Friday, December 20, 2013

አባ እስጢፋ እና ማቅ “በሽርክና” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ለመቆጣጠር ያረቀቁት ደንብ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡

በሙስና ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ ተዘፍቀው የሚገኙት ባለትዳሩና ባለዕቁባቱ “ጳጳስ” አባ እስጢፋ ከጥቅም ወዳጃቸው ከማቅ ጋር በፈጠሩት የእከክልኝ ልከክልህ ሽርካና ተቋማዊ ለውጥ አመጣለሁ በሚል በማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች የተረቀቀውንና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኙ አድባራትና ገዳማት ተግባራዊ ይሆናል ብለው የቋመጡለትን “ጥናታዊ” ያሉትን የለውጥ መዋቅር ለውይይት ባቀረቡ ቁጥር ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለማጥፋት ተብሎ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከአራት አህጉረ ስብከት ወደ አንድ ሀገረ ስብከት መጠቃለሉና በአንድ ሊቀጳጳስ እንዲመራ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይህ ሀገረስብከት ከምንጊዜውም በበለጠ በሙስና ጨቅይቶአል፡፡ ከሊቀጳጳሱ ከአቡነ እስጢፋ ጀምሮ እስከ ልዩ ልዩ የመምሪያ ኃላፊዎች የሙስናን ደረጃ በእጅጉ አሻቅበውታል፡፡ ለምሳሌ ያህል ብናነሳ እንኳን አቡነ እስጢፋ የጅማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን አሠራለሁ በሚል ሰበብ ከእያንዳንዱ ደብር ከብር አንድ መቶ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ያለምንም ሕጋዊ ደረሰኝ በእጃቸው እየተቀበሉ ነው፡፡ ገንዘብ ያልሰጡአቸው አድባራት ቢኖሩ እንኳን “ሻይ ሳያጠጡኝ” እያሉ በግልጽ በማስጠንቀቅ ይቀበሉአቸዋል፡፡ እኚህ ሙሰኛ ጳጳስ ስለሙስና የመናገር ድፍረት በማጣታቸው ሙሰኞችን በድፍረት የመናገር ብቃት ካለማግኘታቸውም በላይ ቤተክርስቲያንን ወደ ሌላ ታሪካዊ ቀውስ እየመሯት ነው ያሉት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የለውጥ መዋቅሩን ሠርቻለሁ የሚለው ማቅ በአባ እስጢፋም ሆነ በሌሎች ሙሰኞች ላይ ቃል ትንፍሽ አላለም፡፡ በተለይ ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው ብዙዎች ያለቀሱበት የአቶ ዮናስን ዓይን ያወጣና በተጨባጭ በሲዲ ጭምር የተደገፈ ሙስናዊ ማስረጃ ቀርቦላቸው ሳለ አባ እስጢፋም ሆኑ ሸሪካቸው ማቅ እስካሁን ምንም አለማለታቸውና ዮናስ ከቦታው ሳይነሳ ዝርፊያውን አጠናክሮ መቀጠሉ፣ ጉዳዩን የቤተክርስቲያንን አስተዳደር የማስተካከል ሳይሆን የሙስናውን መንገድ ይበልጥ ውስብስብ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ አስመስሎታል፡፡ 
 

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሀገረስብከት በየሣምንቱ ቅዳሜና እሁድ እየተደረገ ያለው ስብሰባ የአዲስ አበባ አስተዳዳሪዎችንና ካህናትን ልዩ ልዩ ሠራተኞችን ከጫፍ እስከ ጫፍ እያስቆጣ ከመገኘቱም በላይ ቤተክርስቲኗን ሙሉ ለሙሉ ለመውረስ ለ2ዐ ዓመታት በስውርም ይሁን በግልጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ከእኚህ አቡነ ጐን ሆኖ እኩይ ስራውን ለመፈፀም እየተጋ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አቡነ ጳውሎስ ከአረፉ በኋላ የማኅበሩ ፈንጠዝያ ትልቅ ነበር የሚለው ቃል አይገልፀውም፡፡

የጳጳሳቱን ደካማ ጎን እየተከታተለ የሚያጠምደውና ውደቀታቸውን የሚዘግበው እኩይ ፍልስጣ የሆነው ይኸው ማኅበር የአቡነ እስጢፋ ዝርክርክ ሕይወት በእጁ እንደወደቀለት ለራሳቸው “ከእኔ ጋር ካልሠሩ ጉድ አወጣለሁ” ብሎ ያስጠነቀቃቸው መሆኑን የቅርብ አማካሪዎቻቸው ይናገራሉ፡፡ በሌላም አቅጣጫ ይህን መዋቅር በእርስዎ ዘመን ተግባራዊ ቢያደርጉ ትልቅ ስምና ዝና ያተርፉበታል በሚል ውዳሴ ከንቱም ደልሏቸዋል ነው የሚባለው፡፡ ባለብዙ ሚስትና ባለብዙ ልጅ ናቸው እየተባሉ የሚነገርላቸው አቡነ እስጢፋ በዚህ እኩይ ማህበር ሥር ከወደቁ በኋላ ማምለጥም ሆነ ወደ ኋላ ማለት ስለተቸገሩ ባይወዱም የማህበሩ ጉዳይ አስፈፃሚ መሆን ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያንንም ለታሪካዊ ቀውስ እየዳረጓት ነው፡፡

በሰባቱ ወረዳዎች የሚገኙ አስተዳዳሪዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች እስካሁን ያገለገሉትን አገልግሎትና መንፈሳዊ ሙያቸውን ከግምት ሳያስገቡ በቤተ ክርስቲያን ላይ ምንም ዓይነት መብት እንዳይኖራቸውና ተቀጣሪ ሆነው እንዲሠሩ፣ የአዲስ አበባ አድባራት የገንዘብ ምንጭ ስለሆኑ በገንዘባቸው የማቅ አባላት በቦርድ እንዲያዝዙበት፣ የአድባራት ሰባክያነ ወንጌል ወደ ጐን ተብለው የማቅ ሰባክያን እንደፈለጉ እንዲያዝዙና እንዲናዝዙ ባጠቃላይ ካህናት (የቤተክርስቲያን አገልጋዮች) ተቀጣሪ እንጂ የመንጋው ጠባቂ እንዳይሆኑ የሚያደርገውን የማህበሩን ዕቅድና አላማ ለማስፈፀም አቡኑ እንቅልፍ አጥተዋል፡፡ ማቅም በበኩሉ የመከር ጊዜ አሁን እንደሆነ ሁሉ ያለ የሌለ አቅሙን እየተጠቀመ ነው፡፡ ሙስናን ለመዋጋት በሚል ሰበብ የራሱን ሰዎች ሕግ አርቃቂ ሕግ አጽዳቂና ሕግ ተርጓሚና ሕግ አስፈጻሚ አድርጎ ተንኮሉን ለማስፈፀም እየተጋ ነው፡፡

ማቅ ከጎኑ ካሰለፋቸው መካከል ብናንሳ እንኳን አቶ ታደሰ አሰፋ መኖሪያው በሰሚት የሆነ የዚህ ስርዓት ዋና አስፈፃሚ የአቡነ እስጢፋ የአገር ልጅ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ ግለሰብ እንኳን የቤተክርስቲያንን ችግር ሊፈታ ራሱ የቤተክርስቲያን ችግር ስለመሆኑ በሚኖርበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ ግለሰብ በሰሚት ኪዳነምህረት በሰበካ ጉባኤ አባልነት ተመርጦ ሳለ ከተመረጠበት ጊዜ ጀምሮ በሕዝበ ክርስቲያኑ መካከል ዘረኝነትን በካህናቱና በልዩ ልዩ ሠራተኞች ዘንድም መከፋፈልን እያወጀ ያች ቤተክርስቲያን እስካሁን ድረስ በነገር እየታመሰች ትገኛለች፡፡ ለምሳሌ ብናነሳ እንኳን መላከገነት አባ ሢራክ የተባሉትን የደብሩን አስተዳዳሪና ሊቀትጉሃን አበጀ የተባለውን ፀሓፊ ስም በማጥፋት ክስ ተመስርቶበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ታስሮ የነበረ ሲሆን በይቅርታና በማስጠንቀቂያ ከእስር ተፈትቷል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሰበካ ጉባኤ አባልነቱ ከአንዴም ሁለቴ የታገደው ግለሰብ በማቅና በሊቀጳጳስ ተሾሞ “የሙስና ታጋይ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የቤተክርስቲያኗን መዋቅር ለመናድ ከክፉው ማኅበር ከማቅ ጋር እየዶለተም ይገኛል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አጀንዳዎችን ግልጽ ሳያደርጉ ስብሰባ የጠሩትና ረቂቅ ሕጉን በደፈናው ደግፉ እያሉ ያሉትን አባ እስጢፋን ለምሳሌ በቅርቡ ሕዳር 28 እና 29/2006 ዓ.ም. የሰበሰቡአቸው ተሰብሳቢዎች በጥያቄ አፋጠዋቸዋል፡፡ ከተሰብሳቢዎቹ በዋናነት አጀንዳዎች ግልጽ ሆኖ ይቅረብልን የሚል ጥያቄ ቢነሳም አባ እስጢፋ ጥያቄውን መመለስ ተስኖአቸው ታይቷል፡፡ እስካሁን ክፉ ሥራውን ደብቆ የኖረውና ከጀርባ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ማቅ አሁን ተንኮሉ እየተራቆተና ዕርቃኑን እየቀረ ነው፡፡ ተሰብሳቢዎቹ፡-
·        ይህ ሐሳብ የማቅ ነው
·        ለቤተክርስቲያን ማን ይቀርባል? እኛ ወይስ ማቅ?
·        ለፖለቲከኞች ቤተክርስቲያንን አሳልፈን አንሰጥም
·        ማቅ አክራሪ እንጂ መንፈሳዊ ተቋም አይደለም፡፡
·        ጩኸታችንን መንግስት ይስማልን
·        አክራሪው ማቅ በሥራችን ጣልቃ እየገባብን ነውና መንግስት ጣልቃ ይግባልን
የሚሉትንና ሌሎችንም ከማስተጋባታቸው በላይ ስብሰባውን ረጋግጠው የወጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ የሲኤምሲ ሚካኤል አስተዳዳሪ፣ ሊቀ ሊቃውንት አባ ዕዝራ የየካ ሚካኤል አስተዳዳሪና ሌሎችም ለዚህ ተቃውሞ ዋነኛ ምክንያታቸው ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን ሊወርሳት አቅዷል ማለታቸው ነው፡፡ በተለይ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ “አባ አስጢፋኖስ እኛ በአጠገብዎ ሰው ያለ መስሎን ነበር፤ ለካ ሰው የልዎትም፤ የቤተክርስቲያን ለውጥ ካስፈለገ ማህበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን ከቤተክህነት ከምእመናን ከሊቃውንትና ከሌሎችም ከሚመለከታቸው አካላት ተውጣጥቶ ነው ሕጉ ሊረቅ የሚገባው” ብለዋል፡፡ የኮተቤ ገብርኤል ዋና ጸሐፊም በበኩላቸው “ምን ተፈልጎ ነው በአንድ አቅጣጫ (በማቅ በኩል) ሕጉ የሚታየው? ሕጉን አርቅቀናል እናሰለጥናለን የሚሉ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ሥነምግባራቸውን ጭምር እናውቅ የለም ወይ?” ሲሉ ተችተዋል፡፡

በሌሎቹም የስብሰባ ቀናት ከስብሰባው አዘጋጆች በዋናነት ሲወራ የዋለው የቀረበውን የለውጥ መዋቅር በደፈናው ተቀበሉት የሚል ሲሆን፣ በተለይ አባ አስጢፋ ከመጀመሪያው በትእዛዝ መልክ መቀበል አለባችሁ ከሚለው አቀራረባቸው ለስለስ ባለ መልኩ “እኔ እናንተን የሚጎዳ ነገር እንዲወጣ አደርጋለሁ?” ወደሚል ልምምጥ መግባታቸው ሲታወቅ፣ ዞሮ ዞሮ ግን በትእዛዝም ሆነ በልምምጥ ሕጉን መቀበል አለባችሁ እያሉ ነው፡፡ በካህናቱ በኩል ደግሞ ሳንወያይና ሳንመክርበት አንቀበልም የሚል ጠንካራ አቋም ይዘዋል፡፡ ሊቀጳጳሱን ሳያፍሩ በድፍረት እየተናገሩና ለመብታቸው እየተከራከሩ የሚገኙ ካህናት ተነሥተዋል፡፡

መጀመሪያ ላይ በተለይ አባ እስጢፋ እያንዳንዱ ካህን ለሦስት ወር ጋምቤላ ሄዶ ያገለግላል ሲሉ እንዳልነበር፣ ሰሞኑን ግን የተቃውሞውን ማየል ተከትሎ ኧረ እኔ እንደዚያ አላልኩም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ይህም በካህናቱ በኩል ይህን ሐሳብ ለመቃወም ምክንያት የሆነው መዋቅር የተባለው ለቤተክርስቲያን በማሰብ የተዘጋጀ አይደለም፤ እንዲያ ቢሆን ኖሮ ግን እጅግ በርካታ ደጀጠኚዎች ብዙ ዓመት ተምረው ያለስራና የሚያደምጣቸው ሳይኖር በየቀኑ የሀገረስብከቱን ደጅ አጣብበው ሳለ እነርሱ ተቀጥረው የአገልጋይ እጥረት ወዳለበት እንዲሰማሩ ማድረግ በተቻለ ነበር፡፡ በአዲስ አበባ እያገለሉ ያሉትን ከቦታቸው ለማፈናቀል ማሰባቸው ግን ከበስተጀርባ ተንኮል ያለበት ነው እንዲሉ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ አጋጣሚም የማቅ ድብቅ አጀንዳና ለካህናት ያለውን ንቀትና ጥላቻ ገሃድ ያወጣ ነው ተብሎለታል፡፡ የዚህ አንዱ ማሳያ በህግ ማርቀቁ ሂደት ብዙ ሊቃውንት ላሏት ቤተክርስቲያን ሊቃውንቱን ሳያካትት ማቅ ሕግ ያወጣላት ዘንድ የማይመጥን መሆኑ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ቃለ ዐዋዲው በሥራ ላይ እያለና እርሱ ወደጎን ገሸሽ በማድረግ አዲስ ሕግ ለማርቀቅ መሞከሩ ማቅ ቤተ ክርስቲያኗን ለመቆጣጠር የያዘውን ዕቅድ ከግቡ ለማድረስ ሊጠቀምበት ፈልጎ መሆኑን አያያዙ ያስታውቃል፡፡ የዚህ አንደኛ ማሳያ አርቅቄያለሁ የሚለውን ሕግ ለካህናቱ ወይይት ሳያቀርብ በጉዳይ አስፈጻሚው በአባ እስጢፋ በኩል ዝም ብላችሁ ተቀበሉት ዓይነት ግፊት እያደረገ መሆኑ ነው፡፡ የማቅ ብሎግ ሐራም ሕጉን ተቀበሉት ከማለት ባለፈ ይህን አካሄድ የተቃወሙትን ልዩ ልዩ ስም እየሰጠች ስትሰድባቸው ነው የሰነበተችው፡፡

በአንድ በኩል ከማቅ ጋር ተሰልፈዋል ተብለው ይታሙ የነበሩትና በሌላ በኩል ግን በሀገረ ስብከቱ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ የነበሩት ንቡረእድ አባ ገብረ ማርያም ሥራ አስኪያጅ ይሆናሉ ተብሎ በአንዳንዶች የተጠበቀ ቢሆንም፣ አባ እስጢፋን ጨምሮ ብዙዎቹ ጳጳሳት ንቡረ እዱ አያዘርፉንም፣ እኛ የምንልካቸውን ልጆቻችንን ጥሩ ገቢ ባለው ደብር ላይ አይቀጥሩልንም በሚል ወደስራ አስኪያጅነት እንዲመጡ አለመፈለጋቸውን ሲያንጸባርቁ እንደነበር ምንጮቻችን የተናገሩ ሲሆን፣ (በዚህ ረገድ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የራሳቸውን ሰው ግቢ ገብርኤል ጠቅላላ አገልግሎት አድርገው ያስመደቡ ሲሆን፣ ዋና ጸሐፊው አቡነ ሉቃስም ደ/ን ሀብታሙ የተባለ ዲያቆን ቅድስት ማርያም እንዲመደብ አድርገዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በጳጳሳት በኩል ስለመጡ ጉቦም ሳይጠየቁ በቀጥታ ነው የተቀጠሩት) አባ እስጢፋም ንቡረ እድ ገብረ ማርያምን ማምጣት የተጀመረውን ሙስናዊ አካሄድ ማደናቀፍ ስለሚሆንባቸው ከዚህ ቀደም እርሳቸው ሥራአስኪያጅ በነበሩ ጊዜ ምክትላቸው የነበሩትንና አብረው ሲዘርፉ ነበር የሚባሉትን ቀሲስ በላይን ወደ ሥራ አስኪያጅነት ያመጡበት መንገድ ፖለቲካዊ መልክ እንዲኖረው ማድረጋቸው በብዙዎች ዘንድ ተአማኒነቱ አጠራጥሯል፡፡ አባ እስጢፋ እንዳወሩትና እንዳስወሩት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አባዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ኩማ ድሪባ “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የኦሮሞ ተወላጅ ነው ሥራ አስኪያጅ መሆን ያለበት” ብለዉኛል በማለት የመንግስት ጣልቃ ገብነት በጉዳዩ ላይ እንዳለ ለማስመሰል ሞክረዋል፡፡ ይህ ግን ለብዙዎች የማይዋጥ ነው የሆነው፡፡ ቀሲስ በላይ ዘመናዊ ትምህርትም የተማሩ በመሆናቸው በአግባቡ ከሠሩ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ መሆናቸውን ብዙዎች ቢያምኑም እርሳቸውን የፖለቲካ ተሿሚ አስመስሎ ማቅረብ ካህናቱን ለማስፈራራትና እንዲገዙ ለማድረግ፣ እንዲሁም ንቡረ እድ ገብረ ማርያም ወደስራ አስኪያጅነት እንዳይመለሱ ሲሉ የዘየዱት መላ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡


የአባ እስጢፋንና የማቅን ሸርክና እየተቃወሙ ያሉ ካህናት መንግሥት ጉዳዩ የሃይማኖት ነው በሚል ቸል እንዳይለው እየወተወቱ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ቤተክርስቲያን የሕግ መገኛና ለሌላው የምትተርፍ ሆና ሳለ ሊቃውንቷ ያልመከሩበትና ማቅ ለብቻው ያረቀቀው ህግ ተብዬ ሰነድ ለቤተክርስቲያን የማይበጅና ማቅ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲንሰራፋና አክራሪነትን በተቋም ደረጃ እንዲያጠናክር በር የሚከፍት መሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡ በመንግስት በኩል አክራሪ የተባለውና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ መለስ ዜናዊ ለአልሻባብ ምሳሌ መሆኑ የተነገረለት ማቅ በምን ሞራል ነው ለቤተክርስቲያን ሕግ አረቃለሁ የሚለው ሲሉ ክፉኛ እየተቃወሙት ይገኛሉ፡፡ ካህናቱን ይበልጥ እያስቆጣ ያለውም ማቅ “ካህናቶቻችን መስከርና መሳከር እንጂ ምንም አያውቁም ስለዚህ የሚመሩበትን ሕግ እኔ አረቅላቸዋለሁ፤ እነርሱ መቀበል ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው” በሚል ምክንያት በተላላኪው በአባ እስጢፋ በኩል እንዲቀበሉ አድርጉ ሲል ቀጭን ትእዛዝ ማስተላለፉ ነው፡፡ በካህናቱና በማቅ መካከል እየተፈጠረ ያለው ክፍተት ወደፊት በቤተክርስቲያን ውስጥ የማይበርድ ግጭት እንዳያስከትል ተሠግቷል፡፡    

18 comments:

 1. Tekateıachihu aydeı!! Ay menafikan...

  ReplyDelete
 2. wow, this is the right time to remove MK from our truth orthodox church. Let us stand together for our Orthodox church unit..........time is coming for MK to go hell or die..........Aba Selama, Pls keep continue to bring truth for us...........Lord God bless you !!!!!

  ReplyDelete
 3. ዘመኑን ያልዋጀውንና ጥራት የጎደለውን፣ ለሙስናና ብክነት የተጋለጠውን የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ አሠራርና ቁጥጥር ችግር ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተቀባይነትና ተጠያቂነት ባለው የፋይናንስ አያያዝ ሥርዐት ለመቅረፍና ለማድረቅ ያስችላል፤ በሚል በቀረበው የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ረቂቅ ላይ እንደተጠቀሰው÷ በማንኛውም መንገድ የተሰበሰበ ገቢ ገንዘብ ሕጋዊ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወዲያውኑ ሊቆረጥለት የሚገባ ሲኾን ይህም በዋናነት በካሽ ሬጅስትር ማሽን እንደሚከናወን ተመልክቷል፡፡

  ReplyDelete
 4. balemuya atinto betekrstiyan zemenawi aserar endinorat sltena mestet endi abesacheto yemiyatsefachew man mehonachewn yasayal........... musegna menafik melkam neger aywedim

  ReplyDelete
 5. minale wengel bitisebkulin ahunis ene ye enante teketay kehonku hulet amet honegn gin minim fire atahu neger bicha were bicha BEKAGN BYE BYE wede neberkubet temelshalhu BESTETET.

  ReplyDelete
 6. zarem aba selebawech ke selebinetachihu alewetachihum? tekewamiwoch yezerefutin eskimelisu bizu sewu liyakoselu yechilalu gin menigisitim betekiresitiyanim bekirib tasewegedachewalech....le manegnawum tesasetachihu enkua melekam awuru...

  ReplyDelete

 7. የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመሸጥ የሚታወቁት የ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባዮቹ ዋነኛ አስተባባሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ፣ በቅርቡ በ1.3 ሚልዮን ብር በገዙትና ለቻይና ተቋራጭ ባከራዩት ሲኖ ትራክ መኪና ብቻ በወር ብር 70,000 ገቢ ያገኛሉ፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ለውጥ ለማምጣት የተነሡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተንገላቱበት የግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም. ጥቃት የተሳተፉትና ሞዴል ፴ በማቃጠል የሚታወሱት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ፣ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች ጋራ ስልታዊ ግንኙነት መጀመራቸው የሚነገርላቸውና ለአፃዌ ኆኅትነት እንኳ ሳይበቁ በደ/ምሕረት ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እልቅና ለመሾም ‹‹መቶ ሺሕ ብር እከፍላለኹ›› በሚል ልጆቻቸውን ለረኀብ የዳረጉት መልአከ ብሥራት መልአከ አበባው (ብይዱ ይመር)ስ እነማን ናቸው?

  * * *

  የካህናቱን፣ የሊቃውንቱን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የምእመናን ተወካዮችን ከ92 – 97 በመቶ ድጋፍ ያረጋገጠው የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናታዊ ውይይት ዛሬ ይጠናቀቃል፤ የጥናቱን ትግበራ የሚቆጣጠር በአፈጻጸምም እየተከታተለ የሚያርምና የሚያስተካክል ራሱን የቻለ አካል እንዲቋቋም ተሳታፊዎቹ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡

  ‹‹ይህ መዋቅርና አደረጃጀት ስለ መታሰቡ፣ ቅንብር ስለ መደረጉ በቤቱ ስም አመሰግናለሁ፡፡ አባታችን የልማት አርበኛ ናቸው፡፡ በየመንደሩ ያለው አሉባልታ ይህ ነው አይባልም፤ እዚህ ስናየው ግን የተለየ ነው፡፡ የጥናት ዘገባው ቀጥሎ እንድናየው እንጂ ሁከት አያስፈልግም፡፡ ጀርባዬም ፊቴም አንድ ከኾነ በሕግ ለመተዳደር ምን ያስፈራኛል? አስቀድሞ ይህ እንዲህ ይኾናል እያሉ መደንበርስ ምን ያስመለክታል? ወጡም ሊጡም እያሉ ያሉት ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ነው ይህ ኹሉ ጭፋሮ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ለመጠበቅ ከፍተኛ ሓላፊነት ያለበት ቅ/ሲኖዶስ ይውጣ ያለውን ሕግ መደገፍ ተገቢ ነው!!›› /የደብር አስተዳዳሪ/

  ‹‹አንድ ድጓ ከዲግሪ ጋራ ይወዳደራል ካላችኹ መቼ ነው እውን ኾኖ የምናየው? እውን ይኾናል ወይ? አምስት እንትን የምንላቸው ካልኾኑ በቀር ይህን የሚቃወም አይኖርምና ቶሎ ይተግበር፡፡ ብፁዕ አባታችን ከዚህ የበለጠ ምን ይጠበቃል? ይሄ ነገር ቶሎ የማይተገበር ከኾነና ወደ ኋላ የምታዘገዩት ከኾነ የልብ ልብ እንዲያገኙ ታደርጓቸዋላችኹ፤ እናንተም ተጠያቂዎች ትኾናላችኹ፡፡›› /የመምህራን ተወካይ/

  ‹‹የማይነካው ተነካ፤ የዘመናት ጸሎቴ ነበር፤ ፍጻሜውም ዛሬ ዛሬ. . .ይለኛል፤ እንግዲህ ጸሎተ ስምዖንን ነው የምጸልየው፤ ጌታዬ የቤተ ክርስቲያንን መዳን አሳይተኸኛልና ባሪያኽን አሰናብተኝ እለዋለኹ፡፡›› /የምእመናን ተወካይ/

  ReplyDelete

 8. ዛሬ ዐርብ ታኅሣሥ ፲፩ – ፲፪ የሚካሄደውን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና የልደታ፣ አዲስ ከተማና ቂርቆስ ክፍላተ ከተማ አብያተ ክርስቲያን ልኡካን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት መስተንግዶ የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል እና የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፤ ከታኅሣሥ ፲፫ – ፲፬ የሚካሄደውንና የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት ደግሞ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ስፖንሰር ለማድረግ በየሰበካ ጉባኤያቸው ማስወሰናቸውንና የሀ/ስብከቱን ወጪ መጋራታቸውን ገልጸዋል፡፡

  ታኅሣሥ ፮ እና ፯ በኮልፌ ቀራንዮ፤ ታኅሣሥ ፬ እና ፭ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍላተ ከተማ አብያተ ክርስቲያን እንደ ቅደም ተከተላቸው የተካሄደው ጥናታዊ ውይይት÷ ከአሉባልታዎች ይልቅ ከቀረበው የጥናት ረቂቅ ይዘት ጋራ ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው፣ ለሰነዱ መዳበር ብቻ ሳይኾን የይዘት መስተካከልም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ገንቢና ሞያዊ እንደነበር ባለሞያዎቹ፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ እና አዘጋጅ ኮሚቴው ጥናታዊ ውይይቶቹ በተካሄዱባቸው ዕለታት በመደበኛነት ያደረጓቸው የውሎ ምዘናዎች/ግምገማዎች በጉልሕ ያመለክታሉ፡፡

  በክፍላተ ከተማው ልኡካን ከተነሡት ነጥቦች መካከል በሀ/ስብከቱ አድባራት፣ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የደረጃ መስፈርት ጥናት÷ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች ጋራ የተመጣጠነ የሰው ኃይል /በቁጥር፣ በክህሎት፣ በሞያና ልምድ/ እንዲያገኙ የሚጠቁመው ሐሳብ ይገኝበታል፡፡ ሐሳቡ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ያላቸውን ሀብት፣ ታሪክ፣ ንብረት፣ ገንዘብ በተሻለ ደረጃ ለመጠቀም የሚችሉበትን ኹኔታ ለማመላከትና መንፈሳዊ ቅናትን በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጥ ተነሣሽነትን በአገልጋዮች መካከል ማስፈን መኾኑ ተገልጧል፡፡

  በአሁኑ ወቅት አብዛኛዎቹ ገዳማትና አድባራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል ክምችት እንደያዙ የታመነበት በመኾኑ በጥናቱ መሠረት ገዳማቱና አድባራቱ ካሉበት ደረጃ ጋራ ተመጣጣኝ የኾነ የአገልጋይ ቁጥር በመደበኛነት ከያዙ በኋላ ቀሪዎቹን ሳያፈናቀሉ ለማስተዳደር የሚችሉባቸው አግባቦች/አማራጮች በጥናቱ ተቀምጠዋል፡፡ ከአግባቦቹ አንዱ፣ ከመደበኛው (ስታንዳርድ) የአገልጋይ ቁጥር የቀረውን አገልጋይ ጊዜያዊ ምደባ ሰጥቶ ደመወዛቸውና ጥቅማጥቅማቸው ሳይነካ የሰው ኃይል ወደሚፈልግባቸው አጥቢያዎች የሚንሸራሽበት ሥርዐት ነው፡፡

  ሌላው አማራጭ፣ አጥቢያዎች በራሳቸው አልያም ከሌሎች አጥቢያዎች፣ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት፣ ከሌሎች አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት ጋራ በልማት ተቋማት ማስፋፊያ ፖሊሲው መሠረት እየተቀናጁ በሚከፍቷቸው የልማት ተቋማት አንጻር ተገቢውን የክህሎት/ሞያዊ ሥልጠና በመስጠት ማሰማራት ነው፡፡ ከመደበኛ ቁጥር ውጭ የኾነው አገልጋይ በትርፍነት የሚቆየው ለረጅም ጊዜ ከኾነ ደግሞ ሲያገኘው የቆየው ደመወዝና ጥቅማጥቅም እንደተጠበቀለት በአዲስ አበባ ዙሪያ ይኹን በአህጉረ ስብከት የካህናት እጥረት ባለባቸው አብያተ ክርስቲያን አበል እየታሰበለት ለተወሰነ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥበት መንገድ ነው፡፡ የገጠሪቱን ቤተ ክርስቲያን ከማገልገልና የቅጥር ወጭን ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ ትርጉም ያለውን ይህን ሐሳብ የጥናታዊ ውይይቱ ተሳታፊዎች በሙሉ ልብ የደገፉ ሲኾን አፈጻጸሙ በአገልጋዩ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እንዲኾን በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡

  ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባይ ተቃዋሚዎቹ ግን አሁን በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሰው ኃይል ክምችት መኖሩ ችግር መኾኑን እያወቁ፣ ከዚህ አንጻር የቀረበው የመፍትሔ ሐሳብም በገጠርም በከተማም ያለችውን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ለማገልግል የሚያስችል እንደኾነ ሳይሰወራቸው መረጃው አይኖረውም ብለው የሚያስቡትን ብዙኃኑን ካህን ‹‹በየአጥቢያው ኻያ ኻያ ካህን ብቻ ነው የሚያስፈልገው ተብሏል፤ መፈናቀላችኹ ነው፤ ወደ ጋምቤላ መበተናችኹ ነው፤›› እያሉ ሰፊ ውዥንብር መፍጠራቸው የ‹ቅሬታቸውን› አግባብነትና ቅንነት አጠያያቂ የሚያደርገው ነው፡፡

  የለውጡ ተቃዋሚዎች ኅቡእ ስብሰባ እንደተካሄደበት የተዘገበው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬ÷ የኅቡእ ስብሰባውን መካሔድ በማስተባበልና የኅቡእ ስብሰባውን ዓላማ በጽኑ በመቃወም ለለውጡ ተግባራዊነት ያላቸውን ድጋፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ለረዳት ሊቀ ጳጳሱ እና ለሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ጽፈዋል፡፡

  ReplyDelete

 9. በቀንደኛ የሀገረ ስብከቱ ሙሰኛ የአድባራት አለቆች፡- መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ (ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ (ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል)፣ መልአከ ብሥራት መልአክ አበባው (አፍሪቃ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል) እና ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ (የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል) የሚመሩ ‹ተቃዋሚዎች›÷ ፓትርያርኩ ጥያቄዎቻቸውን የማይቀበሏቸው ከኾነ ‹‹የ[አቡነ] መርቆሬዎስ ደጋፊዎች ነን ብለን ሰልፍ እንወጣለን፤ መግለጫ እንሰጣለን›› እያሉ በፓትርያርኩ ላይ ሲዝቱ ውለዋል፤ ‹‹በቅዱስነትዎ ዘመን ደም እንዲፈስ ይፈልጋሉ ወይ? ይህ ጥናት የማይቆም ከኾነ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እናሳውቃለን፤ ፐርሰንት አንከፍልም፤ ለሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾች አስተዋፅኦ አናወጣም፤ የአባ እስጢፋኖስን ስም አንጠራም፤ ተገንጥለን በቦርድ እንተዳደራለን፤›› በማለትም የለውጥ ትግበራ ሂደቱን ለእነርሱ ብቻ በሚታያቸው ብጥብጥ የማወክና የማምመከን ዝንባሌና ውጥን እንዳላቸው ገልጠዋል፡፡

  በፓትርያርኩ ጽ/ቤት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች፣ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ከሚገኙ ግለሰቦች ጋራ የጥቅምና ዓላማ ግንኙነት መፍጠራቸው የሚነገርላቸው ‹ቅሬታ› አቅራቢዎቹ÷ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለጥናቱ አጸዳደቅ የሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ እንዲፈጸም መስማማታቸውን በፊርማቸው ያረጋገጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹ጥናቱን ይቃወማሉ›› በሚል ከፓትርያርኩና ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ ለማጋጨት፣ በዚህም የተቋማዊ ለውጥ ሒደቱ ርስ በርሱ ተጠላልፎ የሚወድቅበትን ውጥን መዘርጋታቸው ተጠቁሟል፡፡ የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ የኾነው ሊቀ ትጉሃን ደነቀ ተሾመ በዋናነት የሚያስፈጽመው ነው የተባለው ይኸው ሊቃነ ጳጳሳቱን የመከፋፈል ውጥናቸውም፣ የውሳኔውን አፈጻጸም በመረጃ ደረጃ እየተከታተሉ የማያቋርጥ ምክር በመለገሥ ላይ የሚገኙትን እንደ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ያሉ የተቋማዊ ለውጥ ጠበቆችን ማስቆጣቱ ነው የተሰማው፡፡

  ‹ቅሬታ› አቅራቢ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎቹ ከትላንት በስቲያው ምክራቸው በኋላ ለፓትርያርኩ አቀረቡት በተባለው አቤቱታ ‹‹ሙሉ የጥናት ሰነዱ›› እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ይህን እነርሱ ባይሉትም በየደረጃውና በየሞያ ዘርፉ በተለየ ኹኔታ በሚዘረጋው የሥልጠና መርሐ ግብር መሠረት ለየአብያተ ክርስቲያናቱ የሥራ ክፍሎች 13ቱም ጥራዞች እንደሚደርሱ በጥናታዊ ውይይቱ ላይ በተደጋጋሚ በመገለጽ ላይ ያለ ነው፡፡ ሊተኮርበት የሚገባው ግን፣ የጥናት ረቂቅ ሰነዱን በጋራ ውይይትና ግንዛቤ ለማዳበር የተዘረጋላቸውን መድረክ በአካል እየተገኙና አግባቡ እየተሳተፉ አስተዋፅኦ ባላደረጉበት፣ አንዳንዶቹም በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ተራቸው ደርሶ ባልተወያዩበትና ባልተሳተፉበት ኹኔታ ይህን ጥያቄ የማቅረባቸው መግፍኤ ነው፡፡

  ከዚህ አኳያ በተወካዮቻቸው በእነ መልአከ ገነት ኃይሌና ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ አማካይነት በፓትርያርኩ፣ በረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እና በቋሚ ሲኖዶስ አባላት ፊት ያቀረቡትን ‹ቅሬታ› በጥሞና ያዳመጡት የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ‹‹ከዚህ የሚያደርሳችኹ ነገር አልነበረም፤ እዚህ ከመምጣታችኹ በፊት ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ መነጋገር ነበረባችኹ›› ሲሉ የሰጧቸው ምላሽ አግባብነት ይኖረዋል፡፡ ውሏቸውን በቅርበት የተከታተሉ ምንጮች እንደተናገሩት ‹ቅሬታ› አቅራቢዎቹ፣ ‹‹ሙሉ ሰነዱን እንመረምራለን›› በሚል ዐቢይ ኮሚቴና ንኡሳን ኮሚቴዎችንም አዋቅረዋል፡፡

  ReplyDelete

 10. ‹‹በየሬስቶራንቱና በየሆቴሉ ከምትሰበሰቡ›› በሚል በተፈቀደላቸው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ከትላንት በስቲያ፣ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀትር ጀምሮ ሲመክሩ የዋሉት ከ60 የማይበልጡ ‹ቅሬታ› አቅራቢዎቹ÷ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በጦር ሜዳ የተሸነፈው የደርግ ርዝራዥ ነው፤ በጦር ሜዳ ገጥሞ ያልቻለውን ሥርዐት በሃይማኖት ገብቶ ሊጥለው ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አሠራር በጥናት ስም እየዘረጋ ነው፤ አሸባሪ ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ባወጣው ደንብ አንመራም፤›› በማለት ከመሠረተ ቢስ ውንጀላ፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ሕገ ወጥ ጥቅምን አስጠብቆ ለመኖር ከመፈለግ በቀር ለውጡን በግልጽ መድረክ በምክንያት ተደግፎ በሚቀርብ የአማራጭ ሐሳቦች ግብግብ የሚሟገቱበት መሬት የረገጠ መከራከርያ እንደሌላቸው አረጋግጠዋል፡፡

  ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና የባለሞያ ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ታደሰ አሰፋ÷ በጥናት ሰነድ ረቂቅ ዝግጅቱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደተቋም ያደረገው ተሳትፎ እንደሌለ በየጥናታዊ ውይይቶች ላይ ከባለሞያዎቹ ዝርዝር ማንነትና ስብጥር ጋራ ተደጋጋሚ መረጃዎች በመስጠት ሲያስረዱ ቆይተዋል፡፡

  ከባለሞያ ቡድኑ መካከል የማኅበረ ቅዱሳን አባላት መኖራቸው ርግጥ ቢኾንም ሀ/ስብከቱ የተጠቀመው ግለሰባዊ ዕውቀታቸውን/ሞያቸውን እንጂ የማኅበራቸውን መዋቅር እንዳልኾነ ለተወያዮች በተደጋጋሚ ሲገልጹ የቆዩት ብፁዕነታቸው፣ ‹‹ሰነዱን ማን አዘጋጀው ትታችኹ መሬት ወድቆ ብታገኙት አትጠቀሙበትም ወይ?›› ሲሉ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ባለሞያዎቹ በመደበኛ ሥራቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚከፈላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች መኾናቸውን የጠቀሱት ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ፣ ጥናቱ የቤተ ክህነታችንን ችግር በቅርበትና በጥልቀት በማወቅ ላይ ተመሥርቶ በአጭር ጊዜ መከናወኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ከመኾኑም በላይ ከባለሞያ ክፍያ አንጻር ብቻ ከ2 ሚልዮን ብር በላይ ወጭ የዳነበት መኾኑን አስረድተዋቸውም ነበር!!

  በዚህ ረገድ የባለሞያ ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ታደሰ አሰፋ ከሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ ተቃውሞ አይሉት ጥያቄ ጋራ ያደረጉት ምልልስ በተሳታፊዎች ዘንድ የጥቅስ ያህል የተያዘ ነው፡፡ የቤት እና የንግድ መኪኖች፣ ከአንድ በላይ መኖርያ ቤቶች ባለቤትነታቸው ብቻ ሳይኾን ከሽጉጥ ታጣቂነታቸው ጋራ በቁጣቸውና ለመነኮስ ከሚገባ አኗኗር መራቃቸው የሚታወቅላቸው የየካ ደብረ ሣህል ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ በውይይቱ ወቅት ርስ በርሱ በሚምታታው አነጋገራቸው እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሙስና ሙስና ትላላችኹ፤ ሙስና የለም! በልጆቻችን እንድንሠለጥን ያደርጉናል ወይ? ሕግ አያስፈልግም! ማንነታችኹ አይታወቅም፤ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አይደላችኹም፤ ልጅና ጎረቤት እኮ ልዩነት አለው፡፡››

  አቶ ታደሰ ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ በሰጡት አስተያየት፡- ‹‹የቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን በ፵ እና በ፹ ቀን በተፈጸመልን ጥምቀተ ክርስትና ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ልጅነት እኩል ነን እንጂ ልጅና ጎረቤት የለም፡፡ በዘመናችን የእግዚአብሔር የለሽ ፍልስፍና ስንቶች ፀረ ቤተ ክርስቲያን ኾነው ወጥተዋል፡፡ እኛ የሥላሴ ልጅነት ካገኘንባት ቤተ ክርስቲያን ሳንወጣ እዚህ በመገኘታችን መሰደብ አለብን?

  እግዚአብሔር በሰጠን ዕውቀትና ሞያ ለቤተ ክርስቲያናችን መታዘዝ እንዳለብን እናምናለን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ተጠርተንና ሞያችንን ዐሥራት አድርገን የሠራነው ጥናት የልጅነት ድርሻችንን የተወጣንበት የመታዘዝ ፍሬ ነው፡፡ እነ ሊቀ ሊቃውንት ደግሞ የጠመመውን ማቅናት፣ የጎደለውን መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡ ካልፈለጋችኹት ጋርቤጅ ውስጥ ጣሉት፤ ይጠቅማል ካላችኹ አሻሽሉት፡፡

  ሊቀ ሊቃውንት እንደተናገሩት፣ በቤት ልጅና ጎረቤት ዘይቤ ከቀጠልን ግን ወደ 43.7% የወረደውና በዐሥር ሚልዮኖች ያጣነው የምእመናን ቁጥር ከ20% ወርዶም እናገኛዋለን፡፡ ሊዘነጉት የማይገባው ቁም ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የካህናትም የሊቃውንትም የምእመናንም መኾኗን ነው!!››

  ReplyDelete

 11. ሀ/ስብከቱ ከኑሮ ውድነት አንጻር በአጥቢያዎች ተሳትፎ እያስጠናው የሚገኘው ጊዜያዊ የደመወዝ ጭማሪ ማስተከከያ ጥናት በመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ ረቂቅ ውስጥ ካለው የአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት፣ የሥራ መደብ ግምገማ፣ የአገልጋዮች ጥቅምና ጫና ጥናት ጋራ አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡

  ለፊርማ አቤቱታው የቀረቡት ጥያቄዎች ይዘት ‹ተቃዋሚዎቹ›÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከቃለ ዐዋዲ ደንቡ ጋራ ያለውን ልዩነትና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ላይ ያለውን ተፈጻሚነት በቅጡ ለይተው እንደማያወቁ፣ ስለ ለውጥ አመራር መዋቅርና አደረጃጀት ጥናት ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በካህናትና ምእመናን አንድነት የተዋቀረ መኾኑንና ምእመናንም ድርሻ እንዳላቸው የማይቀበል፣ በፍትሕ ሥርዐት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ጉዳዮች በራሷ ተቋማት ለመዳኘት ያላትን ሉዓላዊነት የማያምንና ኦርቶዶክሳዊ ውግንና የጎደለው፣ የለውጡ ከፍተኛ ተጠቃሚዎች የሚኾኑት ካህናትና ሊቃውንት በተወሰነላቸው የተሳትፎ ቁጥር ልክ በጥናታዊ ውይይቱ እንዳይሳተፉ በጥቅመኛ አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች አፈና መፈጸሙ፣ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዕውቅና የሰጠውን የባለሞያ ቡድን ‹‹ኅቡእ አካል›› በማለትና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትን ጥናቱን ‹‹የኅቡእ አካሉ የግል ፍላጎት ነው›› የሚል ዐመፀኝነት፣ በፓትርያርኩና በረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው መካከል ቅራኔ ፈጥሮ የተቋማዊ ለውጥ ሂደቱን በመቆጣጠርና በማክሸፍ ሕገ ወጥ ጥቅምን ለመከላከል ያለመ መኾኑ የተጋለጠበት ነው፡፡

  በወጣው የክፍላተ ከተሞች መርሐ ግብር መሠረት በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ሳይሳተፉ ጥናቱን ከተቃወሙትና ካህናትን በግዳጅ ለተቃውሞ ከሚያነሣሡት አስተዳዳሪዎች መካከል ጥቅመኛው የአፍሪቃ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብሥራት መልአክ አበባው ይገኝበታል፡፡ በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ካህናት፣ ሊቃውንትና ሠራተኞች ስም በጸሐፊው ሊቀ ትጉሃን ሲሳይ ገብረ ማርያም የተሰበሰበው የተቃውሞ ፊርማ ገዳሙን እንደማይወክል ሊቀ ሊቃውንቱ አባ ኃይለ መስቀል ውቤ ለሀ/ስብከቱ በደብዳቤ ያስታወቁ ሲኾን የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል አስተዳዳሪም ዋና ጸሐፊው፣ ዋና ተቆጣጣሪውና ሒሳብ ሹሙ በካህናቱ ስም አሰባሰብን ያሉትን ፊርማ በመቃወም ጥናታዊ ውይይቱን በጉጉት እንደሚጠብቁት ለጽ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡

  YeEne Meleak Abebaw Tekawumo01

  ከካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት አመራሮችና ምእመናን ተወጣጥተው በጥናታዊ ውይይቱ እንዲሳተፉ ለተጠሩ 16 ልኡካን በአግባቡ ጥሪውን ሳያስተላልፉ የአስተዳደር ሠራተኞችን ብቻ ይዘው ከተገኙትና በአጥኚው ቡድን ውስጥ ‹‹ካህናትና ሊቃውንት አልተካከተቱም›› በሚል ራሳቸውን በግንባር ቀደምነት ተቃዋሚ ካደረጉ የአጥቢያ አስተዳደሮች መካከል፡- ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (5 ተሳታፊዎች ብቻ የላከ)፣ ድል በር መድኃኔዓለም (1 ተሳታፊ ብቻ የላከ)፣ ደብረ ቢታንያ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት(6 የቢሮ ሠራተኞች ብቻ የላከ)፣ መሪ ሎቄ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (4 የቢሮ ሠራተኞች ብቻ የላከ) መኾኑ ተረጋግጧል፡፡

  የቅዳሜው የጥቂት ጥቅመኞች ኅቡእ ስብሰባ በሀ/ስብከቱና ኹኔታውን በቅርበት በሚከታተለው የፖሊስና የደኅንነት አካሉ መታወቁን ተከትሎ ተሰብሳቢዎች አንዳቸው ሌላቸውን በማጋለጥ ትርምስ ላይ ናቸው፤ ካህናቱና ሊቃውንቱም ባልተሳተፉበትና በማያውቁት ጥያቄ በአስተዳደር ሓላፊዎቹ እየተዋከቡ ‹የቅሬታ ፊርማቸውን› መስጠታቸውን ለሀ/ስብከቱ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

  በጥናት ላይ ለተመሠረተውና ወደኋላ ለማይመለሰው የሀ/ስብከቱ የተቋማዊ ለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ጥናት ተግባራዊነት አገልጋዩ የለውጥ ሐዋርያ እንዲኾን ያሳሰቡትና የለውጥ ተቃዋሚዎቹ ‹ቅሬታ› የቀረበላቸው ፓትርያርኩ የሚሰጡት ወሳኝ ምላሽ ዛሬ ይጠበቃል፡፡

  ReplyDelete
 12. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር ባካሄደው የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተሳትፎ እንዲዳብርና በቋሚ ሲኖዶሱ አማካይነት በሥራ ላይ እንዲውል በመወሰን በሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናታዊ ውይይት ለማወክ አፍራሽ ተግባራትን ሲያራምዱ የቆዩ ጥቅመኛ የአድባራት አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ኅቡእ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰማ፡፡
  Holy Synod direction on the A.A Change mgt.

  ምልአተ ጉባኤው ስለ አ/አ ሀ/ስብከት የአስተዳደር መዋቅር ጥናት ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲፈጸም የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ያዘዘበት ደብዳቤ

  በቅ/ሲኖዶሱ የምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መግለጫ መሠረት÷ በብዙኃን ተሳትፎና ውይይት ለመዳበርና የበለጠ ለመስተካከል ክፍት የኾነውን የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ረቂቅ በመድረክ ከመሞገት ይልቅ በአሉባልታዎችና አሻጥሮች ለማሰናከል የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የቆዩት የለውጡ ተቃዋሚዎች÷ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በኅቡእ የጠሩትን ስብሰባ ለማካሄድ ያቀዱት የገዳማቱና አድባራቱ በርካታ ልኡካን በረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤትና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት ተከታታይ ዙር ውይይቶችን እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

  የሀ/ስብከቱ የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የሥነ ምግባር ችግሮች ለቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ተልእኮ መጠናከርና መስፋፋት ትኩረት በሰጠ አኳኋን እንዲስተካከሉ፤ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ሰብአዊ፣ ፋይናንሳዊና ቁሳዊ ሀብቶቿ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ታስቦ በቅ/ሲኖዶሱ ዕውቅናና ይኹንታ የተዘረጋውን አሳታፊ መድረክ በመርገጥ በኅቡእ የተጠራውን ስብሰባ በዋናነት ያስተባበሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ተለይተው መታወቃቸው ተገልጦአል፡፡

  ኹኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ሐራዊ ምንጮቹ እንደጠቆሙት፣ በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኅቡእ ይካሄዳል የተባለውን ስብሰባ በዋናነት በማስተባበር ረገድ ከተዘረዘሩት 15 ግለሰቦች መካከል በቀዳሚነት የተጠቀሱት፡-

  የየካ ደብረ ሣህል ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣
  የኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የሳሪስ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አስተዳዳሪ፣
  የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣
  የጉለሌ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የአፍሪቃ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት፣
  የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
  የቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
  የአውግስታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
  የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ጸሐፊና ሒሳብ ሹም፤
  የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ጸሐፊ ናቸው፡፡

  ከእኒህና ከመሰሏቸው ግለሰቦች አብዛኞች፡- ከገቢያቸው በላይ በልዩ ልዩ የዝርፊያ ስልቶች ባጋበሱት የምእመናን ገንዘብ ከአንድ በላይ መኖርያ ቤቶች የሠሩ፤ የኪራይና ንግድ ቤቶች፤ የጭነት፣ የሕዝብ ማመላለሻና የቤት መኪኖች፣ ድልብ የባንክ ተቀማጭ፣ በቤተ ክርስቲያን የሥራ ሰዓት የግል ሥራ እየሠሩ ገቢ የሚያገኙበት ቢዝነስ ያላቸው፣ አንዳንዶቹም በሕገ ወጥ የጦር መሣርያ ይዞታና በተለያዩ ሥነ ምግባራዊ ችግሮች የተከሰሱና የተቀጡ መኾኑ ታውቋል፡፡ የተቋማዊ ለውጥ ሒደቱን የሚቃወሙትም እኒህን ሕገ ወጥ ጥቅሞች የሚያስጠብቁባቸው ክፍተቶች÷ መተግበሩ አይቀሬ በኾነው የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ እንዳይስተካከል ለመከላከል መኾኑ ተነግሯል፡፡

  ከኅቡእ ስብሰባው አስተባባሪዎች መካከል ለሁለት፣ ለሁለት ቀናት በየክፍላተ ከተማቸው የተካሔደውን ጥናታዊ ውይይት አሟልተው ያልተከታተሉ፣ ካለባቸው ሓላፊነት አኳያ መገኘትና ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ሲገባቸው ጨርሶ ያልተገኙ፤ በፈንታው ሐሰተኛና የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ከሚቀርበው ርእሰ ጉዳይ ጋራ ጨርሶ የማይገጥምና ለርእሰ ጉዳዩ መዳበር አንዳችም አስተዋፅኦ የሌለውን የአሉባልታ ጥያቄ በማንሣት አቅጣጫ ለማሳት አበክረው የሚንቀሳቀሱ እንዳሉባቸው ተጠቅሷል፡፡

  እኒህ አካላት የሚነዟቸው አሉባልታዎች ሊሸፍኗቸው/ሊከላከሏቸው የሚፈልጓቸውን ጥቅሞችም የሚያመላክቱ እንደኾኑ ግንዛቤ የተወሰደ ሲኾን ከእነርሱም መካከል፡-

  አስተዳዳሪዎች ወደ ግብዝና ወርዳችኋል፤ ሥልጣን የላችኹም፤
  ጸሐፊ ሥልጣንና ማኅተም ልትነጠቅ ነው፤ ወደ ድጋፍ ሰጪነት ወርድኻል፤ ድራሽኽ ጠፍቷል፤
  ቁጥጥር ሥራኽ በኮሚቴ ተወሰደብኽ፤ ማኅበረ ቅዱሳን የራሱን ሰዎች ሰግስጎና ሰንጎ ሊይዝኽ ነው፤
  የድጋፍ ሰጪ መዋቅሩ በመስፈርቱ የማኔጅመንት ምሩቅ ስለሚጠይቅ ማኅበረ ቅዱሳን የራሱን ሞያተኞች ሊያስቀምጥበት ያዘጋጀው መዋቅር ነው፤
  በየአጥቢያው 20፣ 20 ካህናት ብቻ ነው የሚያስፈልጉት ተብሏል፤ ካህን ሆይ፣ መበተንኽ ነው፤
  በየአጥቢያው በቅዳሴ ላይ የአባ እስጢፋኖስን ስም አንጠራም፤
  ጥናቱን ለምን ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ያጠናዋል፤

  የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

  እስከ አሁን በአራት ተከታታይ ዙሮች በተደረጉት ጥናታዊ ውይይቶች፣ አብዛኛው ተሳታፊ ለውጡ ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አመራርና አስተዳደር ትንሣኤ መኾኑን እየመሰከረ፣ በየዙሩ ከጥናታዊ ውይይቱ በፊትና በኋላ በሚሰበሰብ አስተያየት ከአጠቃላይ ተሳታፊው ከ92 – 95 በመቶ የሚኾነው ረቂቁ በአስቸኳይ ጸድቆ መተግበር እንዳለበት ድጋፉን እየገለጸ፤ በመድረኩ ላይ የሚነሡ ከርእሰ ጉዳይ ያፈነገጡ የቅስቀሳ መሰል አስተያየቶችንም ርስ በርሱ እየተጋገለባቸው መኾኑ ሲታይ፣ በኅቡእ ተሰብሳቢዎቹ የለውጡን ሒደት ጋት ያህል ሊመልሱት እንደማይችሉ የብዙዎች እምነት ነው፡፡

  * * *

  አሁን ዘግይቶ በተሰማ መረጃ መሠረት÷ በደብረ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት (ቀድሞ መልአከ መንክራት) ኃይሌ ኣብርሃ ሰብሳቢነት፣ በደብሩ ጸሐፊ ዲያቆን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጸሐፊነት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኅቡእ መደረጉ የተገለጸው ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

  ስድስት አስተዳዳሪዎችንና አምስት ጸሐፊዎችን ጨምሮ 15 ያህል ተሰብሳቢዎች እንደተገኙበት የተነገረው ይኸው ኅቡእ ስብሰባ የተጠናቀቀው፣ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ‹አቤቱታውን› ለቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለማቅረብ በመስማማት ነው ተብሏል፡፡

  በሌሎች ምንጮች ጥቆማ ደግሞ ስምምነቱ በዕለቱ÷ ነጭ በጥቁር የለበሱ ኻያ ኻያ ሰዎችን ከየአድባራቱ አደራጅቶ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገናኘት በቀድሞው ፓትርያርክ መቃብር ዙሪያ ማልቀስንና የለውጥ ሒደቱን የሚቃወም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠትን እንደሚያካትት ተመልክቷል፡፡

  ReplyDelete
 13. መቅ አላችሁ?ተነቅቶባችኁል

  ReplyDelete
 14. አባ ሰላማ! አንተ ማን ነህ?

  ReplyDelete

 15. enema. wushetamu, ketafiw, sim atfiw, aba selama, negn.

  ReplyDelete
 16. Not only daniel balcha why you did not send other mk elements. I knew you are mk agent.

  ReplyDelete
 17. IN THE NAME OFTHE FATHER THE HOLY SPRIT ONE GOD AMEN!

  IF EOTC is to remove corruption and despotism and train the clergy with modern management system and on spreading the Gospel to frontier beyond frontiers in all languages, Satan will not be happy. He will wage final struggle by creating united front his servants some that use EOTC as the source of their finance, others who fear the modernization of the management of EOTC will be hindrance for stealing the sheep by blaming EOTC as Arogitua, others who have secretly betrayed Our Lord and Savior Jesus Christ to Stan and others who fear a strong EOTC will not be manipulated to their political objectives. Hence, if we in change that implements God's plan, there can be several types of resistance like the one her and we must fight with fasting and prayer knowing the enemy fro the behind!
  Amen

  :Let God light your path
  Amen

  ReplyDelete