Sunday, January 26, 2014

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም ክፍል 16

Read in PDF

የግንቦት 15/2004 ዓ.ም «ውግዘት»ን በተመለከተ ኑፋቄ ተብለው በተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የተላለፈውን ሕገወጥ ውግዘት በተመከለተ በአዋልድ መጻሕፍትና በልማዳዊ ትምህርት ሲመዘኑ ኑፋቄ ተብለው የተወገዙትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ከዚህ በፊት በ15 ክፍሎች ማቅረባችን የሚታወስ ነው፡፡ በ“የእውነት ቃል አገልግሎት” ላይ የቀረቡትንና ኑፋቄ የተባሉትን ነጥቦችን መመልከት እንቀጥላለንና ይከተሉን፡፡ 16ኛው ክፍል ይኸው፣

“ሐ. በዓለመ ሙታን የሚገኙ ነፍሳትን መጥራት በእግዚአብሔር ቃል በእጅጉ የተወገዘ የባዕድ አምልኮ ድርጊት ነው” በማለት በአጸደ ነፍስ የሚማልዱ ቅዱሳንን ይተቻል፡፡ መጽሐፈ ሰዓታት በመቅደሱ ሚዛን ገጽ 33፡፡”

ከሊቃውንት ጉባኤ የማይጠበቅ ትልቅ ስሕተት! ለእውነት ሳይሆን ለተረት የቆመ መከላከያ! እውነትን ለሐሰት የሰዋ ትልቅ ድፍረት! ለሃይማኖት ዋና መሰረት የሆኑትን ብሉያትና ሐዲሳት ወደጎን ብሎ ልማደ አሕዛብን መከተል! የስህተት ትምህርትን በመደገፍ መጽሐፍ ቅዱስን ኑፋቄ ያደረገ አሳፋሪ ምላሽ! ለአምልኮተ እግዚአብሔር ደንታ ቢስ የሆነና ለአምልኮተ ባዕድ መስፋፋት ቀኝ እጁን የሰጠ ዳኝነት! 

አሁን ይህን ለቤተክርስቲያን የቀረበውን የማስተካከያ ሐሳብ እንዳለ መቀበል እንጂ ስሕተት ነው ብሎ ማውገዝ ምን ይሉታል? “በዓለመ ሙታን የሚገኙ ነፍሳትን መጥራት በእግዚአብሔር ቃል በእጅጉ የተወገዘ የባዕድ አምልኮ ድርጊት” አይደለምን? “አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።” (ዘዳ. 18፡11) የሚለው ካንቀላፉ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሌለን ወደእነርሱ መጸለይም ሆነ በአምልኮተ ባዕድ ልምምድ ውስጥ በሙታን ሳቢዎች ድግምት እንዳንነካካ የሚናገር የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው፡፡

ይህ ክልክል ድርጊት በአጸደ ነፍስ ካሉ ቅዱሳን ጋር መገናኘትን እንደማይጨምር አድርጎ አድርጎ ማቅረብ ከማኅበረ ቅዱሳን መራሹ የሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ የተሻለ እውነትን ለመግለጥ ከማቅ ተጽዕኖ ነጻ መሆን ነበረበት፡፡ ግን አልሆነምና በዓለመ ሙታን የሚገኙ ነፍሳትን መጥራት አልተከለከለም በማለት ከቅዱሳን የአጸደ ነፍስ ምልጃ ጋር ነገሩን በማያያዝ ወዳንቀላፉ ቅዱሳን ሰሚ የሌለውንና በቅዱሳኑ ስም ሰይጣን የሚቀበለውን ጸሎት እንድንጸለይ ፈቃድ ሰጥቶናል - ባንጠቀምበትም፡፡

በዓለመ ሙታን ያሉ ነፍሳትን በሰይጣን ወይም በሙታን ሳቢ መንፈስ በመጠቀም ካልሆነ በቀር በማንኛውም መንገድ ማነጋገር እንደማይቻልና ክልክል እንደሆነም ይታወቃል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር የናቀው ሳኦል አስቀድሞ አጥፍቷቸው የነበሩትን ሙታን ሳቢዎች ወይም መናፍስት ጠሪዎችን በመፈለጉ “እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።” (1ዜና. 10፡13-14)፡፡ ሳኦል ሳሙኤልን እንድታስነሣለት ነበር ለመናፍስት ጠሪዋ የነገራት፡፡ እርስዋም ስታሟርት ሳሙኤል ነኝ ባይ መንፈስ ነበር ተገልጾ ያነጋገረው (1ሳሙ. 28፡6-16)፡፡ መቼም ያንቀላፋው የእግዚአብሔር ነቢይ ሳሙኤል በሙታን ሳቢ ይመጣል ብሎ መጠበቅ ብርሃንና ጨለማ ኅብረት አላቸው ከማለት የተለየ አይደለም፡፡

አንዳንዶች ይህን ሙታን የመሳብን አሕዛባዊ ልምምድ በአጸደ ነፍስ ወዳሉ ቅዱሳን ከመጸለይ ጋር አይገናኝም ይላሉ፡፡ ምንም ብናመናፍሰው (መንፈሳዊ ለማድረግ ብንሞክር) ዞሮ ዞሮ ድርጊቱ ከዚያ የተለየ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ካንቀላፉ ቅዱሳን ጋር መንፈሳዊ ኅብረት ያለን መሆኑ ቢታወቅም በቀጥታ ወደእነርሱ እንጸልያለን፤ ከእነርሱ ጋርም በጸሎት ቀጥተኛ ግንኙነት ይኖረናል ማለት ግን እንዳልሆነ ሊታወቅ ይወገባል፡፡ በጌታ ያንቀላፉ ቅዱሳን በክብር እንዳሉና ሕያዋን እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እኛና እነርሱ በቀጥታ የምንገናኝበትና የምንነጋገርበት መሥመር ግን የለም፡፡ እግዚአብሔር ታላቁ ነቢይ ሙሴ ዐልፎ ኢያሱ ሊተካ ባለ ጊዜ ስለሙሴ የተናገረው “ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።” በማለት ነበር (ኢያሱ 1፡2)፡፡ ሙሴ ታላቅ ነቢይ የነበረ ቢሆንም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ሕያው ቢሆንም በስጋ ካሉት እስራኤላውን ጋር የነበረው ቀጥተኛ ግንኙነት ተቋርጧልና ደቀመዝሙሩ ኢያሱም ሆነ ሕዝበ እስራኤል ከዚያ በኋላ የእርሱን አመራር ስለማያገኙ ኢያሱ ሕዝቡን እንዲመራና ወደተስፋይቱ ምድር እንዲጓዙ ተነገረው፡፡ ይሁን እንጂ ሙሴ ቢሞትም ሕያው ስለሆነ በአጸደ ነፍስ ባለበት ሁኔታ ወደእርሱ እየለመንን እንደቀድሞው አመራሩን እናገኛለን በሚል እውነታውን ከመቀበል ወደኋላ አላሉም፡፡ የኢያሱን መሪነት በመቀበል ለሙሴ እንደታዘዙት ለእርሱም እንደሚታዘዙ ቃል ገቡ፡፡

ጳውሎስም ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ እንደገለጸው በሕይወት በመኖርና በመሞት መካከል የቱን እንደሚመርጥ እንደተቸገረ ይናገራል፡፡  ቢሞት ወደክርስቶስ ስለሚሄድ በዚያ እጅግ ደስተኛ ነው፡፡ በሕይወት ቢኖር ደግሞ እነርሱን በማገልገል የሥራ ፍሬ ይኖረዋል፡፡ ለፊልጵስዩስ ሰዎች የሚጠቅመው ግን መሞቱ ሳይሆን በሕይወት መኖሩ ነው፡፡ እነርሱን በመጥቀሙ ደግሞ እርሱ ከጌታ ዘንድ የሚሸለምበትን መልካም ሥራ ያፈራል፡፡ “በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው። ይህንንም ተረድቼ፥ በእናንተ ዘንድ እንደ ገና ስለ መሆኔ፥ በእኔ መመካታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ይበዛ ዘንድ፥ በእምነት ታድጉና ደስ ይላችሁ ዘንድ እንድኖር ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ አውቃለሁ።” (ፊልጵስዩስ 1፡23-26)፡፡ ይህ መልእክት ግልጽ ነው፡፡ ጳውሎስ ካንቀላፋ በኋላ በጻፈላቸው ደብዳቤ አማካይነት የሚጠቅማቸው ካልሆነ በቀር እርሱም እነርሱን እነርሱም እርሱን በቀጥታ ማግኘት ስለማይችሉ ግንኙነታቸው ይቋረጣል፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ ሆይ ብለው ሊጸልዩም ሆነ አማልደን ብለው ሊለምኑት አይችሉም፡፡ እርሱም ይህን የሚሰማበት እድል የለውም፡፡

በአጸደ ነፍስ የነበረውና በስቃይ ውስጥ የሚገኘው ባለጠጋው (እንደቤተክርስቲያናችን አጠራር ነዌ) “አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ” ሲል ላቀረበው ጥያቄ አብርሃም የሰጠው ምላሽ እሺ ወይም እማልድልሃለሁ የሚል አልነበረም፡፡ በእኛና በእናንተ መካከል ገደል አለ፤ መገናኘት አንችልም የሚል ነው፡፡ ከዚያ በምድር ስላሉ ዘመዶቹም በማሰብ አልዓዛርን እንዲልክላቸው ቢለምነው በአጸደ ስጋ ላሉትማ በአጸደ ነፍስ ያለነው እኛ እንማልድላቸዋለን አላለውም፡፡ ሙሴና ነቢያት አሉላቸው እነርሱን ይስሙ ነው ያለው፡፡ ለምን ቢባል በአጸደ ነፍስ ያሉ የቅዱሳን ነፍሳት በአጸደ ስጋ ካሉት ቅዱሳን ጋር  የማይታይ መንፈሳዊ ኅብረት ቢኖራቸውም በቀጥታ የሚገናኙበት መስመር ግን የለም፡፡

በአጸደ ነፍስ ወዳሉ ቅዱሳን አማልዱን በሉ የሚለው ትምህርት ወደእግዚአብሔር ብቻ ሊቀርብ የሚገባውን ጸሎትን ወደቅዱሳን እንዲቀርብም የሚያዝ ስለሆነ የተሳሳተ ልምምድ ነው፡፡ ምንም መንፈሳዊ ልናደርገው ብናስብ እንኳን አሕዛባዊ ልማድ ነው፡፡ ግንኙነቱም ከአምልኮተ ባእድ ጋር ነው፡፡ ምክንያቱም ወዳንቀላፉ ቅዱሳን የምንጸልየውን የአማልዱኝ ጸሎት የሚቀበለው ቅዱሳኑ አይደሉም፡፡ በስማቸው የሚነግደው ሐሰተኛውና የእግዚአብሔርን ክብር ከጥንቱ ሲፈልግ ከክብሩ የወደቀው ሰይጣን ነው፡፡ ታዲያ ይህ የተሳሳተ ልምምድ እንዲስተካከልና በጸሎት መገናኘት ያለብን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ መሆን አለበት የሚለውን ማስተካከያ መቃወም ትርፉ ምንድነው? “በዓለመ ሙታን የሚገኙ ነፍሳትን መጥራት በእግዚአብሔር ቃል በእጅጉ የተወገዘ የባዕድ አምልኮ ድርጊት ነው” የሚለው እርማት በአጸደ ነፍስ የሚማልዱ ቅዱሳንን መተቸት ተደርጎስ እንዴት ተቆጠረ? ቅዱሳንን መተቸትስ ያልሆኑትን ሆናችኋል ብሎ በስማቸው ያልሆነ ነገር መናገር ነው፡፡ ስለዚህ ሊቃውንት ሆይ የተሳሳተውን ሳይሆን ትክክለኛውን ትምህርተ ቤተክርስቲያን ጠብቃችሁ በማስጠበቅ እንደስማችሁ ሁኑ አሊያ ስሙን ለሚሠሩበት መልሱ፡፡


ይቀጥላል

21 comments:

 1. ከመናፍቅ(ከመንፍስት) አፍ ድሮም ማር የሆነ የእግዝአብሔር ቃል አይወጣም ወይም አይፈልቅም የበላህበት ወጭት ሰባሪ የእናት ጡት ነካሽ እብድ ውሻ ለመናፍቅ ፍርፋሪ ለሆድህ ያደርክ የቦንኬ ርዝራዥ ንስሐ ግባ ቀኑ ሣይመሽብህ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are living in dark. Read the bible and open your heart for the word of God.

   Delete
 2. ከመናፍቅ(ከመንፍስት) አፍ ድሮም ማር የሆነ የእግዝአብሔር ቃል አይወጣም ወይም አይፈልቅም የበላህበት ወጭት ሰባሪ የእናት ጡት ነካሽ እብድ ውሻ ለመናፍቅ ፍርፋሪ ለሆድህ ያደርክ የቦንኬ ርዝራዥ ንስሐ ግባ ቀኑ ሣይመሽብህ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰጠህ/ሽ መልስ ከመጽሐፈ ቅዱሳት ተጠቅሶ እንጂ እንዳንተ/ቺ ስሜታዊ መልስኮ አይደለም። እስቲ ረጋ ብለህ/ሽ መጽሐፉን አንብብ/ቢ። ለነገሩ አንድም ቀን መጽሐፍ ቅዱስን አገላብጦ ለማያውቅ ሰው ወይም እንድያነብ ላልተፈቀደለት አማኝ ነኝ ባይ ይህንን እውነታ በቀላሉ ለማስረዳት አስቸጋሪ ይመስላል። ከማንም ክርስቲያን እንዲህ ዓይነት የድፍረት ስድብ አይጠበቅም። ለዚህ ምላስ የመንፈስ ቅዱስ ልጓም ያስፈልገዋል። እግዚአብሔር መንፈሳዊ አይኖቻችሁን ይክፈትላችሁ!

   Delete
 3. This is the real fruit of evil protestantism

  ReplyDelete
  Replies
  1. Maru Kebede, what does protestant means? If you use appropriately the word protestant for this article, I agree with you because the writer of the above article is protesting the evil and supporting the word of God.Come on Maru, unless you living by doing evil works (tenkolena, metete, muarte, debeterena), you shouldn't have to oppose this great biblical based article.
   Geta wodeweantu yametah!

   Delete
  2. Who said evil is evil,but if u
   got time to posted,why you
   don't get time to read bible ?
   it goon cured ur ignorant
   thought.u don't deserve the
   name Christian,PS open ur
   eyes,don't leave with your
   darkness,surrender your
   self to Jesus,don't collide with the truth .PS get this quote.(TRUTH is by nature self.evident as soon as you
   remove the cobwebs of ignorance that surround it,it shines clear).Mahatma Gandhi.
   (Peace if possible,truth at all costs).Martin Luther.
   (He who knows nothing is closer to the truth than,he whose mind is filled with falsehoods &errors.)

   Delete
 4. cherashunu pentenawi honachu ende???

  ReplyDelete
 5. ንስሐ ግባ ቀኑ ሣይመሽብህ

  ReplyDelete
 6. ካንቀላፉ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሌለን ወደእነርሱ መጸለይም ሆነ በአምልኮተ ባዕድ ልምምድ ውስጥ በሙታን ሳቢዎች ድግምት እንዳንነካካ የሚናገር የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው፡፡ your own explanation, i do have my own

  ReplyDelete
 7. ውድ የሰላማ ጸሀፊ፡
  በአቀራረብ ራስህን እንደመጽሀፍ ሊቅ አድርገህ አስቀምጠህ ሁሉን ትተቻለህ!!ግን በማመሳሰል(analogy)ካልሆነ በቀር አንድም በአጸደስጋ የተለዩ ቅዱሳን አያማልዱም የሚል ጥቅስ አላቀረብክም-ማቅረብም አትችልም!!!ስለዚህ በክርክሩ ራስህን የተሻለ ቦታ ላይ የምታስቀምጥበት መሰረት የለህም!!ቢሆንም ትንሽ ልበልልህ….
  (1)መጀመሪያ የሳሙኤልና የሳኦል ታሪክ በ1ኛ ነገ 28 ቁ 6እስከ19 ስላለ እሱኑ ላስቀምጠው፡
  “ሳኦልም እ/ርን ጠየቀ፣እ/ርም በህልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም. ሳኦልም ባሪያዎቹን ወደ እርስዋ ሄጄ እጠይቅ ዘንድ መናፍስትን የምትጠራ ሴት ፈልጉልኝ አላቸው….በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ….ሴቲቱም ሳኦልን አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ አለችው…..ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ አወቀ፣በፊቱም ተጎነበሰ፣በምድርም ላይ እጅ ነሳ…ሳሙኤልም አለ….እ/ር መንግስትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል ‘የእ/ርን ቃል አልሰማህምና’….እ/ርም የእስራኤልን ጭፍራ ደግሞ በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል.”
  ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው ሳኦል በእ/ር ተስፋ ቆርጡዋል፣የእ/ርን ቃል አላከበረም፣ወደቤተመቅደስ ሳይሆን በግልጽ ወደ ጠንቁዋይ ነው የሄደው፣መንግስቱም ከእጁ የወጣች ሳሙኤልን አማልደኝ በማለቱ ሳይሆን ባለመታዘዙ ነው!!እኛ ግን ቅዱሳንን አማልዱን ስንል በአምላካችን ተስፋ ቆርጠን ሳይሆን በአንድም በሌላም መንገድ መሀሪነቱን እንደሚገልጽ በማመን ነው፣የምንሄደውም ስሙ ዘወትር ወደሚጠራበት ቤተመቅደስ እንጅ ወደጠንቁዋይ ቤት አይደለም!!!እንዲያውም ከዚህ ንባብ የሳሙኤልን ስላለፈው፣ስለነበረውና ስለሚመጣው የተነገረ ቃልና የቃሉን መፈጸም ማለትም ሳኦልን ትሞታለህ ብሎት መሞቱንና መንግስቱም ሳሙኤል ከሙታን ተነስቶ ለሳኦል እንደነገረው ለዳዊት መተላለፉ የሞቱ ጻድቃን ስለእኛ ያላቸውን እውቀት የሚያሳይ ነው!!ሳኦል ከሞት ለተነሳው ሳሙኤል ያደረገው የጸጋ ስግደት አለመነቀፉም የእኛን በክብር ላረፉ ቅዱሳን የሚደረግ ስግደት ትክክለኛነት ያሳያል!!!
  እኛ ለቅዱሳን ስንሰግድ፣ውዳሴ ስናቀርብ፣ስናከብራቸው፣ፍቅራችንን ስንገልጽ፣አማልዱን ስንል ፍጡርነታቸውን ዘንግተን እነሱን በልዑል እግዚአብሄር ቦታ ተክተን አይደለም!!!ስለዚህ በምንም መልኩ ድርጊታችን ባእድ አምልኮ ሊሰኝ አይችልም!!ሲጀመር ማማለድ የአምላክነት ተግባር ስላልሆነ የእነሱ ማማለድ በምንም መንገድ የጌታን የአምላክነት ግብር እንደሚጋፋ ተደርጎ መቅረብ የለበትም!!
  (2) ስለሞቱ ጻድቃን እውቀት፡በ2ኛዜና መዋእል ምእራፍ 21ቁ12እስከ14 የይሁዳ ንጉስ ኢዮራም ብዙ ሀጢኣት በመስራቱ ከአመታት በፊት በእሳት ሰረገላ ወደ ሰማይ ተወስዶ የነበረው ነቢዩ ኤልያስ የተግሳጽና የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደላከለት ተገልጹዋል!!በኤር 15ቁ1 ላይም “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙ እንኩዋ ልቤ ወደዚህ ህዝብ አልመለስ አለ” የሚለው እነሙሴ ከሞቱ ከብዙ አመታት በሁዋላ የተነገረ ቃል, የሞቱ ጻድቃን በምድር ስላለው ህይወት እውቀት እንዳላቸውና ስለእኛ እንደሚማልዱ የሚያሳይ ነው!!!በ1ኛ ቆሮ13ቁ12 “አሁን በመስታወት እንደምናየው አይነት በድንግዝግዝ እናያለን፣በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሄር እኔን የሚያውቀኝን ያህል ሙሉ እውቀት ይኖረኛል” በማለት የሞቱ ጻድቃንን እውቀት ፍጹምነት ይገልጻል!!!ታዲያ በድንግዝግዝ ያለው ምድራዊ ሰው ያማልዳል ,በፍጹምነት ያሉት ቅዱሳን ግን አያማልዱልም የምትል አንተ ማነህ??እንዲህ አይነት ትምህርትስ በየትኛው ጉባኤ ተማርክ??የሞቱ ቅዱሳንን ቀርቶ ቅዱስ ዳዊት ፍጥረታቱን፣አህጉራቱን፣መላእክቱን ሁሉ እግዚአብሄርን አመስግኑት እያለ ያናግራቸው የለ!!አንብብ….እመሰ ረሳእኩኪ ኢየሩሳሌም ለትርስአኒ የማንየ….ስምዒ ወለትየ ወርዕይ ወአጽምኢ እዝነኪ….ሰብህዎ ለእ/ር ኩልክሙ መላእክቲሁ….ወዘተ ሲል ታገኘዋለህ!!
  (3) “ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ ይወስዳል፣ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል” ተብሎ በማቴ 10ቁ40 የሰፈረው ቃልም በጥሞና ላነበበው ከበቂ በላይ ነው!!አስተውል፡ጌታ በአጸደነፍስ ያሉና የሌሉ ብሎ አልከፈላቸውም!!!እንዲያማ ቢሆን ኖሮ ‘ጻድቁን/ነቢዩን በህይወት ባለ ጻድቅ/ነቢይ ስም የሚቀበል’ የሚል አነጋገር ይጠቀም ነበር!! እነዲያውም ጌታ ይህን ቃል ሲናገር አንድም ነቢይ በአጠገቡ አልነበረም!!ስለዚህ ቃሉን የተናገረው ስለሞቱ ነቢያትና ቅዱሳን ጭምር እንደሆነ እናምናለን!!ጻድቅን በጻድቅ ‘ስም’ የሚለው ንግግር ግልጽ ነው!!ወደ ራሱ ወደጻድቁም አማልደን ብሎ በራሱ በጻድቁ ስም መጠየቅ እንደሚቻል የሚያሳይ ነው!!

  ReplyDelete
 8. ካለፈው የቀጠለ……
  (4)የእኛን በቅዱሳን አማላጅነት ማመን ባህላዊ ነው ብለሀል….ትክክል!!ግን ይህ ባህል የቢሊዮን ክርስቲያኖች ባህል መሆኑን ስነግርህ በኩራት ነው!!መ/ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ባህል መሆኑን ስገልጽልህም ከላይ ባስቀመጥኩዋቸው ጥቅሶች እንዳልኩት አንገቴን በኦርቶዶክሳዊ ትምክህት ቀና አድርጌ ነው!!ማተቤ እስኪታይ!!!የኛ ሃይማኖት በመጽሀፍ ባለው ብቻ ሳይሆን በትውፊትም ጭምር እንደምትታገዝ በአደባባይ እንናገራለን!!ታለቁ መጽሀፍም በ2ኛተሰሎንቄ ም.2ቁ15 “በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ‘ወግ’ ያዙ” በማለት መንፈሳዊ ወግና ባህልም እንዳለ ይገልጻል!!3ኛዮሐ ም.1ቁ13’ንም አንብበው….. አፍ ለአፍ በመነጋገርም…. መንፈሳዊ ትውፊቶች ወደትውልድ እንደሚተላለፉ ይነግርሀል!!ስለዚህ በአማላጅነት በማመናችን ብትነቅፈን አንሸማቀቅም-ይበልጥ ሰአሉ ለነ ጻድቃን እንላለን እንጅ!!
  ክርስቶስ ራሱም በሉቃስ 2 እንደተጻፈው፡በ8ኛው ቀን መገረዙ፣በ40ኛው ቀን ወደ ቤተመቀደስ መወሰዱ፣በ12 አመቱ ለፋሲካ በዐል መውጣቱ ለመንፈሳዊ ባህል ቅድስና መስጠቱን የሚያሳይ ነው!!ጳውሎስ ስለት ስለነበረበት ራሱን ስለመላጨቱ የተገለጸበት የሐዋ.ስራ 18ቁ18 ሐዋርያትም ቢሆኑ በመንፈሳዊ ባህል ውስጥ ይመላለሱ እንደነበር ያረጋግጣል!!
  እናንተ ‘የምን ባህል ቃሉን ብቻ’ የሚል የፈረንጅ አመለካከት በመያዛችሁ በሐዋርያው ጳውሎስ ተከናንበው ይምጡ የተባሉት ሴቶች ‘የሀበሻ ቀሚስና ነጠላ ለኦርቶዶክስ ነው’ ብለው በሚኒ ሲያስረግጡ፣ በታይት ሲያሸበሽቡ እያያችሁ በሃይማኖት ስም የባህል ወረራ መካሄዱን አታስተውሉም፣እንደራፐር መሀረብ ይዘው የሚጮሁ ፓስተሮች እህቶች ለምን ረጅም ቀሚስ ለበሱ እያሉ ጭራሽ ያሳቅቁዋቸዋል ያስቁባቸዋል፣በራእይ የተገለጸልኝ ነው እየተባለ …ምናለ ጌታ ምናለ…..ኢየሱስ አንደኛ….ጀግናው ኢየሱስ… የሚል በመጽሀፍ የሌለ ቃል ተይዞ ዳንኪራ ይመታል፣ፍጹም ከመጽሀፍ ጋር የማይገናኝ በባህላችንም በቃልቻ ቤት ካልሆነ የማይገኝ ልሳን የሚባል ነገር አምጥታችሁ አረፋ ስትደፍቁ ትውላላችሁ፣ይሄ ሁሉ መንፈሳዊ ባህልን እያጣጣለ ነገር ግን ራሱም የራሱን ጥሎ ከአውሮፓ በመጣ አጉል ባህል ከታወረ ትውልድ የሚጠበቅ ነው!!እኛ ግን እንዲህ እንዳሁኑ የህትመት ቴክኖሎጅ ባልነበረበት እና የብራናውን መ/ቅዱስ ለሁሉ ማዳረስ ባልተቻለበት ወቅት ሃይማኖታችንን ተሸክሞ ለኖረው መንፈሳዊ ባህላችን ያለን ክብር የነበረ፣ያለ፣የሚኖር ነው!!አላየህም፡ መሀይምናኑ እናቶቻችን በደብረታቦር፣በደብረዘይት ነዳያንን እየዘከሩ ጌታን ሲያስቡት፣የእግዜር እንግዳ ሲቀበሉ፣ሲጾሙ፣ህማማት ብለው የጌታን ስቃይ ሲያስቡ!!ይህ ድርጊታቸው የወንጌል ትርጉዋሜ ነው!!እንዳንተ ወንጌሉን አያወሩት ይሆናል ግን ይኖሩታል!! ቤተክርስቲያናችን ክርስትናውን ከባህሉ ጋር ገምዳዋለች-እንዳይበጠስ አድርጋ!!!ለዚህም ነው እኛ በካሌንደራችን መሰረት የጌታን 18 በዐላት ስናከብር እናንተ ግን ‘እኛ ሁሌ ስለምናከብረው ቀን አንወስንም’ ስትሉ ትቆዩና ለልደት እና ለትንሳኤ ‘በአሉን ስናከብር…..’ እያላችሁ የምታስገርሙን!!በዐል ማክበር መንፈሳዊ ባህል መሆኑ ስለተሰወረባችሁ!!
  (5) በቤተክርስቲያናችን ከ2ሺህ አመታት በላይ የዘለቀውን የአማላጅነት አስተምህሮ ትናንት የተፈጠረ የ20 አመት ማህበር ያመጣው አስመስሎ ለማቅረብ የምታደርጉት ሙከራም አልገባኝም!!በማህበረቅዱሳን ላይ ብዙ ቅሬታዎች አሉኝ!!ግን የቅሬታየ መሰረት ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎችን ያጣምማል የሚል አይደለም!!በዚህ ረገድ እንደውም የማህበሩ ደጋፊ ነኝ!!የኔ ቅሬታ ሌላ ነው!! እሱን በሌላ ጊዜ በማህበሩ በራሱ ህቡእ ልሳናት ብቻ ነው የምገልጸው!!!በዚህ እናንተ ባቀረባችሁት ውግዘት ላይ ለሊቃውንት ጉባኤ እርድታ አድርጎ ከሆነ ግን ሊደረግ የሚገባውን አደረገ እላለሁ!!!

  ReplyDelete
 9. (4)የእኛን በቅዱሳን አማላጅነት ማመን ባህላዊ ነው ብለሀል….ትክክል!!ግን ይህ ባህል የቢሊዮን ክርስቲያኖች ባህል መሆኑን ስነግርህ በኩራት ነው!! I only read this sentence out of your non sense and non-substance tert tert. Let me ask you do you know that Islam also የቢሊዮን followers? Worshiping through Jesus to the Father, Son and Holy Spirit the only way to take us to the kingdom. Please! Read the bible or click to the following link: http://www.tinyvod.com/v/ZAJCTofMbIU

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያላነበብከው ጽሁፍ ተረት ተረት ይሁን ወይም ቁምነገር እንዴት እንዳወክ አልገባኝም!!ምናልባት ለእናንተ ጌታ ቅርብ ስለሆነ በራእይ ገልጾልህ ይሆናል ብየ ልገምት!!ያው ተስፋየ ገ/አብ በመጽሀፉ ከገጽ 348 እስከ 357 እንዳለው ጌታን አውርዳችሁ አውርዳችሁ የትንሽ የትልቁ ድርጊት ሁሉ ተላላኪ አድርጋችሁት የለ!!
   ስለባህል ያነሳሁልህ ግን እናንተ የእኛ የሆነው ሁሉ ድንበር ማይሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ ልማድ እድርጋችሁ ስለምትመለከቱትና በአዘጋጁን ጽሁፉም ተመሳሳይ ስሜት ስለተንጸባረቀ የአማላጅነት አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ ድንበር ተሻጋሪ ሀሳብ መሆኑን ለመግለጽ ያህል ነው!!በዚያውም ስለአማላጅነት አስተምህሮ በኢንተርኔት ላይ እንኩዋ እንደማይገኝ በመለፈፍ እንደእነ ፓስተር ዳዊት ተካልኝ አይነቶቹ ጌታን በማወደስ ከሚያጠፉት ጊዜ ይልቅ ኦርቶዶክስን የሚያጣጥሉበት ጊዜ ለሚበልጥ ፍሬሽ አማንያን የፕሮቴስታንቲዝም አስተምህሮ ያን ያህል universal truth ወደሚባል ደረጃ እንዳልደረሰ ለማሳየት ያህል ነው!!እንጅ ቁጥር የትክክለኛነት መለኪያ ሊሆን እንደማይችል አልጠፋኝም!!
   የአብ ወልድ መንፈስቅዱስ ስም በፕሮቴስታንቶች ሲጠራ ስለማልሰማና ይህ ስም የኦርቶዶክስ ሁዋላቀርነት ተደርጎ የሚቀርብበትን አስተያየት በመስበር Worshiping through Jesus to the Father, Son and the Holy Spirit ስትል ማየቴ ደስ ብሎኛል!!ግን አንተ through Jesus ስትልና እኔ through Jesus ስል ይለያያል!!አንድ አይደለም!!!ይቺ ይቺ ወስዳ ስለ ስላሴ አንድነትና ሶስትነት(ምስጢረ ሥላሴ) እንዲሁም ስለ ጌታ ሰው የመሆን ምስጢር(ምስጢረ ስጋዌ) ጨምራን ሰፊ ርእስ ስለምትፈጥርና በዚህ ጉዳይ የእናንተን አቁዋም ስለማላውቅ ምንም ማለት አልችልም!!
   ቁም ነገሩን ሁሉ ተረት ከማድረግ አባዜ እንድትወጣ ግን ያንተ ጸሎት የሚሰምር ስላልመሰለኝ ስላንተ ሊጸለይልህ ይገባል!!ይግለጽልህ!!


   Delete
 10. Why the hell do you need a mediator in the first place? What is the purpose of calling any Tsadik or Nebiy while Jesus is standing at the door and knocking? He is asking us to pray to His father in His name. Be enatachihu yihin chigir yametachihut lemin endehone asredugn. I see the discussion as pointless. Above all, why are you so angry at something that should not be your concern. If you are a Christian and know that God gave you His only son, why should you refer to saints and angels to ask for something reeeealllllly small as compared to the blood of Jesus? Yalbelachihun makek yimeslegnal, neger filega.

  ReplyDelete
  Replies
  1. በዘፍ 20 ቁ 7 አቤሜሌክን “አብርሃም ይጸልይልህ”፣በኢዮ 42 ቁ 8 የኢዮብን ባለንጀሮች “ኢዮብ ይጸልይላችሁ” ተባሉ-ስለበደላቸው፣በሐዋ.ስራ 8 ቁ 14 ሲሞን እነ ፔትሮስን ወደ ጌታ ለምኑልኝ ይላል፣በት.ዘካ 1 ቁ 12 የእግዚአብሄር መልአክ ስለኢየሩሳሌም ይቅርታ ለመነ፣በዘፍ 25 ቁ 21 ይስሀቅ ስለሚስቱ ርብቃ ጸለየ፣በማቴ 15 ቁ 23 ሐዋርያት ልጁዋን ጋኔን ስለያዘው እናት ጌታን ለመኑት…..ወዘተ፣
   እነዚህ ሁሉ ልመናዎች አንዱ ስላንዱ ያደረጋቸውና እ/ር የምህረት መልስ የሰጠባቸው ናቸው.ስለዚህ አልተሳሳትንም!!! እኛም እኮ ቀጥታ ወደ ኢየሱስ እንጸልያልን-እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ-አቤቱ ማረን እያልን!!!አያይዘንም በእንተማርያም መሀረነ ክርስቶስ-ስለማርያም ብለህ ማረን እንላለን ጌታ ለወዳጆቹ የገባውን ኪዳን እንደሚጠብቅ ስለምናምን!!ሁለቱንም እንጠቀማለን!!ኢየሱስ ሲጀመር ተማለጅ እንጅ አማላጅ ስላልሆነ አድርግልን እንጅ አማልደን ብለን አንጠይቀውም!!
   ‘ወደጌታ ብቻ የምን አንዱ ላንዱ መጸለይ ነው’ በማለት እኛን የምትነቅፉ በቅድሚያ ከላይ የሰፈሩትን ጥቅሶች ስለመቀበል አለመቀበላችሁ ሳትገልጹ ዝምብለን ባንጩዋጩዋህ ደስ ይለኛል!! በተለይ “ስለ” የሚለውን ውክልና አመልካች ቃል እንዴት እንደምትረዱት ባውቅ!!

   Delete
 11. Haile

  I am just wondering which angel told you that protestantism is the right way to Heaven. In the first place how did you believe the fictional stories of gangsters Bonkie and Luther? The world knows that evil protestantism was invented 1500 years after CChristianity. So if you have the working mind, how did you convince yourself that evil protestantism is true?

  ReplyDelete
 12. Hiruy! God Bless you!!!.It is really great to read and learn a lot from your posts.May God bless you more and more.

  ReplyDelete
 13. ክፍል1
  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የወላዲት አምላክን ንግስተ ሰማይ ወምድር (ወላዲት አምላክነትን) ተቀብላ የምታምን የምትሰብክ ሃይማኖት ናት፡፡ ወላዲተ አምላክ መትሕተ ፈጣሪ መልእልተ ሁሉ ፍጡራን ናት፡፡ (ከፈጣሪ በታች ከፍጥረታት ሁሉ በላይ ናት፡፡) ይህን ማእረግ እንድታገኝ ያስቻላት እሳትን የተሸከመች፣ የአብ ማደርያ የነበረች፣ የወልድ ቤት የነበረች የመንፈስ ቅዱስ ማረፍያ የሆነች ስለነበረች ፤ ሁለተኛም ደግሞ እግዚያብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከስጋዋ ከፍሎ የተዋሃዳት ስለሆነ፣ 9 ወር ከ 5 ቀን በማህጸኗ የኖረ ስለሆነ ( ይህ ደግሞ በጣም ድንቅ ነገር ነው፡፡ እራሷ እናቱ ወላዲት አምላክ በክርሰቶስ መኃል እጅ ነበረች፡፡ ምክንያቱም ይህ አለም በክርስቶስ መሃል እጅ የተያዘ መሆኑ የታወቀ ነገር ነው፡፡ በመሃል እጁ በምትገኝ በእናቱ በወላዲት አምላክ እጅ ተጸንሶ መገኘት ደግሞ በጣም አስደናቂ ምስጢር ነው፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም በስተቀር ይሕ እድል የገጠመው የለም፡፡ ለሷ ብቻ ነው ይህ እድል የተደረገው፡፡ ክርስቶስ እና እናቱ ቅድስት ማርያም የሚያውቁት ብዙ ምስጢር አለ፡፡ በእናቱ ልብ ውስጥ የተቀመጠ የክርሰቶስ የግርማዊነቱና የጌትነቱ ብዙ ምስጢር አለ፡፡ በሷ ስጋ በሷ ደም የተመላለሰ እራሱ መለኮት ነው፡፡ እራሱ ባለቤቱ ልኡል እግዚያብሔር ማለት ነው፡፡
  ስለማንነቷም ቢሆን ነብያትም የተናገሩት ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ያበሰረው ነው፡፡ አዳም ራሱ ተስፋ ሲያደርገው የነበረ ነገር ነው፡፡ እራሷም ቅስት ድንግል ማርያም የተናገረችው ነው፡፡ ቅድስት ኤልሳ ቤትም የመሰከረችው ነው ፡፡ በኋላም ደግሞ ቅዱስ ደቅስዮስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የጻፈው ምስክር ነው፡፡ የቅድስት ማርያም መልክ ያምላክን መልክ ይመስላል ሃሳቧም እንደ አምላክ ሃሳብ ነው፡፡ አለም ሳይፈጠር በአብ ልቡና ታስባ የነበረች ናት፡፡ አዳም ፣ ይህ አለም (ሰማይ ከነከዋክብቱ ጸሃይ ጨረቃው፣ ምድርም ደግሞ ከነሰው ከነእንስሳት አራዊቱ ፣ ከነእጽዋት አዝርእቱ፣ ከነአሳ እንብሪ አሳይቱ፣ በባህር ውስጥ ካሉት ተርመስማሽ ተንቀሳቃሽ፣ ከማንኛውም ስነፍጥረት ጋራ እንዳለ ስለ እመቤታችን ክብር ተፈጠሩ ብሎ ቅዱስ ደቅስዮስ የጻፈው ነው፡፡ ስለዚህ እኛም ሰዎች አስቀድመን ስለ እመቤታችን ክብር ከተፈጠርን ታማልዳለች አታማልድም የሚለው ሰነፍ ክርክር በሙሉ የተረታና የተመታ ነገር ነው፡፡ እኛ ራሳችን አስቀድመን የተፈጠርነው ስለሷ ክብር ከሆነ፤ እሷን ለማክበር የሷን ክብር ለማስፋት ለማግነን ከሆነ፤ በሰማይና በምድር በምህረት የሰለጠነ ስሟን ከፍ ከፍ ለማድረግ ከተፈጠርን ታማልዳለች አታማልድም የሚለውን ነገር ልናነሳው የማይገባን ነገር ነው፡፡ በመሰረቱ መነሻችን እራሱ አፈጣጠራችን ስለሷ ክብር መሆኑን ከታወቀ ታማልዳለች አታማልድም የሚለው ነገር ከቁጥር የማይገባ ውድቅ ሃሳብ ነው፡፡ ስለዚህም ወላዲተ አምላክ መትሕተ ፈጣሪ መልእልተ ሁሉ ፍጡራን ናት፡፡ (ከፈጣሪ በታች ከፍጥረታት ሁሉ በላይ ናት፡፡)
  ስለዚህ ወላዲት አምላክ ከመላእክትም ከቁዱሳንም ይልቅ ንጽህይት ሆና በመገኘትዋ ምክንያት የአምላክ እናት የመሆን እድል ገጥሟታል፡፡ የማይደገም እድል ነው፡፡ ክርስቶስ ዳግመኛ ሊወለድ፣ ግንድ ሊሸከምና ጨርቅ ሊያገለድም አይመጣም፡፡ አንዴ ተወለደ፣ አንዴም ጨርቅ አገለደመ፣ አንዴም ግንድ ተሸከመ፣ መከራን ተቀበለ፣ ስጋውን ቆረሰ፣ ደሙን አፈሰሰ፣ ለባህሪው ካሳ አለሙን አዳነ፡፡
  አለሙ የዳነበት ስጋና ደም ከእመቤታችን የተዋሃደው ስጋና ደም ነው፡፡ ከሰማይ ያመጣው ስጋና ደም አይደለም፡፡ ከመላእክትም የተዋሰው ባህሪ አይደለም፡፡ ከእመቤታችን የነሳው ነብስ፣ ስጋና ደም ነው፡፡ በነብሱም ወርዶ ሲኦልን መዘበረ፡፡ ቀኙን ዘረጋላቸው፡፡ ጥምቀትም፣ ፀጋም፣ ረድኤትም ሁሉም ነገር ሆኖላቸው ወደ ገነት ገቡ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ በመወለዱ ነው፡፡ ከዚያ በፊት 5500 አመት አዳምና ልጆቹ ጠብቀዋል፡፡ ምንም ያገኙት ረብ ጥቅም የለም፡፡ ነብያትም ቢነሱ የእየሱስ ክርስቶስን ሃልሆቱን ተናገሩ መሰከሩ ነገር ግን ከመቃብር በኋላ ወደ ሲኦል ከመውረድና ከመቀሰፍ ማንንም አላዳኑም፡፡ በግዜው በዘመኑ እልፍ ተረፍ ያለውን ሰው ምድር እየተከፈተች ትውጠው ነበር፡፡ እሳትም እየፈላ ያጠፋው ነበር፡፡ ንፍር ውሃም ይቀቅለው ነበር፡፡ የሰው ልጅ በጣም ብዙ መከራ ነበረበት፡፡ እየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ተዋህዶ ሰው ከሆነ ወዲህ ከሷ ከተዛመደን በኋላ ይህ ሁሉ መከራ ቀርቶልናል፡፡ ስለዚህ የቅድስት ድንግል ማርያም ውለታዋ ከማማለድ በላይ ነው፡፡ እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶያውያን የማከናወን ስልጣን አላት ነው የምንለው፡፡ የምናምነውም፣ የምናስተምረውም፣ የምንመሰክረውም ማንኛውም ክንውን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር የተነሳ እንደሚከናወን ነው፡፡ ስሟም በሰማይ እና በምድር በምህረት የሰለጠነ እንደመሆኑ በመአትም የሰለጠነ ነው፡፡ ራሱ የተሸከመችው ስም ኪዳነ ምህረት ማለት መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ መንግስተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው፡፡ ስሟ በራሱ ሃይል ያለበት ስልጣንን የተላበሰ ስም ነው ፡፡ የግርማዊነቱ የክርሰቶስ ጌትነት አብሯት ያለች ንግስት ናት፡ ታማልዳለች አታማልድም የሚለው ክርክር ምንም ቁም ነገር የሌለውና ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ሚገባው ነገር አይደለም፡፡
  እድሜውን ሁሉ መናፍቅ ሃጥያት እየሰራ አጋንትን በጣለው ትእቢትና ቅናት ተወጥሮ በክርስቶስ የባህሪ አምላክነትና በወላዲት አምላክ የማከናወንና የማማለድ ስልጣን ብሎም በመላእክት፣ በሰማእታትና በቅዱሳናት አማላጅነት እና የጸጋ አምላክነት እየተዘባበተ ሃጥያት አይስራ፡፡ በቁሙ ስጋውን አድልቦ ነብሱን ግን መጻተኛ አድርጎ አይቁም፡፡

  ReplyDelete
 14. ክፍል 2
  ወንጌልም የሚለው እንከ መጨረሻይቱ ህቅታ የጸና ይድናል ነው የሚለው፡፡ ትእግስቱን ያጸና ሰው የታገሰ ሰው ይድናል ነው የሚለው፡፡ እንጂ የወላወለ ና የጀመረ ሰው ይድናል አይልም፡፡ ደሞ በዚ ላይ አባቶቻችን ሐዋርያት አውግዘዋል እኛ የሃይማኖት ለዋጮችን ነገራቸውን እንጸየፋለን ፈጽመን እንጠላለን ብለዋል፡፡ ስለዚህ የሰማይ ነገስታት የሆኑ፣ በአስራ ሁለቱ ነገድ ላይ ፣ በሰው ፍጥረት ሁሉ ላይ ለመፍረድ የተሰናበቱ ሐዋርያት የነብስ ነገስታት ያወገዙትን ውግዘት የተናገሩትን ነገር ሽሮ እንደፈለጉ ሆኖ መቅበዝበዝ የሚያዋጣ አይደለም፡፡
  የሃይማኖት ስርአት አንዲት ናት፡፡ እግዚአብሔር አንድ ነው፡፡ በሰማይና በምድር አንዲት ስርአት አለች፡፡ አንድ አምላክ አለ፡፡ አንዲት አምልኮት ናት ያለችው፡፡ ሰላሳ አይነት ነገር ማቀንቀን ተገቢ አይደለም፡፡ ሰው እንደፈለገው ሰው እንደሚስማማው መሆን የለበትም፡፡ አንድ ግዜ የተሰራው ስራ ጸንቶ ለዘላለም ነው የሚኖረው፡፡ እግዚአብሔር አይለወጥም፡፡ እና ከአባቶቻችን ስርአት ከቀደመው ልማድ ከቀደመው ትምህርት ወደቀኝ ና ወደግራ መባል የለበትም፡፡ አስተውሉ፡፡
  እመቤታችን እራሷ በእግዚአብሔር ቀኝ የምትገኝ ናት፡፡ በልጇ ቀኝ ያለች ናት፡፡ ካላይ እንደገለጽኩት የምታከናውን ናት፡፡ መናፍቆች ደግሞ እራሱ እየሱስ ክርስቶስ በምድር ሳለ ለሰው ልጆች ያማልድ ነበር ይላሉ፡፡ ይህ በፍጹም ሃሰት ነው፡፡ እውነታው ግን ወንጌሉ ግን የሚለው ከሀጥያት በስተቀር ሰው የሚሰራውን እየሰራ ኖረ ነው የተባለው እንጂ አማላጅ ነበር አይልም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የጻፈው እግዚአብሔር ሳለ እራሱን እንደ እግዚአብሔር መቁጠር አልፈለገም ነው ያለው፡፡ የመጨረሻ ትሁት ሆነ ነው የሚለው ቅዱሱ መጽሃፍ፡፡ ከእየሱስ ክርስቶስ አፍ ሰላማዊነት የተነሳ የሚጤስ የጧፍ ዝንጣፊ ቦግ ብሎ ድርግም አላለበትም፡፡ ከእግሩም ሰላማዊነት የተነሳ አስኳሉ የወጣለት የእንቁላል ቅርፊት አልደቀቀበትም ብለው ነው አባቶቻችን ሐዋርያት ያስተማሩን፡፡ ነገር ግን ሁሉም የእየሱስ ክርስቶስን የባህሪ አምላክነት በጎላ በተረዳ አስተምረውናል፡፡
  እኔና አብ አንድ ነን እያለ፡፡ እኔን ያየ አብን አየ እያለ ፡፡ እራሱ እየሱስ ክርስቶስ እየመሰከረ፡፡ የተረገመው ትውልድ ግን እንደገና አማላች ነበረ በኋላ ብዙ ጨዋታ አለ የሚሉ የሚያስተምሩ መናፍቆች አሉ፡፡ ያመሙ የጠመጠሙ፡፡ ይሄ ከተዋህዶ ትምህርት ውጪ ነው፡፡ ቃል ስጋ ሆነ የባህሪ አምላክ ነው ብለው አባቶቻችን ሐዋርያት ካስተማሩን ከወንጌል ትምህረት ውጪ ነው፡፡ እርሱ እራሱ እየሱስ ክርስቶስ ከነገረን ትምህርት ውጪ ነው፡፡ የተወገዘ ትምህርት የተረገመ ትምህርት ነው፡፡ እየሱስ ክርስቶስ ሰውም ቢሆን የባህሪ አምላክ ነው፡፡ ሰው የሆነ አምላክ ነው ብለን ነው ተዋህዶ ኦርቶዶክሳውያን የምንመሰክረው፡፡
  የእመቤታችንም ነገር ደግሞ ከላይ እንደገለጽኩት ነው፡፡ እጅግ በጣም የከበረች ናት፡፡ በልማድ ከሚሰማውና ከሚታወቀው በላይ እጅግ የከበረች ናት፡፡ ሰማውያውያን ሃያላን ምድራውያንም በሙሉ ሊወዳደሯት አይችሉም፡፡ በሁሉ ላይ እስከምጽአት ከዛም በኋላ ለዘላለም የሰለጠነች ናት፡፡ በሰማይም የተለየ ማእረግ ያላት ናት፡፡ በምድርም የተለየ ማእረግ ያላት ናት፡፡ የቅዱሳን እናቶች ቅዱሳንን ነው የወለዱት፡፡ ስሷ እኮ የቅዱሳን ህልውናቸው ሆነውን ፈጣሪአቸውን እኮ ነው የወለደችው፡፡ እየሱስ ክርስቶስን ነው የወለደችው፡፡ ከስጋዋ ስጋ፣ ከጥፍሯ ጥፍር፣ ከጸጉሯ ጸጉር፣ ከአጽሟ አጽም፣ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ እንደኛው ሰው የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሌላ አይደለም፡፡
  እየሱስ ክርስቶስ እንግዳ ፈጣሪ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከሷ ከናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰውም ቢሆንም እየሱስ ክርስቶስ የባህሪ አምላክ ነው፡፡ ይለመናል እንጂ አይለምንም፡፡ ይማለዳል እንጂ አይማልድም፡፡ አይማልድም፡፡ በጌቴ ሰማኒም ለሰው አርአያ ለመሆን "አባት ሆይ ቢቻልህ ይህች ጽዋ ከኔ ትለፍ ባይቻልህ ያንተ ፈቃድ ትድረስ፡፡ ያንተ ፈቃድ የኔ ፈቃድ ነው፡፡ የኔ ፈቃድ ያንተ ፈቃድ ነው፡፡" ያለው፡፡ ባባቱ ፈቃድ፣ በሱም ፈቃድ በባህሪ ህይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ስጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ ለባህሪው ካሰ አለሙን አዳነ፡፡ በቃ፡፡ የባህሪ አምላክ ነው፡፡
  ክርስቶስ የባህሪ አምላክ ባህይሆን እንዴት ሊኮን ነበር፡፡ መናፍቅ ሁሉ አስተውል፡፡ ስጋውስ እንዴት ያድናል ደሙስ እንዴት ህይወት ይሆናል፡፡ ስጋው ና ደሙ ህይወት የሆነን እየሱስ ክርስቶስ የባህሪ አምላክ ስለሆነ ነው፡፡ ይህን የሚቃወሙና የእየሱስ ክርስቶስን የባህሪ አምላክነት የሚክዱ ከተረገሙት ወገን ናቸው፡፡
  ስለ እመቤታን ቅድስት ድንግል ማርያምም ቢሆን ለክብሯ የተፈጠርን ነን፡፡ ለክብሯ ከተፈጠርን ከሆንን ደግሞ ጸጥ ለጥ ብለን መገዛት ነው፡፡ ይህን የተዋህዶ ኦርቶዶክስን ነገር የሚያነብ ስጋም ነብስም ይህን ነገር ያስተውል፡፡ ቀልድ እንዳይመስለው፡፡ ሃይማኖት ማለት ተረት ማለት አይደለም፡፡
  እየሱስ ክርስቶስ በመልካችን እንደ አምሳላችን እንፍጠር ብሎ በመልክ የሸለምን በአካል ያቆመን አይደለም እንዴ፡፡ የራሱን ውበቱን የራሱን መልኩን አይደለ የሰጠን እና የሸለመን፡፡ ቆመን የምንሄደው በ እየሱስ ክርስቶስ ህልውና አይለም እንዴ፡፡
  አትወላውል፡፡ የፈጣሪን አንድነቱን እና ሶስትነቱን አምነህ በስላሴ ቸረነት፡፡ የእናቱንም የእመቤታን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲት አምላክነት አምነህ ምክንያቱም እየሱስ ክርስቶስ በመለኮት የአብ ልጅ በስጋ የእመቤታን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ስለሆነ፡፡ የታላቅ እህታችን የእመቤታን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ማለት ነው፡፡ እርሱም እየሱስ ክርስቶስ እኮ በስጋው ታላቅ ወንድማችን ማለት እኮ ነው፡፡ ከእመቤታን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ተዘመደን እኮ፡፡ አስራ ሁለቱን ሐዋርያት ወንድሞቼ አለ፡፡ እየሱስ ክርስቶስ ወንድሞቼ ማለትን አላፈረም፡፡ አቀረባቸው፡፡ በጸጋ የእግዚያብሔር ልጆች አደረጋቸው፡፡ በእየሱስ ክርስቶስ ስለሚያምኑ የእግዚያብሔር ልጆች የመባል ስልጣን ሰጣቸው፡፡ የመሆንም ስልጣን በጸጋ ተሰጣቸው፡፡ አማልክት በ በጸጋ ተባሉ፡፡ አባቶቻችን ሐዋርያት በየቦታው ሲያስተምሩና ሙታንን ሲያስነሱ ብዙ ድንቅ ሲሰሩ አምላክ ሰው መስሎ መቷል የተባሉበት ቦታ አለ፡፡ ዛሬም ብትሆን ያች የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አለች፡፡ በምድር ላይ ተዘርግታ እያከናወነች ናት፡፡ እሳታዊት ናት፡፡ እግዚያብሔር የሚባላ እሳት እንደሆነ ክህነትም የምትባላ እሳት ናት፡፡
  የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ነገር ሳትረዱ ምላሳችሁ ቀደም ቀደም ብሎ ዘብቶ የማያባራ እሳት እንዳይበላችሁ፡፡
  አሜን፡፡

  ReplyDelete