Thursday, December 26, 2013

የዳንኤል ክብረትን ጥፋት ማን ያርመው?

ከመምህር አዲስ
መንደርደሪያ
በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ሚዲያውን ያፍናል እየተባለ ከተቃዋሚዎችና ከግል ጋዜጠኞች በኩል ሮሮ ይሰማበታል፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ነጻ የሚባሉት ሚዲያዎች ብዙዎቹ ራሳቸው ከወገንተኛነት ያልጸዳ አሠራርን የሚከተሉና ነጻ አስተሳሰብን የሚያፍኑ ሆነው መገኘታቸው ነው፡፡ በተለይ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚወጡ ዘገባዎች ነጻ በተባሉ ሚዲያዎች ዘንድ የሚዘገቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ፍላጎትና ጥቅም አንጻር ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ተችቶ ወይም ከማኅበረ ቅዱሳን በተጻራሪ ቆሞ ነጻ ሐሳብን ማራመድ እጅግ ከባድ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁንም ያ ሁኔታ አልተለወጠም፡፡ ታዲያ ራሳቸው ነጻ አስተሳሰብን እያፈኑና የአንድ ወገን ዘገባን ብቻ ሚዛናዊ ባልሆነ መልኩ ማቅረብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ሚዲያ የሚባለውን አካል ጥያቄ ውስጥ አይከተውም ትላላችሁ፡፡ ይህን ለማለት ያበቃኝ ከሳምንታት በፊት “አዲስ ጉዳይ” በተሰኘ መጽሔት ላይ ዳንኤል ክብረት በሁለት ክፍል ለጻፈው ጽሑፍ ምላሽ አዘጋጅቼ ለመጽሔት ክፍሉ ብልክ የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረቱ ነው፡፡

Saturday, December 21, 2013

የማቅን ሤራ ቀድመው የተገነዘቡ የአዲስ አበባ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ቤተ ክርስቲያንን ስለመታደግ ፓትርያርኩን አነጋገሩ

·        አለቆቹ “እስካሁን ብፁዓን አባቶች ብሎ ማክበር አገሪቷ ያቆየችው ታሪክ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን ይበላሻል፡፡” ሲሉ አስጠንቅቀዋል
·        ማቅ የሰራው የመዋቅር ለውጥ ሕግ ላይ የተጀመረው ውይይት እንዲቆም ቋሚ ሲኖዶስን ጠይቀዋል
·        በመንግስት ጉዳያቸው እንዲታይላቸውና ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ መንግስትን እየጠየቁ መሆኑ ተመልክቷል  
·        ማቅ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ በተቃውሞ እንዲነሱባቸው እየቀሰቀሰ መሆኑ ታውቋል
·        የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለሕይወታቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ለፓትርያርኩ ጥያቄ አቀረቡ
·        አለቆቹና አገልጋዮቹ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልጋትና እነርሱም ለውጡ የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል
·        የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅራዊ ለውጥ መሰራት ያለበት ስውር አላማ ባለውና የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግስቱን ስልጣን በኃይል ለመቆጣጠር በመታገል ላይ ያለው ማቅ የሚባለው አሸባሪ ቡድን መሆን አይገባውም
·        ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው የራሷ ልጆች የሆኑ ምሁራን ስላሉ በእነርሱ አጠቃላይ መዋቅራዊ ማሻሻያው ሊሠራ ይገባል
·        ማቅ ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ የሚጨነቅ ከሆነ ለውጡን ከራሱ እንዲጀምርና የሰራውን ሕንጻና ንብረቱን እንዲያስመዘግብ፣ ገቢውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ሞዴላሞዴሎች እንዲያደርግ ኦዲትም እንዲደረግ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል

Friday, December 20, 2013

አባ እስጢፋ እና ማቅ “በሽርክና” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ለመቆጣጠር ያረቀቁት ደንብ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡

በሙስና ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ ተዘፍቀው የሚገኙት ባለትዳሩና ባለዕቁባቱ “ጳጳስ” አባ እስጢፋ ከጥቅም ወዳጃቸው ከማቅ ጋር በፈጠሩት የእከክልኝ ልከክልህ ሽርካና ተቋማዊ ለውጥ አመጣለሁ በሚል በማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች የተረቀቀውንና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኙ አድባራትና ገዳማት ተግባራዊ ይሆናል ብለው የቋመጡለትን “ጥናታዊ” ያሉትን የለውጥ መዋቅር ለውይይት ባቀረቡ ቁጥር ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለማጥፋት ተብሎ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከአራት አህጉረ ስብከት ወደ አንድ ሀገረ ስብከት መጠቃለሉና በአንድ ሊቀጳጳስ እንዲመራ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይህ ሀገረስብከት ከምንጊዜውም በበለጠ በሙስና ጨቅይቶአል፡፡ ከሊቀጳጳሱ ከአቡነ እስጢፋ ጀምሮ እስከ ልዩ ልዩ የመምሪያ ኃላፊዎች የሙስናን ደረጃ በእጅጉ አሻቅበውታል፡፡ ለምሳሌ ያህል ብናነሳ እንኳን አቡነ እስጢፋ የጅማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን አሠራለሁ በሚል ሰበብ ከእያንዳንዱ ደብር ከብር አንድ መቶ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ያለምንም ሕጋዊ ደረሰኝ በእጃቸው እየተቀበሉ ነው፡፡ ገንዘብ ያልሰጡአቸው አድባራት ቢኖሩ እንኳን “ሻይ ሳያጠጡኝ” እያሉ በግልጽ በማስጠንቀቅ ይቀበሉአቸዋል፡፡ እኚህ ሙሰኛ ጳጳስ ስለሙስና የመናገር ድፍረት በማጣታቸው ሙሰኞችን በድፍረት የመናገር ብቃት ካለማግኘታቸውም በላይ ቤተክርስቲያንን ወደ ሌላ ታሪካዊ ቀውስ እየመሯት ነው ያሉት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የለውጥ መዋቅሩን ሠርቻለሁ የሚለው ማቅ በአባ እስጢፋም ሆነ በሌሎች ሙሰኞች ላይ ቃል ትንፍሽ አላለም፡፡ በተለይ ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው ብዙዎች ያለቀሱበት የአቶ ዮናስን ዓይን ያወጣና በተጨባጭ በሲዲ ጭምር የተደገፈ ሙስናዊ ማስረጃ ቀርቦላቸው ሳለ አባ እስጢፋም ሆኑ ሸሪካቸው ማቅ እስካሁን ምንም አለማለታቸውና ዮናስ ከቦታው ሳይነሳ ዝርፊያውን አጠናክሮ መቀጠሉ፣ ጉዳዩን የቤተክርስቲያንን አስተዳደር የማስተካከል ሳይሆን የሙስናውን መንገድ ይበልጥ ውስብስብ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ አስመስሎታል፡፡ 

Wednesday, December 18, 2013

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደረጃውን ባልጠበየቀ የአስተዳዳሪዎች ዝውውርና ሐሳብ እየታመሰ ነው

F አዲሱን የማኅበረ ቅዱሳን  መዋቅር ይቃወማሉ የሚባሉ አንጋፋዎቹ የአዲስ አበባ አስተዳዳሪዎችን ጡረታ ለማውጣት እንቅስቃሴው ቀጥሏል፡፡
Fአዲሱ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሐሳቡ አልተስማሙም ፡፡
F የአቡነ እስጢፋኖስ አስተዳደር አይገዛንም የሚሉ የምእመናን ቡድኖች እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
F የደብር አስተዳዳሪዎች እስጢፋኖስ ዲያቆን ነው ድሮም ዲያቆን ቤተክርስቲያንንን ይራዳል እንጂ አይመራም በማለት ቅኔ እያስቀኙባቸው ነው፡፡
F እነ ዳዊት ያሬድ በጅማ አብያተ ክርስቲያናት ስም ገንዘብ በማሰባሰቡ ሥራ ተጠምደዋል
የአቡነ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚካሄደው ሹም ሽር እንደቀጠለ ሲሆነ ዋናው  የቤተክርስቲያኗ የአስተዳደር ማእከል አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም ባልተረጋጋ ሁኔታ ሲኖዶስ በተሰበሰበ ቁጥር እንደ ዝክር ዳቦ አንዴ ከ አራት አንድ ከሰባት እየተሸነሸነ በመካከል ባለው አለመረጋጋት የአስተዳደር ክፍተትን በመጠቀም የቤተክርስቲያኒቱ ሐብት እየባከነ ይገኛል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ተረኛ ዘካሪ አቡነ እስጢፋኖስ ከሁለት ቤት ደግሰው አንዴ ጅማ አንዴ አዲስ አበባ እያሉ ሲያሻቸውም አዲስ አበባ ላይ ለደጆችሽ አይዘጉ. ለጅማ እጓለ ማውታ፣ ለአበልቲ አብያተክርስቲያናት  በሚል ከአንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎችና ሀብታሞች ገንዘብ ማሰባሰባቸውን ቀጥለዋል፡፡

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስም ሽፋን ሕገ ወጥ አካሄድ

ምንጭ፦ www.ethiofreedom.com
ጸሐፊ፦ ታዬ ብርሀኑ (taye_berhanu@ymail.com)

በ 38ኛው የስደተኛው ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የተካሄዱ ውይይቶችንና ከስብሰባውም በሁዋላ የተከናወኑ አንዳንድ ክስተቶችን የሚተች  ሐተታ።

ሙሉውን ሐተታ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Monday, December 16, 2013

በስደተኛው ሲኖዶስ ሥር የሚገኙ ሰባክያነ ወንጌልን የማጥቃት እንቅሥቃሴው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

   ጥቃቱ ያነጣጠረው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ጨምሮ ሌሎችን አገልጋዮችንም ይጨምራል። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት 13 ሰዎች ለውግዘት ታጭተው ነበር። እነርሱም ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል፣ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ አባ ገብረ ስላሴ ጥበቡ፣ ቀሲስ መላኩ ባወቀ፣ አባ ላእከ ማርያም፣ አባ ገ/ ማርያም፣ አባ ገ/ሚካኤል፣ ቀሲስ ጌታቸው፣ ቀሲስ እንዳልሃቸው ሲሆኑ አሥራ ሦስተኛው ማን እንደሆነ አልታወቀም፤ ይህ ስም ዝርዝር ዲሲ አካባቢ በሚገኙ የአቡነ መልከ ጼዴቅ ደጋፊ ነን የሚሉ ፣ ነገር ግን ከነዶክተር ካሱ ይላላ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ያቀረቡት እንደነበረ ምንጮቻችን ገልጸዋል። አንድ የደረሰን መረጃ  የዚህ ሐሳብ ዋና ተዋናይ ዶ. ነጋ መሆኑን ይጠቁማል። ይህ ጥቆማ የደረሰን የዛሬ ሁለት ዓመት ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እስክናሰባስብ አቆይተነዋል። አሁን ግን በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ ይህንን ጥቆማ የሚደግፉ በርካታ ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ ለጥንቃቄና አሁን በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ የሚስተዋለውን ትርምስ ለመገንዘብ አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል አቅርበነዋል።
    አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ኢሕዴግ ወይም ማህበረ ቅዱሳን ወይም በራሱ ተነሳሽነት የሲኖዶሶች የእርቅ ኮሚቴ የሆነው የነ ሊቀ ካህናት ኀ. ሥላሴ እጅ አለበት ሲሉ  አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ስደተኛውን ሲኖዶስ ወክለው የእርቅ ኮሚቴ አባል የነበሩትና በማሀረ ቅዱሳንነት የሚጠረጠሩት የዲ.አንዷለምና የአባ ጽጌ ደገፋው እጅም ሊኖርበት እንደሚችል ጠቁመዋል። እንደሚታወቀው በእርቅ ኮሚቴነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፦ የአገር ቤቱን ሲኖዶስ የወከሉት ሊቀ ካህናት ኀ. ሥላሴና ቀሲስ አንዷለም ዘኦሪገን (ሁለቱም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው) ሲሆኑ በስደተኛው ሲኖዶስ የተወከሉት አባ ጽጌ ደገፋው፣ ዲ.አንዷለም ዳግማዊ እና መምህር ልኡለ ቃል አካሉ ነበሩ። ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ  በ ዶ/ አማረ ተወክለው ተሳትፈዋል።

Thursday, December 12, 2013

ምድሪቱን በምስጋና ጐርፍ ያጥለቀለቁት የዘማሪት ዘርፌ ዝማሬዎች

ያለም ቤዛ ኢየሱስ ነው
የፈወሰኝ ጌታ ነው
መዳን በሌላ የለም
እኔ አምናለሁ ዘላለም

በኦሪቱ ሥርዓት ፍጥረት ስላልዳነ
ለሚሻለው ኪዳን ኢየሱስ ዋስ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ተቤዠኝ በደሙ
ያዳነኝ እርሱ ነው ይስማልኝ ዓለሙ

አንዴ ለዘላለም ደሙ ፈሶልኛል
አሁን ያለ ኀጢአት ወዴ ይታይልኛል
ነፍሴን እንዲያነጻ ታርዷል ፋሲካዬ
መርሕ ሆኖ ወደ ክብር አስገባኝ ቤዛዬ

የዘላለም ርስትን የተናዘዘልኝኝ
መቃብርን ቀብሮ በሰማይ ያለልኝ
ሞቶ በመስቀሉ ሰላም ያደረገው
እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው

እንድንበት ዘንድ ተሰጥቶናል ስሙ
አማራጭ የሌለው መዳኛ ነው ደሙ
ሞትን መሞት እንጂ መግደል የተቻለው
ከኢየሱስ በቀር ሌላ ጌታ ማነው?

የመቅደስ አዛዦች እጅ ቢጫንብኝ
ከክርስቶስ ፍቅር መቼም አይበልጥብኝ
በልቤ ያመንሁትን ልመስክረው በአፌ
አልችልም ዝምታ በሞቱ ተርፌ
ይህ ከሰሞኑ ከተለቀቀው የዘማሪት ዘርፌ ከበደ ድንቅ ዝማሬዎች አንዱ ነው፡፡ ዝማሬዎቹን በጥቂቱ ከመቃኘታችን በፊት ግን ወደኋላ መለስ ብለን የዝማሬያችንን መነሻ፣ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶችና ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ እጅግ ባጭሩ ለመቃኘት እንሞክር፡፡

Wednesday, December 4, 2013

በቅርቡ ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል የበላው ጅብ ምነው አልጮህ አለ?በቅርቡ ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ጉዳይ ተከትሎ ከፍተኛ ውዝግብ ተነሥቶ የነበረ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ መስቀሉን አስመልክቶም ለሕዝብ በይፋ ይታያል ከሚለው የወሬው ፈጣሪዎች እቅድ አንስቶ ጉዳዩ መጣራትና ሐሰት ሆኖ ከተገኘም እንዲህ ያደረጉት አካላት ተጠያቂ ይሆናሉ እስከሚለው የአባ እስጢፋኖስ ቃለመጠይቅ ድረስ ብዙ ተብሎ ነበር፡፡ እስካሁን ግን ቀኑን ከማራዘምና ጉዳዩን ከማረሳሳት በቀር መስቀሉ ለእይታ አልቀረበም፤ የዚህ ግርግር ፈጣሪዎች ጉዳይም በሲኖዶስ ታይቶ ተገቢው ምላሽ አልተሰጠም፡፡ ቋሚ ሲኖዶስም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ ላይ እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ለዚህ ነው ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል የበላው ጅብ ምነው አልጮህ አለ? ስንል መጠየቅ የፈለግነው፡፡

ለመሆኑ የዚህ ሐሰተኛ ተአምር ደራሲ የሆነው ሰው ማነው? ዓላማውስ ምንድነው? ከዚህ ቀደምስ የሠራቸው ሐሰተኛ ተመሳሳይ “ተአምሮች” ምን ይመስላሉ? ቤተክርስቲያን እንዲህ ያሉትን ሐሰተኞች አቅፋ የምትጓዘው እስከመቼ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት እንወዳለን፡፡