2ቱ የከፈሉ ስለሆነ ደብሩ ይጎዳል እንጂ የ1ዱ ቅጥሩ አይቋረጥም ምክንያቱም/ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም // ብቻ የቤተክርስቲያኒትዋን ችግር እንዲቀረፍ ችግርዋን በግልጽ ለአደባባይ የምታውሉ ባለሙያዎች እግዚአብሄር ይባርካችሁ ግን አባ እስጢፋስ 10 ውሽሞችን ለማጥገብ ቤተክርስቲያኒትዋ እስከመቼ ይሆን የሚጎዳት ጸሎት ያስፈልጋል ፓትርያርኩም ካህን ናቸው ክህነት እንዲከብር ቢያደርጉ ባሕታዊ ናቸው ባሕታዊ እና ሽፍታ በዱር መኖራቸው ቢያመሳስላቸውም ጉዳያቸው እንደሚለያይ መለየት አለባቸውና ሌባና ከሀቀኛ መለየት ቢችሉ አባ እስጢፋኖስ እያሉ የጽድቅ ሥራ ይሠራል ማለት ግን ዲያብሎስ ንሥሃ ገባ ማለት ነው፡፡
  በዚህ ሳምንትም አዲስ ቡድን አደራጅተዋል ከኮተቤ ፋኑኤል ወደ ሰዋስው ብርሀን ጳውሎስ ብር 70000.00 ከፍሎ ያደገው አለቃ የሰአሊተ ምህረት ማርያመ ቀዳሹ የነበረና የሰው ደለላ የሆነው ሴት ልጆችን ወደ አረብ በመላክ የከበረው ሰው አማካኝነት ጉቦ አቀባዩን የማደጎ ልጅ ዳዊት ያሬድን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሆንለት አለቃ ያልሆነውን አላቃ ፤ጸሐፊ ያልሆነውን ጸሐፊ እያለ የድጋፍ ደብዳቤ በማስፈረም ላይ ናቸው ሥራ አስኪያጅ የሚመድበው ክፍል ልብ እንዲልበት ነው፡፡

  ReplyDelete
 10. yemigerimew church yaliseru ena yaladegu lebeal bemesebiseb woyim kidase lay bicha derisew yemihedu sewoch asiteyayet lemesitet memokerachew new.ene bebekule church new yadegihut ahunm ezaw negn.abaselama yeman endehone alawukim.but church wusit silalehu ewinetawun awikalehu.zare abat tebilew yemichebechebilachewuna yemisegedilachew babizagnaw leboch..zeregnoch...amenizirawoch..bitidenegitum andandoch yelijoch balebet nachew.ena wusitu satinoru lemedegef atichekulu.gudayunm kemenafikan ga atagenagnut. mechem papas lij endalew bemasireja bininegirachihu menafik tilalachihu.yeabatochachihu degafi mehonachihu woy alemawek new kalihonem bekifatachew tebabari nachihu.yikir yibelachihu.!!!

  ReplyDelete
 11. I am an Ethiopian leaving in Addis Ababa. Although I did not attend the meeting, I know Mahibre Kidusan and Abba Estifanos. Mk is the defender of EOTC. Even the Government know MK is against corruption. Abba Estifanos stood firm when the extremist massacred Christians and burned our Churches. He coordinated the reconstruction of burned churches.While he was in Betkenhet as Administrator he stood against attempt corruption by layities surrounding Abba Paulos those who were trying to exploit the church We need such type of Fathers and Mahiber.

  Your father was the First lair and you continue to lie, this will not lead you heaven! Your mission is to destroy EOTC by making unholy alliance ! Yyour days are numbered ! Repent!

  ReplyDelete
 12. bemeseretu enezih lijoch endezih bota yagegnu almeselegnim biyanse ke asir amet befit new yemawiqachew huletum bebete kiristiyan yadegu sinemigbar yalachew yawim ke hulte degree belay yalachew nachew yonas &tadewos huletum yeharer lijoch nachew yeh hulu teqawimo lemin tsegure liwit(Oromo) wede siltan meta new demos lemin ke aba estifanos gar tagenagutalachihu betam biqat yalachew lijoch nachew hager memirat yemichilu naw gid yelem EOTC ye OROMO'm mehonuan emenu eskemeche new OROMO ke betekiristiyan wichi yemihonew

  ReplyDelete
 13. Oromo bemehonachw min alin Egan yalin gubegnoch nachw alin lzihm benesu mikniyat balfut 5 werat ksirachew tefenakelu masrja ye bolehohitebirhan mariyam astedadr seratgnoch endizawrulachw yeakebabiw miemenan teykew bgubae hulum biro seratgnoch endizawrulachw tewesino ensuring botany kmifelgu karat biro bmekebl Ramayana yetigray Tewelde yehonutin demwzachew lenses ziyazawru ledebru genzeb mezrefna hintsaginbata mekom #1 miknyat yenochiw Oromo Tewelde yhonech hisab kill metewachewna .alekawm.genzeb yazum .tsehafiwm Oromo madregachewem altekaweminim bicha Egan yawned Niagara yachesalu. chat yikmalu. sekrw biro yikmalu. yetmihrt .ytadewose yetmihrt masrja forbid nw sinemigbar yelachewm yih hulum godolo iyalachw Mahler Kiduman ena abaestifo fikregna bemehonachw menorah yelachewm new yeminlew

  ReplyDelete