Wednesday, December 4, 2013

በቅርቡ ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል የበላው ጅብ ምነው አልጮህ አለ?በቅርቡ ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ጉዳይ ተከትሎ ከፍተኛ ውዝግብ ተነሥቶ የነበረ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ መስቀሉን አስመልክቶም ለሕዝብ በይፋ ይታያል ከሚለው የወሬው ፈጣሪዎች እቅድ አንስቶ ጉዳዩ መጣራትና ሐሰት ሆኖ ከተገኘም እንዲህ ያደረጉት አካላት ተጠያቂ ይሆናሉ እስከሚለው የአባ እስጢፋኖስ ቃለመጠይቅ ድረስ ብዙ ተብሎ ነበር፡፡ እስካሁን ግን ቀኑን ከማራዘምና ጉዳዩን ከማረሳሳት በቀር መስቀሉ ለእይታ አልቀረበም፤ የዚህ ግርግር ፈጣሪዎች ጉዳይም በሲኖዶስ ታይቶ ተገቢው ምላሽ አልተሰጠም፡፡ ቋሚ ሲኖዶስም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ ላይ እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ለዚህ ነው ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል የበላው ጅብ ምነው አልጮህ አለ? ስንል መጠየቅ የፈለግነው፡፡

ለመሆኑ የዚህ ሐሰተኛ ተአምር ደራሲ የሆነው ሰው ማነው? ዓላማውስ ምንድነው? ከዚህ ቀደምስ የሠራቸው ሐሰተኛ ተመሳሳይ “ተአምሮች” ምን ይመስላሉ? ቤተክርስቲያን እንዲህ ያሉትን ሐሰተኞች አቅፋ የምትጓዘው እስከመቼ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት እንወዳለን፡፡


ምንም እንኳን በየጋዜጣው ላይ “ተአምሩን በዓይኔ አይቻለሁ” ሲሉ በየጋዜጣው ላይ ቃለ ምልልስ ሲሰጡ የነበሩት ሰው መጋቤ ሐዲስ ፍስሐ ናቸው ቢባልም፣ እርሳቸው መድረክ ላይ የተወኑት እንጂ ደራሲው አባ ሕፃነ ማርያም የተባለ መነኩሴ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁት ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ይህ ሰው እንደዚህ ያለ ሐሰተኛ ተአምር ደርሶ ሕዝብን ሲያሳስት ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደምም በሌሎች ነገሮች ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙን አባ ሕፃንን የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ አላማውም ያልታወቁ ደብሮችን እንዲታወቁና ገቢያቸው እንዲጨምር ማድረግ ነው፡፡ ቤተ ክህነቱም በዚህ ረገድ የሚገኘውን ጥቅም በመመልከት ይመስላል ልዩ ልዩ የሐሰት ትምህርቶች ሲስፋፉና ሐሰተኛ ራእዮች ሕዝብ እንዲሳሳትባቸው ሲደረግ ዝምታን መርጧል፡፡ ይህ የሚሆነው ግን እስከ መቼ ነው? እንዲህ እየተደረገባት ያለች ቤተክርስቲያን ታዲያ ተሐድሶ ማድረግ የለባትም ይባላል?

አባ ሕፃነ ማርያም ማነው?
አባ ሕፃነ ማርያም “አገልግሎቱን” የጀመረው በድሬደዋ ሲሆን በድሬደዋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርቲያን በፀበል አጥማቂነት ተቀጥሮ ይኖር ነበር፡፡ በነበረበት ቦታ ግን ጥሩ ስም አልነበረውም፡፡ ስሙን ያበላሸው ደግሞ ከተለያዩ ሴቶች ወልዷል፣ የቤተክርስቲያን ገንዘብ ይዘርፋል፣ ፀበል ሲያጠምቅ ሰው የሚለፈልፈው በሰውየው ፀሎት ሳይሆን ከተለያዩ ደጋሚዎች በሰበሰበው የጥንቆላ መንፈስ ሕዝቡን የሚያስጮህ በመሆኑ ነበር፡፡ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በሰውየው የሕይወት ታሪክ ላይ ጥናት ሲያደርግ የሚመጡበት ክሶች እውን መሆናቸውን አረጋግጦ እርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲጀምር፣ የሠራው ጥፋት አደገኛ ስለነበርና ወደ ወህኒ ከገባ የመውጣት እድል እንደሌለው ነገሩን የወንጀሉ ባለቤት የሆነው አባ ሕፅነ ማርያም ሲረዳ በአስቸኳይ አገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል፡፡

ድሬደዋን እንደለቀቀ ቀጥታ የመጣው ወደ አዲስ አበባ በካራ አሎ በሚገኘው ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል ካህናተ ሰማይ ቤተክርስቲያን ሲሆን፣ በጊዜው አባ ህፃን ምንም የቤተክህነት ትምህርት ባይኖረውም አለመማሩ በሰጠው ድፍረትና ሳይመነኩስ መንኩሻለሁ በማለት የውሸት ቆብ ከመርካቶ በመግዛት በፀበል አጥማቂነት ተቀጠረ፡፡ በቦታው ፀበል የሚጠመቅ ሰው ሲጠፋ በቅርቡ መስቀል ከሰማይ ወረደ እንዳሰኘ ሁሉ፣ ወደ ደብሩ ሰዎችን ለመሳብ ካሉት ካህናት ጋር በመተባበር (በመመካከር) የሐሰት ትምህርት ማመንጨትና ማሰራጨት ጀመረ፡፡

ይህ ትውልድ እንደ አይሁድ ምልክት ፈላጊ እንደሆነ ይታወቃልና የሕዝቡን ደካማ ጎን በመፈለግ አንድ የበሰበሰ እንጨት ሌሊት ቆፍሮ ከቀበረ በኋላ፣ “ሰማያዊቱ ማርያም በዚህ ቦታ ስለወረደች ቦታውን ቆፍረህ አስወጣ ብላኛለች” በማለት ይህን ምስኪን ሕዝብ ያለምንም ይሉኝታ ካስቆፈረ በኋላ የቀበረውን እንጨት አውጥቶ ሰማያዊቱ ማርያም ቀባችኝ በማለት የአዲስ አበባ ሕዝብ ካለበት አጥቢያ “ሰማያዊቱ ማርያም በካራ ወረደች” እያለ ቤቱንና ሥራውን እየተወ ቦታውን ማጨናነቅ ጀመረ፡፡ ለሕዝቡ ማሳመኛ እንዲሆን በአካባቢው የማይታወቁና አይናቸው ያልታወረ ሰዎችን ከሩቅ አገር የመጡ በማስመሰል አይናቸውን አሸፍኖ “አሁን የአዲስ አበባ ሕዝብ ተመልከት አይን ሲበራ እይ” እያለ በሕዝቡ ሲቀልድና ሲያሾፍበት ይታወቃል፡፡ በአካባቢው የሚታወቁ እውራን ሲሄዱ ግን አይፈወሱም፡፡ ይህም ለአንዳንድ ሰዎች ጥያቄ ሆኖ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሕዝብ እንደዚህ ላሉ የሐሰት ትምህርቶችና ሐሰተኛ መገለጦች መጋለጡ አይቀርም፡፡

በዚህም የአንድ ሰሞን ግርግርም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ስር ተመዝግቦ ነበር፡፡ ፍቃድ ሲጠይቁ ግን “ሰማያዊት ማርያም የምትባል የለችም፤ እኛ የምናውቀው የአብርሃምና የዳዊት ዘር የሆነች ማርያምን ነው” በማለት ተወዛግበው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የኛ ቤተክርስቲያን የምትመራው በሲኖዶሱ ሳይሆን በሕዝቡ ስለሆነ ሕዝቡን ስለፈሩ ስሕተቱን ቢያውቁትም የማታ ማታ “ሰማያዊቱ ማርያም” በሚለው ስም ፈቃድ ሰጥተውታል፡፡ ከዚያም ምንም ገቢ ያልነበረው ያ ቤተክርስቲያን በጥቂት ጊዜ ውስጥ በአመት ያስገባ የነበረውን ገንዘብ በአንድ ቀን ወደማስገባት ተሸጋገረ፡፡ ለመሆኑ ሰማያዊቱ ማርያም የምትባል አለች ወይ? በፍጹም!!! ይህ የጎጋው አባ ሕፃን ስያሜ ነው፡፡ ማርያምን “አርያማዊት ኃይል ናት” የሚለው ትምህርት በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የተወገዘ ነው፡፡ ታዲያ አባ ሕፃን ኑፋቄውን ባለማወቅና ለገቢ ማስገቢያ ሲል ሲጠቀምበት ግን እንደኑፋቄ አለመቆጠሩ ያስገርማል? በዚህ ስያሜ ፈቃድ ለመስጠት እንዴት ተቻለ? ሰማያዊት የምትባል ማርያም በየትኛው መጽሐፍ ውስጥ ነው ያለችው? ከሌለች እንዳለች ተቆጥሮ ፈቃዱ የተሰጠው ለምን ይሆን? ብዙዎች እንደሚጠረጥሩት ከዚህ የአባ ሕፃን ድርሰት በኋላ የደብሩ ገቢ ስለጨመረ ከሚያገባው ገቢ ዳጎስ ያለ ጉቦ በመስጠት መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ያለጉቦ ኦርቶዶክስ ውስጥ መንቀሳቀስ ከማይቻልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል፡፡ አለቆቿ በጉቦ የሚፈርዱባት ቤተክርስቲያን “ሰማያዊቱ ማርያም” በሚል ስም ፈቃድ ብትሰጥ ብዙም አያስደንቅም፡፡

ዘራፊዎች ገንዘብን ሲሰርቁት እንጂ ሲከፋፈሉት ብዙ ጊዜ እንደማይስማሙ የታወቀ ነው፡፡ በመሆኑም አባ ሕፃንና ካህናቱ በገንዘቡ አከፋፍል ላይ ትልቅ ጦርነት አንስተው ነበር፡፡ አባ ሕፃነ ማርያም ይህ ሁሉ ገንዘብ የመጣው በእኔ ምክንያት ስለሆነ በአብዛኛው የሚገባው ለኔ ነው በማለት ከነበሩት አስተዳደር ጋር ግጭት ፈጠረ፡፡ አስተዳደሩና ካህናቱም የቦታውን የገንዘብ ለውጥ ስለፈለጉ ብቻ ለጊዜው ዝም አሉት፡፡ ይሁን እንጂ አጠምቃለሁ እያለ በአንዳንድ እህቶች ላይ የሚሠራው ሥራና የሚፈፅመው አፀያፊ ተግባር ለአእምሮ የሚዘገንን ነበር፡፡ ብዙ ሴቶች በየጊዜው አቤቱታቸውን ለደብሩ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቱ ቢያቀርቡም ከሚገባው ብር የተነሣ ሰውየውን ማባረር አልቻሉም ነበር፡፡ ከነርሱ ጋር ግጭት ውስጥ ሲገባ ግን የያዟቸውን መረጃዎች በማጠናከር አካባቢውን እንዲለቅ ጥብቅ የፖሊስ ክትትል ሲደረግበት እንደለመደው ለተወሰነ ጊዜ ጠፋ፡፡

ከ3 ዓመት በኋላ አካባቢውን ቀይሮ አሁን እያሳሳተ ወዳለበት ስፍራ በመምጣት የተለመደ ውሸቱን ለማስፋፋት ከከተማ ራቅ ባለ ቤተክርስቲያን ፀበል ላጥምቅ በማለት ለተወሰነ ጊዜ ቢቀመጥም በአካባቢው የሚጠመቅ ሰው ጠፋ፡፡ የደብሩን አስተዳደርና ካህናት በመሰብሰብ ልዩ የገቢ ማሰባቢያ ዘዴ እንፍጠር አላቸው፡፡ ካህናቱም ሌተቀን የሚያሳስባቸው የመንጋው ጉዳይ ሳይሆን የሆዳቸው ነገር ብቻ ስለሆነ በሐሰት ምክሩ ተስማሙ፡፡ ምክሩም አንድ መስቀል ገዝተው ወርቅ መሰል የቀለጠ ፈሳሽ አፈሰሱበት፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ሌሊት የተለየ ሮኬት ተኩሰው ድምፅ በአካባቢው ካሰሙ በኋላ ደወል ደውለው መስቀል ከሰማይ ወረደ አሉ፡፡ አንዳንድ ለወሬ የሚቸኩሉ እንደ አዲስ አድማስ ያሉ ሚዲያዎችን በመጠቀምም ወሬውን ናኙት፡፡ እውነትን ለመስማት የሚዘገየውና በሐሰት ትምህርት ለመወሰድ የሚፈጥነው ሕዝብም ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ለማየት በሚል ቦታውን አጨናነቀው፡፡ ልብ እንበል መነሻውን ድሬዳዋ ያደረገው አባ ሕፃነ ማርያም አሁን ደግሞ በዚህ አዲስ ግን ያረጀ ተረት የአዲስ አበባን ሕዝብ መዋሸትና ማምታት ጀመረ፡፡

ተረቱ ለጊዜው የተፈለገውን ሕዝብ መሳብና ገቢ ማምጣት ችሏል፡፡ ከተነሱበት ዓላማ አንጻርም (ገንዘብ ማግኘት) ያሰቡት በተወሰነ መልኩ ተሳክቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ተንጠልጥሎና ተድበስብሶ ነው የሚገኘው ለምን? በቅድሚያ መስቀሉ ለሕዝብ ይታያል የተባለው ጉዳይ የውሃ ሽታ ሆኖ ነው የቀረው፡፡ ይህን ለማድረግ ምን አስፈራቸው? ወይስ “ከተነቃ ይቀራል!” ነው ነገሩ፡፡ እነአባ ሕፃን ሕዝቡን በሐሰት ሲያሳስቱና ሲበዘብዙ ኀላፊነት ያለበት የአባ እስጢፋኖስ አስተዳደር ለምን ዝም አለ? ለምንስ ጉዳዩ ተጣርቶ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጥም? እንደነዚህ ያሉ አሳሳቾች ገንዘብ ካስገቡ ምንም ችግር የለውም ተብሎ ነው? ይህ ነገር ውሎ አድሮ ችግር አይፈጥርም ወይ? ሕዝቡ ከዚህ ቀደም አሳሳቾች የፈጠሩትን ተረት እንደ እውነት ይዞ ከወንጌል ሲርቅ ዝም ብሎ ማየት ከቤተክርስቲያን አይጠበቅም፡፡ ቤተክርስቲያን ስሕተቶችን እያረመች ካልሄደች በቀደሙት ስሕተቶች ላይ ሌሎችን መጨመር ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ሊያስብብት ይገባል እንላለን፡፡

ወሬውን ይዘው የወጡና እንድንቀበለው ሊያግባቡን የሞከሩ ሚዲያዎች በተለይም አዲስ አድማስ ጋዜጣ “ሲኖዶስ ተወያይቶ ምላሽ ይሰጥበታል ስሕተት ሆኖ ከተገኘም እንዲህ ያደረጉት ሰዎች ይጠየቃሉ” የተባለውን ጉዳይ የደረሰበትን መጠየቅና ለሕዝብ ማሳወቅ አለበት፡፡ አሊያ “ቀደሞም ባልዘፈንሽ ኋላም ባላፈርሽ” ይመጣል፡፡


22 comments:

 1. It is true!!! Orthodox Church has a responsibility to find out.

  ReplyDelete
 2. God bless you brothers.

  ReplyDelete
 3. ጉድ በል ጎንደር!

  ReplyDelete
 4. ወደ ቀልባችሁ ተመለሳችሁ እንዴ!!!!ያሁኑ ዘገባችሁ መልካም እና ገንቢ ነው!!!ጎሽ እስኪ አንዳንዴ እንኩዋ እንዲህ የሰከነ ጽኁፍ አውጡ.

  ReplyDelete
 5. የተሐድሶ መናፍቃን ነገር ; የኢት.ኦ.ተ.ቤ/ክ የተአምራት ቤት ናት፣
  ሂድ ሆሳዕና አምናና ካቻምና የተከሰተውን በዛፍ ላይ የቅዱሳን ስዕላት // ድንግል ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ ከልጇ ጋር ሌሎችም //ይህ ደግሞ ተዐምር የተከሰተው በእናንተው ዘመዶች ግቢ ነበር፣እነርሱ እኮ በሆነው ነገር አመኑ ተጠመቁ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ ሄዳችሁ ለምን አታዩም? መስቀሉም ጋ ሂዱ፤እዚሁ አዲስ አበባ ነው፣ ወይስ ይህ የጥርጥር እርኩስ መንፈስ ያዋርደናል ብላችሁ? ከሆነም ይለይለት፣የንስሐ ግዜ አያምልጣችሁ…

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዘመናችንን መታረም ሪት ልምን ይሆንብናል ሁላቸህንም እናውቃታልን 1000 አመታት ስትዋሽ ምቆየትዋን፡፡

   Delete
 6. bless bless bless to you
  you are the children of God and Jesus, the children of apostle paul

  ReplyDelete
 7. Lemejemriay gize Aba selam Mahbere Kidusann saykese were tsafe...

  lol

  ReplyDelete
 8. አንተን የበላው ጅብ ከሳምንት በኃላ ጮኸ ማለት ነው?? ሥራ ፈት:: የምትሰራው ከሌለህ በነካ እጅህ ታዲያ የታምራት ላይኔን ኢየሱስ ታየኝን ድራማስ አብረህ አፅፈውም ነበር?? የጴንጤ ድራማ ሲሆን ትክክል ነው ማለት ነው??

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you that good point ye meskelu neger lenga lemnaminew hiywot new le maymnut mognat new

   Delete
 9. In the name of the Father, the Son and Holy Spirit One God Amen
  I have read that the miraculous descending of the cross is approved by the Holy synod (Mahidre sebhat lideta) and many people are cured miraculously in this church including several blind persons were able to see.
  What you write in this website is like the Parsee when our Lord and Saviors Jesus Christ was on earth and during the era of Apostles. When the blind person was able to see and was miraculously cured by Jesus Christ. The Parsee said you did not.

  God is not like us, but his patience is only to give you time to repent! please use it. I am praying for you to repent and be saved.

  Amen

  ReplyDelete
 10. why don't you post my information based on fact! Because it is discredit you! how long can you continue erring in dogama as well as deeds! Please repent before the door is closed!

  ReplyDelete
 11. "Be Mahibere kidusan midegefut aba Hitsane "... bileh metsafun endet resahew ? :)

  ReplyDelete
 12. yihe ye mak sira naw

  ReplyDelete
 13. thanks brothers for positive and encouraged articles regard Zerfe Spiritual song. We love our sister for great, her spiritual song. let us love each others through Lord God Jesus blood. he paid everything for our sin. why do hate each others for nothing? .......................we are putting down our orthodox faith for stupid craze MK members ............So sad....but our great God take care all good things for us............yebel be leanal !!!!

  ReplyDelete
 14. Teamer taye altaye milket taye altaye this is not the point . Bekrstos mamen is the point .we are blivers .we dont need milket like kefuna amenzera twoled milketen yishal endemilew kedus mesaf.

  ReplyDelete
 15. I absolutly knew this site is "ye menafeqan or kahadiwoch or sem atifiwoch" but I just check in once a month not often ...however every time I visit this page I really sorry for the writer for his unmatured article and disrespect our church's believes and fathers. What ever they wrote is untrue... hope some of you understood there misleading the people.

  ReplyDelete
 16. pentie ke ortodox ras laye mch new yemitiwordut?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የቤተ ክርስቲያን ዶግማዋ አይታደስም... ነገር ግን በንስሐ መታደስ ያለባችሁ እናንተ ናችሁ ..... ምክንያቱም ሠዎችን በውዥንብር የሐሰት ወሬ እያወራችሁ ልታውኩት ትፈልጋላችሁፈልጋላችሁ... "ወደ ቀድሞ መንገድ ተመልከቱ ...ለነፍሳችሁም እረፍትን ታገኛላችሁገኛላችሁ"

   Delete