Monday, January 20, 2014

“ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ በቃና ዘገሊላ” መድኃኒታችን በቃና ዘገሊላ ተአምርንና ድንቅን አደረገ

በየዓመቱ ጥር 12 ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ወር በገባ በ12 በዓለ ሚካኤል ነው ተብሎ ስለተወሰደ፣ በተጨማሪም ለጥምቀት በዓል ጥር 10 የወጣው የሚካኤል ታቦት ወደቦታው የሚመለሰው በ12 ስለሆነ በዓሉ የሚካኤል በዓል የሚመስላቸውም ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከዚህ ባሻገር በዓሉ ጌታ ውሃውን ወደወይን የለወጠበትና ክብሩን የገለጸበት ቢሆንም የጌታን ሳይሆን የማርያም አማላጅነት የታየበት ነው በማለት ተአምር ሰሪውን ጌታ ሳይሆን የማርያምን አማላጅነት ማጉላት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በዓሉ ጌታችንና መድኃኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀና የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በአብና በመንፈስ ቅዱስ ከተመሰከረለት በኋላ ያደረገውና ክብሩን የገለጸበት የመጀመሪያው ተአምር ነው፡፡

በቃና ዘገሊላ በተደረገው በመጀመሪያው ተአምር ምን ሆነ? በቃና ዘገሊላው ሰርግ ላይ የኢየሱስ እናት በዚያ እንደ ነበረችና ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ሰርጉ እንደታደሙ ዮሐ. 1፥1-2 ይናገራል፡፡ የወይን ጠጅ ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም ስትል ለጌታ ነገረችው፡፡ እርሱም “አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።”   ይህ አነጋገር የአክብሮትም የአርኅቆትም አነጋገር ነው፡፡ ልብ እንበል እናቱን “አንቺ ሴት” በማለት አክብሮ የጠራት ቢሆንም “እናቴ ሆይ” በማለት ፈንታ የሩቅን ሰው እንደሚያናግር “አንቺ ሴት” በማለቱ ደግሞ የሩቅ ሰው አድርጎ ነው ያናገራት፡፡ “አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?” ሲል የተናገረውም፥ በውስጡ “ምን አድርግ ትይኛለሽ?” የሚል መልእክት አዝሏል፡፡ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም” የሚለው ምክንያትም መልእክቱ ያዘለውን ሐሳብ ይበልጥ ያጎላል፡፡ ሆኖም ምላሹ አዎንታዊ በመሆኑ “እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።” ኢየሱስም በዚያ የነበሩትን ስድስት የድንጋይ ጋኖች በውሃ እንዲሞሉአቸው አዘዘና ሞሉአቸው፡፡ ከዚያ ለአሳዳሪው ቀድታችሁ ስጡት አለ፡፡ “አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።”

ከላይ እንዳልነው በዚህ ተአምር ውስጥ ማርያም “የወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል” ብላ ለኢየሱስ መናገሯ “ምልጃ” ነው ብለው የሚያስተምሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ አነጋገር ምልጃ ነወይ? ምልጃ የሚቀርበው በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ነው። እመቤታችን በጊዜው በሰርጉ ቤት የወይኑን ማለቅ ተመልክታ ለልጇ መንገሯ በጊዜው የነበረውን የዚያን ቤተሰብ ችግር ለማቃለል ያቀረበችው ጥያቄ እንጂ የምልጃ ጸሎት ሊባል አይችልም። ጌታም ለጥያቄዋ የሰጣት ምላሽ ጊዜዬ ገና አልደረሰም የሚል ነው፡፡ ስለዚህ የእርስዋን ጥያቄ ለማርያም አማላጅነት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ ፍጹም አላዋቂነት ነው፡፡

ስለምልጃ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ምን ይላል? ብዙዎች የሚያስቡት ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ባሉበት ሁኔታ እኛ ከዚህ ምድር ወደእነርሱ ስንጸልይ እነርሱ ጸሎታችንን ሰምተው ወደእግዚአብሔር እንደሚለምኑልን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፈጽሞ የተሳሳተ ልምምድና አምልኮተ ባእድ ነው፡፡ ቅዱሳን በአጸደ ስጋ ሳሉም ቢሆን ወደእነርሱ እንድንጸልይ አልታዘዝንም፤ ነገር ግን በአካል ያገኟቸው ሰዎች እንዲለምኑላቸው አሳስበዋቸው ወይም እግዚአብሔር ለምሳሌ አብርሃም ለአቢሜሌክ ኢዮብ ደግሞ ለባልንጀሮቹ (ዘፍ. 20፡7፤ ኢዮ. 42፡8) ይለምኑላችሁ ብሎ ተናግሮ እነርሱም ጸልይውላቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በተለይ ወደአንቀላፉ ቅዱሳን በአጸደ ሥጋ ያለ ማንኛውም የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሰው ወደ ቅዱሳን አማልዱኝ ብሎ እንዲለምን የታዘዘበትንና እርሱም የለመነበትን ስፍራ ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥቀስ አይቻልም፡፡ ብዙ ጊዜ ስለቅዱሳን ምልጃ ተብለው የሚጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱሳን ክፍሎች ቅዱሳን በአጸደ ሥጋ ሳሉ ያቀረቡትን የምልጃ ጸሎት ነው፤ ከዚህ ውጪ በአጸደ ነፍስ ሆነው ያቀረቡትን የምልጃ ጸሎት በማስረጃነት ማቅረብ አይቻልም፡፡ ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ሆነው ሊጸልዩ ቢችሉም እንኳ እኛ በአጸደ ሥጋ ያለን ይህን የምናውቅበት እድል ስለሌለንና ከእነርሱ ጋር የምንገናኝበት መሥመር ስላልተዘረጋልን ለምኑልን የምንልበት እድል ከቶ የለም፡፡ ስለዚህ ወደአንቀላፉ ቅዱሳን የምናቀርበው የአማልዱን ጥያቄ ሰሚ የሌለው ጩኸት ከመሆኑም ሌላ እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ እኛንም አላዋቂ የሚያሰኘን የስንፍና ተግባር ነው፡፡ የጌታ ቃል እንዲህ ሲልም ይዘልፈናል፤ “ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ ዕውቀት የላቸውም።” (ኢሳ. 45፡20)
  
ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት ውጪ የሚኖሩትን ሰዎች አስተሳሰብ ትተን የቤተክርስቲያን ትምህርት የሚለውን ብንመለከት ቅዱሳን በአጸደ ሥጋ ሳሉ እንደሚማልዱና በአጸደ ነፍስ ግን ማማለድ እንደሌለባቸው ምስክር እናገኛለን፡፡ “መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት” በተባለው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ተጽፏል፡፡ “ቅዱሳን ጻድቃን ያማልዳሉ ስለ ተባለ ግን ከላይ እንዳልነው በሕይወተ ሥጋ ሳሉ እግዚአብሔርን አገልግለው የተቀበሉት ቃል ኪዳናቸው እስከ ዕለተ ምጽአት ሲያማልድ ይኖራል ማለት ነው እንጂ እንደ ገና በአካለ ነፍስ መውጣት መውረድ መስገድ መጸለይ መለመን አለባቸው ማለት አይደለም። ... ሊቃውንትም ሰአሊ ለነ ቅድስት ያለውን ንባብ ሲተረጉሙ በቀደመ ልመናዋ የምታስተምር ስለ ኾነ ነው ይላሉ። ቃል ኪዳን ማለትም መሐልኩ በርእስየ ሕያው አነ ያለው ቃሉ ሕያው ሆኖ ከእነርሱ በኋላ ለሚነሡ ትውልዶች የሚያደርገውን ይቅርታና ቸርነት በመሐላው እንዳጸናላቸው ይኖራል ማለት ነው እንጂ ከሞቱ በኋላ ሲያማልዱ ይኖራሉ ማለት አይደለም።” (ገጽ 125-126)።

ልብ እንበል በውዳሴ ማርያም ላይ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” ወይም ቅድስት ሆይ ለምኝልን ሲባል አሁን እርሷ የምትለምን ሆና ሳይሆን በቀደመ ልመናዋ ማለትም በዚህ ምድር ሳለች የለመነችውን ልመና መሠረት በማድረግ እንደሆነ የሊቃውንቱ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡ ይህም ቢቸግር ነው እንጂ አሁን እርሷን ቅድስት ሆይ ለምኝልን ማለት ፈጽሞ አይገባም፡፡ ሊቃውንቱ በተሳሳተ መንገድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን የተባለውን ጸሎት በትርጉም በማቃናት የጸሎታችን አድራሻ እግዚአብሔር ብቻ እንዲሆን ማመላከታቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የሰማቸው የለም፡፡ እንደመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከሆነ መጸለይ ያለብን ወደአምላካችን ወደእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡

የቃና ዘገሊላ ተአምር የተደረገው በማርያም ምልጃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዕቅድና ሐሳብ ነው፤ ጌታ በዚያ የተገኘው ለሰርጉ ታድሞ ቢሆንም ወሃውን ወደ ወይን መለወጡ ክብሩን ለመግለጥና ደቀመዛሙርቱ በእርሱ እንዲያምኑ ለማድረግ ነው፡፡ በመጨረሻ የተገኘው ውጤትም “ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።” የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ታዲያ ከየት አምጥተን ነው የቃና ዘገሊላን ተአምር ከማርያም ምልጃ ጋር ለማያያዝ የምንሞክረው? ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንደሚባለው ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የጥቅስ ድጋፍ የሌለውን “የማርያምን ምልጃ” በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማስደገፍ የሚሞክሩት ወገኖች ጥቅስ ቢያጡ ከብዙ ጊዜ ጀምረው በዮሐንስ 2፡3-5 ላይ የማርያምን የምልጃ ትምህርት መስርተው ሲሰብኩ ኖረዋል፡፡ ይህንኑ አቋማቸውን በ2000 ዓ.ም በታተመው ሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲንጸባረቅ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቀውን ርእስ “ስለእናቱ ምልጃ” ብለው በመስጠት መጽሐፍ ቅዱስን በስሕተት ትምህርታቸው በርዘውታል፡፡ ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተፈጸመ እጅግ ትልቅ ድፍረትና ወንጀል ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ራሷን ልትፈትሽና ለእግዚአብሔር ቃል ትልቅ ስፍራ በመስጠት ልትታደስ ይገባታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቃለ እግዚአብሔርን ለራስ አስተምህሮ በሚስማማ መንገድ መተርጎም ከጀመረችና በዚሁ ከቀጠለች ውጤቱ የከፋ ይሆናል፡፡  

32 comments:

 1. jiloch jil bitagegnu...? Eneman Endehonachihu silawekinachihu ena Yewutet riketachihu Yet Endemikom lemawek nebiye Ayasfeligenim... Keberowoch Nachihu...

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔን የገረመኝ!! የጅል ብሎግ ማንበብህ ነዉ እስቲ በሞትህ ተንደርደረህ የምትከፍተዉ አንድ እዉነት ይኖረዋል ብለህ አይደለም? ታዲያ አሁን ጅሉ ማነዉ ?

   Delete
  2. ለነገሩ አንተ የሚመችህ የዳንኤል ክብረት የገድላት ስብስብ ብቻ ነው!

   Delete
  3. የዳንኤልን ገድላት የምትለዉ አንተ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ታውቀዋለህ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ በበርካታ የገድል ሥራዎች የተሞላ እንደሆነ ታውቃለህ፡፡ የአንተን የምንፍቅና ትምህርት ሳነብ ጊዜየን እንዳጠፋ በመፈለግህ አዝናለሁ፤ ከዳንኤል ጋር ራስህን ለማነፃፀር መሞከርህ ራሱ የትእቢትህን መጠን ያሳያል …

   Delete
  4. ልክ አንተ የጴንጤ ነገር እንደሚመችህ ማለት እኮ ነው:: እሱም ወደ ዳንኤል አንተም ወደ ጴንጤዎች ጋር ታዲያ ለምን አትሄድም:: ወሬኛ ጅል::

   Delete
  5. ወይ ሞኞ አሁን አንተ ዳንኤልን ሰው አድርገኸው ነው አይደል? የባለጌና የደንቆሮ ዘመዱ ብዙ ነው ይባላል። ዳንኤል እኮ በጉልበቱ ነው ሊቅ የሆነው። ከእሱ ጋር ለመነጻጻር መመዘኛው ደፋርና ባለጌ መሆን ብቻ ነው። አስተያየት የሰጠው ወንድም ከእሱ ጋር በመነጻጻር ደረጃውን ማሳነስ የሚፈልግ አይመስለኝም።

   Delete
 2. ግለጹት!!!
  1. “…ለልጁዋ መንገሩዋ በጊዜው የነበረውን የዚያን ቤተሰብ ችግር ለማቃለል ያቀረበችው ጥያቄ እንጅ የምልጃ ጸሎት አይባልም….” ‘ቀልቀሎ ስልቻ፣ስልቻ ቀልቀሎ’ ታዲያ ይሄ ጥያቄ ምልጃ ከመባል በቀር ምን ስም ይሰጠዋል???
  2. እሱ ‘በእሱዋ በኩል ለምን ጠየቃችሁኝ፣ራሳችሁ ቀጥታ ጠይቁኝ’ አላለ!!!ወይስ በአካለ ስጋ አብሩዋት ላለው ልጁዋና ፈጣሪዋ ቀጥታ ጥያቄዋን ከማቅረብ በቀር ገና በሞተ-ስጋ ሳይለያት ሱባኤ ገብታ በለሆሳስ እንድትለምነው ፈለክ???!!!
  3. አልፎ ተርፎስ ቅዱሳን በአካለ-ስጋ ሳሉ ያማልዳሉ እያላችሁ ትውልድ ሁሉ ብጽእት የሚሉዋት እመቤታችን በአጸደ-ስጋ ሳለች ልጁዋን ወዳጁዋን ለምና ማማለዱዋ ምን ይገርማል??
  4. በእመቤታችን ምልጃ የምናምን እኛ የኢኦተቤክ ምዕመናን ብቻ እንደሆንን ለማሳመን የምታደርጉት ጥረት ደግሞ ሁሌ ይገርመኛል!!!የድሮ ሚሽኖች የነዙትን ይዛችሁ ችክ አትበሉ!!!ከዓለም የክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ወደ 70% የሚጠጋው በእመቤታችንና በቅዱሳን አማላጅነት ያምናል!!!
  5. መ/ቅዱሳችንም ከጊዜ በሁዋላ የመጣውን የእንግሊዝኛ ቁዋንቁዋ ሳይሆን ጥንታዊውን የግእዝ ቁዋንቁዋ ተከትሎ ትክክለኛ ትርጉዋሜውን እንዲይዝ ነው የተደረገው!!ችግሩ ለእናንተ ከእንግሊዝኛ ያልተጣጣመ ሁሉ ከዐለም ያልተጣጣመ ይመስላችሁዋል!!!ብታውቁ ክርስትና ከእንግሊዝኛ ይልቅ ለግእዝ ይቀርባል!!እኛ ክርስትናን ስንቀበል እኮ እንግሊዞች እንኩዋን ሊጠመቁ ግርዘትም የማያውቁ አህዛብ ነበሩ!!እባካችሁ ዓይናችሁን ለታሪክ ሲሆን እንኩዋ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hiruy, bertaln menafikin endih eyeteketatelu af afun kalalut yewahochin yisetkal.

   Delete
  2. ስለእግዚአብሔር አንድ ጥያቄ ልጠይቅ፡፡ ማንም ሊመልስልኝ ከቻለ ወሮታዉን እከፍላለሁ፡፡ ጌታችን በወንጌሉ በስሜ አንዳች ነገር ብትጠይቁ አባቴ የሰጣችሁዋል፡፡ ለምኑወይም እሹ ታገኛላችሁ፡፡ ደጅ ምቱ ይከፈትላችሁዋል፡፡ ብሎ እንዲያዉም ባለመጠየቃችን ያጣነዉን በረከት ይናገራል ታዲያ ምን ሆነን ነዉ የጥሪ መሥመራችንን አስረዝመን ሙታንና ሕያዋንን አማልዱን የምንለዉ?ልብ በሉልኝ እኔ ሰለሙታናና ስለሕያዋን አማላጅነት ለመከራከር ሳይሆን ጌታችንን ምን ጠይቀን አጥተን ነዉ በሌላ ሰዉ በኩል ደጅ ጥናት ያስፈለገን? ይህንን በመጠየቄ ቀና መልስ እንጂ የተለመደዉን ቀረርቶ መስማት አልፈልግም

   Delete
  3. more like for Hibst ! Bertolihsal anchima....

   Delete
  4. እህት ህብስቴ በጽሁፉ ከቀረበው እንኩዋ ብትነሽ እሱ ራሱ ምሬያችሁዋለሁ ማለት ሲችል በዘፍ 20 ቁ 7 አቤሜሌክን “አብርሃም ይጸልይልህ”፣በኢዮ 42 ቁ 8 ደግሞ የኢዮብን ባለንጀሮች “ኢዮብ ይጸልይላችሁ” ያላቸው ለምን ይመስልሻል??አጠረም ረዘመም እሱ አድርጉት ካለ መከተል ነው!!ዕምነት ሎጂክ አይደለማ!! ለማንኛውም “የጻድቅ ጸሎት ሀይልን ታደርጋለች” የሚለው ጥቅስ የት ነበር የሚገኘው ለእኔ መልሱ እሱ ነው!!!ፈለጊውማ….

   Delete
 3. ለካ እንዲህ አይነት ከሀዲያንናችሁ እንክዋን አወቅናችሁ!

  ReplyDelete
 4. አንባቢው ያስተውል

  ReplyDelete
 5. ይህ ትምህርት ሳይሆን ነቀፋ ነው፡፡ ክርስቶስ እኮ እናት አባትህን አክብር ይላል እርሱ ባያከብራት ኖሮ አክብሩ አይለንም ነበር፡፡ በቃና ዘገሊላ ውሀውን ወደ ወይን ጠጅ ያስቀየረችው ድንግል ማርያም ናት፡፡ የውስጣቸውን ጭንቀት አውቃ ያማለደቻቸው የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡

  †እመቤቴ ሆይ መናፍቃንንና አህዛብን አስታግሽልን፡፡†

  ReplyDelete
 6. thank you Hiruy. God be with you.

  ReplyDelete
 7. Betam yemegeremew be beteketsteyan teketetew demos yeblalu protestantum yekefeluachewal degemo megeremew sehafeyanu yetewrsenut kalhone denakurt nachew age sekefet......

  ReplyDelete 8. yale ewket zeme blachew ende geza semetachew atletatifu wodage gena bizu memare yalebhe yemeslechal

  ReplyDelete
 9. ጅል ማለት አንድዋ እኔው ነኝ የቤንጤን ብሎግ ከፍቸ የማነብ። ያልገባኝ ?ለምን ሙስሌሞችን ካቶሊኯችን አሳምናችሁ ልትቀይሩ አትሞክሪም ? አንድም እንኳ!
  የድንግል ማርያም ልጅ ይቅር ይበላችሁ።

  ReplyDelete
 10. አስደናቂ ማብራሪያ ነው! ግሩም ብዬዋለሁ! እውነትን ለሚፈልግ እና ለሚጠማ የነፍሱንም ጩኸት ለማዳመጥ ፈቃደኛ ለሆነ በተለይም በዚህ ወሳኝ እና አስጨናቂ በሆነ በዘመኑ ፍፃሜ የሕይወትን መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስን) ለሚያነብ ሰው ያለምንም ጥርጥር በቂ ማሳሰቢያ ነው የቀረበው፡፡እንዲሁ በጭፍን ያለ ምንም እውቀት በ”መንፈሳዊ ቅንዓት” በመነሳሳት በፈሪሳዊያን መንፈስ በመሞላትና ልብን ጠርቅሞ በመዝጋት ለመከላከል መሞከር ጥሩ አይደለምና አንተ ትውልድ የመንቂያውን ደወል ድምፅ ቸል አትበል! እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል እንደሚል ቃሉ ሁላችንም በዚህ እውነት አርነት እንድንወጣ ጥርዬን አቀርባለሁ፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

  ReplyDelete
 11. እኔ የገረመኝ ተአምሩን ማሳየትና በሱ አንድአምኑ ብቻ ከፈለገ ከሆነ የ አመቤታቺን ጌታን መጠየቅ ለምን አስፈለገ .....አርሱ አራሱ ያለማንም ጠያቂነት አና አሳሳቢነት ለምን አላደረገውም ነበር .....አንዲሁ አራሳችሁ ከራሳችሁ ጋር አንኩአ መስማማማት አትችሉም አስኪ በንፁህ ልብ ጌታን ለምኑት አንዲገልጥላችሁ ....ዝም ብላችሁ የጥመትን (የዲአብሎስን ) ጎዳና አትመላለሱበት.......

  ReplyDelete
 12. ከካዱ ላይቀር እንዲህ ነው የበግ ለምድ ለባሾች ፡፡

  ReplyDelete
 13. የቅዱሳን አማላጅነት እና የኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ልዩነት!!

  አንዳንድ ወንድሞች ነገረ ቅዱሳንን ከነገረ ክርስቶስ ጋር ይቀላቀልባቸዋል፡፡ከሚያነሱዋቸው ሐሳቦች አንዱና ዋነኛውም “ጻድቃን፣ ሰማዕታት እና ቅዱሳን መላእክት ብቃት ያላቸው አማላጆች አይደሉም፤ ይልቁንም ብቃት ያለው አማላጅ (ጠበቃ) ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው” የሚል ይገኝበታል፡፡ነገር ግን ወንድሞቼ የክርስቶስ መካከለኛነትና የቅዱሳን አማላጅነት ልዩነቱ የገባቸው አይመስልም፡፡
  ቤተክርስቲያናችን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በመላእክትና በቅዱሳን አማላጅነት ታምናለች፣ ታስተምራለችም፡፡ ይኼንን ትምህርት የማያምኑ ወንድሞቻችን ግን ለ“ትምህርታቸው” እንደ ማስረጃ ከሚያቀርቡዋቸው ጥቅሶች መካከል “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፣ እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /1ዮሐ.2፡1/” እና “በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም ሰው የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /1ጢሞ.2፡5/” የሚሉ ይገኙበታል፡፡
  ቤተክርስቲያናችን በእነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦች ላይ ያላት እምነት የሚከተለውን ነው፡፡

  1. የኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃነትና የቅዱሳን ጠበቃነት ፈጽመው የማይገናኙ ነገሮች ናቸው፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃችን ነው” ስንል አስታራቂነቱን ፣ ቤዛነቱን መናገራችን ነው፡፡ይህም ማለት እያንዳንዳችን በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ገዛ መንገዳችን ስናዘነብል ጌታ የሁላችንን በደል በመሸከም ዕዳችንን ከፍሎ ከአባቱ ጋር ጠበቃ በመሆን አስታርቆናል /ኢሳ.53፡6/፡፡ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ብቸኛው መካከለኛ (ወልድ ዋሕድ) ነው፡፡አባቱን ያረካ ብቸኛው መሥዋዕት በመሆንም ለምናምን ለኛ በእኛ ፈንታ በመሞት ጠበቃ ሆነልን፡፡ስለዚህ “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን”፡፡ምክንያቱም ከየትኛውም ዐይነት ኃጢአት መንጻት የምንችለው በጻድቁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነውና፡፡

  የቅዱሳን አማላጅነት ግን ኃጢአትን ከማንጻት እና ከቤዛነት ጋር ፈጽሞ የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡እነሱ መካከለኛም አይደሉም ፤ ሊሆኑም አይችሉም፡፡እነሱ መካከለኛ መሆን ቢችሉ ኖሮ በእነ ይስሐቅ፣ በእነ ኢሳይያስ ፣ በእነ ድንግል ማርያም አማካኝነት በዳንን ነበር፡፡ የእነሱ አማላጅነት በእኛ ፈንታ በክርስቶስ ፊት የሚያቀርቡት ጸሎት ብቻ ነው፡፡ምናልባት ከእናንተ መካከል “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው /ሮሜ.8፡34 እና ዕብ.7፡25/ ተብሎ በደማቅ ቀለም ተጽፎአል” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡እውነት ነው!! ነገር ግን ይህንን ሐሳብ ለመረዳት መጀመርያ የኢየሱስ ክርሰቶስ ሊቀካህንነትን ማወቅ ይጠይቃል፡፡

  የብሉይ ኪዳኑ ሊቀካህን በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት በመግባት ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፡፡ይህም ማለት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ሰዓት ስለ ሕዝቡም ይማልድ ነበር፡፡የሐዲስ ኪዳኑ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፡፡ስለዚህ “ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል” ሲባል ዛሬውኑ ተሰቅሎ ያድናል ማለት እንዳልሆነ ሁሉ “ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳል” ሲባልም በመስቀል ላይ ሆኖ “ጌታ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ያለው ቃል ዛሬ ለእኛም ይሠራል ማለት ነው እንጂ አሁንም ይማልዳል ማለት አይደለም፡፡ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “ሊቀ ካህናት ሲል ብትሰማው ዘወትር የሚያገለግል አይምሰልህ፤ ራሱን አንድ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋ …(ጳውሎስ) ሁል ጊዜ ቆሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ … ራሱን አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡አንድ ጊዜ ሰው እንደሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፤ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ባገለገለም ጊዜ በማገልገል ሥራ ጸንቶ አልኖረም /የዕብራውያን መልእክት ትርጓሜ ድርሳን 13፡184-190/” ብሎአል፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሁል ጊዜ ይለምናል” ብሎ ማሰብ ክብር ይግባውና ጌታን ደካማ ማድረግ ነው፡፡ምክንያቱም እንደኛ ኃይል የሌለው ነው ሁል ጊዜ የሚለምነው፡፡ አንድም ባለማወቅ ሁል ጊዜ እሱን መስቀል ነው፡፡

  2. የቅዱሳን አማላጅነት ከኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ፍጹም የተለየና ጸሎት ብቻ እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ይህን ዐይነቱ ጸሎት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ የሚደግፈው ጸሎት ነው፡፡ “እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ /ያዕ.5፡16/” እንዲል፡፡ ቅዱሳን ራሳቸው “ስለኛ ጸለዩ /1ተሰ.3፡1፣ ዕብ.13፡18 ኤፌ.6፡18/” ብለዋል፡፡ታድያ እነሱ እንኳን የእኛ ጸሎት እየፈለጉ እኛ የእነሱን አንፈልግም እንበልን? እንደኛ ተጋድሎአቸውን ያልጨረሱ ወንድሞቻችንን እንኳን እንዲጸልዩልን እየጠየቅን “ከመውጣቴም (ከመሞቴም) በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ /2ጴጥ.1፡15/” ያሉንንና በገነት ከክርስቶስ ጋራ ያሉትን ቅዱሳን እንዲጸልዩልን መጠየቅ አይገባንምን? ከምድር ወደ ገነት ከሄዱ በኋላስ ይህን ባለሟልነታቸው አጥተውታልን? ወይስ “የእነሱን ጸሎት መጠየቅ የሚቻለው ወደ ክርስቶስ እቅፍ ከሄዱ በኋላ ሳይሆን በዚህ ምድር ሳሉ ብቻ ነው” ተብሎ ተነግሮናል? ሰዎች እንዲጸልዩልን ከጠየቅንስ መላእክትን መጠየቅ አይገባምን?

  3. እግዚአብሔር ፃድቅ የሆኑ ሰዎች ስለ ሌሎች ይማልዱ ዘንድ ጠይቆአል፤ እንደሚችሉ አረጋግጦኣል፤ ይህ እዲደረግም ፈቅዶአል፡፡ለምሳሌ፡ አብርሃም ስለ አቤሜሌክ፣ ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ፣ አብርሃም ስለ ሰዶም ሰዎች፣ ሙሴ ስለ ሕዝበ እስራኤል ያቀረቡት ምልጃ ይጠቀሳል፡፡እነዚህ በምደር ሳሉ ያቀረቡት ምልጃ ሲሆን ወደ ገነት ከሄዱ በኋላ ያቀረቡ ደግሞ ዳዊት ስለ ሰሎሞን /1ነገ.11፡12-13፣31-34፣ መዝ.132፡10/፣ ጴጥሮስ ስለ ምእመናን /2ጴጥ.1፡15/፣ ሰማዕታት መከራ ስለሚደርስባቸው ምእመናን /ራዕ.6፡10/…ይገኙበታል፡፡
  ጸሎት ብቻ የሆነው የቅዱሳን አማላጅነት እንደ ጥብቅና ከተቆጠረ እና ምንም ተቀባይነት የሌለው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው ስለሌላው የሚጸልየው ጸሎትም አላስፈላጊ ጥብቅና ነው፡፡
  ይህ ግን ፈጽሞ የተሳሳተ አካሄድ እና እንግዳ ትምህርት ነው፡፡እግዚአብሔር እያንዳንዱ አማኝ (ከዚህ ምድር የተለየውም ያልተለየውም) ስለሌላው እንዲጸልይ የፈቀደው አንዱ ለሌላው ያለውን ፍቅር የሚገልጽበት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ በዚህ ምድር ያለንና በገነት ያሉት የክርስቶስ ብልቶች በጸሎት ድልድይ እንገናኛለን፡፡
  ስለዚህ የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለችና፤
  የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ እግዚአብሔር ይህን ዐይነት ጸሎት ፈቅዶአልና፤
  በቅዱሳን አማላጅነት እናምናለን፣ የሚመጣውን ሕይወት እናምናለንና፤ እነሱም ሕያዋን ናቸውና፤
  በቅዱሳን አማላጅነት እናምናለን፣ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንድነት እናምናለንና፤ ሁላችንም (ከዚህ ምድር የተለዩትም ያልተለየንም) የአንድ ክርስቶስ ብልቶች እንደሆንን እናምናለንና!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. you stated very well, but many didnot have an understanding on those differences(yekirstos amalajinet ena ye tsadikan milja)
   ነገ   ቃ ከሞቱ በላ ደሚያማዱ የሚያሳ ቀ ዮሆነ መሀ ዱሳዊ ማሰረጃ ይሰ!

   Delete
 14. የኢየሱስን አማላጅነት ወይም አስታራቂነት የሚናገሩ ኃይለ ቃሎች
  - ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ። ኢሳ 53፡12 (አስታራቂነቱ ከልደቱ አስቀድሞ በትንቢት ተነግሮናል ማለት ነው)

  - እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃ 22፡32 (በተዋሕዶ በከበረው ሥጋዊ አካል በመሃላችን በኖርበት ዘመን አብን እየለመነ እንደ አማለደ የሚያስረዳን ነው)፡፡

  ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ቃሎች በአንድነት የሚብራሩ ስለሆኑ ቃሉን በአጠቃላይ ለመረዳት ሁሎችንም በአንድነት እናነባለን ፤
  1 - እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሮሜ 8፡33-34

  - “እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤” ዕብ 5፡7

  እንደ ቃሉ በትንቢት የተነገረውን የአማላጅነት ወይም የአስታራቂነት ሥራ ከጽንሰት እስከ መስቀለ ሞት በመጓዝ ኢየሱስ ፈጽሞ መደምደሙን ያስረዳል ፡፡ ይህንንም በዕብራውያን መልዕክቱ በሚዳሰስና በሚታይ አካል በነበረበት ጊዜ እንደፈጸመው ሲያስረዳን በስጋው ወራት በማለት ገልጾታል ፡፡ ኢየሱስ አሁን ፣ ከትንሣዔውና ከእርገቱ በኋላ ማለት የአዳምን በበደል የወደቀ ሥጋ አክብሮ ፣ ወደ ጥንት መንበሩ ተመልሶ ፣ ዳግም ለመምጣትና ለመፍረድ ዝግጅት ላይ ነው ፡፡ እንህ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ያለው (ማር 16፡19 ፤ ማቴ 26፡64 ፤ሉቃ 22፡69 ፤ ሥራ 2፡33 ፣7፡55-56 ፤ ቆላ 3፡1 ፤ ዕብ 1፡3 ፣ 8፡1 ፣ 12፡1-2 ፤ 1 ጴጥ 3፡22 ) የሚሉት ቃሎች በክብር ዙፋኑ በእኩልነት ለመፍረድና ይቅር ለማለት ዝግጅት ላይ መሆኑን ያስተምራሉ ፡፡

  ነገር ግን በጌታ የቀረበው መስዋዕት (ዕብ 13፡12) ዘለዓለማዊ ስለሆነ (ዕብ 7፡17፡24 ፣ 9፡12 ፣ 1ዐ፡1ዐ፡12)፣ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደምና ያቀረበው ሥጋ ፣ ላላመኑና ኢየሱስን ላልተቀበሉ ሁሉ ፣ ዓይናቸው ተገልጦ በሚያምኑ ጊዜ ይድኑበት ዘንድ ግን ዛሬም ሕያው መስዋዕት ሆኖ ይታይላቸዋል (ዕብ 7፡25 ፣ 9፡28)፡፡ ከሞተ በኋላ በጦር ጎኑ ሲወጋ ደም የፈሰሰበት ምሥጢር ፣ ሕያው መስዋዕታችን መሆኑን ያስረዳል ፡፡ ኢየሱስን አምነን ክርስቲያን የተባልን ሁሉ ከርሱ ጋር አንድነትንና ኀብረትን የመሠረትን ስለሆነ ከየዕለት ድክመታችንና በደላችን የምንታደሰው በንስሓና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያዘውንን በመፈጸም ነው ፡፡ “ስርየት ባለበት ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም” ይላልና ወደ እቅፉና ርሱ ጥበቃ ሥር ከገባን በኋላ ተደጋጋሚ መስዋዕትነቱን ፤ ምልጃውን አንጠብቅም ፤ ዕብ 1ዐ፡18 ። ኢየሱስ አማላጅ ሳይሆን ይቅር ባይ አምላካችን ነው ብለን እናምናለን ፡፡

  ይህንኑ መጽሐፍ ሲያብራርልን ፣ ዕርቁንም ፈጽሞ የጥል ግድግዳው መፍረሱን ሲያበስረን “አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤ በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።(ኤፌ 2፡13 – 22)” ይላል ፡፡

  ይህንንም አንብበው የጥል ግድግዳውን ከፊት ለፊታቸው ያኖሩ ካሉ ግን አሁንም ዘለዓለማዊ መስዋዕቱ ስላለላቸው በእምነት በመቅረብ ድኀነታቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ፤ ዕርቁም ይፈጸምላቸዋል ፡፡ በክርስቶስ ነው ያለነው እያሉን አሁንም አማላጅነቱን የሚያምኑና በየዕለቱ የሚጠብቁ ካሉ እውነትም ሃቅን እንዳያስተውሉ ግድግዳው ተጋርዶባቸዋል ማለት ይቻላል ፡፡

  ሥላሴ አንድ መለኮት ፣ አንድ ፈቃድ ፣ አንድ ሥልጣንና ባህርይ ስላላቸው ለአዳም ትውልድ ምሕረትን ለማምጣት ተስማሙ እንጅ በመሃላቸው መከፋፈል ያለ አስመስሎ አንደኛውን ዘላለማዊ ለማኝና አማላጅ ፣ የተቀረውን ደግሞ ተቀያሚ ወይም አኩራፊ ፣ ይቅር ለማለት የማይፈልግ ማድረግ የዶግማን ተፋልሶ ያስከትላል ፡፡ አማለደ የተባለውም በአዳም ላይ የተላለፈ ፍርድን ለመፈጸምና ለማስታረቅ ጌታችን ሰው መሆኑንና ዕዳችንን ለመክፈል ሞታችንን ሞቶ ፣ እኛን ነጻ ማውጣቱን ነው ፡፡ ዕዳችንን በመክፈል ፣ ቤዛነቱን ለማለት ፡፡

  አንድ ሰው የሚታረቀውና ይቅር የሚባለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡ ነጋ ጠባ ሲታረቅና ይቅር ሲባል አይኖርም ፡፡ በተለይም በሃይማኖት ሲሆን ደግሞ ከፈጠረን አምላክ ያለያየን አዳም የተሰጠውን ትእዛዝ አማክበሩ ነው ፡፡ ይህን ጸብ ጌታችን በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶና ሥጋውን ቆርሶ ፣ ሕይወቱንም አሳልፎ ሰጥቶ የልዩነት ግድግዳውን አፍርሶታል ፡፡ ክቡር ሕይወቱን ስለ እኛ ፍርድ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ዕርቁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተፈጽሟል ፡፡ ማስታረቁን ላመኑት ሰዎች ፣ የውርስ በደላቸውም ሆነ ፣ እርሱን እስከ አመኑበት ዕለት የፈጸሙት ኃጢአት ይሻርላቸዋል ፤ ሌሎች ወደፊት የሚመጡት ትውልዶች ደግሞ ሕያው መስዋዕት ስለሆነ ካመኑበት ሊድኑበት ዘላለም ይኖራል ፤ ይህ ትውልድ በእምነት ድኀነትን እንዳገኘ ሁሉ ፣ ከመቶና ሺህ ዓመትም በኋላ የሚያምነው ህዝብ በቀራንዮ መስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙና በተቆረሰ ሥጋው ድኀነትን ያገኛል፡፡ ዕብ 7፡24-25

  ሁሉንም ለመረዳት ጌታችን ሰው መሆን ያስፈለገው ፣ በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ ያስገደደውን በደል ለይተን ማወቅ ጠቃሚ ነው ፡፡ ምክንያቱም ጻድቃን እንደነበሩ መጽሐፋችን ይናገራል ፡፡ እኒህ ጻድቃን ፣ ቅዱሳን ነቢያት የተባሉ ሁሉ ራሳቸውን ከሥጋዊ በደል ቢጠብቁም ፣ ከአዳማዊው በደል ማለትም ከጥንተ አብሶ ግን ራሳቸውን ማጽዳትና ነጻ ማድረግ አልቻሉም ፡፡ የኢየሱስም ወደ እዚህ ምድር በሥጋ መምጣት ይኸን በሰዎች ሊወገድ ያልተቻለውን ኃጢአት ፣ ካሳውን ከፍሎ ለመሻር ነው ፡፡

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡

  ReplyDelete
 15. የኢየሱስን አማላጅነት ወይም አስታራቂነት የሚናገሩ ኃይለ ቃሎች
  - ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ። ኢሳ 53፡12 (አስታራቂነቱ ከልደቱ አስቀድሞ በትንቢት ተነግሮናል ማለት ነው)

  - እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃ 22፡32 (በተዋሕዶ በከበረው ሥጋዊ አካል በመሃላችን በኖርበት ዘመን አብን እየለመነ እንደ አማለደ የሚያስረዳን ነው)፡፡

  ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ቃሎች በአንድነት የሚብራሩ ስለሆኑ ቃሉን በአጠቃላይ ለመረዳት ሁሎችንም በአንድነት እናነባለን ፤
  1 - እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሮሜ 8፡33-34

  - “እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤” ዕብ 5፡7

  እንደ ቃሉ በትንቢት የተነገረውን የአማላጅነት ወይም የአስታራቂነት ሥራ ከጽንሰት እስከ መስቀለ ሞት በመጓዝ ኢየሱስ ፈጽሞ መደምደሙን ያስረዳል ፡፡ ይህንንም በዕብራውያን መልዕክቱ በሚዳሰስና በሚታይ አካል በነበረበት ጊዜ እንደፈጸመው ሲያስረዳን በስጋው ወራት በማለት ገልጾታል ፡፡ ኢየሱስ አሁን ፣ ከትንሣዔውና ከእርገቱ በኋላ ማለት የአዳምን በበደል የወደቀ ሥጋ አክብሮ ፣ ወደ ጥንት መንበሩ ተመልሶ ፣ ዳግም ለመምጣትና ለመፍረድ ዝግጅት ላይ ነው ፡፡ እንህ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ያለው (ማር 16፡19 ፤ ማቴ 26፡64 ፤ሉቃ 22፡69 ፤ ሥራ 2፡33 ፣7፡55-56 ፤ ቆላ 3፡1 ፤ ዕብ 1፡3 ፣ 8፡1 ፣ 12፡1-2 ፤ 1 ጴጥ 3፡22 ) የሚሉት ቃሎች በክብር ዙፋኑ በእኩልነት ለመፍረድና ይቅር ለማለት ዝግጅት ላይ መሆኑን ያስተምራሉ ፡፡

  ነገር ግን በጌታ የቀረበው መስዋዕት (ዕብ 13፡12) ዘለዓለማዊ ስለሆነ (ዕብ 7፡17፡24 ፣ 9፡12 ፣ 1ዐ፡1ዐ፡12)፣ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደምና ያቀረበው ሥጋ ፣ ላላመኑና ኢየሱስን ላልተቀበሉ ሁሉ ፣ ዓይናቸው ተገልጦ በሚያምኑ ጊዜ ይድኑበት ዘንድ ግን ዛሬም ሕያው መስዋዕት ሆኖ ይታይላቸዋል (ዕብ 7፡25 ፣ 9፡28)፡፡ ከሞተ በኋላ በጦር ጎኑ ሲወጋ ደም የፈሰሰበት ምሥጢር ፣ ሕያው መስዋዕታችን መሆኑን ያስረዳል ፡፡ ኢየሱስን አምነን ክርስቲያን የተባልን ሁሉ ከርሱ ጋር አንድነትንና ኀብረትን የመሠረትን ስለሆነ ከየዕለት ድክመታችንና በደላችን የምንታደሰው በንስሓና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያዘውንን በመፈጸም ነው ፡፡ “ስርየት ባለበት ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም” ይላልና ወደ እቅፉና ርሱ ጥበቃ ሥር ከገባን በኋላ ተደጋጋሚ መስዋዕትነቱን ፤ ምልጃውን አንጠብቅም ፤ ዕብ 1ዐ፡18 ። ኢየሱስ አማላጅ ሳይሆን ይቅር ባይ አምላካችን ነው ብለን እናምናለን ፡፡

  ይህንኑ መጽሐፍ ሲያብራርልን ፣ ዕርቁንም ፈጽሞ የጥል ግድግዳው መፍረሱን ሲያበስረን “አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤ በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።(ኤፌ 2፡13 – 22)” ይላል ፡፡

  ይህንንም አንብበው የጥል ግድግዳውን ከፊት ለፊታቸው ያኖሩ ካሉ ግን አሁንም ዘለዓለማዊ መስዋዕቱ ስላለላቸው በእምነት በመቅረብ ድኀነታቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ፤ ዕርቁም ይፈጸምላቸዋል ፡፡ በክርስቶስ ነው ያለነው እያሉን አሁንም አማላጅነቱን የሚያምኑና በየዕለቱ የሚጠብቁ ካሉ እውነትም ሃቅን እንዳያስተውሉ ግድግዳው ተጋርዶባቸዋል ማለት ይቻላል ፡፡

  ሥላሴ አንድ መለኮት ፣ አንድ ፈቃድ ፣ አንድ ሥልጣንና ባህርይ ስላላቸው ለአዳም ትውልድ ምሕረትን ለማምጣት ተስማሙ እንጅ በመሃላቸው መከፋፈል ያለ አስመስሎ አንደኛውን ዘላለማዊ ለማኝና አማላጅ ፣ የተቀረውን ደግሞ ተቀያሚ ወይም አኩራፊ ፣ ይቅር ለማለት የማይፈልግ ማድረግ የዶግማን ተፋልሶ ያስከትላል ፡፡ አማለደ የተባለውም በአዳም ላይ የተላለፈ ፍርድን ለመፈጸምና ለማስታረቅ ጌታችን ሰው መሆኑንና ዕዳችንን ለመክፈል ሞታችንን ሞቶ ፣ እኛን ነጻ ማውጣቱን ነው ፡፡ ዕዳችንን በመክፈል ፣ ቤዛነቱን ለማለት ፡፡

  አንድ ሰው የሚታረቀውና ይቅር የሚባለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡ ነጋ ጠባ ሲታረቅና ይቅር ሲባል አይኖርም ፡፡ በተለይም በሃይማኖት ሲሆን ደግሞ ከፈጠረን አምላክ ያለያየን አዳም የተሰጠውን ትእዛዝ አማክበሩ ነው ፡፡ ይህን ጸብ ጌታችን በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶና ሥጋውን ቆርሶ ፣ ሕይወቱንም አሳልፎ ሰጥቶ የልዩነት ግድግዳውን አፍርሶታል ፡፡ ክቡር ሕይወቱን ስለ እኛ ፍርድ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ዕርቁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተፈጽሟል ፡፡ ማስታረቁን ላመኑት ሰዎች ፣ የውርስ በደላቸውም ሆነ ፣ እርሱን እስከ አመኑበት ዕለት የፈጸሙት ኃጢአት ይሻርላቸዋል ፤ ሌሎች ወደፊት የሚመጡት ትውልዶች ደግሞ ሕያው መስዋዕት ስለሆነ ካመኑበት ሊድኑበት ዘላለም ይኖራል ፤ ይህ ትውልድ በእምነት ድኀነትን እንዳገኘ ሁሉ ፣ ከመቶና ሺህ ዓመትም በኋላ የሚያምነው ህዝብ በቀራንዮ መስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙና በተቆረሰ ሥጋው ድኀነትን ያገኛል፡፡ ዕብ 7፡24-25

  ሁሉንም ለመረዳት ጌታችን ሰው መሆን ያስፈለገው ፣ በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ ያስገደደውን በደል ለይተን ማወቅ ጠቃሚ ነው ፡፡ ምክንያቱም ጻድቃን እንደነበሩ መጽሐፋችን ይናገራል ፡፡ እኒህ ጻድቃን ፣ ቅዱሳን ነቢያት የተባሉ ሁሉ ራሳቸውን ከሥጋዊ በደል ቢጠብቁም ፣ ከአዳማዊው በደል ማለትም ከጥንተ አብሶ ግን ራሳቸውን ማጽዳትና ነጻ ማድረግ አልቻሉም ፡፡ የኢየሱስም ወደ እዚህ ምድር በሥጋ መምጣት ይኸን በሰዎች ሊወገድ ያልተቻለውን ኃጢአት ፣ ካሳውን ከፍሎ ለመሻር ነው ፡፡

  ReplyDelete
 16. ቀደም ያሰፈርኩትን መልስ የሚያጠናክር ወይም የሚያሟላልኝ ስለሆነ ሽመልስ መርጊያ የተባሉ ወንድም በሌላ ገጽ ላይ ሲያስተምሩ ካሰፈሩት ተወስዷል ፡-

  “ክርስትና በሞት የምትቋጭ አይደለችም፡፡ እንደውም እኛ ከክርስቶስ ጋር ሞተን በትንሣኤው በመነሣት በሰማያዊ ሥፍራ ውስጥ አለን ፡፡ አሁን እኛ በጻድቃን ጉባኤ ውስጥ ነን፡፡ ክርስቶስ በሰጠን ሕይወት ውስጥ ሞት የለም የሥጋ ሞት ከቅዱሳን ነፍሳት ጋር ያለንን ሕብረት ፍጹም ያደርገዋል እንጂ አያቆራርጠውም፡፡ ሕይወታችንም መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ቆየ፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ “በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን”(ኤፌ.2፡8) እንዲሁም “እንግዲህ ከተነሣችሁ በክርስቶስ በእግዚብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም ፡፡ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፡፡”(2ቆላ.3፡1-3) እንዲሁም “ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም በደስታም ወደ ተሰባሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት በሰማያት ወደ ተጻፉ የበኩራት ማኅበር የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሚሆነው ወደ ኢየሱስ ደም ከአቤልም ደም ይለቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል፡፡”(ዕብ.12፡22-24)ይለናል፡፡ ደርሳችኋል ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ሥፍራ ነው ያላችሁት ማለቱ አይደለምን? አንድ ሥፍራ መሆን ብቻ አይደለም “ከእንግዲህ ከቅዱሳን ጋር ባለአገሮች ናችሁና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም፡፡”(ኤፌ.2፡19) ይለናል፡፡ ስለዚህ ቤተሰብ ለቤተሰቡ አባል ማሰቡ ተገቢ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ያለበለዚያ ከአመነም ሰው ይልቅ የከፋ ነው (1ጢሞ.5፡8) ፡፡በእነዚህ ሁሉ መስረጃዎች እኛ ከቅዱሳን ሕብረት ውስጥ እንዳለን ተነግሮአል፡፡ እነዚህ ቅዱሳንም “የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡(ራእ.20፡6) የተባለላቸው ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው ደግሞ የክህነት ሥልጣን በከንቱ አይሰጥም፡፡ ይህ ሁሉ ማስረጃዎች በዙሪያችን አሉ፡፡ ስለዚህ በጥምቀት የተመሠረተውን ሕብረትና አንድ ቤተሰብ መሆንን የሥጋ ሞት አይቆርጠውም እንደውም ይበልጥ ያጠናክረዋል፡፡ ለእናንተ የሥጋ ሞት ትልቁ ቁምነገራችሁ ነው፡፡ ምክንያቱም ገና ሥጋዊያን ናችሁና፡፡ በክርስቶስ የጥምቀት የተሰጠንን ሌላና አዲስ የሆነውን ሕይወት ባሕርይ ባለማወቃችሁ ነው፡፡”

  ReplyDelete
 17. masetwalun yisten

  ReplyDelete

 18. wwww.Mary Defended:A Defense of Marian Doctrine

  6. Mediatrix

  Much of the devotion to Mary shown by Christians of the Catholic and other Ancient Churches depends upon Mary's mediation. This mediation is seen in terms of Mary's assistance in prayer and in obtaining grace.

  Many Protestants oppose prayer to Mary and the Saints, citing this verse:

  "For there is one God and one mediator between God and men, the man Christ Jesus; " (I Timothy 2:5).

  SO IF JESUS IS THE ONE MEDIATOR, WHY PRAY TO MARY?

  As in other cases, Protestant fundamentalists often tend to quote just one verse completely out of context. So let's look at the whole passage.

  "I urge then, first of all, that requests, prayers, intercession and thanksgiving be made for everyone - for kings, for all those in authority, that we may lead a quiet and peaceful life in all godliness and holiness. This is good and pleases God our Saviour, who wants all men to be saved and come to the knowledge of the truth. For there is one God and one mediator between God and men, the man, Christ Jesus."
  1Timothy 2:1-5

  From this full text of the passage we can see three important things:

  1. Paul is asking fellow Christians to pray and intercede with God for those in authority and for other third parties.

  2. These prayers and intercessions are being made on behalf of other people, and to God. This is a mediation of prayer. Christians are being asked to mediate between all people, Christian and non-Christian, and God.

  3. Since this is all one passage, it is absolutely clear that when Paul refers to there being only one mediator between God and men, he is not referring to the mediation of prayer. Jesus's unique mediation is a different mediation - the mediation of our salvation.

  Jesus is the one Mediator of our salvation, our only Saviour. But He is not our only intercessor, as the whole passage above clearly indicates. So the one passage that fundamentalists have used to deny intercessionary prayer, when read in context, actually backs up intercessionary prayer.

  YES. BUT WHY SHOULD I ASK MARY OR ANYONE ELSE TO PRAY TO GOD FOR ME WHEN I CAN PRAY TO HIM MYSELF?

  When we are ill, or someone we care for needs prayer, we ask other people to pray to God for us. Why do we do this if our own prayer is enough?
  In James 5. 14-16 we are told to get the Elders of the Church to pray for us and to annoint us when we are sick. Reading on, we find:

  James 5: 16-18 " ...The fervent prayer of a righteous person is very powerful. Elijah was a human being like us; yet he prayed earnestly that it might not rain, and for three years and six months it did not rain upon the land. Then he prayed again, and the sky gave rain and the earth produced its fruit."

  So we see that intercession strengthens prayer. And the more righteous and faithful the intercessor is, the more powerful the prayer.


  ReplyDelete
 19. BUT THAT IS PRAYER ON EARTH. I'VE BEEN TOLD THAT PEOPLE IN HEAVEN CAN NEITHER SEE US OR PRAY FOR US.

  That is a recent, man-made doctrine, with no authority behind it.

  Hebrews 12.1 speaks of "a great cloud of witnesses" who surround us, and who consist of the faithful holy ones of God. Many examples of these witnesses are given in the preceding Chapter 11 of Hebrews.

  Later in the Bible we see this vision of heaven:

  Revelation 4.4: Surrounding the throne were twenty four other thrones, and seated on them were twenty four elders. They were dressed in white and had crowns of gold on their heads.
  Revelation 5.8: ...and the twenty four elders fell down before the Lamb. Each one had a harp and they were holding golden bowls full of incense, which are the prayers of the saints.

  The twenty-four elders are shown offering the prayers of Christians to God; which is a mediatory role.

  WHY MARY IN PARTICULAR?

  The basic creed of Christianity, the Nicene Creed, accepted by all Trinitarian Christian Churches, refers to the Communion of Saints. All Christians in heaven and on earth are together (i.e. in communion) through Christ. As we have seen, those in heaven can witness what goes on on earth and offer prayers to God. This intercession is powerful, because those in heaven are truly "righteous".

  Of all creatures in heaven, Mary is closest to God, being the God-bearer. As a fellow Christian, and indeed the first Christian, she has access to the throne of grace through Jesus. As the Mother of all Christians, she cares and intercedes for her children. As the Heavenly Queen Mother (see above) it is her office to make requests of the King of Kings. Therefore Mary's intercessionary prayer is the most powerful and effective.

  Seeking Mary's intercession probably dates back to the earliest Christians. One of the oldest Christian prayers recorded in writing, the Sub Tuum, from the 200s AD, is a prayer to Mary:

  We fly to your patronage, O holy Mother of God.
  Despise not our petitions in our necessities,
  But deliver us from all dangers,
  O ever-glorious and Blessed Virgin!

  BUT I DON'T NEED MARY WHEN I CAN GO DIRECTLY TO GOD.

  Why not say "I don't need the rest of my family as long as I have my father"? The Church is a single body; the different members interelate and rely on one another: "The eye cannot say unto the hand, "I don't need you!" And the head cannot say to the feet, "I don't need you!" (I Co 12:21).

  ReplyDelete
 20. WHY DO WE NEED MARY?

  Mary has a vital part in the entire work of redemption. The Lord does not want to save us without our participation. He seeks our voluntary acceptance of salvation. He stands at the door, knocks and waits. (Rev. 3:10).
  In the same way, since the incarnation of the Son of God was necessary for the salvation of the human race, that incarnation would not be achieved by force, but needed the consent of the chosen one. Thus the incarnation, and the salvation of the entire human race were brought about to a major extent because the Virgin Mary, by faith, consented to God's plan.
  "I am the Lord's servant," Mary answered. "May it be to me as you have said." (Luke 1:38)

  The extent of Mary's act of faith is often overlooked. She was a single virgin, betrothed to Joseph, and giving birth to a fatherless child would place her in dire peril of disgrace, abandonment and possibly much worse, in a society that customarily stoned adulterers to death. Nor did she know what Joseph's or her family's personal reaction would be. Yet she did not hesitate to accept God's commission. Her trust in God made her the first Christian believer and the first among the redeemed. As the Mother of God, the girl from Galilee became the highest created being. When she said "yes" to God her answer was on behalf of the whole human race. Just as Eve's disobedience was on behalf of the whole human race. In this way, the Virgin Mary's significance in the work of our salvation is of the first order.

  St. Irenaeus Against Heresies (circa 189 A.D.) :

  ..the virgin Eve, betrothed to a man but nevertheless still a virgin, was unhappily led astray,-- yet that deception was done away with because the Virgin Mary, betrothed to a man but nevertheless still a virgin, heard the truth spoken by an angel, and was obedient. For just as the former was led astray by the word of an angel, so that she fled from God when she had transgressed His word; so did the latter, by an angelic communication receive the glad tidings that she should
  sustain (portaret) God, being obedient to His word.
  The former disobeyed God, yet the latter was persuaded to be obedient to God, so that the Virgin Mary might become patroness (advocata) of the virgin Eve. And thus, as the human race fell into bondage to death by means of a virgin, so is it rescued by a virgin; virginal disobedience having been balanced in the opposite scale by virginal obedience. In the same way the sin of the first created man (protoplasti) is made amends by the correction of the First-begotten, the coming of the serpent is conquered by the harmlessness of the dove, those bonds being unloosed by which we had been fast bound to death.

  In reference to the Blessed Virgin, St. Ephraem (373) said: "With the Mediator, you are the Mediatrix of the entire world" Antipater of Bostra, a Father of the Council of Ephesus (AD 431), wrote: "Hail you who acceptably intercede as a Mediatrix for mankind."

  Revelation 12.17: Then the dragon was enraged at the woman and went off to make war against the rest of her offspring - those who obey God's commandments and hold to the testimony of Jesus.

  Having been given to all Christians by Jesus as their heavenly Mother, Mary is always there for the help of her children.

  ReplyDelete
 21. arif new bertulene

  ReplyDelete
 22. ሰላም ለናንተ ይህን ምን እንደምል አላቅም ምክንያቱም አንዳንድ ስተት በመጋለጡ ደስ ብሎኛል ሌላው ደሞ እዚሁ ሳይት ላይ ስተት የሆነ የፕሮቴስታንት ትምህርትን አያለው፡እንደ ማርቲን ሉተር ከአዱ ስተተ ወደ ሌላው እንደምትሄዱ ነው ማየው ፡ አባ ሰላም ብላቹ ምታስተምሩት የማርቲን የፕሮቴስታንት ትምህርት ነው።

  አሁን በቃና ሚታየውን ታምር ጌታ ካለግዜው መቀየሩላይ ነው ማተቆር ያለብን ፡ ይህ ታምር የሆነው መጻፍ ቅድስ ላሳየን የፈለገው ነገር ስላለ ነው የተጻፈው ፣ ጌታ አንድ ቀን ታምር እንደሚሰራ የታወቀ ነው በብሉ ኪዳንም ተጸፏል ፡ ጥያቄው እንዴት እናቱን ሰምቶ ግዜውን ማፋተኑ ነው ፡ ማነው የአምላክን አሳብ ግዜ ሊያፋጥን የቻለው ከሰው ልጆች ?ስለ ሰርጉ ምንም ምናቀው ነገር የለም ስለ ጌታችን እና ስለ እናቱ ነው የበለጠ የተጻፈው እንደ ቃሉ እናቱን ሰምቶ ታምርን ካለ ግዜ አደረገው ፣ ማነው የአምላክን ግዜ ሊያፋጥን ሚችለው ?

  ReplyDelete