Tuesday, January 28, 2014

ሰራተኞችን በሕገወጥ መንገድ በማዘዋወር አባ እስጢፋኖስና ሰራተኞቻቸው የጀመሩት ቢዝነስ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ተስተጓጎለ

F አቡነ እስጢፋኖስን ይቃወማሉ የተባሉ አስተዳዳሪዎችን በዝውውር ስም ከደረጃ ዝቅ ለማድረግ የታሰበው እቅድ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ታደገ፡፡
F  አቡነ እስጢፋኖስ በኩርፊያ ወደ ጅማ ሄደዋል፡፡
F እስከ ዛሬ ሐራን በመሰሉ ስውር ብሎጎቹ ብቻ ‹‹መዋቅራዊ ነውጥ›› ብሎ የሰየመውን የትርምስ እስትራቴጂ ሲደግፍ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን ከደረሰበት ኪሳራ ለመውጣት በመደበኛ ድረ ገጹ እቅዱ እንዲጸድቅ ቅስቀሳውን ቀጥሏል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥልጣን ቆንጥጦ ለመያዝ ካለው ጽኑ ፍላጎት አንጻር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተግባራዊ ለማድረግ የቋመጠለትንና ሥልጣኑን በሙሉ ከካህናት ነጥቆ ለማኅበሩ ደጋፊ እና አባል ምእመናን የሚሰጠውንና ካህናቱ እንደ ግል ድርጅት ሰራተኛ በቤተክርስቲያናቸው አንዳችም የጎላ ድርሻ ተግባር (ከመቀደስ ከማወደስ ውጪ) እንዳይኖራቸው የሚያደርገውን ‹‹መዋቅራዊ ነውጥ›› በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ልዩ ልዩ ሰራተኞችና ካህናት በመቃወማቸው ምክንያት በተነሳው ተቃውሞ ዕቅዱ አካሄዱን ያልጠበቀ ሕግ አርቃቂው ክፍልም በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ ያላገኛና ቤተክርስቲያኒቱን ለአንድ ነጋዴ ማኅበር አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ ታግዶ በሊቃውንት ሁሉን ያማከለና ከቤተክርስቲያኗ ሕጎችና መመሪያዎች ጋር የተዛመደ ጥናት እንዲቀርብ በቋሚ ሲኖዶስ መመሪያ ከተሰጠ በኋላ የእቅዱ መክሸፍ ያሳሰባቸው አቡነ እስጢፋኖስና የማኅበሩ ስውር አንቀሳቃሾች በፓትርያርኩ እና በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ላይ ግፊት ለማድረግ የተለያዩ ስብሰባዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በሰሜን አሜሪካ ያለው ሲኖዶስ ደጋፊ አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርቶቻቸውን አስቀድመው ወደ ጠቅላይ ቤተክህነቱ ቢልኩም አንዳች ጠብ ያለ ነገር አላገኙም በዚህ መዋቅራዊ ለውጥ ዋና አስተባባሪ የአፍሪካ ኅብረቱ የሕንጻ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የነበረውና ቤተክርስቲያን ውስጥ ከቀድሞዋ ሒሳብ ሹም ወ/ሮ ምንጭቱ ጋር በመሴሰን ተይዞ የተባረረው  ሙሰኛውና ጎሰኛው  ጌታቸው ደግፌ፤ ወጂ መድኃኔ ዓለም አለቃ ፤ በቅርቡ ከእስልምና ሃይማኖት ተመልሶ በአንድ ዓመት የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ  ሰበካ ጉባዔ ምክትል ሊቀ መንበር የሆነውና ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በሥርዓተ ቁርባን ላይ ጭምር ከህናትን የሚሳደበው አቶ አበበ ይማም የሚቻላቸውን ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም፡፡ ማኅበሩ በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ያደራጃቸውንና ዩኒፎርም በማልበስ ለዓላመው ማስፈጸሚያነት የሚገለገልባቸውን ስውር አባላት ወደ መንበረ ፓትርያርኩ በመላክ አንዳች ውጤት ጠብቆ ነበር፡፡ ይሁንና በሀገረ ስብከቱ ካሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ያልተወከሉና ማኅበሩ አባል የሆኑ ጥቂት ወጣቶችም የተሰጣቸውን የአቡነ እስጢፋኖስን ሥልጣን የማስቀጠል እና የማኅበሩን መዋቅር የማጸደቅ ተግባር በብቃት መወጣት ባለመቻላቸው አቡነ እስጢፋኖስ ተስፋ ወደ መቁረጡ አዘንብለዋል፡፡

ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ አቅራቢያ ወዳለ አንድ ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲሄዱ አቡነ እስጢፋኖስም በአጃቢነት ተገኝተው ነበር፡፡ እናም አቡነ እስጢፋኖስ በፓትርያርኩ መኪና ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ‹‹ቅዱስ አባታችን ሞራሌ በጣም ተጎድቷል ይህን ‹ መዋቅራዊ ለውጥ › ያጽድቁልኝ እባክዎ ›› በማለት ልመና አቅርበው ነበር፡፡ ነገር ግን ፓትርያርኩ ‹‹ እርስዎ ነውጥ ይወዳሉ ለምን አይረጋጉም እንደውስ ለምን ወደ አዲስ አበባ ይሄዳሉ እኔ እርስዎን ብሆን በዚሁ ጅማ እሳፈር ነበር ›› በማለት በቁጣ መልሰውላቸዋል፡፡ በመንገድም ፍፁም ሳያነጋገሩ አዲስ አበባ ለመግባት ችለዋል፡፡

አቡነ እስጢፋኖስ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ድሬደዋ የወለዱትና ከጫት ቤት ሆኖ ሀገረ ስብከቱን የሚያሽከረክረው ልጃቸው ዮናስ ፍቅረንና  እና እንደ እስስት ከሁሉ ጋር ለመመሳሰል የሚሞክረውንና ካሸነፈው ጋር ለመለጠፍ አለሁላችሁ የሚለውን ዳዊት ያሬድ ጠርተው ሁኔታዎች ከቁጥጥጥራቸው ውጪ መሆኑን በመግለጽ ምክር ይጠይቃሉ፡፡ በሀገረ ስብከቱ ባሉት በሁሉም ኮሚቴዎች (በግዥ፣ በጨረታ፣ በመዋቅራዊ ለውጥ፣ በእድገትና ዝውውር፤ የሀገረ ስብከቱን ባዶ ክፍሎች በሚያከራየው ኮሚቴ) አባል የሆነው ዮናስ እንዲሁም ያለምንም ትምህርት በሕግ ክፍል የተመደበው ሌላው የአቡኑ ልጅ አቶ ታዲዮስ የጳጳሱን እቅድ የተቃወሙ አንጋፋዎቹን የአዲስ አበባ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች በዝውውር ስም ዝቅ ለማድረግ ይመክራሉ፡፡ በዚሁም መሠረት መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃን ወደ ቦሌ ሚካኤል በማድረግ ከመጣው ጋር በመለማመጥ የሚኖረውን ጠንቋዩን የቦሌ ሚካኤሉን አለቃ የየካውን ታላቁን ሊቅ ሊቀ ሊቃውንት እዝራን ጡረታ በማውጣት እሱን መድበውታል፡፡ የሲኤምሲ ሚካኤሉን አስተዳዳሪ ሊ/ት ዘካርያስን ወደ ደብረ ኢያሪኮ መድኃኔዓለም፤ የደብረ ኢያሪኮውን አለቃ ወደ አጉስታ ቅ/ማርያም በማድረግ የአጉስታውን አለቃ ወደ ሳሪስ አቦ በመመድብ ታላቁን ሊቅ መልአከ ገነት ተስፋ ፍስሐን በጡረታ ለማሰናበት ተወስኗል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የዜማ መምህር ሊቀ ጉባዔ ኤርሚያስ ወ/ኢየሱስን ጡረታ በማውጣት በምትካቸው መሪጌታ ለይኩን የተባለ በፍልሰታ ሴት ይዘው በመገኘቱ ከጉራራ ኪዳነምህረት የተባረረውን ለመተካት ወስነዋል፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅበረቱን አለቃ ወደ ፉሪ ሐና፤ የወጂ  መድኃኔዓለሙን አለቃ ወደ ሲኤምሲ ሚካኤል፤ የአርሴማውን አለቃ ሊቁን መልአከ ጸሐይ ጸዳሉን ወደ ወጂ መድኃኔዓለም፤ ታላቁን ሊቅ አራት ዐይናውን መምህር ዘለአለም እሰይን ጡረታ በማውጣት የጃቲ ኪዳነምህረቱን አለቃ መልአከ ገነት ልሳነ ወርቅን ወደ ቅዱስ ቂርቆስ፤ የሰዋሰው ብርሃኑን አለቃ ቄስ ለይኩን ወደ ጃቲ ኪዳነምህረት የየረር ዑራኤሉን ዘማርያም ሙጨ ወደ አፍሪካ ኅብረት ሚካኤል፤ የቅድሥት ሥላሴውን አለቃ አባ ኪሮስ ኮተቤ ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን፤ ዘንድሮ ጵጵስና አያልፈኝም በማለት ልብሰ ጵጵሥና በማሰፋት ሥራ የተጠመዱትን የኢያቄም ሐናውን አለቃ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ የደብረ ሊባኖሱን ፀባቴ ወልደማርያም ወደ እንጦጦ ማርያም፤ የእንጦጦ ማርያምን አለቃ ወደ አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለማዛወር ተስማምተው እንደተለያዩ ይኸው ወሬ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይደርሳል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም አቡነ እስጢፋኖስ ጋር በመደወል ‹‹ የያዝከው ሥራ የልጅ ሥራ ነው እነዚህ ሰዎች ያንተን ለውጥ መቃወም መብታቸው ነው ›› በማለት ሥልኩን ይዘጉታል፡፡ ከዚያም ማንኛውም አይነት ቅጥር፣ እድገትና ዝውውር እንዳይፈጸም በደብዳቤ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡ ለአዲሱ ሥራ አስኪያጅ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተደውሎ ይኸው ውሳኔ እንዲከበር መመሪያ የተሰጣቸው ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅም ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መመሪያ እንደማይጣስና ትክክለኛ በመሆኑ እንደሚደግፉት ተናግረዋል፡፡ ደብዳቤውን ያነበቡት አቡነ እስጢፋኖስ በኩርፊያ ወድያው ወደ ጅማ ሄደዋል፡፡


በዚህ ዝውውር ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለመቀበል የአቡኑ ደጋፊ አስተዳዳሪዎች ጋር በኪንግስ ሆቴል ቅልጥ ባለ ግብዣ እና ድርድር ላይ የነበሩት ዳዊት ያሬድና አቶ ዮናስ የፓትርያርኩን ደብዳቤ መጻፍ እንደሰሙ ወደ አባታቸው ቢሄዱም በኩርፊያ ወደ ጅማ መሄዳቸውን ከጥበቃ ሰራተኞች ሰምተዋል፡፡ አቶ ዮናስ ሚስቱ በአሜሪካን ሀገር የምትገኝ ሲሆን ከዝውውሩ የሚገኘውን ገንዘብ ይዞ ወደዚያው የማቅናት ሐሳቡ ለጊዜውም ስለተስተጓጎለ መጪውን ጊዜ በመናፈቅ ወላጅ አባቱ በሰጡት  ሥልጣን  እንደሚቆይ ይጠበቃል፡፡

8 comments:

 1. Ayi menafik hulla! Yasebkew enna sitineza yekeremkew wore afer dibe sibela gize, yemewakir lewutu tegbarawinet ayikere mehonun sitreda gize bedem filat yihen tsafk. Min alefah yemewakir tinatu yebelete tetenakiro yimetal. Min yiwutih yihon?

  ReplyDelete
 2. አባ ሰላማ?
  ማህበረ ቅዱሳን የመዋቅር ነውጥ ለማፀደቅ በዋናው ድረ ገጹ ቅስቀሳ ጀምሯል የተባለው ፈትሸን ማግኘት አልቻልንምና የተፃፈውን ፖስት አድርጉልን::

  ReplyDelete
  Replies
  1. check their Facebook page of ማህበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል

   Delete
 3. አቡነ እስጢፋኖስ ታላላቅ ተግባራትን ያከናወኑ አባት ናቸው- በተለይ በጅማ. ሀዳጌ በቀል-ይቅር ባይ በመሆናቸውም አከብራቸዋለሁ.የአሁኑ አስተዳደራቸው ግን ከሰሩት ስራ ያስነሱት አቡዋራ በለጠ.ከምንጊዜውም በባሰ መልኩ በዚህ እሳቸው ዘመን መልካም አስተዳደር ጠፍቱዋል.ጥናት ጥናት እያሉ ከኩታሮች ጋር ሲሩዋሩዋጡ የየእለት ተእለት የሀገረስብከቱን የአስተዳደር ስራ ዘንግተውታል.ባጉዋጉል የሚዲያና የኢንተርኔት ሽፋን በከንቱ ውዳሴ ተጠልፈው ለካህናቱ ፍትህ ከመስጠት ተዘናግተዋል. መፍትሄ የሌላቸው የእግድ፣የዝውውር፣የደረጃ መቀነስ አቤቱታዎች ሰሚ እያገኙ አይደሉም. የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ የሚያዩ የመንግስት ፍርድ ቤቶችም ከዐለማዊው ክርክር በበለጠ መልኩ በቤተክርስቲያን ሰራተኞች በሚቀርብ ክርክር መጨናነቃቸው የአቡነ እስጢፋኖስ ዘመን መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ነው የሚያሰኝ አይደለም.በተለይ ብዙ በደሎች የሚፈጸሙት የእሳቸው ደጋፊ ነን በሚሉ አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት መሆኑ ያሳዝናል.
  ወደጥናቱ ስመለስ ካህናት ያልተሳተፉበት ጥናት በጉዋሮ በር መጥቶ እንዲጸድቅ ያደረጉት ውትወታም አያሳምንም. እስከጠቀመን ድረስ እንኩዋን ማህበረቅዱሳን አጥንቶት ለምን ወድቆ አይገኝም ማለታቸውም ቅር ያሰኛል. እንዲያ ከተባለማ ከዚህ ሁሉ ልፋት ለምን ምርጥ የአስተዳደር ስርዐት አላቸው ከሚባሉት ካቶሊካውያን አንቀዳውም.የራሳችንን የሚመስል ፈልገን እንጅ.ለካህን መተዳደሪያ የሚሆን ህግ ምእመን እንዲያወጣ አድርጎ 2ሚሊዮን ህዝብ ደገፈው እያሉ ማስወራትም ብዙም አያሳምንም.ቁጥርንና ፐርሰንተን ማርከስ ነው.
  ካህናት ባለመሳተፋቸው ቃለዐዋዲው የማያውቃቸው አዳዲስ የስራ መስኮች ተፈጥረዋል፣በቃለዐዋዲው ከተጠቀሱ ስራ መዘርዝሮች ጋር የሚጋጩ አዳዲስ የስራ መደቦችና መዘርዝሮች ተካተዋል.በዚህ ሁኔታ ደግሞ ቃለዐዋዲው ካልተሸሻለ በቀር ጥናቱን በምንም መንገድ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም.ም/ቱም ቃለአዋዲው ከጥናቱ ስለሚጣረስ.ከተጣረሰ ደግሞ የበላይ የሚሆነው መመሪያው ሳይሆን ቃለዐዋዲው ነው.ለምሳሌ፡አሁን በቀረበው ጥናት መሰረት አንድ አለቃ በፋይናንስና በሰው ቅጥር ዙሪያ ሚና እንደሌለው የተገለጸ ሲሆን በቃለዐዋዲው ደግሞ ሚና እንዳለው ተደንግጉዋል. አንድ አለቃ የለም እኔ በቃለዐዋዲው ነው የምመራው የምን ጥናት የምን መመሪያ ነው ቢል መብቱ ነው.ቃለዐዋዲው የበላይ ስለሆነ.ይሄ ሁሉ እንግዲህ ካህናትን በማግለል እናውቅላችሁዋለን በሚል መንፈስ ስለተሰራ ነው.
  አውቃለሁ. ማህበረቅዱሳንም የቤተክርስቲያኒቱ አካል ነው.ግን ይህ አካልነቱ እንደ አንድ ባለድርሻ በጥናቱ የመሳተፍ መብት ይሰጠው እንደሆነ እንጅ ጠቅልሎ ስልጣኑን ወስዶ ስለካሽ ሬጅስተር በገዳማውያን ጸሎት ታግዠ አጠናሁ ለማለት እስኪደፍር ስልጣን መስጠት ተገቢ አይደለም.በምሳሌ ላጠናክረው፡መንግስት አንድ ሲሆን አካላቱ የሚሆኑት ሚኒስትሮቹ ደግሞ ብዙዎች ናቸው.ታዲያ በእነዚህ የአንድ አካል ልዩ ልዩ ብልቶች በሆኑት የመንግስት መዋቅሮች አሰራር ግብርና ሚኒስቴር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መመሪያ የሚያወጣበት አካሄድ የለም.ሁሉን አቀፍ እቅዶች ማለትም እንደትራንስፎርሚሽን አይነቶችም ቢሆኑ ሁሉም ወገን የየራሱን ሀሳብ ጨምሮባቸው ይወጣሉ እንጅ አንዱ ስላንዱ አውቅልሀለሁ እያለ አያወጣም.ስለዚህ በምንም መመዘኛ ያለካህናት ተሳትፎ በማህበረቅዱሳን ሞኖፖሊ የተሰራው ጥናት ሂደቱም ሆነ ይዘቱ ጉድለት አልነበረበትም ማለት ይከብዳል.ለዚህ ጉድለት አንዱ አቡነ እስጢፋኖስ አስተዋጽኦ አላደረጉም ለማለትም አስቸጋሪ ነው.
  ስለጥናት ብቻ እየሰበኩ መልካም አስተዳደር ሲጠፋ ማየትም የቤተክርስቲያን ተቆርቁዋሪ ነኝ ከሚል ወገን አይጠበቅም.ስለሆነም እንደኔ ወይ ቦታውን በሚመጥን መልኩ አመራር መስጠት ወይም ሌላው ባለተራ እንዲሞክረው መንበሩን መልቀቅ መፍትሄ ነው.

  ReplyDelete
 4. የሚገርመኝ ነገር ሌላ ሥራ የለህም ጎንበስ ብለው የሠውን ቂጥ ስያዩ ይራስ ይታያል አሉ እና አባ ሰላማ የተባልክ ከአባ ሰላቢ ነፃ ለመሆን የመዳን ቀን ዛሬ ነውና ንሥሓ ግባ ከድንግል ማርያምና ከልጇ ከወዳጇና ከቅዱሳን መላዕክት ካስቀየምካቸው ቅዱሳን አባቶች ጋር ታረቅ ታጠብ መጀመሪያ የራስህን ጉድፍ ተመልከት ልቦና ይሥጥህ

  ReplyDelete
 5. wow wow wow brother too sad
  for our church.

  ReplyDelete
 6. እረ እባካችሁ ተቻቻሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን በሌላ ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ መሳቂያ መሳለቂያ አታድርጓት ሁሉችሁም ለቤተ ክርስቲያን አስባችሁ አይደለም ለግል ጥቅማችሁ ነው እንጂ በድንግል ማርያም

  ReplyDelete