Thursday, December 26, 2013

የዳንኤል ክብረትን ጥፋት ማን ያርመው?

ከመምህር አዲስ
መንደርደሪያ
በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ሚዲያውን ያፍናል እየተባለ ከተቃዋሚዎችና ከግል ጋዜጠኞች በኩል ሮሮ ይሰማበታል፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ነጻ የሚባሉት ሚዲያዎች ብዙዎቹ ራሳቸው ከወገንተኛነት ያልጸዳ አሠራርን የሚከተሉና ነጻ አስተሳሰብን የሚያፍኑ ሆነው መገኘታቸው ነው፡፡ በተለይ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚወጡ ዘገባዎች ነጻ በተባሉ ሚዲያዎች ዘንድ የሚዘገቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ፍላጎትና ጥቅም አንጻር ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ተችቶ ወይም ከማኅበረ ቅዱሳን በተጻራሪ ቆሞ ነጻ ሐሳብን ማራመድ እጅግ ከባድ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁንም ያ ሁኔታ አልተለወጠም፡፡ ታዲያ ራሳቸው ነጻ አስተሳሰብን እያፈኑና የአንድ ወገን ዘገባን ብቻ ሚዛናዊ ባልሆነ መልኩ ማቅረብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ሚዲያ የሚባለውን አካል ጥያቄ ውስጥ አይከተውም ትላላችሁ፡፡ ይህን ለማለት ያበቃኝ ከሳምንታት በፊት “አዲስ ጉዳይ” በተሰኘ መጽሔት ላይ ዳንኤል ክብረት በሁለት ክፍል ለጻፈው ጽሑፍ ምላሽ አዘጋጅቼ ለመጽሔት ክፍሉ ብልክ የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረቱ ነው፡፡


“አዲስ ጉዳይ” ዳንኤል ክብረት የሚያዝበትና ባለድርሻ (Shareholder) የሆነበት መጽሔት እንደሆነ በስፋት ይወራል፡፡ ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን ነጻ ነኝ የሚለው “አዲስ ጉዳይ” መግፈፉ ግን ተገቢ አልነበረም፡፡ ዳንኤል ክብረት ብዙ መረጃዎችን አዛብቶ በሁለት ክፍል ያቀረበው ጽሑፉ እንዲተችና ጸሐፊው እንዲታረም ስላልተፈለገ ይሁን ሌላ ምክንያት ኖሮ ባላውቅም የተላከውን ጽሑፍ ሊያስተናግዱ አልወደዱም፡፡ ዳንኤልም ቢሆን ባቀረበው ጽሑፍ ላይ የተሰጠው ምላሽ እንዲስተናገድ ቢያደርግ  ለእርሱ ጥሩ እንጂ መጥፎ አልነበረም፡፡  ከአዲስ ጉዳይ ሌላ ለዕንቁና ለሎሚ መጽሔቶች ጽሑፉ ቢላክም እነርሱም ሊያስተናግዱት አልወደዱም፡፡ እንደእኔ ያሉ ሐሳባቸው ለሚታፈንባቸው ግለሰቦች አባሰላማ ብሎግ ባይኖር የት እንተነፍስ ነበር እላለሁ፡፡ ለመጽሔቶቹ ተልኮላቸው የነበረው ጽሑፍ እነሆ!

የዳንኤል ክብረት ተስፋዬ ገብረአብን አርማለሁ ብሎ ጥፋቶችን ፈጽሟል
አንዳንድ ነገሮች ባለማወቅ ሲበላሹ ስሕተት ተፈጸመ ሊባል ይችላል፤ ያው ነገር ሆን ተብሎና ታቅዶ ሲፈጸም ግን ጥፋት ተፈጸመ ነው የሚባለው። ዳንኤል ክብረት ተስፋዬ ገብረ አብን በመተቸት ሲጽፍ ዓላማው ስሕተትን ማረም እንደ ሆነ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ እርሱ ያደረገው ስሕተቱን ማረምና እውነትን መመስከር ሳይሆን እርሱ የሚያምንበትንና በተስፋዬ እይታ ስሕተት የተባለውን የተክለ ሃይማኖትን ጕዳይ መከላከል ነው። ይህን ሲያደርግም ብዙ እውነታዎችን አስተባብሏል።

ዳንኤል ሳያውቅ በጋዜጣና በመጽሔት ላይ በሚጽፋቸው ጽሑፎች ያገኘውን ዕውቅና እንደ ሊቅነት በመውሰድ በሁሉን ዐዋቂነት ወንበር ላይ ራሱን አስቀምጧል። ይህ ሁሉ ሲሆን ተው ባይ ስለጠፋ፣ ዳንኤል በራሱ ጊዜ ራሱን ወደማይሳሳትና “ተጠያቂ የታሪክ ሊቅ” ወደ መሆን አሸጋግሯል። ዳንኤልን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ ያለው ማን ይሆን? የኢቲቪ ጋዜጠኞች? (ይህን ታይትሉን ያየነው በቴሌቪዥን ነውና) ወይስ …  

ተስፋዬ ገብረ አብ “የስደተኛው ማስታወሻ” በሚል ርእስ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ በገጽ 306 ላይ “የፍሥሓ ጽዮን ፖለቲካ” በሚል ርእስ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጻፈው ጽሑፍ አለ። ይህን አስመልክቶ ከሁለት ሳምንት በፊት ዳንኤል ክብረት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ በሁለት ተከታት ዕትሞች ተስፋዬ “የማያውቀውን ነገር ጽፏል። ስለማያውቀው ነገር የጻፈው ባለማወቁ ብቻ አይመስለኝም። አንድም ለማወቅ ባለመፈለጉ፣ አሊያም ሆን ብሎ የማፍረስ ዓላማ ይዞ ይመስለኛል።” ሲል ተችቶታል።

ዳንኤል እንዲህ አፉን ሞልቶ ሲናገር እርሱ እጅግ ዐዋቂና የሚለው ሁሉ እውነት የሆነ ይመስላል። ዳንኤልን በሚገባ ያላወቁት ሰዎች እንዲህ እንደሚያስቡ እገነዘባለሁ። ነገር ግን ዳንኤል ያቀረበውንና፣ “ተስፋዬ ተሳስቷል፤ ትክክለኛው ታሪክ እኔ የማቀርብላችሁ ነው” ዐይነት ድምፀት ያለውን ሐሳቡን ስንመለከትና አንባብያንን ለማሳሳት ያቀረባቸውን የተዛቡ መረጃዎቹን ስናጤን ዳንኤል አስመሳይ እንጂ እውነተኛ “ታሪክ ተመራማሪ” አለመሆኑን እንረዳለን። ለነገሩ ይህን “ታይትል” ዳንኤል ከየት እንዳገኘውና ማን እንደ ሰጠው ቢያብራራልን ደግ ነው ስል በድጋሚ እጠይቃለሁ።

እስከዚያው ግን ራሱን በራሱ የታሪክ ተመራማሪ እንዳለ እንቁጠርና ያቀረባቸውን የተሳሳቱና የተዛቡ መረጃዎች እንመልከት። ዳንኤል ለተስፋዬ ጽሑፍ ምላሽ ሲሰጥ ያላጠናቸውንና ከቅንፋዊ ማስታወሻ ወይም ከዋቢ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ የገለበጣቸውን ጥቅሶች በመደርደር “የታሪክ ተመራማሪ” ነኝ ለማለት እንደዳዳው ምንም አያጠራጥርም። ይህ በተለይ “የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች” በሚል፣ ስም ለውጦ ባወጣውና “ዐማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት” በተሰኘው የዶ/ር ስርግው ሐብለ ሥላሴ ሥራ ላይ በፈጸመው ቅሰጣ ድርሰት /ፕሌጀሪዝም/ ታይቷል። (ከዚህ መጽሐፉ ጋር በተያያዘ በሌላ ጊዜ በሌላ ጽሑፍ እመለስበታለሁ)። 

እስኪ አንዳንድ ጥፋቶቹን ወደማረም እንግባ፤ ገድል ጠቃሹ ዳንኤል ገድለ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ በሌሎች ስፍራዎች ያሉትን ጨምሮ፣ በኢየሩሳሌም ስላሉት ሦስት ገድላት ጠቅሷል። ይሁንና እነዚህ ገድላት የሸዋ ነገሥታት በስጦታ ያበረከቷቸው መሆናቸውን “ደብረ ሥልጣን በኢየሩሳሌም” የተሰኘው የአቡነ ማቴዎስ መጽሐፍ በገጽ 25 ላይ ይተርካል። በመሆኑም እነዚህ ገድላት ወደፊት እንደምንመለከተው የቀዳማይ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ለዕጨጌው የሰጡና የእርሳቸው ሆነው የተቈጠሩ ገድላት እንደ ሆኑ መገመት አይከብድም። ዳንኤል ግን “የሰባተኛው መክዘ ተክለ ሃይማኖት የሉም።” ሲል በድፍረት ጽፏል። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌንም “የለም” እንዲሉ እማኝ አድርጎ ጠርቷል። ይህን ከእርሳቸው ማረጋገጥ ግን ሳያስፈልግ አይቀርም። 

ዳንኤል አለአቅሙ የተቻቸው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ስለ ቀዳማይና ደኃራይ ተክለ ሃይማኖት “ሃይማኖተ አበው ቀደምት ወፍልጠተ ውሉድ ደኃርት” በተሰኘው ድንቅ መጽሐፋቸው ላይ ተርከዋል። ቀዳማይ ተክለ ሃይማኖት ያረፉት በስምንተኛው ምእት ዓመት (በ710 ዓ.ም.) መሆኑን ምንጭ ጠቅሰው በዜና ቅዱሳን አበውና በሌሎችም ይህ ጕዳይ መታወቁን መስክረዋል። በዚህ ስም (በተክለ ሃይማኖት) ከዚያ በኋላ የዛጔ ንጉሥ መራ ተክለ ሃይማኖት መጠራቱን፣ በኋላም መንግሥትን ከዛጔ ወገን ወደ ይኩኖ አምላክ በማዛወሩ ሂደት ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዕጨጌ ተክለ ሃይማኖት መጠራታቸውን ጠቅሰዋል። እኚህ ተክለ ሃይማኖት (ዕጨጌው) በመጀመሪያ ባለትዳር የነበሩ ሲሆን የመነኰሱት በኋላ ነው ይላሉ። ከዚህ የተነሣም ስለእርሳቸው ውስጠ ምስጢሩን የሚያወቁ ጎንደሮች “አቦ ብልኃት ዕጨግነት ከሚስት” ብለው እንደተረቱባቸው ይኸው መጽሐፍ ይጠቅሳል።

ስለ ዕጨጌ ተክለ ሃይማኖት ትክክለኛ ማንነት የሚጠቅስ ገድል በአንዳንድ ገዳማት እንደሚገኝና ሰውዬው አስቀድመው ሕጋዊ (በጋብቻ የተወሰኑ) ካህንና ባለጠጋ እንደ ነበሩና ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዳልመነኮሱ፣ በኋላ ላይ እንደ መነኰሱ እነዚሁ ገድላት እንደሚናገሩ ጠቅሰዋል። ይህን ምስጢር የያዙት ገድላት በአንዳንድ አድባራትና ገዳማት ውስጥ እንዳሉና በተለይም ወይንጌ ዘብሔረ ወግዳ፣ በግራርያ ዘበጌምድር እንደሚገኙ ጠቅሰዋል። አክለውም ዕጨጌው ከሞቱ ከ254 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ለእርሳቸው መሰጠቱን እንዲህ በማለት ይተርካሉ፤ “ከግራኝ በኋላ ባፄ ሚናስ ዘመን ዕጨጌው ተክለ ሃይማኖት በሞቱ በ፪፻፶፬ ዓመት የኋላ ሰዎች እናባ ዮሐንስ ከማ እንደ ቅኔና እንደ ድርሳን ቀምመው አጣፍጠው የጣፉት ገድል ግን የጻድቁን ሥራ ለዕጨጌው ሰጥቶ ጻድቁንና ዕጨጌውን በሙጫ ጸያፍ አጣብቆ ለጥቆ ባንድ ስም ጨፍልቆ ፩ ሰው አድርጎ ያልጠራ ያልበራ ድፍርስ ጨለማ ታሪክ ይተርካል። በጻድቁና በጨጌው መካከል ፪ቱን የሚለይ ታላቅ ረዥም ገደል ፭፻፶ ዓመት አለ።” (ሃይማኖተ አበው ቀደምት ገጽ 12)።  

ዳንኤል የለም ብሎ የካደው የመጀመሪያው ተክለ ሃይማኖት ገድል “የሮማውያን ስንክሳርና በሺሕ ካርባ ኹለት (፲፻፵፪) ዓመተ ምሕረት በላስቶች ዘመን ተጥፎ ከደብረ ሊባኖስ ወደ ኤውሮፓ የኼደው ጥንታዊው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ሥጋዊና ደኃራዊ (በኋላ የተፈጸመ) ነገር ሳይጨምር መንፈሳዊና ቀዳማዊ ብቻ ይተርካል። ይህነንም ገድል አንድ ፩ ባለታሪክ ዲልማንና አንጧን ዳባዲ የሚባሉ ግእዝ ዐዋቆች የኤውሮፓ ሊቆች በእንግሊዞች አገር አግኝተው እንዳዩትና እንደ መረመሩት በመጣፋቸውም እንደ ጠቀሱት ዛሬም በሎንዶን እንዲገኝ ይናገራል።” (ሃይማኖተ አበው ቀደምት ገጽ 11)።

ይሁን እንጂ ዳንኤል ይህን የተክለ ሃይማኖትን ጉዳይ አስመልክተው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ምንጮችን ጠቅሰው የጻፉትን ክቡር ሥራ በማጣጣል እንዲህ ብሏል፤ “አለቃ ኪዳነ ወልድ በብዙ ሥራዎቻቸው የተከበሩና የተመሰገኑ ሊቅ ናቸው። አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ላነሡት ሐሳብ ግን ያቀረቡት ማስረጃ የላቸውም።” ከላይ የጠቀሷቸው ምንጮች የዳንኤልን ሐሳብ ስላልደገፉ ትክክል አይደሉም ሊባል ነው? ወይስ አንባቢን ለማደናገር? ስለዚህ ዳንኤል አለአቅሙ በመንጠራራት ሊተቻቸው ሲሞክር ፕሮፌሰር መስፍን በትክክለኛው ቦታ ዳንኤልን የገለጹበትን አባባል ልጠቀምና “ዳንኤል የአለቃ ኪዳነ ወልድን መጽሐፍ አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም” ልበል።

አለቃ ኪዳነ ወልድን የመሰለ ሊቅ፣ ይህን ዳንኤልና መሰሎቹ ሊቀበሉት የማይፈልጉትን ሐቅ የጻፉት፣ መረጃውን ስላዩት ወይም ስለ መረጃው ስለ ሰሙ እንጂ እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተው ልቦለድ ይጽፋሉ ማለት አስቸጋሪ ነው። ከዕጨጌ ተክለ ሃይማኖት ጋርስ ምን ጠብ ኖሯቸው ይህን ያደርጋሉ? ዳንኤል ለመቀበል ስላልፈለገ ነው እንጂ ኪዳነ ወልድ በመዝገበ ቃላታቸው ላይ ስለ ተክለ ሃይማኖት በተጨማሪ የሚከተለውን አስፍረው “ታሪክና ገድል እይ” በማለት ምንጭ ጠቅሰዋል። “… ዕጨግነትም የተዠመረ በ፲፪፻፷፫ (፶፫) ዓመት ይኩኖ አምላክን ቀብተው ባነገሡ በዳግማይ ተክለ ሃይማኖት ነው። ርሳቸውም በናታቸው የነገሥታት ወገን የይኩኖ አምላክ ያክስት ልጅ ወይም የናት ወንድም አጎት ወዲህም የደብረ ሊባኖስ አበምኔት ነበሩ ይባላል። ፊት በሕግ ቀሰው በኋላ መንኵሰው አቡን ስለ ኾኑ ያልተማሩ ሰዎች የማይገባ መስሏቸው አቦ ብልኀት ዕጨግነት ከሚስት ብለዋቸዋል። ዳግማይ ማለትም በ፯ኛው (ሴክል) መቶ ይህን ሐዲስ ስም ተክለ ሃይማኖት መባልን እንደ ያዕቆብ በጌታ ቃል ለተሰየሙት ለጻድቁና ለቅዱሱ ለታላቁ ሐዋርያ እንጂ በ፲ኛው (ሴክል) መቶ መንግሥትን ከድልነዓድ ወስዶ መዠመሪያ ከዛጔ ወገን ለነገሠው መራ ተክለ ሃይማኖት ለተባለው ለላሰታው ንጉሥ አይደለም። በጻድቁና በጨጌው መካከል ያለው ዘመን ከ፭፻፶ ቢበልጥ እንጂ አያንስም።”(ታሪክና ገድል እይ) (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ ፬፶፯)።

አለቃ ኪዳነ ወልድ በመዝገበ ቃላታቸው ውስጥ ምንጮችን በዚሁ መንገድ ነው የሚያስቀምጡት። ታዲያ ታሪክ እና ገድል ያሉት የሌለ ምንጭ ነው ማለት እንዴት ይቻላል? መዝገበ ቃላታቸው ከመጻፉ በፊት ውስጥ ውስጡን የሚነገርና በኋላ እንዲጠፋ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ግምት አለ። ይህን አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል፤ “ሀሎ ጽሑፈ ማእከለ ገድል ከመሰ ኢይርአዮ ሰብእ ወኢያንብቦ ከመ ኢይበል ላዕሌሁ ቃለ መሐደምት ከመ ሰብአ ጎንደር ደኀርት ‘አቦ በልኀት ዕጨግነት ከሚስት’ ሀሎ ስፉየ ወልጹቀ ጥቁበ ወድርጉሐ ኅቱመ ወዝጉሐ እስከ ዮም።”
ትርጓሜ፦ “በገድሉ መካከል ሰው እንዳያየው እንዳያነበውም፣ እንደ ኋለኞች የጎንደር ሰዎችም ‘አቦ ብልኀት ዕጨግነት ከሚስት’ የሚል የቧልት ንግግር እንዳይናገር እስከ ዛሬ ድረስ ተሰፍቶ፣ ተገጥሞ፣ ታስሮ፣ ተደርቶ፣ ታትሞና ተዘግቶ ይገኛል።” በማለት ይህ ምስጢር እንዳይወጣ የተሠራውን እውነትን የማዳፈን ሥራ አጋልጠዋል (ሃይማኖተ አበው ቀደምት ወፍልጠተ ውሉድ ደኀርት ገጽ 9)። ይህም ሁኔታ እንደ ዳንኤል ያሉ አንዳንዶችን ትረካው ምንጭ የለውም እንዲሉ ሰበብ ሆኗቸዋል።

ምናልባት የመጀመሪያውን ተክለ ሃይማኖትን ታሪክ ለዳግማዩ (ዕጨጌው) ተክለ ሃይማኖት የሰጡ ክፍሎች ስለ ዕጨጌው ትክክለኛ ማንነት የተጻፈውን አጥፍተዉት እንደ ሆነ ምንም አያጠራጥርም። ደፋሩ ዳንኤል ግን አፉን ሞልቶ “እስካሁን ግን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ሆኑ ሌሎች የሚሉት ‘ሌላ ገድል’ አልተገኘም። አለቃም ያነበቡት ከሆነ ያነበቡትን፣ ያገኙት ከሆነም ያገኙበትን አልነገሩንም። ምንጭ የላቸውምና ለታሪክ ክርክር ሊጠቀሱ አይችሉም።” ብሏል። ይሁን እንጂ እስካሁን አለቃ ኪዳነ ወልድ ካቀረቧቸው ምንጮች በተጨማሪ ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ “መርሐ ልቡና” በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ የቅዱሳንን የገድላት መጻሕፍት ቍጥር በዘረዘሩበት ክፍል ውስጥ ኹለት ዐይነት ገድለ ተክለ ሃይማኖት እንዳለ ጠቅሰዋል። እነርሱም፦ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ እና ገድለ ተክለ ሃይማኖት ዘተንቤን ናቸው (1945፣ 78)። እዚህ ላይ የተንቤኑ ገድል የቀዳማይ ተክለ ሃይማኖት ገድል እንደሆነ አያጠራጥርም።

“የደብረ ሊባኖስ ገዳም አመሠራረት ታሪክና ዜና” በሚል ርእስ በግንቦት 12/1989 ዓ.ም. የታተመች ትንሽ መጽሐፍ “አንዳንድ በአለ ታሪኮችን የሚያወዛግቡ ልዮ[ዩ] ልዮ[ዩ] ተክለ ሃይማኖቶች እንዳሉ ይነገራል። አንዱ በዘመነ አክሱም ፍጻሜ ላይ ትግራይ ውስጥ በብሕትውና ኖረው ከአለፉ በኋላ ቤተክርስቲያን የታነጸላቸው፤ ገድል የተጻፈላቸው ጻድቅ አባ ተክለ ሃይማኖት የተባሉ መንፈሳዊ አባት ናቸው።” (ገጽ 6)። መጽሐፉ አክሎም ስለ ዕጨጌ ተክለ ሃይማኖት ሲተርክ “የቤተ ክህነት ትምህርታቸውን እያጠናቀቁ ከአደጉ በኋላ በማእረገ ድቁናና ቅስና፤ በኋላም በምንኩስና ሳሉ …” እያለ ይተርካል። በዚህ ውስጥ ቅስና የያዙት ከምንኩስና አስቀድሞ መሆኑ ተጠቁሟልና ምናልባት በመጀመሪያ ባለትዳር ቄስ እንደነበሩ ሊያመለክት ይችላል። ምክንያቱም በቤተክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት አንድ ዲያቆን ሊቀስ የሚችለው ሚስት አግብቶ ወይም መንኩሶ ነው። በዚህ ንባብ ውስጥ ግን ከምንኩስናው ቅስናው ስለቀደመ ያገቡ ቄስ መሆናቸው በግልጽ ይታያልና፣ ከምንኩስና በፊት አስቀድመው መቅሰሳቸውም ተጠቅሷልና የቀሰሱት (ቄስ የሆኑት) አግብተው መሆን አለበት። ስለዚህ በትዳር ውስጥ ያለፉና በኋላ መንኩሰው የጰጰሱ ሰው ነበሩ ማለት ነው ከሚለው ከአለቃ ኪዳነወልድ ትረካ ጋር ይስማማል።

ፍንጭ ፍተሻ በተሰኘችው ትንሽ መጽሐፍ ላይ ዶ/ር ሐዲስ የሻነውም ዕጨጌውን ዳግማዊ ተክለ ሃይማኖት” ብለው ጠርተዋቸዋል። ለምን ዳግማይ አሏቸው? ቀዳማይ ተክለ ሃይማኖት በመኖራቸው አይደለምን? አያይዘውም ዕጨጌ ተክለ ሃይማኖት ለቤተክርስቲያን ሲሦ መንግሥት በማሰጠታቸው ባለውለታ መሆናቸውን ጠቅሰዋል (ፍንጭ ፍተሻ ገጽ 44)።  ይሁን እንጂ ብዙዎች የተስማሙበትን የተክለ ሃይማኖትን ፖለቲካዊ ሰብእናና መንግሥትን ከዛጔ ሰሎሞናዊው ነኝ ወደሚለው ወደይኩኖ አምላክ ለማዛወር ያደረጉትን ተጋድሎ በማስተባበል፣ ዳንኤል እርሳቸው ከቅድስና በቀር ፖለቲካ ውስጥ ያልገቡና ሲሦ የሚባል መንግሥት ያልተቀበሉ “ጻድቅ” መሆናቸውን ጽፏል። ለዚህ ብዙዎች ለተስማሙበት እውነት ማስረጃ መጥቀስ አንባቢን ማታከት ስለሚሆን ፍርዱን ለአንባቢ መተዉ የተሻለ ነው። እንግዲህ ዳንኤል በስምንተኛው ምእት ዓመት በነበሩት ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ገድል ሌላ ሰብእና መላበስ የቻሉት ዳግማዊ (ዕጨጌ) ተክለ ሃይማኖት ያለሙት ብቻ ሳይሆን ያጠፉትም ተጠቅሶ ከሚሰነዘርባቸው ትችት እንዲያመልጡ ለማድረግ ሲል እነዚህን ሐቆች ክዷል። 

መ/ር ጽጌ ስጦታው ባሕታዊ ሰይጣን በሚል ርእስ ከግእዝ ወደ ዐማርኛ ተርጕሞ ያሳተመው መጽሐፍ ምንጩ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ “ሃይማኖተ አበው ቀደምት ወፍልጠተ ውሉድ ደኃርት” የተሰኘው መጽሐፍ ነው። ዳንኤል ግን የጽጌ ሥራ እንዳይታወቅ ሆን ብሎ ለመሸፈን ያሰበ ነው የሚመስለው። ምክንያቱም ጽጌ በተክለ ሃይማኖት ላይ ተመሳሳይ ሐሳብ የሰነዘረው በጽሑፍ ይሁን በቃል ዳንኤል ምንም ያለው ነገር የለም። ምናልባት ማስታወቂያ መሥራት እንዳይሆንብኝ ብሎ በምቀኝነት ያደረገው ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሪ አለኝ።

በዳንኤል ላይ “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ” የሚለው ቃለ ወንጌል ተፈጻሚ ሆኖበታል። ይኸውም እርሱ ስለተስፋዬ አስተያየት ሲሰጥ ተስፋዬ “በአንዳንድ ጉዳዮችም ሆን ብሎ ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ያሉ” እንደሚመስለው ጠቅሷል። እውነት ነው። ይሁን እንጂ ዳንኤልም በተረት ላይ የተመሠረቱ አንዳንድ ሃይማኖታዊ ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲፈተሹና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሲጋጩ እንዲስተካከሉ የሚፈልግ አይመስልም። ለምሳሌ ስለቦሩ ሜዳው ክርክር በጠቀሰበት ክፍል ውስጥ ዐፄ ዮሐንስ  በመጨረሻ ላይ አንደኛው ተከራካሪ ስላቀረበው ሐሳብ ቤተ ክርስቲያን ለሃይማኖት ትምህርት መሠረት አድርጋ ከምትመራባቸው መጻሕፍት (ከአራቱ ጉባኤያት) ማስረጃ እንዲያቀርቡ በጠየቋቸው ጊዜ ማስረጃ አድርገው የጠቀሱት የደብረ ብርሃንን ተኣምረ ማርያም ነበር። በዚህ ጊዜ ንጉሡ “ከምታስተምረው ከአራቱ ጉባኤ ዐጣህና ስለ ሃይማኖት ተኣምረ ማርያም ትጠቅሳለህን?” እንዳሏቸው መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ጽፈዋል (መጽሐፈ ቅኔ ዝክረ ሊቃውንት 1963 ገጽ 282)። ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።

ዳንኤል ግን ከዚህ ጥቅስ ውስጥ ሆን ብሎ ያጎደለው ሐረግ አለ፤ - “ስለ ሃይማኖት” የሚለውን ሐረግ። ይህን ያደረገው ተኣምረ ማርያም ስለሃይማኖት የሚጠቀስ መጽሐፍ አለመሆኑን ስለሚናገርበትና እርሱ በካበው ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ገድላዊ ትምህርት ላይ ጥያቄ ስለሚያከትልበት ነው። መቼም “ስለ ሃይማኖት” የሚለውን ዳንኤል ሆን ብሎ ቢገድፈውም በዚህ ስፍራ የተያዘው ጉዳይ ሃይማኖታዊ በመሆኑ ተአምረ ማርያም ለሃይማኖት ማስረጃነት የሚጠቀስ መጽሐፍ አለመሆኑ መነገሩን ማስተባበል አይችልም። በደፈናው እንኳ “ከተአምረ ማርያም ትጠቅሳለህን” መባሉ ተአምረ ማርያም እንደ ዳንኤል ባሉ ገድል ጠቃሾች ዘንድ እንጂ በሊቃውንቱ ዘንድ ያለውን ዝቅተኛ ስፍራ፣ እንዲያውም ለምንም መጠቀስ የማይገባው መጽሐፍ መሆኑን ያሳያል።

ሌላው ዳንኤል የተሰፈረበትና እርሱ ተስፋዬን የሰፈረበት መስፈሪያ አላዋቂነቱን እንደ ዕውቀት  መውሰዱ ነው። ለምሳሌ ከማይክሮፊልም ጋር በተያያዘ ያቀረበው መረጃ ምንጭ የሌለው ከመሆኑም በላይ በጉዳዩ ላይ የተጻፉ ተጨባጭ መረጃዎች ከሚሉት ተቃራኒ የሆነ የተሳሳተ መረጃ ነው የሰጠው። “ማይክሮፊልም የተነሡ መጻሕፍት ካታሎግ” በሚል ርእስ በ1966 ዓ.ም በትምህርትና ሥነጥበብ ሚኒስቴር የባህልና የውጭ እርዳታ ዋና መምሪያ የታተመው መጽሐፍ እንደሚጠቍመው መጻሕፍቱ የተነሡት ከአዲስ አበባና ከጐጃም ጠቅላይ ግዛት ነው። ጊዜውም ከጳጉሜ 3/1961 - የካቲት 2/1962 ዓ.ም. ድረስ ነው። ታዲያ ዳንኤል ከየት አምጥቶ ነው ሥራው የተጀመረው በ1964 ከሰሜን ሸዋ ነው ሊል የደፈረው? ምናልባት ይህ ስለጉዳዩ የሰማ እንጂ ያነበበ አለመሆኑን አሳብቆበታል። እንዲያ ከሆነም “እንደ ሰማሁት” ብሎ እንጂ እንዳነበበ ሰው ደረቱን ነፍቶ አፉን ሞልቶ የተሳሳተ መረጃ ለአንባቢ መስጠት አልነበረበትም።

በዩኔስኮ ተንቀሳቃሽ ማይክሮፊልም ጓድ የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለይ ከጐጃም ማይክሮፊልም ለተነሡት መጻሕፍት ታላቅ ባለውለታ የነበሩት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ መሆናቸው ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ላይ ተመልክቷል። ጓዱም “ከጐጃም ጠቅላይ ግዛት የተገኙት መጻሕፍት ምርጫ ሥራ ሊቃና የቻለው ከመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ በተገኘው የዐዋቂነት ምክርና መመሪያ ነው፤ ይህንንም ጓዱ እንደ ከፍተኛ ውለታ ይቆጥረዋል” በማለት ትልቅ አክብሮቱን ገልጿል። ዳንኤል ግን ይህን ለሊቁ የተሰጠውን ዋጋ አለመጥቀሱና ስርግው ሐብለ ሥላሴን ብቻ ማንሣቱ ስለጉዳዩ (በሚገባ ሳያጣራ) የሰማ እንጂ ያነበበ አለመሆኑን ይጠቍማል። ይህን ያደረገው ደግሞ ከላይ ለመጠቈም እንደተሞከረው በስርግው ሥራ ላይ የፈጸመውን ቅሰጣ ድርሰት በዚህ አጋጣሚ ያካካሰ መስሎት ሊሆን ይችላል።

ዳንኤል ለተስፋዬ ገብረአብ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት ሲነሣ ዐላማው ምን ይሆን? ከዚህ ቀደም በተክለ ሃይማኖት ላይ ተወዳጅ የሆነና እስከድብደባ የደረሰ ዋጋ ያስከፈለውን ጽሑፍ ለጻፈውና ዳንኤል ጻድቅ በሚላቸው ዕጨጌ ተክለ ሃይማኖት ላይ “እግር አልባው ባለክንፍ” በሚል ርእስ መጽሔት ላይ ላቀረበው ጽሑፍ የሰጠው ምላሽም እዚህ ግባ የሚባል እንዳልነበረ አንባቢ አይረሳውም ብዬ አስባለሁ፡፡   

በዕውቀቱ ሥዩም በተባ ብዕሩ በባህላችን ላይ ሒስ ሲሰነዝር ባህላችን ሃይማኖታዊ ነው ከማለት ይልቅ ተክለሃይማኖታዊ ነው ቢባል የተሻለ ነው ብሎ ነበር። ይህን ሲያብራራም “በገድላቸው እንደሰማነው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙ ዓመታት ቆመው በመጸለያቸው እግራቸው ተሰበረ። ፈጣሪም በገድላቸው ጽናት ተደስቶ ደርዘን ሙሉ ክንፍ ሸለማቸው። ታሪኩ ተፈጽሟል ወይስ የደብተራ ፈጠራ ነው የሚለው አያሳስበኝም። ግን በግሌ ሚዛን ስገመግመው ለጻድቁ የቀረበላቸው ካሳ የሚበጃቸው አልመሰለኝም። በምድር ተወስኖ ለሚኖር ሰው ለእግር ዕጦት ክንፍ ጥሩ ማካካሻ አይደለም። እግሩን ላጣ ሰው ፈጣንና ብርቱ እግር ቢተካለት የበለጠ ይጠቅመዋል።” እያለ የተክለ ሃይማኖትን እግር አጥቶ ክንፍ የማብቀል ቧልት ይተቻል። እንደ እርሱ ሁሉ አንድ ባለቅኔም ቀደም ብሎ ስለ ተክለ ሃይማኖት ከተቀኘው ቅኔ ሦስት ስንኝ ቆንጥሮ የሚከተለውን ትችት አቅርቧል፦
“ዘገቢረ ጸሎት አዝለፈ
ብሂሎ አወርድ ዘተሰቅለ ክንፈ
ዘአኀዘ ሰኰና ገደፈ” 
(ትርጉም) 
“ጸሎትን ያዘወተረ (አብዝቶ የተማለለ)
የተሰቀለ ክንፍ አወርዳለሁ ብሎ
የያዘውን ተረከዝ ጣለ”
ባለቅኔው ጻድቁ የተሰቀለ ክንፍ [ለ]ማውረዳቸው እንኳ እርግጠኛ አይደለም። “የተሰቀለ ክንፍ አወርዳለሁ ብሎ” የሚለው መሥመር ጥርጣሪውን ይገልጣል። ተረከዛቸውን ለመጣላቸው ግን እርግጠኛ ነው። እንግዲህ በሰማዩ ላይ አለቅጥ ሲያተኵር ምድሩን የሚከዳ ምድርም የምትከዳው ማኅበረሰብ ተክለ ሃይማኖታዊ ነው።”

ይህንና ይህን ለመሰለውና በዕውቀቱን ለድብደባ ለዳረገው ትችት ዳንኤል በጊዜው የሰጠው ምላሽ በዕውቀቱ ማሰብና መጻፍ ባልፈለገበትና ዳንኤል በዕውቀቱ እንዲያስብና እንዲጽፍ በሚፈልግበት መንገድ ነው፡፡ ዳንኤል በዕውቀቱን ሊከራከረው የሞከረው ተክለ ሃይማኖት ክንፍ ያበቀሉት እግር ከማጣታቸው በፊት ነው እንጂ እግር ካጡ በኋላ ማካካሻ ተደርጎ ተሰጥቷቸው አይደለም በሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ እግራቸው የተቆረጠበትን ምክንያት ሊገልጽ አልወደደም፡፡ ያው እንደተለመደው በአንድ እግራቸው ቆመው ሲጸልዩ ነው እግራቸው የተቆረጠው ከሚለው ምክንያት ውጪ ሊያቀርብ እንደማይችል በወቅቱ በጽሑፉ አስነብቦናል፡፡ ይህ ግን በሸዋዎች ዘንድ እንጂ በዛጔዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ተክልዬ አንድ እግራቸውን ያጡበትን ምክንያት የምናውቅ እኛ ነን፤ መንግሥትን ሲያዛውሩ በተነሣው ጦርነት ነው አካል ጉዳተኛ ያደረግናቸው እየተባለ በእነርሱ ዘንድ በግልጽ ይወራል፡፡ ያን ለማስተባበል ግን በአንድ እግራቸው ቆመው ስለነበረ በጸሎት ብዛት ነው የተቆረጠው፤ በኋላም በክንፋቸው በርረው በሰማያዊቱ መቅደስ ገብተው ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር አጠኑ ይላል፡፡

መቼም በእውነተኛ ጸሎት ፈውስ እንጂ ጉዳት አይመጣም፤ በጸሎት የተሰበረው ይጠገናል እንጂ ደኅናው አይሰበርም፡፡ ምናልባት ተክልዬ የተሰበሩት በጸሎት ነው ከተባለም እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያመጡት የራሳቸው ጣጣ ነውና ጌታ ቀድሞም ተባለ ኋላ የሰጣቸውን ክንፍ ተጠቅመው ወደሰማያዊቱ መቅደስ ገቡ ማለት ተረት ተረት ነው፡፡ ምድር ላይ ያለ ሰው ወደዚያች በተምስጦ ወይም በራእይ ቢገባ እንጂ በክንፍ በርሮ ይገባል ማለት ከቶም የሚታሰብ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛ ሰማይ በመነጠቅ ስላየው ራእይና መገለጥ በትሕትና ሲናገር እንዲል ብሏል፤ “በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ። እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤” ብሏል (2ቆሮንቶስ ምዕራፍ 12 ቍጥር 1-4)፡፡

በቅድሚያ ጳውሎስ ወደዚያ የተነጠቀው በራእይ ወይም በመገለጥ መሆኑን፣ እንዲሁም በሥጋ ይሁን አይሁን እርሱ እርግጠኛ አለመሆኑንና ይህን ጌታ ብቻ እንደሚያውቅ መስክሯል፡፡ በሌላ አነጋገር ክንፍ አላስፈለገውም፡፡ ስለዚህ ተክልዬ በክንፍ ወደ ሰማይ በርረው በሰማያዊቱ መቅደስ ውስጥ አጠኑ ማለት በሐዲስ ኪዳን ትምህርት ውስጥ የሌለ ነገር ነው፡፡ የክርስትና ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ የቆመ እንጂ የዳንኤል ክብረት “ቅዱሳት መጻሕፍት” በሆኑት በኢትዮጵያውያት ገድላትና ድርሳናት ላይ ሊመሠረት ከቶም አይችልም፡፡ ስለዚህ ገድላቱንና ድርሳናቱን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መፈተሽ ተገቢ ነው፡፡

በራእየ ዮሐንስ ላይ የተጠቀሱት ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች እነማን እንደሆኑ በእርግጠኛነት መናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን እግዚአብሔርንና የታረደውን በግ ኢየሱስ ክርስቶስን በውዳሴ፣ በቅኔ፣ በስግደትና አክሊላቸውን በማውረድ ሲያመልኩ በራእይ ያየው ዮሐንስ ነው፡፡ ይህ ራእይ ነው፡፡ በመጽሐፉም ስድስት ጊዜ ያህል ተጠቅሷል (ራእየ ዮሐንስ ምዕራፍ 4፥4፡10-11፡ 5፥6፡8፤ 11፥16፡ 19፥4)፡፡ ቍጥራቸው ሃያ አራት ብቻ ነው፡፡ ሃያ አምስተኛ የሚጨመርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያውያን ገድላት ደራሲዎች ችሮታ በሃያ አራቱ ሽማግሌዎች መካከል ተክልዬን ማስገባትና ሃያ አምስተኛ ማድረግ ምንም መሠረት የለውም፡፡

ዳንኤል ታዲያ ይህን የመሳሰለውን የአንተን ስሕተት ማን ያርመው?   

80 comments:

 1. endew enante alemaferache edme lek sew metechet ande ken enqan wengelen astemero

  ReplyDelete
  Replies
  1. someone start talking about no one , and no one cares about anyone. so anyone start to think about no one until he realize there is no one but someone.

   Delete
  2. ለምንት አንገለጉ አሕዛብ ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ
   ሕዝብ ብርሃነኔ ገብረ ፃድቃን፣ መርከብ መኩሪያ፤
   አሕዛብ አእመረ አሸብር፡ አይነ ኩሉ ጌታነህ፡ ግርማ ባቱ፤ ያሬድ ክብረት

   ለምን የበሰበሰ ከንቱ ነገርን ይናገራሉ ለምንስ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለክህደት ይሰበሰባሉ፤

   መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ ሕግ መጽሐፋዊ ሕግ ጠባያዊን ሲፍጽም አድጓል
   ሕግ ጠባያዊ ቀስበቀስ ማደግ ነው ያም ማለት አምላክ ነኝና ዕለቱን ልደግ አላለም ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር እንዲል ሉቃስ 2፡51
   ሕግ መጽሐፋዊ ሕግን ሁሉ ሲፈጽም ማደግ ነው፡-
   አምላክ ሆኖ እያለ የአባቶቹን ሥርዓት ጠብቆ ማለፉ ግልጽ ነው፤ ያም ማለት ቤተ ግዝረት በመግባት ከዓመት 3 ጊዜ ለበዓል ኢየሩሳሌም መውጣት

   ወላጆቹም በየዓመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር።
   የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤
   ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።
   ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤
   ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
   ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤
   የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።
   ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።
   እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው።
   ወዘተ---- ነገር ግን ይህ ሆኖ እያለ ግን ይቀኑበት ነበር እውነቱን ነገር ሲነግራቸው ይበሳጩ ነበር እስከ ሞት ድረስ የጠሉትም ለዚህ ነበር፤ እንደ እነርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሞታል እኛም የምንፈልገውን ሁሉ እናደርጋለን ነበር አሳባቸው፤ የሞትና የሕይወት ባለቤት መሆኑን አልተገነዘቡም ነበር ምክንያቱም አንዴ ቅናት አይናቸውን አሳዉሮት ነበርና፤ ዛሬም ተረፎቸ ከአይሁድ የተረፉት እኒህ ኮሌጁን ምሽግ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ሥርዓት ጠብቀዉ የሚያስጠብቁትን አባቶቸ ከኮሌጁ እንዲወጡና ኮሌጅን ለኘሮቴስታንት እንዴት እንደሚያስረክቡት ዕለት ዕለት በዲያቆን ብርሃኔ ቢሮ በመሰብሰብ እየሰሩ ያሉት ሥራ በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ዛሬም በ21/ 4/ 2006 ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ አንድ ማንነቱ ያልታውቀ ሰው ይዘው ተሰብስበው አምሽተው ነበር የሚገርመው ደግሞ ዲያቆን አንድነት አሸናፊ አብሮ ተሰብስቦ ነበር፤ ቤተ ክርስቲን ስላስተማረች ምን አደረገች ለዲዳዉ ሁሉ አፍ ሆና ምንም ያልነበረዉን ሰዉ ከቁጥር አግብታ ሙሉ ሰዉ ስላደረግች ዉለታዋን መክፈል ቢቻል መልካም ነዉ ካልተቻለ ደግሞ ፍቅሩዋን ማጣጣም ነበር:

   አንድ እዉነታ አለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ ዘንድ የሞተና ሁሉም ነገር ያከተመ መስሎአቸዉ ነበር ነገር ግን በሦስተኛዉ ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ እነርሱ የከመሩት ድንጋይ በእርሱ ዘንድ ቁም ነገር አልነበረዉም ፤ ዛሬም የቤተ ክርስቲያንን አንጀራ እየበላችሁ ነገር ግን የሰይጣንን ምግባር ይዛቸዉ የይሁዳን ስንቅ አንግባችሁ የምትጓዙ፤

   ዲያቆን ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን
   ›› ግርማ ባቱ
   ›› ያሬድ ክብረት
   ›› ልዝቡ ሰይጣን አንድነት አቸናፊ
   ›› አእመረ አሸብር
   ›› አይነ ኩሉ ጌታነህ፡
   ›› መርከብ መኩሪያ፤

   ምን አልባት ቤተ ክርስቲያን አናንት በቆፈራችሁት ጉድጓድ ምትገባ መስሏችሁ ከሆነ ያጠመዳችሁ ሰይጣን አያታልላችሁ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ የታነጸችዉ በክርስቶስ ደም ነዉ፡ ስለሆነ ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፡፡

   የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሆይ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በፕሮቴስታንት እየተከበበ ነዉ፡

   ግርማ ባቱ Academic dean
   አንድነት አቸናፊ Registrar
   አይነ ኩሉ Teacher of Old Testament Commentary
   ያሬድ ክብረት Vice dean
   ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን ወግ አይቀር ያለ አቅሙ እንኳን ለማስተማር ተማሪ ለመሆን ብቃት የሌለው Teacher of petrology

   ሰለዚህ መፍትሔዉ ምን እንደሆነ እስኪ እንወያይ

   Delete
  3. Naming names isn't going to change anything, but laying the truth(fact) on the ground may teach some.
   May God bless.

   Delete
 2. Well done, Memhir Addis.

  I hope you will come up with more research and findings on so many of the church's writings including Gedlats, Ziks, and Tamrats, that have been competing to take the place of our creator, GOD, himself. Do we ever need them at all? Which synod approved them for use in the church?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ante kiftaf dekamanetihiun mamen siyakitih alawaki yetsafewun tidegifaleh..... mogn!!!!!!!!!!!! jil!!!!!!!!!!!

   Delete
  2. You don't have the least courage to accept the truth. Listen, only truth will set you free if you have read the bible. Before you start to criticize any one know yourself. I wonder if you have read a single chapter of the Holy Bible. I pray that you are not going to be one of the lost, honestly. May the Good Lord open your eyes and the eyes of your likes so that you may see because you have eyes, yet you don't see!!!!

   Delete
 3. ሰው ለማሳሳት ምነው ባትደክሙ ሰልፋችሁ ከማ እንደሆነ ስላወቅናችሁ እናንተ ሂዱ እኛን ግን በቤታችን ተዉን አባቶቻችን የሄዱበት ጠባቡ መንገድ ሲከብዳችሁ በኑፋቄ መሀንዲስ የተጠረገላችሁን መንገድ አእየተጓዛችሁበት አብረን እንሙት አትበሉን.....

  ReplyDelete
 4. ለዳንኤል ምላሽ ስለተጻፈው ለዚህ ጽሁፍ አፌን ይዤ ዝም አልኩ። እውነት የሚጽፉና እጃችንን በአፋችን ላይ እንድንጭን የሚያደርጉ እንደነዚህ ዓይነት ሊቃውንት እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ስለሰጠን ስሙ ይባረክ። ለክብሩ ቀናዒ የሆነው እግዚአብሔር የክብር ስሙን ወስደው ለሌላ ከለጠፉት ሁሉ እንዲመለስ የሚጽፉ አእላፋትን ይላክልን። አሜን!!

  ReplyDelete
 5. መ/ር ቃለ ፅድቅDecember 26, 2013 at 8:45 PM

  በመጀመሪያ ስምህ ማስተካከያ ቢደረግበት ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ መ/ር አዲስ የሚለው አንተን አይገልፅም፡፡ ለነገሩ መ/ር/መሰርይ/ ተሐድሶ /መምህረ ተሐድሶ/ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ መምህር የሚለውን ታይትል ራስህ ለራስህ እንዳጎናጸፍከው ተረድቻለሁ፡፡ በሚገባህ የድፍረት ቋንቋ እኔም ራሴን መምህር ብየ አስተዋወቅሁህ /ለአንባብያን ግን ቃለ ፅድቅ ብቻ ነኝ/፡፡
  እኔ የገረመኝ አንተ ከሁለት ሸህ ዓመታት ያለነሰ እድሜ ያላትን ቤተክርስቲያን ለማፍረስ ሌት ከቀን የምትባዝነው፣ መምህር ከተባልህ ቤተክርስቲያኗ ሃይማኖቷን፣ ሥርዓቷን፣ ትውፊቷን-- ጠብቃ፣ ተጠናክራና ተደረጅታ እንድትቀጥል፣ ትውልድ በሃይማኖትና በምግባር እንዲታነፅ ሌት ተቀን የሚተጋው ዳንኤል ክብረት የቤተክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ ቢባል ምኑ ነው ስህተቱ? ዳንኤልን ምቀኛ ለማለት ሞከርህ እንጅ አንተ የምቀኞች አለቃ ሳትሆን አትቀረም/ ዳንኤል ለምን ተመራማሪ ተባለ? ድንግል ማርያም ለምን ተወደሰች? ተክለሃይማኖት ለምን ተከበረ? ነቢያት ለምን በስማቸው ፆም ተሰየመላቸው?ወዘተ ምቀኝነት/ እንዲያውም እንደኔ ከአንተ ዕወቀትና ዓላማ አንፃር የሱ እወቀትና ዓላማ ከተመዘነ/ በእርግጥ ፍፁም ተቃራኒ ናችሁ- አንተ ለማፍረስ እርሱ ለመገንባት/ዳንኤል ሊቀ ሊቃውንት ነው መባል ያለበት፡፡

  ዳንኤልን እንርሳው ተስፋዬንም አናንሳው የአንተም ዋናው አጀንዳ ዳንኤል ተሳስቷል ተስፋዬ ትክክል ነው ለማለት እንዳልሆነ አንተም እኔም ብዙኃኑ አንባቢም እናውቀዋለን፡፡ የአንተ ዓላማ ባገኘሀው አጋጣሚ የቤተክርስቲያናችን የሆነውን ሁሉ/ ሥርዓቷን፣ ቀኖናዋን፣ ቅዱሳኗን ወዘተ/ ማብጠልጠል፣ ማንቋሸሽ ከዚያ ባዶ ማድረግ ከተቻለ ፕሮቴስታንታዊት ማድረግ በቃ ይሄው ነው የአንተ ዓላማ፡፡ እኔ የማይገባኝ ምን ዓይነት የማይፈወስ በሽታ እንደለከፈህ ብቻ ነው፡፡ ዛሬም ለአንድ ሽህ ጊዜ እንደገና ልንገርህ ፕሮቴስታንት ያው ፐሮቴስታንት ነው ካቶሊክም ካቶሊክ ሆኖ ይቀጥላል ኦርቶዶክስም ኦርቶዶክስ ነው ፡፡ እስካሁን ባለው የክርስትና ታሪክ እውነታው ይህ ነው ካቶሊክ ብዙ ተከታይ ስላለው ኦርቶዶክስ አልተዳከመም፣ ፐሮቴስታንት በመፈጠሩ ካቶሊክ አልጠፋም፡፡ ለአንተ እኮ ከኦርቶዶክስ ይልቅ ካቶሊክን ብታቀወም ነበር የሚሻልህ ምክንያቱም ፐሮቴስታንት ስለሆንክ ፡፡

  የአንተና የመሰሎችህ ጉዳይ ጉንጭ አልፋ የሆነብንኮ እኛ ወደ ፐሮቴስታንትነት ከተቀየርን የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ ቤ/ክርስቲያንም ወደ ፐሮቴስታንትነት መቀየር አለባት ብላችሁ ማሰባችሁ ነው ፡፡ ምን ዓይነት በዓለም ላይ የሌለ ክፉ አባዜ እንደተጠናወታችሁ ፈጣሪ ይወቅ፡፡ ይህኮ ሌላ የክርስትና ሁለት ሺ ዓመታት ቢጨመር እንኳን ፈጽሞ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፐሮቴሰታንት ሌላ ነው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶም ሌላ ነው፡፡ እናንተኮ የቀራችሁ ነገር ቢኖር እግዚአብሔርን ራሱን ቅዱሳንን ለምን አከበርህ? ብላችሁ በቀጥታ መቃወም ነው፡፡ ስማ መሰርይ ተሐድሶ/ ይቅርታ መ/ር አዲስ/ ቤተክርስቲያንቱን ልቀቃት ምን አገባህ አንድ ተክለሃይማኖት ታክብር ሠላሳ ተክለሃይማኖት ትዘክር አንተ ምን ቤት ነህ? አንተ የተሻለ ነው ያልከውን ፐሮቴስታንትን መርጠሃል መብትህ ነው የኛን መብት አትጋፋ፡፡እንኳን በእግዚአብሔር አምነን ቅዱሳንን ማክበር አይደለም ድንጋይ እንኳን የማምለክ መብት እንዳለን አታወቅም? መቸሞ ላይፀድቁ ይችላሉ ብለህ ተቆርቁረህ ሊሆን አይችልም እንዲዚህ ዓይነት ሰብእና ቢኖርህ ኖሮ በእግዚአብሔር የማያምኑ የሰው ልጆችን ወንጌል በሰበክህላቸው ነበር/ ለነገሩ አንተ ወንጌልን የምትጠቀምበት ሰውን ለማዳን ሳይሆን-- ተወው ብቻ ሆድ ሲያውቅ--/ እኔ አሁን እያልኩህ ያለሁት ተወን በቃ ተወን እናምልክበት ሲድብ አታስተምረን መ/ር ያንተ ጉዳይኮ አልቋል ቤተክርስቲያኒቱም ወዳንተ አትመጣም አንተም ወደሷ አትማጣም በቃ ትንሽም ቢሆን ጎድተሃታል ነክስሃታል አድምተሃታል አሁን ግን በቃ እምቢ ካልህ ደግሞ ምን አደርግሃለሁ የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያንቱ ፈተና ሆነህ ታልፋለህ በፈተና ውስጥ እንዴት ማለፍ እንዳለባት ጠንቃቃ የምታውቀው የኛ ቤተክርስቲያን ግን ትቀጥላለች ሌላ የታሪክ ዘመን ትሻገራለች ነገ ሳትወድ በግድ የምትጠፋው አንተ ግን ዋ ትዝብት

  ReplyDelete
  Replies
  1. If u don't want learn it's easy
   try illiteracy,if u got time to post this nonsense comment
   why you don't take time to dig
   deeper &know the unknown ,
   how Ganiel he goon learn?if someone stands with his huge mistake like he did before,l personally posted a comment about him on his blog &the other three MK blogs,but no one posted on BC they don't
   believe in freedom of speech,
   if you are his true friend PS
   don't covered up his mistakes ,
   to me it seems like u stab in his back,he destroyed Ethiopian church and MK destroyed the church and the country,days come for them who is waiting with patience,I really appreciate the person who is fought for the truth,
   thanks aba Selma be blessed
   u doing outstanding and awesome job long life those who stand for the Gospel.🎄
   The bete pawlos @Dallas 🎄
   by the way have a wonderful
   Christmas 🎄

   Delete
  2. @ቃለ ፅድቅ
   Great job.

   Delete
  3. WOW!!!!!!!!!! great article which deserves to the writer 'Memhir Adiss --- Shame to say'

   Delete
 6. መምህር አዲስ ለጽሁፋቸው ባጠፉት ጊዜ አደንቃቸዋለው፤
  ሆኖም ግን ...ለጥሩም ለደጉም መምህር አዲስ ማንና የየት አገልጋይ/ አልያም ሰባኪ መምህር ናቸው?
  እንደ ዲ/ን ዳንኤል ወጣ ብለው ጽሁፋቸውን ብንተቸው፤ ብንደግፈው፤ ወዘተ

  አልያ የ'ደህንነት' ጽሁፍ ቋት አይሞላም!


  ዳላስ-ቴክሳስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስሙ ሳይሆን ጽሑፉ ነው መተቸት ያለበት፤ የዳንኤል ሐሰት እንዲህ ባለእውነት ሲጋለጥ ዳንኤልን ተው ተስተካከል ማለት ሲገባ እውነትን መንቀፍ ተገቢ አይደለም፡፡ ስለዚህ ግለሰብን ትን ሐሣብ ላይ ብናተኩር የተሸለ ነው፡፡ የዳንኤል ቀደመዛሙርት ግን ሐሰታችሁ ሲጋለጥ እውነትን ለመተቸት አቅም ሲያንሳችሁ ያልሆነ ጥያቄ ታነሳላችሁ፡፡ ልእኔ ይህን ጽሑፍ መ/ር አዲስ የተባለ ሰው ነው የጻፈው፡፡ ማንነቱን ማወቅ ምንም አይሠራልኝም፡፡ የብእር ስምቢሆን እንኳ የጻፈው ነገር እንጂ ስ ምንም አይሰራልኝም፡፡ አንተ ግን ሐሣቡን በሐሳብ መተቸት ሲገባህ አቅም በማጣትህ ማነህ ወደሚል ተራ ነገር ውስጥ ገባህ፡፡ ስለዚህ እባክህን ይህን ወልጋዳ አስተሳሰብህን አርም፡፡

   Delete
  2. አቦ! ከፀሀፊው ይባስ ደግሞ አንተ ተጃጃልክ!
   ለመሆኑ በአጀንዳዎች ዙሪያ ሰውን አዳምጠህና ከሰውም ተምረህ፤ 'ተሽንፈህ'.. የነበርክበትን ጊዜ ኖሯህ ያውቃል? አይዞን እንዴ~~
   ... ግና ወጣት ከሆንክ ግን በጣም ይቅርታ

   Delete
 7. አሳፋሪና ጭብጥ የሉለው ፅሁፍ!!!! ለመሆኑ የጠቀስካቸው መጽሔቶች ለምን እነዳልተቀበሉህ እነ¡ን መገመት እነዴት ተሳነህ? የመይመጥንና መያዣ መጨበጫ የሌለው ብትን ጨርቅ ማነ ያንብበው ብለው? አቅሙና ፍላጎቱ ካለህ በርካታ ጠቃሚ ማጣቀሻዎች ተጠቅሰዋል ፡፡ በጣም የሚገርመው ደገሞ ገደኛህ ፅጌ አለመጠቀሱ ማዘንህ ነው፡፡ የሰው ቀባጣሪ ፅጌኮ መመከር እነጂ ያለበት የሱን ክህደት ልክ ነው ብሎ መመስከር አይደለም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Can I say some,not me the whole world knows about this
   blog and like ashenafi,abenzer
   &bete fikir blogs are the true
   advocate blogs.go&goggle it
   u goon get heel for UR blindness,after that u goon see things clearly,I goon pray for you to get good heart and ur saver .god bless you.

   Delete
  2. Word of the day: goon
   ማፈሪያ።

   Delete
 8. Woregna.... mk....daniel minamin minagebah lib kaleh wongel sibek adakari

  ReplyDelete
 9. ድንቅ አቀራረብ ነው! “የታሪክ ተመራማሪው” ዳንኤል ምን ነካው? ለነገሩ እኔ ድሮም ዳንኤል ተረት ተረት እንጂ ታሪክ የሚያውቅ አይመስለኝም ነበር!

  ReplyDelete
 10. kalat yelegnm...amilak yaberitachihu..letesadabiwoch bota atisitu..diro theology eyalen bezih zuria bizu neger anibibenal.yemiasazinew sayanebu ena sayimaru betawakinet sim hizibun yemiasasitutn yemigesits alemegegnetu new. God bless you!!!

  ReplyDelete
 11. ante lej bakeh yale akemeh atenterara endatekesefh

  ReplyDelete
 12. This shows that Mr. Daniel has only the passion for Ethiopian history but nothing else! I hope he’ll be a good ‘YETERET ABAT’¡

  ReplyDelete
 13. Did Daniel say Tekle-haimanot was standing by his one leg and then it is cutoff? if it is, what was doing his another leg?

  ReplyDelete
 14. Menalebet wongel benemarbet Abne Teklehimanoten Eskemechereshaw Amalagachen Ena Yebek Kidus Nachew. Danielenem Tiru Temeramarie New Yawme Yeortodox tewahedo lege. Egziabhere Rejime Edemena Tena Yestelen. Enwodewalen. Temehrtume Yesmamanal. Enante Bere Wolde blachehu yemetaworu Bicha Nachehu Gen Bere Mechem Behobe Aywoldem.Atwashu.

  ReplyDelete
 15. tesfaye be abunu lay endih yale neger mesafu le wengel yalewn kinat sayhon shufu lela gib endimetalet blo new.daniel degmo sm ena zna lematrf new. weg ena wengel yetegachebachew bzu nachew..ke enezihm andu daniel new!!!

  ReplyDelete
 16. You are entitled to your opinion, but your piece is simply a garbage. The Copts honor this Saint more than we do and tell the same stories as we do. There are also other pieces or books written by independent writers on this subject matter. Why don't you consult them? Your attempt to write a new history will be a futile exercise... thanks

  ReplyDelete
 17. አንተ ከሁለት ሸህ ዓመታት ያለነሰ እድሜ ያላትን ቤተክርስቲያን ለማፍረስ ሌት ከቀን የምትባዝነው፣ መምህር ከተባልህ ቤተክርስቲያኗ ሃይማኖቷን፣ ሥርዓቷን፣ ትውፊቷን-- ጠብቃ፣ ተጠናክራና ተደረጅታ እንድትቀጥል፣ ትውልድ በሃይማኖትና በምግባር እንዲታነፅ ሌት ተቀን የሚተጋው ዳንኤል ክብረት የቤተክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ ቢባል ምኑ ነው ስህተቱ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደሚባለው ተረት ስለሚሆን
   ለዳንኤል ድፍረትአጉል እውቅና አትስጥ

   Delete
 18. woy daniel ena mahibere kidusan....teketayochachewuna degafiachew yemiamesasilachew yemayanebu..yalibeseluna tesadabiwoch mehonachew new.lenegeru daniel sef ansu kale wedehuala ayilum...mahiberekidusan kidusanin yemayamin yigedel kale seyifina temenja yizew lemeselef yemikedimachew yelem.lenegeru yemeriwochachew lijoch abatochachewun new yemimesilut.yikir yibelachew.WENGEL YASHENIFAL.wenjelegna yiketal...

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከምር የበሰለ ሰው ስድብ። የ“ፃዲቅ ጴንጤ ቃል”። መቼ ትሳደብና።

   Delete
 19. In the Name of the Father, the Son and Holy Sprit One God Amen!

  You have the right to be protestant or deny the intercession of angles and saints even be atheist like Tesfaye Gebreab! But you can not tell me that Gedele Tekel Haymanot is a total fabrication, while i have seen with my ones eyes in Debre Libansos when evil spirit was crying leaving person at the Debre Asebo Tsebele, at the Gedel Bete and even eating the Dabie! The miracles of Abba Tekele Haymanot is continuing! We shall trust God on what He does in the Name of Tekele Haymanot not you! Your aim is one and one, destroy EOTC.

  :Let God light your path
  Amen

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you serious?PS bra take
   ur time and start to read that
   stereotype book,finally u feel
   guilty about ur thought, arguably that book is novel,it's
   a big mess for that church,
   even for the believers open ur
   eyes and mind u goon figured
   out who they drug every body
   to hell,instead of lessoning those dam religious leaders try
   to read,still u got time u are not late,remember the 11th hour gay,he made it finally.

   Delete
  2. let me ask you
   do you think all miracles are from God?
   I saw the same miracle but it is in India and they are Hindu so can I conclude that Hinduism is the right path?

   Delete
  3. The choice is yours,no doubt about it,but be careful what you goon answer at final day?God is
   the true judge,I am not said
   it but the blue book (bible).
   definitely I believe in this book,it's Gods true word,

   Delete
  4. Hinduism work is in in different sprit, but St. Teklehaimanot worked and works in Jesus Christ love and name. Jesus Christ the Lord the savior, the King, the God of all saints; praise His Name.

   Delete
  5. really Teklehaimanot knew Jesus Christ?
   why his act is against bible?Teklehaimanot gedel is full of garbage. It is not suit for Christians even not for idle
   worshiper

   Delete
 20. ye abunu gudayima kezih tewiled behuala yalikeletal!

  ReplyDelete
 21. tekeliye ema bezih tiwelid yalikelachewal

  ReplyDelete
 22. ለፅጌ ስጦታው፦
  መቼም አንተን እንደቁም ነገር ቆጥሮ መፃፉ ትርፉ ድካም ቢሆንም እስኪ ጥቂት ነገሮችን ልጠይቅህ።
  በመጀመሪያ ከመፅሃፍህ ውጪ በስምህ የማትፅፍ ሰው እንዴት በብዕር ስም ሌላውን ልተች ብለህ ተነሳህ? ፈርተህ ነው? በየትኛውም ስም ፃፍ ፅጌ ስጦታው መሆንህ ይታወቃል። ሰላም፥ ተስፋ፥ አዲስ፥ አማረ....

  ስለ ፕሬስ የፃፍከው፤ አንተ እኮ ስም በማጥፋት በመርከብ ጋዜጣህ ወህኒ የወረድክ ሰው ነህ። ለባለቤትነቱም ቢሆን የትሪኒቲ እና የጮራ መፅሄት ግማሽ ባለቤት አይደለህ? ፅሁፍህን እዛ ላይ አታወጣውም?
  አባ ሰላማስ የአንተ አይደል? ሚዲያ ነው። ይኸው አወጣህበት አይደል? ይቺ የተለመደች ክሳችሁ ተከታይህ ሙሉጋኔንም ይላታል። የራሱ ሳይቶች አውደ ምህረት፥ ሳልሳዊ ወያኔ ና የአንተ አባ ሰላማ እያሉለት ሌሎቹ አላወጡልኝም ብሎ ያለቅሳል። እንዲህ ማለት ታክቲካችሁ ነው ማለት ነው?

  ሌላው አንተ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ከመጥላትህ የተነሳ “ባህታዊው ሰይጣን” ብለህ በፃፍከው መፅሃፍ በራስህ ውሸትና ፈጠራ፥ መቆራረጥና በመሰለኝ በፃፍከው የጥላቻ መፅሃፍ ራስህን አሳይተሃል። ካንተ ከዛ በላይ አይጠበቅም።

  ሌላው ተክለ ሃይማኖት በተነሳ ቁጥር መቼም በዕውቀቱ መነሳቱ ግድ ሆኗል። አንተና መሰሎችህ ቆርጦ መቀጠል እና ቆርጦ የተመቻችሁን ብቻ ስለምትወስዱ ቆንፃዮች ስለሆናችሁ ነው እንጂ በዕውቀቱ በዛ ፅሁፍ ሊያስተላልፍ የፈለገው ነገር እግዚአብሔርን ተስፋ ከምታደርጉ ስሩ እግዚአብሔር የለም ነው። ተክለ ሃይማኖት ለዚህ ምሳሌው ናቸው። እርግጥ የእናንተም የመጨረሻ ግባችሁ ከገድል ስህተት ጀምራችሁ መፅሃፍ ቅዱስን ዳሳችሁ እግዚአብሔር የለም ለማለት ነውና በሃሳቡ ብትስማማ አይገርመኝም።

  በዕውቀቱ ያለው፦
  “ሕሩይ ወልደስላሴ የተባሉ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ባለስልጣን በ1910 ዓ.ም. “ የልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ “ የሚል መጽሐፍ ጽፈው አሳትመዋል። መጽሐፉን የጻፉት በቀጥታ ለልጃቸው ፈቃደ ስላሤ ፤ በእጅ አዙር ደግሞ ልጃቸው አባል ለሆነበት ትውልድ ምክር እንዲሆን ነው። መጽሐፉ በጊዜው በተደጋጋሚ ታትሞ ተነቧል ፤ በመጽሐፉ ከተመዘገቡት ምክሮች አንዱ ‘ ልጄ ሆይ አሳብህ ሁሉ ከሞት በኋላ ወዲያኛው ዓለም ስለሚሆነው ስለነፍስህ ነገር ይሁን እንጅ በዚህ ዓለም በስጋህ ስለሚሆነው ነገር እጅግ አትጨነቅ ‘ ይላል። ምክሩ የወጣው ከባህታዊ አንደበት ቢሆን አይገርምም ፤ መካሪው ግን የአገር አስተዳዳሪ ባለስልጣን ነው ፤ የምክሩ አላማ ትውልዱ አገሩን ጥሎ እንዲመንን ለማድረግ ይሆን? ‘ በዚህ አለም በስጋህ ስለሚሆነው አትጨነቅ ‘ ማለት ‘ ልጄ ሆይ ጀዝባ ሁን ፣ ቦዘኔ ሁን ፣ ደደብ ሁን ‘ ብሎ ከመምከር ጋር በይዘት አንድ ነው። ልዩነቱ የመጀመሪያው መንፈሳዊ አቀራረብ መያዙ ነው። ደግነቱ ልጅዬው ፈቃደ ሥላሴ የአባቱን ምክር አልተቀበለም። ለሥጋው ተጨንቆ ተምሮ አገሩ በፋሺስት ጣሊያን ስትወረር ከውጭ ተመልሶ ለአገሩ ደረሰላት ፣ ተዋጋላት ፣ ሞተላት ፤ ታሪክ ሰሪዎች ሰዎች እንጅ መላዕክት እንዳልሆኑ አሳያት።”

  ሲቀጥል፦
  ....“የሕሩይ ምክር ይቀጥላል፦ “ ... ልጄ ሆይ ወደፊት እንደዚህ ያለ መከራ ያገኘኛል ብለህ አትጨነቅ ፤ ነገር ግን የሚሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና ያለ እርሱ ፈቃድ የሚሆነው አያገኝህም። የውስጥህን የሚያውቅ እግዚአብሔር ካልፈረደብህ ንብረትህ እየሰፋ ጠላትህ እየጠፋ ይሄዳል እንጅ ምንም ክፉ ነገር አይመጣብህምና አትጨነቅ። በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመጣውን መከራ በጉልበቴ ፣ ወይም በእውቀቴ አስቀረዋለሁ ብሎ መጣጣር በመከራ ላይ መከራ ለመጨመር ነው እንጅ ሌላ ትርፍ አይገኝበትም። አስቡት የሰውን ጥረት በሙሉ ዋጋ የሚያሳጣ ምክር ነው።”

  “የዳርዊን አገር ከአቡነ ተክለሃይማኖት አገር በላይ ተሳክቶለታል ፤ ዋናው ነገር ጠፈሩ የምናስበው ያክል የዋህ አለመሆኑን ማወቅ ነው ፤ ምድሪቱ ከፀሎታችን በላይ ላባችንን ፣ ከእንባችን ይልቅ ደማችንን ትጠይቃለች። ”

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you know what you token
   about?really really are you
   series?do you know who is
   Daniel (ganiel) he got lost,he
   don't know nothing about history even about church,he
   is in the middle of nowhere,he
   is not a politician or religious person.if he is a politician he need to join a political party but not,if he is a religious he need to serve God &his people as a
   shepherd,but not he is a CANCER,this is who he is.
   bete pawlos @Dallas.u got it?

   Delete
  2. seriously dude. where do you got a gut to criticize others? you couldn't even spell words correctly. I said this because you live in Dallas not in Ethiopia. please, before trying to criticize people, who got way far better knowledge than you, learn how to spell and write a sentence. ማፈሪያ::

   Delete
  3. Thanks your honor,I see you are highly educated guy,that is why u breathing
   same air like your mentor,
   go hell ,don't drug any body
   with you,this is 21 century,
   we are not playing hide &ride,every thing is clear like Chrystal,no where to hide,enough is enough,so can stop playing game?

   Delete
  4. OMG! You did it again. Please, learn. You're living where people speak the same language you trying to write. Learn. Don't be like your uneducated mentors of yours; Tsege, Muluganen and the likes.
   Hide & ride?
   Are you serious? You don't even have a little knowlage to criticize others. Writing in Amharic is not shame. Shame is what you do. Misspell words frequently.

   I will say this again
   “I said this because you live in Dallas not in Ethiopia. please, before trying to criticize people, who got way far better knowledge than you, learn how to spell and write a sentence. ማፈሪያ::

   Delete
  5. I feel sorry about your big
   mouth,this is who you are,
   I am not criticized any body
   let me clear this soon or later u goon figured out what you said it,the truth
   set everybody free,I am who I am ,I am proud of my self , i goon learn thanks for your advice,don't forget sky
   is the limit,l goon made it.be blessed.

   Delete
  6. I fell sorry about your mind man.
   What's goon? Oh my God! There I time for everything man. When you open your wild stinky mouth I see an empty mind of yours and and nonsense.
   You said you're not criticize any one?
   This is what you wrote “Do you know what you token
   about?really really are you
   series?do you know who is
   Daniel (ganiel) he got lost,he
   don't know nothing about history even about church,he
   is in the middle of nowhere,he
   is not a politician or religious person.if he is a politician he need to join a political party but not,if he is a religious he need to serve God &his people as a
   shepherd,but not he is a CANCER,this is who he is.”

   What was you doing then?

   Word of the day: goon

   Delete
  7. ፅጌ ስጦታው እንደ መፅሃፎቹ ሁሉ እዚህም ሳይት ላይ ሲያምታታ አዋቂ ሲመስል ሌላ ሰውን ሲሳደብ እና ራሱን አዋቂ አርጎ ሲፅፍ ምንም አላፈረም:: ሰውን ተሳሳተ ብሎ መረጃ ሊሰጥ እየሞከረ መሳሳት መቼም የጤና አይደለም::
   -''...አርማለሁ ብሎ ጥፋቶችን ፈጽሟል'' ያለ ሰው ሲዋሽ ተልመልከቱ::
   ፅጌ ስጦታው አቡነ ጎርጎርዮስንም በሌብነት ይከሳል:: "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።" ይለናል:: በመጀመሪያገፅ ፯፪ ላይ እንዲህ የሚል ጭራሽ የለም:: በሁለተኛ ደረጃ ገፅ ፯፱ ላይ በትክክል ተፅፎ ይገኛል:: በዚህ መፅሐፍ እንዲህ የተሳሳተ ሰው በሌላው እመኑኝ ሲል እንዴት ይታመናል::

   ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ ፯፱ ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ፍረዱ:: ይሄን ውሸታም ጴንጤንም ታዘቡት::
   https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG
   ማፈሪያ::

   Delete
 23. ስሙ ሳይሆን ጽሑፉ ነው መተቸት ያለበት፤ የዳንኤል ሐሰት እንዲህ ባለእውነት ሲጋለጥ ዳንኤልን ተው ተስተካከል ማለት ሲገባ እውነትን መንቀፍ ተገቢ አይደለም፤ አሁን አንተን መ/ር ቃለ ጽድቅ ከማለት መ/ር ቃለ ሐሰት ማለት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ግለሰብን ትን ሐሣብ ላይ ብናተኩር የተሸለ ነው፡፡ የዳንኤል ቀደመዛሙርት ግን ሐሰታችሁ ሲጋለጥ እውነትን ለመተቸት አቅም ሲያንሳችሁ ያልሆነ ጥያቄ ታነሳላችሁ፡፡ ልእኔ ይህን ጽሑፍ መ/ር አዲስ የተባለ ሰው ነው የጻፈው፡፡ ማንነቱን ማወቅ ምንም አይሠራልኝም፡፡ የብእር ስምቢሆን እንኳ የጻፈው ነገር እንጂ ስ ምንም አይሰራልኝም፡፡ ቃለ ጽቅ ግን ሐሣቡን በሐሳብ መተቸት ሲገባህ አቅም በማጣትህ ማነህ ወደሚል ተራ ነገር ውስጥ ገባህ፡፡ ስለዚህ እባክህን ይህን ወልጋዳ አስተሳሰብህን አርም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Anonymous commentator:

   Can you give us one good reason for your presumption that this writing is not of the truth. Do you ever know the meaning of truth? The author of this article gave us more than enough supportive evidence to prove his case. I believe we should credit this promising author for his pioneering and noble work and encourage him to write more so that the blind and your likes may see and come to believe the truth which is Jesus Christ himself ( John 14:6)

   Delete
  2. ፅጌ ስጦታው እንደ መፅሃፎቹ ሁሉ እዚህም ሳይት ላይ ሲያምታታ አዋቂ ሲመስል ሌላ ሰውን ሲሳደብ እና ራሱን አዋቂ አርጎ ሲፅፍ ምንም አላፈረም:: ሰውን ተሳሳተ ብሎ መረጃ ሊሰጥ እየሞከረ መሳሳት መቼም የጤና አይደለም::
   -''...አርማለሁ ብሎ ጥፋቶችን ፈጽሟል'' ያለ ሰው ሲዋሽ ተልመልከቱ::
   ፅጌ ስጦታው አቡነ ጎርጎርዮስንም በሌብነት ይከሳል:: "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።" ይለናል:: በመጀመሪያገፅ ፯፪ ላይ እንዲህ የሚል ጭራሽ የለም:: በሁለተኛ ደረጃ ገፅ ፯፱ ላይ በትክክል ተፅፎ ይገኛል:: በዚህ መፅሐፍ እንዲህ የተሳሳተ ሰው በሌላው እመኑኝ ሲል እንዴት ይታመናል::

   ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ ፯፱ ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ፍረዱ:: ይሄን ውሸታም ጴንጤንም ታዘቡት::
   https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG
   ማፈሪያ::

   Delete
 24. Daniel Malet Haymanotenya yihun poletikenya. yaleyelet erasun babetakirstiyan shomo kahulu balay erasun yamikoter yekristos fiker ewunat yalgabawu betakristiyanitun ersuna mahbere kidusan bamifelegut melk lamemerat asbawu gin yaltesakalet wenbede naw. ahun leamanyu yamiyasfelegewu adenagari yekidusan tarik sayihon ewunetenya yahone wengel naw. kidusanochu beteley kametshaf kidus wuchi yalutena betekristiyan yemitekebelachewu kalu enyam wengel semten erasachenen lewuten endenersu lemehon mesrat enji awezagabi yehonu yekidusan tarik eyaweru mewezageb asfelagi aydelem. yihe damo labetekristiyan aytekmim gizewum aydelem ahun nisehana memeles yasfelegal. abatoch endih aynetunena leloch awezagabi yehonu kagize bahuala yegebu awezagabina kemeteshaf kidus gar yemikarenu tarikochen leyetewu ermet mewused yasfelegal. yihen gen bayadergum ahun hizbu ewunetun eyawekena ke amlak eyetemare silemeta minim chiger yelem.

  ReplyDelete
 25. ewnetna nigat eyadere yiteral

  ReplyDelete
 26. Can you post Daniel kisret profile that showing where and when he was atended theological education????

  ReplyDelete
  Replies
  1. Can you post your profile that enables you to critic Daniel?

   Delete
 27. መምህር አዲስ ለጽሁፋቸው ባጠፉት ጊዜ አደንቃቸዋለው፤
  ሆኖም ግን ...ለጥሩም ለደጉም መምህር አዲስ ማንና የየት አገልጋይ/ አልያም ሰባኪ መምህር ናቸው?
  እንደ ዲ/ን ዳንኤል ወጣ ብለው ጽሁፋቸውን ብንተቸው፤ ብንደግፈው፤ ወዘተ

  አልያ የ'ደህንነት' ጽሁፍ ቋት አይሞላም!

  ReplyDelete
  Replies
  1. memihir Addis........yabatih sim? ayeeee tehadiso .....eiskemechae rasachihun debikachihu...

   Delete
 28. መምህር አዲስ ለጽሁፋቸው ባጠፉት ጊዜ አደንቃቸዋለው፤
  ሆኖም ግን ...ለጥሩም ለደጉም መምህር አዲስ ማንና የየት አገልጋይ/ አልያም ሰባኪ መምህር ናቸው?
  እንደ ዲ/ን ዳንኤል ወጣ ብለው ጽሁፋቸውን ብንተቸው፤ ብንደግፈው፤ ወዘተ

  አልያ የ'ደህንነት' ጽሁፍ ቋት አይሞላም!

  ReplyDelete
 29. Iwunetin lematifatina lemeshwfen tirotalehi,E/r gin atirohi yizohal,mechem aysakalihim,wushetaaaaaaaaaaaaaaaaaam!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 30. በክርስቶስ ኢየሱስ ወንድሞቼ የትምትሆኑ ሁላችሁ አንድ ነገርን አባካችሁ እናስተውል አንድ ነገርን ስናደርግ ጥቅምና ጉዳቱን እናስተውል ለማነጽ ለማስተማር የልሆነ ነገር ካለ እንኳን ለእኛ ለክርስቲያኖች ይቅርና ለማንም አይጠቅምም ስልዚና መጸሐፍም እንደሚል ለማነጽ ካልሆን የባስ በስድድብ ጌታንም ከምናስዝን ዝም ብንል ደሞም ክርስቲያን ለመተናነጽ ካልሆነ ምንም ቢጻጻፍ እይጠቅመውም አንባቢያ እኛ ዳንኤልም ይጻፍ አዲስ እዲሁም ሊሎቹ አንብበን ነገሮችን ወስደን ከመጸሐፍ ቅዱስ አኳያ መመዝን አለብን እንጂ የማንም ሐሳብ ትክክል ወይም አይደለም ማለት አንችልም ጌታ ኦኮ መጸሐፍ ቅዱስን እንድንመራበት እንዲንሔድበት ነው በምድር የስቀረልን በመጽሃፍ ቅዱስ ተመዝኖ ትክክል ያልሆነ ነገር ታሪክ ወይም አፈ ታሪክ ነው አስተውሉ ወንዶሞቼ ጌታ ባለው ጊዜ ተመልሶ ይመጣል ይህ የምህረት ጌዜ ነው ጌታ ሲገለጥ ግን ዳንኤልም ሌላውም ጸሐፊ ምስክር አይሆኑንም የምንመዘነው በቃሉ ነው "እግዚአብሔር እጅግ የሚምር የሚራራ ነው " "እግዚአብሔር በምህረቱ ባለፀጋ ነው" ይላል በሌላ ክፍል ደግሞ"እግዚአብሔር ማንም በማይቀርቡት ብርሐን ውስጥ ይኖራል" ይላል አያችሁ እርሱ መሐሪ እንደመሆኑ መጠን ፊቱ የሚያስፈራ ደግሞም በእውነት የሚፈርድ ነው ስለዚህ ከዚህ የምናመልጠው የተባለውን ምህረት ስንጠቀም እንጂ ታራክ በማወቅ የዚህ ዘመን ባለታራክ ነን በማለት አይደለም በታሪክማ መፀሐፍ ቅዱስ የሚቀደም የለም እኮ እናስተውል ከትናንት ይልቅ ዛሬ የጌታ መምጫ ቀርቧል ያኔ ሌያድነን የሚችሉው በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን በመኖር እንጂ በክርክር አይደለም እናስተውል፡፡ ጌታ ማስተዋልን ይስጠን

  ReplyDelete
 31. dani mert new gena bezu ytsefal endenante dedeb aydelema

  ReplyDelete
 32. መምህር አዲስ ለጽሁፋቸው ባጠፉት ጊዜ አደንቃቸዋለው፤
  ሆኖም ግን ...ለጥሩም ለደጉም መምህር አዲስ ማንና የየት አገልጋይ/ አልያም ሰባኪ መምህር ናቸው?
  እንደ ዲ/ን ዳንኤል ወጣ ብለው ጽሁፋቸውን ብንተቸው፤ ብንደግፈው፤ ወዘተ

  ReplyDelete
 33. .......ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)። enante yematerebuna alamachu sewin madenager ena mamtatat becha new. yehen demo hulum sew yawkewal yalawekem kale yawkal. yebelogachu mejemeriya lay Aba Gorgoriyosin yebetekrestiyan fertoch belachu kaskemetachuachew abatoch mehal nachew neger gin yaninim yaderegachut ortodoxawi lememsel new sewun lemasasat ahun demo esachewin setesadebu tegegnalachu. lemanegnawim enante tsere betekrestiyan tehadso mehonachun bedenib enawkalen. Egziabher amlak lebona yestachu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. @Ephratah Fekadu
   Thank you for your comment.
   ፅጌ ስጦታውን እንደቁም ነገር ስላልቆጠርኩት እውነቱን ለመናገር አንተ ያመታሃትን አላየሁትም ነበር:: "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።"
   ከዛ መፅሐፋን አይቼ ለምን አላረጋግጥም አልኩና አየ ሁት:: እሱ ሰውን ተሳሳቱ እያለ የመክሰስ ልምድ ያለው ሰው ያልተደረገ ነገርን ተደርግዋል እያለ ለምን እንደሚያወራ ማወቅ ከባድ አይደለም::

   ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ ፯፱ ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ይሄን ውሸታም ጴንጤ ታዘቡት::
   https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG
   ማፈሪያ::

   Delete
 34. I have heared unconfirmed information from one elements of mk said that Daniel kisret who has been with Aids is next patriarc of mk religion. Long live for abaselama, tplf. Death to Mk. Aba Abrham was sexually abused mk married women when he was USA. Research more dude about fake vagina lover of Abreham or Aba Abrar.

  ReplyDelete
 35. ይደፋህ ባለጌ ምንስ ቢሆን አባ ሰላማ እንዲህ ዓይነት ብልግና ታወጣላቸሁ በጣም ያሳዝናል እናንተንም እንደ ማቅ ከቤተከርስቲያን ይቀልልንና ይህንን በልግና ከመስማተ ይሰዉረን

  ReplyDelete
 36. አንድ መስመር መጻፍ የማይችል ሁሉ አቦ ተወና የዳንኤል እይታ እንኮምክምበት፨ ጊዜአችንን አታባክኑብን ለነገሩ እናንተ ለወሬ እርሱ ለፍሬ እናንተ ለጥፋትእርሱ ለድነት የተዘጋጃችሁ ስለሆነ አይደንቅም
  ለነገሩ የሱንና የማህበረ ቅዱሳንን ሥም ካላነሳችሁ ማን የናንተን ዌብ ሳይት ይካፍታል፤ ዌብ ሳይት አይወገዝም እንጂ በማይም ቃሌ እኔ አወገዝኳችሁ በቃ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፅጌ ስጦታው እንደ መፅሃፎቹ ሁሉ እዚህም ሳይት ላይ ሲያምታታ አዋቂ ሲመስል ሌላ ሰውን ሲሳደብ እና ራሱን አዋቂ አርጎ ሲፅፍ ምንም አላፈረም:: ሰውን ተሳሳተ ብሎ መረጃ ሊሰጥ እየሞከረ መሳሳት መቼም የጤና አይደለም::
   -''...አርማለሁ ብሎ ጥፋቶችን ፈጽሟል'' ያለ ሰው ሲዋሽ ተልመልከቱ::
   ፅጌ ስጦታው አቡነ ጎርጎርዮስንም በሌብነት ይከሳል:: "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።" ይለናል:: በመጀመሪያገፅ ፯፪ ላይ እንዲህ የሚል ጭራሽ የለም:: በሁለተኛ ደረጃ ገፅ ፯፱ ላይ በትክክል ተፅፎ ይገኛል:: በዚህ መፅሐፍ እንዲህ የተሳሳተ ሰው በሌላው እመኑኝ ሲል እንዴት ይታመናል::

   ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ ፯፱ ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ፍረዱ:: ይሄን ውሸታም ጴንጤንም ታዘቡት::
   https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG
   ማፈሪያ::

   Delete
 37. ከደቀመዝሙርJanuary 1, 2014 at 12:37 AM

  @መምህር አዲስ
  ስለሚዛናዊ ሚዲያ በተነሳው ላይ እኔም በተደጋጋሚ ስለታዘብኩት የሚዲያዎቻችንን በአንድ መንገድ መንጎድ በተመለከተ በሰጠኸው አስተያየት እስማማለሁ፡፡ሆኖም ይህ በአንድ መንገድ እየነጎዱ ከእውነት ይልቅ ቡድንን የመከተል አዝማሚያ/በሽታ የአባ ሰላማ ብሎግም መሆኑን አምናለሁ፡፡now let me continue…….ጀመርኩ….
  1. የቀረበው ጽሁፍ ጉድለቶች
  -ጸሀፊው ቀዳማይ ተክለ ሓይማኖት የተባሉትን ጻድቅ በትክክል ሳያስተዋውቀን ትክክለኛው የደብረ-ሊባኖሱ አይደሉም እያለ የያዝነውን ለማስጣል ያለመ በሚመስል መልኩ ያልተጨበጡ ማስረጃዎችን ይጠቅሳል፣
  -ከማይጨበጡት ማስረጃዎች፡ አለቃ ኪዳነወልድ በሎንዶን የሚገኘውን ገድል ስለማየታቸው ባልጻፉበት ሁኔታ አይቸዋለሁ ያለውን ዳንኤል ለማጣጣል በመነሳት ብቻ አለቃ ኪ/ወ/ክ ያህል ሰው ካላዩ አይጽፉም ብሎ በመላምት መከራከር ከባለቤቱ ያወቅ ምንትስ ስለሚያሰኝ ለመቀበል ይከብዳል!!ደግነቱ የእሳቸው መከራከሪያ በገድሉ ፈጻሚ ማንነት ላይ እንጅ ገድሉ መፈጸሙን አልካዱም፡፡ስለሆነም አሁንም ቢሆን ኪ/ወ/ክ ከመምህር ሀዲስ ይልቅ ለዲ/ዳንኤል ይቀርባሉ!!!
  -ውድ መመህር፡ የተክለሃማኖትን ገድል ተረት-ተረትና ፈጠራ መሆን ለማስረዳት መልሰህ የጎንደርና የዛጉዌን ተረት፣የበእውቀቱንና የተስፋየ ገ/አብን የፈጠራ ውጠየቶች እንደወደሩ መጠቀምህም ቢያንስ ባንተ መለኪያ እንኩዋ ሲለካ ጽሁፍህ ስህተትን በሌላ ስህተት ማረም ይሆናል!!!ለማጣቃሻነት ያቀረብከው ግእዝ ቅኔም ተቆርጦ የቀረበ በመሆኑ ሙሉ ሀሳቡን ለማግኘት ባይቻልም ተቆርጦ የቀረበውም ቢሆን ግን “ዘገቢረ ጸሎት አዝለፈ” በማለት የተ/ሃይማኖትን ጸሎት አዘውታሪ መሆን ስለሚገልጽ በቅኔው ‘ሰም’ እንጅ ‘በወርቁ’ የተ/ሃይማኖትን ገድል በመካድ የተደረገ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል!!!አንተ እንዳልከው ክዶ ቢቀኘውም ፈጠራ እስከሆነ ድረስ አንተ ለምታቀርበው የማስተባበያ ሀሳብ የታሪክ ማጣቀሻ የሚሆን አይደለም!!!
  2. በነካ እጅህ ለዚች ተስፋየ ገ/አብ በስደተኛው ማስታወሻ “ፍቅር በለጠ” በሚል ርእስ ስር ከገጽ 348 እስከ 357 በፕሮቴስታንቶች ላይ ላቀረባት ትችትም መልስ ስጥባትማ!!!ትንሽ ልጥቀስልህ፡
  -“ ‘ጌታ ነገረኝ’ የሚለውን አባባል ለረጅም ጊዜ ሳስብበት ቆይቼ ነበር…..ሁዋላ ግን ሰዎች ‘አምላክ ነገረኝ’ የሚሉት ከህሊናቸው ጋር የሚያደርጉትን የርስበርስ ንግግር መሆኑን ደረስኩበት፡፡በጀርመን አገር ከሚገኙ የጰየንጠየ ፓስተሮች አንዱን በዚህ ጉዳይ ላይ አነጋግሬው ነበር፡፡በግልጽ ነገረኝ፡፡ ‘ክርስቲያኖች ጌታ ነገረኝ የሚሉት እውነት እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ስህተት መሆኑን መግለጽ ግን አንችልም፡፡ምክንያቱም ሰፊ ቁጥር ያላቸው አማኞቻችን በዚህ መንገድ ቀጥለዋል፡፡ስህተቱን ማስተካከል ወይም ለማረም መሞከር መጠራጠርን ስለሚያስከትል ዝም ማለትን መርጠናል፡፡’…..አንዳንድ የማውቃቸው ጰየንጠየዎች ኢየሱስ አልጋ ላከልኝ….ፍሪጅ ገዛልኝ…..እያሉ….ብር ሳይኖራቸው ኢየሱስ ይከፍልልኛል ብለው እየተሳፈሩ የሚፈጥሩትን አተካራ የጠላ ሰው በቃ ‘እኔ እከፍላለሁ’ ሲል ‘ኢየሱስ ከፈለልኝ’….እያሉ ኢየሱስን ከአምላክነት ወደ ተላላኪነት አውረደውታል…..”
  ለሚለው የተስፋየ ገ/አብ ጽሁፍ እስካሁን ድረስ ማስተባበያ ስላልተሠጠበት ይህን ቀጥታ ከፓስተር በተገኘ ማስረጃ ተደግፎ የቀረበ ጽሁፍ ለማመን እገደዳለሁ!!!!አይ ካላችሁ መልስ ስጡበት….
  3. ስደመድም ስለገድል ትንሽ ልበል፡
  ገድል “ነፍሱን ስለእኔ የሚያጠፋ ያገኛታል” በሚለው የማቴ.10-39 አምላካዊ ቃል መሰረት በገዛ ፈቃድ የሚደረጉትን እንደ ጸሎት፣ስግደት፣ጾም፣ምጽዋት የመሳሰሉትንና ከአላውያን ነገስታት እና ከመናፍቃን የሚደርሱ ጸዋትወ-መከራዎችን ችሎ በእምነት መጽናትን የሚገልጽ የቅዱሳን ታሪክ ስብስብ ነው፡፡ “ቀኝ አይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ጣላት” በሚል በማቴ5-29 የሰፈረውና ቅ/ጳውሎስም “የሰውነትን ስራ ብትገድሉ በህይወት ትኖራላችሁ” በማለት በሮሜ8-13 እንዲሀም “የተጣልሁ እንዳልሆን ስጋየን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ” ሲል በ1ኛቆሮ9-26 መልእክቱ የከተበውን ይዘው አባቶቻችን መከራ መቀበላቸው ሀቅ ነው፡፡ራሱ ባለቤቱስ በማቴ 10-30 “ዘኢጾረ መስቀለ ሞትየ ኢይክል ይጸመደኒ” ብሎ የለ!!
  Please ቅዱሳን በእ/ር ተራዳኢነት የፈጸሙዋቸውን ገድላትና ታምራት በእምነት ውስጥ ሳንሆን በሎጂክ ተመርተን እንመርምራቸው ካልን ተስፋየ ገ/አብ የሙሴን ባህር መክፈል ከጂኦግራፊያዊ ሀቅ ተነስቶ እንዳለው ብዙ መ/ቅዱሳዊ ተአምራትንም ወደመጠራጠር ውስጥ ይከተናል-መቼም እ/ር በመ/ቅዱስ ከተጠቀሱት ውጭ ተአምራት አልሰራም አትሉም!!!በየቀኑ በፕሮቴስታንቶች ቸርች ተአምራት ተደረጉልን የሚሉ ምስክርነቶችን ካለያችሁ እየተባልን የእኛ ጊዜ ሲሆን ግን ተረት-ተረት እያሉ ማጣጣልም አያከባብርም!!!ስጋቸውን በጾም መጎሰም ሳይሆን የሚያደልቡት የሚሊኒየሮቹ የነ Pastor Chris እና Prophet T.B Joshua የተአምራት ዝና ያልከለለው አምላክ የኢትዮጵያዊው ጻድቅ የተ/ሃይማኖት ገድል መነገር እንዴት አድርጎ ክብሩን እንደሚከልለው አይገባኝም!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፅጌ ስጦታው እንደ መፅሃፎቹ ሁሉ እዚህም ሳይት ላይ ሲያምታታ አዋቂ ሲመስል ሌላ ሰውን ሲሳደብ እና ራሱን አዋቂ አርጎ ሲፅፍ ምንም አላፈረም:: ሰውን ተሳሳተ ብሎ መረጃ ሊሰጥ እየሞከረ መሳሳት መቼም የጤና አይደለም::
   -''...አርማለሁ ብሎ ጥፋቶችን ፈጽሟል'' ያለ ሰው ሲዋሽ ተልመልከቱ::
   ፅጌ ስጦታው አቡነ ጎርጎርዮስንም በሌብነት ይከሳል:: "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።" ይለናል:: በመጀመሪያገፅ ፯፪ ላይ እንዲህ የሚል ጭራሽ የለም:: በሁለተኛ ደረጃ ገፅ ፯፱ ላይ በትክክል ተፅፎ ይገኛል:: በዚህ መፅሐፍ እንዲህ የተሳሳተ ሰው በሌላው እመኑኝ ሲል እንዴት ይታመናል::

   ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ ፯፱ ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ፍረዱ:: ይሄን ውሸታም ጴንጤንም ታዘቡት::
   https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG
   ማፈሪያ::

   Delete
 38. አባ ወልደትንሳኤን በሚገባ ፕሮሞት አደረጋችኋቸው። ምነው ታዋቂነታቸው ቀዘቀዘ እንደ? ተሃድሶነታቸው ከፓትርያርኩ ጋር ያጋጫቸው ነበር ይባላልና ያንን ማስተባበላችሁ ነውን? ፓትርያርኩ እንድህ እንደወረዱ አላወቅንም ነበር፣ አሁን ግን ብዙ ሰው ሊገባው ይችላል።

  ReplyDelete
 39. The patriarch of the Ethiopian Orthodox Tawahedo Chruch, Abune Mathias, was placed under house arrest temporarily, but has since been released, according to a report by the Ethiopian Review today.

  The move is reported to have been carried out by National Security Adviser to the Prime Minister, Tsegaye Behane, allegedly over the patriarch’s criticism of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Force (EPRDP).

  The Ethiopian Orthodox Church is currently facing a leadership crises and many church leaders have publicly rebelled against the authority of the church, which only split from the Coptic Orthodox Church in 1959.

  Abune Mathias was reportedly interrogated for 72 hours before his release. Although the actual reasons for his temporary arrest is unknown, there are speculations that it relates to comments made by the patriarch recently where he revealed that most of the church’s current problems are being created by the state.

  The Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF), one half of the ruling EPRDP coalition, is also reported to have been the focus of some of the patriarch’s recent critical comments.

  This is not the first time Abune Mathias, who was born in the Tigray region, is clashing with the government.

  In the 80′s, when he was Bishop of the Ethiopian Orthodox Church in Jerusalem, Abune Mathias was critical of Menghistu Haile Mariam’s regime. His outspokenness eventually caused him to go on exile in the United States of America for about 30 years until the downfall of Meghiatu’s regime.

  Abune Mathias, 71, was installed as the 6th patriarch of the Ethiopia Orthodox Church in March 2013 after winning about 500 out of 806 votes cast by an elective council a month earlier. His appointment has since been disputed by many, who say the 4th patriarch Abuna Merkorios should have been reinstated, since he was deposed under questionable circumstances.

  ReplyDelete
 40. http://www.danielkibret.com/2013/10/blog-post_5157.html (Part one)
  http://www.danielkibret.com/2013/11/blog-post_5.html (Part two)

  Readers here also Daniel's write, need it for comparing

  ReplyDelete
 41. አቶ አዲስ አስተያየት በመቀበልና ከሊቃውንቱ እግር ስር ቁጭ ብለህ በመማር አቅምህን አሻሽል፤ የጽሑፍህ ይዘት ምንም ውኃ የማያነሣ እንቶ ፈንቶ ሆነባቸውና የጠየቅሃቸው የሕትመት ሚዲያዎች ሁሉ ከፈለግህ ተሸክመኸው ዙር እንጅ ይህ ለእኛ አይመጥንም ዞር በልልን አሉህ፡፡ ድንቁርናህን በሰዎች እያሳበብክ ለምን ከመማር ትዘገያለህ? አሁንም ጊዜ አለህ ለመማር ተዘጋጅ፡፡ ያለ አቅምህ ደግሞ ባትንጠራራ ለመሆኑ ይህን መደዴ ጽሁፍህን ስትጽፍ አንድ ማስረጃ አለማቅረብህ የማንነትህ መገለጫ መሆኑን የዚህ የሰለጠነ ዘመን ትውልድ የሚያጣው ይመስልሀል? ቂል ነህ!!

  ReplyDelete
 42. hhhhhhhhhh hhhhhhhhhhh hhhhhhhhhh ay tsehuf ay teshuf yegermal abo d/n Danei kebret nurelen lela menem alel,d/n Daniel kebret ene lerase ye bete cherstiyan lik or temeramari beyehalew yansebahal mitsefuten asatahachew haset be adebabay kolewaa tegefefef

  ReplyDelete
 43. who are you yewshet tarik awaki sew alawk silachu sew yawekewn bemetechet tawaki lemehon metar ye bizu sew chiger ebakachu sira siru

  ReplyDelete