Wednesday, November 27, 2013

ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ


ዳንኤል ክብረትን ካበ ማኅበረ ቅዱሳንን ተረበ
አንጋፋው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በጥቅምትና ኅዳር/2006 ዓ.ም. እትሙ በርእሰ አንቀጹ “፴፪ኛውን አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ እንደ ታዘብነው” በሚል ርእስ ባስነበበው ጽሑፍ ዳንኤል ክብረትን አለቅጥ የካበውና “ዕውቅ ጸሐፊና የበጎ ፈቃድ  ሐዋርያ” የሚል ማዕረግ ሰጥቶ እላይ የሰቀለው ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንን ደግሞ በዚህ አያያዝህ ዕድሜህ ዐጭር ነው ሲል ተርቦታል፡፡ በመካብም በመናድም የማይታማው ዜና ቤተ ክርስቲያን ዳንኤልን የካበው በአውስትራሊያ የሜልቦርን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ምእመናንን አስተባብሮ 18,500 ብር ለ32ኛው የሰበካ አጠቃላይ የፐርሰንት ክፍያ ፈጽሟል በማለት ነው፡፡

እንዲህ ማለት ይገባ ነበር ወይ? እውን ዳንኤል የፈጸመው የፐርሰንት ክፍያ ነው ወይስ ስጦታ? እንደሚታወቀው የፐርሰንት ክፍያ ከአብያተ ክርስቲያናት ገቢ ላይ ለቤተክህነት የሚደረግ የ20% ፈሰስ ነው፡፡ ታዲያ በምን ሒሳብ ነው ዳንኤል ምእመናንን አስተባብሮ አስገባ ያለውን ገቢ “ፐርሰንት” ነው ሲል የጠራው? ነው ወይስ ማቅን ለመናድ የዳንኤልን ስጦታ እንደ መቅድም መጠቀሙ ይሆን?  ምናልባትም በአካል ከማቅ ቢወጣም በመንፈስ ግን  መቼውንም ቢሆን ከማቅ የማይለየው ዳንኤል እንደ ግለሰብ ለዚያውም ቤተክርስቲያን በመደበኛ ሠራተኛነት ሳትመድበው ፐርሰንት ከከፈለ፣ ማቅ ፐርሰንት የማይከፍለው እስከ መቼ ነው? ብሎ ለማሳጣትና ማቅን ለመናድ የልብ ልብ እንዲሰጠው ብሎ የድፍረት መርፌ ለመወጋት ሲል ዳንኤልን “ፐርሰንት አስገባ” ሲል አሞግሶታል፡፡ እርግጥ ይህን ያልህ የሚያጽፍ ባይሆንም ዳንኤል እንዲህ ማድረጉ ለማቅ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ተብሎ ተገምቷል፡፡


ዜና ቤተ ክርስቲያን ዳንኤልን በካበበት ጽሑፉ ማቅን ደግሞ ተርቦታል፡፡ ማቅን ለመተረብ “በነገራችን ላይ” ሲል የተንደረደረው ጋዜጣው ከሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ጋር በተያያዘ የማቅን “በጎ” ሊባል የሚችል ጎኑን በመጥቀስ ነው የጀመረው፡፡ “በነገራችን ላይ ሲጀመር ጀምሮ ማኅበረ ቅዱሳን ከጉባኤው ተለይቶ አያውቅም፤ በአንዳንድ ሥራዎች ቤተ ክርስቲያንን እንደሚያግዝም በአህጉረ ስብከት ሪፖርት አልፎ አልፎ ይጠቀሳል፡፡” ብሏል፡፡ “ሆኖም” ይላል ጋዜጣው ፈራ ተባ እያለ፡፡ “ሆኖም እንደ ድፍረት አይቆጠርና [ማኅበረ ቅዱሳን] ከሚያገኘው ገቢ ፐርሰንት እንዲከፍል የማይጠየቀው እስከ መቼ ድረስ ነው? በዘንድሮው ጉባኤ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የፋይናንስ አቅሙን እንዲቆጣጠረው መወሰኑ ታላቅ የምሥራች ነው፡፡ ምናልባት ዕድሜ ከሰጠው ወይም በለስ ከቀናው በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ፐርሰንት ለመክፈል ቃል እንደሚገባ ተስፋ እናደርጋለን፡፡” ብሏል፡፡

ትሕትናው ከአጉል ትሕትና እንዳይቆጠርበት እንጂ ይህ ጥያቄ ለዜና ቤተ ክርስቲያን ተገቢ ጥያቄ እንጂ እንደ ድፍረት የሚቆጠር አይመስለንም፡፡ የማቅን የፋይናንስ አቅም ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመቆጣጠር መወሰኑ እንደ ተባለውም “ታላቅ የምሥራች ነው፡፡” ነገር ግን “ምናልባት ዕድሜ ከሰጠው ወይም በለስ ከቀናው” የሚለው አገላለጽ ግን ነገር አለው፡፡ ማቅ በመንግሥትና በእውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እይታ በአክራሪነት ከመፈረጁ ጋር ተያይዞ የዕድሜ ገመዱን በራሱ ሊበጥስ ይችላልና “ዕድሜ ከሰጠው” የሚለው በቀቢጸ ተስፋ የተሞላ አገላለጽ ማቅ የተወሰነበትን ተግባራዊ ካላደረገ ዕድሜውን ማሳጠሩ ነው የሚል አንድምታ ያለው ይመስላል፡፡

“በለስ ከቀናው” የሚለውም እንደተለመደው ሳይቀሰፍ በፊት አንዳንድ ጳጳሳትን በጥቅማ ጥቅም ይዞ ዕድሜ ካስጨመረ ዞሮ ዞሮ ፐርሰንት ለመክፈል ቃል መግባቱን በሚቀጥለው የሰበካ ጉባኤ አጠቃላይ ስብሰባ ላይ እንሰማ ይሆናል የሚል ትርጉም ሊሰጠው ይችላል፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዳንኤልን የካበውና ማቅን የተረበው ለምን ይሆን? የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት ሲሆን፣ በዋናነት ለማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት ጥቂትም ብትሆን የዳንኤልን ሥራ አጉልቶ በማሳየት ማቅ በቤተ ክርስቲያን እየተጠቀመ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን እየጠቀመ አለመሆኑን መግለጽ ይመስላል፡፡ አንድ ግለሰብ ያደረገውን ያህል እንኳን አንድ ቤተ ክርስቲያንን ትልቅ የገቢ ምንጩ ያደረገ ማኅበር ማድረግ የተሳነው መሆኑን ያሳያል፡፡ በእርግጥም ማቅ በቤተ ክርስቲያን ስም ከሚሰበስበው ገንዘብ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ፈሰስ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይሁን እንጂ ከማቅ ባሕርይ አንጻር ከሚያገኘው ገቢ ፐርሰንት ያስገባል ተብሎ አይታሰብም፡፡ እንኳን እርሱ ሊያስገባ ለቤተክርስቲያን አሥራትና መዋጮ የሚሰጡትን ምእመናንንም በማሳመፅ “ለማንም ቄስ መስከሪያ ነወይ የምትሰጡት? ወደእኔ ገቢ ብታደርጉ ለገዳማትና ለቆሎ ተማሪዎች መደጎሚያ አደርገዋለሁ” እንደሚል ምንም አያጠራጥርም፡፡ በ32ኛው የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በማቅ ላይ የቀረበው ክስም ይህንኑ ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ ማቅ ፐርሰንቱን ለማስገባት ራሱን ካላዘጋጀ ዕድሜውን ለማሳጠር ወስኗል ማለት ነው፡፡      

13 comments:

  1. You speak as you want! You do not understand misinterpreting is a sin! Let God forgive you

    ReplyDelete
  2. Ere ebakih? Pe pe pe! Doro bitalm.... doro neger neh

    ReplyDelete
  3. ይበለው ደሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ!!!

    ReplyDelete
  4. ይበለው ደሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ!!!

    ReplyDelete
  5. WEY GUDD EKO NEW WEGENOCHE MK LEKAS BEHULUM BOTA NEW ATEKEFELU EYALE MEMENUN MEYASAMETSEW ENE EZHI BEMENOREBET GERMEN FRANKFURT MAREYAM BETEKERESETEYAN YALU TIKIT MK ENDEFELEGUT LEMECHEFER BIMOKIRUM TENKARA BEHONUT ASTEDADARIW ENA SENBET TEMARIWOCH BOTA SELALETESETACHEW TKIT MEMENANE BEMASAMETS WERAWI KIFEYA ENDAYEKEFELUNA LE MK ENDIREDU MASAMETS JEMERU HEZIBUM SELENEKA ABARERACHEW AHUN YERASACHEW YETSELOT BET KEFETEW EYETSELEYU NEW KKKKKKK LEKAS YEHE SERACHEW HULUM BOTA NEW

    ReplyDelete
  6. አይ አማረ ተስፋዬ በቃ እንዲህ የዲያብሎስ መጫወቻ ሆነህ ቀረህ? ምስኪን ጴንጤ።

    ReplyDelete
  7. Abaselama meaning the father of peace, truth preacher, voce of voiceless and the truth children of Ethiopian orthodox church. As I informed you in the last comment here in Atlanta church is changed in to simply mart store. Guys change your gear to investigate this shame activity to release public instead of to accuse one person Daniel kissret that living in third world. In Atlanta St. Micheal store mart church that owned by Mr . Efrem it is very deep corruption. Peoples living in Atlanta has plan to protest this Sunday please write and invistegate some. We will send you concrete and detail information. The fake priest Merkebu sex women inside of the church every Monday at 4pm in down stairs. Daniel balcha released from jail that related to drug and drunk made followers to switch eotc to protestant. I my self I go to protestant Church. Please join us for protest at smith street This Sunday.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!ሥራ ፈት!

      Delete
  8. Daniel kisret is suffering from HIV aids leave him alone.

    ReplyDelete
  9. An infantile stage of cultism.

    ReplyDelete
  10. ante yekifu zer ye Egiziabiher lijoch yehonutin Danielinina mahibere kidusanin yemitiferawun yakil Amlakihin bitifera endet tiru neber? nisiha giba tesfa atikuret !!!

    ReplyDelete