Wednesday, January 29, 2014

የዘንድሮ ጥምቀት በሎስ አንጀለስ

Read in PDF
የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን አዳዲስ እና እንግዳ ነገሮች ተከስተዋል። የሎስ አንጀለስ የጥምቀት በዓልን በመላው ዓለም የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ሁሉ ልዩ የሚያደርገው የበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት አይደለም። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ትላልቅ የወንጌል ሰዎች በመፈራረቅ የእግዚአሔርን መንግሥት ምሥጢር የሚገልጡበት በመደማመጥና በአንድነት መፈሳዊ ዝማሬዎች እንደ ውሃ የሚፈሱበት፣ የእግዚአብሔር ክብር በግልጥ የሚታይበት በዓል ነው። ጥምቀት መከበር ካለበት እንደ ሎስ አንጀለስ ነው። በካልፎርኒያ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የፕሮቴስታንት እምነት አባላት ሳይቀሩ ወንጌልን ለመስማት ከሩቅ የሚመጡበት ነው። ወንጌል በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ ሲሰበክ በታሪክ አይታወቅም ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንትና ካህናት ሰባክያን ጭምር ቁጭ ብለው ወንጌል የሚማሩበት ጊዜ ቢኖር የሎስ አንጀለስ ጥምቀት ነው። ሕዝቡ የዓመት ቀለቡን እንደሚሰበስብ ገበሬ መንፈሳዊ እና መለኮታዊ ምሥጢራትን ሰብስቦ ወደ ቤቱ የሚገባበት ጉባኤ ነው። ጥምቀት በሎስ አንጀለስ ከባሕላዊ እሴትነቱ ይልቅ የመዳን ምሥጢር በሰፊው የሚገለጥበት የደከመው በርትቶ የተጠራጠረው አምኖ ያላወቀው ንስሐ ገብቶ የተጣላው ታርቆ የሚመለስበት ልዩ በዓል ነው። የታደለም ሚስት ወይም ባል ሊያገኝ ይችላል።
  ይህን በዓል መንፈሳዊ ውበት እንዲጎናጸፍ ያደረጉት ግን ታሪክ የማይረሳቸው የቅድስት ማርያም እና የድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ናቸው የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን ሁሉም ባይሆኑም የክርስቶስን ምሥጢር የተረዱና በእግዚአብሔር የተደሰቱ ናቸው። ካሊፎርኒያዎቹ  በእግዚአብሔር ሥራ የሚደነቁ በወንጌል ጉዳይ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ጤነኛ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

 እንደዚህ ዓይነቱን ጤነኛ ሕብረተ ሰብእ በመፍጠር እውነተኛውን ወንጌል በመስበክ ትልቅ ሚና የተጫዎቱት ግን ሰባኪዎቹ ናቸው። ዘንድሮ በቅድስት ማርያሙ መነኩሴና በዲ. ግማዊ ዘዳላስ አማካኝነት ሰባኪዎች መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት መልካም ገጽታ አልታየም ነበር። ያንን ልዩ ሰማያዊ ፍቅር የሚያንጸባርቅ ጉባኤ ባዕድ ነገር ተቀላቀላቅሎበት ነበር ተብሏል። ልዩነቱን በትክክል ለማሳየት ይመስላል። ለረጅም ጊዜ የጥምቀትን በዓል ውበት ከሚሰጡት ሰባኪዎች መካከል ዘንድሮ አንዱም አልተጋበዘም ነበር። ለምሳሌ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ ዶ.አባ ገ ሥላሴ፣ ቄስ መላኩ ባወቀ፣ ቄስ ልዑለ ቃል አካሉ፣ ቄስ መብራቱ ኪሮስ፣ ቄስ እንዳልሃቸው፣ መ/ተከስተ ጫኔ ዋና ዋና ሰባኪዎች ሲሆኑ በዘንድሮው ጥምቀት አልተገኙም ተብሏል። ሌሎች አዳዲስ ሰባኪዎች ከገለልተኛ የተጋበዙ ሲሆን የተለመዱት ሰባኪዎች ተቃዎሞ እንደሌላቸው ነገር ግን በእልህ ለበቀልና ለቂም ልዩነት ማሳያ መሆኑ እንዳሳዛናቸው ሲናገሩ ቆይተዋል። የመከፋፈል ሴራ እንዳለ አስቀድመው የነቁ የሁለቱም አባያተ ክርስቲያናት ምእመናን አንድነታቸውን ለመጠበቅ ውስጥ ለውስጥ ሲመካከሩ ቆይተዋል። ከተጋበዙት አዳዲስ ሰባኪዎች ውስጥ ዲ ግማዊን ጨምሮ ቀሲስ ደረጀ ስዩም ከዋሽንግተን ዲሲ፣ ቀሲስ መኮነን ከሂውስተን መድኃኔ ዓለም ይገኙበታል። ቀሲስ ደረጀ ስዩም የክርስቶስን ምሥጢር የተረዳና ራሱን ከፍርሐት ነጻ ያደረገ ሰባኪ መሆኑ ይነገርለታል።
 በርካታ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ልዩነት ባመጡ ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ እንደነበር የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሌላ በኩል ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደተቆሙት ጉባኤውን ለሁለት ለመክፈልና ለማበጣበጥ የተዘጋጁ ቡድኖችም ነበሩ። የፓትርያርኩን ደብዳቤዎች የሚሽሩና ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያገለግሉ የሲኖዶሱ ሰባኪዎችን የሚቃወም ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ለሕዝብ ሊበተን ታስቦ ነበር ተብሏል። ይህን ወረቀት ያዘጋጁ ሰዎች የጓዳ ስብሰባ በማድረግ ከፍተኛ ቀውስ በመፈጠር የማይበርድ ልዩነት ለማምጣት አስበው ነበር። ይህን የሰይጣን ሐሳብ አስቀድሞ ያወቀው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ጉባኤውን በመንፈስ ቅዱስ በመቆጣጠር የሰይጣንን ሥራ አፍርሶታል። የእግዚአብሔር ልጅ የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ተገለጠ 1ዮሐ 3፡8 ተብሎ እንደተጻፈ የሎስ አንጀለስ ምእመናን ጠላት ዲያብሎስን ከግራቸው በታች በመቀጥቀጥ መንፈሳዊ ድልን አጎናጽፏቸዋል።
  ነገሩ እንዲህ ነው ሳይታሰብ ወደ ጉባኤው የተጋበዘው ቀሲስ ደረጀ መድረክ ላይ ከወጣ በኋላ የተዘጋጀበትን ትምህርት እየተወ እግዚአብሔር የተናገረውን ሲሰብክ ሰንብቷል። የቀሲስ ደረጀ ሐሳብ ቀርቶ የእግዚብሔር ሐሳብ ሲገለጥ ነበር። መከፋፈልን እና ዘረኝነትን በማውገዝ ከእግዚአብሔር ቃል እየጠቀሰ ይቅርታን ሰበከ፣ ቃሉን ሲናገር ምንም ዓይነት ፍርሐትና ሐፍረት አይታይበትም ነበር። በርሱ ስብከት ላይ የዘርፌ መዝሙር "አለው ነገር‚ ሲጨመር ደግሞ ሰይጣን የሰውን አእምሮ ለቆ ተሰደደ። ወዲያው ታቦት እንደወረደ አቶ ግርማ የሚባል የድሮ ዘፈን ባለሙያ አቡነሽ ዘፋኝ በነበረችበት ጊዜ በድያታለሁና ዛሬ ባባታችን ቤት ተገናኝተናል በሕዝብ ፊት ይቅርታ እጠይቃታለሁ አለ። አቡነሽም ተነሥታ ይቅርታዋን አደረገች። ተከታትሎ ቀሲስ ደረጀ ስዩም እንደተለመደው የተዘጋጀበትን ርእስ ትቶ ስለ ይቅርታ ማስተማር ጀመረ፣ ጣቱን ወደ ጳጳሳቱና ካህናቱ በመጠቆም ተነሡ ታረቁ በማለት በድፍረት ተናገረ። ችግሩ እነርሱ መሆናቸውን በመግለጥ ሕዝቡ እንዲነሣና በሃይማኖት አባቶቹ ላይ እንዲጮህ ጠየቀ። ሕዝቡ በእንባና በጩኸት ሲታወክ ይቅርታውን የሚጀምር አልተገኘም ነበር። አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ ተነሥተው የበድልኋችሁ ይቅር በሉኝ እያሉ ሲዞሩ ጳጳሳቱም ሆኑ ካህናቱ አንገት ላንገት በመያያዝ ሲላቀሱ ታይተዋል። ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ የ90 ዓመት ሽማግሌ ሆኜ ማስታረቅ ሲገባኝ አላቻልሁም ጥፋተኛው እኔ ነኝ ይቅር በሉኝ በማለት በሕዝብ ፊት ራሳቸውን ዝቅ አድረገው የእግዚአብሔርን ከፍታ አግኝተዋል። በእለቱ የሰውም ሆነ የሰይጣን ሐሳብ ፈርሶ የክርስቶስ ሐሳብ ጸንቶ በዓሉ ተጠናቋል።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የመከፋፈል አላማ ይዞ በሥውር ሲንቀሳቀስ የነበረው የነዲያቆን ግማዊ ቡድን እቅዱ በድንገት በመበላሸቱ በድንጋጤ ሲርበተበት ታይቷል። ቡድኑ በትልቅ ኪሳራ ወደየመጣበት መመለሱን ምንጮች ተናግረዋል። ልዩነቱን ለማስፋት እንደ ምንጭ ሆነው የተጠቀሱ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት በቅዱስ ፓትርያርኩ ተቀባይነት ቢያገኙም በብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ውድቅ ሆነው የነበረ ሲሆን እርቁ የጸና እንዲሆን እነዚህ አብያተ ክርስቲያናትን አቡነ መለከ ጸዴቅ እንዲቀበሉ አንዳንድ ስደተኛ ምእመናን በመማጸን ላይ ይገኛሉ። ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጠየቁት ይቅርታ መሠረት ጸንተው እንዲቆሙ እነዲያቆን ግማዊን ካጠገባቸው ማራቅ የግድ ነው። ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ታጥቦ ጭቃ እንደሚባለው ሁከቱ እንዳይባባስና ክፍፍሉ እንዳይሰፋ የብዙዎች ስጋት ነው ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል።


16 comments:

 1. ዘመነ አስተርእዮ
  አስተርእዮ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን መታየት መገለጥ ማለት ነው፡፡ ገሐድ የሚለው ቃልም በጾምነቱ ሌላ ትንታኔ ሲኖረው ትርጉሙ ያው መገለጥ ማለት ነው፡፡ በግሪክ ኤጲፋኒ ይሉታል፡፡ የኛም ሊቃውንት ቀጥታ በመውሰድ ኤጲፋኒያ እያሉ በዜማ መጻሕፍቶቻቸው ይጠሩታል፡፡ ትርጉሙም ከላይ ከጠቀስናቸው ጋር አንድ ነው፡፡

  አስተርአየ የተባለው ግሥ ራሱን ችሎ ሳይለወጥ በአምስቱ አዕማድ የሚፈታ ብቸኛ ግሥ ነው፡፡ ይህም ማለት፡- አስተርአየ፤ ታየ፤ ተያየ፤ አሳየ፤ አስተያየ፤ አየ ተብሎ ይፈታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዘመነ አስተርእዮ ሲያጥር ከጥር 11 ቀን እስከ ጥር 30 ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት 20 ቀናት ይሆናሉ፡፡ ሲረዝም ደግሞ ከጥር 11 ቀን እስከ መጋቢት 3 ቀን ይሆናል፡፡ ይህም 53 ቀናት ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

  ጌታን ለሐዋርያት ህፅበተ እግር ያደረገበት ቀንም ከጸሎተ ሐሙስ እስከ ጰራቅሊጦስ ቢቆጠር 53 ቀናት ስለሚሆኑ የእነዚህ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ዮሐንስ በጥምቀት ዕለት ለልዕልና /ጌታ ሰውን ምን ያህል እንዳከበረው/ ለማሳየት እጁን ከጌታ ራስ በላይ ከፍ እንዳደረገ ጌታም ለትህትና እጁን ከሐዋርያት እግር በታች ዝቅ አድርጎ እግራቸውን አጥቧቸዋልና ነው፡፡ ጥምቀት የህጽበት አምሳል ሲሆን፤ /ህጽበት/ መታጠብ በንባብ አንድ ሆኖ ሁለት ምሥጢራት አሉት፡፡

  አንደኛ፤- ምእመናን የእንግዳ እግር እንዲያጥቡ ትምህርት ማስተማሩ ሲሆን፤ ሁለተኛው ለሐዋርያት ጥምቀት ነው፡፡

  በጸሎተ ሐሙስ ቢጠመቁም መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት የጰራቅሊጦስ ነውና ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፤ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያን ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት ጥምቀት እንደጠየቀውና ጥምቀታቸው ህጽበተ እግር መሆኑን እንደመለሰለት፡፡

  በሌላ በኩል ከዘመነ ልደት እስከ ጥምቀት ተወልደ፤ ተሰገወ /ሰው ሆነ/ ይባላል እንጂ አስተርአየ አይባልም፡፡ ከጥምቀት በኋላ ግን አብሮ ተባብሮ ተጠምቀ፤ ተወለደ፤ ተሰገወ አስተርአየ ይባላል፡፡ ከጥምቀት በፊት አስተርእዮ ለመባሉ በሦስት ነገሮች ነው፡፡

  አንደኛ፡- የማይታየው ረቂቅ አምላክ በበረት ተወልዶ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ ቢታይና እንደ ሕፃን ሲያለቅስ ቢሰማም ሰው ሁሉ ሠላሳ ዓመት ሲሞላው ሙሉ ሰው ይሆናል እንደሚባለው፤ አምላክ ነኝ ብሎ በአንድ ቀን ሳያድግ በጥቂቱ ማደጉንና ስደት እንደ ውርደት ሆኖ እንዳይቆጠር ለሰዎች ጀምሮ ለመስጠት፤ ሄሮድስም ሊገድለው ይፈልገው ስለነበር የሚሰደድበት እንጂ የሚታይበት ስላልነበረ ነው፡፡

  ሁለተኛ፡- ሰው በተፈጥሮም ሆነ በትምህርት አዋቂ ቢሆን ለሚመለከተው ሥራና ደረጃ እስከ ተወሰነ ጊዜ ይህ ሕፃን ለእንዲህ ያለ ማዕረግ ይሆናል አይባልም፡፡ ተንከባክባችሁ አሳድጉት ይባላል እንጂ፤ አዋቂ ነው አይባልም፡፡ ያውቃል ተብሎም ለትልቅ ደረጃ አይበቃም፡፡ በየትኛውም ሓላፊነት ላይ አይሰጥም ራሱን በመግዛት ይጠበቃል እንጂ፡፡ እንዲሁም ጌታ የመንፈሳዊ እና የሥጋዊ ባለሥልጣን ቢሆንም ፍፁም ሰው ሆኗልና የሰውን ሥርዓት ከኃጢአት በቀር ለመፈጸም በበሕቀ ልሕቀ ይላል፡፡ አምላክ ነኝና ሁሉን በዕለቱ ልፈጽም ሳይል በየጥቂቱ ማደጉን እናያለን፡፡ በዚህም የተነሣ ሰው ሁሉ 30 ዓመት ሲሆነው ሕግጋትን እንዲወክል እንዲወስን እስከ 30 ዓመት መታገሡ ስለዚሁ ነው፡፡ ከሠላሳ ዓመት በኋላ ግን ሰው ቢመቸው ይወፍራል፤ ቢከፋው ይከሳል እንጂ ቁመት አይጨምርም አይቀንስም፡፡ ስለዚህ ጌታ ሙሉ ሰው የ30 ዓመት አዕምሮው የተስተካከለለት ሰው /ጎልማሳ ሆኖ በመታየቱ ዘመነ አስተርእዮ ተብሏል፡፡

  ሦስተኛው፤- በ30 ዓመት እሱ ሊጠመቅበት ሳይሆን የመጀመሪያ መንፈሳዊ ሕግና ሥርዓት መሠረት የሆኑ ጥምቀትንና ጾምን ሰርቶ በመሳየትና መመሪያ አድርጎ በመስጠት አምስት ገበያ ያህል ሰው የቃሉን ትምህርት ለመስማት፤ የእጁን ተአምራት ለማየት፤ እሱ ሙሉ ሰው ሆኖ ተገልጾ ትምህርት፤ ተአምራት የሚያደርግበት ሥራዬ ብሎ የመጣበት መንፈሳዊ ሕግና ሥርዓት የተፈጸመበት ዘመን ነው፡፡

  የታየውም ብቻ አይደለም፤ አብ ይህ የምወደው ልጄ ነው፤ ሲል መንፈስ ቅዱስም በእርግብ አምሳል ረቂቁ የታየበት የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ምሥጢር የተገለጠበት ስለሆነ ዘመነ አስተርእዮ ተብሏል፡፡

  በዚህ ምክንያትም ሌሎች በዓሎችም ይጠሩበታል፡፡ ለምሳሌ ድንግል ማርያም ጥር 21 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት ለጻድቃን ሰዎችና ለመላእክት በሰማይና በምድር የተሰጣት ጸጋና ክብር የተገለጸበት ዕለት ስለሆነ በዓሉ አስተርእዮ ማርያም ይባላል፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንት በዚህ ቃል ሐሳባቸውን ያስተባብራሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ አምላክ በሥጋ ከድንግል መወለዱን በዚህ አካለ መጠን ለዓለም መገለጡን አስተርእዮ ብሎ ሲናገር፤ አባ ጽጌ ብርሃን ደግሞ በማኅሌተ ጽጌ “የትንቢት አበባ እግዚአብሔር እኛን ሥጋ የሆነውን የአንቺን ሥጋ ለብሶ በምድር እንደተገለጠ ለእኛም እንዲታወቅ ድንግል ሆይ የወገናችን መመኪያ ዛሬ ለእናታችን ለማርያም በሰማይ ፍጹም በደስታ መገለጥ ሆነ እያልን እናመሰግናለን” ብሏል፡፡ ዳዊትም እንዲህ አለ “በከመ ሰማዕና ከማሁ ርኢነ” መዝ. 47፡6 ፡፡ በነቢያት ይወለዳል ሲባል የሰማነው በበረት ተጥሎ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግዕዘ ሕፃናት ሲያለቅስ ሰማነው እንዲሁም በዮርዳኖስ ሲጠመቅ አየነው፡

  ReplyDelete
 2. betam des yimil zena new

  ReplyDelete
 3. ያቀረባችሁት ዜና በአብዛኛው ትክክል ቢሆንም አንዳንድ ስህተቶችን አግኝቼበታለሁ። ለምሳሌ" አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ ዶ.አባ ገ ሥላሴ፣ ቄስ መላኩ ባወቀ፣ ቄስ ልዑለ ቃል አካሉ፣ ቄስ መብራቱ ኪሮስ፣ ቄስ እንዳልሃቸው፣ መ/ተከስተ ጫኔ ዋና ዋና ሰባኪዎች ሲሆኑ በዘንድሮው ጥምቀት አልተገኙም ተብሏል። " የሚለው ዜና ትክክል አይደለም። እዚያው ወረድ ብሎ አባ ወልደትንሳኤ ይቅርታ ለመጠየቅ የመጀመሪያው አባት እንደሆኑ ገልጻችሁዋል። ስለዚህ አባ ወልደትንሳኤ ነበሩ ማለት ነው። መምህር ተከስተ የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አገልጋይ ስለሆነ እርሱ እንዳውም ቅዳሜ ሙሉ ቀን የፕሮግራም መሪ ነበረ ። ቀሲስ መላኩ ባወቀ ከሳውዝ አፍራካ ቅዳሜ ተመልሶ በእሁዱ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ አይቼዋለሁ ምስክርነቱንም ሰጥቷል ። ሌሎችን የጠቀሳችሁዋቸውን ማለትም ቄስ ልዑለ ቃል አካሉ፣ ቄስ መብራቱ ኪሮስ፣ ቄስ እንዳልሃቸው፣ እኔመሪ አላየሁዋቸውም። በቀረው እግዚአብሔር በቀሲስ ደረጀ በኩል ያደረገውን ድንቅ ስራና ስለጉባኤው (በዓሉ) አከባበር የዘገባችሁት ትክክል ነው ። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ትላልቅ የወንጌል ሰዎች በመፈራረቅ የእግዚአሔርን መንግሥት ምሥጢር የሚገልጡበት በመደማመጥና በአንድነት መፈሳዊ ዝማሬዎች እንደ ውሃ የሚፈሱበት፣ የእግዚአብሔር ክብር በግልጥ የሚታይበት በዓል ነው።።።።ሕዝቡ የዓመት ቀለቡን እንደሚሰበስብ ገበሬ መንፈሳዊ እና መለኮታዊ ምሥጢራትን ሰብስቦ ወደ ቤቱ የሚገባበት ጉባኤ ነው። ጥምቀት በሎስ አንጀለስ ከባሕላዊ እሴትነቱ ይልቅ የመዳን ምሥጢር በሰፊው የሚገለጥበት የደከመው በርትቶ የተጠራጠረው አምኖ ያላወቀው ንስሐ ገብቶ የተጣላው ታርቆ የሚመለስበት ልዩ በዓል ነው።።።።
  እግዚአብሔር አባቶቻችንን በመንፈስ አንድነትና ህብረት ይጠብቅልን። አሜን።።

  ReplyDelete
 4. ይህ መልካም ዜና ነው። ቸር ወሬ ማውራት ደስ ይላል። በርቱ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. እናንተን አባ ሰላማ ሳይሆን አባ አደፍርስ ነበር መባል የነበረባችሁ። አንባቢን ወይም ሕዝብን እንደማትፈሩ ተረድተናል። ባይሆን እግዚአብሔርን አትፈሩም? እናንተ እውነት ስለ እግዚአብሔር ለመናገር የሞ ራል ብቃት አላችሁ? ጥላቻችሁ ከመብዛቱ የተነሳ የሰውን ስም እየቀየራችሁ ትጽፋላችሁ። በጥላቻ የሚኖር ደግሞ እግዚአብሔርን ሊያውቅ አይችልም። በጥላቻ የሚኖር ብብሩህ ህሊና ሊያስብና ሊወስን አይችልም። በጥላቻ የሚኖር ኃይል የለውም ለምን ቢባል እግዚአብሔርን አልያዘምና። ከጥላቻችሁ የተነሳ የተባለውን ሳይሆን ያልተባለውን ትናገራላችሁ። ለመሆኑ የትላይ ነው "ችግሩ እነርሱ መሆናቸውን በመግለጥ ሕዝቡ እንዲነሣና በሃይማኖት አባቶቹ ላይ እንዲጮህ ጠየቀ" ያላችሁት የተፈጸመው? በመምህሩ የተባለው አባቶቻችሁን ይቅርታ ጠይቁ ነው። ይህንንም ሲል ቀሲስ መላኩ አይደለም እግር ላይ የወደቀው? ይህንን በማድረጉም አባቶች መከበር እንዳለባቸው በአርያነት አስተምሯል። አባ ወልደትንሳኤም ይህንኑ ፈጽመዋል። ሁልጊዜ ስለልዩ ነት ትጽፋላችሁ። ስለ ፍቅርና መከባበር ግን አትጽፉም። ዋኖቻችሁን አክብሩ ይባላል እናንተ ግን የ90 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋውንና ሕይዎታቸውን በሙሉ ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉትን አባት ዝቅ ለማድረግ ትሞክራላችሁ። አሁን በእርሳቸው ወይም በመጽሓፋቸው ያልተማረ አለ? ታዲያ መምህሩን ሊያዋርድ የሚፈልግ ምን ይሉታል? ምስጋና ያመጣልናል ብላችሁ እንዳታስቡ። በእርግጥ በገዝ እጃችሁ እርግማንን እየጠራችሁ ነው። እናንተ ካላስተማራችሁ ስብከት የማይመስላችሁ፣ እናንተ ካልዘመራችሁ መዝሙር የማይመስላችሁ የዚህ ዓለም ባለሟሎች እንጂ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አትባሉም። እውነተኛ አገልጋዮች ብትሆኑማ ሌሎች አገልጋዮች በመብዛታቸው ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር።
  http://www.youtube.com/watch?v=ixxycVw4TQY

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሰተያየቱ ትንሽ ብስለት የጎደለው በመሆኑ የተናቀ ነው ታሪክ የምታውቅ ከሆነ የ90 አመት እድሜ የምትላቸው አዘውንት በስማቸው መጽሐፍ ተጻፈ እንጅ እሳቸውና ብእር አይተዋወቁም ይህንን ደሞ ካዋቀኢወች ጠይቅ ለነገሩ አንተ ከበሮ ከመደብደብ በቀር ሌላ ነግር አታውቅ አየፈረድብህም

   Delete
  2. አባስላማ ቀጥሉበት እኔ ግን ያልተመቸኝን ነገር ልናገር ቆይ በዚህ ታላቅ ጊዜ መመስግን እና መጠራት ያለበት ማን ነው በድነኩአኑ መሀል ሆኘ የነበረውን ነገር እታዘብ ነበር ደያቆኑም ቄሱም መነኩሴወም ጰጳ ሱም ተንስቶ የሚያመሰግነው የዘጠና አመት ሽማግሌ እያለ አንድ ጳጳስ ነበር በዘመናት የሸመገለውን ጌታ ረስተውት ነበር እና ይህ ከንቱ ውዳሴ መቅረት እንዳለበት ማስተማር አለባቸሁ

   Delete
  3. የዘረኝነት መንፈስህና ያልታወቀህ ድንቁርናህ ስለጋረደህ እንጂ አባ ሰላማዎች ትክክለኛውን መረጃ አስተላልፈዋል። ስለአባ መልከጼዴቅ ማንነት ከንጉሡ እልፍኝ እስከ ቤተ ክህነት፤ ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ የታወቀ ነው። ዘጠና የተባለውም እድሜ የተንኮል፤ የክፋት፤ የመብጥበጥ ሥራ የተከናወነበት መሆኑን ከሚያውቁት ተረዳ። በጭፍን አስተሳሰብ እየሔድህ እውነትን አትቃወም።
   የብርሃናት አምላክ ዓይነ ልቡናህን ያብራልህ።

   Delete
  4. አይ ክርስቲያንነት። ለመሆኑ ግማዊ የሚል የየት አገር ስም ነው። የምታደንቓቸው ሰወች ሁሉ እናወቃቸዋለን። የዚሀ ዊብሳይት ባለቤቶቸ ናቸው። በከረስቲያኖች ስም ለምሰሩት ውንብድናና ስም ማጥፋት ትጠየቁበታላሁ። ካስፈለገ የዚሀን ዊበሳይት አዘጋጆች ስም ዝርዝር እናወጣለን።

   Delete
 6. ሰላም ጓደኞቼ በአይኔ ያየሁትን ገጠመኜን ይዤላችሁ መጥቻለሁ አንብቡ፤ አስተያየታችሁን እንቀበላለን፤ የሉተራውያኑንም የተለመደ ፕሮቴስታንታዊ ስድብ በተመሳሳይ መልኩ እንቀበላለን፡፡
  መልካም ንባብ
  …………..ብዙ ህዝብ ተሰብስቧል አንድ ሰው ቆሞ የጌታ ክብር እየወረደ ነው ጩሁ በማለት በከፍታ ድምጽ ይናገራል፤ግማሹ ይጮሃል፤ግማሹ ይስቃል ፤ሌላው ደሞ ከወንበር ወንበር ይዘልና ጠረጴዛ ላይ ወጥቶ ያለቅሳል፤ በማጅራቱ ወንበር ተሸክሞ ካልዘለልኩ ብሎ ለያዥ ለገናዥ የሚያስቸገረም አለ ምክንያቱም መንፈስ ውርዷልና ፤ ብቻ ምኑ ቅጡ……….
  ይሕ ሁሉ የሚሆነው የት መሰሎት ሲኒማ ቤት (ቤተ ተውኔት) ነው ብለው ከሆነ ተሳስተዋል፤ ቦታው ከ6 ኪሎ
  ወደ ቤላ ሲጓዙ የቀበናን ወንዝ ተሸግረው ወደ ቀኝ እንደታጠፉ ካለው በነሱ አጠራር ሙሉ ወንጌል ቸርች ይሉታል፤
  በዚህ አዳራሽ የማይሰራ ስራ የለም ፤እስቲ በዛ ያጋጠመኝን ላወጋችሁ ነውና አዳምጡኝ፡፡
  ከዚህ በፊት እንዳጫወተወኳችሁ እኔም በወቅቱ የእምነቱ ተከታይ በመሆኔ በእለቱ ቀደም ብዬ ነበር በቦታው የታደምኩት፤ ሰውነታቸውን በስስ ሱሪ የወጠሩ የፕሮቴስታንት ኮበሌዎች ወደ በአዳራሹ ተሰብስበዋል …………
  ፕሮግራሙ ተጀመረ አንድ ኮሜዲ አይነት ሰውዬ በእለቱ እንዲያስተምር መድረኩ ተሰጥቶት አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሳይናገር ኢየሱስ ጌታ ነው!! እያለ በመፎከር የኢየሱስን ጌትነት ሳይሆን የራሱን ጀብዱ አሜሪካን ሃገር የፈመውን ተአምር በእንግሊዘኛና በአማርኛ ልሳን ሲያወራ አረፈደ ፤ የሚያስገርመው ህዝቡ ያለቦታው አሜን!! የሚለው ነገረ ነው፤ ባለቤቴን ሳገባ የ17 አመት ኮረዳ ነበረች ሲል ታዳሚው አሜን!! ይላል፣ የመጀመሪያ ልጄ እኔን ትመስላለች! አሜን!!! ……………..
  ቀጥሎ ድምጸ ምልካሙ ጎልማሳ በባንዱ ታጅቦ ማስጨፈር ጀመረ፤ ሁሉም ይደንሳል፤ ሁሉም ይጮሃል፤ በዚህ መሃል አንድ ሃብተ መርገም የተሰጠው ሰው፤ የተለያየ አብታዊ መፈክሮቹን ካሰማ በኋላ የተለመደውን ፕሮቴስታንታዊ እርግማን መራገም ጀመር፤ ሃሌ ሉያ ብሎ የራሱን ቅጥልጥል የበዛበት ዲስኩር ካሰማ ቡሃላ መራገም ጀመረ፤
  የኦርቶዶክስ መንፈስ በኢየሱስ ስም ይመታ ሲል አሜን!! ይሉለታል፤
  የማርያም መንፈስ በየሱስ ስም ይመታ………አሜን!!!
  የገብርኤል ›› ›› ›› ›› ………. ››
  እኔን የገረመኝ አንድም ጊዜ የሰይጣን መንፈስ ሲወገዝና ሲረገም አለመስማቴ ነው፤
  ከእርግማኑ በኋላ በድጋሚ ጭፈራው ደራ፤ ሃይ ባይ በሌለበት በዛ ሰፊ መጋዘን ሁካታውና ከበርቻቻው ጩኸቱና ዳንሱ ቀጠለ፤ ምንጃርኛ፤ ጎጃምኛ ፤ጉራጊኛ ፤ፈረንጂኛ ፤ቡጊ ፤ቡጊ ምኑቅጡ የሙዚቃ ባንዱም እየደነሰ ያስደንሳል ……
  ታዲያ ግን በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ዘፈን ኃጢያት ነው፡፡ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ… ናይት ክለብ ውስጥ ያሉ በሚያስመስል ሁኔታ የሚደረገው ተግባር እጅግ ያሳፍር ነበር፤
  አንዳንዶቹ ጠረጴዛ ላይ በመቆም ሌሎቹ ወንበሩን ጭንቅላታቸው ላይ በመሸከም ቅጥ አምባሩ በወጣ ቋንቋ ልሳን ተናገርን በማለት ይጮሃሉ፤ ሃለ ሉያ ሻምባራራራራራ…… በገደማነቲሪምባራራራቲሪያ….. ታማታራሪያ……… ዲዲሞስወርታቆፖፖቲ………..ወዘተ በማለት የአማልክቱን ስም እየተጣራ ሲራገም ሁሉም ይረገም ይመረቅ ትርጉሙን ሳያውቅ አሜን ይላል ይዘላል፤
  መቼም ትዕይንቱ ልዩ ነው፤የሚያጓራም አለ፤ ጥቂቶቹ ባለ ውቃቢው ፓስተር ወዳለበት መድረክ ወጥተው ተሰልፈው ሲቆሙና ሰውየው በጣቱ ነካ ሲያደርጋቸው ለመውደቅ ሰልፍ ይዘዋል ለዚሁ ተውኔት የተዘጋጁ ተዋንያን እየደገፉ ያስተኟቸዋል፤ እኩሌቶቹ እየተንደፋደፉ አረፋ ይደፍቃሉ፤
  ጾታዊ ትንኮሳው እንዳለ ሆኖ የሚያለቅሱና ሱሪያቸው ላይ ምናምናቸውን ምናምን የሚያደርጉትን ጎረምሶችንም ታዝቤያለሁ ፤ኡኡታው እሪታው ፉከራው ለቅሶው ……………………
  በሃገሪቱ ላይ ህግ የሌለ እስኪመስል ድረስ ነገ አድገው ሃገር ይረከባሉ የሚባሉትን ሕጻናት በግድ በማስጨነቅ መድረክ ላይ ልሳን ተናገሩ እያሉ ሲያፋጥጧቸው ገና ለአቅመ ትምህርት ያልደረሱትን ብላቴናዎች በዚህ መንፈስ አስረው ሲያስጨንቋቸውና ከፍተኛ የህሊና ኪሳራ ሲያደርሱባቸው ተመልክቻለሁ፡፡
  ከሁሉም በጣም የሚያስገርማችሁ ሳቁ ነው፤ ለቀሶውስ የንስሃ እንባ ነው ይባላል፤ ሳቁስ? እንደጉድ ይሳቃል፤ በላቸው ምስጋና ይጣ ትላላችሁ፤ ለነገሩ የቅዱስ ሳቅ ኣማኞች የሚባል ቸርች አለ አይደል? ባለፈው በመንፈስ መገንደስ፤ ዘንጥ ለክርስቶስ፤ ………….. ወዘተ የተባሉ ቤተ ተውኔቶች እንዳሉዋቸው አንድ ወዳጃችን አስነብባናለች፤
  ……….. አወኩልህ ስላንተ ጌታ እንዲህ ብሎ ነግሮኛል፤እንዲህ ትሆናለህ ተገልጦልኛል …………. ከፈለገ ልቡ የፈቀዳትን ጉብል ጌታ አዞኛል አንቺ የኔ ነሽ ካለ ማን ከልክሎት……….
  በዚህ በፈረንጅ የጥንቆላ መንፈስ ለተያዙ ሰዎች እግዚአብሄር መፈታትን ያድላቸው፤
  ለዛሬው ይቆየን !!!
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 7. እግዚአብሔር ይባርክህ ቀሲስ ደረጄ

  ReplyDelete
 8. False! I think as I understood, you visited protestant church to got women, but you were not successful that was the main reason you said wrong or negative about prorestant worshiping. Becareful!

  ReplyDelete
 9. የታደለም ሚስት ወይም ባል ሊያገኝ ይችላል። yaaaaaaaaaaaaaaaaaaa

  ReplyDelete