Wednesday, December 18, 2013

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደረጃውን ባልጠበየቀ የአስተዳዳሪዎች ዝውውርና ሐሳብ እየታመሰ ነው

F አዲሱን የማኅበረ ቅዱሳን  መዋቅር ይቃወማሉ የሚባሉ አንጋፋዎቹ የአዲስ አበባ አስተዳዳሪዎችን ጡረታ ለማውጣት እንቅስቃሴው ቀጥሏል፡፡
Fአዲሱ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሐሳቡ አልተስማሙም ፡፡
F የአቡነ እስጢፋኖስ አስተዳደር አይገዛንም የሚሉ የምእመናን ቡድኖች እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
F የደብር አስተዳዳሪዎች እስጢፋኖስ ዲያቆን ነው ድሮም ዲያቆን ቤተክርስቲያንንን ይራዳል እንጂ አይመራም በማለት ቅኔ እያስቀኙባቸው ነው፡፡
F እነ ዳዊት ያሬድ በጅማ አብያተ ክርስቲያናት ስም ገንዘብ በማሰባሰቡ ሥራ ተጠምደዋል
የአቡነ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚካሄደው ሹም ሽር እንደቀጠለ ሲሆነ ዋናው  የቤተክርስቲያኗ የአስተዳደር ማእከል አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም ባልተረጋጋ ሁኔታ ሲኖዶስ በተሰበሰበ ቁጥር እንደ ዝክር ዳቦ አንዴ ከ አራት አንድ ከሰባት እየተሸነሸነ በመካከል ባለው አለመረጋጋት የአስተዳደር ክፍተትን በመጠቀም የቤተክርስቲያኒቱ ሐብት እየባከነ ይገኛል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ተረኛ ዘካሪ አቡነ እስጢፋኖስ ከሁለት ቤት ደግሰው አንዴ ጅማ አንዴ አዲስ አበባ እያሉ ሲያሻቸውም አዲስ አበባ ላይ ለደጆችሽ አይዘጉ. ለጅማ እጓለ ማውታ፣ ለአበልቲ አብያተክርስቲያናት  በሚል ከአንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎችና ሀብታሞች ገንዘብ ማሰባሰባቸውን ቀጥለዋል፡፡

በዚሁ መስፈርትም አንጋፋዎቹን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ታላላቅ አድባራት አስተዳዳሪዎች በጡረታ ለማግለል የቀረበውን እቅድ የሀገረ ስብከቱ አንዳንድ የስራ ኃላፊዎች አልተቀበሉትም፡፡የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጆችን ባገለለው በዚሁ ስብሰባ መልአከ ገነት ተስፋ ፍስሀ የሳሪስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የጎላ ሚካኤሉ አስተዳዳሪ ፤የዩሐንስ ወልደ ነጎድጓደዱመምህር ዘመንፈስ ቅዱስ፤ የየካ ደብረ ሳልህ ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ፤ የቂርቆሱ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ዘለአለም እሰይ እንዲሁም የሰአሊተ ምህረቱ አስተዳዳሪ አባ ገብረ ሥላሤ በጡረታ እንዲገለሉ በአባ እስጢፋኖስ አማካነት ሐሳብ ቀርቦባቸዋል፡፡
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የአቡነ እስጢፋኖስን አስተዳደር አንቀበልም የሚሉ የምእመናን ቡድኖችም በሰአሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ቅዳሜና እሑድ ስብሰባ እያደረጉ ናቸው፡፡  እነዚሁ  በህገ ወጥ መልኩ በሰንበቴ ሽፋን ተደራጅተው በሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል  ይዞታ በሰሯቸው አዳራሽና ፉካ በከፍተኛ የፉካ ንግድ አንድ ፉካ ለሀገር ውስጥ በ30 ሺ እናከውጪ ለሚመጣ በ 50 ሺህ ብር በመሸጥ ኦርቶዶክስ ላልሆኑ ግለሰቦች በ 70 ሺ ብር ፉካ በመሸጥ እና በመቅበር በተሰማሩና ከዚሁ ባገኙት ገንዘብ    በተለያዩ የቢራ አክስዮን ማኅበራት አክሲዮን ገዝተው በሚነግዱ 7 የጡረተኛ ቡድኖች በምትታመሰው እና ቤተክርስቲያኗን ከማእከላዊ አስተዳደሯ  በመገንጠል ገለልተኛ ቤተክርስቲያን እንመሰርታለን በሚል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሊመራን አይችልም በሚል አቡነ እስጢፋኖስን በመቃወም በግልጽ ደብዳቤ በመጻፍ ለእሳቸው እንደማይመሩ ያሳወቁትን በቀድሞው የደርግ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪና በቅርቡ ከእስር ቤት በተፈታው አንሙት ክንዴ እና በቀድሞው የሕንጻ ኮሚቴ ሊቀ መንበር አቶ ወልዴ ጥላዬ እንዲሁም ሴቶች በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ሊያስተምሩ ይገባል በማለት ‹‹ የሊዲያ ቤተሰብ  ›› በማለት የራሷን በሴት መምህራን የተዘጋጀ ጉባዔ  በመመራትና በማስተማር በምትገኘው ቅድስት አሳልፍ የሚመራውና  ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የጥቅም መስመር ዘርግተው የሚበጠብጡት ግለሰቦች የልብ ልብ ተሰምቷቸው በቅርቡ ወደ ቦታው የተላኩትን የአቡነ  እስጢፋኒስ ወዳጅ ሰአሊተ ምህረቱን አዲስ አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ሥላሴን በአስቸኳይ ቤተክርስቲያኗን ለቀው እንዲወጡ ያስፈራሯቸው ሲሆን የአቡነ እስጢፋኖስ አስተዳደር የሚልካቸውን አለቆች ባለመቀበል የካቴድራሉን ዋና ጸሐፊ እና ሒሳብ ሹም እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች ቢሮ አሽጎ   ለማባረር ያሰቡት ሐሳብ በፖሊስ አማካኝነት ከሽፎባቸዋል፡፡
  
ይህ ሁሉ ግርግር ቢኖርም አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ የራሳቸውን ደጋፊዎች በማተባበር ለአበልቲና ለጅማ ወላጅ አልባ ሕጻናት በሚል ገንዘብ በማሰባሰብ ሥራ ተጠምደዋል፡፡ ይህንኑ ሥራ የሚሰሩላቸው የአፍሪካ ኅብረት ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲን ዋና ጸሐፊ የሆነው አብርሃም አቧህይና ቀድሞ  ከርቸሌ ሚካኤል የሚባለው አሁን አፍሪካ ኅብረት ዋና ጽ/ቤት በተሰራበት ጊዜ ለቤተክርስቲያኑ በካሳ መልክ የተከፈለውን 4 ሚሊየን ዶላር ተቀብለው፤ የተቀበልኩት  4 ሚሊዮን ብር ነው በማለት ከ 76 ሚሊየን ብር በላይ የሚቆጠር ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉትን ጁፒተር ሆቴሎችን በካሳው ብር በመገንባት የከተማዋ ዝነኛ ሀብታም ለመሆን የቻሉትን የጁፒተር ሆቴል ባለቤት አቶ ብስራት እንዲሁም በዘረኝነታቸውና በጠንቋይነታቸው የሚታወቁትን የቦሌ ሚካኤሉን አለቃ መልአከ ፀሐይ ስዩምን በቅርቡ አቡነ እስቲፋኖስ በሕጋዊው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዘረፋ ፕሮግራም በሚባለውና ሰራተኞቹ አይ ኤም ኤፍ በሚሉት የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናት አስተባባሪነት በአቡነ እስጢፋኖስ እንዲሾሙ ተደርገዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ የአርሴማው አለቃ መልአከ ፀሐይ ፀዳሉ በዚሁ የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሚሳተፉ ሲሆን በቅርቡ በአቶ ብስራት አማካኝነት 200.000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለአባ እስጢፋኖስ በማደጎ ልጃቸው በዳዊት ያሬድ አማካኝነት ተሰቷቸዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ አባ እስጢፋኖስ ከፍተኛ ሹም ሽር ለማካሄድ እና የራሳውን ሰዎች ለመጥቀም ረቂቅ ያዘጋጁ ሲሆን የሚዛወሩትም አለቆችና ጸሐፊያን አዲሱን የማኅበረ ቅዱሳን የአስተዳደር መዋቅር ይቃወማሉ የሚባሉትን አለቆች ከደረጃ ዝቅ በማድረግ
የቦሌ ሚካኤሉ አለቃ መልአከ ፀሐይ ስዩም ወደ የካ ሚካኤል በጡረታ በሚገለሉት በአባ እዝራ ቦታ ፤ መልአከ ጸሐይ ጸዳሉ ወደ ሰሚት መድኃኔ ዓለም፤ የሰሚት መድኃኔዓለሙ አለቃ አባ ገብረ ስላሴ  ቀደም ሲል ከአያት ገብርኤል በዘረፈው ብር መኪና እንደገዛ እያወቁና ገንዘቡን የሰጠሁት ለቤተክርስቲያኗ  ነው የሚሉ ምእመን አቤቱታ እያቀረቡበት የአቡነ እስጢፋኖስ ዘመድ በመሆኑ ብቻ   የልማት አባት በሆኑትና ለቤተክርስቲያኗ ጥቅም ቀን ከሌት የሚሮጡት ከ 30 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ትልቅ ካቴድራል ግንባታ እያፋጠኑ በሚገኙት መልአከ ምህረት ዘካርያስ ሐዲስ በቦታ ሰሲኤም ሰሲ መሚካኤል በቦ ቦታ ሲኤም ሲ ሚካኤል ፤ ሕጋዊ መነኩሴ የሚባለውና ልጆቹና ሚስቱን ይዞ በሚኖረው  የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ አለቃ ‹‹አባ›› ገብረ ሚካኤልን ወደ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል፡፡ የቦሌ መድኃኔዓለሙን ዋና ጸሐፊ ቀሲስ ሰሎሞን በቀለን ወደ አፍሪካ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል በማድረግ የአፍሪካ ኅብረቱን ዋና ጸሐፊ አብርሃም በቧሀይን ወደ ቦሌ መድኃኔዓለም፡፡ የአራዳ ጊዮርጊሱን አለቃ መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃን ወደ ቦሌ ሚካኤል፣ የአቡነ ቄርሎስ የእህት ልጅ የሆኑትን የአፍሪካ ኅብረቱን አለቃ መልአከ ሕይወት መልአክ አበባውን ወደ ፉሪ ሐና፤ የጊዮርጊሱን ዋና ጸሐፊ የማነ ዘመንፈስን ወደ ሳሪስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በማዛወር ሌሎቹን ክፍት ቦታዎች ከጅማ በሚመጡ አዳዲስ አለቆች ለማሟላት ረቂቅ አዘጋጅተው በቅርቡ በ 500.000.00 ብር የኮንዶሚኒየም ቤት በአያት በገዛው የአቡነ እስጢፋኖስ የማደጎ ልጅ በዳዊት ያሬድ አማካኝነት ለሀገረ ሰብከቱ የአስተዳደር ጉባዔ አባላት በየቢሯቸው እንዲፈርሙ ቃለ ጉባዔ ቢላክም ብዙዎቹ ጉዳዩን በመደበኛ ስብሰባ እንዲታይ በማለታቸውና አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ባለመስማማታቸው ረቂቁ ማክሰኞና ሐሙስ በሚኖረው ስብሰባ እንደሚታይ ታውቋል፡፡

2 comments:

  1. tehadiso kalgebabet wogel, astedader, awaki yele

    ReplyDelete
  2. shum shiretun besentereje beekemet anbebo lemeredat yekelal....

    ReplyDelete