Friday, February 21, 2014

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

 ክፍል 17

የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» በተመለከተ ኑፋቄ ተብለው በተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የተላለፈውን ሕገወጥ ውግዘት በተመከለተ በአዋልድ መጻሕፍትና በልማዳዊ ትምህርት ሲመዘኑ ኑፋቄ ተብለው የተወገዙትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች በ16 ክፍሎች ማቅረባችን የሚታወስ ሲሆን ለዛሬው በማህበረ በኩር ላይ የቀረቡትንና ኑፋቄ የተባሉትን ነጥቦች መመልከታችንን እንቀጥላለን፡፡ ለዛሬው በመጀመሪያ የተነሣውን ነጥብ ነው የምናየው፤ እንዲህ ይላል፦

 ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኖቿን ከመናፍስት ጋር ለማቆራኘት በቅዱሳን ስም እየደረሰና እያስደረሰ የጸሎት መጻሕፍት አሰራጭቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ እየጻፈና እያጻፈ ከበተናቸው የድግምት ጸሎቶች አንዱ ዛሬ ከአባታችን /አቡነ ዘበሰማያት ቀጥሎ የሚደገመው በሰላመ ገብርኤል /በገብርኤል ሰላምታ/ የሚለው ነው፡፡ ይህ የድግምት ጸሎት እንደዛሬው ሁሉ ያንጊዜም የአባ እስጢፋኖስ ደቀመዛሙርቱ እንዲከሰሱ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡’ ሲል እመቤታችን መመስገን እንደሌለባት ይጽፏል፡፡ ጮራ መጽሔት - ቁ.19፥ ገጽ 21”

ከሳሹ ማህበረ ቅዱሳን፣ አጣሪው የሊቃውንት ጉባኤና ዳኞቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተመሳሳይ የዕውቀት ደረጃና አመለካከት ላይ እንደሚገኙ ባስመሰከሩበት የግንቦቱ 15ቱ ውግዘት መወገዝ የሚገባው የስሕተት ትምህርትና ኑፋቄ የተከበረበት፣ መከበር የነበረበት የእግዚአብሔር ቃል ግን የተወገዘበት ጉባኤ ነበር ቢባል ስሕተት አይሆንም፡፡ አንዱና መወገዝ የነበረበት የስሕተት ትምህርት ጌታ ባስተማረው አባታችን ሆይ ጸሎት ላይ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የጨመረው እመቤታችን ሆይ የሚለው አድራሻው እግዚአብሔር ያልሆነ ጸሎት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ጸሎት ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሆነና ወደእግዚአብሔር በምንጸለየው አምሳል ወደማርያም እንድንጸልይ የሚያደርግ ስለሆነ ስሕተት ብቻ ሳይሆን አምልኮ ባእድን ማስፈጸሚያም ነው፡፡አንዳንድ የዋሆች ግን ይህ ምንም አይመስላቸው ይሆናል፡፡ ምናልባትም ገብርኤልና ኤልሳቤጥ ማርያምን ያመሰገኑበት ምስጋና ስለሆነ ችግር የለውም ይሉ ይሆናል፡፡ ችግር ግን አለው፡፡ ትልቁ ችግር ጸሎት መቅረብ ያለበት ወደእግዚአብሔር ብቻ ነው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አዋጅና ከእግዚአብሔር ውጪ ወደማንም እንዳንጸልይ የተቀመጠውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክልከላ ጥሰን ወደማርያም እንድንጸልይ መደረጉ ነው፡፡ ነገሩ በማርያም ስም ስለቀረበ ትክክለኛ ነው የሚል ካለ ግን ፈጽሞ ተሳስቷል፡፡ ጸሎቱ ለስሙ ወደ ማርያም ቀረበ ይባል እንጂ የጸሎቱ ተቀባይ ሰይጣን መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

አንዳንዶች በዚህ ድንግል ማርያም የምትደሰት ይመስላቸዋል፡፡ እርሷ ግን ይህን ብታውቅ በዚህ ታዝናለች እንጂ ፈጽሞ አትደሰትም፡፡ እርሷ የጌታ ኢየሱስ እናት እንጂ አምላክ ስላልሆነች ወደእርሷ የሚጸለየውን ጸሎት አታውቀውም፤ ብታውቀውም አጥብቃ ትቃወመዋለች እንጂ ፈጽሞ አትደግፈውም፡፡ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ጠንቅቃ የምታውቅና እርሷም እርሱን ብቻ የምታመልክ መሆኗን “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች” በሚለው ጸሎቷ ግልጽ አድርጋለች፡፡ እርሷ ካንቀላፋች በኋላ በስሟ ወደእርሷ ብንጸልይ የዚህ ጸሎት ተቀባይ ስሟን ተውሶ አምልኮትና ስግደትን ለራሱ የሚወስደው ሰይጣን እንጂ እርሷ ልትሆን በፍጹም አትችልም፡፡

የዚህ ጸሎት መሠረት ነው የሚባለውና አንዳንዶች መከራከሪያ አድርገው የሚያቀርቡት ገብርኤልና ኤልሳቤጥ የተናገሩትን ነው፡፡ ገብርኤል ድንግል ማርያምን ሲያበስራት ኤልሳቤጥንም ልትጎበኛት በመጣች ጊዜ ኤልሳቤጥ ስለእርሷ የተናገረችው ከዚያው ሁኔታ ጋር የተያያዘና ለዚያው ጊዜ የሚያገለግል እንጂ ወደጸሎትነት ተቀይሮ እንድንደግመው የተሰጠ ፈቃድ አይደለም፡፡

ገብርኤልና ኤልሳቤጥ የተናገሩትን በማቀነባበር ጸሎት አድርጎ እንድንደግመውና እንድንስት ያደረገን አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ነው፡፡ እመቤታችን ሆይ የእርሱ ድርሰት መሆኑን ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ እርሱ ለእነዚህ ለሁለት ፍጡራን ማለትም ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ክብር ይገባቸዋል በማለት ማርያምና መስቀልን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካከለ ደፋርና ባእድ እምልኮን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያስፋፋ ስሑት ነው፡፡ ለዚህ የተሳሳተ አስተምህሮ ስኬታማነት እመቤታችን ሆይን ደርሶ ወደእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ወደማርያምም እንድንጸለይ አድርጓል፡፡ ከዚያማ ወደ ጻድቃንና ወደ ሰማዕታት፣ ወደ መላእክትም እንድንጸልይ ገድላ ገድሉንና መልክአ መልኩን ደረሰ አስደረሰ፡፡ በመጨረሻም ለእኔም ስገዱ አሉ፡፡

እንጸልይ ዘንድ አስተምረን ላሉት ደቀመዛሙርቱ ጌታችን ኢየሱስ ያስተማረው ግን አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በቀር የምንጸልይበት ሌላ አምላክ ስለሌለ መጸለይ ያለብንም ወደእርሱ ብቻ ስለሆነ ከዚህ ውጪ ወደእናቴም ጸለዩ አላለም፡፡ ቤተክርስቲያንም ስትጸልይ የኖረችው አባታችን ሆይ በማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ ጸለዩ ሲል ሕዝቡ በዜማ አቡነ ዘበሰማያትን ብቻ እንጂ በሰላመ ቅዱስን አይልም፤ ለምን? በሰላመ ቅዱስ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ድርሰት እንጂ ጌታችን ያስተማረን ጸሎት አይደለምና፡፡ የአባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳ ጉንዲ ተከታይ የነበረው አባ ዕዝራ ከደብተሮች ጋር እንዲከራከር በተደረገ ጊዜ ደብተራዎቹ እስኪ በሰላመ ገብርኤልን (አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የደረሰውን) ድገም አሉት፡፡ ጥበበኛው ዕዝራ ግን እነሱ ያላሰቡትን፥ ወበሳድስ ወርኅን “በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ከሚለው ጀምሮ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈውን አነበበላቸው (ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ 1996 ገጽ 300)፡፡ ይህም የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ድርሰት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሃይማኖት ትምህርት መሠረት ተቀባይነት የሌለው ወደቤተክርስቲያን ግን በኃይል የገባና የግድ ተቀባይነት እንዲኖረው የተደረገ ድርሰት ነው፡፡ በተለያዩ ቅዱሳን ስም የተደረሱት ውዳሴዎችና መልኮች ሁሉ የቅዱሳኑን ስም ተውሶ ለሚሰራው ክፉ መንፈስ የሚቀርቡ ናቸው፡፡

ማንም ሰው ለምሳሌ መልክአ ሚካኤልን እየደገመ ወደ እግዚአብሄር ነው የምጸልየው ካለ ራሱን እያታለለ ነው፡፡ በመልክአ ሚካኤል እየተናገረና እያናገረ ያለው የሚካኤልን ስም ተውሶ የሚያስተውን መንፈስ ነው እንጂ እግዚአብሔርን ወይም ቅዱስ ሚካኤልን አይደለም፡፡ እንዲህ ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ፈጽሞ የተከለከለ አምልኮ ባእድ ነው፡፡ ሚካኤል በስሙ እንዲያ ያለ አምልኮት ምስጋናና ስግደት የሚቀርብለት መሆኑን ቢያውቅ ግን በራእየ ዮሐንስ መልአኩ፣ ዮሐንስ ሲሰግድለት እንደከለከለው እርሱም በከለከለ ነበር፡፡   

ታዲያ ወደእመቤታችን መጸለይን ዘርዓ ያዕቆብ ከየት አመጣው? ያው ከሐሰት አባት ከዲያብሎስ እንጂ ሌላ ከየት ያመጣዋል? ስለዚህ ከእግዚአብሔር ውጪ ወደሌላ ጸልዩ የሚል ቢኖር እርሱ የተወገዘ ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ወደቅዱሳን ጸልዩ ማለት ብቻ ሳይሆን ለእኔም ስገዱ ባይ ነበር፡፡ እነ አባ እስጢፋኖስ ይህን በመቃወም ለሥላሴ (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) ካልሆነ በቀር ለሌላ አንሰግድም፤ በሥላሴ ላይ አራተኛ አንጨምርም ብለው የተቃወሙትና በዚህ ምክንያት በልዩ ልዩ መከራና ሥቃይ ሰማዕትነትን የተቀበሉት፡፡ ነገር ግን ከሳሹ አጣሪውና ዳኛው አንድ የሆኑበት የግንቦት 15ቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ይህን ቅዱሳን ብዙ ዋጋ የከፈለሉለትን እውነት አውግዞ መወገዝ የነበረበትን የስሕተት ትምህርት ሕጋዊ አደረገው፡፡


ሲኖዶሱ ከላይ ባቀረበው ነጥብ ላይ ክስ አድርጎ ያቀረበው ማኅበረ በኩር “እመቤታችን መመስገን እንደሌለባት ጽፏል፡፡” የሚል ነው፡፡ በቅድሚያ ማኅበሩ የጻፈውና የተቃወመው የድግምት ጸሎትን ሆኖ ሳለ ነገሩን ከማርያም ጋር ማያያዝ በዘዴ ለማምለጥ የተዘየደ መላ ነው የሚመስለው፡፡ ስትጸልዩ “አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።” የሚል ትእዛዝም በቅዱስ ወንጌል ተጽፏል (ማቴ 6፡7)፡፡ ይሁን እንጂ በነጥቡ ውስጥ ስለድግምት የተነሣው ጉዳይ በዝምታ ነው የታለፈው፡፡ ደግሞስ ድንግል ማርያም ጌታን በድንግልና ፀንሳ ስለወለደች ይህን ስራ በአድናቆት መመልከት እንጂ ምስጋና የሚቀርበውማ ምስጋና ለሚገባውና በእርሷ ይህን ድንቅ ሥራ ላደረገ ብቻውን ጌታና አምላክ ለሆነው ለፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ “እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” ስትልም በዚህ ነገር ትውልድ ሁሉ እንደሚደነቅ መናገሯ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ እግዚአብሔር በእርሷ ታላቅ ሥራን ማድረጉ ነው፡፡ ስለዚህ “ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ” (መዝ. 18፡3፤ 22፡4) ነው የሚባለው እንጂ፣ የፈጣሪ የብቻው ገንዘብ የሆነውን አምልኮትና ምስጋናን ለፍጡራን አናጋራም፡፡ እንዲህ ካደረግን ያው በቅዱሳን ስም የተፈጠረ ጣኦት አምላኪዎች ነን፡፡ ታዲያ መወገዝ ያለበት ማነው?

31 comments:

 1. zendow ende dingil maryam yemitelaw yelem besua lij dil temetualna be emebetachin misigana tselot wisit ye ashenafi ye egiziabeher enat yemil talak misikirinet ale yihin seyitan enidibal ayifeligm lezi new be tehadiso aramaji menifes amakgnenet tikikil ayidelem eyale yemikawemew

  ReplyDelete
 2. እንግባባ…ቃሉ ግልጽ ነው!!
  1. ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል!!!…..እንዴትም ቢተረጎም “በመገረም” የሚቆም አይደለም!!ያለፈውም፣ያለውም፣የሚመጣውም ትውልድ ያመሰግኑኛል ማለት ነው!!....ትውልድ ሁሉ….የሚለው ቃል ይሄን ይገልጻል!!
  2. ድርሰቱም ….ሰዐሊ ወጸልይ ለነ ምህረተ ሀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይስረይ ለነ ኃጣውኢነ- ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን…ከሚለው ቃል ውጭ ሙሉ ጸሎቱ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 1ቁ 26 እስከ 56 ውስጥ የሚገኝ ቅ/ገብርኤልና ኤልሳቤጥ ለእመቤታችን ካቀረቡት ምስጋና የተወሰደ እንጅ እናንተ እንደምትሉት የንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ድርሰት አይደለም!!
  3. የእሱ(የዘርዐያዕቆብ) ድርሰት ቢሆንማ ሁሌም እንደምንለው እመቤታችን የምትመሰገነው በኢትዮጵያ ብቻ ሆኖ ይቀር ነበር!!ግን አደለም!!የምስራቅ ኦርቶዶክሱም፣ካቶሊኩም፣ኦሪየንታሉም ከሉተር ልጆች በቀር አማናዊውን መድህን ያስገኘችውንና በመ/ቅዱስ ውስጥ በመልአክ ቃል ብጽእት ተብላ ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተጠራቸውን ወላዲተአምላክ ሰአሊ ለነ ቅድስት ሳይሉዋት አይውሉም!!የእሱዋ ምስጋና በሀገር ብቻ ሳይሆን በአህጉራትም የታወቀ ነው!ወንዝ ይሻገራል!!
  4. ስለ መላእክት በመዝ 102 ቁ 20…ባርክዎ ለእ/ር ኩልክሙ መላእክቲሁ-መላእክት ሁሉ እ/ርን ባርኩ…ተብሎ ተጽፎልሀል!!እና ቅ/ዳዊትን ያህል ነቢይና መዘምር መላእክትን እንዲህ በጸሎቱ ሲያናግራቸው ለጣኦት ምስጋ እያቀረበ ነበር ልትለን ነው???ባርክዎ ያለው ዳዊት ሰአሉ ለነ-ለምኑልን እንዳይል የትኛው ጥቅስ ነው የሚከለክለው??እስኪ ጨምረህ በመዝሙር 148 የተጻፈውን አንብበው!!መዝሙር 32 ቁ 1…..ተፈስሁ ጻድቃን በእ/ር-ጻድቃን በእ/ር ደስ ይበላችሁ…..ይላል ቅ/ዳዊት ያሉትን በሞተ ስጋ ከተለዩት ሳይለይ ነው…ደስ ይበላችሁ…የሚለው!!እኛም እሱን አብነት አድረገን ቅድስት ድንግል ማርያምን ደስ ይበልሽ ስንላት ልባችን ሀሴት ያደርጋል!!
  5. ደጋግሜ እንደምለው የሞቱ ቅዱሳንና መላእክት አያማልዱም የሚል የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም!!ወፍራሞቹ ፓስተሮች ያማልዳሉ እየተባለ በክርስቶስ ህያው የሆኑት እነ ቅ/ጳውሎስ አያማልዱም ማለት የክርስቲያንን ሞት ከአረማዊ ሞት ለይቶ ካለማወቅ የተነሳ የሚመጣ አመለካከት ይመስለኛል!!
  ለማንኛውም ስለ እመቤታችን ምስጋና ስላነሳችሁ መዝሙረኛውን ደጋግሜ ብጠቅስም የልቤ ስላልደረሰ መመለሴ እንደማይቀር ገልጨ ሀሳቤን ልግታ!!
  ሰዐሊ ለነ ቅድስት!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውድ ሕሩይ

   በ ልጇ በ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ (ይህን በማመንና በመቀበል) የሀጥያት ይቅርታ ና ምህረት እንዳገኘን መፅሐፍ ቅዱስ ያስረግጣል:: ታዲያ አንዴ ያገኘነውን የሀጥያት ስርየት ድንግል ማርያምን አስሰጭን ብለን እንዴት እንጠይቃለን?

   ዳዊት በመዝሙሩ (ም 102 ና 148) ላይ ''እግዚአብሔርን ባርኩ'' ብሎ የጠቀሰው መላእክቱን ብቻ ሳይሆን ፍጥረቱን ሁሉ ፀሐይ: ጨረቃ ና ከዋክብቱንም ጭምር ነው;; ዳዊት ባርክዎ ብሏቸዋልና ግኡዛን ፍጥረታቱንም ሰአሉ ለነ-ለምኑልነ ልንል ነው ማለት ነው?

   ስለሌሎች ወደ እግዚአብሔር መፀለይና ለቅዱሳንና መላእክት ፀሎትን ማቅረብ የተለያዩ ነገሮች ናቸው:: የሞቱ ቅዱሳንና መላእክት ያማልዳሉ ወይም ፀሎትን ይቀበላሉ የሚል የምትጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም:: ይልቁንም: መፅሐፍ በ ዮሃ 1:12 ለተቀበሉት በስሙም ላመኑት የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ስልጣን ስጣቸው እንደሚል: ፀሎታችንን በቀጥታ ለእግዚአብሔር የማቅረብ የልጅነት መብት አለን

   Delete
  2. yabatu lij lela min yawuqal bileh newu

   Delete
  3. ቶ ሕሩይ ለመሆኑ ጌታችንን ምን ጠይቀዉ ተከልክለዉ ነዉ አማላጅ የሚልኩበት? ደግሞስ በሃጢአት ብዛት ምክንያት ከሆነ እመቤታች ከጌታ ይልቅ አዛኝ ሆና ነዉ ማለት ነዉ? እርስዋ ወለደችዉ እንጂ ተሰቀለችልን? የሐዋሪያትን ፈለግ በመከተል መዳን በሱ እንጂ በሌላ እንደሌለ ማመን መላልሶ እንደለመነን በር በማንኩዋኩዋት አምነን በመለመን ከምንጠይቀዉ አንዳች እንደማናጣ ላረጋገጠልን ጌታ መንገር እንጂ እንደ ሩቅና ጨካኝ አምላክ ሽማግሎዎችን ወደሱ መላክ የልጅነት መብታችንን ስለሚጥሰ እርስዎ በወንጀለኛ ሕግ ይቀጣሉ. ከእመቤታችን ጋር እጃን ለማጣላተ መሞከርም ከንቱ ልፋት ነ ዉ ከናነተ ይለቅ ለኛ በእምነት ትቀርባለችና

   Delete
  4. ወንድሜ ያሬድ
   1. መጀመሪያ ሰላማ ያቀረበልንን ጽሁፍ እየው!!ብሎጉ መላእክትን ማነናገርን ከሰይጣን እንደመነጋገር አድርጎ ነው ያቀረበልን!!ይህ እውነት እንዳልሆነ ለማሳየት የዳዊትን መላእክት እግዚአብሄርን ባርኩ የሚል በቀጥታ ለመላእክት በአድራሻቸው የቀረበ ጸሎትና ዝማሬ ጠቀስኩ!!
   2. ፀሓይና ጨረቃም በዳዊት ተጠቅሰዋልና ለእነዚህ ግኡዛን ፍጥረታትም አማልዱን ብለን ልንጸልይ ነወይ አልከኝ!!እሱን አንተ አልክ እልሃለሁ!!የዳዊት የመላእክትን ስም አንስቶ የመጸለይ ድርጊት ቢያንስ አምልኮ ጣኦት ሊባል እንደማይችል ግን እኔም አንተም እናውቃለን!!በሌላ በኩል ስለመላእክት አማላጅነት እና ስለእኛ በእ/ር ፊት ስለመቆማቸው ግን ብዙ ጥቅሶችን ልሰጥህ እችላለሁ!!
   3. በክርስቶስ አንድ ጊዜ በቀራንዮ የተፈጸመውን ማደንና የቅዱሳንን አማላጅነት ልዩነት ለማስረዳት ከዚህ በፊት ብዙ ጽፈናል!!አሁን እሱን መድገም አንባቢን ማሰልቸት ስለሆነ ቀደም ሲል የሰላማ ብሎግ የምታመልኩትን ምረጡ በሚል ርእስ ስር ባወጣው ጽሁፍ የተሰጡ አስተያየቶችን እያቸው!!
   4. ለማሳያ ያህል ግን በ2ኛ ቆሮ 5 ቁ 18 ያለውንና የሁለቱን ልዩነት የሚያሳየውን ቃል በቃል ላስቀምጠው…ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከእርሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዙአብሄር ጋር ነው.እግዚአብሄር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከእርሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸው አይቆጠርባቸውም ነበር.በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ .እንግዲህ እግዚአብሄር በእኛ እንደሚማለድ ስለክርስቶስ መልእክተኞች ነን.ከእግዚአብሄርም ጋር ታረቁ ብለን ስለክርስቶስ እንለምናለን…..
   5. እንግዲህ ከዚህ ቃል በላይ የክርስቶስን በራሱ ቤዛነት በአዳም ፈርሶ የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ ከራሱ ጋር ማስታረቅና የነጳውሎስን እኛን በተሰጣቸው ጸጋ በአማላጅነት ወደ ክርስቶስ የማቅረብ ጸጋ ልዩነት ፍንትው አድርጎ ሚያሳይ ጥቅስ የለም!!የማስታረቅ ቃል ያኖረባችሁ ሆይ አሁንም አስታርቁን!!እለት በእለት እንበድላለንና!!በአዳም ምክንያት ከመጣብን የውርስ በደልማ አንዴ በደሙ አንጽቶናል!!ቅዱሳንና እመቤታችንን እንዶክተር፣ ጌታን በመርፌው ውስጥ እንዳለ ፈዋሽ መድሃኒት፣እኛን እንደ ህሙማን መስለው ያስተማሩት የአባ ወልደትንሳኤ አያልነህ ስብከት እዚህ ላይ ይጠቀሳል!!
   6. ቀጥታ ለኢሱስ ኃጢአቴን፣ ጸሎቴን አቀርባለሁ ካልክ!!መብትህ ነው!!እኛም እንዳንተ ዘወትር ማረን ይቅር በለን እያልን ስለምንጸልይ በግማሽ ልትዛመደን ትችል ይሆናል!!ነገር ግን አንዱ ስላንዱ እንዲጸልይ መጽሀፉ ያዛል!!ራሱ ባለቤቱም አብርሃም ይጸልይላችሁ፣ኢዮብ ይጸልይላችሁ ማለቱን አንብበናል!!ስለዚህ ካህናቱን፣እናቶቻችንን ጸልዩልን እንላለን!!በህይወተ ስጋ የተለዩ ቅዱሳን ስጋቸው እንጅ ነፍሳቸው አልሞተም!!ወትሮም ማማለዳቸው የነፍስ ድርጊት እንጅ የስጋ አይደለም!!መናገር፣ልብ ማለት፣ህያውነት የነፍስ መገለጫ ነው!!በልብና በንግግር የሚደረገው ጸሎትም የነፍስ ስራ ነው!!ነፍስ ደግሞ አትሞትም!!በተለይ አምኖ፣ተጠምቆ፣በምግባር ጸንቶ የሞተ ክርስቲያን ፍጹም ወደሚሆንበት ዓለም ሄደ እንጅ ወደ ግኡዝነት ተቀየረ ብለን አናምንም!!
   7. ታዲያ ይሄን ፍጹም ባልነበረበት ወቅት ጸልይልን ያልነውን ቅዱስ ይበልጥ ወደ ጌታ ሲቀርብማ እንዴት ይበልጥ ጸሎታችንን አናሰማ!!እናውቃለን!! ጻድቃን ዘወትር ለእኛ የማማለድ ስራ የለባቸውም!!ነገር ግን እሱ አንዴ ጻድቁን በጻድቄ ስም ለሚቀበል ወጋው እንደማይቀርበት ተናግሩዋልና ጸሎታችንም ሆነ በስማቸው ምናደርገው ሁሉ ወደ ሰይጣን ገጽ ሳይሆን ወደባለቤቱ እንደሚያደርሰን እናምናለን!!
   ሰአሉ ለነ ጻድቃን!!

   Delete
 3. min yishalachihual! tinish linisemaw yemnichilewun neger bititsifu endet tiru neber. ke zinb mar ayitebekim. ke menafiqi deros min yitebekal??? eski eyandadun kal eyetekesk kemetsihaf wuchi new bel? beselam kidus gebrel melak......zim bleh politikegna tsihuf new eko yetsafkew. hayimanotegna adergew enji. metsihaf kawek? lenegeru yemititagelutin yematawuku yesat eratoch nachu! enate talfalachihu betekirstiyan gin tinoralech. ahunim bemin huneta wust endalachihu hilinachihu yawukewal.

  ReplyDelete
 4. "ንኅድጎ ለምግባረ ኀፍረት ዘኅቡእ ወኢንሑር በትምይንት ወኢንትመየኖ ለቃለ እግዚአብሔር፣ ወናቅም ርእሰነ በጽድቅ ገሃደ እንበይነ ግዕዘ ኵሉ ሰብእ በቅድመ እግዚአብሔር።

  በስውር የሚሠራውን አሳፋሪ ሥራ እንተወው፣በተንኰልም አንመላለስ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅል፣(አንተናኮል) ለሰውም ሁሉ አርአያ ስለ መሆን አውነትን ገልጠን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን እናጽና።" 2ቆሮ 4 ቊ 2

  በዚህ በአባ ሰላማ ብሎግ ላይ ስለ ግንቦት ፲፭ ውግዘት ክፍል ፲፯ ገምጋሚ የገመገመው ግምገማ ቀረቦ እየተነበበ ይገኛል። ገምጋሚ የተናገራቸው ቃላት አብዛኞቹ ራሱንና የእግዚአብሔርን ቃል የሚቀረኑ ናቸው። ጸሎትን አስመልክቶ ገምጋሚ "ጸሎት ለስሙ ወደ ማርያም ቀረበ እንጂ የጸሎቱ ተቀባይ ሰይጣን መሆኑ አያጠራጥርም" ብሏል ገምጋሚ፣ ለመሆኑ ሰይጣን ይህ ጸሎት መቀበል ይችላል ወይ? ሰይጣን ይህን ጸሎት የሚቀበልና ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን የሚያሰጥ ከሆነ ምኑን ሰይጣን ሆነ፣ይህ አባባል ለሰይጣን ያልተሰጠውን ሥልጣን እንደመስጠትና የማይሠራውን በጎ ሥራ እንደሚሠራ አድርጎ የሚያሳይ አባባል ነው። ሰይጣን ተቃራኒ ባላጋራ ከሳሽ ጠላት እንጂ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለሰው ይቅርታ የሚጠይቅ ወዳጅ አይደለም።

  እንዴት ክርስቲያን ነን እያላችሁ ሰዎች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅታን ለምኚልን በማለት የለመኑትን ልመና የሚቀበል ሰይጣን ነው ትላላችሁ? ሰይጣን ለሰው ልጅ ከፈጣሪ ይቅርታን የመጠየቅ ሥልጣን የለውም እንጂ እንደ እናንተ አባባል ጸሎቱን ተቀብሎ ለሰው ልጅ ይቅርታን ካስገኘ ክፋት የለው። በመሠረቱ ጸሎት ልመና ነው ልመና ደግሞ እንደ አቀራረቡ ነው ልመና ሁሉ አምልኮ ሊሆን አይችልም።ከልጅሽ ከጌታች ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኚልን በማለት የቀረበው ልመና እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አይደለም ሰይጣንንም ቢሆን በአምልኮ ደረጃ አያስቀምጠውም ልመናው ወይም ጥያቄው ጉዳዬ ለበላይ አካል ይቅረብልኝ ማለትን የሚያመለክት ልመና እንጂ የአምልኮ ጉዳይ አይደለም። ይቅርታ አድራጊ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን የጸሎቱ ዐረፍተ ነገር በሚገባ ገልጾታልና ከትዕቢትና ከጥላቻ መንፈስ በራቀ አእምሮ እናስተውል። ስለ ሌሎቹ የገምጋሚ ቃላት በሌላ ጊዜ እንመለስበታልን እስከዚያው ድረስ ቸር ያሰንብተን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እናንት ማቆች እንዴት ነው የምታስቡት? እውነትን ላለመቀበል ስትፈልጉ የጽሑፉን ይዘት ትታችሁ ወደቃላት ስንጠቃ ትዞራላችሁ፡፡ ለምሳሌ "ጸሎት ለስሙ ወደ ማርያም ቀረበ እንጂ የጸሎቱ ተቀባይ ሰይጣን መሆኑ አያጠራጥርም" ብሏል ገምጋሚ፣ ለመሆኑ ሰይጣን ይህ ጸሎት መቀበል ይችላል ወይ? ሰይጣን ይህን ጸሎት የሚቀበልና ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን የሚያሰጥ ከሆነ ምኑን ሰይጣን ሆነ፣ይህ አባባል ለሰይጣን ያልተሰጠውን ሥልጣን እንደመስጠትና የማይሠራውን በጎ ሥራ እንደሚሠራ አድርጎ የሚያሳይ አባባል ነው። " ብላሃል፡፡ የቀረበው ጽሁፍ መንፈስ ግን ይህን የሚል አልመሰለኝም፡፡ ወደዚህ አቅጣጫ የጎተትከው አንተ ነህ፡፡ ጽሁፉ የሚለው ወደማርያም የሚቀርበውን ጸሎት የሚቀበለው እግዚአብሔር አይደለም ሲል ሐሳቡ ቀድሞውኑ ወደማርያም እንዲጸለይ ያደረገው ሰይጣን ስለሆነ የጸሎቱ ተቀባይም እርሱ ነው ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰይጣን ከመጀመሪያው የእግዚአብሔርን ክብር ለራሱ ሊያደርግ ፈልጎ ከክብሩ የተዋረደና በልዩ ልዩ መንገድ ሰዎችን እያሳተ አምልኮትን ስግደትን ምስጋናን በቅዱሳን ስም ወዘተ ለራሱ የሚወስድ ነው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሰይጣንን ጸሎት ተቀባይ በማድረግ የሌለው ክብር እንደተጨመረለት ተድረጎ መቆጠር የለበትም፡፡ ጽሁፉም እንዲህ አላለም፡፡ ሰይጣን ሰዎችን እያሳተ ለእግዚአብሔር ብቻ ሊቀርብ የሚገባውን ክብርን ለራሱ በመውሰድ የእግዚአብሔርን ስራ ያበላሻል ለማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሰይጣን በጎ ይሰራል የሚል ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው የለም፡፡ አንተ እንዲህ አድርገህ ያልተጻፈውን ማንበብህ ግን ጤነኛነትህን ሳያጠራጥረው አይቀርም፡፡ ለሁሉም ጸሎት ሊቀርብ የሚገባው በኢየሱስ ስም ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ አበቃ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
 5. አውጋዥና አስወጋዥ አንድ አይነት ጥቅም ቢኖራቸው ነውጂ ስንኳን በዚህ ዘመን ድሮም አይገባም ነበር
  እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ያመነ ከምኩራብ ይለያል ብለው አይሁድ እንዳወጁ የዘመናችን ተረፈ አይሁድም ሲያወግዙና ሲስወግዙ ይኖራሉ።

  ReplyDelete
 6. ENEZIH MEANFKAN AYENE ESKMAWTAT DERSEW BELUKAS WENGEL 1 MELAKU GEBRELNA ELSABET LEMEBETACHN YETENEGEREWN YEGXEABHER KAL GEZE YALFEBET NEW .SELOTUM BYOHNES RAEY 12 LAY EMBETACHNN LEWTTAT AFUN WEDKEFETW SYTAN NEW YEMIDRSWE BMALET BWNGEL ATMENU EYALUN EKO NEW.LEKA ABSELAMA YELEYELT MENAKIK NEW.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ገብርኤልን ብስራት የካደ የለም ጉዳዩ ከእመቤታችን ሳይሆን እናንተ መመለስ ያልቻላችሁትና መቶ ጊዜ ጠይቄ መልስ ያላገኘሁት ጌታ ምን ከልክሎ ያዉቅና ነዉ ወደ ምልጃ የተኬደዉ ነዉ ርህሩህ ጌታ እንክዋን ለምነነዉ ሳንጠይቅ የሚሰጥ ጌታ በደም የተገዛን ስለሆንን ከእንግዲህ ልጆች አንጂ ባሮች አይደላችሁም ያለንን እንደገና እንደ ባዕድ በክብር ቢበልጡንም እንደኛዉ ሰዉ በሆኑና በአንቀላፋ ወገኖቻችን ማስጠየቅ ዉሃ የሚቁዋጥር አይደለም ራሳችሁን ጠይቁ እንጂ ፍቅሩን ካለመረዳት ወይም ካለማወቅ የተነሳ ጌታችንን ገፋገፋ ማድረግ ከማንም የበለጠ የምትጎዱት እናንተ ናችሁ እመቤታችን ልመናችንን ሰምታ ይህንና ያንን አደረገችልን ለምትሉት ደግሞ እርሱዋ ለመሆንዋ እርግጠኛ አትሁኑ መንፈስን ሁሉ ማመን ሌላዉ ስህተት ነዉና በዚህ የአብይ ፆም ጌታችን የቀራንዮን ምስጢር እንዲያበራላችሁ አብረን እንፀልይ በእዉነት የቤተክርስቲያናችን ነገር ያስለቅሳል እንዲጎበኛትና እንደሚጠብቀው ንፅህት ሙሻራ እንድትሆንለት እንጂ ደባሎችን አስገብታ እንዳታስቀናዉ ለንሰሐዋ እንድትበረታ ክርስቶስ እንዲረዳት የዚህ የአብይ ፆም ዋና ጉዳይ መሆን አለበት የአምላካችን ጸጋ አይለየን

   Delete
  2. ትልቁ ነገር ክርስቶስ ለእናንተ ማን ነዉ አምላክ ወይስ አማላጅ?

   Delete
 7. Well engidhe, yilal Yagerese sew. min endemil alawkim sehafiw gin andande amelekaketein azabetobegal

  ReplyDelete
 8. I am against Mahibere Kidusan. But this time you are going to extreme. It sounds Tehadiso.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is who the menafekans are.How on earth they forget tewlid hulu betsehit yelugnal?????isn't it Emebetachen dengil mariamen mamesgen ?So why it bother u emebtachn mesgana after abatachn hoye unless u r the zendo who try to attac setitun.I will pray for u guys Ye emebetachen kiberna fiker yeamlakachen enatenet belbachehu endigeba.I really feel sorry for u.Ayene lebonachehun yekfetlachehu amen

   Delete
  2. yes, indeed we are!! What is wrong with Tehadiso?

   Delete
 9. እመቤታችን የጌታን ሰው መሆን ከዓለም ሁሉ ቀድማ በብስርዓተ መልአክ ስላወቀች፣በሉቃ 2 ቁ 22 በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ተብሎ በአረጋዊው ስምኦን እንደተነገረ ጌታን ይዛ በግብጽ በረሃ በመንከራተቱዋ፣ሲያስተምር ትጎበኘው ስለነበር(ማቴ 12 ቁ 46)፣የመጀመሪያውን ተአምር በቃና ዘገሊላ በእሱዋ አማላጅነት በመጀመሩ(ዮሀ 2 ቁ 1)፣እስከቀራንዮ ድረስ ሳትለየው በጽናት በመቆሙዋ(ዮሐ 19 ቁ 25)፣ከእርገቱም በሁዋላ የሐዋ ስራ 1 ቁ 12 እንደሚነግረን ከሐዋርያት ባለመለየት ስሙዋ ከሌሎች ቅዱሳት አንስት በተለየ ከበሬታ በመጠራቱ፣በሉቃ 1 ቁ 26 ጀምሮ ስላሉት ብጽዕናዋ፣እምነትዋ፣መታዘዝዋ፣ትህትናዋ፣በሰማያዊ መልአክና በምድራዊት ቅድስት በአንድነት መመስገኑዋ፣ምስጋናዋ፣እውቀትዋ ተደማምረው ቤ/ክ ከፍጡራን በላይ ከስላሴ በታች አድርጋ እንድታከብራት እንድታወድሳት አድርገዋታል!!የእመቤታችን ውዳሴ ምንጮችም…
  1. ትንቢት፡ ቤ/ክ ዳዊት በመዝ 44 ቁ 16….ለልጅ ልጅ ስምሽን ያሳስባሉ…ሲል የተናገረው ትንቢት እመቤታችን በሉቃ 1 ቁ 48….እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል…ስትል በተናገረችው ቃል ፍጻሜ አግኝቱዋል ብላ ታስተምራለች!!ይሄው እኛም ለፈጽሞ ትንቢት ሰአሊ ለነ ቅድስት እያልን ስሙዋን እንጠራለን-ለትውልድ እናሳስባለን!! የለም፣ የዳዊት ትንቢት ለኢየሩሳሌም የተነገረ ነው የሚል ካለም ጌታ ተመላለሰባት ተብሎ ከምትወደሰው ግኡዝ ምድር ጌታን ወልዳ፣ተሰዳ፣አጥብታ፣ከቀራንዮ እስከ ጰራቅሊጦስ ያልተለየቸው ወላዲተ አምላክ ምስጋናም ሲያንሳት ነዋ እንላለን!!
  2. ቀደምት አበው፡እነ ቅ/ኤፍሬም፣እነ አባ ህርያቆስ፣እነ ቅ/ያሬድ፣እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣እነ ዮሐንስ አፈወርቅ እረ ስንቱ…..አወድሰዋት፣ቅድስናዋን አማላጅነቱዋን ተናግረው አይጠግቡም!!እነዚህ ቅዱሳን ስለ ብሉይና ሐዲስ ያላቸው እውቀት ደግሞ አይጠረጠርም!!በምስጋናዋ የሚደረድሩት የነቢያት ትንቢትና አምሳል፣የሐዋርያት ስብከት ምጥቀታቸውን ያሳያል!!ትምህርቱን ፈጥረው፣አመንጭተው ሳይሆን ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ እናዳገኙም እናውቃለን!!እኛም የእነሱ ልጆች ስለሆንን አርዓያነታቸውን ተከትለን ...ተፈስሂ ኦ ማርያም እም ወአመት-እናትነትን ከአገልጋይነት ያስተባበርሽው ብቸኛዋ እመቤት ሆይ ደስ ይበልሽ… እያልን በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንላታለን!!እናወድሳታለን!!ሆኖም አናመልካትም!!
  3. ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ እውቅና ከምትሰጣቸው ጉባኤያት መካከል በ431 ዓ.ም 200 ሊቃውንት ተሰብስበው ሁለት አካል፣ ሁለት ባህርይ ባዩን ንስጥሮስን ያወገዙበት ጉባኤ አንዱ ነው!!በዚህ ጉባኤ ላይ ንስጥሮስ እመቤታችን የወለደችው መለኮትነት የሌለው ወልድን ብቻ (እሩቅ ብእሲ) እንጅ መለኮት የተዋሀደው ስጋን አይደለም በማለቱ “ታዲያ ሰብዐ ሰገል አምኃ አቅርበው የአምልኮ ስግደት የሰገዱት ለሩቅ ብእሲ ነው እንዴ” ተብሎ ተረታ!!የእመቤታችን ወላዲተአምላክነትም በጉባኤው ዳግም በአጽንኦት ተነገረ!!በመጨረሻም በውሳኔው አንቀጸሃይማኖት….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን….ሲሉ የቀደሙ አባቶችን ትምህርት አጽንተው ከ1500 አመት በፊት በዶግማ ደንግገውልናል!!ዶግማ ደግሞ አይሻሻልም፣አይጨመርበትም፣አይቀነስበትም!!ስለሆነም በመላው ዓለም ይሄን ጉባኤ በሚቀበሉ የምእራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሉተራውያን በቀር እመቤታችንን ‘ሰአሊ ለነ ቅድስት’ ሳይል የሚውል ክርስቲያን የለም!!
  4. እንግዲህ የአማላጅነትን አስተምህሮ ትናንት በትጉሃን ወጣቶች የተመሰረተው ጨቅላው ማህበረቅዱሳን አመጣው ማለትን እንደ ፌዝ ቆጥረነው ዘርዐያዕቆብ አመጣው መባሉም ተአማኒነት እንደሌለው በአስተምህሮው ቅድምና አይተናል!!በመሰረቱ ዘርዓያዕቆብ ከላይ ከተጠቀሱት አበው በሁዋላ 1ሺህ አመት ዘግይቶ ከ1426ዓ.ም እስከ 1460ዓ.ም የነገሰ የቅዱሳት መጻህፍት እውቀት ያለው ክርስቲያናዊ ንጉስ ሲሆን የእመቤታችንን ተአምር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅ/መጻህፍትም ወደ ግእዝ እንዲመለሱ በማድረግ፣ሰንበታት እንዲከበሩና አምልኮ ጣኦትም እንዲጠፋ በማድረግ በአንድ በኩል በበጎ የሚነሳ ታሪክ ያለው ነጋሲ ከመሆኑ በቀር የእመቤታችንን አማላጅነት ማመን በእሱ ዘመን ተጀመረ የሚል የአፍም፣የመጣፍም ታሪክ የለም!!እርግጥ ነው በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የወሰዳቸው ምላስ የመቁረጥና አፍንጫ የመፎነን ድርጊቶች ክርስቲያናዊ ናቸው ለማለት ይቸግራል!!እንደ ሥርዓቱም መወገዛቸው ብቻ በቂ ቅጣት ነበር!!ሆኖም ይህ ድርጊቱ ለሃይማኖቱ መነቃቃት ያበረከታቸውን ስነጽሁፋዊ እና የስርዐት መስተካከሎች የመሳሰሉ በጎ አስተዋጽኦዎች አይሸፍንበትም!!እኛም በጎ አርአያውን ይዘን ያልተገባውን በመዝገብ ቤት እናኖረዋለን-ለታሪክ!!
  ይቀጥላል…..

  ReplyDelete
 10. .......የቀጠለ
  5. ደቂቀ እስጢፋኖስን አባቶቻችሁ ለማድረግ ስትጥሩ እመለከታለሁ!!አይሆንም!!የእነሱ ልጆች አይደላችሁም!! “በቅሎ አባትሽ ማን ነው ቢሉዋት ፈረስ አጎቴ ነው አለች” የሚባለውን ያስተርትባችሁዋል!!የደቂቀ እስጢፋኖስና የዘርዓያዕቆብ ውዝግብ መንስኤው ጥርት ብሎ ያልታወቀ መሆኑ እንደተጠበቀ ነገር ግን እነሱ ከእናንተ በሚከተሉት ምክንያቶች ይለያሉ!!ልዘርዝራቸው…..
  (ሀ)የጉንዳጉንዲንና የአሲራ መቲራ ቅ/ድ/ማርያም ገዳማትን ጨምሮ የመሰረቱዋቸው ገዳማት በሙሉ በእመቤታችን ስም ናቸው፣በጻፉዋቸው መጻህፍትና ገድላት ሁሉ የምስለፍቁር ወልዳ ስዕል አለ፣ውዳሴማርያምና አንቀጸብርሃን ይደግማሉ!!ስለሆነም ለእናንተ ያላቻው የመንፈስ አባትነት ሩቅ ነው!!አትዛመዱም!!በነገራችን ላይ ደቂቀ እስጢፋኖስ በእመቤታችን አማላጅነት አንዳችም ጥርጣሬ የላቸውም!!አማላጅነቱዋን ያምናሉ!!
  (ለ)እናንተ የምታናንቁትን የምናኔ ህይወት በዘርዓያዕቆብ ዙሪያ ካሉት መነኮሳትም በላይ ማጥበቃቸው አንዱ ከንጉሱ ያላስማማቸው ምክንያት እንደሆነ ፕ/ር ጌታቸው ይገልጻሉ!!እናም እናንተን የእነሱ ልጆች ማለት የሚያስቀስፍ ውሸት ነው!!
  (ሐ)ደቂቀ እስጢፋኖስ ወደ ደቡብ ከተሰደዱ በሁዋላ ቤ/ክ ተክለው፣ታቦት አስገብተው የወንድሞቻቸውን ተዝካር ስለማውጣታቸው ታሪካቸው ይናገራል!!እናንተ ደግሞ ታቦትና ተዝካርን የሚቀበል ሰው አባቴ ለማለት ስትደፍሩ አናይም!!
  (መ)ለእመቤታችን ሊደረግ ስለሚገባው የጸጋ ስግደትም ንጉሡ ለእኔ ካልሰገዳችሁ ይላቸው ስለነበርና አቀራረቡም እልህ የተሞላበት ስለነበር አልፎ አልፎ አንሰግድም ሲሉ ቢሰማም ድርሰቶቻቸው ግን ይህን አያሳዩም!!ለምሳሌ አባ እስጢፋኖስ “በእንተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም” በሚለው ድርሰቱ ገጽ 38 ላይ ….አንቺን ከፍ እናደርግሻለን በስብሐትና በውዳሴም(በአምልኮ አላለም)እንሰግድልሻለን…ይላታል!!ደቀመዝሙሩ አባ ዕዝራም በገድሉ ገጽ 294/5 እንደተጻፈው…ለማርያምና ለአንድ ልጁ መስቀል ስለመስገድ እኔ እሰግዳለሁ፣መምህሮቼም ይሰግዳሉ፣ምክንያቱም መጽሐፍ የጌታችን እግር በቆመበት ቦታ እንሰግዳለን(መዝ131ቁ7)ይላል.ቦታውም የማርያም ሆድ ነው…..ይልባችሁዋል!!እንግዲህ በተአምረ ማርያም ያን ያህል የተወቀሱት ደቂቀ እስጢፋኖስ ገድላቸውን በጻፉበት ወቅት አቁዋማቸውን ቀየሩ ወይስ ከመጀመሪያውም ንጉሡ ሀሳባቸውን በቅጡ ሳያዳምጥ ለግዝትና ለግዞት ዳረጋቸው የሚለው ዝርዝር ጥናት ይጠይቃል!!
  (ሠ)ነገር ግን በፕሮቴስታንት አስተምህሮ ላይ አንዳችም ነቁጥ ሳትጨምሩና ሳትቀንሱ ተሃድሶ የሚለውን ቃል ብቻ ከሰንደቁ በላይ የምታውለበልቡ አውለብላቢ ዘመነኞች ከደቂቀ እስጢፋኖስ ጋር አንዳችም ተዛምዶ እንደሌላችሁ ለመናገር የዐይነልቡና ንባብ አይጠይቅም!!ዐይነስጋችን በቂ ነው!!ልዩነታችሁ ከመታየትም የሚዳሰስ ስለሆነ!!እናንተ ሌላ፣ደቂቀ እስጢፋኖስ ሌላ!!ማሞ ሌላ፣መታወቂያው ሌላ እንዲሉ የመሀል አገር ሰዎች!!
  6. እናንተማ ወላዲተአምላክን ከውሃው እንጅ ከቡዋንቡዋው፣ከሽቶው እንጅ ከብልቃጡ ጉዳይ የለንም እንደምትሉዋት ሰማን!!አዘንን፣ተከዝን፣ተከፋን!!ባይገለጽላችሁ!!ባታስተውሉ!!ቡዋንቡዋ ውሃ የሚያልፍበት እንጅ የሚመነጭበት አይደለም፣ብልቃጥም ሽቶ የሚቀመጥበት እንጅ የሚቀመምበት አይደለም!!ጌታ ግን ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ፣ከነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ የህጻንነትን ሥርዓት ሳያፋልስ ተወለደ እንጅ እንዲያው እንደ ቡዋንቡዋ ውሃ ሳይነካካ-የራሱን አካል ብቻ ይዞ ሽው ብሎ አላለፈም!!ስለዚህ ምሳሌው የሚገባ አይደለም!!ህጹጽ ነው፣ጸያፍ ነው!!እንኩዋን የጌታ እናት በአመጻ የወለዱ እናቶችም ለልጆቻቸው ቡዋንቡዋ፣ብልቃጥ አይደሉም-እናት እንጅ!!9 ወር ተሸክሞ ከሚበላው በጥበበ እ/ር በህንብርቱ ለጽንሱ ምግብ እያቀበለ የሚወልድ ቡዋንቡዋም ሆነ ብልቃጥ ያለ ስለማይመስለኝ እባካችሁ በየመንገዱ ጌታን ተቀበሉ ለሚሉን ወገኖቻችሁ ይሄን ምሳሌ ቀይሩት በሉልን!!
  7. መቼም የጥቅስና የድርጊት ጫፍ ይዛችሁ የእናንተ ያልሆነውን ሁሉ የእኛ ነው ለማለት ስለማትቦዝኑ ሰሞኑን ደግሞ ዘማሪት ዘርፌን የእኛ ናት ለማለት ስትቃጡ አየን-ደቂቀ እስጢፋኖስን የእኛ ለማለት እንደምትቃጡት ማለት ነው!!እሱዋ የእናንተ ስላለመሆኑዋ በተግባር ከገለጸችባቸው ለእመቤታችን የቀረቡ ዝማሬዎች ውስጥ በአንደኛው የመዝሙር አንጉዋ ይሄን እድል ስለሰጣችሁኝ በእግዚአብሄር ስም አመስግኘ ልሰናበታችሁ!!

  መሰንቆ በገናን ያዙ፣
  በእልልታ ውዳሴን አብዙ፣
  ሰማያት ምድርም ያድምጡ፣
  ለማርያም ምስጋና ስጡ.
  በጥዑም ልሳን በሚንቆረቆረው፣
  በሰማዩ ስልት ከአበው በወረስነው፣
  ሰላም ለኪ እጅ እንነሳለን፣
  ከመቅደሱዋ ገብተን…….

  ሰአሊ ለነ ቅድስት!!
  ወስብሐት ለእግዚአብሄር!!

  ReplyDelete
 11. I am very sorry to read this because the prayer to virgin Mary has been practiced in eastern orthodox and oriental churches 1000 years before Atse Zereyacob. You are not afraid of GOD to lie!
  Mary is not like any other children of Adam, stained with sin. No! The Angel called her FULL OF GRACE AND BLESSED AMONGST WOMEN. Mary is the Mother of Jesus Christ and consequently Mother of God. There is no higher dignity to which a creature can be raised. The Gospel says that the generations will proclaim her blessed and you are trying to despise her and look down on her. Your spirit is not the spirit of the Gospel or of the Bible which you proclaim to be the foundation of the Christian religion

  ReplyDelete
 12. Some individuals who tolerate this blog because you have misunderstanding with Mahibre Kidusan and this unresolved misunderstanding developed to contradiction inflamed with war of words. This site is protestant site the only thing these guys have read geez books. They are not heretic only but also liar! They insight people like you to stop Mahibre Kidusan. But, there aim is to make EOTC a protestant denomination!Let us all resolve our contradiction in Christian way and turn against the,unless they repenT!

  ReplyDelete
 13. Aba Selama,

  Enough has been said to respond to this misguided ill conceived article. I to the most part agree the spirit of this site but this one looks like a coming out party to me.

  So, what is next

  Kidase Mariam ? :)

  Geta yirdan

  ReplyDelete
 14. Aba selamawoch,

  Maq'n atibiken eminikawom
  EOTC wust, Lewut eminifelig (for better that is)
  But remember that we know our Dogma/kenona very well to look at out of bound articles.

  Many have answered the question very well and no need to repeat

  ReplyDelete
 15. ገብርኤልን ብስራት የካደ የለም ጉዳዩ ከእመቤታችን ሳይሆን እናንተ መመለስ ያልቻላችሁትና መቶ ጊዜ ጠይቄ መልስ ያላገኘሁት ጌታ ምን ከልክሎ ያዉቅና ነዉ ወደ ምልጃ የተኬደዉ ነዉ ርህሩህ ጌታ እንክዋን ለምነነዉ ሳንጠይቅ የሚሰጥ ጌታ በደም የተገዛን ስለሆንን ከእንግዲህ ልጆች አንጂ ባሮች አይደላችሁም ያለንን እንደገና እንደ ባዕድ በክብር ቢበልጡንም እንደኛዉ ሰዉ በሆኑና በአንቀላፋ ወገኖቻችን ማስጠየቅ ዉሃ የሚቁዋጥር አይደለም ራሳችሁን ጠይቁ እንጂ ፍቅሩን ካለመረዳት ወይም ካለማወቅ የተነሳ ጌታችንን ገፋገፋ ማድረግ ከማንም የበለጠ የምትጎዱት እናንተ ናችሁ እመቤታችን ልመናችንን ሰምታ ይህንና ያንን አደረገችልን ለምትሉት ደግሞ እርሱዋ ለመሆንዋ እርግጠኛ አትሁኑ መንፈስን ሁሉ ማመን ሌላዉ ስህተት ነዉና በዚህ የአብይ ፆም ጌታችን የቀራንዮን ምስጢር እንዲያበራላችሁ አብረን እንፀልይ በእዉነት የቤተክርስቲያናችን ነገር ያስለቅሳል እንዲጎበኛትና እንደሚጠብቀው ንፅህት ሙሻራ እንድትሆንለት እንጂ ደባሎችን አስገብታ እንዳታስቀናዉ ለንሰሐዋ እንድትበረታ ክርስቶስ እንዲረዳት የዚህ የአብይ ፆም ዋና ጉዳይ መሆን አለበት የአምላካችን ጸጋ አይለየን

  ReplyDelete
 16. "አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ በእናንተ ዘንድ እንደ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፋጠንና እንዲከብር ጸልዩልን። ከክፉዎችና ከከሓዲዎች ሰዎችም እንድን ዘንድ ጸልዩልን፣ ሁሉ አማኝ አይደለምና። 2ተሰ 3 ቊ 1 ከዚህ ቃል ወይም ጥቅስ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ እርሱ አስተምሮ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያምኑ ካደረጋቸው ምእመናን ለሚሠራው ሥራና ለሕይወቱ ደንነት የጸሎት እርዳታ እንደጠየቀ እንረዳለን።
  ይኸን የመሰለ አንዱ ለአንዱ እንዲጸልይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛት በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን በብዛት ይገኛል።
  ቅዱስ ጳውሎስም ይህን መሠረት በማድረግ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመኑ ከምእመናን የጸሎት እርዳታ መጠየቁ፣ ጌታ እኔ ብለምነው አይሰማኝም የሚያስፈልገኝን አይሰጠኝም ብሎ አይደለም። እንዲህ እንደማይል የቅዱስ ጳውሎስን እምነትና ጸጋ የሚተረዳ ሁሉ ያውቀዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በእምነትም ሆነ በጸጋ ስጦታ ከእርሱ ከሚያንሱ ምእመናን የጸሎት እርዳታ ከጠየቀ፣ ዛሬም አንድ ኃጥእ(ኃጢአተኛ) ምስኪን "አንትሙሰ ንጹሐን አትሙ" ማለትም እናንተስ ንጹሐን ናችሁ ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰከረላቸው ከደጋግ ሰዎች የጸሎት እርዳታ መጠየቅ ስህተትና አምልኮ ባዕድ ይሆናል ማለት መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ ካለመረዳት የሚመጣ የግንዛቤ ጉድለት ነው።

  በልዩ ልዩ ጊዜ ከአእምሮአችን የሚፈልቀውን ሀሳብ በእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ እናስተካክል እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ እኛ ሀሳብ ለመለወጥና ለመጣመም ባንሞክር መልካም ነው፣ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድ በፍርድ ያስጠይቃል።

  በትሕትና በፈሪሃ እግዚአብሔር ራስን ዝቅ በማድረግ በእግዚአብሔር ያመነውን ሰው ጸልይልኝ፣ አማልደኝ፣ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት ዘመን ጀምሮ ያለ የኖረ እምነት እንጂ ዛሬ የተፈጠረ አምልኮ ባዕድ አይደለም። በእግዚአብሔር ያመነ ጻድቅን ሰው ከፈጣሪህ አማደኝ ጸልይልኝ በማለቱ አምልኮ ባዕድ ፈጽመሃል ተብሎ የተፈረደበት አንድም ሰው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች" ይለናልና በእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ እንመራ። ያዕ 5 ቊ 16

  ReplyDelete
 17. የምትገርሙ ናችሁ ቆይ ሰው መጽሃፉን አያውቀውም ብላችሁ ነው መጽሃፉን ለማታውቁት ውዳሴ ማርያምን ያክላል ገዝታችሁ ማየት ትችላላችሁ ጸሃፊው ስለሚዘባርቀው ነገር አንዳች ነገር የለም ...ወይም መዝገበ ጸሎት የጸሎት መጽሃፍ ካላችሁ እዛም ላይ ተተርዞ ይገኛል እዩት ምን ይባላል እንግዲህ እግዚአብሄር ይማራቼው እንጂ አባ ሰላማዎች እንደሆነ ሰይጣን ከልከፋቼው ቆይⶆል እና በዚህ አልደነቅም እነህሩይ ስለ ራእየ ማፘም መጽሃፍ ባለማወቃቼው እውነት ይሁን ዉሸት ሳያረጋግጡ በማመናቼው ተደንቅያለሁ

  ReplyDelete
 18. Thank you Bemnet, Astewaye sew neh.

  ReplyDelete