Monday, November 18, 2013

መናፍቁ ማነው?


አንዳንድ ጊዜ ስም አለቦታው ይወድቃል፡፡ አለቦታቸው ወድቀው ከሚገኙ ስሞች መካከል “መናፍቅ” የሚለው ስያሜ አንዱ ነው፡፡ በሚያምኑት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ምክንያት መናፍቃን የሆኑ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ያላቸውን ሰዎች መናፍቃን ማለታቸው እየተለመደ መጥቷል፡፡ እንዲህ የሚያደርጉትን መጽሐፍ ቅዱስ “ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፡ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፡ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!” ይላል (ትንቢተ ኢሳይያስ 5፡20)፡፡ ይህን ብዙ ጊዜ አለቦታው ወድቆ የሚገኘውን ስም ወደቦታው መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ ማድረግ ቀላል አይደለም፡፡

“መናፍቅ” የሚለው ቃል “… የሚጠራጠር፣ የሚያጠራጥር፣ ጠርጣሪ፣ አጠራጣሪ፣ ሃይማኖቱ ሕጹጽ የሆነ፣ ምሉእና ፍጹም ትክክል ይደለ፣ መንፈቁን አምኖ መንፈቁን የሚክድ” የሚል ፍቺ እንዳለው የኪዳነ ወልድ መዝገበ ቃላት ይናገራል (ገጽ 646)፡፡ ፍቺው እንደሚያስገነዝበን እግዚአብሔር በገለጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ላይ የሚጠራጠርንና የሚያጠራጥርን ሰው ነው መናፍቅ ብለን መጥራት የምንችለው፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ በአብዛኛው እግዚአብሔር የገለጠውን እውነት ሳይሸራርፍ የተቀበለውና ለዚያ ጥብቅና የቆመው፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር እውነት ላይ ሰዎች የጨመሩትን የስሕተት ትምህርት ስሕተት ነው የሚለው ሰው ነው መናፍቅ እየተባለ ያለው፡፡ ይህም የሚያሳየው “መናፍቅ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ሳይሆን ሰው በመሰለው መንገድ ‘እኔ ልክ ነኝ ሌላው ግን ተሳስቷል’ ሲል እያነሣ ለሌላው የሚቀጽለው የስድብ ስም ነው፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ ይህ ቃል የአንድን ሰው መናፍቅነት በተገቢው መንገድ በማረጋገጥ የሚቀጸል ሳይሆን በጠሉት ሁሉ ላይ ቀድመው የሚለጥፉት ክፉ ስም ሆኗልና ወደ ተገቢው ስፍራ መመለስ ይገባዋል፡፡


በክርስትና ትምህርት መሠረት መናፍቅ የሚባለው በሃይማኖት ትምህርት ላይ የሚጠራጠርና ገሚሱን አምኖ ገሚሱን የሚክድ ነው፡፡ የሃይማኖት ትምህርት የሚባሉትም በዋናነት ምስጢረ ሥላሴና ምስጢረ ሥጋዌ ናቸው፡፡ አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣ ንስጥሮስና ሌሎቹም ከቤተክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ የተደረጉትና መናፍቃን ለመባል የበቁት ከላይ በተጠቀሱት የሃይማኖት ትምህርቶች ላይ ስለተጠራጠሩና ከጥርጣሬያቸው ወደእምነት ለመመለስ ፈቃደኞች ስላልነበሩ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ያወገዘቻቸውና መናፍቃን ያለቻቸው በግብታዊነትና ወይም በሌላ ድብቅ አላማ ላይ ተመሥርታም አይደለም፡፡ እንዲህ ያደረጉና የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች በየዘመናቱ ባይጠፉም በአብዛኛው ግን ተገቢውን አካሄድ በመከተል የተከናወነ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ሆኖም መናፍቅ ብለው ከመፈረጃቸው በፊት ግን የተጠራጠረውን ሰው ከስሕተቱ ለመመለስ ብዙ ሥራ ይሠራል፡፡ ካልሆነና አልመለስም ብሎ በመጠራጠሩ ከጸና ግን ሌሎችን ከስሕተት ለመጠበቅ ስትል ቤተክርስቲያን በሕጋዊ አሠራርና በሕጋዊ አካል አልመለስ ያለውን ሰው ከአንድነቷ ትለያለች፡፡

ዛሬ እየሆነ ያለው ግን ከዚህ ትክክለኛ አሠራር ፈጽሞ ያፈነገጠ ተግባር ነው፡፡ አንድን ሰው መናፍቅ ለማለት ሕጋዊ አሠራርን መከተልና ተገቢው የቤተክርስቲያን አካል ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረግ ሳያስፈልግ ሁሉም በሌላ ጉዳይ የተጣላውንና ከእርሱ የተለየ አመለካከት የያዘውን ሰው ለማጥቃት ሲል መናፍቅ ማለት ይቀናዋል፡፡ ይህ የስድብ ስም፣ አንዳንድ ጊዜ ስም ሆኖ የሚቀረው ቀድሞ በተናገረ ስለሆነ ቀድሞ መናፍቅ ያለ ትክክለኛ፣ የተባለው ደግሞ መናፍቅ ተብለው የሚቀሩበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ በዚህ መንገድ መናፍቅ የሚለው የስድብ ስም የወጣላቸውን ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡

ትልቁ ጥያቄ ቀድሞ መናፍቅ በማለት ሰውን መናፍቅ ማስመሰል እንጂ ማድረግ ይቻላል ወይ? የሚለው ነው፡፡ አንድ ሰው መናፍቅ የሚባለው በሃይማኖት ትምህርት ማለትም በምስጢረ ሥላሴና በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ተጠራጣሪ ሲሆንና መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው እውነተኛ ትምህርትና በዚያ ላይ ከተመሠረተው የአባቶች አስተምህሮ አፈንግጦ ሲገኝ፣ ተመክሮ ተዘክሮም አልመለስ ሲል ነው፡፡ ዛሬ ግን በእነዚህ ትምህርቶች ላይ የሚጠራጠሩ አማንያን በእነዚህ ትምህርቶች የሚያምኑት ደግሞ መናፍቃን እየተባሉ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ “መናፍቅ” ለማለት መቅደም እንጂ መናፍቅ ሆኖ መገኘት እንደማያስፈልግ ያሳያል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጳውሎስ ትክክለኛ የክርስቶስ ሐዋርያ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አይሁድ እነርሱ መናፍቃን ሆነው ሳለ ሐዋርያውን ጳውሎስን መናፍቅ ብቻ ሳይሆን “የመናፍቃን መሪ” ሲሉት እናነባለን (የሐዋርያት ሥራ 24፡5)፡፡ ጳውሎስ የመናፍቃን መሪ የሚለው ስም የወጣለት እንደእግዚአብሔር ቃል ያልሆነውን የእነርሱን ትምህርት ስለተቃወመና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለሱ ተግቶ ስላገለገለ ነው፡፡ በእውነተኛው የሃይማኖት ትምህርት ላይ ሳይሆን እነርሱ እንደሃይማኖት የሚቆጥሩት ወግና ልማድ በእግዚአብሔር ቃል መታረም አለበት ስላለ ነው የመናፍቃን መሪ የተባለው፡፡

ዛሬ ብዙዎች መናፍቃን የተባሉትና የሚባሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነው የክርስትና እምነት ላይ ስለተጠራጠሩ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተጨመሩ የሰው አስተሳሰቦችና ትምህርቶች በእግዚአብሔር ቃል መታረም አለባቸው፤ የእግዚአብሔር ቃል መከበር አለበት ብለው ስለተናገሩና ስለጻፉ ነው፡፡ በዚያኛው ጽንፍ ያሉት ደግሞ በሃይማኖታቸው ውስጥ ያለው ነገር ትንሹም ትልቁም ነገር ሃይማኖት ስለሚመስላቸው ሃይማኖት ያልሆነውን ነገር ሁሉ ሃይማኖት አድርገው ስለሚወስዱ በእግዚአብሄር ቃል ለመታረም ፈቃደኛ አይሆኑም፡፡ በዚህ ጊዜ አይሁድ ጳውሎስን የመናፍቃን መሪ እንዳሉት በዚህ ዘመንም የአይሁድን አሰረ ፍኖት የተከተሉ ተረፈ አይሁድ በእግዚአብሔር ቃል እንታረም ያላቸውን ሁሉ መናፍቅ ይሉታል፡፡ ለእነዚህ ክፍሎች ጳውሎስ እንደሰጠው መልስ “ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤” ከማለት በቀር ምን ማለት ይቻላል? (የሐዋርያት ሥራ 24፡14)

ለምሳሌ ታቦት የብሉይ ኪዳን ሥርዓት እንጂ እንጂ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የለም፡፡ በምድር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ታቦት ያስፈልጋል፤ እኔም ታቦት አለኝ ትላለች፡፡ ይህ ስሕተት ነውና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማረም አለብሽ ስትባል እንዲህ የሚሏትን ወገኖች መናፍቃን ናችሁ ትላለች፡፡ እውን መናፍቅነት እንዲህ ማለት ነው? ወይስ ከአዲስ ኪዳን ወደብሉይ ኪዳን ሥርዓት በመመለስ ታቦት ያስፈልጋል ማለት? መቼም የዕብራውያንን መልእክት ያነበበ ሰው መናፍቁ ማን እንደሆነ ሳይረዳ አይቀርም፡፡

የአዲስ ኪዳን መካከለኛ አንድ ብቻ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው “ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፡ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ [ኢየሱስ ክርስቶስ] የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።” (ዕብራውያን 9፡15)
“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፡ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።” (ዕብራውያን 12፡24)፡፡
“አንድ እግዚአብሔር አለና፡ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፡ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5)

ሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀ ዛሬም በሕያውነቱና አንድ ጊዜ ባቀረበው ምልጃና መሥዋዕት መካከለኛችንና አስታራቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር መካከለኛ ያደረገውን ኢየሱስን ከመካከለኛነቱ ስፍራ ላይ በማንሳት ያንቀላፉ ቅዱሳንንና መላእክትን መካከለኛ አድርገው ለሾሙ ክፍሎች ይህ ኑፋቄ ነው፡፡ እነርሱ የሚሉት ይህ የስህተት ትምህርት ግን እውነተኛ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ከታየ ኑፋቄ የሚባለው የቱ ነው? መናፍቁስ ማነው?

ደግሞስ በመካከለኛነቱ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ በግልጽ ተጽፎና ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም መዳን እንደማይገኝ ተነግሮ ሳለ (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) “ያለማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለው ቅዠት እንደትክክለኛ የሃይማኖት ትምህርት ተቆጥሮ እንዲህ የሚሉ አማኞች ሲባሉ ይህን የተቃወሙት ደግሞ መናፍቃን ሲባሉ ከማየት በላይ ምን ውድቀት ይኖር ይሆን?


በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቅዱሳን አንዳቸው ለሌላኛው እንዲጸልዩ ታዟል (ያዕቆብ 5፡16)፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ቅዱሳኑ በሕይወት ሥጋ ባሉበት ዘመን ብቻ ነው፡፡ ካንቀላፉ በኋላ በኋላ ግን ያንቀላፉ ቅዱሳን በሕይወት ካሉት ቅዱሳን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሌላቸው አንዳቸው ለሌላቸው መጸለይ የሚችሉ ቢሆኑ እንኳ ሁለቱም ይህን የሚያውቁበት ዕድል ፈጽሞ የላቸውም፡፡ ደግሞም አንዱ ስለሌላው እንዲጸልይ እንጂ አንዱ ወደሌላው እንዲጸልይ ፈጽሞ አልታዘዘም፡፡ በሕይወት ያሉ ቅዱሳን ወይም ምእመናን ወደአንቀላፉ ቅዱሳን አማልዱን ብለው መጸለያቸው እውነተኛ የሚመስል ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሲመዘን ከእግዚአብሔር ሌላ ወደ ፍጡራን የሚቀርብ ጸሎት በመሆኑ አምልኮ ባዕድ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ወደእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ወደ ፍጡራን መጸለይ ትልቅ ስህተት ነውና መታረም አለበት ቢባል ወደፍጡራን መጸለይን የሃይማኖት ትምህርት አድርገው በያዙ ክፍሎች ዘንድ ይህም መናፍቅነት ነው፡፡ ነገር ግን መናፍቁ ይህ ስህተት መታረም አለበት ያለው ሳይሆን ከእግዚአብሔር በተጨማሪ ወደአንቀላፉ ቅዱሳንና ወደመላእክት የሚጸልዩ ናቸውና የስም ዝውውሩ የግድ ያስፈልጋል፡፡    

74 comments:

 1. Today abaselama came clearer in its stand than anytime before. We have heard your teaching loud and clear. Absolutely the church respects your teaching. But a simple question for anyone claiming to be a Christian-if the church does not accept your idea why don't you you worship your own way leaving the church alone? Do u think you are making Jesus happy by insulting, humiliating, and arguing with people? Ok, I don't have a lot of knowledge on bible teachings to be honest. But I cannot see on this blog the minimum respect for people's dignity I usually see in worldly magazines. In this and some other (perhaps opposition) blogs it's very common to see Christians' sins uncovered. Really sad!!! I really wonder if the bloggersv themselves are Christians or know Jesus at all.

  ReplyDelete
  Replies
  1. If you don't know about bible,
   stuck with your stereotypes &
   drug u hell.PS open your eyes
   we are in 21 century .

   Delete
 2. Good job! Perfect article and please let us more biblical article. Thank!

  ReplyDelete
 3. ታዲያ ምን አታከተህ? ለምን ጥለህ መናፍቅ ያልሆኑት¡(ድንቄም) ጋር አትሄድም? ታቦት የሌላቸው ጋር፤ የአንተን እምነት 100% የሚቀበሉት የምትመስላቸው ጴንጤዎች አሉልህ አይደል የምን ሙጥኝ ማለት ነው? “መናፍቅ” ጋር ምን ትሰራለህ? እባክህ ከ“መናፍቅ ቤት” ውጣልንና እንገላገልህ። ረስቼው ሁለተኛ ደሞዝህ፤ እንጀራህ ነው ለካ።

  ReplyDelete
 4. Aba Selama woch Ahun Bedemb Mannetachu Begils Asqemetachu Lemin Eske Ahun Zegeyachu. Tadya Aba Selama Selama Abatachin Brhan Gelachu Yetelatachin Seytan Haily Yadekemk Le Hagerachin Ethiopia Brhanwan Ena Selamuwan Neh Yemilew Restachut New Seal Lene Selama Awune Kesate Brhan

  ReplyDelete
 5. wey girum Yasegal. tiru eyeta new.

  ReplyDelete

 6. “ገዳይ ገድላት” ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ ካልወጡ ምዕመናኑ መበተናቸው የማይቀር ነው ፡፡
  ምክንያቱም አሁን ያለውን አንባቢና አስተዋይ ትውልድ እንደ ቀድሞው ማታለል አይቻልም፡፡
  ኦርቶዶክስ ሆይ! ጊዜው እየቀደመሽ ነውና ንቂ ፣ ፍጠኚ ፣ ሩጪ…………ልጆችሽን ለማዳን ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ante Ke Orthodox Tewahedo Ga Min Atabeqeh Yemataminbet Kehone Le Min Wede Beth Athedim Antem Engnam Eko Bezemenu Twild New Yalenew Atalayu Manew Endyaw Yabye Wede Emye New Yetebalew. Yefelegkew Mehon Mebt Aleh Neger Gin Yesew Mebet Weym Emnet Gin Mesadebm hon Mananaq Beyetngnawum Ager Nur Hegu Ayfeqdilihim Bedngay Mamlek Mebth New Be Orthodox Sim Gin Meneged Antena Melaw Ye Ante Gwadengnoch Yqirbachu.

   Delete
  2. ውሸታም ሰውን ውሸታም ነህ ብለህ ካልነገርከው እውነተኛ እንደሆነ ያህል እራሱን ቆጥሮ ይኖራል፤ ስለዚህ ውሸታምን ውሸታም ነህ ማለት ስድብ ሳይሆን ተግሳጽ ነው፡፡ ተግሳጽና ስድብም ለየቅል ነው፡፡ ኸረ ለመሆኑ ከሞት በኋላ ይሄ ሁሉ እውነትን የማያውቅ መንገዱ በመናፍቃን አስተማሪዎች የጨለመበት ሰው ይግባኝ የሌለው ፍርድ እንደሚጠብቀው ታውቅ ኖሯል? እዚያ ጋ ከደረስክ በኋላ የኋላ ማርሽ የለም!!! ስለዚህ "ዛሬ አሁን ተብሎ ሲጠራ ሳለ ልብን ከማደንደን በንሰሃ መመለስ የጠቢባንና የአስተዋዮች ምላሽ ነው፡፡ ጨካኙ ሂትለር ለፖለቲካ ጥቅሙ ቁጥር የሌላቸውን ሰዎች ሲጨፈጭፍ ሰዎችን ከዚህ ዓለም ህይወት በመለየቱ እጅግ አረመኔያዊ ተግባሩ በዓለም ህዝብ ዘንድ ሲወገዝና ሲጠላ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ሂትለር ሰዎችን ጊዜያዊ ከሆነ ከዚህ ዓለም ህይወት በመግደል በማስወጣቱ ጨካኝ አረመኔ መባል ከተገባው፤ እነዚህ ለጊዜያዊ ጥቅማቸውና ደሞዛቸው እንዲሁም ላገኙት ሃሰተኛ ክብር ሲሉ እውነት ዛሬ ሲነገር ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው እራሳቸውን ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠረውን ተከታያቸውን የገዛ ገንዘቡን እየዘረፉና እየበሉ ለሲኦል ይግባኝ ለሌለው ፍርድ አስረው የሚያቆዩትን ምን እንላቸው ይሆን፡፡ እነዚህ ሰዎች ተግሳጽ አይደለም እውነተኛ ዳኛ ቢኖር ከሂትለር ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ፍርድ ባገኛቸው ነበር፤ ምክንያቱም ሂትለር የምድርን እነርሱ ግን የዘላለምን ህይወት ከሚወዳቸውና ከሚያከብራቸው ገንዘቡን ሳይሰስት ከሚሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ያለ ርህራሄ ነጥቀዋልና፡፡

   Delete
  3. ውሸታምን ሰው ውሸታም ነህ ብለህ ካልነገርከው እውነተኛ እንደሆነ ያህል እራሱን ቆጥሮ ይኖራል፤ ስለዚህ ውሸታምን ውሸታም ነህ ማለት ስድብ ሳይሆን ተግሳጽ ነው፡፡ ተግሳጽና ስድብም ለየቅል ነው፡፡ ኸረ ለመሆኑ ከሞት በኋላ ይሄ ሁሉ እውነትን የማያውቅ መንገዱ በመናፍቃን አስተማሪዎች የጨለመበት ሰው ይግባኝ የሌለው ፍርድ እንደሚጠብቀው ታውቅ ኖሯል? እዚያ ጋ ከደረስክ በኋላ የኋላ ማርሽ የለም!!! ስለዚህ "ዛሬ አሁን ተብሎ ሲጠራ ሳለ ልብን ከማደንደን በንሰሃ መመለስ የጠቢባንና የአስተዋዮች ምላሽ ነው፡፡ ጨካኙ ሂትለር ለፖለቲካ ጥቅሙ ቁጥር የሌላቸውን ሰዎች ሲጨፈጭፍ ሰዎችን ከዚህ ዓለም ህይወት በመለየቱ እጅግ አረመኔያዊ ተግባሩ በዓለም ህዝብ ዘንድ ሲወገዝና ሲጠላ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ሂትለር ሰዎችን ጊዜያዊ ከሆነ ከዚህ ዓለም ህይወት በመግደል በማስወጣቱ ጨካኝ አረመኔ መባል ከተገባው፤ እነዚህ ለጊዜያዊ ጥቅማቸውና ደሞዛቸው እንዲሁም ላገኙት ሃሰተኛ ክብር ሲሉ እውነት ዛሬ ሲነገር ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው እራሳቸውን ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠረውን ተከታያቸውን የገዛ ገንዘቡን እየዘረፉና እየበሉ ለሲኦል ይግባኝ ለሌለው ዘላለማዊ ፍርድ (ሞት) አስረው የሚያቆዩትን ምን እንላቸው ይሆን፡፡ እነዚህ ሰዎች ተግሳጽ አይደለም እውነተኛ ዳኛ ቢኖር ከሂትለር ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ፍርድ ባገኛቸው ነበር፤ ምክንያቱም ሂትለር የምድርን እነርሱ ግን የዘላለምን ህይወት ከሚወዳቸውና ከሚያከብራቸው ገንዘቡን ሳይሰስት ከሚሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ያለ ርህራሄ ነጥቀዋልና፡፡ ስለዚህ ጸሃፊ ሆይ "እምነት ለሁሉ ሰው አይሆንምና" ቢሆንም ግን እያደረክ ያለኸው ነገር ብዙዎችን ከእሳት ነጥቆ የማዳን ሥራ ስለሆነ እውነትን በማያውቅ ሰው ነቀፋና ትችት ልብህ አይዛል፣ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነውና ትጋ ! ትጋ! ትጋ!፡፡ እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ነው፤ የእውነተኛነታችን ማመሳከሪያ ብቸኛ ዳኛም እርሱ ነው፡፡ እውነትን ያወቀ ከብዙ ሺ ውሸቶች ጥቃት በሚያውቀው እውነት ምክንያት ይጠበቃል ነገር ግን ሰው ብዙ ውሸቶችን ስላወቀ ያወቀው ውሸት ብዛት ወደ እውነት ሊደርሰው ፈጽሞ አይችልም፡፡ ስለዚህ በአንተ ላይ የማክለው ነገር ቢኖር ሰዎች ሆይ መጽሐፍ ቅዱስን (እውነትን) ሳታውቁ እንዴት የሃሰትን ትምህርት ልታውቁት ትችላላችሁ? ወደ መጽሐፋችሁ ተመልሳችሁ ግን ጥቂት ጊዜ ብታሳልፉ ያን ጊዜ እውነት እንደ ንጋት ብርሃን እየጨመረ ሲበራ ግራ መጋባታችሁም ከእናንተ ሲርቅ ታገኙታላችሁ፡፡ ስለዚህ እባካችሁ አሁን ወደ ብቸኛው እውነተኛና ሃሰተኛውን ሁሉ ወደሚያጋልጠው እውነተኛ ዳኛ ወደ መጽሃፍ ቅዱሳችሁ ተመለሱ፡፡ ምክንያቱም የብዙዎቻችሁን አስተያየት ሳነብ ያስተዋልኩት መጽሐፍ ቅዱስን እንደማታውቁ ነው፡፡ ሁላችሁ እውነትን ታውቁም ዘንድ ጥልቅ የልቤ መሻትና ፍላጎት ነው፡፡

   Delete
  4. yet endayhedu. kehedum yaw orthodox honum alhonum yaw protestant nachew. endayhedu bityz astemrowa protestant kehone yaw hedewal malt new

   Delete
 7. አይ ማህበረ ሰይጣን ማህረ ቅዱሳን በቅዱሳን እየነገደ ስም ያጠፋል

  ReplyDelete

 8. 1. ቃል በቃል በሀዲስ ኪዳን ታቦት አያስፈልግም የሚል ጥቅስ(በጥሬ ንባብ) ካለህ ወዲህ በል!!!!
  ያለበለዚያ በትርጉዋሚ ለማምጣት መሞከር ሌላ 82ኛ የመ/ቅዱስ ክፍል መፍጠር ነው!!!
  2. የሞቶ ጻድቃንና መላእክት አያማልዱም የሚል ጥሬ ንባብ እስኪ…..
  3. በምድር ላይ ታቦት ያላት ኢኦተቤክ ብቻ ናት ትላለህ፡፡እና ብቸኛ መሆን ትክክለኛ ያለመሆን ምልክት ነው እንዴ!!??እንደውም በቁጥር ብዛት ከተባለማ በምድር ላይ ካሉት 2.3 ቢሊዮን ክርስቲያኖች ውስጥ ካቶሊኮችን ጨምሮ ቢያንስ 1.6ቱ ቢሊዮን በአማላጅነት ዙሪያ ባሉ አስተምህሮዎች ከኢኦተቤክ ጋር ተመሳሳይ የሆነ አስተምህሮ ይከተላሉ….we never walk alone!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተስ ለመከራከሪያህ ጥሬ ንባብ ስጠና
   1 በሀዲስ ኪዳን ታቦት ያስፈልጋል የሚል
   2 የሞቱ ጻድቃን ያማልዳሉ የሚል
   3. ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም የሚል
   እና የመሳሰሉትን ወንዝ አፈራሽ አስምህሮዎችህን የሚደግፍ ጥቅስ ቃል በቃል አምጣ
   በነገራችን ላይ ሊቨርፑል ስንተኛ ነው? ለሱ መቼም ማስረጃ አታጣም አይደለም? You never walk alone

   Delete

  2. ውድ anonymous Nov.20/2013 at 9:40

   በህግ ቁዋንቁዋ የማስረዳት ሸክም(burden of proof) የሚባል መርህ አለ፡፡ትርጉዋሜውም፡ ምንጊዜም ማስረጃ አስቀድሞ የማቅረብ ግዴታ ያለበት “አንድ ነገር አለ/የለም” ሲል ክስ የመሰረተው ከሳሽ ነው ማለት ነው፡፡ከጽሁፉ እንደምትረዳው አባ ሰላማ ብሎግ ከሳሽ ነው፡፡ስለዚህ ራሱ ክሱን በማስረጃ አስደግፎ የማቅረብ ግዴታ ይወድቅበታል እንጅ እኛ ለ2ሺህ አመታት ስለያዝነው ጉዳይ እንድናስረዳ የምንገደድበት ምክንያት የለም፡፡

   ቢሆንም ላንተ ለወንድሜ ስል ትንሽ ልበል፡

   1. መቼም ታቦት በኦሪት በመገናኛው ድንኩዋን የብሉይ መስዋዕት ይቀርብበት እንደነበር ታውቃለህ፡፡ ዛሬ ደግሞ የሀዲስ ኪዳኑ በግ ክርስቶስ ይቀርብበታል፡፡ምክንያቱም በግልጽ ያልተሻሩ የኦሪት ስርዓቶች ሁሉ የሀዲስ-ኪዳን አካል ሆነው ቀጥለዋል፡፡በሌላ አነጋገር “ያልተከለከለ ሁሉ ተፈቅዱዋል” ማለት ነው፡፡ስለዚህ በኦሪቱ ስለታቦት የተጠቀሱ ጥቅሶች ሁሉ ከመስዋእቱ መቀየር በቀር አሁንም ያገለግላሉና ባልፈረሰ እውነት ላይ ከሀዲስ ኪዳን ማስረጃ ካላቀረብክ ተብየ አልገደድም፡፡ለኔ አለመሻሩ በቂ ነዋ!!!

   2. የሞቱ ጻድቃን ማማለድ ለኛ እኮ የየእለት አጋጣሚ ነው፡፡ብ….ዙ ..ጊዜ ላረፉ ጻድቃን ተስለን ምልጃቸው ረድቶናል፡፡ለማንኛውም ግን 2ኛ ፔጥሮስ 1፤5 አንብብ “ከሞቴ በሁዋላ ስለ እምነታችሁ እተጋለሁ” ይላል፡፡

   3. ባማላጅነቱዋ ባምንም ያለ ድንግል አማላጅነት ዓለም አይድንም ስላላልኩ መልስ መስጠት አያስፈልገኝም፡፡

   4. ወንዝ አፈራሽ ትምህርቶችህ ላልከው ግን ግዴለህም search አድርግ፡፡ ያን ጊዜ በኛ ሰፈር ያሉ ወንዞች ብቻ ሳይሆን ከሮም እስከ አርመኒያ፣ከሶርያ እስከ ራሺያ፣ከኤሽያዋ ፊሊፒንስ እስከ ድፍን የላቲን ህዝብ ያሉ 1.6 ቢሊዮን ክርስቲያኖች በአማላጅነት አስተምህሮ ላይ ልክ እንደኛው ተመሳሳይ አቁዋም እንዳላቸው ትረዳለህ፡፡ለዚህም ነው we never walk alone የምለህ እንጅ ስለ አውሮፓ ቅሪላ (ኩዋስ) ልነግርህ አልነበረም፡፡አሁንም ደግሜ we never walk alone እላለሁ፡፡ ምንላርግ??ብቻችንን አይደለንማ!!! እንደምታየው ይህ ትምህርታችን ከወንዝም ውቅያኖሶችን ያቁዋረጠ ሆኖ ተገኝቱዋል!!!ችግሩ ብዙዎቻችን ዓለም ማለት በአንግሎፎን የሚግባቡትና ኢንተርኔቱን ጨምሮ ሚዲያውን የተቆጣጠሩት ምዕራብ አውሮፓና አሜሪካ ብቻ ይመስሉናል፡፡መቼም የእነሱ “ቃሉን እንጅ የምን ስርዓት” የሚል የእምነት ፈሊጥ ሂዶ…. ሂዶ… የት እንደ ደረሰ አልነግርህም!!!

   Delete
  3. አንተና መሰሎችህ እንዲሁም አንዲት እውነት ይዞ ዘጠና ዘጠኝ ውሸት የዋሸው የእምነታችሁ መስራች የሆነው እራሱ እራሳችሁን ችላችሁ አትንቀሳቀሱም እኔ የምለው ከመኮረጅ ውጪ ሌላ እውቀት የላችሁም እንዴ? ወንድሜ ህሩይ የጠየቀህን ሳትመልስ የተጠየከውን መልሰህ ትጠይቃለህ አሁንም ወንድሜ የጠየቀህን ላስታውስህ 1. ቃል በቃል በሀዲስ ኪዳን ታቦት አያስፈልግም የሚል ጥቅስ(በጥሬ ንባብ) ካለህ ወዲህ በል!!!!
   ያለበለዚያ በትርጉዋሚ ለማምጣት መሞከር ሌላ 82ኛ የመ/ቅዱስ ክፍል መፍጠር ነው!!!
   2. የሞቶ ጻድቃንና መላእክት አያማልዱም የሚል ጥሬ ንባብ እስኪ…..
   3. በምድር ላይ ታቦት ያላት ኢኦተቤክ ብቻ ናት ትላለህ፡፡እና ብቸኛ መሆን ትክክለኛ ያለመሆን ምልክት ነው እንዴ!!??እንደውም በቁጥር ብዛት ከተባለማ በምድር ላይ ካሉት 2.3 ቢሊዮን ክርስቲያኖች ውስጥ ካቶሊኮችን ጨምሮ ቢያንስ 1.6ቱ ቢሊዮን በአማላጅነት ዙሪያ ባሉ አስተምህሮዎች ከኢኦተቤክ ጋር ተመሳሳይ የሆነ አስተምህሮ ይከተላሉ

   Delete
  4. 1. እግዚአብሄር በትንቢተ ኤርምያስ 3-16 " በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን። የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።" የሚል ቃል ተናግሮአል፡፡ በአዲስ ኪዳን መድገሙን ለምን ፈለግከው? ብሉይ ኪዳን የመሀፍ ቅዱስ ክፍል አይደለም እንዴ? መዳን ለሚፈልግ ሰው እኮ አንዲት እውነት ትበቃዋለች፡፡
   2.ላረፉ ጻድቃን ተስለን ምልጃቸው ረድቶናል የምትለው ነገር በመፅሃፍ ቅዱስ ማስረጃ የሌለው ፈጠራ ነው፡፡ ለመሆኑ የትኛው ሰው ነው በመፅሃፍ ቅዱስ በሞተ ሰው ስም አንተ የምትለውን አይነት ልመና የለመነውና ልመናውን የተቀበለው፡፡ ምን አልባት ይህ አይነት አሰራር በጥንቆላና በመናፍስት አሰራር ሊገኝ ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር አሰራር ግን በሞተ ሰው ስም ሳይሆን በሞተልን በእየሱስ ስም ብቻ ልመናና ፀሎት ይደረጋል፡፡ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው የሞቱ ሰዎች በህይወት ያሉትን ሰዎች ፀሎት መስማት የጀመሩት? ÃI”” nM Mw wKI }SMŸƒ "ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ።ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ። ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር።ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር።" የሀዋርያት ስራ ም. 7 ቁጥር 9-10 አየህ ሰው ምን ያህል አሳሳች እንደሆነ፡፡ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እስኪባል ድረስ ያሳስታል፡፡ በጥንቆላ ስራ ያስገርማል፡፡ ነገር ግን መንግሰተ-ሰማይ የሚያስገባ ትምህርት የለውም፡፡ ስለዚህ የፈለገው አይነት ተአምር ቢያደርግ እውነትን የሚያውቅ ሰው አይገረምም፡፡
   3. በቁጥር ጉዳይ ላይ ብዙም መነታረክ ዋጋ የለውም፡፡ ጌታ እየሱስ የላካቸው ሀዋርያት በቁጥር 12 ነበሩ፡፡ የሚድኑ ሰዎች ሲጨመሩ ግን እየበዙ ሂደዋል፡፡ የቁጥር ማነስና መብዛት የአንድን ሀይማኖት እውነተኛነትና ሀሰተኛነት አይገልጽም፡፡

   Delete
  5. በጣም ይቅርታ የሀዋርያት ስራ ምዕረፍ 8 ቁ. 9-10 ነው፡፡

   Delete
 9. መናፍቅነታችሁን ለመቀበል የዳዳችሁ ትመስላላችሁ:: ተረፈ አርዮሳውያን! ሁሉ የሉተር ደቀ መዛሙርት!

  ReplyDelete
 10. ብዙ ጊዜ ስትጽፍ ትቀላቅላለህ፡፡ ታቦት በእኛ ቤ/ያን ክርሰቶሰ ራሱ መስዋቱ አንድ ጊዜ በእለተ አርብ የቀረበው እለት እለት የሚቀርብበት ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ታቦታ የሌላቸው እህት አብያተ ክርስቲያናት አሉ ግን መናፍቅ ማንም አላለቸውም ይሔ የአንተ ዓይነት ውሸታም መልክተኛ መርዙንና ማሩን እየቀላቀሉ የሚያቀርቡ ፈጠራ ነው፡፡ አመንክም አላመንከም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ የክርስቶስንና የቅዱሳንን ማስታረቅ አትቀላቅልም፡፡ የእሱ ማንም ሊተካው የማይቻል ተስተካካይ የሌለው ነው፡፡ ወዳጆቹ ቅዱሳን በአጸደ ስጋም ሆነ በአጸደ ነፍስ ያማልዳሉ፡፡ ይረዳሉ፡፡ ስለ መላክቱ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የሚያግዙ” በተባለው መሰረት ተረዳኢነታቸውን እንቀበላለን፡፡ ቅዱሳን አላንቀላፉም አረፉ እንጂ፡፡ ዛሬም ከምድር በበለጠ አውቀት አላቸው፡፡ ይሔ የማመንና ያለማመን ጉዳይ ነው፡፡ ቅዱሳንን አለመቀበል ለአኔ መናፍቅነት ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. anten eko tadiya tabot seleleleh aydelem menafek yetbalekewu. selaleh newu. yemetekelakeles ante. daru mastewalachehu tewosdual men taderge?

   Delete
 11. አዎ!!አዎ!! መንፍስቅዱስ ፊታችሁን ጸፍቶ-አፋችሁን ከፍቶ አናገራችሁ. አዎ ስም ያለ ቦተው ይወድቃል. ለዚህም ነው የታለቁ ኦርቶዶክሳዊ አባት የአቡነ ሰላማ ስም ለእናንተ ብሎግ መጠሪያ የሆነው.

  ReplyDelete
 12. መናፍቅ እኮ ማለት የዚህን ጽሁፍ ይዘትና አመክንዮ መቀበል ማለት ነው…
  እኔ የማይገባኝ ለምን እራሳችሁን ችላችሁ አትንቀሳቀሱም… ይቺን ቤ/ክ ለቀቅ አታደርጓትም…
  ደም መጣጮች….

  ReplyDelete
  Replies
  1. bekerestena sem endatenegedu newuna tekekelegnawun kerestena endetawuku newu. yekerestiyan gedeta selalebachewu newu. morons...

   Delete
 13. Wedet eyehedachu newe? geberachu keweyet endehone eyetegalete weyes......?

  ReplyDelete
 14. መናፍቅ እኮ ማለት የዚህን ጽሁፍ ይዘትና አመክንዮ መቀበል ማለት ነው…
  እኔ የማይገባኝ ለምን እራሳችሁን ችላችሁ አትንቀሳቀሱም… ይቺን ቤ/ክ ለቀቅ አታደርጓትም…
  ደም መጣጮች….

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለማን እንዳንተ ላለው መናፍቅ? አይገባህማ

   Delete
 15. at ur level of thinking

  ReplyDelete
 16. protestants are not only menafkan but also 'tequla' and 'kebero' do not hesitate on your identity.

  ReplyDelete
 17. አልገባኝም? ቅዱሳን እና መላእክት ያማልዳሉ የሚሉ መናፍቃን ይባሉ ነው የምትሉት ይህ የ አባ ወደል ትንሳኤ ሀሳብ ነው ወደል ትንሳኤ ጾም አያስፈልግም አሳማ ብሉ የሚለው አለቀባቸው? ዲሲ የተከሉት ሚካኤል ቤተክርስቲያን የማያማልድ ከሆነ ለምን የዋሀን ምእመናን ያታልላሉ ጊዜቸው በሚያሰድብ ነቀፋ ባለበት ቤተክርስቲያን ያባክናሉ' የሞቱ ቅዱሳን እና መላእክት የሚሉ መናፍቃን መባል አለባቸው'? ቀጣዩ ደግሞ ሃይማኖት ያላቸው የሚልጽሁፍ ሳላነብ የማልቀር ይመስለኛል

  ReplyDelete
  Replies
  1. you are a lair and a deceiver to mislead the innocent. Aba weldetensae never denied the intercession of the saints or the angles of God. His sermons on the intercessions of the saints and the Virgin Mary is all over the internet for those who need proof. Eating of the swine is your personal choice as the new testament doesn't mandate you to follow all the Levitical laws; as what defiles a man is not food but sin.

   Delete
  2. Andand asteyayet sechiwoch negeru menem syigebachehu endihu bedefenu ferachana telacha becha sedeb yikenachual. lemen yihon yih yemiyasayewu eko denkurenachehun newu,

   Delete
  3. Lema Zegeye, real stupid. u will never understand the truth. Because u are working for z dabble kkkkk.........

   Delete
 18. Keep it up!! Here in GA Mr. EFREM he has opened a church business with out authorization Of holy synod which he hang up him self as Pappas. Shamefully when Megabe Haimanot kesis Tesfaye refused. To corruption. In thechurch called him menafiq. Mr. Efrem formerly kesis has not moral power to said any thing to kesis Tesfaye he is one of theologian. Mr. Efrem never been in theology school he used church money to pay his mortgage and car loan. Most of his group are criminal released from jail such as Daniel Balcha and kesis Merkebu. You guy's keep in teach. God bless you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Absolutely true. God Bless Aba Selama Blog..

   Delete
 19. ወዳጆቼ አባ ሰላማዎች እኛ እና እናንተ ያልተግባባነው ነገር አለ...እኛ ኦርቶዶክሳዊ ቤትክርስቲያናችን በቃ ትክክል መሆኗ ይሰማናል ወደ እርሷ ስንቀርብ እግዚአብሄርን የተግናኝን ምስሎ ይሰማናል ወደ ርሷ ስንሄድ እንጽናናለን የተረበሽነው እንረጋጋለን...እና ይህንን ስሜት በጉንጭ አልፋ ክርክር አንለውጠውም ነው እያልን ያለነው ! እናንተ የእግዚአብሄርን ህልውና የመጽሃፍቅዱስን የእግዚአብሄር ቃልነት በአምንክዮ ማረጋገጥ እንደማትችሉት ሁሉ - እኛም ብዙ bible ባለማንበባችን ይሁን የጥንታዊ አባቶችን (ancient fathers like jhon chrystom commentaries)መጽሃፍት በብዙ ተርጉመን መጽሃፍ ቅዱስን ባለማጥናታችን ለናንተ ኦርቶክስ ትክክለኝነቷን አላረጋገጥን ይሆናል- ለኛ ግን አክሊላችን ሃይላችን ተስፋችን መጽናኛችን ቤትክርስቲያናችን ናት ይህን ደግሞ እንድታበላሹብን አንፈልግም!!!

  ReplyDelete
 20. መናፍቁ ማነው? ብላችሁ ለጠየቃችሁት መልሱ "አባ ሰላማዎች" ብዬ እገምታለሁ። እኔ የሚገርመኝ ለምን በግልጽ ወጥታችሁ አታውጁም? እስከአሁን ብዙ ደጋፊ ተገኙ ነበር ወይም ደግሞ ትጠፉ ነበር። ስለዚህ ተጠግታችሁ እናት ቤተ ክርስሲያንን ለማዳከም ከምትሞክሩ እራሳችሁን ብትችሉ ይሻላል።

  ReplyDelete
 21. betam yetesasatu sewech nachew enanten menafik yemilu .enante eko wodemeret yetetalew satnael nachihu.it is clear you are Devil

  ReplyDelete
 22. Oh Jesus!!! Efrem kebede is mafia Taxi driver. He came from rural Armachew Gonder he just simply been fight with people that affect him lack of communication which state that the way he grew up. I assure that I got fire from his business church long time ago he called me Tehadeso. But this gang fake priest is ethical problem inaddtion to theft money from the public for the past 20 years. He just been in dropped of Grade four student. Shame on him to accused Tesfaye and Girma in this way. If you ask Ethiopian living in Atlanta not recognized him as priest. You not worry about name that is baseless simply accusation with interest group or elements. The real name awarded by Ethiopian PM Melese Mk internationally recognized as terrorist. called mk terrorist.

  ReplyDelete
 23. EFREM IS paying all his bill from church money.

  ReplyDelete
 24. Merkebu and Efrem are from sexual relation ship.

  ReplyDelete
 25. Efrem has born for conflict. He is not priest with in any measure. He fired Bezabehi after used him.

  ReplyDelete
 26. Eyob of gola & Yonatan . Is that all you have .I know that you are more than menafik with the so called 'kesis ' Solomon .

  ReplyDelete
 27. Eyob of gola & Yonatan . Is that all you have .I know that you are more than menafik with the so called 'kesis ' Solomon .

  ReplyDelete
 28. Menafik Eyob of Gola and Yonatan , Is that all you have . Let us leave a room for God to act . I think it's time .

  ReplyDelete
 29. ይበል ይበል ይበል ብለናል

  ReplyDelete
 30. ታዲያ ምን አታከተህ? ለምን ጥለህ መናፍቅ ያልሆኑት¡(ድንቄም) ጋር አትሄድም? ታቦት የሌላቸው ጋር፤ የአንተን እምነት 100% የሚቀበሉት የምትመስላቸው ጴንጤዎች አሉልህ አይደል የምን ሙጥኝ ማለት ነው? “መናፍቅ” ጋር ምን ትሰራለህ? እባክህ ከ“መናፍቅ ቤት” ውጣልንና እንገላገልህ። ረስቼው ሁለተኛ ደሞዝህ፤ እንጀራህ ነው ለካ።

  ReplyDelete
 31. ታዲያ ምን አታከተህ? ለምን ጥለህ መናፍቅ ያልሆኑት¡(ድንቄም) ጋር አትሄድም? ታቦት የሌላቸው ጋር፤ የአንተን እምነት 100% የሚቀበሉት የምትመስላቸው ጴንጤዎች አሉልህ አይደል የምን ሙጥኝ ማለት ነው? “መናፍቅ” ጋር ምን ትሰራለህ? እባክህ ከ“መናፍቅ ቤት” ውጣልንና እንገላገልህ። ረስቼው ሁለተኛ ደሞዝህ፤ እንጀራህ ነው ለካ።

  ReplyDelete
 32. ታዲያ ምን አታከተህ? ለምን ጥለህ መናፍቅ ያልሆኑት¡(ድንቄም) ጋር አትሄድም? ታቦት የሌላቸው ጋር፤ የአንተን እምነት 100% የሚቀበሉት የምትመስላቸው ጴንጤዎች አሉልህ አይደል የምን ሙጥኝ ማለት ነው? “መናፍቅ” ጋር ምን ትሰራለህ? እባክህ ከ“መናፍቅ ቤት” ውጣልንና እንገላገልህ። ረስቼው ሁለተኛ ደሞዝህ፤ እንጀራህ ነው ለካ።

  ReplyDelete
 33. ታዲያ ምን አታከተህ? ለምን ጥለህ መናፍቅ ያልሆኑት¡(ድንቄም) ጋር አትሄድም? ታቦት የሌላቸው ጋር፤ የአንተን እምነት 100% የሚቀበሉት የምትመስላቸው ጴንጤዎች አሉልህ አይደል የምን ሙጥኝ ማለት ነው? “መናፍቅ” ጋር ምን ትሰራለህ? እባክህ ከ“መናፍቅ ቤት” ውጣልንና እንገላገልህ። ረስቼው ሁለተኛ ደሞዝህ፤ እንጀራህ ነው ለካ።

  ReplyDelete
 34. do you really think that when christian dies his knowledge will also be lost?? If so, those alive are better than those who have died for Christ and if Christianity believes as such, ..., it will lose its all meaning AND negates preaching of Jesus which says" Those who die believing in His Name will live; and those who keep their lives will lose it ..." \
  I BELIEVE THAT TO BELIEVE IN JESUS AND DIE WILL GIVE ME WITH ALL SORT OF GRACE THAT EVEN THOSE WITH GIFT IN THIS WORLD CANNOT ATTAIN. AND YES IF A SAINT CAN PRAY FOR ANOTHER IN THIS WORLD HE WOULD DEFINITELY PRAYS MORE IN THE HEAVENS.

  ReplyDelete
 35. Oh my Jesus ,Kesis Merkebu Hailu was arrested in connection with married women sexual assault when his wife went Ethiopia. This not church People in Atlanta called Efrem. Ethiopian Orthodox Mart similar to any other store. The only people went his Mart is new comer that has no idea about who is Efrem. He fired Professional priest like Girma and others bc they are more Professional serving free. Abeselom is voice of voiceless. Mk not post any comment other wise pay money.

  ReplyDelete
 36. We reside in Atlanta, starting to sign petition to close Kesis Efrem. Church Mart need only 25 signature please follow as in face book.

  ReplyDelete
 37. God Bless you!! it is true!!!!!!!!

  ReplyDelete
 38. wow!!religious people are crying everywhere! God is good and I am sure truth will be truth! instead of insulting,why do not you read the Holy Bible!religion doe not take you heaven but the belief in Christ!
  kkkkkk does Paul teach us about 'Tabot' meditors?...everting wat is in the EOC is something different what Paul,peter,matew,John...preached.May God ope you eyes

  ReplyDelete
 39. wedaje esekisemu mchoke newe kesmu?

  ReplyDelete
 40. kesemuke mechoke newe masetwale yisetachewe

  ReplyDelete
 41. Those who waged Jihad to Aba Wolde tensaye are slowly getting in to the house of shame. Jealousy was obviously the motive behind it. He has this gift and skill of explaining things eloquently. Misinformation against his teachings and himself were allegedly dispensed to discredit him. Thanks God, the dust is settling now the truth is revealed, his opponents are busted.

  ReplyDelete
 42. Religion is distracting our faith to words God, what we need is "only relationship with Lord Jesus." Remember Islam is also a religion believing on killing of other religion followers.

  ReplyDelete
 43. I took few minutes to read some of the comments, I want to say a little "most of the comments that I read were irrelevant, not even considered that a christian comments,there were also not relating to the great biblical article posted in this website ever."

  ReplyDelete
 44. ኣሁንስ በጣም ስራ ፈታችሁ በአሁኑ ጊዜ
  መጸለይ ነዉ ነዉ ያለብን በስደት ላይ ያሉትን ወገኖቻችኅ
  እግዚአብሔር አምላክ በሰላም ወደአገራቸዉ ይመልሳቸዉ ዘንድ
  የእናንተ ተራ ወሬ ነው ይሄ አያሳስበንም ስራ ፈቶች

  ReplyDelete
 45. ኣሁንስ በጣም ስራ ፈታችሁ በአሁኑ ጊዜ
  መጸለይ ነዉ ነዉ ያለብን በስደት ላይ ያሉትን ወገኖቻችኅ
  እግዚአብሔር አምላክ በሰላም ወደአገራቸዉ ይመልሳቸዉ ዘንድ
  የእናንተ ተራ ወሬ ነው ይሄ አያሳስበንም ስራ ፈቶች

  ReplyDelete
  Replies
  1. What you want say,I don't got it,u think they doing wrong?
   what we did back home?are u
   get lost or u forgot it,are we
   live free or we feel comfortable
   region to region,can u tell me
   what happened last 5-6 months,may u forgot it but not
   the rest of the world,if u want
   know ask about benshangul
   region &other areas.

   Delete
 46. ye blowgun sim Aba selama sayihon Aba asama bilenewal. lnegeru bichegiregn new enj asama kenante betam yishalal.

  ReplyDelete
 47. ፈጣሪን ሳያውቁና መንገዱን ሳይገነዘቡ በጻድቃንና በቅዱሳን ስም የሚነግዱ ጭፍን የዘመናችን መናፍቃን
  የራሳቸውን የስንፍና ስም በሰዎች ትክሻ ላይ ሲጭኑና ሲያሸክሙ ይታያሉ ማቴ 23.1---5 ሐዋራው
  ቅ/ጳውሎስም የቅርጤስ ነቢይ ያለውን በመጥቀስ ክሬታውያንን ሁል ጊዜ ውሸታሞች ክፉ አራዊትና
  ከርሳሞች ብሏቸዋል በመካን ሴት ማኅፀንም መስሏቸዋል ተቀብለው የማይረኩ ሬሳ ገፋፊዎች ለማለት! የዘመኑ ተመጻዳቂም ሓዋርያው ከጠቀሰው ውጭ አይሆንም። ካፈርሁ አይመልሰኝ ካልሆነ
  በተቀር መታረምና ወደውነተኛው ሥርዓተ ትምህርት መመለስ ይገበዋል ማቴ 18 1----3

  ReplyDelete
 48. You dead protestants! Your 'Jesus' told you to utter such evil ? We know that he is a devil not the Son of Holy Virgin Mary. You are dead for eternity that is why you write such a filthy! You see our Jesus is our God, nothing less.

  ReplyDelete
  Replies
  1. There is no such thing as "our Jesus" and "your Jesus". The Lord is one! It is true, they might have different understanding on who the Lord Jesus Christ is but that doesn't mean there are 2 Lords or 2 "Jesuses". The name Jesus is only attributed to the divine Son of God who became incarnate for our sake. It baffles my mind whenever I read such posts calming to believe in the Lord Jesus Christ (often times Ethiopian Orthodox Christians). I never hear anyone say "our Mary" or "your Mary", so why do you need to tarnish Our Lord's name just to make an unnecessary point?

   Delete
  2. I assure you,you ended up
   in hell,it looks you hold a key
   for that door,PS open your
   heart and eyes.

   Delete
 49. Are you fuck in block head

  ReplyDelete
 50. የቅድስት ማርያም ዘር ነኝ አትም ኢሜይል

  በዲን. ብርሃኑ ታደሰ

  አባታችን አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ለሚያመልኩ ሁሉ ታላቅ የእምነት አባት ነው። በእርግጥም አምላኩን ፍጥረትን በመመርመር ማግኘቱ፣ አምላኩን ብሎ ቤተሰቡን ተለይቶ መውጣቱ፣ ልጁን ለመሰዋት ፍጹም ፈቃዱን ማሳየቱ ሁሉ ለእምነት አባትነቱ ማሳያዎች ናቸው። ከሁሉ የሚልቀው ከእርሱ አስቀድሞ ከሙታን መካከል የተነሱ ሳይኖሩ፣ ዘርህ በይስሐቅ ይጠራልሃል ከተባለ በኋላ ልጅህን ሰዋልኝ ሲባል፣ እነዚህን ሁለት የሚጣሉ የሚመስሉ ሐሳቦችን በእምነቱ አስታርቆ ማለት ቢሞት እንኳን ያስነሳዋል ብሎ አምኖ ልጁን ሊሰዋ ወደ ተራራ መውጣቱ ነው።(ዕብ11፥19) የሰው ሕሊና ጊዜ ሲያገኝ አንድን ነገር ደጋግሞ ማሰቡ አይቀርም፤ አብርሃም ግን የሦስት ቀን መንገድ ሲሄድ ይህ እምነቱ ንውጽውጽታ አልነበረውም - እፁብ ነው።Lideta_Le_Mariam_1

  እኛ ክርስቲያኖች - የእግዚአብሔር ወልድን ሰው መሆን፣ ለኛ ብሎ መከራ መቀበል፣ በኋላም የቤዛነቱን ሥራ ሲፈጽም በአባቱ ክብር መቀመጡን ስለምናምንና ስለተጠመቅን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል። ይህ ልጅነት በፊት እንደነበረው ከሥጋ የመጣ አይደለም፤ መጽሐፍ - “ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ ግን መንፈስ ነው።” እንዲል፤ ልጅነታችን በጸጋ ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ነው። (ዮሐ3) ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ይህንን ሲያጸናው የተወለድነው ከሚጠፋ ዘር አይደለም ይለናል። (1ጴጥ1፥22)

  ክርስቲያኖች የመሆናችን ምንጭ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ ደግሞ የተወለደው ንጽሕት ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነው። ከድንግል ማርያም የተወለደው እርሱ እኛን በጸጋ ልጆች የምንባልበትን ስልጣን ሰጠን፤ ስለዚህም እናታችን ማርያም እንላለን፣ በሙሉ ጥብዐትም የቅድስት ማርያም ዘር ነን እንላለን። እንግዲህ ሰው የትኛውን ይጠራጠራል? በክርስቶስ ክርስቲያን መሰኘቱን ነው ወይስ ክርስቶስ ከቅድስት ማርያም መወለዱን? ወይንስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጡን? በአንድ ስፍራ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸጋው ለሁሉም እንደተሰጠና የሚሰጥበትን ምክንያት ሲገልጽ “እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ (ለአሕዛብ) ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?” ይላል። (ሐዋ11፥17) ዳግመኛም “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ።” ይላል።(ሉቃ1፥30) በሌላም ስፍራ “ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።” ይላል። (1ዮሐ4፥3) ስለዚህ ተጠራጣሪ አይኑር ይመን እንጂ።

  አቡቀለምሲስ ወይም ባለ ራዕይ የሚባለው ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ካያቸው ራእዮች መካከል አንዱ የክርስቲያኖች እናት እና መመኪያ ስለሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም ነው። ይህንንም በአስራ ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ አስቀምጦታል። የሚጀምረውም ስለክብሯ፣ ከዚያም ስለወለደችው ልጅ፣ በዚህም ምክንያት ስለመጣባት መከራ፣ መከራውም ወደ ዘሮቿ እንደዞረ ያስረዳል። ስለክብሯ፦ “ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።”(ቁጥ 1) ይላል። ስለወለደችው ልጅም፦ “አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች” (ቁጥ 5) ይላል። አሕዛብን ሁሉ የሚገዛ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱን የወለደች ደግሞ ቅድስትና ድንግል ማርያም ናት። ስለዚህም ምክንያት “ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።” (ቁጥ 13) ይለናል - ወደ ግብጽ ስለመሰደዷ። በመጨረሻም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁትን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች የሆኑትን እንደሚያሳድድ ሲገልጽ፦ “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤” ከዘርዋ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሴቲቱን ዘር ነው፤ ይህች ደግሞ የመመኪያችን ዘውድ ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ዘርዋ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች የሆኑትን ነው። ንዋየ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስም፦ “በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።” ብሎ፣ በእርሱዋ የደረሰ በዘሮቿም እንደሚደርስ አስረግጦ ተናግሯል። (2ጢሞ3፥12)

  በአብርሃም ልጅ በይስሐቅ ደም ዓለም እንደማይድን ተነገረ፤ በእመ አምላክ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ግን ክብርን አገኘን። በሥጋ ተወልደው የአብርሃም ዘር የሆኑት ከነዓንን ለመውረስ ተስፋ አደረጉ፤ እኛ በመንፈስ ከአብርሃም ተወልደን የድንግል ማርያም ዘር የሆንነው ደግሞ መንግስተ ሰማያትን ተስፋ እናደርጋለን። እነርሱ ከነዓንን ለመውረስ ብዙ ሰልፍ አደረጉ፤ እኛ መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ መንፈሳዊ ውጊያ እናደርጋለን። እነርሱ በመገረዛቸው ይመካሉ፤ እኛ ግን በጥምቀት ባገኘነው የጸጋ ልጅነት እና የድንግል ልጅ በመስቀል ላይ ባደረገልን ውለታ እንመካለን። እነርሱ ማመን ለሥጋ ዘመዶቻቸው ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፤ እኛ መዳን ለሁሉ እንደተሰጠ እናምናለን። እነርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት መሲህ ወደ ዓለም አልመጣም ይላሉ፤ እኛ የነቢያት እውነተኝነት ይገለጽ ዘንድ ሰውን ለማዳን የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን ድንግል ማርያም ወልዳልናለች ብለን እንመሰክራለን። እነርሱ በሥጋ የአብርሃም ዘር ነን እያሉ ይመካሉ፤ እኛ በመንፈስ የአብርሃም ልጆች፣ የድንግል ማርያም ዘር በመሆናችን እንመካለን።

  እናታችን ማርያም ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን። አሜን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እመቤት ነኝ ከዩኒቨርስቲDecember 11, 2013 at 5:22 AM

   በመሠረቱ ለእመቤታችን ክብር ከተነሳ ጌታን መዉለድዋ ብቻዉን በቂ ነዉ። ወዳጄ ፀሐይና ጨረቃን የፈጠረን መዉለድ ነዉ ወይስ እነዚህን መጫሚያ ማድረግ ነዉ የሚበልጠዉ። ምነዉ ቁጥር 2ን ተዉከዉ? እንዲህ ይላል "እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች"። እዉን እመቤታችን ጌታን ስትወልድ ምጥ ነበራት? እንዲህ ስለክብርዋ የተጨነቃችሁ ምሰሉ እንጂ እንደተራ ሴት ባለምጥ አድርጋችሁ አሰነሳችኋት፤የናንተ ዕዉቀተ ይህን ያህል ነዉ፤ ይቀጥልና ቁጥር 6 ላይ "ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።" እመቤታችን 1260 ቀን እንድትቆይ የተደረገዉ የት ነዉ? መልስ እፈልጋለሁ። ለማንኛዉም ይህ ክፍል ስለ እስራኤል የሚናገርና እስራኤል የተስፋዉ ቃል የሚፈጸምበት ነገድ በመሆኑ ስለሚደርስበት መከራና ምጥ የሚያመለክት እንጂ ቀጥታ እመቤታችንን ማለቱ አይደለም። ንትርኩን ትታችሁ ልብ አድርጉና ተመልከቱት

   Delete
 51. ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ ልባችሁን ደንዳና /እልከኛ አታድርጉት ፤ እብራ 3፡8-9
  እየሱስ ብቻ አማላጅ ነዉ!

  ReplyDelete
 52. ታዲያ ምን አታከተህ? ለምን ጥለህ መናፍቅ ያልሆኑት¡(ድንቄም) ጋር አትሄድም? ታቦት የሌላቸው ጋር፤ የአንተን እምነት 100% የሚቀበሉት የምትመስላቸው ጴንጤዎች አሉልህ አይደል የምን ሙጥኝ ማለት ነው? “መናፍቅ” ጋር ምን ትሰራለህ? እባክህ ከ“መናፍቅ ቤት” ውጣልንና እንገላገልህ። ረስቼው ሁለተኛ ደሞዝህ፤ እንጀራህ ነው ለካ።

  ReplyDelete