Thursday, January 23, 2014

ለቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች እቆረቆራለሁ የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳቱን በስድብና ስም በማጥፋት ዘመቻው ቀጥሎበታል፡፡

አበረ ከምስራቅ ኢትዮጵያ
ስሟን ቄስ ይጥራውና በቅርቡ የተከፈተችውን አንዲት የሐራ ተዋህዶ  እህት የሆነች የማቅ አዲስ ብሎግ  ሰሞኑን ስጎበኛት እስከ አሁን ያወጣቻቸው ጽሑፎች ከሐራ ተዋህዶ የተወሰዱ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡ አንድ በሐራ ያልተጻፈ አዲስ ጽሑፍ ግን አነበብኩኝ እርሱም የማህበረ ቅዱሳን ራስ ምታት የሆነው የምስራቁ የሐገራችን ክፍል እጅግ በሚደንቅና በእግዚአብሔር አጋዥነት የማህበሩ ህዋስ ከእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን መዋቅር ተነቃቅሎ በመውጣቱ ለመጨረሻ ግዜ ያገለግለኛል ብሎ ያስቀመጠውን ጥይት እየተኮሰ እንደሆነ ከዚህችው ብሎግ ላይ ለማንበብ ችያለሁ፡፡ ማህበሩ በእውነት መከራከርና ማሸነፍ ሲያቅተው በመጨረሻ የሚያደርገው ስድብና ስም ማጥፋት እንደሆነ ከዚህ በፊት ሲያሳይ ከነበረው ባህርዩ መረዳት ይቻላል፡፡ ሲሳደብና ስም ሲያጠፋ ደግሞ ማንንም አይፈራም፤ ማንንም አያከብርም፤ ከልምድ አቡነ ጳውሎስንም ከዚህ በፊት ሲሳደብ ሰምተነዋል፡፡

በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ 19 አመት በፊት በድሬደዋ፣ በሐረር፣ በጅጅጋና በአሰበ ተፈሪ በቤተ ክርስቲያን በተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎት ስር ይሳተፉ በነበሩ ወጣቶች ላይ የፈጸማቸው ግፎች ቀን ቆጥረው በራሱ ላይ መጥተዉበት፣ ለረጅም አመታት ተደላድዬ ሁሉን አሸንፌ ተቆጣጥሬዋለሁ ካለው የተለያየ የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ተጠራርጎ በመውጣቱ፣ ከዚህ በፊት ሲያደርግ የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማህበራትና በግለሰቦች እንዲሁም በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ አሁን ደግሞ የመጨረሻ ዱላውን በምእራብ ሐረርጌና ድሬደዋ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዕንባቆም  ላይ አዙሮአል፡፡

“ሊቀ ጳጳሱ በአሰበ ተፈሪ ከተማ ስርአተ አበው ይጠበቅ ያሉ ወጣቶችን ማህበረ ናታኒም ከሚባለው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ህዋስ ከሆነው ማህበር ጋር በመሆን እያሳደዱ ይገኛሉ” በማለትና የተለያየ በደል ፈጽመዋል በማለት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአባታችን ላይ አውርዶአል፡፡ ስለማህበረ ናታኒም አዲስ ነገር አንልም፤ ከዚህ በፊት በሰፊው ስላልን፡፡ ማቅ የሚገዳደረው ማህበር ሲፈጠር ስም ማጥፋት ልማዱ ስለሆነ ይህ እኛን አያስደንቀንም፡፡ ግን የዘነጋው ነገር ቢኖር ናታኒም  ማለት የእግዚአብሔር ቤት ታናናሽ አገልጋዮች ማለት ሲሆን ሌላው ትርጓሜው የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊዎች ማለት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከአሰበ ተፈሪ ማህበረ ቅዱሳን በሚሰራው ተንኮልና ግፍ ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ሰንበት ትምህርት ቤት ያለውን ቦታ በደረጃ ለቆ ለንጹህ የቤ/ክ ልጆች አስረክቦአል፡፡ ስለዚህ በናታኒም ከጌታ ቤተ መቅደስ ተጠራርጎ ወጥቶአል፡፡ ገና ከመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ተጠራርጎ ይወጣል በአጭር ግዜ፡፡ ብፁዕ አቡነ እንባቆም በጣም ታጋሽና ለውሳኔ የማይቸኩሉ ታላቅ አባት መሆናቸውን ማህበረ ቅዱሳን ባሳያቸው ትእቢቶች በአሰበ ተፈሪ ከተማ ለማህበሩ ያሳዩአቸው ትእግስቶች ካህናቱና ምእመናኑ የሚመሰክሩት ሐቅ ነው፡፡ ነገር ግን በትእቢቱና በአመጽ ተግባሩ ረጅም መንገድ ለመጓዝ የፈለገው ማቅ በአባታችን ትእግስት ተንኮታኩቶ ወድቆአል፡፡ ከዚህ በኋላ ለመነሳት የሚችልበት ሀይል የለውም፡፡ በዚህም ምክንያት የአባታችንን ስም ማጥፋት ተያይዞታል፡፡ ይሄ ደግሞ አባቶች በበለጠ ስለማህበሩ ተረድተው ግብአተ መሬቱ እንዲፋጠን በሲኖዶስ ድምጽ ያበዛበታል እንጂ የሚጠቅመው ነገር የለም፡፡

ለአበው ሃይማኖት እቆረቆራለሁ የሚለው ማህበር እስሩ ያሉትን አባቶች ሳያከብር የማያውቃቸውን አባቶች እንዴት አድርጎ ነው ጠበቃ ሆኖ ሊቆምላቸው የሚችለው፡፡ በቅርብህ ያለውን ወንድምህን ሳትወድ የማታውቀውን እግዚአብሔርን አወዳለሁ ብትል ሐሰተኛ ነህ ይላል ታላቁ መጽሐፍ፡፡ ደግሞስ ማነው ይሄንን ማህበር የሰው ኃጢአት ተራኪ ያደረገው? ወንድምህ ቢበድልህ ሰባ ጊዜ ሰባት (490) ግዜ ይቅር በለው ነው የሚለው የአምላክ ቃል፡፡ ማህበሩ ግን ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ሲሳደብ ምንም እፍረት አይሰማውም፡፡ ማህበሩ የሚያራምደው ክርስትና ሐይማኖት ነው ወይስ ፖለቲካ? ክርስትና ሐይማኖት የሚያራምድ ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት አድርጎ ሊጓዝ ይገባው ነበር፡፡ ፖለቲካ ከሆነ በጨዋና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ከሐይማኖት ራሱን አግልሎ ስድቡን ትቶ መታገል፡፡ ግን የእርሱ መንገድ የሽብር መንገድ ስለሆነ ይሄንን መከተል አይፈልግም፡፡ ስለዚህ የግፍ ዋጋውን ከእግዚአብሔርና ከሰው ይቀበላል፡፡ ማንም አያማልደውም ማንም ከመጣበት ችግር አያድነውም፡፡ 

በእርግጥ ማህበሩ የግብር አባቱ የዲያብሎስ ልጅ እንደመሆኑ እንደእኩይ ፍልስጣ የእያንዳንዱን ሊቀ ጳጰስ ህይወት ታሪክ ከዲቁና ጀምሮ እስከ ጵጵስና ያለውን መዝግቦ ይዞ ክፉ ክፉውን ለክፉ ቀን እየመዘዘ እንደሚጠቀምበት አባ ገብረየሱስ የሚባሉ አቡነ ማርቆስ የምእራብ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት የቅድስት ልደታ ለማርያምና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ አስተዳዳሪ የነበሩ አባት አጫውተውኛል፡፡ እኚሁ አባት ደቡብ ክልል ውስጥ አሁን በስም ከማላስታውሳቸው ሊቀጳጳስ ጋር በሚሰሩበት ወቅት ሊቀጳጳሱና እርሳቸው በመጋጨታቸውና ስራቸው ላይ ችግር ስለገጠማቸው ወደ ማህበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ዋናው ማእከል በመምጣት ከሊቀጳጳሱ መረጃ ቋት ውስጥ በክህነት ዘመናቸው ሲሰሩአቸው ነበር ያሉአቸውን ነውሮችና ሐጢአቶች መዝግበው ካስቀመጡበት ሰጥተዋቸው ተመልሰው ሊቀጳጳሱ ያሉበት ድረስ በመሔድ  እንዳዋረዷቸው ሲያጫውቱኝ በወቅቱ እጅግ አዝኜ ነበር፡፡ እና ማህበሩ እያደረገ ያለው ክፋት ሞልቶ እዚህ ደርሶአል፡፡ አሁንም በአቡነ እንባቆም ላይ በሰፊው ሊጽፈው የፈለገው ጉዳይ እንዳለ ከብሎጉ መረዳት ይቻላል፡፡ ከየት ያመጣዋል ብትሉኝ ከመረጃ ቋቱ እያወጣ ይጽፋል፡፡ ያሳዝናል ክርስቶስ እኮ እንደማህበረ ቅዱሳን የሰውን ሐጢአት እየመዘገበ የሚያስቀምጥበት መዝገብ ቤት የለውም፡፡ እንኳን የሊቀ ጳጳሱን አይደለም የማቅ አባላትንም ኃጢአት መዝግቦ አያስቀምጥም ንስሀ እስከገቡ ድረስ፡፡ እና ውድ የኦርቶዶክስ ልጆች ማህበሩን ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ለማስወገድ የአሰበ ተፈሪን ልምድ በደንብ ውሰዱና ተግባራዊ አድርጉት፡፡ የሊቀ ጳጳሱን ጥንካሬ የሐገረ ስብከቱን አስተዳደር ሰራተኞች ጠንካራ አቋም በተጨማሪም ማህበረ ካህናቱና ማህበረ ምእመናኑ ከተለያዩ የጉዞና የጽዋ ማህበራት ጋር አንድነት በመፍጠር የተወሰደውን አቋም ማለቴ ነው፡፡


ስለዚህ አባታችን ላይ የተወረወረው ፍላጸ ተመልሶ ማቅን እንደሚወጋ ይታወቃል ምክንያቱም የሚያወሩት ሁሉ የአባታችን ግብር (ስራ)  ሳይሆን የእነርሱ ግብር (ስራ)  በመሆኑ፡፡ አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ፡፡ 

12 comments:

 1. አቡነ እንባቆም በነካ እጆዎ የድሬዳዋ ማርያምንም ያስለቅቁልን አባታችን የቤተክርስቲያን አባቶች እየተሳዳዱ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣተች እየተሰደቡ ልማቱ እየደከመ ካዝናው ባዶ እየሆነ በቦነስ ስም እየወጣ እየተጠጣበት ነው ያለው ፡፡ ድሬዳዋ ማርያም መሰሪው ድንበሩ ከመግባቱ በፊት 2ሚሊዮን ብር ነበረው አሁን እሱ ከመጣ ወድህ ግን በካዝናው ያለው 44000(አርባ አራት ሽ) ብር ብቻ ነው ሰበካ ጉባኤ መሰማት አልቻሉም አውነተኛ ቤተክርስቲያን ልጆች ይደመጡም እንደውም ይነሱልን ይባላሉ ከነዚህ ሰዎች ወይም ወንድሞች ጋር የሚሰሩ አባቸም በሆነ መንገድ እንድኑ ይደረጋሉ ለዚህ ማሳያውም በደብሩ ላይከፍተኛ ለውጥ ያመጡት አባ ገብረ ስላሴ ያየህ ባላወቁት መንገድ እንደተነሱና በነበሩበት ወቅትም መስራት የፈለጉትን አላሰራቸው እንዳሉ መናገራውን ሁሉም የደብሩ ካህናት ያውቁታል ተናግረውታልም በጣም የሚግርመው ለበተክርስቲያን ሌት ተቀን የምትለፋውን ልጂ ከማህዶት መናፈሻ አስዎጥተው ዘዎትር ለሚጠጡብ ሆቴል ከሆዳሙ ፀሐፊ ጋር በመሆን በጣም በትንሽ ብር አስረክበውታል በጣም የሚገርመው በህጉ መሰረት ይተላለፍ እዚህ ለምራት ከሰሜን መምጣት የለብንም ያሉ በቅንነት ሀሳባቸወን ያቀረቡ ስማቸውን እያጠፉት ይገኛሉ ስለዚህ አባታችን በዘር ማሰበዎን በመተው የናንም ደብር በነካ እጀዎ እንዲያ ጸዱልን አንለምነዎታል አባታችን ድንበሩ ማለት በረጂም ምላሱ የአባቶችን ስም የሚያጠፋ እንጂ ምንም የሚጠቅም ስላልሆነ ቢያስዎግዱልን ቤተክርስቲያንን ከዘረፋ ቢታደጓት የሁሉም ማህበረ ካህናት ደስታ እንጂ የሚቀር የለም እቀጥላለሁ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት መወገድ ያለባቸውን አሳውቃለሁ
  ts

  ReplyDelete
 2. ተሳዳቢውና መናፍቁ ፅጌ ዛሬ ደሞ አበረ ሆንክ? ለመሆኑ ማቅ እንዲህ ብሎ ሰደባቸው ማለት ነው? እስኪ አንተ እዚሁ ከተሳደብከው ለቅምሻ ያህል::

  -የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃምና በኢየሱስ ስም ላይ የከፈተው ዘመቻ::
  -የጉድ ሙዳዮች ሲኖዶስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ አሳዝኗል
  -በሲሚንቶ ሽያጭ ያልታመኑ አባ ሕዝቅኤል
  -አስመሳዩ ጳጳስ አብርሃምና ጉዱ
  -ዘረኛ ነው.....
  -የአባ ሚካኤል ልጅ የዮሐንስ እና የእነ አባ ሳሙኤል ሙግት
  (በነገራችን ላይ ጥር 29/2005 እኮ ዓመት ሆነው::የምታወራው አጣህ?)
  ማፈሪያ መጀመሪያ የራስህን ምሰሶ ከዓይንህ አውጣ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስማ ወዳጄ ይህን ሁሉ ጉድ እኮ የማቅ የመረጃ ቋት ይዞት ነበር፡፡ ጳጳሳቱንም ዋ ኦነዳላወጣ እያለ ያስፈራራበትና የሚፈልገውን እንዲፈጽሙለት ይጠመዝዛቸው ነበር፡፡ አባ ሰላማ ያደረገችው ማስፈራሪያችሁን ለሕዝብ ይፋ ማድረግና ጳጳሳቱን ከኣንተ ፍርሃትና ተገዢነት ነጻ ማውጣት ነው፡፡ ማቅ የታዘዙትን ጳጳሳት ገበና ለጊዜው ይሸፍናል አልታዘዝ ያሉትን ግን ልክ በአቡነ ዕንባቆም ላይ እንዳደረገው በሰውር ብሎጎቹ ስማቸውን ያጠፋል፡፡ ለምሳሌ አቡነ ማርቆስንም መጥቀስ እንችላለን፡፡ ስለዚህ እናንተ ጥቅማችሁ ሲነካ ጊዜ እየጠበቃችሁ ከመረጃ ቋታችሁ ውስጥ እያወጣችሁ አልታዘዝ ያሏችሁን አባቶች ስም ታጠፋላችሁ፡፡ ከላይ የዘረዘርካቸው ሁሉ በመረጃ ቋትህ እንደተያዘ ያስታውቅብሃል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ አደብ ግዙ፡፡

   Delete
  2. እሰኪ አንተም ስማ ወዳጄ:: ያንተን ጅል ሃሳብ (አንተን አይደለም ሃሳብህ እንጂ፤ አንተማ ሁለት ደሞዝ ላጥ የምታደርግ ብልጥ) እንቀበልና የማቅ የመረጃ ቋት ይዞት ነበር እንበል። ከዛም በአንተው አባባል " ጳጳሳቱንም ዋ ኦነዳላወጣ እያለ ያስፈራራበትና የሚፈልገውን እንዲፈጽሙለት ይጠመዝዛቸው ነበር፡፡"እንበል። ከዛ ጉዳቸው እናንተ ታድሶ ተብዪ የጴንጤ ተላላኪዎች "የመረጃ ቋት" ውስጥ ገባና ጳጳሳቱን አስፈራራችሁ አልተቀበሏችሁምና እዚሁ የተሃድሶ ጴንጤ ኦፊሴል ድረ ገጽ እና ግልገል ድረ ገጾቻችሁ ላይ ስማቸውን አጠፋህ። ማቅ የያዘውን ሚስጢር አንተ ገለጽክ። ታዲያ ሚስጢር ምን ቀርቶ ነው? አሁንም ማቅን የሚታዘዙት? አይ ጽጌ እንደው ኮሚክ እኮ ነህ። ይልቁን በጫት ምርቃና የምትጽፈው መቀባጠር ውሸት ስም ማጥፋት መክሰስ አልደከመህም? ለጽጌ የተሰጠው ጸጋ ሲባል እኮ የሚጠቀስልህ ውሸት ስም ማጥፋት በውሸት መክሰስ ነው። በብእር ስም አበረ፤ ተሰበረ ፤አዲስ ፤ አማረ ተስፋዬ ፤ተሰፋ፤ ጎደለ ተስፍስዬ፤ ሰላም ወዘተ በሰማንያ ሚሊዮን ስም ብትፅፍ አንተ መሆንህ አይቀየር:: የፈለከውን እያልክ ብትጽፍ፤ ብትለቀልቅ እውነት ካንተ ዘንድ የት አለች፤ አሁን እንኳን ያለፈው ሳምንት እኮ የአቡነ ጎርጎርዮስን ስም ስታጠፋ ነበር::
   ፅጌ ስጦታው አቡነ ጎርጎርዮስንም በሌብነት ይከሳል::

   "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።" ይለናል:: በመጀመሪያገፅ 72 ላይ እንዲህ የሚል ጭራሽ የለም:: በሁለተኛ ደረጃ ገፅ 79 ላይ በትክክል ተፅፎ ይገኛል:: በዚህ መፅሐፍ እንዲህ የተሳሳተ ሰው በሌላው እመኑኝ ሲል እንዴት ይታመናል:: ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ 79 ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ፍረዱ:: ይሄን ውሸታም ጴንጤንም ታዘቡት:: https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG


   ስለዚህ እባካችሁ አደብ ግዙ፡፡ ወደ አዳራሻችሁ ጥርግ በሉ::

   Delete
  3. እሰኪ አንተም ስማ ወዳጄ:: ያንተን ጅል ሃሳብ (አንተን አይደለም ሃሳብህ እንጂ፤ አንተማ ሁለት ደሞዝ ላጥ የምታደርግ ብልጥ) እንቀበልና የማቅ የመረጃ ቋት ይዞት ነበር እንበል። ከዛም በአንተው አባባል " ጳጳሳቱንም ዋ ኦነዳላወጣ እያለ ያስፈራራበትና የሚፈልገውን እንዲፈጽሙለት ይጠመዝዛቸው ነበር፡፡"እንበል። ከዛ ጉዳቸው እናንተ ታድሶ ተብዪ የጴንጤ ተላላኪዎች "የመረጃ ቋት" ውስጥ ገባና ጳጳሳቱን አስፈራራችሁ አልተቀበሏችሁምና እዚሁ የተሃድሶ ጴንጤ ኦፊሴል ድረ ገጽ እና ግልገል ድረ ገጾቻችሁ ላይ ስማቸውን አጠፋህ። ማቅ የያዘውን ሚስጢር አንተ ገለጽክ። ታዲያ ሚስጢር ምን ቀርቶ ነው? አሁንም ማቅን የሚታዘዙት? አይ ጽጌ እንደው ኮሚክ እኮ ነህ። ይልቁን በጫት ምርቃና የምትጽፈው መቀባጠር ውሸት ስም ማጥፋት መክሰስ አልደከመህም? ለጽጌ የተሰጠው ጸጋ ሲባል እኮ የሚጠቀስልህ ውሸት ስም ማጥፋት በውሸት መክሰስ ነው። በብእር ስም አበረ፤ ተሰበረ ፤አዲስ ፤ አማረ ተስፋዬ ፤ተሰፋ፤ ጎደለ ተስፍስዬ፤ ሰላም ወዘተ በሰማንያ ሚሊዮን ስም ብትፅፍ አንተ መሆንህ አይቀየር:: የፈለከውን እያልክ ብትጽፍ፤ ብትለቀልቅ እውነት ካንተ ዘንድ የት አለች፤ አሁን እንኳን ያለፈው ሳምንት እኮ የአቡነ ጎርጎርዮስን ስም ስታጠፋ ነበር::
   ፅጌ ስጦታው አቡነ ጎርጎርዮስንም በሌብነት ይከሳል::

   "ይህንኑ ታሪክ ምንጭ ሳይጠቅሱ ራሳቸው እንደ ጻፉት አድርገው አባ ጎርጎርዮስ እንደ ወረደ አስፍረዉታል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 1974 ገጽ 72)።" ይለናል:: በመጀመሪያገፅ 72 ላይ እንዲህ የሚል ጭራሽ የለም:: በሁለተኛ ደረጃ ገፅ 79 ላይ በትክክል ተፅፎ ይገኛል:: በዚህ መፅሐፍ እንዲህ የተሳሳተ ሰው በሌላው እመኑኝ ሲል እንዴት ይታመናል:: ይሄ ሊንክ የአቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መፅሐፍ ገፅ 79 ነው:: የፃፉትን አይታችሁ ፍረዱ:: ይሄን ውሸታም ጴንጤንም ታዘቡት:: https://www.dropbox.com/s/m5cexytz5byjac6/IMG_6423.PNG


   ስለዚህ እባካችሁ አደብ ግዙ፡፡ ወደ አዳራሻችሁ ጥርግ በሉ::

   Delete
 3. Aba selama lemehonu enanent selebetekerstian tasebalachihu ende?

  ReplyDelete
 4. ነገረኞች የነገር ሌቦች ባንድ ወይም በሌላ መገድ የሚፈተሹበት ጊዜ ቀርቧልና በሰበበኞች ሊጸለይባቸው
  ይገባል ጸልዩ በእንተ መስተዋድያን ወበእንተ ፍኖቶሙ እኩይ።

  ReplyDelete
 5. ነገረኞች የነገር ሌቦች ባንድ ወይም በሌላ መገድ የሚፈተሹበት ጊዜ ቀርቧልና በሰበበኞች ሊጸለይባቸው
  ይገባል ጸልዩ በእንተ መስተዋድያን ወበእንተ ፍኖቶሙ እኩይ።

  ReplyDelete
 6. ለካም ሁልጌዝም ውሸት ነው የምትጽፉት እኔ ደግሞ እውነት ይመስለኝ ነበረ ድንበሩ ድሬዳዋ ላይ ለውጥ ያመጣ ቄራጥ የቤተክርስተያን ልጂ ነው እውነቱን ልንገርህ እኔ የሱ ደጋፊም አይደለሁም እንደው እውነት ማለፍ ስለማልፈልግ ብቻ ነው የሚገርመው ድንበሩ ድሬዳዋ ላይ የመጣቸው ለውጦች ብዙ ናቸው የታገለባቸው የቤተክርስቲያን ስራዎችም እንደሁ ብዙ ናቸው የካህናት ችግር እንደፈታ ሳይታክት ጥርት አድረጓል ምንደኞች ከቤተክርስቲያን እጃቸውን እንድሰበስቡ ሰርቷል ታግሏል እሱን የሚጠሉትም ከራሳችን ደብር ጄምሮ እናውቃቸዋለን የሰው ሚስት የሚቀሙ ወይም በየዛፍ ስር የሚጎትቱ መናፍቃን ሎቦች ናቸው እነዚህ ደግሞ ተነቅቶባቸዋል በየሰፈሩ ስሙን አጠፍት ነገሩን አልሰማናቸውም አሁን ደግሞ በዚህ መጣችሁ ለምን ወንደማችንን ከጀርባ ታማላችሁ ለምን አትመጡም በአካል? እስኪ እናንተ ለበተክርስቲያን አስባችሁ ነው ? የሚገርመው የደብሯ ገንዘብ አለቀ የለም አላችሁ ማን ወሰደው መቸም እሱ ወሰደው እያላችሁ እንዳይሆን ? ገንዘቡ ቀነሰ አላችሁ እኔ መረጃው የለኝም ግን ቢያልቅስ ምን እየተሰራ እንደሆነ መናገር አቅቷችሁ አይደም እንደው እሱን ስለምጡሉት እንጂ ሳታውቁት ቀርታችሁ አይደልም ደግሞ እሱ በግሉ በድሎችሁ አይደለም ስሙን የምታጠፍት ማህበረ ቅዱሳን ስለሆነ ብቻ ነው በጣም የሚገርመው አለቃውን አስነሳቸው የምትሉት እራሳቸው ሲነገሩ እንደሰማሁት ለጤናየ የሚመቸኝ ቦታ ፈልጌ ነው ያሉት እንደት እሱ አስነሳቸው ይባላል ? መረጃው ቢኖረኝ ስለሌሎቹም በመለስኩ ነበረ ... ምን ይደረግ አላውቀውም ግን እግዜር ይፍረድ em

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስማ ወንድም
   ስለድንበሩ እኮ አስተያየት ነው የተጻፈው የአባሰላማ ጽሁፍ አይደለም። አሁን አንተ ለሰጠኸው አስተያየት አባ ሰላማ ልትነቀፍ አይገባትም። አንተ የተሰማሕን ነው የጻፍከው። እንደዛ ማለት ነው። ስለ ድንበሩ አስተያየት የሰጠው ሰው የግል አመለካከቱ ነው።

   Delete
 7. wey yebirhan meliak meslo yemimetaw ganien yekidusanen kiber kemachihu ahun degimo yerasun enawikewalen yemitlutin amlak kiber le mekemat wazema ai deresachihu enanitew honachihu ke mekidesu aswechi wey natanimoch yemiyasazinew ezih mahiber wis beyewahinet saygebachew yenanite biete crstiyan afrashinet alama asfetsami mehonachew new esti amlak firdun begizew yist

  ReplyDelete
 8. ሰለ ድንበሩ የመሰከርከው እንደት ነው እሱ ለቤተክርስቲያን አባቶች የታገለው ደብራችን መልካም አስተዳር ጠፍቶ ሁሉም እሚያለቅስበት ስላደረገው እንደው በገቢው የሚፈሰው እንባ አልታይህ ብሎህ አይደለም እንደሁ አድር ባይ ስለሆንክ እንጂ ተው እሱ ለማንም ካህን አልታገለም አለፋም በእርግጥ አንድን አገር ከሊቀ ዳቆን እስከ አለቃ ስብስቧል ይህ ያስደነቀዋል ይህ ከሆነ ለካህናት ህይዎት መለወጥ ሰርቷል የሚያስብለው ጥሩ ነው ግን ምነው ለድንበሩ ስትመሰክር ለፀሃፊ አልመሰክርክም ? ነው እሱ የማህበር አባልነት አይከፍልም ? እንድመልስልኝ እጠብቃለሁ

  ReplyDelete