Sunday, November 24, 2013

ጾማችን ይታደስ


የዚህ ጽሑፍ ርእስ ምናልባት ሊያስቆጣ ይችል ይሆናል፤ ቢሆንም አይቈጡ! “አንብብዋ ለመልእክት እምጥንታ እስከ ተፍጻሜታ” ትርጓሜ “መልእክቲቱን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያንብቧት” የሚለውን የአበው ትክክለኛ አስተያየትም እዚህ ላይ በሥራ ላይ ያውሉ፡፡ ጥያቄው የነቢያት ጾም ለእኛ ምናችን ነው? የሚል ነው፡፡

በቤተክርስቲያናችን ከሚጾሙ ሰባት አጽዋማት አንዱ የነቢያት ጾም ነው፡፡ ጾሙ ከኅዳር 16 እስከ ታኅሣሥ 28 ድረስ ባሉት ቀናት ይጾማል፡፡ ይሁን እንጂ በሚጀመርበት ቀን ላይ ውዝግብ አለ፡፡ በ15 ነው መጀመር ያለበት የሚሉ አሉ፤ የለም በ16 ነው የሚሉም አሉ፡፡ ጾሙ ነቢያት በተለያየ ጊዜ የጾሟቸው አጽዋማት በአንድ ላይ ሆነው የሚዘከሩበት ጾም ሲሆን፣ ነቢያት በየዘመናቸው የክርስቶስን ሰው መሆን በመናፈቅ የጾሙት ጾም እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህ ርእስ የጾመ ነቢይ በመጽሐፍ ቅዱስ ይኖር ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግን መነሣት ያለበት ይመስለኛል፡፡ ይሁንና የነቢያቱ ጥያቄ በክርስቶስ መምጣት ተመልሷል፡፡ ታዲያ እኛ መልስ የተገኘበትን ጾም ደግመን መጾማችን ለምን ይሆን? በተመለሰው የነቢያት ጥያቄ ላይ ሌላ ጥያቄ ለማንሣት ነው ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖረን ይሆን?


በሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን በዚህ ጾም ላይ ጥያቄ ተነሥቶ እንደ ዋናዎቹ አጽዋማት የሚታይ ባለመሆኑ አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት ሐሳብ ቀርቦ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት የዚህ ጾም መታሰቢያው እንዳይጠፋ ያህል የጾሙ የመጨረሻ ሳምንት ብቻ እንዲጾም ሐሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎም ነበር፡፡ ይኸው ሐሳብ ሐዲስ ሕይወት በተባለና ቅዱስነታቸው ተሐድሶን በቤተክርስቲያን ውስጥ ለማነሣሣት “ሐዲስ ሕይወት” በሚል ርእስ በሰየሙት መጽሔት ላይም ወጥቶ ነበር፡፡ ጾመ ነቢያትና ጾመ ሐዋርያት “እንደ አበይት አጽዋማት ስለማይቈጠሩ የጾሙ መታሰቢያነት እንዳይረሳ ያህል የነቢያትና የሐዋርያት ጾም ለሕዝቡ ሲባል ካልጾሙ ፋሲካ ካላዘኑ ደስታ አይገኝምና ከየአጽዋማቱ መጨረሻ አምስት አምስት ቀናት በመጾም የክርስቶስ ልደትና የሐዋርያት ዓመት በዓል እንዲከበር” እና ሕሙማን፣ ወታደሮች፣ መንገደኞች፣ የፋብሪካ ሠራተኞች፣ ከፍተኛ ጥናት ባለው በትምህርት ላይ የሚገኙና ከባድ ሥራ የሚሠሩ ከፍስክ ምግቦች በቀር ቁርስ መብላት እንደሚችሉ ተገልጿል። (ሐዲስ ሕይወት 1967፡ 33)። እነዚህ ሁለት አጽዋማት እንዲሻሻሉ ሐሳብ የቀረበበትና ጾማችን ተሐድሶ ያስፈልገዋል የተባለበት ዘመን እንዳልነበረ ዛሬ ግን ማሻሻያው ውሃ በልቶት በማኅበረ ቅዱሳን በኩል 8ኛ ጾም ተብሎ የጽጌ ጾም እንዲጾም በተለያየ መንገድ ግፊት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በእርግጥ ይህ የገና ጾምና የሠኔ ጾም “የቄሶች ጾም” ተብሎ ከአርብ ሮብ በቀር በአብዛኛው ሰው ዘንድ እንደ ጾም ያልተወሰደውና የማይጾመው ይበልጥ በአቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን ከቀረበው የማሻሻያ ሐሳብ በመነሣት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የምታወጣቸው የተሐድሶ ሐሳቦች ሰሚና ተቀባይ ባይኖራቸውም፣ ይኸው በአቡነ ቴዎፍሎስ ጊዜ የቀረበው የአጽዋማት ማሻሻያ ሐሳብ “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻ ዓ.ም. ” በተሰኘውና በ2000 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት በታተመው መጽሐፍ ላይ ታሪክ ለማስታወስ ይሁን ሐሳቡን እንደገና ለመቀስቀስ ባይታወቅም ዳግመኛ ተጽፏል (ገጽ 37፡52)።

አሁን ጥያቄው የነቢያትን ጾም የምንጾመው ለምንድነው? የሚል ነው፡፡ ነቢያት የጾሙት በዘመናቸው ካጋጠማቸው ነገር በመነሣት ወይም የሚፈልጉት ነገር እንደእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲከናወን የእግዚአብሔርን እርዳታ ለመጠየቅ ነው፡፡ ጥያቄያቸው ከተመለሰ እኛ ከዚህ ልንወስድ የሚገባን ትልቅ ትምህርት እኛም ዛሬ በሚያጋጥመን ልዩ ልዩ ችግር ምክንያት በፈጣሪያችን ፊት በጾም በጸሎት መቅረብ ያለብን መሆኑን ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ያለፈውን ታሪክ እያሰብን የምንጾም ከሆነ ለዛሬው ችግሮቻችን መፍትሔ ፍለጋ የፈጣሪን ፊት የማንፈለግ ታሪክ አስታዋሽ ብቻ ሆነን መቅረታችን ነው፡፡ ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት ልንጾምና የእርሱን እርዳታ ልንለምንባቸው የሚገቡ በርካታ ችግሮችና ጉዳዮች አሉን በእነዚያ ላይስ ለምን ጾም ጸሎት አናውጅም? ለምን ወቅት እንጠብቃለን? ስለዚህ የነቢያት ጾም ለእኛ ምናችንም ስላይደለ መጾምንና መጸለይን ከነቢያት ተምረን እኛም የራሳችንን ጾም በየጊዜው በማወጅ በጾም በጸሎት በፈጣሪያችን ፊት እንማለል፡፡ ስለዚህ ጾማችን መታደስ አለበት ቢባል እንዴት ስሕተት ይሆናል?


 


50 comments:

 1. enemenalebet hodamoch

  ReplyDelete
 2. Yihin M/k Endayesema !! metsomu balekefa wendimin megedelu , masadedu , sim meletefu , yesewun tidar maferesu beker ......... lebona yeseten Amen !

  ReplyDelete
 3. yetawojewn aıtsomim eyaık ıeıa bitawoj tiıaıeh?! askign.

  ReplyDelete
 4. ሆዳም!
  ይህ የ"ከርሦሙ አምላኮሙ"አስተያየት ነው፡፡
  ወይከውን፡ ከመ፡ ረቡዕ፡ ወዓርብ፡ ወውእቱ፡ ጾም፡ ዘይቀድም፡ እምልደት፡ ወጥንተ፡ ዚአሁ፡ መንፈቀ፡ ኅዳር፤ ወፋሲካሁ፡በዓለ ልደት፡፡
  ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 15

  ReplyDelete
 5. አዛኝ ቅቤ አንጓች አለ ያገሬ ሰው…
  እስቲ በጾም የተጠቀመ ዕንጂ የተጎዳ ማንአለና ነው ‹‹ይህ ፆም ለኛ አያስፈልግም›› የሚያስብለው…
  እናም እናንተ አይደለንም ብትሉም ግብራችሁ ይመሰክራልና እንደ ግብር አባቶቻችሑ ሲያስፈልጋችሁ ብቻ ጹሙ … ጾምም አውጁ…
  እኛ ግን የነቢያትን አብነት ተከትለን ለነሱ የከፈለውን በረከት ረድኤት እንዲከፍለን እንጾማለን … በዚህም እናንተ የምትሏቸው ‹‹በርካታ ችግሮችና ጉዳዮች›› መልስ ስለሚያገኙ ይህቺ ቤ/ክ መሠረት እንደሌለው የመናፍቃን አዳራሽ ንፋስ በነፈሰ ቁጥር አዲስ ጾም ማወጅ አያስፈልጋትም…
  ልቦና ይስጣችሁ…

  ReplyDelete
 6. you point is always to hammer down the pillars of the church in any direction.

  ReplyDelete
 7. አይመለከታችሁም ከራሳችን ውረዱ፡፡ ተዋሕዶን ለቀቅ፡፡ መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና፡፡አይመለከታችሁም ከራሳችን ውረዱ፡፡ ተዋሕዶን ለቀቅ፡፡ መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና፡፡

  ReplyDelete
 8. አይመለከታችሁም ከራሳችን ውረዱ፡፡ ተዋሕዶን ለቀቅ፡፡ መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና፡፡

  ReplyDelete
 9. አይመለከታችሁም ከራሳችን ውረዱ፡፡ ተዋሕዶን ለቀቅ፡፡ መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና፡፡

  ReplyDelete
 10. አይመለከታችሁም ከራሳችን ውረዱ፡፡ ተዋሕዶን ለቀቅ፡፡ መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና፡፡

  ReplyDelete
 11. “ጾመ ሙሴ፣ጾመ ኤልያስ እግዚእነ ጾመ በእንቲኣነ አርኣያ ዚአሁ ከመ የሀበነ” ይላል ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ፡፡

  ነቢያት የጾሙት ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል ብለው ነው፡፡እኛ ግን የምንጾመው አንድም እናንተ እንዳላችሁት ካልጾሙ ፋሲካ-ካላዘኑ ደስታ የለም ብለን፣ሲቀጥልም የነቢያትን ልመና የተቀበልክ አምላክ የኛንም ተቀበል ብለን ዳግም ምጽአቱን በመጠበቅ እንጅ ክርስቶስ ይወለዳል ብለን ባለመሆኑ ጾማችን ከነቢያት ይለያል፡፡ሌላው ቢቀር በህብረት የሚጾምን ጾም እ/ር አይቀበልም የሚል ድንጋጌ አለመኖሩ በቂያችን እኮ ነው፡፡

  በህብረት መጾም ያስኮንናል የሚል ከእ/ር የሆነ ቃል አለ እንዴ??

  ደግሞም ጾሙ በህብረት ስለ ሆነ ብቻ የግል ልመናን አታቅርቡ ያለ የለ፣እኛ ከበደን አላልን፣ምንድን ነው ወንድሞች በየጾሙ መግቢያ እንደ ቆሮንቶሱ ፈታኝ ብቅ ማለት!!

  ይልቅስ ይቺን ያላችሁዋትንም 5 ቀን እንኩዋ ለመጾም ሞክሩ፡፡በእኛ በኩል 44ቱንም ቀን መጾም ስለምንችል ሀሳብ አይግባቸሁ!!ለጊዜው የሚጾም እንጅ የሚታደስ ጾም የለንም!!

  እናንተ ግን ይህን ሁሉ በማደስ ከመድከም አዲስ ቤት ሰርታችሁ ጎጆ መውጣት አይሻላችሁም???ለነገሩ ምን አደከማችሁ?? አፍራሹ መነኩሴ ሉተር የሰራው ዘመናዊ ቤት የት ሄዶ!!!

  ReplyDelete
 12. ቃለ ህይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 13. የነቢያት ፆም ለኛ የነፍስ ቁስላችንን የምንጠግንበት የነፍሳችን መድኃኒት ነው፡፡ ዛሬ ሰይጣን ከሚያሸንፈን/ከሚጥለን/ የበለጠ ሆዳችን ገደል እየከተተን ስለሆነ አይደለም አባቶቻችን የመሰረቱልንን ፆም ብቻ አይደለም 365/6ቱንም ቀን ብንፆም ስጋን ለነፍስ ማስገዛት እንጂ ምን ይጎልብናል ስጋ ቢሰባ ለኃጥያት እና ለመሬት መሆኑን መገንዘብ መቼም የሚያቅተን አይመስለኝም "ለፆም አድሉ" ነው እኛ የተማርነው ያደለው ዕድሜ ልኩን እንኳን ከጥሉላት ምግብ ይቅርና ……………ከልክሎ እራሱን ለእግዚአብሔር ብቻ ያስገዛል የአባቶቻችን የነቢያት እና የሐዋሪያት አምላክ በረከታቸውን ያድለን ልብ ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 14. Our Father Adam and Our Mother Hewann ate nothing except vegetables and fruit. Hence fasting remember us humanity with original sin.
  The Nativity Lent took place according the Orthodoxy tradition 40 days preceding the Nativity of our Lord and Savior Jesus Christ. It is stated under the Orthodoxy Tradition these 40 days correspond to the 40 days that the Arch-Prophet Moses fast on the mountain Sinai, before receiving the Ten Commandments from God, or the word of God to his people. Thus, with Our Lord Jesus Christ being the Word of God, We Christians fast those 40 days in preparation of receiving the Word of God in flesh at the Feast of the Nativity.

  An additional 3 days were added later by the Patriarch of Alexandria to commemorate the 3 days of fast that moved the Mountain from Cairo leaded by Saint Simon the Tanner during the ruling of Caliph One can see many cases. The apostles fasted after Pentecoste day before they were dispersed to spread the Gospel. We are fasting the Prophet fast in order to live withe Our Lord and Savior Jesus Christ By the grace of the Prophets and the Apostles fast to sustain our Christian faith and deeds by the grace of the Apostles.! Moreover fasting is also good for the flesh. It cleanse cholesterol and uric acid!

  ReplyDelete
 15. Fasting periods
  Fasting In Eastern Orthodox!

  The Apostles' Fast which varies in length from 8 days to 6 weeks. It begins on the Monday following All Saints Sunday (the first Sunday after Pentecost) and extends to the Feast of Saints Peter and Paul on June 29. Since the date of Pentecost depends on that of Pascha, and Pascha is determined on the lunar calendar, this fast can disappear completely under New Calendar observance (This is one of the objections raised by opponents to the New Calendar).

  The Dormition Fast, a two-week long Fast preceding the Dormition of the Theotokos (repose of The Virgin Mary), lasting from August 1 through August 15.

  In addition to these fasting seasons, Orthodox Christians fast on every Wednesday (in commemoration of Christ's betrayal by Judas Iscariot), and Friday (in commemoration of Christ's Crucifixion) throughout the year. Monastics often fast on Mondays (in imitation of the Angels, who are commemorated on that day in the weekly cycle, since monastics are striving to lead an angelic life on earth, and angels neither eat nor drink).

  Even the Eastern Orthodoxy fast are almost the the same as ours! This shows that EOTC received Fasting period through Apostolic succession

  ReplyDelete
 16. የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የማታውቀውን የዘከዘክ አይመስልህም? ካላወቅሃቸው ነገሮች ኣንዱን ከነመልሱ አነሆ፥ በቤተክርስቲያናችን የጾመ ነቢያት መግቢያና የሚያበቃበት ቀን አያከራክርም፥፥ በዘመነ ዮሐንስ (ጳጉሜ 6 ቀን በሚሆንበት ዘመን) ጾሙ በህዳር 15 ይጀምራል በታህሳስ 28 ያበቃል፥፥ በሌሎቹ በዘመነ ማቴዎስ በዘመነ ማርቆስና በዘመነ ሉቃስ (ጳጉሜ 5 ቀን በሚሆንበት ዘመን) ደግሞ ጾሙ በህዳር 16 ይጀምራል በታህሳስ 29 ያበቃል፥፥ በሁሉም ዘመናት ማለትም በያመቱ የምንጾመው 43 ቀን ነው፥፥ የሰው ሃይማኖት ውስጥ ገብተህ የማታውቀን ነገር ከመዘባረቅ በፊት ጠይቀህ አውቀህ ብትጽፍ መልካም ነው፥፥

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሞኞ ይህንንማ የጥንት ልማድ ሲኖዶስ ተብየው ቀየረው እኮ አልሰማህም እንዴ?? ምነው ለቤተክርስቲያን እቆረቆራለሁ ስትል ይህን አለማወቅህ

   Delete
 17. gr8.besal meleekit new. I know this truth. but min ale belugn comment yemiaderiguachihu yesidib nada endemiazenibu.gin afim yistum bilachihu melesulachew.lelaw hodachew amilakachew yemilewun tikism yalebotaw litikisubachihu yichilalu.yihe gin zemenun kasitewalin lehodu yaderu...lekiristos wengel yemayitazezu bizu menekosatina ageligayochnm yimeleketal.ewunetin behodachew yekeyeru...yeenjeragguday honobachew lehilinachew menor yetesanachewun.....bet yikuterachew. geta yikir yibelachew.beritu beritu beritu.!!!

  ReplyDelete
 18. Always putting protestant ideas at the end. We understand the purpose of your writings. You start out with a question that attracts the Orthodox audience, but you close with protestant beliefs about anything. Could you please answer this questions for me-Why do not you leave the Orthodox church alone and preach to your choir?

  ReplyDelete
 19. Always putting protestant ideas at the end. We understand the purpose of your writings. You start out with a question that attracts the Orthodox audience, but you close with protestant beliefs about anything. Could you please answer this questions for me-Why do not you leave the Orthodox church alone and preach to your choir?

  ReplyDelete
 20. You don't have to fast if you don't want to.

  ReplyDelete
 21. Weyy Teamirr, bezih zemen yemayisema neger yelem. Bilachihu bilachihu demo yihen ametachihu? Eshi, engidiyaw Catholic enihuna?! Tsomu hulu sikorett sikorett, amist amist ken setachihutina arefachihut? ene sake betam eyasichegeregn new yemir. kkkkkkkkk yeEwinet hasabachihu betam yasikal, betam. Beka lenante sinil eshi, enantenim aferr kedime yabilachiu. Tsomin yemishir hulu yesiga tegezzi new eko!!

  ReplyDelete
 22. One day, I was expecting this kind of post on this blog from you, a pseudo theologian. Trust me, you won't sale your idea in Seattle. You better back to your shoe/tunnel you vacated out in the last couple of months.

  ReplyDelete
 23. I do agree with you. We have to arrange our own fasting and praying days instead of remembering historical fasting days. Good Job!

  ReplyDelete
 24. HODAM ERE ANTES YEMOTK NEH CHERSEH GETA YIKIR YIBELIH. ASAMA

  ReplyDelete
 25. Absolutely, you are right!!! However, be careful "Mak & Papas" whom don't want to hear the truth.

  ReplyDelete
 26. Bezmenachen kemiwerdut mekerawech antsar,menem sem yinurew,bemanem sem yiseyem (emneten yemitsarer sem eskalehone deres) 8 aydelem 10 tsom benetsom melkam new.yih tsom babatochachin nebiyat sem biseyem menden new chegru?eyandandu betsomu weqt yefelegewun,yederesebeten mekera eyasebe yitsum.ke semu aydelem chegeru,wanaw metsomu new,bicha ende gebr ababatachihu ende luther yemekawem (protest) yemadreg sus hunobachihu weym aweku aweku lemalet new enji yih cheger aydelem.hodachew amlakachew yehonu sewech tsom yitelalu.meknat felgo ketspm kemeleyet endenante,meknat felgo metsom yibeltal (adeleo letsom new ena).lebona yisteh

  ReplyDelete
 27. በመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ልጅ ስላልሆንክ ቤተክርስቲያናችን አትበል መናፍቃን ሁሌ ለስጋችሁ የሚመቻችሁን ብቻ ነው የምታደርጉት እየው ባለፈው አንዱ የመናፍቅ ቄስ ከኦርቶዶሶች ጋር እንጹም ሲል ነበር አንተ ደሞ ይታደስ ትላለህ ምን አይነት ግራ የገባችሁ ናችሁ ጾም እኮ ወደ አምላክ ያቀርባል ጹሙ ጸልዩ ያለው እሱ ነው እሮን ጌታ ስለታየዘ አርብ ስለተሰቀለ እየጾምን ሐዋርያት የጾማትንም እየተጾምን ነው ገናናን የምናከብረው በቃ ተወልዶል አንዴ ተንስል አንተ ለምን ገናና ፋሲካን ታከብራለህ ስለሚበላ ሆድንህን ስለምትሞላ ግን ለምን እራስህን ጠይቅ ለመጾም ምክንያተ እንፈልጋለን እኛ ወደ ጌታ ለመቅረብ እናንተ ደሞ ለመብላ ለነገሩማ አንዴ በክርስቶስ ድነናል ሐጢያት ብንሰራም እያላችሁ የምትሰሩትን ወንጀል ይከው በብሎጋችሁ እያየነው ተራ ሐሜተኞችና ውሸታሞ አይደላችሁ ልቦና ይስጣችሁ እቺ ቤተክርስቲያን ሐዋርያት በደማቸው ያመሠረት ነች እንዲ እንፓስተር እከሌ እንደሚፈልት የመሠረት አይደለም እና ስለቤተክርስቲያን ከምታወራ ስለወንጌል አውራ ሁሉ መንቀፍ መናፍቅ ሥራ ይኼ ነው በቃ አይደል ልብ አለህ ስለሙስሊም በሙስሊም ስም ብሎግ ከፍተህ አውራ ምንም ለማያውቁት ግን አላማህ እውነት ለማጥፋት አሁን ጾም ምን ክፋት አለው ምን አገባህ እኛ በጾምን ይሄ እኮ የመብትም ጉዳይ ነው ምን አገባህ ስለ ራስህ አስብ

  ReplyDelete
 28. ስለጾም ካነሳችሁማ ካህናትና ሰሰባክያን መነኮሳትም ሳይቀር አይጾሙም። ለህዝቡ ያውጃሉ እነሱ ግን ህዝቡን እየተደበቁ ይበላሉ። እዉነት ነው ህዝቡ አይታለል በይፋ ይነገር እስከመቼ በድብቅ ቤተክርስቲያን ይገለገላል? በተለይ አባቶች መች ነው ስለእውነ ምትኖሩት? እስኪ እናንተ በድብቅ የምታደረጉትን ለህዝቡም እውነቱን ገሩትና እናንተም ጽድቅ አግኙ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሌባ አጭበርባሪ አንተምን አግባህ ታዲያ ያንተን ነው የበሉት እንኩን በሉ ቅናህ እንዴ ካንተ እኩል ሲበሉ አስወደዱብህ ወሬኛ የኛ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ በጌታ ዘመን ሀዋርያቱ በሉ ሲሉ ከሳሾች ምን አለ ጌታ ; በሉ በሉ በሉ ሀሜተኛ ወሬኛ አርፈህ ከርስህን ሙላ የሰው ስጋ አትብላ

   Delete
 29. tebarek,tiru melikit new

  ReplyDelete
 30. Protestant begin to fast! Methodits Church
  During Lent, which starts Wednesday (Feb. 13), the 40-year-old mother of two keeps a type of Daniel Fast, which involves eating only food from seeds (vegetables, fruits, unleavened grains), drinking only water and practicing daily devotions.
  A similar regimen kept Daniel and his friends free from corruption in King Nebuchadnezzar’s Babylonian court, according to the Bible. Now the Old Testament example guides growing numbers of Christians in the 40-day period of preparation for Easter.
  “We set apart a sacrifice in Lent in order to identify, even the smallest (bit), with what Jesus sacrificed for us,” said Lester, who attends University Carillon United Methodist Church in Oviedo, Fla. “He died for me. The least I can do is to sacrifice the foods that are comforting to me.”
  Devotees say the Daniel Fast brings them closer to God by enhancing self-control, purging bad habits and improving health. It bears echoes of ancient tradition. Forgoing meat, dairy and sweeteners for a season makes the Daniel Fast resemble Orthodox Lent, which restricts consumption of meat, dairy, and oils in the run-up to Easter.
  Observers see benefits to linking Lenten spirituality with healthy eating in a nation that can afford to shed a few pounds. But some also worry about food becoming a distraction or an obsession in a season of repentance and renewal.

  ReplyDelete
 31. የተሀድሶ መናፍቃን ነገር ሁሉ ነገራችሁ ምድራዊ፤ጥርጥር
  መብላት ከፈለጋችሁ መጥረግ ትችላላችሁ፤ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና የተወለደውና ዘመን የተቆጠረለት ነቢያት ስለ ፆሙ ሱባኤ ስላስቆጠሩ ብቻ አይደለም፤ በቸርነቱ ነው እንጂ፤የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ግን ይለያል መወለድህን ስላሳየኽን ዳግመኛም ግርማ መንግስትህ ስለምትመጣ ብለን ፆምን አብዝተን / ለነፍስ አድላ በሚለው መንፈሳዊ አስተምህሮ

  ReplyDelete
 32. ይሄ ያንተ ና መሳዮችህ ፍልስፍና ነው ሁል ጊዜ ስለመብላት ክርክር ማንሳት ትወዳላችሁ ዝም ብለህ ብላ ሆዳም እስቲ ልጠይቅህ መጾም ያስቀጣል እኔ እንደማምነው በሀይማኖቴም እንደሚያስተምረው ለጾም ማድላት እንዳለብኝ ነው የምረዳው መሰሎችህንንና እራስህን ለመደለል ጾም መታደስ አለበት ፤ አረንግረን ለምን ልደቱን እናከብራለን ጊዜው አልፎዋል ትንሳዬውንም እንዲሁ መታደስ አለበት ምነው ህይወት ብትሰብክ ስለመወለዱ በመታሰቢያነት ብንጾም አንተ ምንህ ተጎዳ ? አንተ እኮ ጌታን አማላጅ የምትል ስለሆነ አንተ አድስ ጾምህን መናፍቅ ::
  ‹‹ትልቅ የማይታረቅ ልዩነት ስላለን ለእኛ ጌታ ፈራጅ ነው ›› ፡፡

  ReplyDelete
 33. ይሄ ያንተ ና መሳዮችህ ፍልስፍና ነው ሁል ጊዜ ስለመብላት ክርክር ማንሳት ትወዳላችሁ ዝም ብለህ ብላ ሆዳም እስቲ ልጠይቅህ መጾም ያስቀጣል እኔ እንደማምነው በሀይማኖቴም እንደሚያስተምረው ለጾም ማድላት እንዳለብኝ ነው የምረዳው መሰሎችህንንና እራስህን ለመደለል ጾም መታደስ አለበት ፤ አረንግረን ለምን ልደቱን እናከብራለን ጊዜው አልፎዋል ትንሳዬውንም እንዲሁ መታደስ አለበት ምነው ህይወት ብትሰብክ ስለመወለዱ በመታሰቢያነት ብንጾም አንተ ምንህ ተጎዳ ? አንተ እኮ ጌታን አማላጅ የምትል ስለሆነ አንተ አድስ ጾምህን መናፍቅ ::
  ‹‹ትልቅ የማይታረቅ ልዩነት ስላለን ለእኛ ጌታ ፈራጅ ነው ›› ፡፡

  ReplyDelete
 34. this shows who are you

  ReplyDelete

 35. Great Idea!!!
  We protestants need to revise our fasting seasons.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይልቅ ራስህን አድስና ወደ ኦርቶድክስ ተመልሰህ ከበረከቱ መካፈል ነው ምንፍቅና አይጠቅምም በልቶ ተበልቶ ወደ ----- ነው

   Delete
 36. የተሀድሶ መናፍቃን ነገር ሁሉ ነገራችሁ ምድራዊ፤ጥርጥር
  መብላት ከፈለጋችሁ መጥረግ ትችላላችሁ፤ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና የተወለደውና ዘመን የተቆጠረለት ነቢያት ስለ ፆሙ ሱባኤ ስላስቆጠሩ ብቻ አይደለም፤ በቸርነቱ ነው እንጂ፤የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ግን ይለያል መወለድህን ስላሳየኽን ዳግመኛም በግርማ መንግስትህ ስለምትመጣ ብለን

  ReplyDelete
 37. የተሀድሶ መናፍቃን ነገር ሁሉ ነገራችሁ ምድራዊ፤ጥርጥር
  መብላት ከፈለጋችሁ መጥረግ ትችላላችሁ፤ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና የተወለደውና ዘመን የተቆጠረለት ነቢያት ስለ ፆሙ ሱባኤ ስላስቆጠሩ ብቻ አይደለም፤ በቸርነቱ ነው እንጂ፤የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ግን ይለያል መወለድህን ስላሳየኽን ዳግመኛም በግርማ መንግስትህ ስለምትመጣ ብለን

  ReplyDelete
 38. Mahibere kidusanen satanesu malef atichilum aydel. kakakakaka!

  ReplyDelete
 39. Tekekele nehe e/z yeberekeh

  ReplyDelete
 40. Yalegebagn... yalebetachewu lemen ye sewu bet tanekuakualachewu...stay away from..
  one tewahedo.. leyunetachen eko yeh newu ... back offffffff

  ReplyDelete
 41. endewum tsom ansonal,,, mikneyatum hazen mekera sidet be hagerachin lay silebeza ahunim lela bezemenachin yemichemer tsom yasfeligenal,,, endih endenante ayinetunim
  tekula yeminatefaw betsom new,,,, silezih kenante yemintebikew endih ayinet neger silehone ayigermenim,,,,,,,

  ReplyDelete
 42. ሲወልዱ አይታ ምን አለች ይባላል የሚገርም ነገር መናፍቆቹ መናፍቃን ሲሉ የራሷን አበሳ በሰው አብሳ
  ግልብ ቀደማ ለመሆኑ በተፈጥሮ ወንድሙን መናፍቅ በማለት ሊጸደቅ ነው አየ ጉድ ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ
  በተሆነ ሆድን ከእህል ከማስጾም አፍን ከነገር መለጎም ሰው ጾሞ ከግዜር ሳይሆን ግንኝነቱ ከሐሜትና ክምጽድቅ ነው እውነት ቢሆን ዕውነት ነበር ኩሉ ዐረየ ወኅቡረ ዐለወ እንዲያው ሆድ ይፍጀው!

  ReplyDelete
 43. ሲወልዱ አይታ ምን አለች ይባላል የሚገርም ነገር መናፍቆቹ መናፍቃን ሲሉ የራሷን አበሳ በሰው አብሳ
  ግልብ ቀደማ ለመሆኑ በተፈጥሮ ወንድሙን መናፍቅ በማለት ሊጸደቅ ነው አየ ጉድ ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ
  በተሆነ ሆድን ከእህል ከማስጾም አፍን ከነገር መለጎም ሰው ጾሞ ከግዜር ሳይሆን ግንኝነቱ ከሐሜትና ክምጽድቅ ነው እውነት ቢሆን ዕውነት ነበር ኩሉ ዐረየ ወኅቡረ ዐለወ እንዲያው ሆድ ይፍጀው!

  ReplyDelete
 44. Hodam ..........:...........

  ReplyDelete