Thursday, December 12, 2013

ምድሪቱን በምስጋና ጐርፍ ያጥለቀለቁት የዘማሪት ዘርፌ ዝማሬዎች

ያለም ቤዛ ኢየሱስ ነው
የፈወሰኝ ጌታ ነው
መዳን በሌላ የለም
እኔ አምናለሁ ዘላለም

በኦሪቱ ሥርዓት ፍጥረት ስላልዳነ
ለሚሻለው ኪዳን ኢየሱስ ዋስ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ተቤዠኝ በደሙ
ያዳነኝ እርሱ ነው ይስማልኝ ዓለሙ

አንዴ ለዘላለም ደሙ ፈሶልኛል
አሁን ያለ ኀጢአት ወዴ ይታይልኛል
ነፍሴን እንዲያነጻ ታርዷል ፋሲካዬ
መርሕ ሆኖ ወደ ክብር አስገባኝ ቤዛዬ

የዘላለም ርስትን የተናዘዘልኝኝ
መቃብርን ቀብሮ በሰማይ ያለልኝ
ሞቶ በመስቀሉ ሰላም ያደረገው
እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው

እንድንበት ዘንድ ተሰጥቶናል ስሙ
አማራጭ የሌለው መዳኛ ነው ደሙ
ሞትን መሞት እንጂ መግደል የተቻለው
ከኢየሱስ በቀር ሌላ ጌታ ማነው?

የመቅደስ አዛዦች እጅ ቢጫንብኝ
ከክርስቶስ ፍቅር መቼም አይበልጥብኝ
በልቤ ያመንሁትን ልመስክረው በአፌ
አልችልም ዝምታ በሞቱ ተርፌ
ይህ ከሰሞኑ ከተለቀቀው የዘማሪት ዘርፌ ከበደ ድንቅ ዝማሬዎች አንዱ ነው፡፡ ዝማሬዎቹን በጥቂቱ ከመቃኘታችን በፊት ግን ወደኋላ መለስ ብለን የዝማሬያችንን መነሻ፣ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶችና ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ እጅግ ባጭሩ ለመቃኘት እንሞክር፡፡


የቅዱስ ያሬድ ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ከያሬድ መነሣት ጀምሮ በዝማሬ የተባረከች አገር እንደሆነች ሁሉም የሚመሰክረው ሐቅ ነው፡፡ ለብዙ ምእት ዓመታት ቅዱሳት መጻሕፍትን መሰረት አድርገው በግእዝ በተደረሱ የያሬድ ዝማሬዎች የዘለቀው የዝማሬያችን ታሪክ ወደአማርኛ ዝማሬዎች ከተሸጋገረ እነሆ ሰባት ዐሥርት ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፡፡ በኢሳይያስ ዓለሜ ሐምሌ 16/1947 በዐማርኛ የታተመችውና መዝሙረ ጸሎት የተሰኘችው የመዝሙር መጽሐፍ ለአማርኛ ዝማሬዎች ፈር ቀዳጅ ናት፡፡ እስከዛሬም የዘለቁ “እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረኝ” ያሉ ዝማሬዎች የኢሳይያስ ዓለሜ ድርሰቶች ናቸው፡፡ ምን ያረጋል? ያን በመዝሙር 51 ላይ የተመሠረተ ድንቅ የንስሐ መዝሙር አንዳንድ ባሕታውያን ጰራቅሊጦስ የሚለውን ስም በተለያዩ የጻድቃንና የመላእክት ስሞች እየተኩ ድርሰቱን አበላሽተዉታል፡፡
“አሁን ትባርክ ዘንድ ማኅበራችን
 ፈጥነህ ላክልነ ጰራቅሊጦስን”
በሚሉት ስንኞች አምሳል እንደ ዚቅ “… ፈጥነህ ላክልን ድንግል ማርያምን፣ ቅዱስ ሚካኤልን፣ ቅዱስ ገብርኤልን … በማለት ነው ያበላሹት፡፡ አሁን ጰራቅሊጦስ ከተባለው መንፈስ ቅዱስ በላይ ባራኪ ማን አለና ነው በእርሱ ላይ ሌሎችን መደረብ ያስፈለገው? በእውነቱ ይህ ትልቅ ክሕደትና አምልኮተ ባእድ ነው፡፡ 

ከኢሳይያስ ዓለሜ ለጥቆ በታላቁ ሊቅ በመሪጌታ ፀሐይ ብርሃኑ በአማርኛ የተደረሱትን የያዘውና “መዝሙረ ስብሐት” የተሰኘው ከኖታው ጋር ባስር ዓይነት ድምፅ የተዘጋጀ የመዝሙር መጽሐፍ ይገኛል፡፡ ይህም መጽሐፍ በጥር 3/1961 ዓ.ም. ነው የታተመው፡፡ ከእነዚህ ዝማሬዎች እስከዛሬ ድረስ የዘለቁ አሉ፡፡
“የአብርሃም አምላክ የይሥሐቅም ቤዛ
          ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ”  የሚለው ይጠቀሳል፡፡

እነዚህ የዚያ ዘመን ወጣቶችና ጕልማሶች የዛሬ አባቶች የደረሷቸውን እነዚያን ዝማሬዎች ተከትሎ በርካታ ዝማሬዎች ሲፈስሱ ኖረዋል፡፡ በተለይም በሃይማኖተ አበውና በሌሎቹም በዚያ ዘመን በነበሩ የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበሮች ውስጥ አጥንትን የሚያመለምልሙና በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረቱ ዝማሬዎች  ሲዘመሩ ኖረዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ብቅ ያለውና የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ ጉዞ ወደኋላ ለመመለስ ሲታገል የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን ከተፈጠረ ወዲህ ግን ዝማሬዎቻችን የኋሊት ተመልሰው “ማርያም ወረደች አሸዋ ላሸዋ” “ኧረ እንዴት ነሁ አቦዬ ኧረ እንዴት ነሁ ጻድቁ” አይነትና በባልቴቶች ተረት የተሞሉና መንፈሳዊ ጥማትን በማይቆርጡና አዚምና ድንዛዜን በምእመናን አእምሮ በሚረጩ እንጉርጉሮዎች ተተኩ፡፡ እነሃይማኖተ አበውና ሌሎችም መንፈሳውያን ማኅበራት እየተዳከሙ ማቅ መድረኩን መቆጣጠር ሲጀምር ግን የዝማሬው ጉዞ ተገትቶ በወንጌላውያኑ ወገን ግን ታላቅ የመዝሙር አብዮት ፈነዳ፡፡ ይህ በአንድ በኩል በኦርቶዶክሶች ዘንድ ዝማሬዎቻችን እየወረዱ ሲመጡ በተፈጠረ ክፍተት የተከሠተ አብዮት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እነዚያ ዝማሬዎች ብዙ ኦርቶዶክሳውያንን መሳብና ከቤተክርስቲያን ማፍለስ ችለው ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ የእነማቅና በእነርሱ መንገድ ለመዘመር የሞከሩ ዘማርያንና ዘማርያት እንጉርጉሮዎች እንኳን በሌላው ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ኦርቶዶክሳውያንንም መያዝና ማቆየት አልቻሉም፡፡  

በምርጫ 97 አካባቢ ዘማሪት ምርትነሽ  ይዛው ብቅ ያለችውና “ሰረገላዎችህ የእሳት ናቸው” የተሰኘው የዝማሬ አልበም ግን ለዓመታት ተዳፍነው ለቆዩት የአማርኛ ዝማሬዎች ትንሣኤን በመስጠት በአማርኛ መዝሙር ታሪክ ሌላ አብዮት አስነሣ፡፡ ዳግም የፈነዳውን ይህን የመዝሙር አብዮት ለመቀልበስ ማቅና መሰሎቹ መዝሙሩ ዘፈን ሆነ፣ ያሬዳዊ ዜማን አልጠበቀም፣ ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ውጪ ነው ወዘተ. የሚሉ ጩኸቶችን ቢያሰሙም በየጋዜጣውና መጽሔቱ ላይ ቢለፍፉም ሰሚ አላገኙም፤ ምርትነሽ ካወጣችው ዝማሬ በግጥም ይዘትም በዜማ ጣዕምም የወረደ ሥራ ይዞ የመጣውን ዘማሪ ሁላ ሕዝቡ ባለመቀበልና ከገበያ ውጪ በማድረግ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ከመድረክ እንዲገለል ሲያደርገው ማቅ በተደጋጋሚ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተባቸውን የዚህን ዘመን ዘማርያንንና ዘማርያትን ግን በልዩ አክብሮትና አድናቆት በመቀበል ዝማሬዎቻቸውን አድምጦላቸዋል፡፡ በየታክሲው፣ በየካፌውና በየሱቁ የሚደመጠው የእነርሱው ነው፡፡ ማውገዝና ስም ማጥፋት ያንን ሰው በከፍተኛ ሁኔታ ማስተዋወቅ መሆኑን ግን አውጋዦች እስካሁን አልተረዱትም፤ ለወደፊቱም አይረዱትም፡፡

ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክፍለ ሀገሩ በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጡ የሚገኙት የዘርፌ ዝማሬዎች በግጥማቸው ይዘትም ሆነ በዜማቸው ጥዑምነት ተወዳዳሪ አልተገኘላቸውም፡፡ የዘርፌ ዝማሬዎች ታላቅነት የሚመነጨው በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረቱ ከመሆናቸው ነው (ከአንዳንዶቹ ስንኞች አጠገብ የድርሰቱ ምንጭ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመጥቀስ ሞክረናልና ይመልከቱ)፡፡ በአብዛኛው የዘመረችው ቃሉን ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ዘመን የማይሽረው፣ ወረት የማያውቀው፣ እርጅና የማያገኘው ሕያው ስለሆነ መቼም ቢሆን አይሰለችም፡፡ ስለዚህ በቃሉ ላይ የተመሠረቱ ዝማሬዎች ዘመን አይሽሬ ናቸው፡፡

ኧረ እንዳንተ ያለ ከወዴት አለ
የበደሌን ሸክም ያንከባለለ (ኢሳ. 53፡6)
ውዴ እንዳንተ ያለ ከወዴት አለ

ጻድቅ ጠፍቶ አንድ ስንኳ በሕጉ ፊት ሲመዘን (ሮሜ 3፡11)
አይደለም በደላችን ጽድቃችን መርገም ሲሆን (ኢሳ. 64፡6)
የእግዚአብሔር ልጅ ተገልጠህ የጠላት ምክሩ ፈርሷል (1ዮሐ. 3፡9)
ኢየሱስ ዕርቃን ሆነህ ትውልዱ ምሕረት ለብሷል

ባርያዋን እንድታነግሥ የባሪያን መልክ ይዘሃል (ፊል. 2፡7)
እንባዬን የዓይኔን ጅረት በደምህ ገድበሃል
የልቤ ልብ አንተ ነህ ነፍሷ እኮ ነህ የነፍሴ
መኖሬ ሕልም ነበር ባትሆነኝ እስትንፋሴ

ለጻድቅ ነፍሱን ‘ሚሰጥ በጭንቅ ይገኝ ይሆናል
ገና ደካማ ሳለሁ አንተ ግን ወደኸኛል(ሮሜ 5፡6-8)
በሞትህ እንደታረቅሁ በሕይወትህ እድናለሁ (ሮሜ 5፡9-10)
የዘላለም መሥዋዕቴ ዘላለም አምንሃለሁ

በኪዳን ነው ሕይወቴ በኪዳን ነው ኑሮዬ
ደምህ ነው ማዕተቤ ያጌጥሁበት ድሪዬ
ሞትህን በሚመስል ሞት ካንተ ጋር ብተባበር (ሮሜ 6፡5)
በትንሣኤህ ታድሼ ‘በራለሁ እንደ ንሥር

በሌላ በማንምና በምንም ሊከናወን ያልቻው መዳናችን በኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ሥራ መከናወኑን ቃሉን መሠረት በማድረግ የተሰናኘው ይህ የዝማሬ ግጥም ለነፍስ ትልቅ ዕረፍትን የሚያጎናጽፍ ነው፡፡ የስንኞቹ መልእክት ከዜማው ጣዕም ጋር ተዋሕዶ በዘርፌ ስርቅርቅ ድምፅ ሲንቆረቆር ለሚሰማ ሰው ከዚህ ዓለም ለይቶ በተመስጦ ቤዛችን ወደሚገኝባት ወደ ሰማያዊቱ መቅደስ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ ይህን ዝማሬ በተመስጦ እየሰማ ያዳነውን ጌታ ውለታ እያሰበ በፍቅሩ እሳት እየነደደ ጉንጮቹ በእንባ የማይርሱበት ማን አለ?

ሌላው የዘርፌ ዝማሬ ሁሉ የረሳውን መንፈስ ቅዱስን ያስታወሰና ለእርሱ ክብርን የሚያመጣው ዝማሬ ነው፡፡ ዓለማየሁ ሞገስ መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያናችን ምን ያህል የተረሳ መሆኑን ለማሳየት እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደ መንፈስ ቅዱስ ችላ የተባለ ወይንም ያልታወቀ ከሦስቱ አካላት የለም፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ (በ1987 ዓ.ም. ነው መጽሐፉ የታተመው) በአዲስ አበባ 56 አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም የታነጸ ግን አንድም የለም፡፡ የሥላሴ 2 የእግዚአብሔር አብ 3፣ የመድኀኔዓለም 7፣ ይህም ከማርያም ስለተወለደ እንጂ ማን ዙሮ አይቶት አያ፣ በጠቅላላ በአስማተ ሠለስቱ ሥላሴ አሐዱ አምላክ 10 አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ የተቀረው ግን በማርያም፣ በመላእክት፣ በጻድቃን በሰማዕታት ስም ነው፡፡ ምስኪን የቤተክርስቲያን ጠባቂ መንፈስ ቅዱስ ግን አንድም እንኳ የለውም፡፡ ያመት እንጂ የወር በዓልም የለውም፡፡ ሰዎች ሲደነግጡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሲሉ በቀር ስሙን ማን አንሥቶት አያ፣ ከእነዚሁም በጣም ካልደነገጡ በስመ አብ ብቻ ብለው ዝም የሚሉ አሉ” ብለው ነበር (ሁሉም ሁሉን ይወቅ ገጽ 140)፡፡

ዘርፌ በዝማሬዋ መንፈስ ቅዱስን አንሥታለች፡፡ ከሳሾች ስለማርያም አልተዘመረም፤ ስለቅዱሳን አልተዘመረም ወዘተ እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ አልተዘመረም ሲሉ ሰምተን አናውቅም፡፡ ዘርፌ ግን በብዙ ስለተረሳው ስለመንፈስ ቅዱስ ስትዘምር መንፈስ ቅዱስን ለዝማሬ አነሣሿ፣ አጽናኟ፣ ልቧን አሳራፊ፣ መካሪዋ፣ እግዚአብሔርን አባ አባት ብላ እንድትጠራው የሚያደርጋት ኀይሏ ነው፡፡ ከዚያም በላይ ብዙ ነገሯ ነው!! ይህን አጽናኝ መንፈስ እንዲህ ስትል ነው የወደሰችው
መንፈስ ቅዱስ አገዘኝ
ዘምሪ ዘምሪ አለኝ
በእሳት ልሳን አጠበኝ (የሐዋ. 2፡3)
እንዳልፈራ አደረገኝ

ስውሩን የሚገልጸው ልቤን የሚያሳርፈው
አጽናኝና  መካሪ መሪዬ ነው መምህሬ
ሲናገረኝ እስማለሁ ሲያበረታኝ እጸናለሁ
አባ አባት ‘ሚያሰኝኝ እርሱ ነው ኀይል የኾነኝ (ሮሜ 8፥14-15)

ዘርፌ የቅድስት ማርያምን ታላቅነት የእግዚአብሔር ቃል በሚለው መሠረት አውስታ ዘምራለች፡፡ 
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች
መንፈሴም በእርሱ ትደሰታለች
ብላ ዘመረች ድንግል ማርያም
መርጧታልና ለዘላለም

ያሬድም ይህንኑ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈውን የማርያምን ጸሎት እንደ ወረደ ዜማ ሠርቶለት እንዲዘመር አድርጓል፡፡ “ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ማርያም ትቤ ማርያም እስመ ገብረ ሊተ ኀይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ … ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች፤ ማርያም አለች፤ ማርያም አለች፤ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራን አድርጓልና ስሙም ቅዱስ ነው …” (ምዕራፍ ዘዘወትር ስብሐተ ነግህ)፡፡ ዘርፌም ያንን መንገድ መከተሏ የያሬድ እውነተኛ ልጅ የሚያሰኛት ነው፡፡ ማርያምን ጠቅሰን ልንዘምር በሚገባን ተገቢ መንገድ ዘምራለች፡፡ ማርያምን አለቅጥ ከፍ ከፍ አድርጋ ወደአምላክነት ደረጃ ከፍ ሳታደርግ መዘመሯ የሚያስመሰግናት ነው፡፡ ስለመላእክት ስለቅዱሳንን ጠቅሰን መዘመር ቢያስፈልግ በዚሁ መንገድ በተለይም በሦስተኛ መደብ “እርሷ እርሱ” እያለን ያለፈውን በመመስከር እንጂ በሁለተኛ መደብ “አንተ አንቺ” እያልንና ከእነርሱ ጋር እንደምንነጋር አድርገንና አምልኮ አከል ውዳሴና ልምና ለፍጡራን በማቅረብ መዘመር “ዘይቤ” ቢሆንም ከአምልኮት ጋር ሲገናኝ አምልኮተ ባዕድ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ የመዝሙር ደራሲዎች ይህን ትክክለኛ መንገድ ተከተሉ፡፡

ሌላው ዝማሬ እንዲህ የሚለው ነው፤
ያለም ቤዛ ኢየሱስ ነው
የፈወሰኝ ጌታ ነው
መዳን በሌላ የለም (የሐዋ. 4፥12)
እኔ አምናለሁ ዘላለም

በኦሪቱ ሥርዓት ፍጥረት ስላልዳነ
ለሚሻለው ኪዳን ኢየሱስ ዋስ ሆነ (ዕብ. 7፡22)
ከባርነት ቀንበር ተቤዠኝ በደሙ
ያዳነኝ እርሱ ነው ይስማልኝ ዓለሙ

አንዴ ለዘላለም ደሙ ፈሶልኛል (ዕብ. 9፡28፤ 10፥10፡14)
አሁን ያለ ኀጢአት ወዴ ይታይልኛል (ዕብ. 9፥24፡28)
ነፍሴን እንዲያነጻ ታርዷል ፋሲካዬ (1ቆሮ. 5፡7)
መርሕ ሆኖ ወደ ክብር አስገባኝ ቤዛዬ (ዕብ. 2፡10)

የዘላለም ርስትን የተናዘዘልኝ
መቃብርን ቀብሮ በሰማይ ያለልኝ
ሞቶ በመስቀሉ ሰላም ያደረገው
እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው (ዕብ. 9፡15፤ 12፡24)

እንድንበት ዘንድ ተሰጥቶናል ስሙ (የሐዋ. 4፡12)
አማራጭ የሌለው መዳኛ ነው ደሙ
ሞትን መሞት እንጂ መግደል የተቻለው (2ጢሞ. 1፡11-12)
ከኢየሱስ በቀር ሌላ ጌታ ማነው? (1ቆሮ. 12፡3)

የመቅደስ አዛዦች እጅ ቢጫንብኝ
ከክርስቶስ ፍቅር መቼም አይበልጥብኝ
በልቤ ያመንሁትን ልመስክረው በአፌ
አልችልም ዝምታ በሞቱ ተርፌ

ዘርፌ በመንፈስ ቅዱስ የጀገነች ዘማሪት በመሆኗ “ኢየሱስ” ብሎ መዘመር እንደመናፍቅ በሚያስቆጥርበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ በመሆን መዳን በሌላ የለም ብላ በመዘመሯ እውነተኛ ምስክር ሆናለች፡፡ እንዳለችው “የመቅደስ አዛዦች እጅ” ቢጫንባት ከክርስቶስ ፍቅር መቼም አይበልጥባትም፡፡ በልቧ ያመነችውን በአፏ ለመመስከር የደፈረችው በክርስቶስ ሞት የዳነች መሆኗን ስለተገነዘበችና ዝም ማለት ስለማትችል ነው፡፡ ጥንትም ሆነ ዛሬ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ስሙን ጠርተን አዳኝነቱን እንዳንመሰክር በልዩ ልዩ መንገድ ያስፈራሩናል፡፡ አንዳንዶቻችን ፈርተን ያመነውን ሳንመሰክር እንቀራለን፡፡ ሐዋርያት በዚህ ስም እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ ዝተን እናስፈራራቸው ብለው “በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው። እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደ ሆነ ቍረጡ፤ እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም አሉአቸው።” (የሐዋርያት ሥራ 4፥18-20)፡፡ የዘርፌም የዚህ ዝማሬ የመጨረሻ ስንኞች ይህን ታሪክ ያስታውሱናል፡፡ በእርግጥም በክርስቶስ ሞት መዳንሽን ከተረዳሽ ይህን እውነት አለመመስከር አትችይምና እኅታችን ሆይ እውነተኛ ምስክርነትሽን ግፊበት፡፡ ደግሞም በሌላው ዝማሬሽ፥

አንድ ጌታ ኢየሱስ አለኝ ክርስቶስ አለኝ (1ቆሮ. 8፡6)
ሰልፌን ሰልፉ ያደረገልኝ የሚዋጋልኝ
የማይፈታ ማተቤ ነው ደሙ
ከፍ ላ’ርገው ዐርማዬ ነው ስሙ
በማለት እንደገለጽሽው እርሱ ስላንቺ ይዋጋልና ጠንክሪ፡፡

ሌላው ዝማሬ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስን ሊቀ ካህናትነት የሚመሰክረው ዝማሬ ነው፡፡ አዝማቹ እንዲህ የሚል ነው፡፡
ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ሊቀ ካህናት (ዕብ. 4፡14፤ 7፥26)
የአዲስ ኪዳን በግ ንጹሕ መሥዋዕት (ዮሐ. 1፡29)
መሥዋዕትም አቅራቢ ተቀባይም ሆነ
በደሙ ቤዛነት ፍጥረት ሁሉ ዳነ

ይህም ዝማሬ የክርስቶስን ሊቀ ካህናትነት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ የተደረሰ በመሆኑ ዘመን አይሽሬ እውነት ነው፡፡ ሦስተኛው ስንኝ “መሥዋዕትም አቅራቢ ተቀባይም ሆነ” የሚለው “መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት ሆነ” መባል ነበረበት የሚል እምነት አለን፡፡ እርግጥ “ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ወለሊሁ ተወካፌ መሥዋዕት ምስለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ - እርሱ መሥዋዕት የሚያቀርብ ሊቀካህናት ነው፤ የሚሠዋ መሥዋዕትም ነው፡፡ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕቱን የሚቀበል ነው” የሚል ንባብ በአበው ሃይማኖት ውስጥ አለ፡፡ አበው ይህን ያሉበት ምክንያት ሥጋ የሆነው ቃል ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል መኾኑን ለማመልከት ነው፡፡ ይህ በራሱ ትክክል ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ የሠራውን የእርሱን ሥራ ለይቶ ማቅረብ ተገቢ ነው፡፡ ሰው መሆን፣ መሥዋዕት መሆንና መሥዋዕት ማቅረብ በተለየ አካሉ ያከናወነው የእርሱ የብቻው የሊቀ ካህናትነቱ ግብር ነው፡፡ እርሱ መሥዋዕትና መሥዋዕቱን አቅራቢ ሊቀካህናት ነው፤ ያቀረበው ደግሞ ለእግዚአብሔር አብ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ይህን ያረጋግጥልናል፡፡ ለእግዚአብሔር አቀረበ ስለተባለ ክርስቶስ ዝቅ አይልም፤ ተቀባይም ሆነ ስለተባለ ደግሞ ከፍ አይልም፤ ከዚያ ይልቅ የእግዚአብሔር ሦስትነት በአንድነቱ ይጠቀለላል፡፡ ስለዚህ ይህ ወደሰባልዮስ ትምህርት ያዘነበለ አገላለጥ ነውና ሊታረም ይገባል እንላለን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።” (ኤፌ. 5፥2)
እንዲሁም “ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?” (ዕብ. 9፥14) ሐዋርያው ጳውሎስ በእነዚህ ክፍሎች ክርስቶስ ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው ለእግዚአብሔር ነው ይላል፡፡ እውነት ነው፡፡ አሊያ በምስጢረ ሥላሴ ላይ ተፋልሶ ይከተላል፡፡ አብና መንፈስ ቅዱስም እንደ ወልድ መሥዋዕት ሆነዋል፣ መሥዋዕት አቅርበዋል ልንል ነው፡፡ ስለዚህ የግጥሙ ደራሲ “መሥዋዕትም አቅራቢ ተቀባይም ሆነ” ከሚለው ይልቅ “መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት ሆነ” ቢለው ኖሮ ምስጢሩ እንዴት ያረካ ነበር!! በተረፈ ግን ሌሎቹ ስንኞች ሁሉ ኃጢአት ላደከመው ሁሉ ዕረፍትን የሚሰጥ ታላቅ ዝማሬ ነው፡፡ ስለዚህ አዝማቹ በዚህ መንገድ ቢታረምስ

ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ሊቀ ካህናት
የአዲስ ኪዳን በግ ንጹሕ መሥዋዕት
መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀካህናት ሆነ (ዕብ. 9፡11-12)
በደሙ ቤዛነት ፍጥረት ሁሉ ዳነ

የበግ የዋኖሱን - ብዙ ደም ቢያፈሱ (ዕብ. 10፡4)
የብሉይ ካህናት - ቢቆሙ በእርሱ ፊት
የሞት አገልግሎት - ሆኖባቸው ድግምት (2ቆሮ. 3፡7)
መሢሑን ናፈቁ - አዳኙን ዐወቁ

ክርክር የለኝም  - አላጕረመርምም
አመሰግናለሁ - በደሙ ድኛለሁ
እንደ መልከ ጼዴቅ - የነገሠው በጽድቅ
ታላቅ ናት ክህነቱ - ዘላለም መንግሥቱ (ዕብ. 5፡9-10፤ 6፥20)

መድኀኒት ተገልጧል - እኛም አይተነዋል
ሞታችን ተገድሏል - በጸጋው ድነናል
በይሥሐቅ ፈንታ - የተሠዋው ጌታ
እንደ በግ ታረደ - ሁሉንም ወደደ

ስንሠቃይ አይቶ - ክብሩን ሁሉ ትቶ
በሥቃይ ደቀቀ - ሊያነሣን ወደደ
ሲኦል ተብዝብዟል - ሥልጣኑ ተይዟል
ለተቤዠን ንጉሥ - ምስጋናችን ይድረስ

በዚህ የመዝሙር አልበም ውስጥ  የምናገኘው ሌላ ድንቅ ዝማሬ ይኸው፥
እኔስ ለአምላኬ እኔስ ለእግዚአብሔር
ምስጋና አለኝ ምስጋና አለኝ
ውለታው ስለበዛብኝ

አሳዳሪዬ መጋቢዬ የነፍሴን ጩኸት የምትሰማ
ከአንተ ጋር ስኖር በዘመኔ ክፉ ትዝታ የለኝ እኔ
ስለእርሱ የማወራው ብዙ ነገር አለኝ
ዘመንና ዕድሜ ጤና ከተሰጠኝ

ከግብጽ ያወጣኝ ከባርነት ባሕርን ከፍሎ በታምራት
መንገዴን መርቶ ያሳለፈኝ ከመስቀሉ ሥር ያሳረፈኝ
ስለእርሱ የማወራው ብዙ ነገር አለኝ
ዘመንና ዕድሜ ጤና ከተሰጠኝ

አለቅባቱ በላዬ ላይ ከፍ የሚያደርገኝ ወደሰማይ
ለታረደው በግ ምስክር ነኝ ቅኔ በገና ላስታጠቀኝ
ስለእርሱ የማወራው ብዙ ነገር አለኝ
ዘመንና ዕድሜ ጤና ከተሰጠኝ

እየባረክሁህ ልኑርልህ እየዘመርሁኝ ልሙትልህ
የማልጠቅመውን ከጠራኸኝ ላንተ ብቻ ነው የሠራኸኝ
ስለእርሱ የማወራው ብዙ ነገር አለኝ
ዘመንና እድሜ ጤና ከተሰጠኝ


በዚህ መዝሙር ውስጥ ጌታ ያደረገላትን ዋና ዋና ነገር ጠቃቅሳ አዳኟን ስትወድሰው ደጋግማ እንዳለችው በተለይም በመጨረሾቹ ስንኞች ውስጥ እየባረከችው ለመኖር እየዘመረችለት ለመሞት መወሰኗ ያለምክንያት አይደለም፡፡ የማትጠቅመውን እርሷን የጠራት ለእርሱ ብቻ እንድትኖር ለእርሱ ብቻ እንድትዘምር መሆኑን ስለተገነዘበች ነው፡፡ ስለእርሱ ብዙ እንድትዘምርና እንድታወራ ረጅም እድሜና ጤና ይስጣት እንላለን፡፡ ከዚህ የመዝሙር አልበም ጀርባ ያሉት ገጣሚዎችና ዜማ ደራሲዎቹም ሁሉ እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡  እግዚአብሔር የቃሉን ምስጢር ከዚህ በበለጠ ይግለጥላቸው፡፡ ነፍስን የሚያረካ ዜማም ይስጣቸው፡፡

63 comments:

 1. ቤተ ክርስቲያናችን በበጉ ደም የዳኑ የክርስቶስ ምስክሮችን እያበዛች ነው። ሃሌሉያ ይህንን ላደረገ ለእግዚአብሔር! ተባረኪ ዘርፌ።

  ReplyDelete
 2. Her albam is praising lord Jesus. It is the greatest worship, I ever seen in our church, the presence of God will come to our Church if our worship bibiblical. Zemari zerfe, God really loves you, he delighted by your new albam. He selected to shape our wrong worship with tert tert mezmure, to the real one, which you are presenting in your new albam (early Christmas gift).

  Your brother by Jesus

  ReplyDelete
 3. እነዚህ ልጆች ከዘማሪት ዘርፌ ውጭ(እሱዋ ከአለማዊነት የመጣች ናትና አልፈርድባትም) ሁሉም ትናንት ተራ ሰ/ተማሪ ነበሩ. በኛው ጉያ ስር አድገዋል. የልጅነት ድምጻቸው መስጦን በዝማሬያቸው ቆመን ታድመናል. አጨብጭበናል. “ሙዳየ-መና ግሩም” ሲሉ አጅበናቸዋል. በዝማሬያቸው የራቁትን አቅርበዋል.
  1. ሆኖም አሁን አሁን የዝማሬያቸው ቃና ከኛ ይልቅ ለሌሎች የሚቀርብ ሆኖ ይሰማኛል. ችግሩ አብዝተው ስለ ጌታ መዘመራቸው አይደለም፣በገእዝ አለመዘመራቸውም አይደለም(ሰብህዎ በክሂሎቱ ብሉዋልና)ጌታን የሚያነሱበት መንገድ እንጅ. የኔ…ውዴ…ወዳጄ…..ጌትየ….ሰባሪው….ከፍ በል….ከፍታ….ጠላቴ….መሞላት….ወዘተርፈ የሚሉ ጌታን ከንጉስነት ወደ ጥሬ ጉዋደኛነት(ሎቱ ስብሀት) የሚያወርዱ የሚመስሉ ቃላት ምንም እንኩዋ ቃላቱ ኢ-መንፈሳዊ ናቸው ባይባሉም ከኛ ይልቅ በሌሎቹ እነስም-አይጠሬ ቸርቾች ስለተለመዱ ለነፍሳችን አይቀርቡም፣
  2. ምናልባት በኢኦተቤክ ስለ ክርስቶስ አይሰበክም የሚለው አደንቁዋሪ አሉባልታ ወስዱዋቸው ከሆነ ስለ ክርስቶስ ዘወትር በነግህ (ጠዋት) የሚደረሰውን ጸሎተ-ኪዳን ከነእግዚኦታው መታደም ፣
  3. እነ እንትናን ለማናደድ ብለው ከሆነም እልህ በሃይማኖት ስለማይሰራ ሰውን ከእ/ር በመለየት ስመ-ክርስትና ሰጥታ ገና በእቅፍ ሳሉ በስላሴ ስም የተቀበለቻቸውን ርእትእት ቤ/ክ ቅ/ያሬድን አርአያ አድርገው እንዳልሰሙ አልፈው በተአግሶ ማገልገል፣
  4. ሊቀ-መዘምራን ዳዊት እኮ ስንት ጊዜ ስለ ኢየሩሳሌም፣ስለ ጽዮን ዘምሩዋል. “ተዘከር ኪዳነ አግብርቲከ ቅዱሳን” ይል ነበር. እነዚህ ዝማሬዎች የጌታን ክብር ይከልላሉ አልተባሉም. ከዛ ይልቅ በጌታ የታመኑ ቅዱሳንን መዘከር እኛም እንደነሱ ተስፋ-መንግስተ ሰማያት እንዳለን ያዘክረናል. ስለዚህ ስመ-ቅዱሳንን ጠርቶ መዘመርን ችላ አትበሉ. ያለበለዚያ መንጋው የእረኛውን ድምጽ እየለየ መስማቱን ይቀጥላል፣
  5. እኛ ካህናቱም እነዚህን ልጆች ከመንገድ ሲወጡ መክሮ ገስጾ መመለስ. ወጣቶችም ብትሆኑ ልጆቹን እንደ መንፈሳዊ ወንድም ቀርቦ መምከር እንጂ ‘ጠርገን እናስወጣለን’ እያሉ ከሲኖዶስ ቀድሞ እያወገዙ ስም ለማውጣት አለመቸኮል. ወንድም ሲሳሳት ለመመለስ የተቻለን ያህል መጣር እንጅ መገፋፋት ዋጋ አያስገኝም. እና የመሳደድ ስመመየት እንዲሰማቸው አናድርግ. ሌሎች እኛን ለማናደድ ቢሰሙዋቸውም አይግረመን፣
  6. ለመሆኑ የየትኛው ዘማሪ መዝሙር ነው በድጉዋ ምልክት የተጮኸ መዝሙር. በፊት እነ መ/ታ ጸሀይ፣እነ ሊ/መ/ኪነጥበብ፣እነቀሲስ አበበ፣እነ ዲ/መገርሳ፣እነ መ/ር እስመለዓለም….. ለያሬዳዊ ዜማ የቀረቡ መዝሙሮችን ያቀርቡልን ነበር አሁን ሁሉም ድምጹን በሰ/ት/ቤት መዝሙር ክፍል ይፈትሽና ድንገት ተነስቶ “ዘምር-ዘምር አለኝ” ይላል…ባለቤት የሌለው ቤት!!
  7. በማህበረ-ቅዱሳን የሚታተሙ የህብረት መዝሙራት ከላይ ከተጠቀሱት እንከኖች የጸዱ ቢሆኑም ያን ያህል ማስተዋወቂያ ስለማይደረግላቸውና አቀራረጻቸውም ከድሮው የትምህርት በሬዲዮ መዝሙሮች የተሻሉ ባለመሆናቸው ለአድማጩ ምእመን ሰፊ አማራጭ ሆነው መቅረብ አልቻሉም.
  ስለዚህ መፍትሄው ቢያችል በቃለ-ዓዋዲው ላይ ካልሆነም በሊቃውንት ጉባኤ በሚወጣ መመሪያ አንድ መዘሙር የኢኦተቤክ መዝሙር ለመባል ማሙዋለት ያለበት ቅድመ-ሁኔታ ቢዘረዘር፣ቤ/ክ ልክ እንደ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ሁሉ የራሱዋ ሰቱዲዮ ቢኖራት፣በቤ/ክ መድረክ ለመዘመር ከሀ/ስብከቶች ፈቃድ ግድ ቢሆን….. ከዛ በሁዋላ ሳንሳቀቅ የምንሰማቸው መዝሙሮች ቢቀርቡልን!!
  “ወነዓምን በአሀቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!!”

  ReplyDelete
  Replies
  1. mezmurochu zefen meslew ketesemot, zefen mesmatin yakumu!

   Betechemari..ውዴ, ወዳጄ, ጌትየ, ከፍ በል yemilut kalatoch be meshaf kidus sefrew selemigegnu, meseha kidusawi nachew. Erso kaltesmamot, be 1000 yemikoteru leloch mezmroch selalu, jorowon mazor yechilalu

   Delete
  2. አንተ አሁን ጌታን ማክበርህ ነዉ ለምን ታዲያ አንቱ አትለዉም አባትህ አንቀጥቅጠዉ ስላሳደጉህ ፍቅር እንዴት እንደሚገለጽ አላወቅህም ኢየሱሰ አባቴ በኔ ያላፈረ ወንድሜ አማካሪ ጉዋደኛዬ ነዉ ለአንተ ደግሞ የሚያሰፈራራ ሩቅ አምላክ ስታቀርበዉ ተደፈርኩ የሚልና የሚቀስፍ ጌታህ ነዉ ለዚህም አይደል በየገደላገደሉ ጽድቅ ፍለጋ የምትንከራተተዉ ደግሞ ማቅ ምን መዘመር ይችልና ነዉ የህብረት የምናምን የምትለዉ ቤዛ ለሆነዉ ጌታ ክብር የማይሰጥ ከፍጡራኑ ጋራ የምስጋና ሻሞ የሚወረዉርለት ስለሆነ እሱን ባታነሳ ይሻላል

   Delete
  3. Egziabher Yistilign. You did say what I exactly have on my mind. My only with is that if our church could really examine and approve all songs before they get published to the public. So many people are being misled and I don't like the direction where this road of praising "only Jesus" is taking us. Also, I wonder why some people are so impolite when replying. This is not what the church has taught all of us. And even though this is my first day of visiting this site, I happen to find it very un-orthodox. Why are we reporting about personal sins of the Clergy? Is it funny? or Are we taking a pleasure out of peoples' failure? I'm not learning anything from reading such things. In fact, I hate knowing about sins about our Fathers. I'm not going back to this site ever again. For now, I pray God looks our country and religion with his mercy.

   Delete
  4. mezmur berasu selot endehone gena kelegenet gemro yasadegechen senbet temert betachen negranalech! ene zemari kinetebeb, ene leulseged ene yelma... yemesaselut wendemochachen sizemeru aganent sibrekerek aytenal. ahun eyetefetere yalew gen legenzeb masgegna behone akahed kalun lemesbek sayhon sewn azello mehed yetemeretebet slerasachew becha yemizemerubet...honwal lemenfekena kerb yehonu mezmuroch beztewal ihe ihe meshaf kedus lay ale menamen atebelu mesehafun yemiyzew erkus menfes kemeta koytwalna.... ihe kegna alfo menafkan yemizemruten enkwan erkusun liyarek.... menew sebel bota hedachu menfes yalebachew siyangoragurut bayachu... bebetu noro rasun aneso yelikawnte abewn zemarena temert meseret argo yemizemer zema bebetu lenoru sewoch yastawekal yetemal.... manegnawm agelglot yalesom selot tenesto migebabet adelem... tenantena yetefetern sewoch agul mezmuren lematamem ende reformation yale neger mnaregew neger erkuset new! zemarin endemifetatenew aynet erkus menfes yale endaymeslachu yeteebit menfesna yemenfekna menfes hulem bezuryaw nachew!...ahun ahun eyewetu yalute mezmuroch betam yeteberezu nachew ... ihen hulu yalkut gen landandochu new............ beye geteru eyetegwazu hesanaten eyesebesebu bemenfesawi zema yaltenekeruten eyesebesebu demes yalewn kaset kaseruna genzebachewn kagegnu behwala legochun leteebit menfes agaltew yemitefuten sewoch dengel maryam yeker tebelachew ke egziabherem tastarkachew>>>

   Delete
  5. very very true. GOD bless u.

   Delete
 4. አባ ሰላማዎች
  ስለ በጋሻው ደሳለኝ ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ እና ስለ ማህበረ ቅዱሳን/ሰይጣን/ ከመጻፍ ለምን ተቆጠባችሁ? ከእናንተ ብሎግ እውነቱን እናነባለን ብለን ጠብቀን ነበር

  ReplyDelete
 5. betam des yilal tebareku

  ReplyDelete
 6. Tebareku Betam Des yilal

  ReplyDelete
 7. ewntachehun new ende ende ende.sigerem. ATAFRUM TENSHE? YMAYGELTSE YTKEKEDENE YEMAYTAYE YTSHSHEGE NGERE YELEM KETNATENA ZARE KZARE DGEMO NGE KEHEDTACHU YELTSAL ATSASATU BTKERSTIYA ENATE ENDTAMEMACHEHT AYDELEM KERSTOSEN YMTASTEMERW, GETA YGTSESACHU

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደግሞ ቤተክርስቲያን ከዚሀ ዉጪ እንዴት እንድታስተምር ተፈልጎ ነዉ አስተያየት አቅራቢዉን ጌታ የሚገስጸዉ፣ መገሰጽ ያለበት ቤበተክርስቲያናችን ሠርጎ ገብ ትምህርትና የጌታን ዉለታና ክብሩን ዝቅ አድርጎ ከሌሎች ጋር የሚያዳብለዉን መንፈስ ነዉ፣ ጉዳዩ እኮ ያለቀዉ የመድሐኔዓለምን ታቦት የአርሴማ፣ የእመቤታችን፣ የዮሴፍ፣ የሚካኤል ደባል ስታደርጉ ነዉ፣ደግሞ የቀጨኔዉ መድሐኔዓለም ገቢ አያስገባም ተብሎ ግብርኤል እንደተሰራለት ዓይነት ክህደትና ድፍረት ያመጣዉን አሁንም ጌታ ይገስጸዉ!

   Delete
 8. zmarit Zerfe Kebede Geta Kirstos Eyesus Kale Hiwot Yasemashe
  aba Selam blognm Geta Yabertachu Elalehu Amen!

  ReplyDelete
 9. ለኢየሱስ ጌታ ከብር ይሆን ማህበረ ቅዱሳን ይፈር ወራዳ ማህበር

  ReplyDelete
  Replies
  1. Look how many replies this gets from those fanatic blind followers

   Delete
 10. ያለም ቤዛ ኢየሱስ ነው
  የፈወሰኝ ጌታ ነው
  መዳን በሌላ የለም (የሐዋ. 4፥12)
  እኔ አምናለሁ ዘላለም ????? Good song. We know who you are now. ki.. ki...ki............

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yes! you know about her know, She is Christina! If you expect her to sing a song "ale bolale, ale! " go to zemarte fantu.

   Delete
  2. ኪኪ ምንድነዉ ሌላ የፈወሰህ ካለ ማምጣት ነዉ መዳን በሌላ አለ የምትል ከሆነም ከነማስረጃ መቅረብ ነዉ እንጂ ሽሙጥን ምን አመጣዉ

   Delete
  3. የአለም ቤዛ ሌላ አለ እንዴ??
   ኧረ ለቦና እና ማሰተዋሉን ይስተን።

   Delete
  4. ዘርፌ የምትዘምረው ለገንዘብ ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው፤ስለዚህ የተቀበረውን እውነት እንታወጭ የመረጠሽ ጌታ ኢየሱስ ይባረክ አሜን።

   Delete
 11. really realy really it is so nice

  ReplyDelete
 12. You are protestant in religion; Go and preach there. We believe in Christ; through Him we also believe the Mercy that we get from Saints. All words in the bible advocates that.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የፈሪ ዱላችሁ ፕሮቴስታንት ማለት ነዉ አንደ ፕሮቴስታንተ እዉነትን ከተናገረ የማልቀበልበት ምክንያቱን አስቲ ንገሩኝ በእርግጥ ቅዱሱን መጽሐፍ የሚያዉገረግር ከሆነ ያ ሌላ ነዉ የባልቴት ተረት የሚያመጣ ሆነም አወግዘዋለሁ ከዚያ ዉጪ ግን የእነሱነ ስም በመጥራት እንደ ጭራቅ ማስፈራሪያ ማድረግ ማጣፊያ ሲያጥራችሁ ስለሆነ በሰለጠነ መንገድ መወያየትና የጌታነ ዉለታ እንደቃሉ በፍቅር በምስጋና መኖርአማራጭ የለዉም May God bless you, just to respond in the language you used in the above comment.

   Delete
  2. why when somebody preaches or sings the true word of God.based on the bible is called protestant .Don't you realize that the truth is with them .My brother please I beg You by the love of Jesus christ read The Bible Yourself , Do not hear second hand information from others,and You will see if You still talks the same way.God bless You ,I love You, But Jesus loves You more than any body!!!

   Delete
 13. ተባረኩ እንዲህ ነው መተቸት መደገፍም ከተባለ ይህነው: ተባረኩ

  ReplyDelete
 14. በጣም ደስ የሚል ተንታኔ ነው የተጻፈው ስለ መዝሙሮቿ። ሁሉም በጣም ደስ ይላል እና በጣ ትክክል ናቸው። ነገር ግን አንድ ጥያቄ አለኝ። እንዲህ ብለው ጽፈዋል "ስለመላእክት ስለቅዱሳንን ጠቅሰን መዘመር ቢያስፈልግ በዚሁ መንገድ በተለይም በሦስተኛ መደብ “እርሷ እርሱ” እያለን ያለፈውን በመመስከር እንጂ በሁለተኛ መደብ “አንተ አንቺ” እያልንና ከእነርሱ ጋር እንደምንነጋር አድርገንና አምልኮ አከል ውዳሴና ልምና ለፍጡራን በማቅረብ መዘመር “ዘይቤ” ቢሆንም ከአምልኮት ጋር ሲገናኝ አምልኮተ ባዕድ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ የመዝሙር ደራሲዎች ይህን ትክክለኛ መንገድ ተከተሉ፡፡" አሁን እዚህ ጋር እንደተረዳሁት ከሆነ አንተና አንቺ ብሎ መዘመር ወይም መናገር (ባጠቃለይ ማመስገን) ባዕድ አምልኮ ነው ብለዋል። ይህ አይነት ግንዜቤ ካሎት ብዙ የቤተ ክርስቲያናችንን ድርሰቶች ባዕድ አምልኮ ናቸው ወደሚል ግንዛቤ ይዳርጋል ብዬ አምናለው። ለምሳሌ በውዳሴ ማርያም ወይም ክዳሴ ላይ "ሰአሊ ለነ ቅድስት፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን" እያልን እንናገራለን። እኔ እንደተረዳሁት እርሶ ይህ ስህተት ነው እያሉ ነው መሰለኝ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ማብራርያ ቢሰጡ ደስ ይለኛል። በድጋሚ በጣም ደስ የሚል ነው የጻፉት ጽሁፍ እና ለቤተ ከርሰቲያናችን በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለው እንዲህ አይነት ትምህርት። ስለዚህ እግዚአብሔር ያክብርልኝ እና ያገልግሎትን ዘመን ያብዛልን።

  ReplyDelete
 15. leyunetn lemezrat bejet yezachu eyetenkesakesachu endehonena andandem bas sil yefainacerochachun felagot sibezabachu tsom yekenesln belachu tstfalachu lehodach atderu yehaymanot guday yenefs new. yeenante aserar bealem lemata ged new yehun enji eyandandachu begl beza yeseytan aserar west mehonachun awkachu endtneku emekrachuhalew. Geta Egziabher menfesachun yegesetsew.

  ReplyDelete
 16. woy protestant besew bet yifetefital

  ReplyDelete
 17. Thank you guys for explaining the nature and meanings of the songs! Please keep on working such positive jobs especially making the public understand the biblical fact behind these days' songs!!! God Bless U!!

  ReplyDelete
 18. እርሱ የአዲስ ኪዳን "መካከለኛ" ነው ---ይቺ ናት ጨዋታ ዘረፌ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርሱ የአዲስ ኪዳን "መካከለኛ" ነው ---ይቺ ናት ጨዋታ ዘረፌ

   I don't understand, What does it mean ይቺ ናት ጨዋታ ዘረፌ?

   Delete
  2. "You have come to... Jesus the mediator of a new covenant" Heb. 12: 24 ... problemo?

   Delete
  3. ewneteko merara nat esti ke zelmad weta belu

   Delete
 19. wey gud andandu comment aderagi lemogedel yechokelale area yeker yebelen zerfe egziabehare yebarkeshe

  ReplyDelete
 20. ዘተዋህዶ
  አባ ሰላማዎች በዚህ ፅሁፋችሁ ያስተጋባችሁትን መልእክት
  አንብቤው የራሴን መንፈሳዊ መልእክት ልፅፍላችሁ ወድጃለሁ
  በተለይ በሊቀ ካህናት ዝማሬ ላይ መሷዕት አቅራቢ ተቀባይም
  ሆነ የሚለው ለምን እንደኮሰኮሳችሁ ገብቶኛል "ይህቺ ጠጋጠጋ እቃ ለማንሳት ነው " መሷዕት አቅራቢነቱ ብቻ በግጥሙ እንዲገለፅ መፈለጋችሁ ኢየሱስ ዛሬም አማላጅ ነው ለሚለው ክህደት ሰዎችን ለማመቻቸት ነው ። ስለዚህ
  ተቀባይ የሚለው ቃል ያልተመቻችሁ ለዚህ ነው ።
  የቆማችሁለት ጌታ በእውነት ኢየሱስ ከሆነ እና የኢኦተቤክ
  አገልግሎትን ማጥራት ከሆነ ሌላ ቆሻሻ ክህደት አታስገቡ ።
  ዘማሪዋንም አገልግሎቷ በጥርጣሬ እንዲታይ አታድርጉ።

  ReplyDelete
 21. የዘርፌን ስም በመበከል ሁላችሁም ባትሰለፉ መልካም እናንተንም ደግፉኝ አላለችም እኮ ነቃፊዎችንም ንቀፉልኝ አላለችም ማን ገምጋሚ አደረጋችሁ የኦርቶዶክስ ልጅ ስለሆነች ይም ያናድዳል እንዴ?አሁን ማቅ ተነስቶ 《መናፍቃን ናት ለካ》ብሎ ማኖ እንዲነካ ነው እንዴ ፍላጎታችሁ ኸረ እባካችሁ አርፋችሁጠበላችሁ ተቀመጡ!!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 22. ምኑ ነዉ ጨዋታ? ከዚህ የበለጠ ኮስተረ ያለ ሐቅ አለና ነዉ "ጨዋታ ያልካት" ይቅር ይበልህ

  ReplyDelete
 23. This is the true revival for Ethiopian church,here that day comes now let us
  praised our lord Jesus for those days
  we waiting for,I agree from your standing point,but on her next album
  she goon come up with deep understanding &she goon shake it up
  again for all those they don't like the
  true words,keep it up awesome job be
  blessed zerfe .don't look back,just starched for wards for get the past it's
  already gone.by the bete pawlos @Dallas

  ReplyDelete

 24. እኔ የምለው ማስተዋል እንዴት አቃተን መናፍቃን እኮ የያዙት ማተራመስ ነው መዝሙሩ ውስጥ ኢየሱስ የሚል ስም ካለ የሄ የኛ ነው የማርያም የቅዱሳን ከተዘመረ ደግሞ የነሱ ነው ትላላቸችሁ ክርስቲያን ማለት በራሱ በኢያሱስ ክርስቶስ ደም የተመሰረተ ነው ስለፈጠራችሁ ልጆቹን ልታስጠሉ ከሆነ የዚህን ጸሁፍ ጸሐፊንም ሌላ ፈልግ ማስተማሪያ እንጂ ማከፋፈያ አትፍጠር ልጆቹ በጥንካሬያቸው ሁሉንም አሸንፈዋል
  እናንተንም በእናንተ ተመርተው የተታለሉትን በግፍም ሰውንን ያሳደዱትን ወደ ጥሩ አእምሮዋቸው ይመልሳቸው ተሳዳጆቹንም እግዚያብሄር ያገልግሎት ዘመናቸውን ያርዝመው ታላቁን የአለም ፈተና አሸንፈዋል ከዚህ በላይ ምንም አይመጣም በጓደኛ ሳቀር ክህደት የደረሰባቸው ነበሩና፡፡
  ወሬኞች መናፍቅ ነው ሳይወገዝ ተወገዘ ትናንት እዚህ መናፍቅ ጉባዬ ታየ የሚሉ የሚገርም ነው አምላክን በእውነትና በሀቅ አገለግላለሁ በሚል ነው የስም ማጥፋት የተደረገባቸው ምስማርና ክርስቲያን ሲመቱት ይጠነክራል ነውና በርቱልን ወሬኛ ከወሬው አያልፍም ግን ግን ተጠንቀቁ እንጂ ቂም አትያዙ የሞተልንን ጌታ ተመልከቱ እግዚያብሄር ለኛ ለምእመናን አስተዋይ ልብና አእምሮ ይስጠን አሜን!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Does not matter whether you called Yourself a christian,or others menafkan .True christian is the one who Knows the commandments of Jesus Christ and obey them.(read Matthew ch 5) you will Know where exactly what christianity is God bless You!!

   Delete
  2. Ere makim sile Eyesus sayihon sile kirstos mezemer jemiroal!

   Delete
 25. Makim sile Eyesus sayihon sile kirstos mezemer jemirual temesigen naw!

  ReplyDelete
 26. Yzerfia mezmur medritun becha aydelem yatelekelekew; yenantenem manenet agltual. 'Meswatem akerabe tekebayem hune' yemelew tekekelega ye orthodox tewhedo emenet megelech new. Mekneyatum Eyesus bemewl segawiw yemeyastarkew kerasum gar chemer neber engi keabe ena kemenfeskedus gar becha aydelem. Enante endalchewt kehun gen zarim yamaledal lenel new ¡ yeh degmo ye protestant doctrin new. Ye tewahdon mester yazabal. Yeh degmo hulet bahri yemilewn yametal. Selezeh abaselamawch manachew? Bezeh aquamachew protestant eng orthodox tewhedo aydelachhum!....

  ReplyDelete
 27. 1. ቅ/ያሬድን ከጠቀሳችሁ አይቀር “ሰዐሊ ለነ ማርያም ይክስት ለነ መንግስቶ/ሰናይቶ….”(ማርያም ሆይ መንግስቱን/ቸርነቱን ይገልጥልን ዘንድ ለምኝልን….) የሚለውን በ2ኛ መደብ የቀረበ የያሬድን የነሀሴ ኪ/ምህረት ድጉዋስ ለምን ዘለላችሁት??
  2. የመምህር ፀሀይን ‘የአብርሀም አምላክ….’ ካነሳችሁ
  “ድንግል እመቤቴ የአምላክ እናት፣
  አንቺን የፈጠረ ይክበር መለኮት፡፡
  ድንግል ዘመሩልሽ መላእክት በዜማ፣
  ባንቺ ላይ ስላለ የመለኮት ግርማ ፡፡”……ስለሚሉ በ2ኛ መደብ ለእመቤታችን የተደረሱ መዝሙሮቻቸውስ???
  3. “ብዙ ነቢያት የናፈቁትን ፀሀይ የወለድሽ፣
  የምስራቅ ደጃፍ አማላጅቱ ድንግል አንቺ ነሽ፡፡….” የሚል ስንኝ ስላለው ‘ጸጋን የተመላሽ’ በሚል ርእስ በ2ኛ መደብ ለድንግል የተዘመረ የዘማሪት ዘርፌ መዝሙርስ??
  4. ከተቀበላችሁ ሁሉንም መቀበል እንጅ ቆንጽላችሁ ለራሳችሁ የሚመቻችሁን ብቻ በመውሰድ “ሲሞቅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ” አይነት አካሄድ ወይም ፈረንጆች እንደሚሉት double standard መጠቀም አግባብ ካለመሆኑም በላይ ግለሰቦቹንም ያልሆኑትን እንደሆኑ ሚያስመስል ነው፡፡
  5. ስለመንፈስቅዱስ መዘንጋት ያላችሁት እውነትነት ያለው ይመስላል፡፡ ግን ደግሞ በየእለቱ “ፈኑ(ላክልን) ጸጋ መንፈስቅዱስ” እያልን በቅዳሴ እንደምናነሳውና በስላሴ ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከአብና ከወልድ ጋር ስሙ እንደሚጠራ አስተውሉ!!!ለስላሴ በሚቀርቡ የነይልማ፣የነምንዳየ….መዝሙራትም የመንፈስ ቅዱስ ስም እየተጠራ ይዘመራል፡፡6 ኪሎ ማርቆስ ቤ/ክርስቲያንም ለጰራቅሊጦስ የመንፈስቅዱስ ንግስ እንዳለ አውቃለሁ!!!በነገራችን ላይ ብዙ የፕሮቴስታንት መዝሙራትን ሰምቻለሁ፡፡ ግን አንዳቸውም ስለ አብ እና ስለ መንፈስቅዱስ ሲዘምሩ አልሰማም፡፡ለነገሩ ፕሮቴስታንቶች ‘ጌታ ሆይ….ጌታ ሆይ…..’ከማለት ውጭ ስለነገረ-መለኮት ያላቸው እውቀት እምብዛም አይመስለኝም፡፡ ጥንት የሊቃውንት የእውቀት መመዘኛ የሆነው ሚስጥረ-ስላሴ የጌታን ስም የጠራ ሁሉ በጅምላ ይድናል በማለት ሃይማኖት ያለምግባር ሙት እንደሆነ የጻፈውን የሐዋርያው ያዕቆብ መልእክት ዘለው ዓለም በስም ጥሪ ብቻ እንደሚድን ለሚያስተምሩ ዘመናውያን ያን ያህል የሚስብ ባይሆን አይገርምም!!!ለማንኛውም እኛ ልጆቻችንን በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ የምናስጠምቅ ኦርቶዶክሳውያን ከዚህም በላይ ለመንፈስቅዱስ ልንዘምር እንደሚገባ አምናለሁ!!!

  ReplyDelete
 28. enie eko tru medrek meslogn nebere gena sayew.sewoch wstachew yeminegrachewn bcha hasab yemiichohubet yemiyanbuwarqubet mehonun gena haun teredahut.new maletachihun tewuna melkamnetn bcha adrgubet.yesewn hasab yalemedegef mebt enji lk aydelehm blo malet tegebi aydelem antem yerashn menged newna yemtketelew yhe geography weym hisab tmhrt aydelem.qalatn eyesenetateqachihu lehodu endadere tebeqa athunu.rasachihu lemaseb enji letsegur mabqeya bcha ayhun.thanx

  ReplyDelete
 29. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ይህ ደግሞ የፕሮቴስታንት ዶግማ ነው , ወይም ትክክለኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ" ,does not save you the true is what the bible say about Jesus Christ please read Hebreu 6 :20-25. and be informed and be blessed in Jesus Christe name

   Delete
 30. I think they are protestant. That is why they did not say any thing sele hawassa erk.it was big day ...but we did not read any thing about hawassa on this blog.yenebegashawon metark aba selama web site ayfelegewom malet new becos tehadso endihonu selemifelg .....just like mk.

  ReplyDelete
 31. ምድረ መናፍቅ ሁላ ተሰብስሽ ጉዳዩን የቤተክርስቲያን ሳይሆን የአንድ ማኅበር ጉዳይ ለማድረግ ትጥሪያለሽ፡፡ የቀበሮ ባህታዊ

  ReplyDelete
  Replies
  1. do u know wt menafek is ?????? menalbat raseh endathon .

   Delete
 32. It's not ye betekrstiyan guday its ye mahber ...you know why....???? Betekrstiyan selalawegezech....steramashu maheber yeyu endehon hulachenm eyegeban new.egziabher yehn yesytan mahber yebten

  ReplyDelete
 33. OOOh!!! the wolf in the name of Aba Selama, it is my first time to visit your website. Now I understood what you are doing in the name of Orthodox Thewahedo, we know you very well, since our Almighty God Jesus Christ already warned us about you long ago Matthew 7:15-16. Before opening your unknowledgeable mouth just go and learn about Jesus Christ in Thewahedo, then if you are human I am sure you will repent and start a life of Christian practically not in your lips, acts and songs..etc..
  I am sure you are one of THOSE who have allergy for practical Christianity, you call the respected name of our Almighty Jesus unnecessarily many times a day but your heart is very far from him...why you're jealous when we praise saints, don't you know that Almighty Jesus said to his saint disciples (kidusan hawariyat) John 14:12 "Very truly I tell you, whoever believes in me will do the works I have been doing, and they will do even greater things than these" do you read the power and faith Almighty Jesus gave to his Saints, do you have such a very little faith in you, I know you will say yes in you lip but not in your heart b/c you can't do any practical work Almighty Jesus or his Saint did. Do you walk on sea? Can you say to this mountain, 'Move from here to there,'? you see you do not have faith as small as a mustard seed, but your mouth and lips are long and unknowledgeable, we know you from your fruit, you don't like Saint and you think Orthodox Theowedo do not praise Almighty Jesus. Every single action in our church is directly related to Almighty Jesus, we know him from our childhood, that is why the whole world come to Ethiopia to learn from the undivided ancient ONLY one True Church of God. Our Holy Saints are the ancient Christian who do not change the rule of God for sake of human development, we still are very happy the way Kidus King Dawit song to God with very old instrument like Begena, Tsenatsel, kebero etc... the same instrument Begena and song like Kenie zemarie mention by Yonannes raye 5 (the Revelation 5).
  We are not interested on your Gitar, Jass..etc and the way you act while singing like those in the world singer, even you act more rolling on the ground and shouting like animal, I saw myself I don't need any witness you are form your Father Evil, may be you know already you're engulf by evil eye or some of you are innocent and think you are following Jesus... pl's weak up and see things before it is too late for you!. For those of you who do these evil act in our church knowingly, what are you doing in our Holy Church who follow the footsteps of Almighty Jesus. Please go and teach the protestant churches in Europe and else ware such as The United Church of Christ, who are the first mainstream Protestant Christian church to fully support same-sex marriage (homosexuals) and perform marriage ceremonies in their Church ,,, lotu Sebat... those of you who follow this web site your final destination behind the song will be like this, yes this church do this in the name of Almighty Jesus.. if you don't believe go and Google the information on internet.
  Therefore, for those who are true believers of Tewahedo should stay far away from these evil website who tradeoff on the name of Almighty Jesus, they're not from God, they from their father cold liar satan...evil

  ReplyDelete
  Replies
  1. Friend, you have so much hate in your heart

   Delete
 34. In the name of the Father the Son and the Holy Spirit One God Amen!
  OOOh!!! the wolf in sheep closes, here you are again in the name of Orthodox Thewahedo, we know you very well, since our Almighty God Jesus Christ already warned us about you long ago Matthew 7:15-16. Before opening your unknowledgeable mouth just go and learn about Jesus Christ in Thewahedo, then if you are human I am sure you will repent and start a life of Christian practically not in your lips, acts and songs.
  I am sure you are one of THOSE who have allergy for practical Christianity, you call the respected name of our Almighty Jesus unnecessarily many times a day but your heart is very far from him...why you're jealous when praise saints, don't you know that Almighty Jesus said to his saint disciples (kidusan hawariyat) John 14:12 "Very truly I tell you, whoever believes in me will do the works I have been doing, and they will do even greater things than these" do you read the power and faith Almighty Jesus gave to his Saints, do you have such a very little faith in you, I know you will say yes in you lip but not in your heart b/c you can't do any practical work Almighty Jesus or his Saint did. Do you walk on sea? Can you say to this mountain, 'Move from here to there,'? you see you do not have faith as small as a mustard seed, but your mouth and lips are long and unknowledgeable, we know you from your fruit, you don't like Saint and you think Orthodox Theowedo do not praise Almighty Jesus. Every single action in our church is directly related to Almighty Jesus, we know him from our childhood, that is why the whole world come to Ethiopia to learn from the undivided ancient ONLY one True Church of God. Our Holy Saints are the ancient Christian who do not change the rule of God for sake of human development, we still are very happy the way Kidus King Dawit song to God with very old instrument like Begena, Tsenatsel, kebero etc... the same instrument Begena and song like Kenie zemarie mention by Yonannes raye 5 (the Revelation 5).
  We are not interested on your Gitar, Jass..etc and the way you act while singing like those in the world singer, even you act more rolling on the ground and shouting like animal, I saw myself I don't need any witness you are form your Father Evil, may be you know already you're engulf by evil eye or some of you are innocent and think you are following Jesus... pl's weak up and see things before it is too late for you!. For those of you who do these evil act in our church knowingly, what are you doing in our Holy Church who follow the footsteps of Almighty Jesus. Please go and teach the protestant churches in Europe and else ware such as The United Church of Christ, who are the first mainstream Protestant Christian church to fully support same-sex marriage (homosexuals) and perform marriage ceremonies in their Church ,,, lotu Sebat... those of you who follow this web site your final destination behind the song will be like this, yes this church do this in the name of Almighty Jesus.. if you don't believe go and Google the information on internet.
  Therefore, for those who are true believers of Tewahedo should stay far away from these evil website who tradeoff on the name of Almighty Jesus, they're not from God, they from their father cold liar satan...evil

  ReplyDelete
 35. እመቤታችን ጌታን ይዛ ወደ ምድረ-ግብጽ መሰደዱ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ሀቅ ነው. ግብጽን ከእስራኤል የሚያገናኘው የሲና በረሀ በአሸዋ የተሸፈነ መሁኑም ጂኦግራፊያዊ ሀቅ ነው. እናቶቻችን ይህን ሀቅ ይዘው “ማርያም ወረደች አሸዋ ለአሸዋ” ቢሉ ከየትኛው መጽሀፍ ቅዱስ ህግ ተጋጩ?? ከየትኛው አለማዊ እውቀትስ ተጣረሱ?? ዝምብሎ ማጣጣል ለማንም አይበጅም!! እናስተውል!!!

  ReplyDelete
 36. ኦርቶዶክስ መሰረትዋ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ የታወቀ ስለሱ ሲዘመር ለምን እነታመሳለን መናፍቃንስ ለምን ኦርቶዶክስ ስለኢየሱስ አስተምራና ዘምራ እንደማታውቅ ለምን እውነቱን መቀበል አቃተን ልጆቹን ለማዋከብ ለምን እንጥራለን አረ እባካችሁ መንፈሳችሁን ለጠብና ለክርክር አታነሳሱ ጌታ ማስተዋልን ለሁላችንም ይስጠን!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እዉነቱን እኮ ልባኣችእሁ ያውቀዋልእ ትናንእትእ እመሃልሆናኣችሁ ትእፈተፍቱ ያነበራችሁ የእናት ቅድስ ቤተክርስቲያን ጡትነካኾች እኮ ናችሁ የምትዘላብዱ!!!!

   Delete
 37. እዉነቱን እኮ ልባኣችእሁ ያውቀዋልእ ትናንእትእ እመሃልሆናኣችሁ ትእፈተፍቱ ያነበራችሁ የእናት ቅድስ ቤተክርስቲያን ጡትነካኾች እኮ ናችሁ የምትዘላብዱ!!!!

  ReplyDelete
 38. እዉነቱን እኮ ልባኣችእሁ ያውቀዋልእ ትናንእትእ እመሃልሆናኣችሁ ትእፈተፍቱ ያነበራችሁ የእናት ቅድስ ቤተክርስቲያን ጡትነካኾች እኮ ናችሁ የምትዘላብዱ!!!!

  ReplyDelete
 39. በጣም የምታበሳጩ ናችሁ ኦርቶዶክስ ስለክርስቶስ አታስተምርም አትዘምርም ጌታን በማህፀኖ ለተሸከመች እናት ግብፅ ለግብ ይዛ ለተከርተተች እናት አይዘመርም ነው የምትሉት አስተውሉ ሁሌ ለመኮነን አትተኩሉ ድንግል እኮ የመስቀል ስር ስጦታ ፍቅር እናት ናት ማርያም ሀሌ ከፍ ከፍ እናደርግሻለን

  ReplyDelete