Saturday, January 4, 2014

የማቅ የለውጥ መዋቅር በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች ትግል መቀልበሱ የተበሠረበት ስብሰባ ዝርዝር እነሆ


·        አባ እስጢፋኖስ እስከ ልደት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስነት እንዲወርዱ ተጠየቀ
·        የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ታላቁን ሊቅ አቡነ መርሐ ክርስቶስን ተሐድሶ ያሉ ደፋሮች ናቸው!
·        በማቅ የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ውድቅ ሆኖ በሊቃውንት ሌላ ሕግ እንዲዘጋጅ ተብሏል
·        የማቅ አባላት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሕንጻ እንዲለቁ ተጠየቀ
·        “ማቅ የስም አባል እንጂ የቤተክርስቲያን አካል” አይደለም ተባለ
·        ማቅ “እንደ ክብሪት ከጐን ወጥቶ እሳት የሚለኩስ ማህበር ነው፡፡”

ማኅበረ ቅዱሳን ያረቀቀውና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ባለ በሌለ ኀይሉ ሲንቀሳቀስበት የቆየው የለውጥ መዋቅር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች የተደራጀ ትግል መቀልበሱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለተሰብሳቢዎቹ እንዳስታወቁት ባለፈው ቀርበው አቤቱታቸውን ባሰሙ ማግሥት ቋሚ ሲኖዶስ ተሰብብስቦ ማኅበረ ቅዱሳን ያረቀቀው የለውጥ መዋቅር ውድቅ እንዲደረግና የማኅበሩ አባላት ቀርቶ ከማኅበሩ ጋር ምንም ንክኪ የሌላቸው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ አባቶችና ምሁራን በድምሩ 9 አባላቱ ያሉበት ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ የተሠየመ መሆኑን አብሥረዋል፡፡ አክለውም ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብቻ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያኗ በአጠቃላይ የሚሠራ ህግ ነው መውጣት ያለበት ብለዋል፡፡ ለተሠየሙት አባላትም ከጠቅላይ ቤተክህነት ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ ብሥራት በተሰማበት ዕለት በፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፊት ቀርበው አስተያየት እንዲሰጡ የተደረጉት የካህናቱ ተወካዮች ያለአንዳች መሸማቀቅና ያለፍርሀት በመረጃ ላይ የተመሠረቱ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡


ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አንደኛው እንደ ተናገሩት፣ ማቅ አባላቱን በየሰንበት ት/ቤቱ እየሰገሰገና ሰንበት ት/ቤቶች ፈሰስ እንዲያደርጉለት እያስደረገ ሰንበት ት/ቤቶችን የማዳከምና በራሱ ምልምሎች የመዋጥ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ አክለውም በአባ እስጢፋና በደላሎቻቸው አማካይነት ጉቦ ተበልቶባቸውና ከሥራቸው የተፈናቀሉ ከ12 ያላነሱ ጦም አዳሪዎች ወንድሞቻችን ስለሚገኙ እነርሱን በአስቸኳይ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጉ ሲሉ ፓትርያርኩን ጠይቀዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ማቅ የኮፒራይት ሕግን በመጣስ በቤተ ክርስቲያኗና በሊቃውንቶቿ እየነገደ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፣ የሊቃውንቱን የሥራ ውጤትና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብቶችና ንብረቶች በቪዲዮ እየቀረጸ ወደአውሮፓና አሜሪካ በመላክ ዳጎስ ያለ ዩሮና ዶላር እንደሚሰበስብበትና ቤተክርስቲያኗ በስሟ የሚነገድባትን ንግድ እንደማትቆጣጠር ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አንድ በስም ሊጠቅሱት የማይፈልጉት መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በግብረ ሠናይ ስም እየተንቀሳቀሰ 130 ሚሊዮን ዶላር ለሽብር ተግባር አውሎ እንደተገኘ ሁሉ፣ ማቅም በቤተ ክርስቲያን ስም የሚሰበስበውን መጠነ ሰፊ ገንዘብ ለሽብር ተግባር እንደማያውለው ምንም ዋስትና የለም ብለዋል፡፡ በእርግጥም ለእርሱ አልመች ባሉ አንዳንድ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሰባክያነ ወንጌልና መዘምራን ላይ ዱርዬ እየቀጠረ ከቤተክርስቲያን የማስባረር ሥራዎችን እየሠራ መሆኑ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን በሀገረ ስብከታቸው ከሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ማቅ ባደራጃቸው ማጅራት መቺ ቡድኖች ብፁዕነታቸውን ሊያስደበደብ እንደነበረና እንዳስባረራቸውም ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡

ማቅ እንዲህ ዓይነቱን አባቶችን የማዋረድ ሥራ የጀመረው አሁን ሳይሆን ቀደም ብሎ ነው፡፡ በተለይም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶ እንደነበረና እርሳቸውን እንዳይቀበሉ ገና በቆሎ ትምህርት ቤት ሳሉ ይቀሰቀስ እንደነበረ የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፣ በልጅነታችን የእርሳቸው ፎቶ ያሉባቸውን የቤተክርስቲያን መጻሕፍት እያወጣን ፎቷቸውን አጥፉት ቅደዱት እያለ እንድንቀድና ፓትርያርኩን እንድናወግዝ ገንዘብ በመስጠት ጭምር ይቀሰቅሰን ነበር ብለዋል፡፡ 

ሕግ የሚወጣው ሕዝቡ በመረጣቸው እንጂ ባልመረጣቸው አካላት ለዚያውም ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሳቸው ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ በቆሙ አካላት አለመሆኑን የተናገሩት ሌላው አስተያየት ሰጪ “ማቅ የስም አባል እንጂ የቤተክርስቲያን አካል” አለመሆኑን ጠቅሰው፣ “ማቅ ሕግ ያርቅቅ ማለት ኤርትራ ለኢትዮጵያ ሕግ ታውጣላት እንደማለት ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ይህም ማቅ አረቃለሁ የሚለው ሕግ የእርሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የቆመ እንጂ ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንደማይሆን ከአካሄዱ ያስታውቃል ብለዋል፡፡ ማቅ ሕጉን 1500 ገጽ ነው ብሏል፡፡ ለእኛ ኮፒው ይሰጠን ወይም በገንዘባችን ኮፒ እናድርገውና እንመልከተው ብንለው “በአንገቴ ገመድ ይግባ” እንጂ አላሳይም አለን፡፡ አባ እስጢፋኖስም መሐመድም ያርቅቀው ዝም ብላችሁ ተቀበሉት ነው እያሉን ያሉት ብለዋል፡፡ “ለመሆኑ አቶዎች ለቤተክርስቲያን ሕግ የሚያወጡት ከመቼ ወዲህ ነው? ቤተክርስቲያን ሕግ የሚያረቅቁ ሊቃውንት የሏትም እንዴ? አቶ ስለ አብነት መምህራን ምን ያውቃል? አንዱን የማቅ ምልምል አቶ ስለ ድጓ ሳወራው ድጓ የሚባል አለ ወይ አለኝ፡፡ ምዕራፍ የሚባል ደግሞ ምንድነው? አለኝ” በማለት ተሰብሳቢውን አስቀዋል፤ አስጨብጭበዋልም፡፡
እኚሁ አስተያየት ሰጪ ማቅ ለአካሄዱ ያልተመቹትን አባቶች የማዋረዱን ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጎጃም የፈጸመውንና ያዩትን እንዲህ ሲሉ አጋልጠዋል፡፡ “ጐጃም ምድር ታቦቱን ባርኮ የሰጠውን ጳጳስ ታቦቱን አጅቦ እንዳይወጣ በሰንበት ተማሪ አባረሩት፡፡ ይህ ማለት ሰው የወለደውን አትዘዝ ማለት ነው፤ እና የወለድከውን አትጠቀምበት የሚለው ይኸው ማህበር ነው፡፡” ብለዋል፡፡ የማቅ ዓላማ አባቶችን መረጃ ይዤባችኋለሁ እያለ በማስፈራራት ስማችሁን በቪሲዲ እበትነዋለሁ፣ በመጽሔት አወጣዋለሁ በሚል አባቶች ዝም እንዲሉ እያሽመደመዳቸው ይገኛል፡፡ “እንደ ክብሪት ከጐን ወጥቶ እሳት የሚለኩስ ማህበር ነው፡፡” ሲሉም የማቅን እኩይ ተግባር በማይረሳ ምሳሌ አብራርተዋል፡፡

ይኸው ማኅበር አቡነ ጳውሎስ እንዳረፉ፣ “ዘመኑ አሁን ነው፤ ሰርገን የምንገባበት ጊዜ አሁን ነው፤ ስለዚህ የምንገባበትንና ቤተ ክርስቲያኗን የምንቆጣጠርበትን ሕግ እናውጣ፡፡ ሊቃውንቱ መርሯቸው ሲወጡ እኛ እንረከባዋለን የሚል ነው፡፡ ቤተ መንግሥትን ከቤተ ክህነት አጣምረን እንይዛለን የሚል ሕልም ነው ያላቸው፤ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ዘመኑ የእርስዎ ነው፤ ከልጆችዎ ከእኛ ጋር በመሆን የቤተ ክርስቲያናችንን ህልውና ያስጠብቁልን፡፡” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ማቅ ቦታውን በጊዜ የመቆጣጠር ጅማሮዎችን በአንዳንድ ስፍራ እያሳየ መሆኑን የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ “በየሰበካ ጉባኤ ምርጫ በሚል እየመጡ የሥራ ዘመኑን ያልጨረሰውን የሰበካ ጉባኤ አባል ለእነርሱ ስላልተመቸ ብቻ በየምክንያቱ በማውረድ የማህበሩን ሰው እየሰገሰጉ ይገኛሉ፡፡ ቤተክርስቲያንንም እያመሷት ነው” ብለዋል፡፡

አክለውም “እኛው አስተምረን ያመጣናቸው እኛኑ ይሰድባሉ፤ እዚህም ውስጥ (በጳጳሳቱ መካከል) እኮ ችግር አለ በ50 ዓመት ዲቁና ይሰጣል፤ ክህነት እኮ ለአቶዎች ለክብር የሚሰጥ አይደለም፡፡ ክህነት ለአገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ ላይቀድሱበት ቢካኑ ምን ይሠራላቸዋል?” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም “ሕገ መንግሥትን የሚቃረን ሌላ ሕግ መውጣት የለበትም፤ ታዲያ በቤተክርስቲያን ቃለ ዐዋዲውን የሚቃረን የለውጥ መዋቅር ሳንመክርበትና ሳንዘክርበት እንዴት ይወጣብናል? ቃለ ዐዋዲው ተሽሮ ነው ወይስ ምን ምክንያት ይኖር ይሆን?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በአባ እስጢፋ ላይ ያላቸውን አቋምም የገለጹ ሲሆን፣ “የአሁኑ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የማን ረዳት ናቸው? የቅዱስ ፓትርያርኩ ሳይሆኑ የማቅ ናቸው፡፡” ሲሉ አዳራሹ በጭብጨባ ተናግቷል፡፡ ማህበሩ በቤተ ክርስቲያን እንደቫይረስ ተሠራጭቶ በረዳት ሊቀ ጳጳሱ ፈረጂያ ስር ተከቶ በሀገረ ስብከቱ ቢሮ ተሰጥቶት 24 ሰዓት ለግል ጥቅሙ እየሰራ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱን መሸፈቻ አድርገውታል፡፡ ስለዚህ እነዚህ አቶዎች ከሀገረ ስብከት ሕንጻ ለቀው እንዲወጡ ይደረግልን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

በመቀጠል ሌላው አስተያየት ሰጪ አንድ ባለሥልጣን ለሕዝብ ጥቅም ሲሰራ ኑሮ በሙስና ተዘፍቆ ከተገኘ አስቀድሞ እራሱ ግለ ሒስ አድርጎ ለሚያውቃቸው ምስጢሮች ደህንነትና ለሀገር ከዋለው ውለታ አንጻር ሥልጣኑን በገዛ ፈቃዱ በመልቀቅ በሕግ እንዳይጠየቅ በባልደረቦቹ በኩል እንደሚደረግ አስታውሰው፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋም በዚሁ አሰራር መሠረት ሥልጣናቸውን በአስቸኳይ እንዲለቁ ጓደኞቻቸው ጳጳሳት እንዲያግባቧቸው መልእክት ያዘለ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ወቅት አንድ ተናጋሪ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የእኛን ድምፅ ላለመስማትና አቤቱታችንን ላለመቀበል ሁሌም የሚፎክሩት ካልሆነ ወደ ጅማዬ እሄዳለሁ እያሉ ነው፡፡ አንዱ ጓደኛዬ ሰሞኑን “ምነው በከተማው ሰላም ሰፈነ፤ ረዳት ሊቀጳጳሱ የሉም እንዴ አለኝ” በማለት ጉባኤውን በሳቅ አፍርሰዉታል፡፡ ነገር ግን ማስፈራሪያ ያደረጓት ጅማም ብትሆን የኛ የክርስቲያኖች ሁሉ መሆኗን ሊዘነጉ አይገባም ብለዋል፡፡ እኚሁ አስተያየት ሰጪ በዚሁ ቀጥለው “አቡነ እስጢፋኖስ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ይልቀቁ የምንለው የአባቶቻችንን ስም መጠበቅ ግዴታችን በመሆኑ ነው፤ ይህን ሳይደርጉ ቢቀሩ የምናቀርበው ማስረጃ አቡነ እስጢፋኖስን ከአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስነታቸው ብቻ ሳይሆን ከጅማም ሀገረስብከት ብቻም ሳይሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ አባልነትም እንዲሰናበቱ የሚያስደርግ ይሆናል፡፡ ይህንን መረጃ ደግሞ ዛሬ ሳይሆን ያኔ እናቀርባለን፤ ለዚህም እስከ ጅማ መጓዝ አይጠበቅንም ከዚህ እስከ የካ ሚካኤል ድረስ ቢፈጅብን ነው፡፡ የአባቶቻችንን ስም የምንጠብቀው እንደማኅበሩ ስም በማጥፋት ተግባር ባለመሰማራታችን እና እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ስለሆንን ነው፡፡” በማለት ውስጠ ወይራ ንግግር አድርገዋል፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪም “ባልደርስባቸውም አባ እስጢፋኖስ በአባ ጳውሎስ ጊዜ ጥሩ ሰርተዋል ይባላል፤ አሁን ግን የማህበሩ ቃል ኪዳን ስላለባቸው ስፖንሰርም ስለሚሆናቸው የማህበሩን ተልእኮ አስፈጽሜ ታሪኬ ይነገርልኛል እያሉ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማህበሩን ፊት ለፊት አናየውም የሚበጠብጠን በሳቸው ትከሻ ላይ ሆኖ ነውና ቅዱስ አባታችን ረዳትዎን ዘወር ያድርጉልን፡፡ በእጃችን ካለው መረጃ አንጻር ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ይነሱ ከጅማም ሀገረ ስብከት ይነሱ ሳይሆን የሲኖዶስ አባል ሆነው መቀጠል የለባቸውም እያልን ነው፡፡” ብለዋል፡፡

አክለውም ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያደረሰውን በደል አብራርተዋል፡፡ “ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዘረኝነትን ያስተማሩ እነሱ ናቸው፤ አባቶችን መስደብና ማዋረድ ያስተማሩ እነሱ ናቸው፡፡ አባቶችን ተሀድሶ ያሉ እነሱ ናቸው፤ ታላቁን ሊቅ አቡነ መርሐ ክርስቶስን ተሐድሶ ያሉ ደፋሮች እኮ ናቸው! ሊቃውንቱን ተሐድሶ ተሐድሶ ብለው አባረሩ፤ ምእመናኑን ደግሞ አባቶች እንዲህ ናቸው ብለው ወደፕሮቴስታንት ያስገቡ እነሱ ናቸው፤ ከሰበሰቡት ይልቅ የበተኑት ይበልጣል፡፡”

በአዲሱ መዋቅራዊ ጥናት ስብሰባ ወቅት ብፁእ አቡነ እስጢፋኖስ የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊባሉ አይገባም በሚል ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሲነሳ የነበረውን ጥያቄ አወያዮቹ ምላሽ ሳይሰጡ በደስታ እና በሳቅ ስሜት ጥያቄውን በማጀብ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ስምምነት ሲገልጹ እንደነበር ተወያዮቹ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ገልጸው የፓትርያርኩ የፕሮቶኮል ኃላፊ አቶ ታምሩ ሁልጊዜ ቅዱስነትዎን ስንፈልግ ተኝተዋል ይሉናል ለባለጉዳዩም በየጊዜው ተኝተዋል ስለሚባል እኛም ሳናውቅ ስም ሰጥተንዎ (እከ ብለዋቸው ይኾን?) ነበር፡፡ ነገር ግን እውነትም የፍትሕና የሰላም አባት እንደሆኑ አይተናል ነገር ግን እቤትዎና ቢሮዎን ሊፈትሹ ይገባል የሚል አስተያየት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስነታቸውም በየጊዜው እንዲሰበስቧቸው እና መረጃ ልውውጥ እንዲኖር የማጠቃለያ ሐሳብ ተሰጥቷል፡፡ አቶ ታምሩ ግን ጥፋታቸውን ስላወቁ ነው መሰል ለተሰነዘረባቸው ቅሬታ መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ፓትርያርኩ ተሰብሳቢዎቹን፣ “መልካም አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን ይስፈን የሚለውን አልተቃወማችሁም፤ ሰላም ፍቅር አንድነት የሰፈነባትን ቤተክርስቲያን ኃላፊነት፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት አስተዳደር እንዲሆን የቤተክርስቲያን ልጆች ሁላችሁ ትደግፋላችሁ፡፡ ይህ እስከሆነ ድረስ የሚያጣላን ያለ አይመስለንም፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያልሰሩትን ሕግ አንቀበልም ነው እያላችሁ ያላችሁት፡፡ ስለዚህ ኮሚቴው ከማቅ ጋር ንክኪ የሌለው አባልነት ቀርቶ ከእነርሱ ጋር ፈጽሞ ንክኪ የሌለው እንዲሆን ቋሚ ሲኖዶስ ተስማምቶበታል፡፡ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ እየተወረወረ ያለ ከፍተኛ ተቃውሞ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉንም በቅዱስ ሲኖዶስ አመራር እናስተካክለዋለን፡፡” ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ከተናገሩ በኋላ አስፈቅደውና ከእርሳቸው በኋላ መናገራቸው ተገቢ ባለመሆኑ ይቅርታ ጠይቀው የተናገሩት አንድ ሊቀጳጳስ እንዲህ ብለዋል፤ “ይህን በማየቴ በጣም ደስታ ተሰምቶኛል፤ የሚቆረቆሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አሉ ማለት ነው፡፡ የማህበሩ ሁኔታ እንደዚህ ለሁሉም ሰው ግልጽ መሆኑ የሚያስደስት ነው፡፡ እኔ በርግጥ ብቻዬን ያለሁ ነበር የመሰለኝ፡፡ እናንተን ማግኘታችን በጣም ያኮራናል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን የካህናት ጉዳይ ብቻ እንዳታደርጉት አደራ፡፡ በጣም በሰፊው ልትሄዱበት ይገባችኋል፡፡ ግብ ሳትመቱ ወደ ኋላ እንዳትመለሱ፤ ግብ ሳትመቱ ከተመለሳችሁ እናንተ ናችሁ የምትመቱት፡፡

“ቀደም ሲል በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ብዙ አባቶች ስለ ማህበረ ቅዱሳን አልገባንም ነበር፡፡ ሲኖዶሱንና አቡነ ጳውሎስን ሲያዋጉ እና ሲያደባድቡ የነበሩ እነርሱ ናቸው፡፡ ነገ የምንወስንበትን ጉዳይ ዛሬ ማታ ገብተው ለአባቶች መመሪያ ይሰጣሉ፡፡ በዚያ ምክንያት በእነርሱ ተቃጥለው እኮ ነው አቡነ ጳውሎስ የሞቱት፡፡ አሁን ሲያታልሉን ነጠላ አደግድገው ሲሳለሙ የቤተክርስቲያን ልጆች ይመስላሉ፤ እምነት የላቸውም መናፍቃን ናቸው ነው እኔ የምለው፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሰው፣ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሆነ ሰው አባ እገሌ ወልዶአል፤ አባ እገሌ ገሎአል፤ አባ እገሌ ሰርቆአል ብሎ ለመናፍቃን፣ ለአለም ጽፎ አይሰጥም፡፡ እናንተ አሁን ያልተናገራችሁት የለም፡፡ ሁሉን ተናግራችኋል ሙሉ ቀን ብትናገሩ በጣም ደስ ይላል፡፡ እናንተ ባትደርሱ ኖሮ እነርሱ በአቋራጭ ቤተክርስቲያኗን ሊረከቡ ነበር፡፡ አላማቸው ምንድን ነው? ቤተክህነቱንም ቤተመንግሥቱንም ተረክቦ እኛን ስርቻ ውስጥ ወርውሮ ቁራሽ እንጀራ ሊጥሉልን፣ እንደ ውሻ በሰንሰለት አስረው ሊያኖሩን ነው፡፡ ብዙዎቻችን ብፁዓን አባቶች ግን ይሄ አልገባንም፡፡ ስልጣኑን ሁሉ ከእኛ ተረክበው ለሌሎች ሰጥተዋል እኮ፡፡ ሰዎቹ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረቂቅ ሕግ ተብሎ ለእኛ ለሲኖዶሱ የቀረበልን 5 ገጽ ነበር፡፡ ሌላውን ግን አላየነውም፤ ቤተክርስቲያኒቱን ተረክበው ሊቃውንቱ አያስፈልጉም የሚል ነው አላማቸው፡፡ ከዚያ በፊት በአባቶች አንመራም በሚል ወስነዋል፡፡ በየሀገሩ ቅስቀሳ አድርገዋል፤ እኛ ግን አልገባንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቅስቀሳ እያደረጉብኝ ነው፡፡ ለምን ተናገርክብን ብለው በየመንገዱ እየጠበቁኝ ነው ያሉት፤ ለመግደል ማለት ነው!! ብዙ አባቶችም ደግሞ በእነርሱ እጅ ሞተዋል አልቀዋል፤ በመርዝም በተለያየ መንገድ የገደሉአቸው አሉ፡፡ (ብፁዕ አቡነ መርሐን የመርዝ መርፌ ወግተው የገደሏቸው የማቅ አባላት መሆናቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል)፡፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን የእነዚህ ካህናት ጥያቄ በቅርቡ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡ ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ስም የሰበሰበውን ሀብት እያሸሸና ወደአክስዮን እያስገባ ነው፤ ሻይ ቤታቸውን ጭምር አክሲዮን እያስገቡና በሌላ ሰው ስም እያደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተ ወደኋላ እንዳትመለሱ ነው አደራ የምላችሁ፡፡”

የዕለቱም ስብሰባ በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ የሚሆነውን እየተከታተልን ለመዘገብ እንሞክራለን፡፡
16 comments:

 1. This report is from Devil! 100% False!

  ReplyDelete
 2. We can easily identify that the owner of this site is liar devil, since it is going to filter only comments that are positive to devils` idea!

  ReplyDelete
 3. the end of MK is coming soon. Elililililililililililil

  ReplyDelete
 4. Mahibre Kidusan is coming down really hard!!!!

  ReplyDelete
 5. አቤት መመሳሰል:: አንድ:: አንተ የምትለውና እነሱ የሚሉት አንድ ነው:: ለምንድነው? የአንተን ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ስለሆኑ እኮ ነው:: እንደድሮ ጋዜጣ ርስህን አስጩኽህ ውስጡ ባዶ ነው::
  "ሰበር ዜና፦ የማቅ የለውጥ መዋቅር በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች ትግል ተቀለበሰ፤" ተቀለበሰ እና ጥያቄ አቀረቡ መቸም ልዩነት አለው:: ተመኝ ጴንጤው::

  ReplyDelete
 6. ye ewinet amilak yashenifal ayzuachihu beritu!!

  ReplyDelete
 7. ጉድ ነው እያደረ እየዋለ የማይሰማ የለም አይጣል በቤተ ክርስቲያን ሽብር አራማጆች ቅዱሳን
  ተፈጠሩና ቁጭ አሉ ! ጉድ ነው (ከእህል ክፉ ባቄላ ከልብስ ክፉ ነጠላ ከልጅ ክፉ ዲቃላ) እንደተባለው
  የቤተክርስቲያኒቱ ዲቃላዎች ትናት ተዴቅለው ዛሬ አፍ አውጥተው ሰው ሆኑና ሰውን ያብጡ ይበጠብጣሉ ሆነ ይገርማል (እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ አህያ ወደ ሊጥ ውሻ ወደ ግጦሽ)

  ReplyDelete
 8. ጉድ ነው እያደረ እየዋለ የማይሰማ የለም አይጣል በቤተ ክርስቲያን ሽብር አራማጆች ቅዱሳን
  ተፈጠሩና ቁጭ አሉ ! ጉድ ነው (ከእህል ክፉ ባቄላ ከልብስ ክፉ ነጠላ ከልጅ ክፉ ዲቃላ) እንደተባለው
  የቤተክርስቲያኒቱ ዲቃላዎች ትናት ተዴቅለው ዛሬ አፍ አውጥተው ሰው ሆኑና ሰውን ያብጡ ይበጠብጣሉ ሆነ ይገርማል (እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ አህያ ወደ ሊጥ ውሻ ወደ ግጦሽ)

  ReplyDelete
 9. ጉድ ነው እያደረ እየዋለ የማይሰማ የለም አይጣል በቤተ ክርስቲያን ሽብር አራማጆች ቅዱሳን
  ተፈጠሩና ቁጭ አሉ ! ጉድ ነው (ከእህል ክፉ ባቄላ ከልብስ ክፉ ነጠላ ከልጅ ክፉ ዲቃላ) እንደተባለው
  የቤተክርስቲያኒቱ ዲቃላዎች ትናት ተዴቅለው ዛሬ አፍ አውጥተው ሰው ሆኑና ሰውን ያብጡ ይበጠብጣሉ ሆነ ይገርማል (እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ አህያ ወደ ሊጥ ውሻ ወደ ግጦሽ)

  ReplyDelete
 10. የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሆነ ሰው አባ እገሌ ወልዶአል፤ አባ እገሌ ገሎአል፤ አባ እገሌ ሰርቆአል ብሎ ለመናፍቃን፣ ለአለም ጽፎ አይሰጥም so according to this is this blog not accountable? b/c almost every day you post such things. aba swiros unknowingly criticize you

  ReplyDelete
 11. enanete yewshet aramajoch menem atametum atdekmu---

  ReplyDelete
 12. this indicates that there are many non educated church leaders a who are going to be rejected by. because they were political leaders.

  ReplyDelete
 13. Yebiet kersyiyan telatoch mehonachihun. Geberachihu yasayal 0×0=0 malet enant. Nachihu

  ReplyDelete
 14. ደስ የሚለው እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእውነተኞች ጋር ነው፡፡ ምድረ ተሐድሶ እና ሙሰኛ፣ ለነገሩ መዋቅሩ ከተተገበረ የመኪና ወጫችሁን ከየት ትሸፍናላችሁ??? ተነቃባችሁ፡፡

  ReplyDelete
 15. Keep dreaming, MK will continue in strength.

  ReplyDelete
 16. Keep dreaming, MK will continue in strength.

  ReplyDelete