Monday, January 6, 2014

መንፈሳዊ መልእክት


እንኳን ለበዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
“እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
(ሉቃ. 2፥10-11)
ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በተወለደባት በዚያች ሌሊት መንጋቸውን ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች የጌታ መልአክ የተናገረው የምሥራች ነው፡፡ የምሥራቹ በጊዜው ለእረኞቹ የተነገረ ቢሆንም መልእክቱ ግን በእረኞቹ ብቻ የሚወሰንና እነርሱን ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡ የምሥራቹ “ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች” ተብሏልና ለሰው ዘር ሁሉ የሆነ ታላቅ ደስታና የምሥራች ነው፡፡ የጌታ መወለድ ታላቅ ደስታና የምሥራች የሆነበት ዋናው ምክንያት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ የዓለም መድኀኒት፣ እንዲሁም ይመጣል ተብሎ በነቢያት ትንቢት የተነገረለት መሲሕ (ክርስቶስ)መሆኑ ነው፡፡

ዛሬ የልደቱን መታሰቢያ የምንዘክረው መድኀኒት ክርስቶስ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከዛሬ 2006 ዓመት በፊት ተወልዷል፡፡ ልደቱን ስናስብ በዋናነት ማተኮር ያለብን ግን በተወለደ ጊዜ የሆነውን ያለፈውን ድርጊት ብቻ ሳይሆን የተወለደበትን ዓላማ ጭምር ሊሆን ይገባዋል፡፡ የተወለደው መድኀኒት ክርስቶስ ነው፡፡ እንዲህም ስንል መድኀኒትነቱ፦ በኃጢአት በሽታ ለታመምንና በሥጋ ሞት ከዚህ ዓለም ሳንለይ መድኀኒቱን  ካላገኘን ዘላለማዊ ሞት ለሚጠብቀን ለእኛ ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ  የሚበልጥ ምን ደስታና የምሥራች አለ?


ምናልባት እርስዎ መድኀኒቱን በዝና ብቻ የሰሙ፣ በየዓመቱ በዓለ ልደቱን በዘልማድ የሚያከብሩና መድኀኒቱን በእምነት ያልተቀበሉ ከሆኑ እግዚአብሔር በመልአኩ በኩል የላከው ይህ ታላቅ ደስታና የምሥራች ወደእርስዎ አልደረሰም ማለት ነው፡፡ በየዓመቱ ልደቱን በመብልና መጠጥ በባህላዊም ጭፈራና ዳናኪራ በራስዎ መንገድ እያከበሩ ክርስቲያን ነኝ ካሉም እጅግ ተሳስተዋል፤ ስለዚህ እባክዎ የምሥራቹን ይስሙና ወደዚህ መድኀኒት ወደኢየሱስ ክርስቶስ ይቅረቡ፤ ኀጢአትዎን ለእርሱ ይናዘዙና ስለእርስዎ በመሰቀሉና በመሞቱ የኃጢአትዎን ዕዳ እንደከፈለልዎ አምነው የኃጢአትዎን ይቅርታ ይቀበሉ፡፡ እንዲያ ካደረጉ የምሥራቹ ወደእርስዎ ደርሷል፤ እርስዎም ተቀብለዉታል ማለት ነው፡፡ በዓለ ልደቱን መዳንዎን እያሰቡ አዳኝዎን እያመሰገኑ እንዲያከብሩ እየተመኘን መልካም የልደት በዓል ይሆንልዎ እንላለን፡፡   

25 comments:

 1. This holiday belongs to Ethiopian orthodox Tewahido Church as the calendar is its own. While you are denouncing the holy holy church using every effort to westernize it, why why don't you use your masters calendar instead??? You are lucifer disguised in flesh. This calendar is Ethiopian orthodox Tewahido. Protestantism shouldn't use it.
  .

  ReplyDelete
  Replies
  1. Actually buddy, it's not of the Ethiopian Orthodox Church calendar. It's an ancient Egyptian calendar later reformed by the emperor Augustine to keep it synchronized with the calendar of the time; the Julian calendar. In life, if you steal someone's work and call it your own, it's called plagiarism. It's a major offense!

   You are attesting, the Protestant church shouldn't use it because it's not of their own. But technically, the Ethiopian Orthodox Church is using a calendar that is not of their own. So according to your logic, the Ethiopian Orthodox Church is wrong for using a calendar that is not of their own. You see where your simple minded reasoning lead to? Anyway, it's not which calendar one uses that's most important but the celebration of the birth of the almighty Son of God. Merry Christmas!

   Delete
  2. Brother Maru Kebede, your Christian value not determine by celeberating holidays. The above brother or sister replied for your vague comment diligently. Please read bible and find any one bro or sis who is with Jesus to help you on the bible. I ask my lord Jesus for his presence in your life.
   Your brother by Jesus, I love you!

   Delete
  3. ማነው የነገረህ ለምን ቱላቱልን ትነፋለህ አንተ መናፍቅ ?ይችህ ቤተክርስትያን የገሃነም ደጆች የማይችሏት መሆኗን አንተም የገሃነም ደጅ ውስጥ የምትኖረው እንዲሁም ሉሲፈርም እራሱ ታውቁታላችሁ ::

   Delete
  4. Very wrong logic embellished with a response logic. If i am not mistaken the person who commented about the calender is trying to convey about two calenders Christians are using using to celebrate holidays. Protestants and Catholics are using days which is different from the Oriental and Eastern Orthodoxies are using. I think Maru believe that the admin (owner) of this blog is highly affiliated with Protestants and most probably thinks that Ethiopia Orthodox is using the wrong calender. So Maru is telling the blogger that the Genna that we are celebrating now mean nothing for him.

   Delete
  5. Very wrong logic embellished with a response logic. If i am not mistaken the person who commented about the calender is trying to convey about two calenders Christians are using using to celebrate holidays. Protestants and Catholics are using days which is different from the Oriental and Eastern Orthodoxies are using. I think Maru believe that the admin (owner) of this blog is highly affiliated with Protestants and most probably thinks that Ethiopia Orthodox is using the wrong calender. So Maru is telling the blogger that the Genna that we are celebrating now mean nothing for him.

   Delete
  6. I donot have anyword. yemigerim melis new leferisawiw yesetachhut. Be blessed Aba selamawoch!!

   Delete
  7. To Berhanu & ferisawiyan;
   On December 25, you plant Christmas trees and exchange gifts; wishing everyone you know merry Christmas. Did westerners denounce you because you're celebrating Christmas on that day? But you have the nerve to come out here and tell the whole world they have no right to celebrate Christmas on January 7 unless they are Ethiopian Orthodox. Such hypocrites!

   Delete
  8. In my opinion
   1) the Ethiopian Calender is not totally copied from Egyptian's (http://bahirehas.blogspot.com/2013/09/blog-post.html#more) , http://holyfathersundayschool.blogspot.com/2011/09/65-11-12-29-30-1901.html , http://www.eotc-mkidusan.org/site/-mainmenu-24/--mainmenu-26/30----
   2 ) Other religions followers can use the calender but I do have one question for them how they trust Ethiopian calender? are they sure that Jesus was born ton that specific date
   they should trust us other wise they don't have choice Every thing is not found in the Bible thanks to our fathers

   Delete
  9. "In my opinion
   1) the Ethiopian calendar is not totally copied from Egyptian's"

   Your opinion is invalid because it's a well know fact our calendar is the exact same replica of the Coptic calendar (other than the names, obviously). There is no need to argue this truth.

   2) No one knows the specific day Jesus was born. January 7 is the day that was held since early Christianity to commemorate his birth but that doesn't mean our Lord was born on that day. You can look this up.

   Delete
 2. ግሩም የልደት በዓል መልእክት ነው፡፡ የጌታን ልደት በዚህ መንገድ ካላሰብን ትርጉም የለውም፡፡

  ReplyDelete
 3. ማሩ ከበደ በጣም ጠባብ ነህ፡፡ ይህ በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ክርስቲያኖች ነው፡፡ ኢትዮጵውያን ክርስቲያኖች ሁሉ የምንጠቀመው በኢትዮጵያ አቆጣጠር መሠረት ስለሆነ በዓለ ልደትን በተመሳሳይ ቀን ማክበራችንን መቃወም እጅግ በጣም ጠባብ መሆን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይህን የዘመን አቆጣጠር ያመጣችው ከእስክንድርያ ነው፡፡ ስለዚህ ያን ያህል ለጠባብ አመለካከትህ መኩራሪያ አድርገህ የምትጠቅሰው አይደለም፡፡ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኩል የኢትዮጵያውያን ሁሉ መጠቀሚያ ሆኗልና የዚህን መልካም ጎን ማጉላት እንጂ መለያየትን መፍጠር ተገቢ አይደለም፡፡ ይህ የእናንተ የማቅ ሰዎች ጠባብ አመለካከት ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ በእድሜ ተለቅ ያለ ፕሮቴስታንት ነጭ በነጭ ለብሶ ሲሄድ ከአንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ጋር የዘመን መለወጫ ዕለት በመንገድ ተገናኙና እንኳን አደረሰህ ሲለው ማኅበረ ቅዱሳኑ ወጣት በማን ካሌንደር? አለው፡፡ ማሩም የዚህ ጠባብ አመለካከት ሰለባ ነህና እባክህን ልብ ግዛ፡፡ ክርስቶስን ኦርቶዶክሳዊ ብቻ ለማድግ አትሞክር፡፡ ክርስቶስ የሚያምኑበት የሁሉም ነው፡፡ ካሌንደሩን ብቻ ሳይሆን ፊደሉንም ያቆየችው ኦርቶዶክስ ናትና አማርኛ በሚጠቀምበት በግእዝ ፊደልም አትጻፉ ልትል ነው፡፡ አሁን እንዲህ ማለት ምን ይጠቅማል? ሕዝቡን ለመከፋፈል ባንሞክር ምናለበት?
  ከአስተያየትህ የታዘብኩት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም አንተና መሰሎች እንዲህ ዓይነት አስተያየት የምትሰጡት አባ ሰላማ በሚያወጧቸው ጽሑፎች ላይ በተቃውሞም ቢሆን ተገቢና ገንቢ ምላሽ መስጠት ስለማትችሉ ነው፡፡ ስለዚህ አስተያየታችሁ በአብዛኛው ስድብ ብቻ ይሆናል፡፡ አሁን ይህ መንፈሳዊ መልእክት ምን ይወጣለታል? ጌታን ልደት በዚህ መልክ ካላከበርነው የምናገኘው መንፈሳዊ ትርፍ የለም፡፡ ይህን ሐሳብ መቃወም ከተቻለ ሐሳቡን መቃወም ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ካሌንደሩ የእኛ ነው ብሎ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለማግለል መሞከር ተገቢ አይደለምና ማሩ እንዲህ ያለ አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ዳግመህ አስብ፡፡

  ReplyDelete
 4. ወንድሜ ማሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም በ ስጋ ተገልጦ የመጣዉ ፍጥረቱን ለማዳን ነዉ እንጂ አንተ እንደምታስበዉ ካላንደር ተቆጥሮ ባብዛኛው አንተና መሰሎች ህ እንድምታደርጉት በዳንኪራና በጭፈራ በ ስካርና በ ዝሙት ቀኑን እንድናከብር አይደለም። እግዚአብሄር ግብዞችን አይወድም ። ታዲያ ካላንደር ብቻ ሳይሆን ፊደልም ቀርጻ ያበረከተች
  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእዉነተኛዉ መንገድ ላይ ካልቆመችና ነፍሳት ካልዳኑ ምን ጥቅም አለዉ። ይልቅ እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ ክብሬን ምስጋናዬን ለሌላ አልሰጥም ያለዉን አምላክ አጥብቆ መያዝ ነዉ የሚያዋጣዉ ወንድሜ።

  ReplyDelete
 5. deneqemelekekete. tebereku

  ReplyDelete
 6. ማሩ መራራ ሥር ነህ

  ReplyDelete
 7. protestants are not real Christians. look the western , the do not cerebrate properly -even 1/4 of their own birthday. protestants are tequla menafkan aspiring only for their earthly interests. so, why do they depend on orthodox calendar. Russia, Greek, Egypt, armenya.. are Orthodox followers and share same calendar. our protestant menafkan depend on us to loot our sheep. shame on this fox religion

  ReplyDelete
 8. protestants are not real Christians. look the western , the do not cerebrate properly -even 1/4 of their own birthday. protestants are tequla menafkan aspiring only for their earthly interests. so, why do they depend on orthodox calendar. Russia, Greek, Egypt, armenya.. are Orthodox followers and share same calendar. our protestant menafkan depend on us to loot our sheep. shame on this fox religion

  ReplyDelete
 9. protestants are not real Christians. look the western , the do not cerebrate properly -even 1/4 of their own birthday.

  ReplyDelete
 10. ቱላቱልን ትነፋለህ አንተ መናፍቅ ?

  ReplyDelete
 11. please admit what maru says but in a little modification
  no matter use it but recognize the owners ( of course the calender is adopted from Egyptian with some modification )
  but do you have confidence to celebrate all dates in the calender? do you trust all happens on that dates? if so you trust in Ethiopia Orthodox Calender who knows with some other points too. but you may avoid all that are not compatible with your missions
  frankly speaking your "church" will be empity with out this Calender that is why all of you tried to defence to use it no matter use it or modified it as we did in Egyptians
  hopefully you couldn't do that because you are apart from history

  ReplyDelete
  Replies
  1. Protestants in Ethiopian celebrate on January 7. But in diaspora, they celebrate on December 25. So it's not a big deal, relax

   Delete
 12. Geta hoy yemiadergutn ayawqumna yiqir belachew

  ReplyDelete
 13. “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን
  ታላቅ ደስታ የምሥራች
  እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ
  በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም
  ክርስቶስ ጌታ የሆነ
  ተወልዶላችኋልና።”
  (ሉቃ. 2፥10-11)
  ጌታች

  ReplyDelete
 14. ከዛሬ 2006 ዓመት በፊት ተወልዷል malet min malet neew?

  ReplyDelete
 15. defterna eskribito yizeh nana enastemirh

  ReplyDelete