Tuesday, February 25, 2014

ይድረስ ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፡- በኢትዮጵያ ታሪክ ተወቃሾቹ የኦሮሞ ሕዝብና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ነውን እንዴ?!


Read in PDF
በዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን  ~ nikodimos.wise7@gmail.com
‹‹ዕርቅና ሰላም የሕይወት ቅመም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደውለታ ቢስ ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ የሚሆን መልስ እነሆ!›› በሚል ርእስ የጻፉትን ጦማር እጅግ የማክበርዎና ኢትዮጵያዊው የምሆን ወንድምዎ ደጋግሜ አነብበኩት፡፡ ፕሮፌሰር በትክክል ተረድቼዎት ከሆነ እርስዎ በጽሑፍዎ ለማስተላለፍ የፈለጉት ዋንኛ መልእክትዎ፣ አንድም ‹‹ዕርቅንና ሰላም መስበክ›› ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት ወይም ውለታ ቢስ አድርገው ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ መልስ ይሆናል በሚል እነሆ ያሉት ጦማር እንደሆነ ነው፡፡
ፕሮፌሰር ለረጅም ዓመት ካካበቱት ዕውቀትዎ፣ በትምህርት ዓለም በሥራ፣ በምርምርና ጥናትዎ ከሕይወት ተሞክሮዎና ልምድዎ በመነሳትና እንዲሁም ዕድሜዎን ሙሉ ከመረመሯቸውና በአካዳሚያው ዓለም አንቱ ከተሰኙባቸው፣ ከበሬታን ካተረፉባቸውና ጥንታዊ የኾኑ መዛግብቶቻችንን በመመርመር እስካሁን ድረስ እያካፈሉን ስላለው ሰፊ የሆነ እውቀትዎ ከምስጋና ጋር ዝቅ ብዬ እጅ እነሳለሁ፡፡ ከገለታዬ አስከትዬ ግን በተለያዩ ድረ ገጾች ከሰሞኑን ባስነበቡን ጽሑፍዎ ማዘኔን ልገልጽልዎ እወዳለሁ፡፡

Friday, February 21, 2014

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

 ክፍል 17

የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» በተመለከተ ኑፋቄ ተብለው በተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የተላለፈውን ሕገወጥ ውግዘት በተመከለተ በአዋልድ መጻሕፍትና በልማዳዊ ትምህርት ሲመዘኑ ኑፋቄ ተብለው የተወገዙትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች በ16 ክፍሎች ማቅረባችን የሚታወስ ሲሆን ለዛሬው በማህበረ በኩር ላይ የቀረቡትንና ኑፋቄ የተባሉትን ነጥቦች መመልከታችንን እንቀጥላለን፡፡ ለዛሬው በመጀመሪያ የተነሣውን ነጥብ ነው የምናየው፤ እንዲህ ይላል፦

 ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኖቿን ከመናፍስት ጋር ለማቆራኘት በቅዱሳን ስም እየደረሰና እያስደረሰ የጸሎት መጻሕፍት አሰራጭቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ እየጻፈና እያጻፈ ከበተናቸው የድግምት ጸሎቶች አንዱ ዛሬ ከአባታችን /አቡነ ዘበሰማያት ቀጥሎ የሚደገመው በሰላመ ገብርኤል /በገብርኤል ሰላምታ/ የሚለው ነው፡፡ ይህ የድግምት ጸሎት እንደዛሬው ሁሉ ያንጊዜም የአባ እስጢፋኖስ ደቀመዛሙርቱ እንዲከሰሱ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡’ ሲል እመቤታችን መመስገን እንደሌለባት ይጽፏል፡፡ ጮራ መጽሔት - ቁ.19፥ ገጽ 21”

ከሳሹ ማህበረ ቅዱሳን፣ አጣሪው የሊቃውንት ጉባኤና ዳኞቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተመሳሳይ የዕውቀት ደረጃና አመለካከት ላይ እንደሚገኙ ባስመሰከሩበት የግንቦቱ 15ቱ ውግዘት መወገዝ የሚገባው የስሕተት ትምህርትና ኑፋቄ የተከበረበት፣ መከበር የነበረበት የእግዚአብሔር ቃል ግን የተወገዘበት ጉባኤ ነበር ቢባል ስሕተት አይሆንም፡፡ አንዱና መወገዝ የነበረበት የስሕተት ትምህርት ጌታ ባስተማረው አባታችን ሆይ ጸሎት ላይ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የጨመረው እመቤታችን ሆይ የሚለው አድራሻው እግዚአብሔር ያልሆነ ጸሎት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ጸሎት ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሆነና ወደእግዚአብሔር በምንጸለየው አምሳል ወደማርያም እንድንጸልይ የሚያደርግ ስለሆነ ስሕተት ብቻ ሳይሆን አምልኮ ባእድን ማስፈጸሚያም ነው፡፡

Sunday, February 16, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ያዘጋጀው የአብነት መምህራን የምክክር መድረክ ላይ የተጣለው እገዳና አንድምታው

Read In PDF
ከሰሞኑ ማቅ ብዙ ብር ወጪ አድርጎ ያዘጋጀው የአብነት መምህራን የምክክር መድረክ እንዳይካሄድ መታገዱን ተከትሎ የማቅ ብሎጎች ለጉዳዩ ጠቅላይ ቤተክህነቱንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑትን አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ማቅ የፈጸመውን መሰረታዊ ስሕተት በተመለከተ ግን ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡ ማቅ ለጉባኤው በርካታ ገንዘብ ያፈሰሰና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የዓለም ባንክ፣ የወተር ኤይድ እና ዩኒሴፍ ተወካዮች በተገኙበት በግዮን ሆቴል መድረኩን ሊካሔድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም የገንዘቡ ውጪ ብዙ ቢሆንም ያ ብዙም እንዳላሳሰባቸው የማኅበሩ ሰዎች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ብሎጎቹም ሆኑ አመራሮቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ማቅ ስሕተት ፈጽሟል እንዲሉ የማይጠበቅ ቢሆንም በቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ መድረኩ የታገደው “ይህ ነው በማይባል ምክንያት” ነው የሚለው “የአንድ አድርገን” ዘገባ ግን ፍርደ ገምድል ሆኗል፡፡

አንድ አድርገን “ቤተክህነቱ ዘወትር የበጎ ነገር ተቃራኒ ሆኖ እስከመቼ እንደሚዘልቅ አይታወቅም፡፡ አንዳንዴ ቤተክህነቱ የማን ነው? የማንን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ነው ለማስፈጸም የተቀመጠው? እስከ መቼ ነው በጥቂት ሰዎች አማካኝነት የበጎ ነገር እንቅፋት የሚሆነው?” በማለት ቤተክህነቱን ክፉኛ ያብጠለጠለ ሲሆን፣ የማኅበሩ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰሙም ለአብነት መምህራኑ “እስከዛሬ ድረስ የጠቅላይ ቤተክህነቱ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያው እንዲህ እናንተን የተከበራችሁ ሊቃውንት አባቶቻችንን ሰብስቦ አወያይቷችሁ ያውቃል ወይ? እንግዲህ እናንተ ታውቃላችሁ፤ በዚህ ጉዳይ ላይስ ዕቅድ አለወይ? እኛም አናውቅም፡፡ የእኛ ዓላማ ቤተክርስቲያንን መርዳት ነው፡፡ የእኛ ዓላማ የጎደለው ቦታ ላይ ቢያንስ እንዲሁ ጎድሎ እንዳይቀር የሚቻለንን መርዳት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ልትሠራ የሚገባትን ጉዳይ፣ ቤተክህነቱ ሊሠራው የሚገባውን ጉዳይ ሲጎድል እየሄድን ማገዝ ነው የእኛ ሥራ” ሲል ቤተክህነቱን ለማሳጣትና ሊቃውንቱን ከቤተክህነት ጋር ለማጋጨት ሞክሯል፡፡

Tuesday, February 11, 2014

የነነዌ ንስሐ (ዮና.3÷5-9)

Read in PDF                                                         
                                                       ምንጭ፡- የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥እንዲህም አለ፦ ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፡፡ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”(ዮና.3÷5-9)፡፡
      እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን የትድግና ሥራውን ለአህዛብም እንዲናገሩ ነቢያትን አዟል፡፡ እግዚአብሔር በቤቱ ስላሉት ብቻ አይጨነቅም፡፡ በሩቅ ያሉ እስኪሰሙ ድረስም ሳያቋርጥ በፉጨት ድምጽ ይጣራል፡፡ በቀደመው ዘመን ኤልያስና ኤልሳዕ (1ነገ.17÷24፤2ነገ.8÷1-17)በኋላም እነአሞጽ ከይሁዳ ውጪ ለእስራኤልና ለአህዛብ የእግዚአብሔርን የትድግና ሥራ የተናገሩ ነቢያት ናቸው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእስራኤል ውጪ ወዳሉ ከተሞችና ሀገሮች እየሄደ ያስተምር ነበር፡፡ መድኃኒቱ ጌታ “እምነትሽ ታላቅ ነው፤እምነትህ ታላቅ ነው፡፡”(ማቴ.15÷28፤ሉቃ.7÷9) ያላቸው ሁለቱ ሰዎች የተገኙት ኪዳን ከተቀበሉትና መቅደስ ከነበራቸው ህዝቦች መካከል ሳይሆን ከአህዛብ ወገኖች እንደሆነ ቃሉ ይመሰክራል፡፡

Friday, February 7, 2014

በስደት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በስሙ እየተበተነ ያለው ጽሑፍ እርሱን እንደማይወክል አስታወቀ

Read in PDF


በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው በውጭ ያለው ሲኖዶስ በስሙ እየተበተነ ያለው ከፋፋይ ጽሑፍ እርሱን እንደማይወክል በቅዱስነታቸው ፊርማ የወጣው ደብዳቤ ገለጸ፡፡ ደብዳቤው እንደሚለው “በስደት ሀገር እግዚአብሔር ባርኮ የሰጠንን ሐዋርያዊ ተልእኮ በሰላምና በፍቅር እንዳናዳርስ ለማድረግ ራሱን የሰወረ ክፉ መንፈስ እየፈተነን .. ነው፡፡”  ሲል አማሯል፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ ደብዳቤው “ራሱን የሰወረ ክፉ መንፈስ” ሲል የገለጸው ታላቁን አባት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን በማሳሳት ስውር አጀንዳው ለመፈጸም እየተንቀሳቀሰ ያለውን የማቅን ስውር እጅ ነው፡፡


Tuesday, February 4, 2014

የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን

Read in PDF

ከታላቁ የእስራኤል ነቢይና መስፍን ከሙሴ ቀጥሎ ሕዝበ እስራኤልን የመራውና ወደምድረ ርስት ያስገባው ኢያሱ የተናገረው ይህ ቃል በዚያ ዘመን ለነበሩትና በእግዚአብሔር ላይ የአሕዛብ ጣዖታትን ደርበው ከግብጽ ምድር ባወጣቸው አምላክ ላይ ላመነዘሩት ሕዝበ እስራኤል ያስተላለፈው ወሳኝ መልእክት ዛሬ ላለነውም በእግዚአብሔር ላይ ደብለን ሌሎችን አማልክት የምናመልከውን ይመለከታል፡፡
የኦርቶዶክሳውያን ትልቁ ችግራችን የምናመልከው እግዚአብሔርን ብቻ አለመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔርን እናመልካለን ብንልም ከጥንት ያልነበረና ከጊዜ በኋላ ሕዝቡ እያደረገ ያለውን የተሳሳተ ልምምድ ከማስተካከል ይልቅ በዚያው እንዲገፉበት ለማድረግ የሚታወቁና የማይታወቁ ቅዱሳንን ስም እየለዋወጥን በአክብሮት ስም አምልኮት እየፈጸምን እንገኛለን፡፡ በዘመናችን እንኳን ስንቱን ስም እየለዋወጥን የእግዚአብሔርን ክብር በቅዱሳን ስም ለሰይጣን ሰጠን? ለማስተዋስ ያህል፦