Saturday, December 21, 2013

የማቅን ሤራ ቀድመው የተገነዘቡ የአዲስ አበባ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ቤተ ክርስቲያንን ስለመታደግ ፓትርያርኩን አነጋገሩ

·        አለቆቹ “እስካሁን ብፁዓን አባቶች ብሎ ማክበር አገሪቷ ያቆየችው ታሪክ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን ይበላሻል፡፡” ሲሉ አስጠንቅቀዋል
·        ማቅ የሰራው የመዋቅር ለውጥ ሕግ ላይ የተጀመረው ውይይት እንዲቆም ቋሚ ሲኖዶስን ጠይቀዋል
·        በመንግስት ጉዳያቸው እንዲታይላቸውና ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ መንግስትን እየጠየቁ መሆኑ ተመልክቷል  
·        ማቅ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ በተቃውሞ እንዲነሱባቸው እየቀሰቀሰ መሆኑ ታውቋል
·        የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለሕይወታቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ለፓትርያርኩ ጥያቄ አቀረቡ
·        አለቆቹና አገልጋዮቹ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልጋትና እነርሱም ለውጡ የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል
·        የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅራዊ ለውጥ መሰራት ያለበት ስውር አላማ ባለውና የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግስቱን ስልጣን በኃይል ለመቆጣጠር በመታገል ላይ ያለው ማቅ የሚባለው አሸባሪ ቡድን መሆን አይገባውም
·        ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው የራሷ ልጆች የሆኑ ምሁራን ስላሉ በእነርሱ አጠቃላይ መዋቅራዊ ማሻሻያው ሊሠራ ይገባል
·        ማቅ ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ የሚጨነቅ ከሆነ ለውጡን ከራሱ እንዲጀምርና የሰራውን ሕንጻና ንብረቱን እንዲያስመዘግብ፣ ገቢውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ሞዴላሞዴሎች እንዲያደርግ ኦዲትም እንዲደረግ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል
   
ማኅበረ ቅዱሳን ያረቀቀውና ከአባ እስጢፋ ጋር በመመሳጠር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሰቀሳቀሰበት ያለው የመዋቅር ለውጥ ሕግ ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ታኅሣሥ 9/2006 ዓ.ም. ተቃውሟቸውን ለማሰማት ወደመንበረ ፓትርያርኩ ቀጠሮ ለማስያዝ ያቀኑት የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች የወከሏቸው 150 የሚሆኑ ልዑካን በዚሁ ዕለት እንዲገቡና አሳባቸውን እንዲያሰሙ ስለተጠሩ አቤቱታቸውን ለቅዱስ ፓትርያርኩ አቀረቡ፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው አለቆች፣ ጸሓፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞችና ስብከተ ወንጌሎች የሚገኙበት ማቅን የሚቃወም የቤተክርስቲያን መሪዎችና ኃላፊዎች ያሉበት ይህ ቡድን በፓትርያኩና አብረዋቸው በነበሩ አምስት ያህል ጳጳሳት ፊት ቀርቦ ባሰማው ተቃውሞ ማኅበረ ቅዱሳን ሐራ በተባለ ብሎጉ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደከፈተባቸውና በድብቅ ስብሰባ ጠርተዋል እያለ ስማቸውን እንደሚያብጠለጥል ተናግረዋል፡፡ እነርሱ ተደብቆ የሚያሰበስብ ምንም ምክንያት እንደሌላቸውና ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና ልዩ ልዩ ኃላፊዎች እንደመሆናቸው በግልጽ ተሰብስበው ሐሳባቸውን በነጻነት ማራመድ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ የተሰበሰቡትም በግልጽ ለመነጋገር ሲሆን ፓትርያርኩ ግቡ ብለዋችኋል ተብለው እንደቀረቡ አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳን ዛሬ ቀርበን ለመናገር አላሰብንበትም እንጂ ዕድሉ ከተሰጠን የምንናገረው ብዙ ብሶት አለብን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አንዳንድ ጳጳሳት “አሁን ከሌላ ስብሰባ መውጣታችን ነውና  የምሳም ሰዓት ስለደረሰ አስቡበትና በሌላ ቀን ድምፃችሁን ታሰማላችሁ” ሲሏቸው፣ እንዲገቡ እድል ካገኙት አለቆች መካከል በዚህ አጋጣሚ ብሶታቸውን ለማሰማት ሲሽቀዳደሙና የጳጳሳቱን “በሌላ ጊዜ ትናገራላችሁ” የሚለውን ማሳሰቢያ የጉዳዩን አንገብጋቢነት በማስረዳት አስለውጠው ባገኙት ጥቂት ደቂቃዎች ብሶታቸውን አሰምተዋል፡፡ አለቆቹ እንዳሉት ሲኖዶሱ፣ ብፁዓን አባቶች ጠቅላይ ቤተክህነቱ በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ስር የወደቀ ስለሆነ አቤቱታችንን እንኳን ለማሰማት ወደ ፓትርያርኩ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ሁሉም በር እየተዘጋብን ስለሆነ ወደመንግሥት አካላት አቤት ለማለት ተዘጋጅተናል፡፡ ብዙዎቹ እንዲያውም በሩ ስለተዘጋባቸው ወደመንግሥት አቤት እያሉ ነው ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል፡፡

አለቆቹ በንግግራቸው ቅሬታቸውንና በማኅበረ ቅዱሳን እየደረሰባቸው ያለውን ችግር ለመፍታት በየደረጃው ከሀገረ ስብከት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመሄድ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጸው ለመንግሥት አካላትም ጉዳዩን ለማሳወቅ አቅደናል ብለዋል፡፡ “እዚህ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ለሰልፍም ፈቃድ እየጠየቅን ነው፡፡ በየኢንተርኔቱ ስማችን እየጠፋ ነው፡፡ ይሄ ማኅበር እኮ ሊገድለን ነው” ሲሉ አንዱ አለቃ፣ ፓትርያርኩ “ማነው እሱ ማኅበሩ የምትሉት?” ብለው የጠየቁ ሲሆን አለቃውም “ማኅበረ ቅዱሳን ነዋ” በማለት በድፍረትና በጩኸት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሌላው አለቃም “በየክፍለ ከተማችን ተሰብስበን በማኅበረ ቅዱሳን የተረቀቀውን መዋቅር ተቀበሉት በሚል እየተደረገ ባለው ውይይት እየተነገረን ያለውና በየኢንተርኔቱ የሚጻፈው ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ወደእኛ እንዳወረደው ነው፡፡ እኛ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደእኛ እስካወረደው ድረስ እንወያይበት ነው ያልነው፡፡ እነርሱ ግን ረቂቁን አንሰጣችሁም ብቻ ተቀበሉት ነው እያሉን ያለው፡፡ ሳያወያይ እንካችሁ ተቀበሉ የሚል ደርግ ነው፡፡ በኃይል ዝመቱ የሚል ደርግ ነው፡፡ እነዚህ የደርግ ግርፎች ሳንወያይበት እንድንቀበለው እያስገደዱን ነው ያሉት፡፡ ደርጋዊ በሆነ አካሄድ መቀበል አለባችሁ እያሉን ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አክለውም “የመዋቅር ለውጥ ቤተክርስቲያን ያስፈልጋታል፡፡ እኛም ለውጥ እንዲደረግ ፈቃደኛና ደስተኞች ነን፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊ እሴቶቿን የሚጠብቅና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወክሎ በሊቃውንቶቿ ተሳትፎ ከቅዱስ ፓትርያርኩ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ባሉ አካላት የተረቀቀ ሊሆን ይገባል እንጂ በማቅ ኅቡእ አካል ብቻ የተሠራ መዋቅር ለዚያውም ግልጽ ውይይት ያልተደረገበት መዋቅር ለማቅ እንዲጠቅም ካልሆነ በቀር ለቤተክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅም አልታየንም፡፡” ብለዋል፡፡

ይህን የመሰለ ሐሳብ እየቀረበ ሳለ “አሁን ጊዜ የለም በሌላ ጊዜ ተዘጋጅታችሁ ኑ አሁን አቡነ ዘበሰማያት እንበል” ሲሉ ፓትርያርኩ፣ አለቆቹ ግን ለጥያቄያቸው በአባቶች የተሰጠው ቀላል ግምት ተገቢ አለመሆኑን በማመልከት ውይይቱ እንዲቀጥል ግፊት አድርገዋል፡፡ አንዱ አለቃም “ይህ ጉዳይ እንደ ቀላል እየታየ ነው ያለው፣ ግን ቀላል አይደለም፡፡ ይሄ ሰፊ ሰፊ የሆነ ፕሮግራም አገራዊ ጉዳይ እንጂ የግለሰብ ጉዳይ አይደለም፤ በጥልቀት ልታዩት ይገባል፤ ቀጠሮ እንስጣችሁ አቡነ ዘበሰማያት እናድርግ አይደለም፡፡ እስካሁን ብፁዓን አባቶች ብሎ ማክበር አገሪቷ ያቆየችው ታሪክ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን ይበላሻል፡፡ ግዴላችሁም አድምጡን! አድምጡን! አድምጡን!” ሲሉ፣ በዚህ ጊዜ ጳጳሳቱ ሁሉ ሲያጉረመርሙ “ግዴላችሁም ዲሞክራሲ ነው አድምጡን” በማለት ጆሮ እንዲሰጧቸው ግድ ብለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ማቴዎስ “ነጥቡን ተናገር ማስፈራራቱን ተወው” ሲሉ ለተወሰኑ ሰከንዶች ጫጫታ ሆኖ ነበር፡፡ የያዙትን ወደ 30 ገጽ ይጠጋል የተባለ አቤቱታና ፊርማዎችን የያዘ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በተደጋጋሚ አቤቱታውን በንባብ ማሰማት አለብን ቢሉም አቤቱታውን አባቶች እንደሚመለከቱት ገልጸው መነበቡ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

ሆኖም ንግግሩ ቀጥሎ አለቃው በማቅ ላይ አቤቱታቸውን ማሰማታቸውን ቀጠሉ “ማኅበረ ቅዱሳን በአሁኑ ሰዓት ሰንበት ትምህርት ቤትን ደግሞ ቅስቀሳ እያደረገ ነው ያለው፣ ምክንያቱም ማኅበሩን የሚያዘው አለቃ የለም፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያንን እያመሷት ነው፤ ከተማዋን ያምሷታል፣ ቤተክርስቲያንን ተጠግተው የቤተክርስቲያንን ንብረት እየሰበሰቡ ሞዴል የላቸው፤ አድራሻ የላቸው፣ ፎቅ እየገነቡ፤ ከመንግሥት ጋር ባላቸው ግንኙነት ሰላም የላቸውም፡፡ … ብዙ አለቆች ቅዱስነታቸው አይሰሙንም ብለው ወደ መንግሥት ሄደዋል፤ ብፁዓን አባቶችም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው እየተባለ ነው፡፡ ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ምንድን ነው? በምን ስር ነው የሚል ነው ትልቁ ጥያቄያችን፡፡ ሰበካ ጉባኤን ያለእድሜው እያወረዱ እያዋረዱ አለቆችን እያዋረዱ እያወረዱ በየአውደ ምሕረቱ ያተራምሱታል፡፡ አገሪቱን እያመሷት ነው፡፡ ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ምንድን ናቸውና ነው ሲኖዶሱ የሚፈራቸው? እነርሱ የእኛን ሙዳየ ምጽዋት ብቻ ሳይሆን ፎቃቸውን የማያስረክቡት ለምንድነው? ወይም ደግሞ ፖለቲከኞች ከሆኑ ለምን በግልጽ አይወጡም? ስለዚህ ሲኖዶሱ ከማቅ ጥገኝነት ነጻ መውጣት አለበት፡፡ ከእናንተ ስር ይውጣ እንጂ በእናንተ ፈረጂያ ሥር አይጠጋ እንጂ ብቻውን ይውጣና በመድረክ ላይ እንተያያለን፡፡ እንቢ ካላችሁ ወደጠቅላይ ሚኒስትር እንሄዳለን፡፡” ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል፡፡ ይህም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ብሶታቸው የት እንደደረሰ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

በመጨረሻ ጉዳዩ በየደረጃው እየታየ እንዲመጣ በሚል በቅድሚያ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀጠሮ እንዲያዝላቸውና በወኪሎቻቸው በኩል እንዲቀርቡ ከስምምነት ተደርሶ ድንገተኛ የሆነው ውይይት ተጠናቋል፡፡

ለዚህ ሁሉ ውዝግብ መነሻ የሆነውና በማቅ በኩል ብዙ የተባለለት የመወቅራዊ ለውጥ ረቂቅ ሕግ ከ 1000 በላይ ገጽ ያለውና 13 ጥራዝ እንደሆነ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ረቂቁን ያዘጋጁትም 16 የማቅ አባላት ሲሆኑ አባ እስጢፋ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ውስጥ በሰጧቸው ቢሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተቀምጠው የሰሩት ነው፡፡ በረቂቅ ሕጉ በአንድ ደብር 20 አገልጋይ ብቻ ነው መኖር ያለበት የሚል አንቀጽ ያለ ሲሆን ሌላው ሁሉ ግን በሀገረ ስብከቱ በጀት በየገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተመድቦ እንዲሰራ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ መስፈርቱም ዘመናዊ ትምህርት እንጂ የቤተክርስቲያን ትምህርትን ከግምት ያላስገባ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ የሰበካ ጉባኤ ቦርድ እንደሚያቋቁምና የመሻር መብት ግን እንደሌለው፣ ይህን የማድረግ መብቱ የሊቀጳጳሱ እንደሚሆን ረቂቁ ይደነግጋል፡፡ የማቅ አባላትም በቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌልና ልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፎች ያለምንም መስፈርት እንዲመደቡ ረቂቅ ደንቡ ያዛል፡፡ ይህ ሁሉ ማቅ የራሱን የማይቀድሱና የማይወድሱ በ “ክብር” ቅስናና ዲቁና የተጥለቀለቁ አባላቱን በየቤተክርስቲያኑ ለመሰግሰግና ቤተክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር የያዘውን ዕቅድ አልጋ በአልጋ ለማድረግ የቀየሰው ስልት መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ 

እስካሁን በየክፍለ ከተማው ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን አራዳና ጉለሌ፣ የካ፣ ነፋስ ስልክ ላፍቶና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ አድባራትና ገዳማት የሚገኙ አለቆችና ልዩ ልዩ ኀላፊዎች ተወያይተዋል፡፡ በየውይይቱ የተነሣው ዋና ጥያቄ “ረቂቁ ይሰጠንና እንወያይበት” የሚል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጥያቄያቸው ምላሽ ያላገኘ ሲሆን “ጸድቆ ከመጣ በኋላ ይሰጣችኋል” መባሉ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል፡፡ በየስብሰባው ላይ ተወያዮቹን ማሳመንም ሆነ ጥያቄያቸውን በተገቢው መንገድ መመለስ የተሳናቸው አባ እስጢፋ በተለይ ማነው ያረቀቀው ለሚለው ጥያቄ ሰጡ የተባለው ምላሽ ሰውዬውን ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት “ረቂቁን ወድቆም እናግኘው ሰይጣንም ይስጠን ሙስሊምም ያርቅቀው እስከጠቀመን እንቀበለዋን” ብለዋል፡፡ ይህ ከአንድ ጳጳስ ፈጽሞ የማይጠበቅ ቃል ከመሆኑም በላይ ለቤተክርስቲያን የሚሆን ነገር ከቤተክርስቲያን እንጂ ከሰይጣንም ሆነ ከሙስሊም ከመጣ እንቀበላለን ማለታቸው ቤተክርስቲያኗን እንመራለን የሚሉ አባቶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ይህም ሆኖ እስካሁን ድረስ በተደረጉት ውይይቶች ከ70% በላይ የሚሆኑት ረቂቁን እየተቃወሙት መሆኑ ይታወቃል፡፡ አለቆቹ ለፓትርያርኩና ለጳጳሳት ብሶታቸውን ባሰሙበት ወቅት የታየውም ተቃውሞው የት እንደደረሰ ነው፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና አመራር አካላት በማቅ ላይ በተቃውሞ መነሳታቸው ለማቅ ትልቅ ሞት ሲሆን ለመብታቸው ለታገሉ የደብር አለቆችና ልዩ ልዩ ኃላፊዎች ትልቅ ድል ነው፡፡ ማቅ ራሱ በጫረው እሳት እየተለበለበ ሲሆን አለቆቹና ሌሎቹም ሃላፊዎች ግን በዚህ የሚቆሙ አይመስልም፡፡ በ10/4/2006 ተሰብስበው በሚመለከተው የመንግስት አካል ለሰራተኛነታቸው ዋስትና ስለሚያገኙበትና ሕጋዊ መብታቸው የሚጣስበት አሰራር እንዲለወጥ በሠራተኛና አሰሪ ሕግ ስር ከለላ ስለሚያገኙበት ሁኔታ ከሕግ ባለሙያዎች ጋር መምከራቸው ተሰምቷል፡፡

በቀጣይም ማቅ የሰንበት ተማሪዎችን በመጠቀም ሕዝቡን በአለቆችና በልዩ ልዩ ሃላፊዎች ላይ በመሳመፅ ዕቅዱን ለማሳከት የተቻለውን ከማድረግ እንደማይመለስ ተገንዝበው ማቅን አጥብቀው ሊቃወሙና ሕግወጥ እንቅስቃሴውንና ጣልቃገብነቱን ሊያስቆሙ ይገባል እየተባለ ነው፡፡ ማቅ በ32ኛው የሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ ውሳኔው ተፈጻሚ እንዳይሆንና ሌላ አቅጣጫ እንዲይዝ ለማድረግ ይህን አጀንዳ ይዞ እንደተነሳ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ ማቅ አክራሪ ሆኖ በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ስፍራ ካገኘ ብዙ ጥፋት እንደሚያደርስ ተገንዝቦ በእንጭጩ መቅጨት ተገቢ ነው፡፡ በመንግስትም በኩል በአክራሪነት የተፈረጀው እንዲሁ በከንቱ ሳይሆን ማቅ በሃይማኖት ሽፋን እየተንቀሳቀሰ ፖለቲካ አጀንዳውን ከግቡ ለማድረስ የሚተጋ ፖለቲካዊ ድርጅት ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ማቅ የጫረውን እሳት ከማጥፋት በላይ በማቅ አንጻር ስርነቀል ለውጥ እንዲመጣ ተባብረው መሥራት አለባቸው፡፡

አንዳንድ የማቅ የውስጥ አዋቂዎች እንደገለጹት መንግስት ተዳክሟል ቤተ ክህነቱም ተዳክሟል ስለዚህ በ2007 ለሚኖረው ሀገር አቀፍ ምርጫ ግር ግር ሊፈጠር ይችላልና በለስ ከቀናው በሚፈጠረው ግርግር የመንግስትን ፖለቲካዊ ሥልጣን ለመያዝ የቤተ ክህነቱን ሥልጣን ቀድሞ መቆጣጠር ወሳኝ ነው ብሎ ሊወስዳቸው ካሰባቸው እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ይህ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡

ይህም ማቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በዚህ አዲስ መዋቅር መቆጣጠር ከቻለ ቤተ ክህነቱ ላይና  ቤተ መንግስቱ ላይ ጫና ለማሳደር እድል ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ከማግኘቱም በላይ የሕዝብ ንቅናቄ ለመፈጠርም ያመቸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለጊዜው እንዲቋረጥ ብፁአን አባቶች ሀሳብ የሰጡበት የመዋቅራዊ ጥናት ስብሰባ በአቡ እስጢፋኖስ ትእዛዝ እንደቀጠለ ሲሆን የሥልጠናው መሪ ማኅበረ ቅዱሳኑ አቶ ታደሰ ፍስሐ በሥልጠናው ተሳታፊዎች እናንተ እነማን ናችሁ? ከሊቃውንትስ ማንን ይዛችሁ ነው የምትሰሩት በሚል ለተነሳላቸው ጥያቁ በደፈናው የቤተክርስቲያን ልጆች ነን ከሊቃውንትም ታላቁን ሊቅ አቡነ እስጢፋኖስን ይዘን ነው የምንሰራው በማለት ምላሽ ሲሰጡ አዳራሹ በስላቅ ሳቅ ደምቋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኛ አቶ ደስታን በሥልጠናው ሥፍራ በወሬ አቀባይነት መድቦ በሬኒ ካፊና ሬስቶራንት የምሳ እና የሻይ እየተከፈለው አንዳንድ መረጃዎችን ለማኅበሩ ሥውር ብሎጎች እንዲያቀብል መድቦታል፡፡ የአዲሱ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አባል የነበረውና ወደ ቤተክህነት እቃ ሊያደርስ ተልኮ በድንገት ሠራተኛ የሆነው አሁንም በጠ/ቤተ ክህነቱ ገዳማት አስተዳደር ተጧሪ ሆኖ ደመወዝ የሚበላውን ይህንን ጨዋ የአድባራት እና ገዳማት አለቆችንንና ሰራተኞችን ስም በማጥፋት ተግባሩ ማኅበሩ አንቱታን ቸሮታል፡፡ በተጨማሪ እነ ጳውሎስ መልክአ ሥላሴም በዚሁ ተግባር በመሳተፍ ከቤተክህነቱ አደባባይ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ቀጣይ ዘገባዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆናችንን ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡
ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚበጅ አጠቃላይ ለውጥ እንዲመጣ የተቻለንን እናደርጋለን!!
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጀውን ያምጣልን!!


41 comments:

 1. ይሄን ፅሁፍ Getch Addis የተባለ ግለሰብ Facebook ላይ የፃፈው አስተያየት ነው።
  (እርግጥ አንተ ጴንጤው የጴንጤዎችን የኢየሱስ አማላጅነት ልስበክ ባይ፥ የታቦትን ጣውላነት ለመናገር ትንፋሽ እስኪያጥርህ የምታወራ፥ የቅዱሳን አማላጅነትን የምታጥላላ ሰው ይሄን ስትፅፍ፤ ነገር ለማራገብ ያለህን ፅኑ ፍላጎት ቢያሳይም እንደ ቀደመው ሁሉ ምንም አይከሰትም። የአዋሳው ትዝ አለህ? (በነገራችን ላይ የበጋሻው የጴንጤና ተሃድሶ አድናቂ የነበረው ደጀ ሰላም ደጀ ሰላም ተዘግቶብሃል-ምስኪን)
  ርዕስ፦
  አስተያየት ወዲህ እውነታው ወዲያ! Today at 12:03am
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በዘመናዊ መልክ ለማደራጀት የለውጥ ሥራ አመራርና አደረጃጀት ለመተግበር በቅዱስ ሲኖዶር ተወስኖ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በሆኑ ባለሙያዎች ጥናቶች መካሄድ ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የለውጥ ሥራ አመራርና አደረጃጀት ጥናቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የቅርብ ክትትል እየተደረገበት መሆኑም ይታወቃል፡፡ የባለሙያዎች የጥናት ቡድኑ ጥናቱን ካካሄደ በኋላ በጥናቱ ላይ ከትግበራ በፊት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችን እያወያየም ብዙ ዙሮችን ዘልቆአል፡፡ የዚህ ጥናት መሠረታዊ አስፈላጊነትና መነሻው በግርድፉ ለ2000 ዘመናት ያለአንዳች የሰው ሃይል እና የፋይናንስ መመሪያ በደጅ ጥናት የአሠራር “ስልት” ተዘፍቃ አንዳች የኃይማኖት ነቅዕ ሳይኖርባት ነገር ግን በመጥፎ የአሠራር ባለቤትነት ምሳሌ ሆና የኖረችውን ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ አሠራር እራሷን ዋጅታ ጥቂቶች አላግባብ ሃብቷን እንደተለመደው ከሚያግበሰብሱባት የሚገባቸው ሊቃውንቷን ጠቅማ የምትጠቀምበትን አሠራር ለመዘርጋት ነው፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ዘመናዊና ግልጽ መመሪያን የመከተል አዝማሚያ የለመዱትን አላግባብ ጥቅም እንደሚያስቀርባቸው ከወዲሁ የተረዱት ግለሰቦች በተገኘ አጋጣሚ እና ባላቸው አቅም ሁሉ የጥናቱን ሂደት ከጅምሩ ለማክሰም ላይ ታች ሲሉ እንደሰነበቱ ከተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲዎች እየሰማን ነው፡፡ በጥናቱ ላይ የሚካሄደው ውይይት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በተቃረበበት በዚህ ሳምንት እንኳን የተወሰኑ የአጥቢያ ሠራተኞችን በማታለልና የሚጎዱ በማስመሰል የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ማስገባታቸው ከተለያዩ የዜና ምንጮች ተሰምቷል፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ አጥቢያዎች ከወዲሁ “የተሰበሰቡት የድጋፍ ፊርማዎች አጥቢያውን አይወክሉም” ቢሉም፡፡ በዚህ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ ሂደትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በሙያቸው እንዲሠሩላት አምና የተቀበለቻቸውን የጥናት ቡድን “በኅቡዕ የተደራጀ” በማለት፣ “የሀገረ ስብከቱን ሠራተኞች እንደ ጋምቤላ ባሉ ጠረፍ ቦታዎች ለመመደብ ያለመ” በማለት የሌለ ስም በመስጠት፣ ጥናቱንም “የሠራተኞችን የሥራ ዋስትና አደጋ ውስጥ የሚከት ጥናት”፣… እና ሌሎችንም እያሉ የጥናት ሂደቱን ከመጀመሪያ እስካሁን አባታዊ መመሪያ በመስጠትና በመከታተል ለከረሙት ለቅዱስ ፓትርያርኩ አስገብተዋል፡፡ ከዚህ አልፎም የባለሙያዎች የጥናት ቡድን በየውይይት መድረኮቹ ስም ሳይጠቀስ ግብረ መልስ በሚሰበስብባቸው አስተያየት መስጫዎች በጣት የሚቆጠሩ ነገር ግን ለጥናቱ እና ለባለሙያዎች የጥናት ቡድኑ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች የሚሰጧቸው ውሃ የማያነሱ አስተያየቶች የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንዱ አስተያየት በግርድፉ እንደሰማሁት “ጥናቱን ያጠናችሁ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ስለሆናችሁ ዓላማችሁ ሥራ አጥ አባላቶቻችሁን በሀገረ ስብከቱ ለማስቀጠር እንደሆነ እናውቃለን፣ ከዚህ ይልቅ በጥርብ ድንጋይ (Coble Stone) ሥራmብታደራጇቸው ይሻላችኋል” የሚል ነበር፡፡ ከዚህ “አስተያየት” ሁለት ነገሮችን ማንሳት ፈለግኩ፡፡ “ጥናቱን ያጠኑት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው” የሚለው እና “ለማኅበሩ ሥራ አጥ አባላት ሥራ ለማስገኘት” የሚሉትን፡፡ በመሠረቱ ይኸ የለመደብን የጸለምተኝነት አመለካከት (Pessimism) ሆኖ እንጂ ጥናቱ ምንድነው? ምን ጥቅም ያስገኛል? ምን ጉድለት ይሸፍናል? የሚለው ማን አጠናው? ከሚለው መቅደም ነበረበት? በመሠረቱ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የቤተ ክርስቲያን አባላት ናቸው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ከመሆናቸው በፊት የቤተ ክርስቲያን አባላት ነበሩ፣ ዛሬም ናቸው፣ ወደፊትም እንዲሁ፡፡ አባላቱ ብቻ ሳይሆኑ ማኅበሩም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ነው፡፡ አገልግሎቱም የቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡ ይህን ለማለት የፈለኩት እንደ እነሱ አባባል ቢሆን እንኳን ለማለት ነው እንጂ በጥናቱ እየተሳተፉ ካሉት ስንቱ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እንደሆኑ ፈጣሪ ይወቀው፡፡ ሁለተኛው እነሱ ስለምሉት “ሥራ አጥ” የማኅበሩ አባላት ጉዳይ ነው፡፡ እንደ እኔ አመለካከት ይህ ፈጽሞ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ካለማወቅና መረጃ ከማጣት የተሰጠ አስተያየት ነው፡፡ እውነት ሥራ አጥ የሆነ የማኅበረ ቅዱሳን አባል አለ? እነዚህ ሰዎች ባያውቁት ነው እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን እኮ አባላቱ በትፍር ጊዜአቸው (ከሥራ መልስ፣ በሰንበት ቀናት እና በአዳር መርሐ ግብሮች) በሚያበረክቱት አገልግሎት አገልግሎቱን መሸፈን ባለመቻሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለሙያዎችን በሙሉ ጊዜ ቀጥሮ የሚያሠራ ማኅበር ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ሥራ አጥነት ኃጢአትም ጽድቅም ሆኖ ሳይሆን ለእውነታው ብቻ ነው ይህን የማነሳው፡፡ እንዲህ በጭፍን ጥላቻ ለሚመሩት ወገኖች ግን “ልቡና ይስጣቸው” ከማለት በሌላ በምን ልንረዳቸው ይገባ ይሆን?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማሀበረ ቅዱሳን ይህንን ያህል ሰዉ አለዉ ከተባለ ምነዉ አንድ እንኩዋን ሰባኪ ወንጌል አጣ መቸም አዉቆ አጥፊ ቢሆንም ያዉ የነበራችሁ ዳነኤል ክብረት ነበር እሱንም አስመርራችህ ከአባልነት እንደገለል አደረጋችሁ እኛ የጠማን ወንጌል ነዉዉዉዉዉ ሌላዉ ቅብጥርጥር ትርፍ ነዉ ምናለ አኮቴትን ጸጋዉ ለተሰጣቸዉ ወንጌል ሰባኪያን ብትሰጡ እንዲህ ከምትቀልዱበት ደግሞ ይህች ፐሮቴስታንት በለኝ አንተ የመንፈስ ቅዱስን መግለጫ ለነሱ ስትሰጥ እኔ እዉቅና አልሰጥህም ይልቁንም በመንፈሳዊ ቅናት ተነሳስታችሁ የወንጌልን ደወል አሰሙ አለዚያ ተሃድሶ ፐሮቴሰታንተ ምናምን እያላችሁ መሰየም ጊዜዉ አልፎበታል

   Delete
  2. ህረ ባክህ? ከምርህ ነው? ሰባኪ የለም እንዴ? የት ነው የተገለፀልህ?

   Delete
  3. ስምረት ነኝ ከፍቼDecember 27, 2013 at 2:09 AM

   አዎን ከምሬ ነዉ፡፡ አሁን አኮቴት ላይ የሚሰብክ የትኛዉ ሰባኪ ነዉ እስቲ ጥራ! አንዱ አኮቴትን ሲገልጸዉምናለ መሰለህ ይህ ኮተት የሚባለዉ! በሎ አስቆናል፡፡ ለምን መሰለህ አቅራቢዎቹ ነጠላ ማጣፋት ላይ የሚደርስባቸዉ የለም ግን ክርስቶስን ሰበክን ብለዉ ሀያ ቦታ እየረገጡ ምዕመኑን ግራ ከማጋባት ያለፈ ትክክለኛዉን የወንጌል ቃል ስለማይሰብኩ ምናልባትም ችሎታ ስለሌላቸዉ ይሆናል! እስቲ ትዉልዱን ዋጁና ጌታችን ደስ ይበለዉ!!!

   Delete
  4. እውነትሽን ነው። አንዳንዱ ደሞ አለ ካባውን እንደሚሸጥ መኪና እያሳመረ ኢየሱስ በሉ እግዚአብሔር አትበሉ እያለ የሌለ የሚያስተምር። የሚያሳዝነው ስብከቱን ቢዝነስ ማድረጋቸው። ዘመኑን ዋጅተው።

   Delete
  5. የአንተዉ ማቅ የአንድ የታወቀ ሰባኪ ስም በማጥፋትና በዚያዉም እየቆነጸለ ባሳተመዉ ካሴት ከፍተኛ ገቢ ያገኘበትን አሉባልታ እንደ ገደል ማሚቶ የምትደግመዉ ይልቅስ ከሱ ከአፉ ስማ አሱ ያለዉ ኢየሱሰ የሚለዉን ስም አትፍሩት ስለ ኢየሱስ ታሪክ እየተወራም ኢየሱስ ላለማለት እግዚአብሔር ትላላችሁ ነዉ ያለዉ! ወይስ አንተም ኢየሱሰ የሚባል የለም ትላለህ? ማቅ ከcontext ዉጭ በመቆነጠር ያዘጋጀዉ ሰይጣናዊና ቢዝነስ ተሳካለት፡፡ የሰማዩን ግን ለባለቤቱ እነተወዋለን እሱ ያዉቅበታል።ወንድሜ በመኪናና በቁሳቁስ ጉጉት አትሰናከል ሰጪ አምላክህን ለምን ይሰጠሃል!!!

   Delete
 2. According to Gov. Official the security force and secrete service of Ethiopian Gov. investigate Aba. ESTIFANOSE, if his plan is work with mk to remove Gov. will be arrest him in a matter of time. Patriarch Matias has weak in leadership may be the Gov. working hard in other direction to replace him. Now is time to do every thing the fundamentalist mk to demolish in the holy land of Ethiopia. You guys will report in Ethiopian revenue financial institute to control mk financial dispute activity. Here in GA Mr. Eferem has opened church business with out holy synod permission and stole money in the public on behalf of EOTC, he just fired any one not agreed on his idea. But, eotc members reported in GA and USA federal revenue to investigate financial crime that has done by Efrem and Merkebu.
  Now those ganges are under investigation by secrete service. They will be life in prison if the revenue find out financial dispute. Mk is or was making financial crime in the law of land which is run politics and religion at the same time as this result if you have fact, if they have building and other asset on behalf EOTC that Owen by MK notify to Ethiopian revenue service for investigation. Thanks to former PM Melese Zenawi now all citizens are equal and founded real democracy in the land ofEthiopia. Efrem church in Atlanta his service members are criminal that was released from jail such like Daniel Balcha, Abrham Agedew and Merkebu Hailu. All this jail mate are serving as Deacon that is the point use secrete service for investigation as initial point. The same as MK officially identified in Ethiopian Gov. MK as terrersit organization similar to Alshebab and ginbot seven so what and how can Aba ESTIFA is working in this group????? I my self as members of EPRDF Aba Estifa will be arrest him in matter of time if he is connection with MK and other fundamentalist. Unidentified source reported to our office Aba Estifa received 10 million Ethiopian birr to do this dirt game. It is early to say any thing about his corruption activity. IF we get evidence, he will be arrest soon. Some fundemetalist Amahara elementes will have hope to control Ethiopia again just dream only. Now, new Ethiopia is founded by nations and nationality all equal no more jump in and sex practice any more in WOLITTA and south nations. Death to MK.

  ReplyDelete
  Replies
  1. First of all, mind your English language. Do not mix our religion with your Cadre work. Please do not use this web site for your shit politics. We want Aba Selama to thrive. We have had enough of the legacy of your boss, Meles. We do not have to forget the pain that was inflicted upon us by Meles. MK is another type of Meles. They too want to dictate us in the same manner that Meles did. MK is anti democracy, anti New Testament. I am sure, the guy that is writing the above nonsense must be from outside Ethiopia (althouhg your English is too poor to warrant a stay in the US or any English speaking country) who does not understand what we have been through for the last 23 years. Zipping your tongue that likes to talk about Meles, let us be clear about MK's involvement in our Church. Ishi? Gosh yene leflafi.

   Delete
  2. EPRDF is the enemy for our church more than MK. MK is our brothers and sisters by Jesus. It is a matter of time peace will come upon us, and worshiping the lord Jesus together.

   Delete
 3. Must our government protect those who are straggling for their right from MK (terrorist group). Everybody must need to be understand regarding about MK, what is a MK plan for the future ? MK working under ground to control our orthodox church governing position or spot through his few archbishops, by giving money to few numbers archbishop. . those top our church leaders they don't care about orthodox faith, They so craze for money to build fancy houses.. Let us stand together against of MK../...this is the time to remove MK from our church..........to send hell for ever.

  ReplyDelete
 4. አባ ሙስጠፋ በሉት የምን እስጢፋ

  ReplyDelete
 5. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር ባካሄደው የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተሳትፎ እንዲዳብርና በቋሚ ሲኖዶሱ አማካይነት በሥራ ላይ እንዲውል በመወሰን በሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናታዊ ውይይት ለማወክ አፍራሽ ተግባራትን ሲያራምዱ የቆዩ ጥቅመኛ የአድባራት አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ኅቡእ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰማ፡፡
  Holy Synod direction on the A.A Change mgt.

  ምልአተ ጉባኤው ስለ አ/አ ሀ/ስብከት የአስተዳደር መዋቅር ጥናት ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲፈጸም የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ያዘዘበት ደብዳቤ

  በቅ/ሲኖዶሱ የምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መግለጫ መሠረት÷ በብዙኃን ተሳትፎና ውይይት ለመዳበርና የበለጠ ለመስተካከል ክፍት የኾነውን የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ረቂቅ በመድረክ ከመሞገት ይልቅ በአሉባልታዎችና አሻጥሮች ለማሰናከል የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የቆዩት የለውጡ ተቃዋሚዎች÷ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በኅቡእ የጠሩትን ስብሰባ ለማካሄድ ያቀዱት የገዳማቱና አድባራቱ በርካታ ልኡካን በረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤትና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት ተከታታይ ዙር ውይይቶችን እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

  የሀ/ስብከቱ የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የሥነ ምግባር ችግሮች ለቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ተልእኮ መጠናከርና መስፋፋት ትኩረት በሰጠ አኳኋን እንዲስተካከሉ፤ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ሰብአዊ፣ ፋይናንሳዊና ቁሳዊ ሀብቶቿ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ታስቦ በቅ/ሲኖዶሱ ዕውቅናና ይኹንታ የተዘረጋውን አሳታፊ መድረክ በመርገጥ በኅቡእ የተጠራውን ስብሰባ በዋናነት ያስተባበሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ተለይተው መታወቃቸው ተገልጦአል፡፡

  ኹኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ሐራዊ ምንጮቹ እንደጠቆሙት፣ በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኅቡእ ይካሄዳል የተባለውን ስብሰባ በዋናነት በማስተባበር ረገድ ከተዘረዘሩት 15 ግለሰቦች መካከል በቀዳሚነት የተጠቀሱት፡-

  የየካ ደብረ ሣህል ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣
  የኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የሳሪስ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አስተዳዳሪ፣
  የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣
  የጉለሌ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የአፍሪቃ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
  የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት፣
  የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
  የቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
  የአውግስታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
  የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ጸሐፊና ሒሳብ ሹም፤
  የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ጸሐፊ ናቸው፡፡

  ከእኒህና ከመሰሏቸው ግለሰቦች አብዛኞች፡- ከገቢያቸው በላይ በልዩ ልዩ የዝርፊያ ስልቶች ባጋበሱት የምእመናን ገንዘብ ከአንድ በላይ መኖርያ ቤቶች የሠሩ፤ የኪራይና ንግድ ቤቶች፤ የጭነት፣ የሕዝብ ማመላለሻና የቤት መኪኖች፣ ድልብ የባንክ ተቀማጭ፣ በቤተ ክርስቲያን የሥራ ሰዓት የግል ሥራ እየሠሩ ገቢ የሚያገኙበት ቢዝነስ ያላቸው፣ አንዳንዶቹም በሕገ ወጥ የጦር መሣርያ ይዞታና በተለያዩ ሥነ ምግባራዊ ችግሮች የተከሰሱና የተቀጡ መኾኑ ታውቋል፡፡ የተቋማዊ ለውጥ ሒደቱን የሚቃወሙትም እኒህን ሕገ ወጥ ጥቅሞች የሚያስጠብቁባቸው ክፍተቶች÷ መተግበሩ አይቀሬ በኾነው የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ እንዳይስተካከል ለመከላከል መኾኑ ተነግሯል፡፡

  ከኅቡእ ስብሰባው አስተባባሪዎች መካከል ለሁለት፣ ለሁለት ቀናት በየክፍላተ ከተማቸው የተካሔደውን ጥናታዊ ውይይት አሟልተው ያልተከታተሉ፣ ካለባቸው ሓላፊነት አኳያ መገኘትና ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ሲገባቸው ጨርሶ ያልተገኙ፤ በፈንታው ሐሰተኛና የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ከሚቀርበው ርእሰ ጉዳይ ጋራ ጨርሶ የማይገጥምና ለርእሰ ጉዳዩ መዳበር አንዳችም አስተዋፅኦ የሌለውን የአሉባልታ ጥያቄ በማንሣት አቅጣጫ ለማሳት አበክረው የሚንቀሳቀሱ እንዳሉባቸው ተጠቅሷል፡፡

  እኒህ አካላት የሚነዟቸው አሉባልታዎች ሊሸፍኗቸው/ሊከላከሏቸው የሚፈልጓቸውን ጥቅሞችም የሚያመላክቱ እንደኾኑ ግንዛቤ የተወሰደ ሲኾን ከእነርሱም መካከል፡-

  አስተዳዳሪዎች ወደ ግብዝና ወርዳችኋል፤ ሥልጣን የላችኹም፤
  ጸሐፊ ሥልጣንና ማኅተም ልትነጠቅ ነው፤ ወደ ድጋፍ ሰጪነት ወርድኻል፤ ድራሽኽ ጠፍቷል፤
  ቁጥጥር ሥራኽ በኮሚቴ ተወሰደብኽ፤ ማኅበረ ቅዱሳን የራሱን ሰዎች ሰግስጎና ሰንጎ ሊይዝኽ ነው፤
  የድጋፍ ሰጪ መዋቅሩ በመስፈርቱ የማኔጅመንት ምሩቅ ስለሚጠይቅ ማኅበረ ቅዱሳን የራሱን ሞያተኞች ሊያስቀምጥበት ያዘጋጀው መዋቅር ነው፤
  በየአጥቢያው 20፣ 20 ካህናት ብቻ ነው የሚያስፈልጉት ተብሏል፤ ካህን ሆይ፣ መበተንኽ ነው፤
  በየአጥቢያው በቅዳሴ ላይ የአባ እስጢፋኖስን ስም አንጠራም፤
  ጥናቱን ለምን ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ያጠናዋል፤

  የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

  እስከ አሁን በአራት ተከታታይ ዙሮች በተደረጉት ጥናታዊ ውይይቶች፣ አብዛኛው ተሳታፊ ለውጡ ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አመራርና አስተዳደር ትንሣኤ መኾኑን እየመሰከረ፣ በየዙሩ ከጥናታዊ ውይይቱ በፊትና በኋላ በሚሰበሰብ አስተያየት ከአጠቃላይ ተሳታፊው ከ92 – 95 በመቶ የሚኾነው ረቂቁ በአስቸኳይ ጸድቆ መተግበር እንዳለበት ድጋፉን እየገለጸ፤ በመድረኩ ላይ የሚነሡ ከርእሰ ጉዳይ ያፈነገጡ የቅስቀሳ መሰል አስተያየቶችንም ርስ በርሱ እየተጋገለባቸው መኾኑ ሲታይ፣ በኅቡእ ተሰብሳቢዎቹ የለውጡን ሒደት ጋት ያህል ሊመልሱት እንደማይችሉ የብዙዎች እምነት ነው፡፡

  * * *

  አሁን ዘግይቶ በተሰማ መረጃ መሠረት÷ በደብረ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት (ቀድሞ መልአከ መንክራት) ኃይሌ ኣብርሃ ሰብሳቢነት፣ በደብሩ ጸሐፊ ዲያቆን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጸሐፊነት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኅቡእ መደረጉ የተገለጸው ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

  ስድስት አስተዳዳሪዎችንና አምስት ጸሐፊዎችን ጨምሮ 15 ያህል ተሰብሳቢዎች እንደተገኙበት የተነገረው ይኸው ኅቡእ ስብሰባ የተጠናቀቀው፣ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ‹አቤቱታውን› ለቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለማቅረብ በመስማማት ነው ተብሏል፡፡

  በሌሎች ምንጮች ጥቆማ ደግሞ ስምምነቱ በዕለቱ÷ ነጭ በጥቁር የለበሱ ኻያ ኻያ ሰዎችን ከየአድባራቱ አደራጅቶ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገናኘት በቀድሞው ፓትርያርክ መቃብር ዙሪያ ማልቀስንና የለውጥ ሒደቱን የሚቃወም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠትን እንደሚያካትት ተመልክቷል፡፡

  ReplyDelete

 6. ሀ/ስብከቱ ከኑሮ ውድነት አንጻር በአጥቢያዎች ተሳትፎ እያስጠናው የሚገኘው ጊዜያዊ የደመወዝ ጭማሪ ማስተከከያ ጥናት በመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ ረቂቅ ውስጥ ካለው የአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት፣ የሥራ መደብ ግምገማ፣ የአገልጋዮች ጥቅምና ጫና ጥናት ጋራ አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡

  ለፊርማ አቤቱታው የቀረቡት ጥያቄዎች ይዘት ‹ተቃዋሚዎቹ›÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከቃለ ዐዋዲ ደንቡ ጋራ ያለውን ልዩነትና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ላይ ያለውን ተፈጻሚነት በቅጡ ለይተው እንደማያወቁ፣ ስለ ለውጥ አመራር መዋቅርና አደረጃጀት ጥናት ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በካህናትና ምእመናን አንድነት የተዋቀረ መኾኑንና ምእመናንም ድርሻ እንዳላቸው የማይቀበል፣ በፍትሕ ሥርዐት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ጉዳዮች በራሷ ተቋማት ለመዳኘት ያላትን ሉዓላዊነት የማያምንና ኦርቶዶክሳዊ ውግንና የጎደለው፣ የለውጡ ከፍተኛ ተጠቃሚዎች የሚኾኑት ካህናትና ሊቃውንት በተወሰነላቸው የተሳትፎ ቁጥር ልክ በጥናታዊ ውይይቱ እንዳይሳተፉ በጥቅመኛ አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች አፈና መፈጸሙ፣ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዕውቅና የሰጠውን የባለሞያ ቡድን ‹‹ኅቡእ አካል›› በማለትና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትን ጥናቱን ‹‹የኅቡእ አካሉ የግል ፍላጎት ነው›› የሚል ዐመፀኝነት፣ በፓትርያርኩና በረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው መካከል ቅራኔ ፈጥሮ የተቋማዊ ለውጥ ሂደቱን በመቆጣጠርና በማክሸፍ ሕገ ወጥ ጥቅምን ለመከላከል ያለመ መኾኑ የተጋለጠበት ነው፡፡

  በወጣው የክፍላተ ከተሞች መርሐ ግብር መሠረት በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ሳይሳተፉ ጥናቱን ከተቃወሙትና ካህናትን በግዳጅ ለተቃውሞ ከሚያነሣሡት አስተዳዳሪዎች መካከል ጥቅመኛው የአፍሪቃ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብሥራት መልአክ አበባው ይገኝበታል፡፡ በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ካህናት፣ ሊቃውንትና ሠራተኞች ስም በጸሐፊው ሊቀ ትጉሃን ሲሳይ ገብረ ማርያም የተሰበሰበው የተቃውሞ ፊርማ ገዳሙን እንደማይወክል ሊቀ ሊቃውንቱ አባ ኃይለ መስቀል ውቤ ለሀ/ስብከቱ በደብዳቤ ያስታወቁ ሲኾን የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል አስተዳዳሪም ዋና ጸሐፊው፣ ዋና ተቆጣጣሪውና ሒሳብ ሹሙ በካህናቱ ስም አሰባሰብን ያሉትን ፊርማ በመቃወም ጥናታዊ ውይይቱን በጉጉት እንደሚጠብቁት ለጽ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡

  YeEne Meleak Abebaw Tekawumo01

  ከካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት አመራሮችና ምእመናን ተወጣጥተው በጥናታዊ ውይይቱ እንዲሳተፉ ለተጠሩ 16 ልኡካን በአግባቡ ጥሪውን ሳያስተላልፉ የአስተዳደር ሠራተኞችን ብቻ ይዘው ከተገኙትና በአጥኚው ቡድን ውስጥ ‹‹ካህናትና ሊቃውንት አልተካከተቱም›› በሚል ራሳቸውን በግንባር ቀደምነት ተቃዋሚ ካደረጉ የአጥቢያ አስተዳደሮች መካከል፡- ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (5 ተሳታፊዎች ብቻ የላከ)፣ ድል በር መድኃኔዓለም (1 ተሳታፊ ብቻ የላከ)፣ ደብረ ቢታንያ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት(6 የቢሮ ሠራተኞች ብቻ የላከ)፣ መሪ ሎቄ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (4 የቢሮ ሠራተኞች ብቻ የላከ) መኾኑ ተረጋግጧል፡፡

  የቅዳሜው የጥቂት ጥቅመኞች ኅቡእ ስብሰባ በሀ/ስብከቱና ኹኔታውን በቅርበት በሚከታተለው የፖሊስና የደኅንነት አካሉ መታወቁን ተከትሎ ተሰብሳቢዎች አንዳቸው ሌላቸውን በማጋለጥ ትርምስ ላይ ናቸው፤ ካህናቱና ሊቃውንቱም ባልተሳተፉበትና በማያውቁት ጥያቄ በአስተዳደር ሓላፊዎቹ እየተዋከቡ ‹የቅሬታ ፊርማቸውን› መስጠታቸውን ለሀ/ስብከቱ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

  በጥናት ላይ ለተመሠረተውና ወደኋላ ለማይመለሰው የሀ/ስብከቱ የተቋማዊ ለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ጥናት ተግባራዊነት አገልጋዩ የለውጥ ሐዋርያ እንዲኾን ያሳሰቡትና የለውጥ ተቃዋሚዎቹ ‹ቅሬታ› የቀረበላቸው ፓትርያርኩ የሚሰጡት ወሳኝ ምላሽ ዛሬ ይጠበቃል፡፡

  ReplyDelete

 7. ዛሬ ዐርብ ታኅሣሥ ፲፩ – ፲፪ የሚካሄደውን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና የልደታ፣ አዲስ ከተማና ቂርቆስ ክፍላተ ከተማ አብያተ ክርስቲያን ልኡካን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት መስተንግዶ የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል እና የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፤ ከታኅሣሥ ፲፫ – ፲፬ የሚካሄደውንና የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት ደግሞ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ስፖንሰር ለማድረግ በየሰበካ ጉባኤያቸው ማስወሰናቸውንና የሀ/ስብከቱን ወጪ መጋራታቸውን ገልጸዋል፡፡

  ታኅሣሥ ፮ እና ፯ በኮልፌ ቀራንዮ፤ ታኅሣሥ ፬ እና ፭ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍላተ ከተማ አብያተ ክርስቲያን እንደ ቅደም ተከተላቸው የተካሄደው ጥናታዊ ውይይት÷ ከአሉባልታዎች ይልቅ ከቀረበው የጥናት ረቂቅ ይዘት ጋራ ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው፣ ለሰነዱ መዳበር ብቻ ሳይኾን የይዘት መስተካከልም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ገንቢና ሞያዊ እንደነበር ባለሞያዎቹ፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ እና አዘጋጅ ኮሚቴው ጥናታዊ ውይይቶቹ በተካሄዱባቸው ዕለታት በመደበኛነት ያደረጓቸው የውሎ ምዘናዎች/ግምገማዎች በጉልሕ ያመለክታሉ፡፡

  በክፍላተ ከተማው ልኡካን ከተነሡት ነጥቦች መካከል በሀ/ስብከቱ አድባራት፣ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የደረጃ መስፈርት ጥናት÷ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች ጋራ የተመጣጠነ የሰው ኃይል /በቁጥር፣ በክህሎት፣ በሞያና ልምድ/ እንዲያገኙ የሚጠቁመው ሐሳብ ይገኝበታል፡፡ ሐሳቡ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ያላቸውን ሀብት፣ ታሪክ፣ ንብረት፣ ገንዘብ በተሻለ ደረጃ ለመጠቀም የሚችሉበትን ኹኔታ ለማመላከትና መንፈሳዊ ቅናትን በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጥ ተነሣሽነትን በአገልጋዮች መካከል ማስፈን መኾኑ ተገልጧል፡፡

  በአሁኑ ወቅት አብዛኛዎቹ ገዳማትና አድባራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል ክምችት እንደያዙ የታመነበት በመኾኑ በጥናቱ መሠረት ገዳማቱና አድባራቱ ካሉበት ደረጃ ጋራ ተመጣጣኝ የኾነ የአገልጋይ ቁጥር በመደበኛነት ከያዙ በኋላ ቀሪዎቹን ሳያፈናቀሉ ለማስተዳደር የሚችሉባቸው አግባቦች/አማራጮች በጥናቱ ተቀምጠዋል፡፡ ከአግባቦቹ አንዱ፣ ከመደበኛው (ስታንዳርድ) የአገልጋይ ቁጥር የቀረውን አገልጋይ ጊዜያዊ ምደባ ሰጥቶ ደመወዛቸውና ጥቅማጥቅማቸው ሳይነካ የሰው ኃይል ወደሚፈልግባቸው አጥቢያዎች የሚንሸራሽበት ሥርዐት ነው፡፡

  ሌላው አማራጭ፣ አጥቢያዎች በራሳቸው አልያም ከሌሎች አጥቢያዎች፣ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት፣ ከሌሎች አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት ጋራ በልማት ተቋማት ማስፋፊያ ፖሊሲው መሠረት እየተቀናጁ በሚከፍቷቸው የልማት ተቋማት አንጻር ተገቢውን የክህሎት/ሞያዊ ሥልጠና በመስጠት ማሰማራት ነው፡፡ ከመደበኛ ቁጥር ውጭ የኾነው አገልጋይ በትርፍነት የሚቆየው ለረጅም ጊዜ ከኾነ ደግሞ ሲያገኘው የቆየው ደመወዝና ጥቅማጥቅም እንደተጠበቀለት በአዲስ አበባ ዙሪያ ይኹን በአህጉረ ስብከት የካህናት እጥረት ባለባቸው አብያተ ክርስቲያን አበል እየታሰበለት ለተወሰነ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥበት መንገድ ነው፡፡ የገጠሪቱን ቤተ ክርስቲያን ከማገልገልና የቅጥር ወጭን ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ ትርጉም ያለውን ይህን ሐሳብ የጥናታዊ ውይይቱ ተሳታፊዎች በሙሉ ልብ የደገፉ ሲኾን አፈጻጸሙ በአገልጋዩ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እንዲኾን በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡

  ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባይ ተቃዋሚዎቹ ግን አሁን በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሰው ኃይል ክምችት መኖሩ ችግር መኾኑን እያወቁ፣ ከዚህ አንጻር የቀረበው የመፍትሔ ሐሳብም በገጠርም በከተማም ያለችውን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ለማገልግል የሚያስችል እንደኾነ ሳይሰወራቸው መረጃው አይኖረውም ብለው የሚያስቡትን ብዙኃኑን ካህን ‹‹በየአጥቢያው ኻያ ኻያ ካህን ብቻ ነው የሚያስፈልገው ተብሏል፤ መፈናቀላችኹ ነው፤ ወደ ጋምቤላ መበተናችኹ ነው፤›› እያሉ ሰፊ ውዥንብር መፍጠራቸው የ‹ቅሬታቸውን› አግባብነትና ቅንነት አጠያያቂ የሚያደርገው ነው፡፡

  የለውጡ ተቃዋሚዎች ኅቡእ ስብሰባ እንደተካሄደበት የተዘገበው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬ÷ የኅቡእ ስብሰባውን መካሔድ በማስተባበልና የኅቡእ ስብሰባውን ዓላማ በጽኑ በመቃወም ለለውጡ ተግባራዊነት ያላቸውን ድጋፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ለረዳት ሊቀ ጳጳሱ እና ለሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ጽፈዋል፡፡

  ReplyDelete

 8. በቀንደኛ የሀገረ ስብከቱ ሙሰኛ የአድባራት አለቆች፡- መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ (ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ (ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል)፣ መልአከ ብሥራት መልአክ አበባው (አፍሪቃ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል) እና ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ (የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል) የሚመሩ ‹ተቃዋሚዎች›÷ ፓትርያርኩ ጥያቄዎቻቸውን የማይቀበሏቸው ከኾነ ‹‹የ[አቡነ] መርቆሬዎስ ደጋፊዎች ነን ብለን ሰልፍ እንወጣለን፤ መግለጫ እንሰጣለን›› እያሉ በፓትርያርኩ ላይ ሲዝቱ ውለዋል፤ ‹‹በቅዱስነትዎ ዘመን ደም እንዲፈስ ይፈልጋሉ ወይ? ይህ ጥናት የማይቆም ከኾነ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እናሳውቃለን፤ ፐርሰንት አንከፍልም፤ ለሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾች አስተዋፅኦ አናወጣም፤ የአባ እስጢፋኖስን ስም አንጠራም፤ ተገንጥለን በቦርድ እንተዳደራለን፤›› በማለትም የለውጥ ትግበራ ሂደቱን ለእነርሱ ብቻ በሚታያቸው ብጥብጥ የማወክና የማምመከን ዝንባሌና ውጥን እንዳላቸው ገልጠዋል፡፡

  በፓትርያርኩ ጽ/ቤት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች፣ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ከሚገኙ ግለሰቦች ጋራ የጥቅምና ዓላማ ግንኙነት መፍጠራቸው የሚነገርላቸው ‹ቅሬታ› አቅራቢዎቹ÷ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለጥናቱ አጸዳደቅ የሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ እንዲፈጸም መስማማታቸውን በፊርማቸው ያረጋገጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹ጥናቱን ይቃወማሉ›› በሚል ከፓትርያርኩና ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ ለማጋጨት፣ በዚህም የተቋማዊ ለውጥ ሒደቱ ርስ በርሱ ተጠላልፎ የሚወድቅበትን ውጥን መዘርጋታቸው ተጠቁሟል፡፡ የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ የኾነው ሊቀ ትጉሃን ደነቀ ተሾመ በዋናነት የሚያስፈጽመው ነው የተባለው ይኸው ሊቃነ ጳጳሳቱን የመከፋፈል ውጥናቸውም፣ የውሳኔውን አፈጻጸም በመረጃ ደረጃ እየተከታተሉ የማያቋርጥ ምክር በመለገሥ ላይ የሚገኙትን እንደ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ያሉ የተቋማዊ ለውጥ ጠበቆችን ማስቆጣቱ ነው የተሰማው፡፡

  ‹ቅሬታ› አቅራቢ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎቹ ከትላንት በስቲያው ምክራቸው በኋላ ለፓትርያርኩ አቀረቡት በተባለው አቤቱታ ‹‹ሙሉ የጥናት ሰነዱ›› እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ይህን እነርሱ ባይሉትም በየደረጃውና በየሞያ ዘርፉ በተለየ ኹኔታ በሚዘረጋው የሥልጠና መርሐ ግብር መሠረት ለየአብያተ ክርስቲያናቱ የሥራ ክፍሎች 13ቱም ጥራዞች እንደሚደርሱ በጥናታዊ ውይይቱ ላይ በተደጋጋሚ በመገለጽ ላይ ያለ ነው፡፡ ሊተኮርበት የሚገባው ግን፣ የጥናት ረቂቅ ሰነዱን በጋራ ውይይትና ግንዛቤ ለማዳበር የተዘረጋላቸውን መድረክ በአካል እየተገኙና አግባቡ እየተሳተፉ አስተዋፅኦ ባላደረጉበት፣ አንዳንዶቹም በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ተራቸው ደርሶ ባልተወያዩበትና ባልተሳተፉበት ኹኔታ ይህን ጥያቄ የማቅረባቸው መግፍኤ ነው፡፡

  ከዚህ አኳያ በተወካዮቻቸው በእነ መልአከ ገነት ኃይሌና ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ አማካይነት በፓትርያርኩ፣ በረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እና በቋሚ ሲኖዶስ አባላት ፊት ያቀረቡትን ‹ቅሬታ› በጥሞና ያዳመጡት የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ‹‹ከዚህ የሚያደርሳችኹ ነገር አልነበረም፤ እዚህ ከመምጣታችኹ በፊት ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ መነጋገር ነበረባችኹ›› ሲሉ የሰጧቸው ምላሽ አግባብነት ይኖረዋል፡፡ ውሏቸውን በቅርበት የተከታተሉ ምንጮች እንደተናገሩት ‹ቅሬታ› አቅራቢዎቹ፣ ‹‹ሙሉ ሰነዱን እንመረምራለን›› በሚል ዐቢይ ኮሚቴና ንኡሳን ኮሚቴዎችንም አዋቅረዋል፡፡

  ReplyDelete

 9. ‹‹በየሬስቶራንቱና በየሆቴሉ ከምትሰበሰቡ›› በሚል በተፈቀደላቸው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ከትላንት በስቲያ፣ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀትር ጀምሮ ሲመክሩ የዋሉት ከ60 የማይበልጡ ‹ቅሬታ› አቅራቢዎቹ÷ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በጦር ሜዳ የተሸነፈው የደርግ ርዝራዥ ነው፤ በጦር ሜዳ ገጥሞ ያልቻለውን ሥርዐት በሃይማኖት ገብቶ ሊጥለው ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አሠራር በጥናት ስም እየዘረጋ ነው፤ አሸባሪ ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ባወጣው ደንብ አንመራም፤›› በማለት ከመሠረተ ቢስ ውንጀላ፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ሕገ ወጥ ጥቅምን አስጠብቆ ለመኖር ከመፈለግ በቀር ለውጡን በግልጽ መድረክ በምክንያት ተደግፎ በሚቀርብ የአማራጭ ሐሳቦች ግብግብ የሚሟገቱበት መሬት የረገጠ መከራከርያ እንደሌላቸው አረጋግጠዋል፡፡

  ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና የባለሞያ ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ታደሰ አሰፋ÷ በጥናት ሰነድ ረቂቅ ዝግጅቱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደተቋም ያደረገው ተሳትፎ እንደሌለ በየጥናታዊ ውይይቶች ላይ ከባለሞያዎቹ ዝርዝር ማንነትና ስብጥር ጋራ ተደጋጋሚ መረጃዎች በመስጠት ሲያስረዱ ቆይተዋል፡፡

  ከባለሞያ ቡድኑ መካከል የማኅበረ ቅዱሳን አባላት መኖራቸው ርግጥ ቢኾንም ሀ/ስብከቱ የተጠቀመው ግለሰባዊ ዕውቀታቸውን/ሞያቸውን እንጂ የማኅበራቸውን መዋቅር እንዳልኾነ ለተወያዮች በተደጋጋሚ ሲገልጹ የቆዩት ብፁዕነታቸው፣ ‹‹ሰነዱን ማን አዘጋጀው ትታችኹ መሬት ወድቆ ብታገኙት አትጠቀሙበትም ወይ?›› ሲሉ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ባለሞያዎቹ በመደበኛ ሥራቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚከፈላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች መኾናቸውን የጠቀሱት ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ፣ ጥናቱ የቤተ ክህነታችንን ችግር በቅርበትና በጥልቀት በማወቅ ላይ ተመሥርቶ በአጭር ጊዜ መከናወኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ከመኾኑም በላይ ከባለሞያ ክፍያ አንጻር ብቻ ከ2 ሚልዮን ብር በላይ ወጭ የዳነበት መኾኑን አስረድተዋቸውም ነበር!!

  በዚህ ረገድ የባለሞያ ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ታደሰ አሰፋ ከሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ ተቃውሞ አይሉት ጥያቄ ጋራ ያደረጉት ምልልስ በተሳታፊዎች ዘንድ የጥቅስ ያህል የተያዘ ነው፡፡ የቤት እና የንግድ መኪኖች፣ ከአንድ በላይ መኖርያ ቤቶች ባለቤትነታቸው ብቻ ሳይኾን ከሽጉጥ ታጣቂነታቸው ጋራ በቁጣቸውና ለመነኮስ ከሚገባ አኗኗር መራቃቸው የሚታወቅላቸው የየካ ደብረ ሣህል ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ በውይይቱ ወቅት ርስ በርሱ በሚምታታው አነጋገራቸው እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሙስና ሙስና ትላላችኹ፤ ሙስና የለም! በልጆቻችን እንድንሠለጥን ያደርጉናል ወይ? ሕግ አያስፈልግም! ማንነታችኹ አይታወቅም፤ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አይደላችኹም፤ ልጅና ጎረቤት እኮ ልዩነት አለው፡፡››

  አቶ ታደሰ ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ በሰጡት አስተያየት፡- ‹‹የቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን በ፵ እና በ፹ ቀን በተፈጸመልን ጥምቀተ ክርስትና ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ልጅነት እኩል ነን እንጂ ልጅና ጎረቤት የለም፡፡ በዘመናችን የእግዚአብሔር የለሽ ፍልስፍና ስንቶች ፀረ ቤተ ክርስቲያን ኾነው ወጥተዋል፡፡ እኛ የሥላሴ ልጅነት ካገኘንባት ቤተ ክርስቲያን ሳንወጣ እዚህ በመገኘታችን መሰደብ አለብን?

  እግዚአብሔር በሰጠን ዕውቀትና ሞያ ለቤተ ክርስቲያናችን መታዘዝ እንዳለብን እናምናለን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ተጠርተንና ሞያችንን ዐሥራት አድርገን የሠራነው ጥናት የልጅነት ድርሻችንን የተወጣንበት የመታዘዝ ፍሬ ነው፡፡ እነ ሊቀ ሊቃውንት ደግሞ የጠመመውን ማቅናት፣ የጎደለውን መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡ ካልፈለጋችኹት ጋርቤጅ ውስጥ ጣሉት፤ ይጠቅማል ካላችኹ አሻሽሉት፡፡

  ሊቀ ሊቃውንት እንደተናገሩት፣ በቤት ልጅና ጎረቤት ዘይቤ ከቀጠልን ግን ወደ 43.7% የወረደውና በዐሥር ሚልዮኖች ያጣነው የምእመናን ቁጥር ከ20% ወርዶም እናገኛዋለን፡፡ ሊዘነጉት የማይገባው ቁም ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የካህናትም የሊቃውንትም የምእመናንም መኾኗን ነው!!››

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጨረሻ ላይ የልቤን ተናገርክ፡፡ ለመሆኑ የምዕመናን ቁጥር እንዲህ በሚሊዮኖች ሲያሽቆለቁል አንተና ግብረ አበሮችህ ወንጌል እንዳይሰበክ የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም የወንድሞች ከሳሾች ሆናችሁ እንደዘመነ ሐዋሪያት ለወንጌል ስርጭት አንደበት የተሰጠዉን ስታዩ እንደዲያቢሎስ ያንቀጠቅጣችሁዋል፡፡ ያለርህራሄ ታሳድዱታላችሁ፡፡ በገንዘባችሁ የገዛችሁትን ሲኖዶስ ተገን በማድረገ እነዚህን ብርቅዮ ሰባኪዎች በማስወገዝና ከሕዝብ ልብ ለማዉጣት ያላደረጋችሁት የለም፡፡ ለመሆኑ የዉግዘቱን ዉጤት በአቡነ ፓዉሎስ አያችሁት? ዉግዘቱን ያጸደቁበት ፊርማ ሳይደርቅ ጥሪዉ ከቸች አለ!! ነፍሳቸዉን ይማረዉ፡፡ ሌሎቹም ንሰሐ ካልገቡ የማይበጅ ጥሪ የመጣል!! ታዲያ አንተ እንዳልከዉ ከ20 በመቶ በታች ቢወርድ ምን ሊገርምህ ነበር?

   Delete

 10. የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመሸጥ የሚታወቁት የ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባዮቹ ዋነኛ አስተባባሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ፣ በቅርቡ በ1.3 ሚልዮን ብር በገዙትና ለቻይና ተቋራጭ ባከራዩት ሲኖ ትራክ መኪና ብቻ በወር ብር 70,000 ገቢ ያገኛሉ፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ለውጥ ለማምጣት የተነሡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተንገላቱበት የግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም. ጥቃት የተሳተፉትና ሞዴል ፴ በማቃጠል የሚታወሱት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ፣ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች ጋራ ስልታዊ ግንኙነት መጀመራቸው የሚነገርላቸውና ለአፃዌ ኆኅትነት እንኳ ሳይበቁ በደ/ምሕረት ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እልቅና ለመሾም ‹‹መቶ ሺሕ ብር እከፍላለኹ›› በሚል ልጆቻቸውን ለረኀብ የዳረጉት መልአከ ብሥራት መልአከ አበባው (ብይዱ ይመር)ስ እነማን ናቸው?

  * * *

  የካህናቱን፣ የሊቃውንቱን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የምእመናን ተወካዮችን ከ92 – 97 በመቶ ድጋፍ ያረጋገጠው የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናታዊ ውይይት ዛሬ ይጠናቀቃል፤ የጥናቱን ትግበራ የሚቆጣጠር በአፈጻጸምም እየተከታተለ የሚያርምና የሚያስተካክል ራሱን የቻለ አካል እንዲቋቋም ተሳታፊዎቹ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡

  ‹‹ይህ መዋቅርና አደረጃጀት ስለ መታሰቡ፣ ቅንብር ስለ መደረጉ በቤቱ ስም አመሰግናለሁ፡፡ አባታችን የልማት አርበኛ ናቸው፡፡ በየመንደሩ ያለው አሉባልታ ይህ ነው አይባልም፤ እዚህ ስናየው ግን የተለየ ነው፡፡ የጥናት ዘገባው ቀጥሎ እንድናየው እንጂ ሁከት አያስፈልግም፡፡ ጀርባዬም ፊቴም አንድ ከኾነ በሕግ ለመተዳደር ምን ያስፈራኛል? አስቀድሞ ይህ እንዲህ ይኾናል እያሉ መደንበርስ ምን ያስመለክታል? ወጡም ሊጡም እያሉ ያሉት ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ነው ይህ ኹሉ ጭፋሮ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ለመጠበቅ ከፍተኛ ሓላፊነት ያለበት ቅ/ሲኖዶስ ይውጣ ያለውን ሕግ መደገፍ ተገቢ ነው!!›› /የደብር አስተዳዳሪ/

  ‹‹አንድ ድጓ ከዲግሪ ጋራ ይወዳደራል ካላችኹ መቼ ነው እውን ኾኖ የምናየው? እውን ይኾናል ወይ? አምስት እንትን የምንላቸው ካልኾኑ በቀር ይህን የሚቃወም አይኖርምና ቶሎ ይተግበር፡፡ ብፁዕ አባታችን ከዚህ የበለጠ ምን ይጠበቃል? ይሄ ነገር ቶሎ የማይተገበር ከኾነና ወደ ኋላ የምታዘገዩት ከኾነ የልብ ልብ እንዲያገኙ ታደርጓቸዋላችኹ፤ እናንተም ተጠያቂዎች ትኾናላችኹ፡፡›› /የመምህራን ተወካይ/

  ‹‹የማይነካው ተነካ፤ የዘመናት ጸሎቴ ነበር፤ ፍጻሜውም ዛሬ ዛሬ. . .ይለኛል፤ እንግዲህ ጸሎተ ስምዖንን ነው የምጸልየው፤ ጌታዬ የቤተ ክርስቲያንን መዳን አሳይተኸኛልና ባሪያኽን አሰናብተኝ እለዋለኹ፡፡›› /የምእመናን ተወካይ/

  ReplyDelete
 11. አባ እስጢፋ ማለትም እኮ ትርጉሙ የሰይጣን ማኅበር አባት ማለት ነው!! እስጢፋ ሰይጣን ማለት ነው

  ReplyDelete
 12. እን አባ በጥብጥ ብሎጎች ለማበጣበጥ የከፈታችሁት ብሎግ ተመልካችና ሰሚ የሌለው ተዓማኒም ባለመሆኑ በመጀመሪያ እግዚአብሔር አመሰግናለሁ ። እናንተም የምትዘግቡት ሁሉ በጥፋት ልጅ
  በዲያቢሎስ ለመሆኑ የዘመናች ዲዮቅልጥያኖስ በመሆናችሁ ለቤተክርስቲያ ኃይማኖትሥርአት መጠበቅ ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚሉትን ወንድሞችና እህቶች ጥረትለማዳከም በመሆኑ በአላውያን ነገስታት ፊት ገድላቸውን እንደፈጸሙት መስዋእትነትም ተከፍሎ የቤተክርስቲያን ለውጥ ይኖራል።


  አትሰሙም እንጂ ማህበረ ቅዱሳን የሚፈርስ ሕንጻ አይደለም

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንክት!! ይፈርሳል እንጂ!! በክርስቶስ ደም የቀለደ ፀረ ወንጌል የሆነ ማን ሲለመልም አይተሃል

   Delete
 13. እናንተ የዚህ ብሎግ አዘጋጆችተሳድቦ አሰዳቢዎች የሚጽፉ እጆቻችሆንና የሚያዪ አይኖቻችሁን ማን ሸፈነባችሁ

  ReplyDelete
 14. Daniel balcha one of jail released deacon in Mr. Efrem church in Atlanta under investigatipn for additional crime charge that he. was rape elven years old girl. Also one private clinic reported Aba Etifa or Mustifa suffeting from AIDS.

  ReplyDelete
 15. መስሎሻል ቆማጢት

  ReplyDelete
 16. ስም አጥፊው ውሸታም፥ ሃሜተኛ ጴንጤ ለመሆኑ ይሄንን ጥያቄስ ያቀረቡት መነኩሴዎች አይደሉም እንዴ? እንዴት ነው እንዳንተ እንደ መናፍቅ ቅጥረኛው አባባል በጥቁር ራስ አንመራም የሚሉት? ራሳቸው ጥቁር ራስ ሆነው? ነው ወይስ የተሃድሶ ጴንጤ ቅጥረኛ፥ ወይም የሙስና ተባባሪ ሌባ ሲሆኑ ወዲያው ወደ ነጭ ራስነት ትቀይሩላችኋላችሁ? እናንተ እኮ ተዐምረኞች ናችሁ።የጌታ “የሱስ” ተዐምር።
  ከሙሰኞቹና ከእንደ እናንተ አይነት የጴንጤ ቅጥረኞች ጋር የተያዘው የመጀመሪያ ትግል ሙስናና ስርቆት ማስወገድ ነው። ትግሉ የቤተ ክርስቲያኗን ንብረት (አጥንት) ለብዙ ጊዜ ካለ ሃይ ባይ ሲግጡ የነበሩ ሌቦች፥ቅጥረኞች፥ እንደአንተ አይነት ሁለት ደሞዝ የሚቀበሉ ጴንጤዎችን (ውሾችን) -ምሳሌ ነው- ማስለቀቅ ነው። ይሄ ደሞ ከባድ በጣም ከባድ ነው። ውሻን ከአጥንቱ ማስጣል ከባድ ነው።
  ሌላው እግዚአብሔርን፥ ቤተክርስቲያንን፥ ህዝብን ከሆነ የሚያገለግሉት ሁሉም እግዚአብሔርም፥ ቤተክርስቲያኒቱም ሆነ ህዝቡ የሚላኩበት ቦታ ስላሉ የሚያናድዳቸው ነገር የለም። አገልግሎታቸውን ማከናወን ነው። ግን እንደአንተ የገንዘብ ቅጥረኞች ስለሆኑ ከአአ አብያተ ክርስቲያናት መውጣት ጨነቃቸው? ግራ የገባህ።
  ሙስናም ይጠፋል፤ ተሃድሶም ይመነጠራል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ብርሃን ከደሴDecember 25, 2013 at 12:20 AM

   ወንድሜ ምናለ ዝም ብለህ የስድብ ዲክሺነሪ እያሳተምክ ለእፍፍ ኮሌጆች እና ለሥራ ቤቶች ብትሸጥ የሚያዋጣህ ይመስለኛል ለመሆኑ እንዲህ የሚሳደብ ሰዉ ኢነተርኔት መክፈት እንዴት ቻለ

   Delete
  2. እንኩዋን እኔ አንተም ከፍተሃል:: አይመስልህም?
   ይልቁን ማሰብ ከቻልክ እና ግብዝ ካልሆንክ ይሄ ምን ማለት ይመስልሃል?
   -አባ እስጢፋ
   -እነዚህ የደርግ ግርፎች
   -ደርጋዊ
   -በ “ክብር” ቅስናና ዲቁና
   -አክራሪ
   -ወደ ቤተክህነት እቃ ሊያደርስ ተልኮ በድንገት ሠራተኛ የሆነው
   ከፃፉት ውሸት ውጪ ከላይ ያመጣሁልህ ቃላቶች ላንተ ስድብ አይደሉም አይደል? ምስኪን:: ይልቅ የውሸትና የስድብ ድክሽነሪማ እዚሁ ስላለልህ ለምን ከሁለት ቦታ የምታገኘውን ውድ ገንዘብህን ታወጣለህ?? እዚሁ ተማር::
   ብርሃን ከደጀ ብርሃን::

   Delete
  3. በመሠረቱ እኔ የትኛዉንም ተሳዳቢ አልደገፍኩም ያንተ ወይም አንቺ የስድብ ስንኞች የሚሸጡ ስለመሰለኝና እንዲህ ከመንተክተክ መጽሐፍ ቅዱስህን (ካለህ) ገልጠህ-ሽ አንብብና ለንስሐ ተዘጋጅ ለማለት ነዉ ጌታ ያግዝሽ

   Delete
  4. AnonymousDecember 23, 2013 at 10:55 PM
   MK is secretly organised Iapa ( ye Eapa sibsiboch nachew ye beg lemd lebsew yemetu.

   Reply
   Replies

   ወይንሸትDecember 25, 2013 at 12:17 AM
   ስለ ኢህአፓ ምን ታዉቅና ነዉ ደግሞ የምትቀባጥረዉ ስለ ማቅ ጸረ ወንጌልነት ማዉራት ትችላለህ በዚህ ዙሪያ እነዚህ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ትዉልዱ እንዳይድን ስለማድረጋቸዉ ተከራክረህ መባረክ እየቻልክ ስሙን እንኩዋን ለማንሳት ብቃት የሌለህ ሰዉ ስለ ኢህአፓ ታነሳለህ ስንቶች ዋጋ የከፈሉበትን ድርጅት እንዳንተ ያለ የከተማ አዉደልዳይ አፍ አይነሳምና እንዳይለምድህ ዝም ብለህ ኬክህን ግመጥ

   Delete
  5. @ብርሃን
   አንቺም እኮ መንተክተክ ጀመርሽ። ያው እንደምታውቂው መፅሃፍ ቅዱስ አንብብ የምትል የግብዞች ዋሻ ገባሽ። መፅሃፋንማ ብታነቢ ልግዛ ባላልሽ።
   ብርሃን ከደጀ ብርሃን

   Delete
  6. እግዚአብሔር የመረጠዉን እንዲገዛ ያደርጋል። አንድም የተደሰተበት ሕዝብ ሲገኝ መልካሙን ይሾምለታል።አለዚያ ደግሞ ለቅጣት ክፋዉን ያዝለታል። ሰለዚህ እኔ ልግዛ አላልኩም ሕዝባችን ገና ንሰሐ ስላልገባ እኔ ልገዛ አልችልም ።የሚወቅጠዉ ያዞለታልና እነሱዉ ገና መግዛት ይቀጥላሉ። ያንተከተከኝ ግን የብብት እሳት የሆነዉን ማቅን አስቀምጠህ ስትንጠራራ ብትዉል የማትደርስበት ኢህአፓ ጋ ምን ወሰደህ ነዉ። ፍየል ቅዝምዝም ወዲህ ....አሉ? ለማንኛዉም ምድራዊ ፖለቲካና ሃይማኖትን በመደባለቅ ቤተክርስቲያናችን የሆነችዉን ሆናለችና የክርስቶስ ብቻ እንድትሆን ጸልይ

   Delete
 17. Ere tewue kene yalfal EWNET TENAGERU!! Do not worry about us. We Know TRUST MAHBER KIDUSAN . THEY HAVE A LOT TO DO SO LEIVE THEM TO DO WHAT GOD TEL THEM.

  ReplyDelete
 18. MK is secretly organised Iapa ( ye Eapa sibsiboch nachew ye beg lemd lebsew yemetu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ኢህአፓ ምን ታዉቅና ነዉ ደግሞ የምትቀባጥረዉ ስለ ማቅ ጸረ ወንጌልነት ማዉራት ትችላለህ በዚህ ዙሪያ እነዚህ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ትዉልዱ እንዳይድን ስለማድረጋቸዉ ተከራክረህ መባረክ እየቻልክ ስሙን እንኩዋን ለማንሳት ብቃት የሌለህ ሰዉ ስለ ኢህአፓ ታነሳለህ ስንቶች ዋጋ የከፈሉበትን ድርጅት እንዳንተ ያለ የከተማ አዉደልዳይ አፍ አይነሳምና እንዳይለምድህ ዝም ብለህ ኬክህን ግመጥ

   Delete
 19. በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ብሎግ ላይ ብዙ ጊዜ እንደማነበው አብዛኛው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተነጣጠረ ራሱን የቻለ ተራ የጥላቻ ዘመቻ ከመሆኑ ሌላ ማኅበሩ ለሚውነጀልበት ጉዳይ አንድም ተጠጨባጭ የሆኑ ማስረጃዎች ሲቀርብ አንብቤም አላውቅም። አሁን ግን በትክክል እንደገባኝ ተራ ወሬ እየነዙ አላዋቂውን ለማሳሳትና ለጊዜው ጥርጥር ውስጥ ለመክተት በዓላማ የሚሠራ ብሎግ መሆኑን ከምንጊዜውም በበለጠ እየተረዳሁት ነው። አሁን ስለአዲስ አበባ ህ/ስብከት የመዋቅር ጥናት ላይ በተቃውሞ የተነሱ ጥቂት ግለሰቦች የተቃወሙት የብዙኃኑን አግልጋዮች የኑሮ መሻሻል እንጂ በማኅበሩ ላይ የሚያመጡት የቅንጣት ያህል ጉዳት አይኖርም። አንድ የማምንበት ጉዳይ አለ የጥናቱን ይዘት አንድ በአንድ በመተንተን ጎጂ ናቸው የሚሉትን እንኳ ነጥቦች አንስተው የገለጹት አንድም የሚታይ ቁም ነገር የለም። ይህ ከሆነ ዘንድ በግልጽ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አካሄድ በተለይ በአለፉት ሃያ ዓመታት የታየው የአስተዳደር ብልሹነት ካህናት፡ መነኮሳት ይሁኑ አይሁኑ በሚያጠራጥርበት ሁኔታ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ሰርገው በመግባታቸው አሁን የሚታየው ትርምስ ፈጠሪዎች የመሆናቸው አንዱ ትልቁ ማሳያ ሲሆን ይህንን ለማስቆም በማኅበርም ይሁን በግል በቤተ ክርስቲያን ልጅነት ለቤተ ክርስቲያን አጋር በመሆን የቆመ ወጣት ትውልድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱ ያስፈራቸውና በውስጥም ሆነ በውጪም ቤተ ክርስቲያኗን ለማዳከም የሚደረጉት ሤራ ከምንጊዜውም በበለጠ እየተገለጠ በመምጣቱ ነው። እናንተም የመድረኩ ተዋንያን በመሆናችሁ እውነት ለእናንተ ፍጽም እየራቀች ነው። ለጊዚያዊ ጥቅም ሲባል በቤተ ክርስቲያኗ የቆሸሸ እጅን ማንሳት የሚያመጣው መለኮታዊ ቅጣት ቀላል አይሆንምና ከወዲሁ ራሳችሁን መርምሩ።

  ReplyDelete
 20. መልካም ስራ ስሰራ ሰይጣን በእጥፍ ፈተና፡ ዉሸት ያበዛል፡፡ ነገሮች የፖለቲካ ይዘት ያላቸዉ አድርጎም ያቀርባል፡፡ ዋነኛዉ የሰይጣን ቀኝ እጅ በመሆን በዚህ ዘመን የሚሰራዉ ደግሞ የአባሰላማ ብሎግ ነዉ፤፤ለቤተክርስቲያን ዉድቀት ከምን ጊዜም በላይ ተግቶ ይሰራል፡፡አባቶችንም ያዋርዳል፡፡ ሰይጣን ቅዱሳንን ለመሳደብ በአባ ሰላማ ብሎግ በኩል አፉን ከፍተል፤፤ ማስተዋል ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 21. Aba Estifa yibdeachu

  ReplyDelete
 22. እናንተ የዚህ ብሎግ አዘጋጆችተሳድቦ አሰዳቢዎች

  ስለ አውሬው በራዕይ ዮሐንስ 13 ቁጥር 5 ጀምሮ እናንተን ስለሚመለከት ተመልከቱት እንዲህ ይላል ታላቅንም ነገርና ስድብንም የሚናገርበት አፍተ ሰጠው በአርባ ሁለት ወርም እንዲሰራ ሥልጣን ተሰጠው ።እግዚአብሔርንም ለመሰዳብ ሥሙንና ማደሪያውንም በሰማይየሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ። ይህ ትንቢት እየተፈጸመ በናንተ ላይ አየነው። እስቲ መለስብላችሁ አስቡ እራሳችሁን ተመልከቱ ጳጳሳቱን፧ካህናቱን፤ንፁሃን የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ምዕመናን እረ ስንቱን የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆኑትንሁሉ ይህ አፍተሳደበ አሰደበ እረ ይብቃችሁ ይግባኝ ለእግዚአብሔር ብለናል። ነገርግን እንድታውቁት የእግዚአብሔር ይቅደም ብሎግም ፍርድ ቤትይቆማል።


  ReplyDelete
 23. በማኅበረ ቅዱሳን የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር “ግብረ ፊልጶስ” የተሰኘ ሲምፖዚየም ታኅሣሥ 12 እና 13 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ አካሄደ፡፡


  gebra felp 1ታኅሣሥ 12 በብፁዕ አባታችን አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን፤ በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ጠረፋማ አካባቢዎች ከደቡብ ኦሞና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ወረዳዎች ተጋብዘው የመጡ ከዚህ በፊት በሀገረ ስብከቱና በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ በጋራ ተምረውና ተጠምቀው የነበሩ አገልጋዮችና ምእመናን ተገኝተዋል፡፡


  መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ “ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ” በሚል ርዕስ ትምህርት በመስጠት ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የየድርሻቸውን እንዲያበረክቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


  ከጠረፋማ አካባቢ የመጡት ምእመናን የሥላሴን ልጅነት በጥምቀት ያገኙ በመሆናቸው በአካባቢያቸው ስላለው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ምን እንደሚመስል ተጠይቀው ሲመልሱ፡- “ማኅበረ ቅዱሳን በአካባቢያችን ከፍተኛ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በመስጠት ባለፈው ዓመት ብቻ ከ3700 በላይ ምእመናን የጥምቀት አገልግሎት አግኝተናል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ወደ አካባቢያችን በመምጣት ከጨለማ ወደ ብርሃን አውጥቶናል፡፡ ማኅበሩ በቀጣይነትም በቋንቋችን የሚያስተምሩ አገልጋዮችን እንዲያሰለጥንልን እንፈልጋለን፡፡ በአካባቢያችን የተለያዩ የእምነት ድርጅቶቸ በመግባት የቀደሙት አባቶቻችን ሃይማኖት የሆነውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ቤተ ክርስቲያን እንዳንከተል ከፍተኛ ግፊት እያደረጉብን ነው” ብለዋል፡፡


  “የኦርቶዶክስ እምነት ጥንት የቀረ ነው፤ ማስተማር አትችሉም በማለት ከፍተኛ ስቃይ እያደረሱብን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስለሌለን በድንጋይ ላይ ቁጭ ብለን ነው የምንማረው፡፡ በደቡብ ኦሞ ኣሬ ወረዳ ብቻ በቅርቡ ከ800 በላይ ወገኖቻችን ጥምቀትን ያገኙ ሲሆን 365 ከሚሽን የተመለሱ፤ 200 ደግሞ ሃይማኖት አልነበራቸውም” በማለት በአካባቢያቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ገልጸዋል፡፡


  ReplyDelete
 24. ማቅን ከሚቋወሙ አንዱ ነኝ ምክንያቱም በመንፈሳዊ ተሐድሶ ላይ ያላቸው አቋም አነስተኛ ስለሆነ ነው። ቢሆንም አሁን እየሰሩት ያሉት ማሻሻያ የሚደገፍና የሚበረታታ ነው

  ReplyDelete