Monday, January 13, 2014

‹‹ተሐድሶ በቤተ ክርስቲያናችን የነበረ፣ ያለና የሚኖር ነው››


ምንጭ፡- ተሐድሶ ብሎግ

እግዚአብሔር ፍጥረታቱን በተሐድሶ በሕይወት የሚያኖር አምላክ ነው፡፡ ተሐድሶ እግዚአብሔር ከምሕረቱ የተነሣ፣ ከጥንተ ተፈጥሮው የሳተውን ወደ ፈቃዱ የሚመልስበት፣ በሕይወት የሚያኖርበት፣ ከጥፋት የሚያድንበት የበጎነቱ ሥራ ነው፡፡

        በእግዚአብሔር የመታደስ ዕድል ከሚሰጣቸው መካከል አንዷ በምድር ያለችው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን በክቡር የክርስቶስ ደም የተዋጀች፣ የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ የሕይወት ልክ የተሰጣት፣ የሕያው አምላክ፣ የጻድቅነቱ የቅድስናውና የክብሩ መገለጫ እንደራሴው ናት፡፡

        ቤተ ክርስቲያን ከጌታ ከተሰጣት የእምነትና የሕይወት መንገድ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ስትስት ወደ ራሱና ወደ ፈቃዱ ሊመልሳት ከፍቅሩ የተነሣ የመታደስን ዕድል ይሰጣታል፡፡

        ይህን ሰማያዊ የመታደስ በረከት እንዲያገኙ በአምላክ ልብ ቀድሞውኑ ከታሰቡት አብያተ ክርስቲያናትም መካከል አንዷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፣ በዓለም ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ቀድሞ ለተሐድሶ የአምላኳ ጥሪ የደረሳት ናት፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ የተቀበሉ አገልጋዮቿና ምእመናን በቅዱስ ቃሉና በቅዱስ መንፈሱ ራሳቸውን እየመረመሩ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ የሕይወት መታደስን አግኝተዋል፡፡ እስከ ዘመናችንም ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱ በመታደስ ሂደት ላይ ናት፡፡        እንደ አሁኑ ጊዜ ተሐድሶ የሚለው ቃል በአንዳንዶች አሉታዊ ትርጉም ሳይሰጠውና እንደ ባዕድ ሳይታይ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የሚለውን ቃልና አሳቡን ከአምላኳ ተቀብላ፣ የራሷ አድርጋ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆኑ የዘመን ምስክሮችን መለስ ብለን በጥቂቱ እንቃኛለን፡፡
        የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ይባል የነበረው አንጋፋ ጋዜጣ በሚያዝያ 2 1963 ዓ.ም. ዕትሙ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ሲመተ ፕትርክና ጋር አያይዞ እንደዘገበው ‹‹የሌሎች አገሮች አብያተ ክርስቲያኖች እንደ ታደሱ ሁሉ የእኛም እንደ ዘመኑ መራመድይኖርባታል። የዐሥራ ዐምስተኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች አስተሳሰብና የኻያኛው ክፍለ ዘመን ፍልስፍና በጣም የተራራቀና የተለያየ ስለ ሆነ፥ ሊያሳምን በሚችል በዐዲስ ዘዴ መቅረቡ የተሻለ ውጤት ያስገኛል። ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ይህን ሁሉ በማመዛዘን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ፣ በአሠራር፣ በአስተሳሰብና በአፈጻጸምየታደሰችና የዘመኑን ሥርዐት የተከተለች እንደሚያደርጓት ከፍተኛ ኀላፊነት ይጠብቃቸዋል’ በማለት ገልጾ ነበር፡፡

በ1971 ዓ.ም.  ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ ስለ ስብከተ ወንጌል በሚናገረው በክፍል ሁለት በተራ ቁጥር 1 ላይ ‹‹ በቤተ ክህነት በኩል ያለው አስተዳደር በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመራና ተሐድሶ የሚታይበት እንዲሆን ያስፈልጋል›› ተብሎ መደንባቱን ትንሣኤ መጽሔት በቁጥር 20 የካቲት 1971 ዓ.ም. ዕትሙ በገጽ 14 ላይ አስነብቧል፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን የተሰኘው አንጋፋ ጋዜጣም ከነበሩት ዐምዶች አንዱ የተሐድሶ ዐምድ ነበር፡፡ በመስከረም 5 ቀን 1972 ዓ.ም. ዕትሙም በጋዜጣው ርእሰ አንቀጽ ‹‹ተሐድሶ በተግባር›› በሚል ርእስ “የኢትዮጵያ አብዮት ከፈነዳ ወዲህ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ብዙ ጊዜ በቃል ሲነገር ይሰማል፤ ይሁን እንጂ በቤተክርስቲያኒቱ አንዳንድ የተሐድሶ ምልክቶች ሊታዩ አልቻሉም ብለን መናገር ባንደፍርምብዙ በቃል የሚነገረውን ያህል በተግባር ተተርጉሟል ብሎ መናገር ደግሞ አዳጋችይሆናል፡፡” በማለት ተሐድሶ በተግባር እንዲገለጥ ለማሳሰብ በጽሑፉ አትቷል፡፡
በየካቲት 16 ቀን 1972 ዓ.ም. ዕትሙም በተሐድሶ ዐምድ ሥር ‹‹መታደስ በመንፈስ ቅዱስ›› በሚል ርእስ የቀረበውን የቄስ ዘውዴ ደስታን ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ ጽሑፉምበመንፈስ ቅዱስ  ለመታደስና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመሞላት የክርስቶስንመድኀኒትነት ለመግለጽና የአማኞች ሰውነት ከልዩ ልዩ የጣዖት አምልኮት ተላቆ ፍጹምየክርስቶስ ማኅደር ሆነው በእምነታቸው ጸንተው የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም እንዲችሉለማድረግ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉና የተቃኙ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ሥልጣንየተቀበሉ ጳጳሳት ወይም ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዲኖሩን ያስፈልጋል፡፡” የሚል ለሕይወት መታደስ የመንፈስ ቅዱስን አስፈላጊነት በአጽንዖት የሚገልጥ ነበር፡፡

ማዕዶት ይሰኝ የነበረው የቤተ ክርስቲያኒቱ መጽሔት ስያሜውን ያገኘበትን ምክንያት ሲገልጽ “ይህ መጽሔት በዚህ ታዳጊ ዓለምና የሽግግር ወቅት ውስጥ በተሐድሶ ላይ የምትገኘውን ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ታሪክና ዜና ጠቅላላ ህልውናዋንና ወቅታዊ እንቅስቃሴዋን ሁሉ የሚገልጽ ስለ ሆነ ማዕዶት ተብሎ ተሠየመ” በማለት ነበር፡፡ (ማዕዶት ቍጥር 1 ጥር 1972)

ታላቁ ሊቅ አለቃ ነቢየ ልዑል ዮሐንስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ተሐድሶ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ” በሚል ርእስ ትንሣኤ መጽሔት ላይ ካቀረቡት ጽሑፍ የሚከተለውን እንመልከት፡፡ “እስካሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያኗ መሻሻልናመለወጥ እምነትን የሚነካ እየመሰላት እንደ ኩሬ ውሃ በአንድ ቦታ ቆማ በአብርሃና አጽብሐዘመነ መንግሥትና በአቡነ ሰላማ መጀመሪያ በተመሠረተው አመራር ከመሄድ በቀር በውስጧየሚተዳደሩት ሊቃውንትና ምእመናን እነርሱ ተሻሽለው ሌላውም እንዲሻሻል ሳታደርግባለህበት እርገጥ በሚለው ባልሆነ ፈሊጥ እየተመራች እስካለንበት ጊዜ ቈይታለች፡፡ ስለዚህሃይማኖትን ከሚመለከቱ ነገሮች በቀር ጊዜውን ተከትሎ መሻሻልና ለውጥ እንደሚያስፈልግተሐድሶንም ከኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ … እንግዲህ ብዙታሪኮችን አይተናል፤ ያለፈው ዐልፏል፤ ማሰብ ወደ ፊት ለሚመጣው ነው፡፡ የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ የአመራር እንቅስቃሴ ለዚህ ዐይነትአሠራር መነሻ ምክንያት እንደሚሆን የብዙዎቻችን እምነት ነው፡፡” (ትንሣኤ የመስከረምናጥቅምት ወራት 1984 .ም. ቍጥር 150 ገጽ 10-11)፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዐምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው በተመረጡ ጊዜም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተስፋ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የተጣለውን የተሐድሶ መሠረት እንደ ገና ለመጣል መሆኑን እንዲህ ሲል መስክሯል፤ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሠኔ 28 ቀን 1984 ዓ.ም. ባደረገችው ፓትርያርካዊ ምርጫ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በካህናትና በምእመናን ከፍተኛ ድምፅ ተመርጠዋል፡፡ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የተሐድሶ መሠረት በጣሉበት ወቅት የመጀመሪያው ተመራጭ አባትና የተሐድሶውን መሠረት የመጣሉን ተግባርከቅዱስነታቸው ጋር ዐብረው ያከናወኑ ሐዋርያ ስለ ነበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የተሐድሶ ተግባርን በብፁዕነታቸው ዘመነ ሢመት እንደሚቀጥል ስለ ተገመተ የምርጫው ዜና በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ያስተጋባውን ልባዊ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ተመራጭ ቃል አይገኝም፡፡ …

“በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የተሐድሶ መሠረት እንደ ገና ለመጣል ‘ኢትዮጵያ ታበጽሕ አደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር’ በተባለው መሠረት ዘወትር ለጸሎት የተዘረጉት የመላ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እጆች አላፈሩም፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ቀድሞ በትሩፋታቸው የሚያውቃቸውንና በተጋድሎአቸውም ወቅት ለአንድ አፍታም ያልተለያቸውን ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጳውሎስን ከስደት ጠርቷል፡፡ …

“ስለዚህ ‘ፀሓይ ሳለ እሩጥ አባት ሳለ አጊጥ’ እንዲሉ … ራስን በንስሓ አስተካክሎ ለትምህርተ ወንጌል ታጥቆ መነሣትና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ መዘጋጀት የብፁዓን አባቶች የመላው ካህናትና ምእመናን ወቅታዊ ግዴታ ነው” (፭ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ልዩ ዕትም 1984 ገጽ 3-4)።
ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለ2005 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ባሰሙት ቃለ ምዕዳን በክርስቶስ የአድኅኖት ሥራ የተመሠረተና በሕይወት መታደስ ላይ ያተኰረ ግልጽ መልእክት አስተላልፈው ነበር፡፡ እንዲህ በማለት “ያረጀው ነገር ሁሉበክርስቶስ ደም ተቀድሶና ነጽቶ ሐዲስ ኾኖአል፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሠርቶየሚያሠራ የመልካም ነገር ሁሉ አርኣያና መሪ እንደመኾኑ መጠን አዲሱን መንገድ ከፍቶእንድንጓዝ ሲያደርግ እኛም በሐዲስ መንፈስ በሐዲስ ሕይወት ልንመላለስበት እንጂ እንደገናወደአረጀውና ወደአፈጀው ሕይወት ተመልሰን ልንዘፈቅ አይደለም፡፡ አዲስ ሕይወት ማለትእግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ መድኃኒት እንዲኾን በላከው በመድኃኒታችን በኢየሱስክርስቶስ በማመን የዘለዓለም ድኅነትን ማግኘት ነው፤ ምንም ዐይነት አማራጭ የማይገኝለትንይህን የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ የሰው ዘር ሁሉ ተቀዳሚ ሥራው አድርጎ ሊቀበለውይገባል፤ በዚህ በኩል ካልኾነ ሌላ የምንድንበት መንገድ የምናመልጥበት ዐውድ ፈጽሞየለምና፡፡››
ከላይ የተገለጡት አሳቦችና መረጃዎች ምን ያመለክቱናል? ተሐድሶ የሚለው አሳብና ቃሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ የነበረና የሚሠራበት መሆኑን እንጂ መጤና እንግዳ አለመሆኑን ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊና ሁለንተናዊ መታደስን የሚቃወሙ አንዳንዶች ግን ተሐድሶ የሚለውን ክቡር የእግዚአብሔርን ስጦታ ለመግፋት ሲታገሉ ይታያሉ፡፡

እግዚአብሔር የሕይወት መታደስ የሰጣቸውንና የእግዚአብሔር የተሐድሶ ሥራ በቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲስፋፋ የሚተጉትን በመቃወም ከእናት ቤተ ክርስቲያናቸው እንዲገፉ በማድረግ የተሐድሶውን እሳት ለማጥፋት ስያሜውንም ለማጠልሸት ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምበትን የራሷ የሆነውን ‹‹ተሐድሶ›› የሚለውን የከበረ ቃል፣ መናፍቃን ከሚል አሉታዊ ቃል ጋር በማዛረፍና ‹‹ተሐድሶ መናፍቃን›› የሚለውን ስመ ጽርፈት በመስጠት ጥላቻቸውንና ተቃውሟቸውን አሳይተዋል፡፡

    በክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሕይወት መታደስ፣ ከእግዚአብሔር ንስሓና ድነት ካገኙት መካከል አንዳንዶቹ በእነዚህ የተሐድሶ ተቃዋሚዎች መከራና ስደት ደርሶባቸዋል፡፡ ‹‹ተሐድሶ መናፍቃን›› የሚልም ስም አውጥተውላቸው ስማቸውንና መልካም ዝናቸውን አጉድፈዉታል፡፡ በዚህም ምክንያት ተሐድሶ የሚለውን ቃል እነርሱም እንኳ ለመቀበል ተቸግረዋል ይህ ስም ሲጠራ ደስ እንደማይላቸው ሲገልጡም ተደምጠዋል፡፡

እነዚህ ተሐድሶ መናፍቃን በመባል በቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሆነ ስደት ገጥሟቸው የተገለሉ አሁንም በኦርቶዶክሳዊና እውነተኛ በሆነ ክርስቲያናዊ ጎዳና ጸንተው ያሉ ስዱዳን ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦችና የእግዚአብሔር ዕንቊዎች ናቸው፡፡ ተሐድሶ የእግዚአብሔር የፍቅር ሥራ ነው፡፡ ከውድቀታችን የተነሣንበት፣ ከጠፋንበት ወደ መድኀኒታችን የተመለስንበት የአምላካችን የምህረት እጅ የተገለጠበት ነው፡፡
እነዚህ ወገኖች ለቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር በሰጠው የተሐድሶ ዕድልና ዘመን የተገኙ የተሐድሶ ፍሬዎች፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ከእግዚአብሔር የምሕረት እጅ እንደተዘረጋላት የሚመሰክሩ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

ተሐድሶ የእግዚአብሔር ለነበሩና ከመንገዱ ለሳቱ ለመዳናቸውና ለሕይወት ከጌታ  የሚሰጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን የተሐድሶ ዕድል ሰጥቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህን ጥሪ በሙላት እንዳትቀበል የሚታገሉ ቢኖሩም እንኳ ቃሉንና ዐሳቡን የራሷ አድርጋ ስትጠቀምበት ቈይታለች፡፡
    የሕይወት መታደስን ካገኙት አንዳንዶች ይህን ስም ተሸክመው ቢሰደዱም እንኳ ተቃዋሚዎች ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተሐድሶን ሥራ ማስቆም አልቻሉም፡፡
    ተሐድሶ ከእግዚአብሔር የተሰጠ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለ፣ የሚኖር፣ የሕይወትን መታደስ የሚሰጥ፣ ተቃዋሚዎች ሊገቱት የማይችሉት ገና በሙላት የሚገለጥ የእግዚአብሔር ድንቅ የማዳን ሥራ ነው፡፡
    በመሆኑም ለዚህ በቤተ ክርስቲያናችን ለነበረ፣ ላለና ለሚኖር ለተሐድሶ እንቅስቃሴ ጌታ የጀመረውን ሥራ እንዲፈጽምና በሙላት እንዲገለጥ የምታገለግሉ የክርስቶስ ወገኖች ሁሉ በርቱ! ጌታ የሰጠንን ራእይ ይፈጽማል! ተስፋችንም እዉን ይሆናል!
   
 በዚህ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ የተጎበኛችሁ ኦርቶዶክሳውያን፣ ቤተ ክርስቲያን ከሳተችበት ወደ አምላኳና ወደ መድሃኒቷ እንድትመለስና  እንድትታደስ ምህረቱን እንዲያበዛልን በጸሎት የምትተጉ በከባድ ነቀፋና ተቃውሞ ውስጥ ሆናችሁ በአገልግሎት እየተጋደላችሁ የምትገኙ የእግዚአብሔርና የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ መሪጌታዎች፣ የአብነት መምህራን፣ የሥነ መለኮት መምህራን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና አገልጋዮች፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ በወረዳ ቤተ ክህነቶች፣ በአህጉረ ስብከቶች፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በልዩ ልዩ ሓላፊነት የምትሠሩ አገልጋዮችና ምእመናን ሁላችሁም ለተሰጠን አገልግሎት የምታስፈልጉና የምትጠቅሙ በመሆናችሁ ሥራውና የሥራው ባለቤት የእያንዳንዳችሁን ተሳትፎ ስለሚሻ ከዚህ ቀደም ከነበረው ተሳትፎአችሁ በተሻለ መንገድ እንትተጉና ተያይዘን ለኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የተሐድሶ ዕድል ለሕዝባችን ሁሉ እንዲደርስ፣ እንድንጋደል የከበረውን ጥሪያችንን ዛሬም ስናቀርብ ተግባራዊ ምላሻቻችሁን በያላችሁበት  እንደምትሰጡ በመተማመን ነው፡፡

     እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንና ኢትዮጵያን ይባርክ!

    

22 comments:

 1. You don't know what you talking about. Your main mission is Protestantism. You are not working for Jesus or for His Church. You are working hard to convert Christians in to Protestantism.

  I know your mission; I had been in your footsteps. So don't try to mischief us.

  Jesus Christ is Lords of Lord Kings of King our savior. Prise His name. He always uncover your hidden agenda.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሞኝ አትሁን ወንድሜ ሆይ አንድ ጌታ አንድ ቤ/ክ ነው እኮ በሰማይ የሚኖረው ዘረኝነት መከፋፈል የለም እኮ በማሰማይ አዎ አምላኮ ከልባችን ይልቅ ትልቅ ነው ነዚህ እኮ ነው የሰውን ሀሳብ ለማስቀረስ ተሀድሶ ያስፈልጋል የተባለው አትጨነቅ ጌታ ሁሉን ያውቃል ክርስቲያን ማለት ክርስቶስን የሚመልስ አይርሱን ነገር የሚያስቀድም ማለት ነው እኮ

   Delete
 2. ተባርኩ እንዲህበተጨበጠማስረጃሀሳባችሁንስታቀርቡ ደስ ያሰኛል

  ReplyDelete
 3. God bless you. wow

  ReplyDelete
 4. በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው፡፡ በወንጌል ሕይወታቸው የታደሰ በርካታ ሰዎች በቤተክርስያናችን ውስጥ ይገኛሉ፤ ምንም እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የታቀፈ ባይሆንም በማኅበሩ ውስጥ በአባልነትና በአመራር ውስጥ ካሉት አንዳንዶቹ የሕይወት ተሐድሶ እንዳገኙና ሁለንተናዊ ተሐድሶ በቤተክርስያን እንዲመጣ እየሠሩ እንደሆነ የማውቃቸው አሉ፡፡ ማኅበሩም ቢሆን መንፈሳዊ ተሐድሶን እንደማይፈልግ ይናገር እንጂ አስተዳራዊ ተሐድሶ እንዲመጣ ከራ አጀንዳ ጋር በማጣጣም እየታገለ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ በተለይ እነዚህን የሕይወት ተሐድሶ ያገኙትን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ማበረታታት ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡ ተሐድሶ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን!

  ReplyDelete
 5. wow!des yemil meleekit....seyitanina wedajochu yemiafirubet gize qeribual.tebareku abaselamawoch!!

  ReplyDelete
 6. You are working hard to convert Christians in to Protestantism.

  ReplyDelete
 7. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፣ በዓለም ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ቀድሞ ለተሐድሶ የአምላኳ ጥሪ የደረሳት ናት፡፡ by dekike Estifa new?

  ReplyDelete
 8. ተባረኩ የእግዚአብሔር የስራ ጊዜ ነውና በርቱ ብዙ ክርስቲያኖች ተሃድሶ የሚለው ስም ያስደነግጠዋል ግን እኮ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ሰዎች ሲያበላሹ በሃዋርያትም ዘመን ነበር መፀሐፍ ቅዱስን በደንብ በማስተዋል በልህይወት ብለን ካነበብን ምንም አዲስ ነገር እኮ የለም፡፡ በዚህች የኢትዬጵያ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ አያስፈልግም የሚል ከሰይጣን ካልሆነ በስተቀር የጌታን የመስቀሉን ነገር የሚያስብ ሁሉ ይፈልገዋል፡፡ የጌታ ነገር እየተሸፈነ የሰው ሀሳብ እየነገሰ ነውና፡፡ እናንተ ግን በርቲ በማስተዋል ጌታ ፀጋውን ያብዛላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 9. እነደ አሜባ በየጊዜው ለሚበጣጠሱት ለፕሮቴስታንት ዘመዶችህ ተሀድሶ እያልከ ንገራቸው እኛ ጋ አይሰራም ምኞት አይከለከልም እስኪሰለችህ ልፋ ለካ ሰይጣን ተስፋ አይቆርጥም

  ReplyDelete
 10. Ewnet new yehiwot tehadso kelay kalut abatoch jemiro yasfelgal geta iyesusin saywku yelkunim begeta saytawoku papas ,kes,diakon, sebKi, zemari, yehonu bezu nachewina.bertu endzeh yale tenkara melekt astelalfu.ahunim tehadso betkerstian yasfelgatal.

  ReplyDelete
 11. ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ አዲስ ናትና ልበ ስሁታንን እያስተማረች ታድሳለች እንጂ አትታደስም፣አትለወጥም ዘላለማዊት ናት፣ተሀድሶ የሚያስፈልገው የአንተ ልብ ነው መታደስ የሚያስፈልገውና የምንፍቅና ልብህ ይታደስ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ትጠራሃለች፡፡
  ተነሳሒ ልብ ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 12. thank you very much aba selama for this post. this is really very nice.

  ReplyDelete
 13. enante tehadsowoch

  ReplyDelete
 14. እናንተየ ይህ ተሐድሶ የምትሉት ለመሆኑ ዶግማዉን ነዉ ወይስ ቀኖናዉን ነዉ፡፡ የእናንተ የተሐድሶ አጀንዳ በቀጥታ ዶግማ ነክ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል፤ ዶግማ ደግሞ አይለወጥም አይታደስም፡፡ ሠርዓት ግን የደግማዉ ማስፈፀሚያ ስለሆነ አንደወቅቱ ሁኔታ እየታየ ሊታደስና ሊለወጥ ይችላል፤ ይህ የሚሆነዉ ግን እያንዳንዱ ግለሰብ እየተነሳ በራሱ ፈቃድ በመተዉ ወይም በመቀየር አይደለም፡፡ የእናንተን ስዉር የሚባል አይደለም ገሀድ የወጣ የምንፍቅና ስብከት ለመሸፋፈን ያደረጋችሁት ጥረት አሁንም ግልጽ ስለሆነ በዚህ አትምጡብን፡፡ በልባችሁ መታደስ መለወጥ ካለባችሁ አሁንም ቤተክርስቲያን በሯ ክፍት ስለሆነ ተመለሱ፡፡ አስተዋይ ልቦና ይስጣችሁ!

  ReplyDelete
 15. እናንተየ ይህ ተሐድሶ የምትሉት ለመሆኑ ዶግማዉን ነዉ ወይስ ቀኖናዉን ነዉ፡፡ የእናንተ የተሐድሶ አጀንዳ በቀጥታ ዶግማ ነክ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል፤ ዶግማ ደግሞ አይለወጥም አይታደስም፡፡ ሠርዓት ግን የደግማዉ ማስፈፀሚያ ስለሆነ አንደወቅቱ ሁኔታ እየታየ ሊታደስና ሊለወጥ ይችላል፤ ይህ የሚሆነዉ ግን እያንዳንዱ ግለሰብ እየተነሳ በራሱ ፈቃድ በመተዉ ወይም በመቀየር አይደለም፡፡ የእናንተን ስዉር የሚባል አይደለም ገሀድ የወጣ የምንፍቅና ስብከት ለመሸፋፈን ያደረጋችሁት ጥረት አሁንም ግልጽ ስለሆነ በዚህ አትምጡብን፡፡ በልባችሁ መታደስ መለወጥ ካለባችሁ አሁንም ቤተክርስቲያን በሯ ክፍት ስለሆነ ተመለሱ፡፡ አስተዋይ ልቦና ይስጣችሁ!

  ReplyDelete
 16. መታደስ አዎን ያስፈልጋል፡፡ በቤተክርስትያናችን መታደስ የሚችሉ መታደስም ደግሞ የማይቸሉ አሉ፡፡ አንተ በአብዛኛው ስለመታደስ እያነሳህ ያለኸው ስለሰው ህይወት ነው፡፡ ትክክል ነው በኃጥያት የዛለች ነፍስ በክርስቶስ ትታደስ ዘንድ ያስፈልጋታል፡፡ በዚህ አዎን ምዕመናን በንስሃ ታድሰው ክርስቶስን ሊለብሱ ይገባል፡፡ በሌላ በኩልም እንዲሁ ቤተክርስትያን አሰራሯን የሂሳብ አሰራርዋን የሰው ኃይል አስተዳደሯን ማሻሻል የሻታል፡፡ ይሄንንም እያልክ ከሆነ በዚህ ረገድ መታደስ ይገባል እልሃለኁ፡፡ ብሎጉ ግን ቤተክርስትያን በዚህ መልኩ አሰራሯን ማደስ አለባት ብለው ቀን ከሌሊት የአዲስአበባን አሰራር ሂደት ለማሻሻል ሲሰሩ የነበሩትን ማጥላላቱ ብሎጉ በዚህ ረገድ የቤተክርስትያን አሰራር መታደስ የሚዋጥለት አይመስልም፡፡ ሌላው መታደስ ይኖርበታል በሎ በሎጉ የተነሳው የቤተክርስትያኒቷን መሰረተ እምነት ነው፡፡ የሄ ዶግማ ዘመን ቢመጣ ዘመን ቢሄድ የማይለወጥ ነው፡፡ ይህንን የሚለውጥ ለመለወጥም የሚነሳ ቤተክርስትያኒቱን ትቶ መሄድ አለበት እንጂ የቤተክርስትያን አካል መሆን አይችልም፡፡ ብሎጉ መሰረተ እምነቱ የፕሮቴስታንት ሆኖ ሳለ ቤተክርስትያችን ተንጋዳ የፕሮቴስታንትን እምነት መቀበል አለባት የሚል ነውና ፕሮቴስታንታንታዊ ነው፡፡ በሎጉም ሆነ ጸሓፊውን የተንጋደደ እምነቱን ትቶ እምነቷን መቀበል አለዝያም እንደፕሮቴስታንቶች የራሱን ቤተእምነት መክፈት ወይንም ሌሎችን መቀላቀል እንጂ የቤተክርስትያን ነኝ ብሎ ማስመሰል አይኖረባቸውም፡፡

  ReplyDelete
 17. በዶግማ የምንጣላዉ የእመቤታችን አማላጅነት ዶግማ ነዉ ብላችሁ አበዉ በትምህርተ ሃይማኖታቸዉ ያስተማሩትን ያንጋደዳችሁ እናንተ መሆናችሁን አትርሱ አላችሁ ፕሮቴስታንት ማለተ ይቀናችሁዋል እነሱም ቢሆኑ እኮ እዉነቱን ካንሻፈፉ አንምራቸዉም አሁን ግን ከናንተ ተሽለዉ አግኝቼአቸዋለሁ

  ReplyDelete
 18. እነደ አሜባ በየጊዜው ለሚበጣጠሱት ለፕሮቴስታንት ዘመዶችህ ተሀድሶ እያልከ ንገራቸው እኛ ጋ አይሰራም ምኞት አይከለከልም እስኪሰለችህ ልፋ ለካ ሰይጣን ተስፋ አይቆርጥም

  ReplyDelete