Friday, January 10, 2014

በምዕራብ ሐረርጌ አሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ለማርያምና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የመጨረሻ ምሽጉን (ቶራቦራን) ለቀቀ


በምሥራቅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግፍ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ሲፈጽም የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን በአሁን ጊዜ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ ምሽጎቹን እያጣ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በምዕራብ ሐረርጌ አሰበ ተፈሪ ከፍተኛ ምሽግ አድርጎት የነበረው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሀገረ ስብከቱ ሲሆን፣ በተለይ አሁን ያሉት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ብርሃናት ከሃሊ በቃሉ ከመጡ በኋላ በሀገረ ስብከቱ የነበረውን ቦታና ተሰሚነት በሙሉ አጥቶ ምሽጉን ነቅሎ ወጥቷል፡፡ ከፍተኛ ምሽጉ አድርጓቸው የነበሩት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ,  በተጨማሪም ስብከተ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤት ሲሆኑ፣ ከዚህ በፊት እንደ ገለጽነው የስብከተ ወንጌል ክፍሉን አጥቷል፡፡ የሰበካ ጉባኤውን መዋቅር በከፍተኛ የምእመናን ትብብር የሀገረ ስብከቱ ጥንካሬና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጰጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ቆራጥ አመራር ለማህበረ ካህናቱና ለምእመናኑ እድል በመስጠቱ ሥልጣኑን ላለማጣት በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ቢፍጨረጨርም፣ በታላቅ ምት ስልጣኑን አስረክቦ በታሪክ ከ20 ዓመት በኋላ ማህበረ ካህናቱና ማህበረ ምእመናኑ የሰበካ ጉባኤ አመራር ቦታን ሊቆጣጠሩ ችለዋል፡፡

በደረሰበት ከፍተኛ ምት አፈግፍጎ የነበረው ማህበረ ቅዱሳን አባላቱን በከፍተኛ ሁኔታ ያመርትበት የነበረውን ምሽጉን ፈለገ ቅዱሳን ብሎ በሰየመው ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አድርጎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከዚሁ ምሽጉ እየተነሳ የሰበካ ጉባኤውንም ሆነ ስብከተ ወንጌሉን ምርጫ ያውክ የነበረው ይሄው የፈሪሳዊያን ጥርቅም ማህበር፣ ወሳኝና ልክ እንደ ቢላደን ምሽግ ቶራ ቦራ ይመካበት የነበረው ምሽጉ ሰንበት ትምህርት ቤት አዲስ በተመረጠው ሰበካ ጉባኤና የሀገረ ስብከቱ ቆራጥ አመራር ተመቶ ሊለቅ ችሎአል፡፡


ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ጠያቂና አዛዥ ሳይኖርበት ለ20 አመት የራሱን አመራር በዚሁ ሰንበት ትምህርት ቤት በማፍራት የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር እንደፈለገው ሲዘውር የነበረው ማህበር ከጥቂት ግዜ ወዲህ በተለይ የተለያዩ ለቤተ ክርስቲያን የሚቆረቆሩ ማህበራት  ከተቋቋሙ ወዲህ ጥቂት የመደናበር ምልክት ቢታይበትና የተለያዩ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ቢያፋፍምም እንዲህ በቀላሉ ተሸንፎ ስልጣን ይለቃል ተብሎ አልተገመተም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎቹን ምሽጎቹን ያጣው ይሄ ማህበር ሰንበት ትምህርት ቤት ላይ የመጨረሻ ትግል ለማድረግ ያሰበና ሃይሉን በዚሁ ክፍል ያጠናከረ ቢሆንም ሊሳካለት አልቻለም፡፡ አዲስ አመራር ለመምረጥ ታስቦ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉትን አባላቱን እንዲያሳውቅ ሲጠየቅ በሙሉ አባላቶቹ እንዳልሆኑና እድሜአቸውም ከ30 አመት በላይ የሆኑትን አመራሮቹን እድሜአቸው  ከ18 ዓመት በታች እንደሆነ በመግለጽ የማደናበሪያ ስልቱ የሆነውን ውሸት ተጠቅሞ አመራሩን ሊያስቀጥል ምክሮ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ሀሰቱን ያልተቀበሉት የሰበካ ጉባኤውና ሀገረ ስብከቱ ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን እንዲሰጥ ቢጠይቁትም በእንቢታ በመዝለቁ አቋም ይዘው አዲስ አመራር ለመምረጥ ሲወስኑ ይሄው ማህበር ለዞን አስተዳደር, ለኦህዴድ ጽ/ቤት, ለዞኑ ጸጥታ ቢሮ ደብዳቤ በመጻፍ ተጠናክሮና ተደራጅቶ ያለውን ወጣት ሊበትኑት ነው በማለት ቢያሳውቅም እነዚህ የመንግስት አካላት ማህበሩን ቀድሞውኑ በአሸባሪነቱ ስለሚያውቁት ጩኸቱን  ሊሰሙት ባለመፈለጋቸው ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመነጋገር  ሀገረ ስብከቱም ይሁን ሌላው ህጋዊ የቤተ ክርስቲያን አካል በስራቸው ካለምንም ተጽእኖ የቤተክርስቲያኒቱን ህግ በመጠበቅ ማከናወን እንደሚችሉና በስራቸው ጣልቃ እንደማይገቡ ይነግሯቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረትም የሰንበት ትምህርት ቤቱን  ነባር አባላት  በማሰባሰብ ምርጫ ለማድረግ የታሰበ ቢሆንም እነርሱ ግን ረብሻ ለማንሳት እቅድ ስለነበራቸው የፖሊስ አካል ተጠርቶ ምርጫው እንዲካሄድ ሲፈለግ የማህበሩ አባል የነበሩና ጥቅም የቀረባቸው አመራሮች በእንቢተኝነት ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በቀሩት አባላትም ምርጫው ሊካሄድ ችሎአል፡፡ በዚሁ መሰረት አዲስ አመራር ተዋቅሮ ስራ  የጀመረ ሲሆን አመራሩን ተከትለው ወጥተው የነበሩ የዋሀን ወጣቶች በማግስቱ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው በመመለስ ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው ገብተዋል፡፡ በአሁን ሰአት በአሰበ ተፈሪ ከተማ የማህበረ ቅዱሳን ግብአተ መሬት ተፈጽሞአል፡፡ አባላቱ ግን በንስሀ ተመልሰው ከፍጹም ጥላቻ ተለቀው ፍጹም የፍቅር አባት ክርስቶስን መስለው ቢመጡ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጣቸው፡፡ ሌሎችም አህጉረ ስብከቶች ይህንን ስልት በመጠቀም ልጆቻችሁን በተሳሳተና የቤተክርስቲያን ባልሆነ መንገድና ወደ ፍጹም እውነት በማያደርስ መንገድ ሲመራ ከኖረው ማህበረ ቅዱሳን በዚህ መልክ መላቀቅና ልጆቻችሁን በቤተ ክርስቲያን ማቆየት የምትችሉ በመሆኑ ይህንን መንገድ እንድትከተሉ እንመክራለን፡፡ ዘመኑ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰራበት የትንሳኤ ዘመን ነውና የቤተክርስቲያናችንም ትንሳኤ እንደደረሰ አምላክ በቤቱ እየሰራ ያለውን አስተውሉ፡፡

29 comments:

 1. Ketlacha Yetseda Eski And Qen Ewunet Tenageru

  ReplyDelete
 2. Teret tert... MK kal enkilf altegnam yalech yeprotestant ahya neberech...

  There is a group that fantasize prtotestanism and always dream to destroy the Association of Saints.

  Jesus Christ Lord of Lord will protect MK and their mother church. Prise His Name!

  ReplyDelete
 3. Meche yihon ewnet yemitaworut!? Ere ebaKachihu EgziAbHern firu. Min aynet yeSeyitan bahiri new?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewnetima tengerhe gen keabateh kediablos slehonk ewnet aysmamahim

   Delete
 4. አፈንጋጭ ፕሮቴስታንት ውሸታሞች!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. በቃ ይቺን ነው የምታውቀው አይደል? ይልቅ ምክንያታዊ ሆነህ ሀሳብህን ግለጽ

   Delete
 5. MK ketayu zamen lante betam tiru silalehone ba sihetet menged ba sireh yaselefkachewun ya betekristiyan lijoch lekek. ya abatochen sem ba sihetet matifat ayawatahem lib giza.

  ReplyDelete
 6. menafiq egziabher yigesitsih

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wedaje menafik malet lemehonu min malet new? Mejemeria tergumun atena.mengezem behon bekrostos yemiamin menafek yemilew sim aysmamam esh...geta yegletseleh

   Delete
 7. አፈንጋጭ ፕሮቴስታንት ውሸታሞች!!!

  ReplyDelete
 8. menafiq egziabher yigesitsih

  ReplyDelete
 9. Would please change the blog name to " Aba Satan"/ the father of false". Thanks.

  May Jesus Christ open your inner eye to see the positives. Even Gragn Mohammed wasn't able to destroy Our Church/ The Church of Jesus Christ. Prise His Name.

  ReplyDelete
 10. አፈንጋጭ ፕሮቴስታንት ውሸታሞች!!!

  ReplyDelete
 11. አፈንጋጭ ፕሮቴስታንት ውሸታሞች!!!

  ReplyDelete
 12. ነገረ ሥራችሁ ሁሉ እንዴት ያስጠላል፡፡

  ReplyDelete
 13. ቃልስና ነዊሕን መሪንን ኢዩ ዓወትና ናይ ግድን ኢዩ
  ማቅ ይመታል ድባቅ

  ReplyDelete
 14. wfer tebeges kemzi hji bello netimedherheray

  ReplyDelete
 15. እዉነት ትቀጥናለች እንጅ አትበጠስም!

  ReplyDelete
 16. Tehadiso consider them selves as they know every thing

  ReplyDelete
 17. wulude kelebat...ebuyan....

  ReplyDelete
 18. The writer was dismissed from the government office because of corruption. By this time he is wondering here and there doing serious criminals on private taxes in the town. He tries to lead the parish and the diocese as a whole.He was and is the leader of Haymanote Abew.

  ReplyDelete
 19. ጠያቂ፡ የምዕራብ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ማን ይመስልሃል?
  መልስ ሰጪ፡- ይርጋለም ቸኮል ነዋ! አሁንማ ተጠባባቂ እያለ የሰበካው ልማት ክፍል አድርገውት የሌ፤ ሕዝቡ ራሱ በመረጠው ሳይሆን ቢራ በማጠጣት በመጠጥ ቤቶች በአቋራጭ በሚመረጡ ጋባዦች ሆኗል፡፡

  ReplyDelete
 20. ጠያቂ፡ የምዕራብ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ማን ይመስልሃል?
  መልስ ሰጪ፡- ይርጋለም ቸኮል ነዋ! አሁንማ ተጠባባቂ እያለ የሰበካው ልማት ክፍል አድርገውት የሌ፤ ሕዝቡ ራሱ በመረጠው ሳይሆን ቢራ በማጠጣት በመጠጥ ቤቶች በአቋራጭ በሚመረጡ ጋባዦች ሆኗል፡፡

  ReplyDelete
 21. የተሐድሶን ዓላማ ለማሳካት የተቋቋሙ ግለሰቦች ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አይኖራቸውም

  ReplyDelete
 22. Hello there! የዘረፍከውን የመንግሥት ብር ከፈልክ? መጀመሪያ እሱን ክፈል ከዲያብሎስ የወረስከውን ስድብ በኃላም ትደርሳለህ፡፡

  ReplyDelete