Friday, November 8, 2013

በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በኮሎምቦስ ኦሀዮ በሚገኘው መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

በብፁዕ ወቅደስ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ስደተኛው ቅዱስ ሲኖድስ 37ኛውን መደበኛ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ጥቅምት 27/ 2006 ዓ.ም በኮሎምቦስ ኦሀዮ በሚገኘው መዴኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እየተካሄደ ነው።  ቅዱስ ፓትሪያርኩ በህመም ምክንያት በስብሰባው ላይ ያልተገኙ ሲሆን የሲኖዶሱን ምክትል ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ በርካታ ካህናትም አልተገኙም።  ምንጮቻችን እንደጠቆሙን በስብሰባው ላይ ካልተገኙት የሲኖዶሱ ሰባክያንና ካህናት መካከል  ሰባኬ ውንጌል አባ ወልደ ትንሳኤ፥ አባ ሃብተ ማርያም፥ ቀሲስ መልአኩ ባወቀ፥ ቀሲስ ጌታቸው፥ ቀሲስ እንዳልካቸው፣ መምህር ተከስተ ጫኔ እና ቀሲስ አንዱዓለም ይገኙበታል።

በስብሰባው ላይ ከተከናወኑና ከደረሱን ዜናዎች መካከል፦
 • የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸሐፊ  ቀሲስ መላኩ በዲያቆን አንዱአለም ግማዊ እንዲተካ ተደርጓል።  ምክንያቱ ምን እንደሆነ የደረሰን መረጃ የለም
 • ዲያቆን አንዱአለም መምህር ተከስተ ጫኔን  ለስዕል አይሰገድም ይላል በማለት እንዲወገዝለት ክስ አቅርቧል። የደረሰን መረጃ እንደጠቆመው ዲያቆን አንዱዓለም  ክሱን በልቅሶ በማጀብ ከማቅረብ በተረፈ መረጃ ተጠይቆ ግን ለማቅረብ አልቻለም።  ሆኖም ግን ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ፤ ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ፤ እና ሌሎችም አባቶች  መምህር ተከስተ ላይ የአስተምህሮ እንከን አይተውበት እንደማያውቁ መስክረዋል።  የአንዱዓለም ክስ በዳላስ በቅርቡ ከተከፈተው የፈለገ ህይወት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የኢየሱስን ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶሱ ስር ለማካተት ውይይት የነበረ ሲሆን ዲያቆን አንዱዓለም ግን ቤተ ክርስቲያኑ በሲኖዶሱ ስር የሚካተት ከሆነ የዳላስ ሚካኤልን ከስደተኛው ሲኖዶስ ስር ሊያስወጣው እንደሚችል ፎክሯል።  

ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሱን እናቀርባለን።


15 comments:

 1. the reason why dn andulem accuse is
  1. He is mahiber kidusan
  . his paper essay in theological college is on "Icons" so that he stands for pictures and images

  ReplyDelete
 2. Air lines have refused to transport one of Eotc priest in GA for the key reason his weight is 650 pound. The name of this fat man priest is Kesis Girma.

  ReplyDelete
 3. Then what happened ?? Are you guys always acting against Tewahido
  what is wrong with you or who are you trying to serve not the God of Tewahido of course Shame on you.

  ReplyDelete
 4. Hi guys the the exile holy synod is at danger situation may be there will split in two .

  ReplyDelete
 5. ይድረስ ለዲያቆን አንዱዓለም ዳላስ

  ሰላም ዲያቆን አንዱዓለም ምነው ጊዜው ረዘመብህ? ምንም ቢሆን የአንተ መነሻ ከሰንበት ትምህርት ቤት ቢሆንም፥ ብዙ ሰዎች እንደአንተ ከሰንበት ትምህርት ቤት እየተነሱ መለወጥና መዳን ችለዋል፡፡ አንተ ግን ምነው የመዳን ጊዜው ረዘመብህ? ምክንያቱም ሰው ሲከሱ ሚኖሩ ያልዳኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ መቸም ከሳሽ ሰው የእግዚአብሔር ወገን እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የአንተ ግን ወገንነትህ ወደሄትኛው እንደሆነ ስላልታወቀ ላሁኑ ልለፍህና ግን አንተ ከሄትኛው መምሕር ቁጭ ብለህ ሀ ሁ ቆጥረህ ተምረህ ነው እራስህን እንደ አዋቂ መምህር ተከሥተን እንዳላዋቂ በማድረግ ክሥ የመሠረትኸው? ከሚገርመው ደግሞ በብዙ ሊቃውንቶች መካከል እስከነ ትርጉሙ ጽፈህ የያዝኸውን ግዕዝ እየጠቀስህ በቃልህ እንደምትተረጉም አድርገህ ስትናገር ብዙ ጊዜ ይሰማል፡፡ ግን ይህ አያሳፍርህም? ምዕመናን ባያውቁህ እንኳ እኛ እናውቅሃለን፡፡ ሌላው ይሄን ተወውና ከመምሕር ተከሥተ እኔ አውቃለሁ ብለህ የእምነት ሕፀጽ እንዳለበት ክሥ አቅርበሃል፡፡ በመድረክ ላይ እንደ ግእዝ አዋቂ ሰው በማያውቁት ምእመናን ፊት ግእዙን እንደ ውዳሴ ማርያም ስታነበንብ ትታያለህ፡ ግን መምሕር ተከሥተ አንዲት ጉባዔ ቃና ቀርቶ ሳታውቅ አወቅሁ የምትለውን መጽሐፍ ቅዱስ አንዷን መሥመር በግዕዝ ቢያቀርብልህ መተርጎም ትችላለህ? ለነገሩ ደፋር ስለሆንህ እችላለሁ ለማለት ወደኋላ አትል ይሆናል፡ ነገር ግን አንድ ቀን አደባብ ላይ ይህ እንደሚገጥምህ እንዳትረሳው፡፡ እርሱ ቢተውህ እንኳ እኛም ዝም አንልህም፡፡
  አሁን እኔ የምመክርህ አማኝ ሁንእጅ ከሳሽ አትሁን ምክንያቱም መምሕር ተከሥተን ለመንቀፍም ሆነ ለመመዘን መሥፈርቱ የለህም፡ በእውቀት ካልህ እርሱ ብቁ ሰው ነው፡ አንተ ግን ይቀርሃል ተማር የትናንትናውን ሕይወትህንም አስብ ትናትና የማኅበረ ቅዱሳን አምባሳደር ሁነህ ሰው ስታሳደድ እንደነበረ እራስህም ታውቀዋለህ፡ አሁንም ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ስም ተጠግተህ ለቤተክርስቲያን ልጆች ካንሰር አትሁን፡፡
  ይቀጥላል

  አመሰግናለሁ ከቤተ ክርስቲያን ልጆች አንዱ ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. I know andualem and he always stands up for the truth. Ethiopia orthodox des yebelish andualem yanchi selehone. At least he has common sense and upper edication unlike some goat watchers.

   Delete
 6. እውነት ይነግር ውሸት ይቁም

  ReplyDelete
 7. ለዲያቆን አንዷለም የጻፉት: "ከሳሽ አትሁን" ሲሉ መክረዋል። መቃወም መክሰስ ከሆነና ይህም ሌላ ስም የሚያሰጥ ከሆነ እርሰዎ ምን እያደረጉ ነው? እየከሰሱት አይመስለዎትም። መዳን አለመዳንስ እርሰዎ የሚያደንቁትን ሰው ከመከተል ጋር ምን አገናኛቸው? መዳን አምላክን በመቀበል እንጂ እርሰዎ የሚሉትን መምህር በመቀበል ነው እንዴ? እንዴት ነው ነገሩ ማስተዋል ቢጨመርበት አይሻልም?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ወንድሜ እኔ የማነኛቸውም ደጋፊ አይደለሁም፡ተከታይና አድናቂም አይደለሁም፡፡ ማደንቀውም ምከተለውም አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ግን የቤተክርስቲያን ልጅ እንደ መሆኔ የቤተክርስቲያንን ልጆች በደንብ ስለማውቅ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማለት ማነኛውም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ የቤተክርስቲያን ልጅ ነው፡፡ ግን በቤተ ክርስቲያን አነጋገርና በአባቶች አጠራር፥ የቤተክርስቲያን ልጆች የሚባሉት ከልጅነቱ ጀምሮ እናት አባቱንና የተወለደበትን ሀገር በመተው አባቶች ወይም መምሕራኖች ከሚያስተምሩበት ቦታ በመሄድ የሚገባውን ተምሮና ብቁ መሆኑ ተመዝኖ የተመለሰ ማለት ነው፡፡ እንደነ አንዱዓለም ዓይነቱ ግን በአቋራጭ መንገድ ቅርንጫፍ ቅርንጫፉን እየቀነጠሰ የመጣ እንጅ ብቁ መረጃ ያለው ዓይደለም፡ ቅድስት ሥላሴና ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጥሬ እህል ተነክሮ ስለወጣ በቂ መመዘኛ አለው ሊባልም አይችልም፡፡ እንድ ጥያቄ ልጠይቅህ. (ምሉዕ በኲሉ ወይም ምሉዕ በኲለሄ) የሚለውን ትርጉም ታውቀዋለህ? የዚህን ትርጉም ካወቅኸው መቸም ዓይንህን ጨፍነህ አትከራከርም፡፡ ስለዚህ አንዱዓለም ማለት ምሉዕ በኲሉ ዓይደለም፡ እርሱም ምሉዕ በኲሉ ነኝ እንደማይልም እርግጠኛ ነኝ፡፡የሚልም ከሆነ ደግሞ ሥራው ያውጣው፡፡
   ወንድሜ ከሳሽ ባይሆንማ የእምነት ችግር አለበት ካለ በኋላ ይግባና መልስ ይስጥ ሲባል እርሱ ተከሥተ መግባት የለበትም በማለት ሲከራከር ውሏል፡፡ እንዲያውም አቡነ መልከጼዴቅና አንድ አባት የእምነት ችግር ሰምተንበት አናውቅም ሲሉት የምላችሁን ካልተቀበላችሁ የዳላስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ከእናንተ ውጭ አደርጋለሁ በማለት የእምነት ችግር የለበትም ብለው የተናገሩትን አባቶች ሃሳባቸውን ለማስለወጥ ቃለ መፈክሩን አሰምቷል፡፡
   ወንድሜ እውነቱን ተናግሮ እውነቱን ይዞ መሞት ወይስ ውሸት እየተናገሩ ውሸትን ዪዞ መሞት?

   እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን

   Delete
  2. አይ ወንድሜ እኔ የማነኛቸውም ደጋፊ አይደለሁም፡ተከታይና አድናቂም አይደለሁም፡፡ ማደንቀውም ምከተለውም አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ግን የቤተክርስቲያን ልጅ እንደ መሆኔ የቤተክርስቲያንን ልጆች በደንብ ስለማውቅ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማለት ማነኛውም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ የቤተክርስቲያን ልጅ ነው፡፡ ግን በቤተ ክርስቲያን አነጋገርና በአባቶች አጠራር፥ የቤተክርስቲያን ልጆች የሚባሉት ከልጅነቱ ጀምሮ እናት አባቱንና የተወለደበትን ሀገር በመተው አባቶች ወይም መምሕራኖች ከሚያስተምሩበት ቦታ በመሄድ የሚገባውን ተምሮና ብቁ መሆኑ ተመዝኖ የተመለሰ ማለት ነው፡፡ እንደነ አንዱዓለም ዓይነቱ ግን በአቋራጭ መንገድ ቅርንጫፍ ቅርንጫፉን እየቀነጠሰ የመጣ እንጅ ብቁ መረጃ ያለው ዓይደለም፡ ቅድስት ሥላሴና ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጥሬ እህል ተነክሮ ስለወጣ በቂ መመዘኛ አለው ሊባልም አይችልም፡፡ እንድ ጥያቄ ልጠይቅህ. (ምሉዕ በኲሉ ወይም ምሉዕ በኲለሄ) የሚለውን ትርጉም ታውቀዋለህ? የዚህን ትርጉም ካወቅኸው መቸም ዓይንህን ጨፍነህ አትከራከርም፡፡ ስለዚህ አንዱዓለም ማለት ምሉዕ በኲሉ ዓይደለም፡ እርሱም ምሉዕ በኲሉ ነኝ እንደማይልም እርግጠኛ ነኝ፡፡የሚልም ከሆነ ደግሞ ሥራው ያውጣው፡፡
   ወንድሜ ከሳሽ ባይሆንማ የእምነት ችግር አለበት ካለ በኋላ ይግባና መልስ ይስጥ ሲባል እርሱ ተከሥተ መግባት የለበትም በማለት ሲከራከር ውሏል፡፡ እንዲያውም አቡነ መልከጼዴቅና አንድ አባት የእምነት ችግር ሰምተንበት አናውቅም ሲሉት የምላችሁን ካልተቀበላችሁ የዳላስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ከእናንተ ውጭ አደርጋለሁ በማለት የእምነት ችግር የለበትም ብለው የተናገሩትን አባቶች ሃሳባቸውን ለማስለወጥ ቃለ መፈክሩን አሰምቷል፡፡
   ወንድሜ እውነቱን ተናግሮ እውነቱን ይዞ መሞት ወይስ ውሸት እየተናገሩ ውሸትን ዪዞ መሞት?

   እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን

   Delete
  3. አይ ወንድሜ እኔ የማነኛቸውም ደጋፊ አይደለሁም፡ተከታይና አድናቂም አይደለሁም፡፡ ማደንቀውም ምከተለውም አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ግን የቤተክርስቲያን ልጅ እንደ መሆኔ የቤተክርስቲያንን ልጆች በደንብ ስለማውቅ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማለት ማነኛውም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ የቤተክርስቲያን ልጅ ነው፡፡ ግን በቤተ ክርስቲያን አነጋገርና በአባቶች አጠራር፥ የቤተክርስቲያን ልጆች የሚባሉት ከልጅነቱ ጀምሮ እናት አባቱንና የተወለደበትን ሀገር በመተው አባቶች ወይም መምሕራኖች ከሚያስተምሩበት ቦታ በመሄድ የሚገባውን ተምሮና ብቁ መሆኑ ተመዝኖ የተመለሰ ማለት ነው፡፡ እንደነ አንዱዓለም ዓይነቱ ግን በአቋራጭ መንገድ ቅርንጫፍ ቅርንጫፉን እየቀነጠሰ የመጣ እንጅ ብቁ መረጃ ያለው ዓይደለም፡ ቅድስት ሥላሴና ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጥሬ እህል ተነክሮ ስለወጣ በቂ መመዘኛ አለው ሊባልም አይችልም፡፡ እንድ ጥያቄ ልጠይቅህ. (ምሉዕ በኲሉ ወይም ምሉዕ በኲለሄ) የሚለውን ትርጉም ታውቀዋለህ? የዚህን ትርጉም ካወቅኸው መቸም ዓይንህን ጨፍነህ አትከራከርም፡፡ ስለዚህ አንዱዓለም ማለት ምሉዕ በኲሉ ዓይደለም፡ እርሱም ምሉዕ በኲሉ ነኝ እንደማይልም እርግጠኛ ነኝ፡፡የሚልም ከሆነ ደግሞ ሥራው ያውጣው፡፡
   ወንድሜ ከሳሽ ባይሆንማ የእምነት ችግር አለበት ካለ በኋላ ይግባና መልስ ይስጥ ሲባል እርሱ ተከሥተ መግባት የለበትም በማለት ሲከራከር ውሏል፡፡ እንዲያውም አቡነ መልከጼዴቅና አንድ አባት የእምነት ችግር ሰምተንበት አናውቅም ሲሉት የምላችሁን ካልተቀበላችሁ የዳላስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ከእናንተ ውጭ አደርጋለሁ በማለት የእምነት ችግር የለበትም ብለው የተናገሩትን አባቶች ሃሳባቸውን ለማስለወጥ ቃለ መፈክሩን አሰምቷል፡፡
   ወንድሜ እውነቱን ተናግሮ እውነቱን ይዞ መሞት ወይስ ውሸት እየተናገሩ ውሸትን ዪዞ መሞት?

   እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን

   Delete
 8. እስካሁን ብዙውን አምናቹህ ነበር አሁን ሰው ያለኝ የሚለኝ ሁሉ እውነት ነው ወብሳይቱ የአባ ገብረ ስላሴ እና የመሰሎቹ ነው አባ ገብረ ስላሴ ጥበቡ ለማበድ ትንሽ የቀረው ይመስላል የሚሰራውና የሚናገረው አይገናኝም 37ኛው ሳይሆን 38ኛው የሲኖዶሱ ጉባዔ

  ReplyDelete
 9. ደደብ አህያ ነህ ተናግረህ ሞተሀል

  ReplyDelete
 10. አይ አባ ሰላማ መምህር ብታጡ መምህረ ተከስተ አላችሁ …ናሽቪል እያለም አንድ ቀን ተማርን ሳንል ጌታ ነቀለልን የሚገርመው ቀሲስ ታደስ መናፍቅ ሰለሆነ መናፍቅ እንዲያስተምር ጋበዘው የናሽቪል ህዝብ መቼም ንቃተ ሂሊና የላችሁም ንቁ ከመናፍቅ ጎራ ውጡ ቀሲስ ታደስ ተከስተ መናፍቅ እንደሆነ እያውቀ ህዝቡን ወደ መናፍቅ ለመውስደ እሱን አመጣ ቀሲሱም ቢሆን ክህነቴን አለፈልግም ጸበል አያድንም ብሎ ሲናገር የነበረ ቄስ ነው ሰው እንዴት አይኑ አይከፈትለትም የናሽቪል ህዝብ ሆይ ንቃ!!!!

  ReplyDelete
 11. Judas sold jesus, aba gebreslassie sold the church.

  ReplyDelete