Monday, December 16, 2013

በስደተኛው ሲኖዶስ ሥር የሚገኙ ሰባክያነ ወንጌልን የማጥቃት እንቅሥቃሴው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

   ጥቃቱ ያነጣጠረው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ጨምሮ ሌሎችን አገልጋዮችንም ይጨምራል። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት 13 ሰዎች ለውግዘት ታጭተው ነበር። እነርሱም ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል፣ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ አባ ገብረ ስላሴ ጥበቡ፣ ቀሲስ መላኩ ባወቀ፣ አባ ላእከ ማርያም፣ አባ ገ/ ማርያም፣ አባ ገ/ሚካኤል፣ ቀሲስ ጌታቸው፣ ቀሲስ እንዳልሃቸው ሲሆኑ አሥራ ሦስተኛው ማን እንደሆነ አልታወቀም፤ ይህ ስም ዝርዝር ዲሲ አካባቢ በሚገኙ የአቡነ መልከ ጼዴቅ ደጋፊ ነን የሚሉ ፣ ነገር ግን ከነዶክተር ካሱ ይላላ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ያቀረቡት እንደነበረ ምንጮቻችን ገልጸዋል። አንድ የደረሰን መረጃ  የዚህ ሐሳብ ዋና ተዋናይ ዶ. ነጋ መሆኑን ይጠቁማል። ይህ ጥቆማ የደረሰን የዛሬ ሁለት ዓመት ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እስክናሰባስብ አቆይተነዋል። አሁን ግን በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ ይህንን ጥቆማ የሚደግፉ በርካታ ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ ለጥንቃቄና አሁን በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ የሚስተዋለውን ትርምስ ለመገንዘብ አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል አቅርበነዋል።
    አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ኢሕዴግ ወይም ማህበረ ቅዱሳን ወይም በራሱ ተነሳሽነት የሲኖዶሶች የእርቅ ኮሚቴ የሆነው የነ ሊቀ ካህናት ኀ. ሥላሴ እጅ አለበት ሲሉ  አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ስደተኛውን ሲኖዶስ ወክለው የእርቅ ኮሚቴ አባል የነበሩትና በማሀረ ቅዱሳንነት የሚጠረጠሩት የዲ.አንዷለምና የአባ ጽጌ ደገፋው እጅም ሊኖርበት እንደሚችል ጠቁመዋል። እንደሚታወቀው በእርቅ ኮሚቴነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፦ የአገር ቤቱን ሲኖዶስ የወከሉት ሊቀ ካህናት ኀ. ሥላሴና ቀሲስ አንዷለም ዘኦሪገን (ሁለቱም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው) ሲሆኑ በስደተኛው ሲኖዶስ የተወከሉት አባ ጽጌ ደገፋው፣ ዲ.አንዷለም ዳግማዊ እና መምህር ልኡለ ቃል አካሉ ነበሩ። ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ  በ ዶ/ አማረ ተወክለው ተሳትፈዋል።

  በስደተኛው ሲኖዶስ በኩል የእርቁ እንቅፋቶች ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና በሲኖዶሱ ሥር የሚገኙ ታዋቂ ሰባኪዎች ናቸው የሚል እምነት እንዳለ ምንጫችን አክሎ ገልጿል። ይህንን አስተሳሰብ የሚጋሩ በርካታዎቹ የእርቅ ኮሚቴ አባላት እና ማህበረ ቅዱሳን ናቸው።  በበርካታና ጠንካራ ሰባኪያን የተደገፈውን የውጭውን ሲኖዶስ መበታተን ካልተቻለ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ማምጣት አይቻልም ብሎ ማህበረ ቅዱሳንና የቅርቅ ኮሚቴው  ያምናል ይላል የደረሰን መረጃ። ኢሕዴግም የውጭው ሲኖዶስ ዲያስፖራውን እያሸፈተ ስለሆነ መበተን አለበት ብሎ ያምናል። ሦስቱም የተለያየ አላማ ይኑራቸው እንጂ በሲኖዶሱ መፍረስ ያምናሉ። ታዲያ ወንጌላውያኑን ማጥቃት ለምን አስፈለገ? ማንም ይሁን ማን  ካህናቱን ለመለያየት የተሄደበት መንገድ የሚከተለውን ይመስላል።
  የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ እርቁ በጉጉት በሚጠበቅበት ወቅት በመላከ ገነት ገዝሃኝና በአባ ጽጌ ደገፋው የሚመራ የስልክ ኮንፈረንስ ተደርጎ ነበር። አጀንዳውም ስለ አገልግሎታችንና ስለ ወቅታዊ ችግሮች የሚል ሲሆን ዋና አላማው ግን ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅን ከዋና ጸሐፊነት ለማውረድ ነበር። በዚህ ስብሰባ የመጀመሪያው ቀን ሁሉም የሲኖዶሱ ካህናት የተገኙ ሲሆን በሁለተኛው ስብሰባ ግን ጥቂት ካህናትና የዲሲ ቦርዶች እንዲሁም ያልታወቁ ሰዎች ገብተው ነበር። ሁለተኛው ስብሰባ ለሲኖዶሱ ካህናት ለሆኑት ለሁሉም አልተነገራቸውም። በዚህ የስበሰባ ቀን ያልታወቁ ተሰብሳቢዎች አቡነ መልከ ጼዴቅ ከጸሐፊነት ይውረዱ የሚል ቃላት ሰንዝረዋል። ወዲያው ለአቡነ መልከጼዴቅ ካህናቱ በርስዎ ላይ አድመዋልና ሌሎች ደጋፊዎች ያስፈልጉዎታል የሚል ምክር ተላለፈላቸው። ይህን አድማ የሰሙት አቡነ መልከ ጼዴቅ  ዶ. ነጋን፣ አቶ ምርጫውን፣ ዶ. አምባቸውን እና ሌሎችንም "የሲኖዶሱ ደጋፊ አባላት» ብለው ከሾሙ በኋላ የካህናት ጉባኤ ብቻ በሆነው የኦሀዮ ሲዶስ እንዲገኙ ስብሰባ ጠሯቸው። ከላይ ስማቸውን የጠቀስናቸው ካህናትና ሰባክያን በስማቸው የተካሄደውን ስብሰባና በአቡነ መልከ ጼድቅ ላይ የተሰነዘረውን ቃል አያውቁም ነበር። ተሳትፈዋል ለማለት ያህል የመጀመሪያውን ስብሰባ እንዲገኙ አድርገው በሁለተኛው ግን ሌሎች ተሰብስበውበታል ይላል የደረሰን ኢ ሜይል። ካህናቱ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ያልተለመደ ነገር ያዩና እነዚህ ምእመናን ናቸውና ይውጡልን ይህ የካህናት ጉባኤ ብቻ ነው ይላሉ። ካህናቱም ሆኑ ጳጳሳቱ ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ የካህናቱን አድማ ለመከላከል የጠሯቸው መሆናቸውን አልተገነዘቡም ነበር። ካህናቱም እርሳቸውን ከጸሐፊነት የማውረድ ሐሳብ አልነበራቸውም። አቡነ መልከ ጼዴቅ እነዚህ ደጋፊዎች ከወጡ እኔም እወጣለሁ አሉ። እንዲያውም ጳጳስ ስላልሆናችሁ እናንተ ውጡ ብለው ነበር የሞገቱት። በዚህ ጊዜ ካሃንቱና አቡነ መለከ ጼዴቅ ተለያዩ።
  ሌሎች ልዩነቶችም ከዚህ በፊት የነበሩ ሲሆን ይህ ሲጨመር ነገሩ እየባሰበት መጣ። ለምሳሌ ፤- በካናዳው ሲኖዶስ አቡነ ዮሴፍ፣ አቡነ ያዕቆብና አባ ገ ሥላሴ ምርጫ እንዲያካሂዱ ወደ ዲሲ ገብርኤል ተልከው ነበር፣ ነገር ግን አቶ መሐሪ ከቦርድ ሊቀ መንበርነት አልወርድም በማለቱና ሦስቱን ልኡካንንም በፖሊስ አባሮ በማስወጣቱ፣ አቡነ መልከ ጼዴቅም አስታርቁ ተባላችሁ እንጂ ምርጫ አድርጉ አላልንም ብለው አቶ መሐሪን በመደገፋቸው በሦስቱ ልኡካንና በአቡነ መለከ ጼዴቅ መካከል ጠብ የጀመረበት ጊዜ ነበር። ከዚህ ጋር ተከታትሎ አባ ቃለ ጽድቅ ሙለጌታ ከኦክላንድ መድኃኔ አለም ቦርዶች ሰንበት ተማሪዎችና አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር ባለመግባባታቸው የሕዝቡም ጥያቄ በአግባቡ ባለመመለሱ መድኃኔ ዓለምን ትቶ ወጥቶ ኢየሱስን በማቋቋም ላይ ነበር። አባ ወልደ ትንሣኤም ሕዝቡ በሄደበት ተገኝተው በማጽናናታቸው አንድ ጥርስ ውስጥ ገቡ። እንዲሁም ቀሲስ እንዳላሃቸው ለቅዳሜ ቅስና ለመቀበል ተዘጋጅቶ እያለ አርብ ወደ ማታ ቅስና እንዳይቀበል አቡነ ሳሙኤልም ቅስና እንዳይሰጡ የታገዱበት ጊዜ ነበር። ይህ ሁኔታ ያሳዘናቸው አባ ወልደ ትንሣኤ ቀና አመለካከታቸውን ከፍ በማድረግ ቀሲስ እንዳልሃቸው ወደ ሎስ አንጀለስ ድንግል ማርያም መጥቶ በአቡነ ዮሴፍ ቅስናውን እንዲቀበል አደረጉ፤ አባ ወልደ ትንሣኤ ጉዳት በደረሰበት አካባቢ እየሄዱ መጠገን ዋና ሥራቸው ሆነ። በዚህም ሁለተኛው ጥርስ ውስጥ ገቡ። ቀሲስ እንዳልሃቸው ቅስና የተቀበለበት ቀን ጥምቀት ነበር። በዚያ ቀን ካህናቱ በሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም አቡነ መልከ ጼዴቅን ይዘው "ምን በደልንዎት? ደጋፊ አባላት ብለው በኛ ላይ ሌላ ያመጡብን ለምንድን ነው?» ብለው ለብቻ ጠይቃውቸው ሲመልሱ "በማን ላይ እዚህ ደረሳችሁና ነው እኔን ከጸሐፊነት ለማውረድ ያደማችሁብኝ? እኔስ ምን በድያችሁ ነው?» ብለዋል። በዚህ ጊዜ ካህናቱ እነርሱን ከርሳቸው ጋር ለማጋጨት ሌላ ያልታወቀ አካል ሴራ እንደፈጸመባቸው ተገነዘቡ። እኛ አላልንም በማለት ቢምሉ ቢገዘቱ ሊቀበሏቸው አልቻሉም።
   ወዲያው በቀል ተጀመረ፤ አቡነ ሳሙኤል ከዲሲ ገብርኤል ተባረሩ። አባ ወልደ ትንሣኤም በዲሲ በተካሄደው ስብሰባ በፖሊስ ተወስደው ታሰሩ። ቀሲስ እንዳልሃቸውም ከሥራ ተባረረ፣ በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን አቋቋመ። አባ ገ/ ሥላሴ ጥበቡ ከሲያትል ገብርኤል ተባረሩ፣ ብጹእ አቡነ ሰላማ በአትላንታ ተቀብለው ማረፊያ ሰጥተዋቸው እየኖሩ ነው። አባ ቃለ ጽድቅ ተወገዙ፣ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ከጸሐፊነት ይወረዱ ተባለ። ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተከላካይነት እስከ 37ኛው ጉባኤ ቢቆዩም የፓትርያርኩን አለመኖር እንዳጋጣሚ በመጠቀም ከጸሐፊነት እንዲወርዱ ተደርጓል። አሁንም ሌላ አዲስ ጥቃት እየተዘጋጀላቸው ነው ተብሏል። ቀሲስ መላኩም ወደ ኦክላንድ ኢየሱስ መጥቶ በመስበኩ ክህነቱ እንዲያዝና ከጸሐፊነት እንዲወርድ ተባለ፣ ከጸሐፊነት መውረዱ ባይቀርም በሎስ አንጀለስ ሕዝብ ከፍተኛ ድጋፍ ያለው በመሆኑ አገልግሎቱን ቀጥሏል።
  ሴራውን አዘጋጅቶታል ተብሎ የተጠረጠርው ቡድን አሁን ወደ ሥልጣን በመምጣቱ ሌሎች አዳዲስ ጥቃቶችን እያዘጋጀ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። ለምሳሌ በኦሃዮ በተደረገው ስብሰባ የፓትርያርኩ ደብዳቤዎች እንዳይሻሩ በሲኖዶሱ ተወስኖ ነበር። ሲኖዶሱ ከተጠናቀቀ በኋላ ግን በምሥጢር የፓትርያርኩን ደብዳቤ የሚሽር ደብዳቤ ተጽፎ በዲሲ ገብርኤል ተነቧል። ደብዳቤው ያለ ምላተ ጉባኤው ውሳኔ የተጻፈ በመሆኑ የኦሐዮው ምላተ ጉባኤ የሻረው መሆኑን የሚገልጥ ነው።
 አባ ጽጌ ደገፋውን ለማነጋገርና እርቅ ለመፍጠር አባ ወልደ ትንሣኤ ከዲሲ፣ አቡነ ዮሴፍ ከላስቤጋስ፣ ዶ. አባ ገ ሥላሴ ከአትላንታ፣ አባ ሀብተ ማርያም ከሳንዲያጎ ወደ ሎስ አንጀለስ ሄደው ነበር፤ አባ ጽጌ ግን አልታረቅም ዘወር በሉ ብለው አሳፍረው መልሰዋቸዋል ተብሏል። ይልቁንም አባ ወልደ ትንሣኤ በድምጽና በቴክስት የበደልንህ ካለ ይቅርታ አድርግልን እባክህ ከሩቅ አገር መጥተን ሳናገኝህ አንሂድ ብለው ቢለምኗቸው መልስ አለማገኘታቸውን ሲናገሩ ተስምተዋል። ይህም ሌላ ጥቃት ሊኖር ይችላል የሚል ሥጋት አሳድሯል። እንዲሁም ዲ አንዷለም ፈለገ ሕይወት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የሚቃወም ደብዳቤ ከአቡነ መልከ ጼዴቅ አጽፎ በዳላስ ሚካኤል በሕዝብ ፊት አስነብቧል። ቄስ ሽታ እና መምህር ተከስተን ጸረ ማርያሞች ለስእል የማይሰግዱ መናፍቃን እያለ በሕዝብ ፊት ሲያወግዛቸው ማርፈዱን የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። መምህር ተከስተ ጠብ አይመቸኝም በማለት አቡነ መልከ ጼዴቅን ትቶ በመሄዱ የተወሰደበት የበቀል እርምጃና ዲ. አንዷለምን ለማስደስት የተጸፈ ደብዳቤ ነው ይላሉ ታዛቢዎች።
 በርካታ ታዛቢዎች ኢሕዴግ ወይም ማሀረ ቅዱሳን ወይም የእርቅ ኮሚቴው ሲኖዶሱን እያመሰው እንደሆነ ብጠቁሙም የትኛው አካል እንደሆነ በርግጠኝነት መናገር አልተቻለም። ከሦስት አንዱ እንደሚሆን ግን ብዙዎች በእርግጠኝነት ይናገራሉ። አቡነ መልከ ጼዴቅ በአንድ ኃይል እጅ ላይ ወድቀዋል። ይህ ኃይል እራሳቸውን በመጠቀም ሥራውን እየተገበረ ነው ይባላል። ቅዱስ ፓትርያርኩም በኦሐዮው 37ኛ ሲኖዶስ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ውድቅ እንዳደረጓቸው ቅዱስነታቸው ያሉበት አካባቢ ያሉ ምንጮች ገልቸዋል። በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያሉ ምእመናን ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉትና እየተመካከሩበት ሲሆን ትኩረታቸውን በዶ. ነጋ፤ በአባ ጽጌ ደገፋው፤ በዲ. አንዷለምና በአቡነ መልከ ጼዴቅ ላይ አድርገዋል ተብሏል።
  መረጃው በትክክል አልቀረበም የምትሉ ካላችሁ ትክክለኛ መረጃዎትን  contact abaselama በሚለው ገብተው ኢሜይል ቢያድርጉልን የርስዎንም እናቀርባለን። አላማችን እውነቱን አፍረጥርጦ ማውጣት ነው። በተጨማሪም ዲ. አንዷለም ከናዝሬት ጀምሮ በጎፋ ገብርኤል በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ያሳደዳቸውን የሰንበት ተማሪዎችና መምህራን እያጣራን ስለሆነ ከማህበረ ቅዱሳን የውስጥ ምንጮችም አንዳድ መረጃዎችን ስላገኘን ታሪኩን እንዳጣራን ለንባብ እናቀርባለን።           

21 comments:

 1. Who cares about External and Internal Synods, Which just need only live with Lord Jesus. The Synod's bureaucrats killed our church. we are looking of the true Apostles like Aba wondentensay, Memeher Tikist, Kissis Shetta, Kisis Endlachew and others. I love Jesus!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Anetes yemotek neh ...sewu enekan atawuqem ...tekeset????? Enedalekachewu??????

   Delete
 2. ማኅበረ ቅዱሳን ከስደት ተመላሾችን ለመደገፍ እንደሚሠራ አስታወቀ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የትኞቹን! ከሳዑዲ ማለትህ ነዉ እኔ ልንገርህ ማቅ እነሱን አይረዳም ምክኒያቱም ባዶ እጃቸዉን ነዉ የመጡት እዚያ ሳሉ የወሰደባቸዉ ይበቃዋል

   Delete
 3. ወሬኛ። በምርቃና፥ በመሰለኝ እንዴት ይፃፋል?

  ReplyDelete
 4. ይቀጥላል ገና ገና መናፍቃን ከቤተክርስቲያን ተጠራርገው ይወጣሉ ንጹሆች ይለያሉ መናጆ አይሆኑም
  ያእቆብ ዮሴፍ በእምነት አይጠረጠሩም ቄሶቹም አይታዎቁም መነኩሴዎቹ ግን ቤተክርስቲያን ታጥቀው ሊያጠፉ ነው ተነስተዋል ፓትርያርኩን ለመናጆነት እየተጠቀሙባቸው ነው ፓትርያርኩን ሁሉም ያከብራል የማክበር ግዴታ አለበት

  ReplyDelete
 5. አባ ሰላማዎች ስለአቀረባችሁ ትክክለኛ መረጃ ምስጋና ይድረሳችሁ።
  ለማንኛውም በታሪኩ ተዋናይ የሆኑትን አባቶችና ወንድሞች በመጠየቅ ትክክለኛውን ታሪክ ብታቀርቡልን ደግሞ የበለጠ እንረዳለን የሚል አሳብ አለኝ።
  የማይዋጥልኝ ነገር ምንም እንካን የሌሎች እጅ መኖር ባይካድም አባ መልከጼዴቅ ግን ለዚህ ክፋትና ተንኮል የሚያንሱ አይደሉም። ዓላማቸውም በታትኖና አጥፍቶ ለመሞት እንደሆነ ብዙዎች ከአንደበታቸው የሰሙት ሐቅ ነው። ስለዚህ ስለአባ ኃብቴ (መልከጼዴቅ) ስትናገሩ በየዋኅነትና ባለማወቅ በሌሎች ወገኖች እንደሚታለሉ አድርጋችሁ ለማቅረብ ከመሞከር ትክክለኛ ጠባያቸውን ማስቀመጡ እውነተኞች ያሰኛችኃል።
  በርቱ ለእውነት መሥክሩ!!!

  ReplyDelete
 6. Abaselamawech pls aba melktsedek (habte) keblogachehu lay kelay kalut kengorgoriosena teophlos gar madregachehu telk sehetet newna ebakachehu awtut.yekfat anate nachew bezemenachew and seru yemibalut teru neger yelachewmena

  ReplyDelete
 7. Let's keep in mind all the characters mentioned in this article are not kids. So let's call a spade... a spade...

  ReplyDelete
 8. የማኅበረ ቅዱሳንን ስም ካልጠራችሁ አይሆንላችሁምን?

  ReplyDelete
 9. please see this important website. It has very important information. http://voiceoftheholysynod.blogspot.com

  ReplyDelete
 10. I have three questions.
  1. WHO bought the car for Aba Tsige of Los Angeles.
  2. WHO is Qes Muse? and WHY he is close friend of Aba Tsige of Los Angeles?
  3. Who is the Patriarch of the exiled Synod? Is Aba Habte ( Melke) or His Holiness Abune Merqorewos? I want to know?

  ReplyDelete
 11. አባ ሰላማዎች እኔ የሚመስለኝ የወያኔው ዶር ደብረ ጽዮን የላከው ዶር ነጋ አለማየሁ አቡነ መልከ ጼዴቅን በደካማ ጎናቸው ገብቶ የመበታተን ተልኮ እያከናወነ ነው

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማዎች ይህ የወያኔ ስራ ነው ዶር ነጋ ከዶር ደብረ ጽዮን የተሰጠዉን ተልእኮ በሚገባ እተወጣ ይመስለኛል ይኅም የ አቡነ መልከ ጼዴቅን ደካማ ጎን በመጠቀም ነው

  ReplyDelete
 13. The solution for our Fathers overseas is to return to Ethiopian and Make Peace with the Holy Synod in Ethiopia.

  ReplyDelete
 14. አልሰማችሁም እንዴ ዶ/ር ነጋ እኮ ትውልዱም ከትግሬ ነው። ቋንቋውንም አቀላጥፎ ይናገራል። እንዲያውም ከዶ/ር ደብረ ጽዮን ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው ይባላል።

  ReplyDelete
 15. 13 Ato kalesidik nschew

  ReplyDelete
 16. Because we are not bearing the the true cross of Jesus Christ, we are here to make strife against one another. Look at the coptic chrisitians who are suffering day by day for carrying the Cross. Unfortunately we are abusing God's mercy and destroying one another instead of destroying our common enemy.

  Do we have the gut to come out of this crisis and work hard for the Gospel of Jesus Christ? Can we work for unity ?

  ReplyDelete
 17. Aba kaltsedik in addis abeba

  ReplyDelete
 18. ሲያሰኛችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ከመንግስት ጋር ታጋጫላችሁ ሲያሰዓችሁ ከመንግስት ጋር አበረ ትላላችሁ ለመሆኑ በመሰለኝ ይወራል እንዴ ሃጢያት አይደል ያውም ከባድ እግዚአብሄር ስረውን ይሰራል መናፍቃን ሁሉ ጉድህ ፈላ

  ReplyDelete