Thursday, January 2, 2014

ሰበር ዜና፦ የማቅ የለውጥ መዋቅር በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች ትግል ተቀለበሰ፤

አባ እስጢፋኖስ እስከ ልደት ከሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስነት እንዲወርዱ ተጠየቀ

ማኅበረ ቅዱሳን ያረቀቀውና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ባለ በሌለ ኀይሉ ሲንቀሳቀስበት የቆየው የለውጥ መዋቅር በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች የተደራጀ ትግል መቀልበሱ ተሰማ፡፡ በዛሬው ዕለት (23/4/2006ዓ.ም) ፓትርያርኩና ስምንት ያህል ጳጳሳት በተገኙበት ወደ 300 የሚጠጉ የደብር አስተዳዳሪዎችና ልዩ ልዩ አገልጋዮች ቀርበው ቀደም ሲል ያቀረቡት አቤቱታተቸው የት እንደደረሰ በጠየቁበት ስብሰባ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንደገለጹት፣ ማኅበረ ቅዱሳን ያረቀቀው የለውጥ መዋቅር ውድቅ እንዲደረግና የማኅበሩ አባላት ቀርቶ ከማኅበሩ ጋር ምንም ንክኪ የሌላቸው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ አባቶችና ምሁራን በድምሩ 9 አባላቱ ያሉበት ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ ተሠይሟል ብለዋል፡፡ አክለውም ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብቻ ሳይሆን ለቤተክርስቲያኗ በአጠቃላይ የሚሠራ ህግ ነው መውጣት ያለበት ብለዋል፡፡ ለተሠየሙት አባላትም ከጠቅላይ ቤተክህነት ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡


ተደራጅተው የማቅን ሤራ ለማክሸፍ የተሰለፉት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች የጥያቄያቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ምላሽ በማግኘቱ መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ማቅ በቤተክርስቲያን ላይ የሸረበውን ሴራ ሁሉ በስፋት አጋልጠዋል፡፡ ለቅዱስ ፓትርያርኩንና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባቀረቡት ጥያቄም የማቅ ገንዘብና ንብረት በጥቅምቱ ሲኖዶስ በተወሰነው መሠረት በቤተክህነት በኩል ቁጥጥር እንዲደረግበትና ወደሕጋዊ አሠራር እንዲገባ የጠየቁ ሲሆን፣ ሲኖዶሱ ይህን ማድረግ ካልቻለ የሚመለከተውን የመንግስት አካል እንደሚጠይቁና ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡ እነዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች የቤተክርስቲያን አሠራር እንዲሻሻልና ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ እንጂ የማይቃወሙ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን በሕግ የማይገዛው ማኅበረ ቅዱሳን ሕግ ላውጣላችሁ ማለቱ ግን ለጥቅሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንዳይደለ ብዙ ማስረጃዎችን በማቅረብ አስረድተዋል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የደብር አለቆቹና ሌሎቹም አገልጋዮች የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ተብለው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የተቀመጡትና በተግባር ግን የማኅበረ ቅዱሳን ረዳት የሆኑት አባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዲነሡላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፓትርያርክ ማትያስም ቅድሚያ የሚሰጡት ለቤተክርስቲያን እንጂ ለግለሰብ አለመሆኑን ጠቅሰው መስተካከል ያለበትን ሁሉ ለማስተካከል እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ የዜናውን ዝርዝር እንደደረሰን በስፋት እናቀርባለን፡፡    12 comments:

 1. ውይ የዜናው ዝርዝር አልደረሰህም? ይሄን በምርቃና ነው የፃፍከው ታዲያ?

  ReplyDelete
 2. Mk will be find cobblestone jobs. No more easy money to steal from church.

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሔር ይመስገን አ/አ ሀገረ ስብከትን ከተረገመው የማቅ ዕቅድ ነፃ ያወጣልን። ጎበዝ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ማቅን ልክ ለማስገባት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የአ/አ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሰ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃን ሥራ አስኪያጅ ሳናደርግ መቆም የለም በእጃችን የገባውን የመንግሥት ድጋፍ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል

  ReplyDelete
 4. Thank you Aba selama for your great and blessed info. Truth never never die, maybe it takes time to be reveal.....fight for truth God be with day and night to help you.......Holy bible said on .Exodus 14:14 God will fight for you, yes yes yes. !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. አይ አባ ሰላማዎች ብላችሁ ብላችሁ ወደ ቤ/ያን ከሚዘርፉ ሙሰኞች ጋር ተሰለፋችሁ በጣም ------------ ብዕፁ አቡነ እስጢፋኖስ የቤ/ያን የልማት አርበኛ ለምዕመኑ የሚያስቡ መሆናቸውን ሁሉም ህዝብ ስለሚያውቅ በስርቆት በተሰማራ እንደ እናንተ ባሉ መናፍቆች ስራው አይደናቀፍም -----

  ReplyDelete
 6. አቤት ምኞት!

  ReplyDelete
 7. እንኳን ደስ አላችሁ
  ማህበረ ቅዱሳንን ማፍረስ ቀጣይ ስራችን ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. እናንተ በቤ/ያን ስር እያጭበረበራችሁ መኖር ስላልቻላችሁ ብዙ ብታወሩም አሁን መሽቶባችኋል ----

  ReplyDelete
 9. This the work of Satan and his Children. Let us fight with fasting and prayer!

  ReplyDelete
 10. ኣንድ ቤት ውስጥ ኣይጦችና ድመቶች ኣሉ፥፥ ድመቶቹ ቤቱ እንዲጸዳ ይተጋሉ፥፥ ኣይጦቹ ግን ቤቱ እንዳይጸዳ ሌት ተቀን ይሽለኮለካሉ፥ ድመትም ኣርፋ አንድትቀመጥ ኣለበለዚያ፤ ኣንበሳ ወዳጃችን ነው አያሉ ያስፈራራሉ፤፤

  ኣይጦች ቤቱ ቆሽሾ ለእንግዳም ሆነ ለቤቱ ኣባል ቢያጸይፍ ግድ የለቸውም፥ ምክንያቱም እዚህም እዚያም የሚረቃቅሙት እና የሚለክፉት እስካገኙ ድረስ፤፤

  (ኣይጦች=ሙሰኛ ኣስተዳዳሪዎች ፤፤ አንበሳ= መንግስት)

  ReplyDelete
 11. Aba Selamawoch TSERE BETEKIRSTIAN mohanachihun eko ager yawokew,tsehay yemokew new.Menafikan yemanafikan telalakiwoch,musegnoch,...nachihu.M.Kidusanen yemitela SEYITAN bicha new,silezih enanite SEYITAN nachihu

  ReplyDelete