Tuesday, February 11, 2014

የነነዌ ንስሐ (ዮና.3÷5-9)

Read in PDF                                                         
                                                       ምንጭ፡- የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥እንዲህም አለ፦ ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፡፡ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”(ዮና.3÷5-9)፡፡
      እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን የትድግና ሥራውን ለአህዛብም እንዲናገሩ ነቢያትን አዟል፡፡ እግዚአብሔር በቤቱ ስላሉት ብቻ አይጨነቅም፡፡ በሩቅ ያሉ እስኪሰሙ ድረስም ሳያቋርጥ በፉጨት ድምጽ ይጣራል፡፡ በቀደመው ዘመን ኤልያስና ኤልሳዕ (1ነገ.17÷24፤2ነገ.8÷1-17)በኋላም እነአሞጽ ከይሁዳ ውጪ ለእስራኤልና ለአህዛብ የእግዚአብሔርን የትድግና ሥራ የተናገሩ ነቢያት ናቸው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእስራኤል ውጪ ወዳሉ ከተሞችና ሀገሮች እየሄደ ያስተምር ነበር፡፡ መድኃኒቱ ጌታ “እምነትሽ ታላቅ ነው፤እምነትህ ታላቅ ነው፡፡”(ማቴ.15÷28፤ሉቃ.7÷9) ያላቸው ሁለቱ ሰዎች የተገኙት ኪዳን ከተቀበሉትና መቅደስ ከነበራቸው ህዝቦች መካከል ሳይሆን ከአህዛብ ወገኖች እንደሆነ ቃሉ ይመሰክራል፡፡

      አገልግሎታችን የራቁትን መቅረብ ካልቻለና ከመቅደስ እስከአውደ ምህረት ብቻ ከሆነ የጌታ ፈቃዱ እንዲህ አይደለምና ዳግም ልናርመውና ልናስተካክለው ይገባናል፡፡ ብዙውን ጊዜ በቤቱ ብቻ ስላለን የምንመካ ጥቂት አይደለንም፡፡ ጽሁፎች ፌስቡክ ላይ ሲለቀቁ የሚሰጡ አስተያየቶችን  አያለሁ፡፡ የሚደንቀው ነገር አስተያየቱን የሚሰጡት ጥላቻን የማያልፉ ፣ቅንነት የጎደላቸው ፣የሌላውን ሰው እምነትና አመለካከት የሚያጥላሉ “የስም ክርስቲያኖች” መሆናቸውን ሳይ ለሌላው የተወደደ አክብሮት ያላቸውን ክርስቲያኖች ያልሆኑ ወገኖቼን አከብራቸዋለሁ፡፡
     ጌታ እግዚአብሔር ጭከናና ዝርፊያ፣አመንዝራነትና ጥንቆላ፣በንግድ ማጭበርበር የምትበዘብዘዋን እንዲሁም በእርሱ ላይ በክፋት የማታሴረውን ታላቂቱን የአሶርን ከተማ ነነዌን (ናሆ.1÷11፤2÷12፤3÷1፡19፤3÷16) እንዲሁ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ነዋሪዎቿ አህዛብ ፤ሥራዋ ደግሞ እንደሰዶምና ገሞራ ክፉ መንገድና አመጽ ቢሆንም (ዮና.3÷8-10) እግዚአብሔር ግን ወደዚህች ከተማ ታላቁን ነቢይ ዮናስን ላከው፡፡

    መድኃኒት ለበሽተኛ እንዲያስፈልግ ቃሉ የሚያሰፈልጋቸው ከሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች እንደሆኑ ለሚያምኑ ነው፡፡ በነነዌ ከተማ የነበሩ ኃጢአቶች ዛሬም ምድራችንን የሚያስጨንቁ ናቸው፡፡ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዛሬ በንግድ ማጭበርበር “ክርስቲያን ነን” የሚሉ ሳይቀሩ የተያያዙት ሥራ ነው፡፡ ስኳር ላይ አሸዋ ፣በርበሬ ላይ ቀይ አፈር፣ቅቤ ላይ ሙዝ … ትርፍ ለማግኘት እየሳሱ የድኃውን ቤት የሚበዘብዙ ብዙ ናቸው ፤እግዚአብሔር ግን እንዲህ ያሉትን ቤታቸውን ያውካል፡፡(ምሳ.15÷27) በንግዱ አለም ሌላው አጸያፊ ነገር አባይ ሚዛን ነው፡፡ ኪሎ እየሰረቁ የሚሸጡና የሚገዙቱ ከሚያገኙት ትርፍ ይልቅ በሀገር የሚያመጡት መርገም ተከፍሎ የማያልቅ ነው፡፡(ምሳ.11÷1) ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ፍጻሜያቸውን መራራ እንደሚያደርገውም ተናግሯል፡፡(አሞ.8÷5-11)
     በዚህ መንገድ የሚመጣውም ገንዘብ በአስራትና በኩራት መልክ ወደእግዚአብሔር ጉባኤ ቢመጣ ያረክስ እንደሆን እንጂ የሚረባ ነገር የለውም፡፡ ሌላው በነነዌ የገነነው ኃጢአት ጋለሞታነትና አመንዝራነት ነው፡፡(ናሆ.3÷4) የዝሙት ርኩሰት የሥጋን ፍላጎት በተለየ መንገድ ያረካ ይሆናል፤ነገር ግን በገዛ አካላችን ላይ ኃጢአትን እንሰራለንና ቅዱሱን የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ሰውነታችንን እናረክሳለን፡፡(1ቆሮ.6÷18) ዛሬ ከገዳም እስከከተማ ፣ከሆቴል እስከቤት ፣ከትምህርት ቤት እስከማረሚያ ቤት ፣ከዩንቨርሲቲ እስከመስሪያ ቤቶች፣ከመጽሔት እስከፊልሞቻችን … እየተሰሩ ያሉትን ዝሙትና ግልሙትና ላየ የእግዚአብሔርን ቁጣ በኃጢአት ደጅ የምንጠና መሆናችንን ያሳብቃል፡፡
     እኒህና ሌሎች ኃጢአቶች በገነኑባትና “ክፋትዋ ወደፊቱ በወጣባት” በነነዌ ሄዶ እንዲሰብክ የአማቴ ልጅ ወደእርስዋ ተላከ፡፡(ዮና.1÷1) ዮናስ “ከእግዚአብሔር ይልቅ ለህዝቡ ሳስቶና ሐሰተኛ ላለመባል ለክብሩ ተቆጭቶ” አለመታዘዝን መርጦ ወደሌላ መንገድ ወደተርሴስ ሄደ፡፡ ከነቢዩ የጠፋው ቅንነት ከአህዛብ መንገደኞች ተገኝቶ በመርከብ ላይታዘዝ የሄደው ዮናስ በባህር ልዩ መንገድ በአሳ አንበሪ ሆድ ተጓጉዞ ወደነነዌ ደረሰ፡፡ ዮናስ ወደነነዌ ቢደርስም በውስጡ ግን ደስተኛ አልነበረም፡፡
    ጌታም “የምነግርህን ስበክላት አለው” ነገር ግን ዮናስ የእግዚአብሔርን መልዕክት አቅራቢ የነቢይነቱን አገልግሎት ችላ ብሎ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ የታዘዘ ቢመስልም የነነዌ ህዝቦች እንዲጠፉ ይፈልግ ነበረ፡፡(ዮና.3÷3፤4÷1)ጌታ ግን የኃጢአተኛውን መጥፋት አይወድድም፡፡ (ህዝ.3÷18፤18÷23)ዮናስ በልቡ እንዲድኑ ባልወደደ መጠን ለከተማይቱ ገብቶ ሰበከላት፡፡ በነነዌ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደተቆረጠ ጮኾ ተናገረ፡፡
       ነነዌ በዮናስ ስብከት በእግዚአብሔር አመነች፤ከታላቁ እስከታናሹም ይጾም ዘንድ ጾምን አወጀች፡፡ ስለኃጢአተኝነቷ ምንም ምክንያት አላቀረበችም፡፡ አህዛባዊቷ ከተማ ታላቅ እምነት ተገኘባት፡፡ በተቆረጠና በተከተተ ዕድሜዋ ራስዋን ለንስሐ አዘጋጀች፡፡ ምህረትና ይቅርታን አብዝታ ወዳለችና እንሰሳት እንኳ ሳይቀሩ እንዲጾሙ አወጀች፡፡ንስሐ ገብተን ለመጾም ምክንያተኞች አንሁን፡፡የዛሬው ድንበር አልባ ክፋታችንን ትላንት በነበሩት ትውልዶች አናመካኝ፡፡ አመንዝራነታችንን፣ ዘፋኝነታችንን ፣አባይ ሚዛን የበዛበት ንግዳችንን፣ጋለሞታነታችንን፣በዘረኝነት መከፋፈላችንን፣ በክፉ ምኞት መንደዳችንን … ለሌላ ሳይሆን በንስሐ መንፈስ ለራሳችን እንናዘዘው፤ በደለኝነታችንን አምነን ወደፊቱ እንምጣ፡፡
    ነነዌ ፊቷን በፊቱ አዋረደች፤ንጉስ ከመኳንንቱ ጋር ዝቅ አለ፤የአመንዝራነቱና የዝሙቱ ጌጥ ልብስ በማቅ ተከደነ፡፡ ሁሉ ከግፍና ከአመጹ ከክፉ መንገዱም ተመለሰ፡፡ በንስሐ ልብ ጾመዋልና በሦስት ቀን የጸሎትና የጾም አዋጅ እግዚአብሔር ሊያመጣ ያለውን ቁጣ መለሰ፡፡ ያለንስሐና የኃጢአት ኑዛዜ የሚሆን ጾም ከምግብ አድማና ከረሃብ የዘለለ ምንም ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ጾማችን ከኃጢአትና መንፈስን ከሚያረክስ በደል መከልከል እንጂ ከመብልና መጠጥ የመከልከል ልማድ ብቻ ሊሆን አይገባውም፡፡
   አዎ! በብዙ ነውርና በደል ተይዘናልና ጾምና ጸሎት ያስፈልገናል፤ጾማችን ግን ለምን እንደምንጾም ርዕስ፣ንስሐና የኃጢአት ኑዛዜ ይቅርታም ሊኖረው ይገባል፡፡ የነነዌ ንስሐ መልስ ያገኘው አምነው ከልብ ኃጢአትን ጠልተው በመመለሳቸው ነው፡፡ እውነት የጌታን ምህረትና ይቅርታ ከወደድን ቀድመን ምንም የኃጢአት ምክንያተኝነት ሳናቀርብ በመታዘዝ ንስሐ እንግባ፡፡
ጌታ ጾማችንን በምህረቱ ይቀድስልን፡፡አሜን፡፡

30 comments:

 1. የጌታ ፍቅርFebruary 11, 2014 at 1:59 AM

  የነነዌም ሆነ የሚቀጥለዉ አብይ ጾማችን ትልቁ አጀንዳ መሆን ያለበት ጌታ መድሐኔዓለም ቤተክርስቲያናችንን እንዲታደጋት፤ ከባልቴቶቸ ተረትና ከስህተተ ትምህርት፤ከማንኛዉም ኑፋቄ ጸድታ አምራና ደምቃ ሙሽራዋን ኢየሱስ እንድትጠባበቅ የክርስቶስን ፈቃድ የሚጠይቁ መሆን አለበት፡፡የኛና ቤተክርስቲያንና ሌሎች በርካታ ክርስቲያን ነን ባዮች ሉተራኖችንም ጨምሮ በእዉነት! ጌታ እንዳይመጣ ምክንያት መሆን የለባቸዉም፡፡ማራናታ እያልን ብንዘምር ዋጋ የሚኖረዉ በንስሐ እንባና ተማጽኖ ስንለምነዉና ለዚህ ከባድ ሃጢአት ይቅርታ ስናገኝ ብቻ ነዉ፡፡ የኔ ጾም አጀንዳ የሚሆነዉ፤የማምነዉ ጌታ ቤተክርስቲያኔን ከስህተት ትምህርትና በምልጃ ሰበብ ኢየሱስን በአርባኛ ረድፍ ከምታመልከዉ ልምዶችዋ ነፃ እንያደርጋትና የክርስቶስ ሙሽሪት ተብላ እኛም አብረን እንድንነጠቅ ስለሆነ በእርግጥ የክርስቶስ ወገኖች የሆናችሁ ሁሉ አጀንዳዬን የጋራ እንድታደርጉልኝ በእግዚአብሔር ስም እለምናለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Anchi. Degimo addis pente mehonsh new? Anchin bilo ye orthodox lij! Maferia nesh yegeta fikir min malet endehone fetsmo alteredashiwum. Yanchi sim mehon yalebet yalsekene/ jemari/ pente/ tehadiso new

   Delete
  2. This comment has been removed by the author.

   Delete
  3. ስድብን ምን አመጣዉ? ስህተት ከተናገርኩ ስህተቱን ማዉጣት እንጂ መሳደብ እኮ ክርስቲያናዊ አይደለም፡፡ ፔንቴ የሚለዉ ማስፈራሪያም ዘፈን እምቢ ሲለዉ በቀረርቶ የገባበት ሰዉዬ ጉዳይ አይነት ነዉ፡፡ የናንተ ወግ እንደልጅነታችን ጅብ መጣብህ ማለት አይቻልም ይልቅስ እናንተ ጅብ ደረጋችሁት ፔንቴ የኦርቶዶክስ በ ክ ክርስትና እያስነሳች ይህንን ሁሉ ህዝብ ያመረተችለት በየጊዜዉፔነቴዉ እየገነደሰ የሚወስድብን ለምንድርነዉ ብላችሁ መጠየቅ ለችግሩ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ ማህበራችሁ ከወንጌል ይልቅ ስድብ ስለሚያስተምራችሁ ነዉና ልብ ግዙ፡፡ እስቲ በሞቴ በኢቢኤስ የአየር ሰዓቱ ወንጌል ለጠማዉ ህዝብ ዜናማቅ ማቅረብስ ያልበላዉን ማከክ አይደለምን

   Delete
 2. ጾመ ሰብአ ነነዌ አትም

  የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ.ም.


  ርዕሰ ደብር ብርሃኑ አካል


  ጾመ ነነዌ ከአዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት 21 ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ 35 ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም አይወጣም ማለት ነው፡፡


  የሦስት ቀኑን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ሲሆኑ ከተማዋ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ መሥራቿም ናሞሩድ ነው፡፡ ዘፍ.10፥11-12 ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነ ከተማ እጅግ ሰፊና ያማረ ፤ የከተማው ቅጥር ርዝመት አሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ነበር፡፡ ሰናክሬም ብዙ ሕንፃዎችንም ሠርቶበት ነበር፡፡ /ዮናስ. 4፥11/


  የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊጠፉ ሲሉ ቸርነትና ምህረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ ሂድ አለው፡፡ ሉቃ.11፥30 ዮናስ የስሙ ትርጉም “ርግብ” ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ትንቢትን ተናግሯል፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል ፡፡ 2ነገ14፥25፣ ት.ዮና1፥1


  እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አልሄድም” አለ፡፡ “አንተ መሀሪ ነህ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ስትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ፡፡” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧበማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባህሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባህር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” አሉት፡፡ ዕጣም ቢጣጣሉ ዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔር የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡ ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ ዮናስ 1እና2 ፡፡ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ማራቸው /ዮና.3/


  ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስህተት መሆኑን እግዚአብሔር ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ /ዮና.4/ ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል፡፡ በስንክሳር ታኅሣሥ 5 እንደሚነግረን ፤ወበልዓ አሐደ ኀምለ ይላል ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር አጥፍቶአል፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የስራጵታ መበለት ሕፃን ዮናስ እንደሆነ /1ነገሥ.17፥19/ ሲያስረዳን ፤ክርስቶስ የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል፡፡ /ማቴ.12፥19-42/ ሉቃ.11፥30-32/፡፡


  ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፡፡ ይሄውም አስቴር አስቀድማ ሦስት ቀን ጾማ ጸልያ በእሥራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች ኢሳ.4፥15-16፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ልጇ ሕፃኑ ኢየሱስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ እንዳገኘችው ሁሉ ሉቃ.2፥46 ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል ሉቃ.13፥32፡፡


  የነነዌ ሰዎች የተነሳህየን ምሳሌ ናቸው ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝቦችና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለሆኑ ያሳዝኑኛል ያለው፡፡


  ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለበት ወቅት እኛም ብንመለስ እና ንስሐ በንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለሆነ “ወደኔ ተመለሱ እኔም ይቅር እላችኋለሁ ”ብሎ አስተምሯል፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ጾመ ነነዌ የሚከተሉትን ምሳለዎች እናገኝባታለን ታሪኩን በማስታወስ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሀሪነት የምናስታውስበት ነው፡፡ ይኸውም ፍጥረቶቹ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርጋል፡፡ ዮናስ ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ በተለየ ጥበቡ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ሌላ ነቢይ አጥቶም አይደለም እሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለፈለገ እንጂ፡፡


  በዮናስ አማካይነት የተደረጉ ተአምራትን መገንዘብና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን ተገንዝበን ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች አና ለወላጆች መታዘዝን እንማርበታለን፡፡ እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን ጸልየን ከኃጢአታችን እንድንነፃ ነው፡፡ ብንጾም እራሳችን፣ ሃገራችንን፣ እጽዋቱንና እንስሳቱም ሳይቀር በኛ በደል ምክንያት በድርቅ በቸነፈር እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ይቅር ስለሚል ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. grum meleekit..biblical....God bless you!!!

  ReplyDelete
 4. Thanks, I follow your link and learn a lot. Keep it up. Please less gossib and agul were.

  ReplyDelete
 5. I am surprise that there is no mention of Mehabire Kidusan in this article. This is some progress from you guys, instead of trashing others just teach the word of God as it is.

  ReplyDelete
 6. Do I see some improvment here??? .You used to say Yenenew tsome legn mendenew???????keep it up

  ReplyDelete
 7. Ye geta fikir

  Your trashy comment doesn't make any harm upon the holy church. First you should learn what a gospel is under orthodox Tewahido scholars. Until then you are living under darkness.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የጌታ ፍቅርFebruary 12, 2014 at 5:06 AM

   ወዳጄ አቶ ማሩ፤ ለመሆኑ የተጠቀሙበት የዓይን ምልክት የአዉሬዉ (the illuminati) መሆኑን አዉቀዋል? ወይስ ስድቡን ሲያቀብልዎት ማንነቱን አልነገረዎትም? ደግሞ የኦርቶዶክስ ወንጌል የሚባል እንዳለም ይህዉ አዉሬ ነገረዎትን? አለዚያማ ወንጌል አንድ ብቻ ነዉ፤ ምናልባት እነዚህ ተረታ ተረት የሞላባቸዉን የሀሰት ትምህርቶች ማለትዎ ይሆን? ለማንኛዉም የርስዎ ባለዓይን በኢየሱስ ስም እንዲታሰርና እርስዎም ነጻ እንዲወጡ በነነዌ ጾም አጀንዳዬ ላይ ጨምሬአለሁ፡፡ ዛሬ ማታ ማለቴ ነዉ፡፡

   Delete
 8. Gete Eyesus Abezetu yebarkeh!

  ReplyDelete
 9. yezihe sehuf sehafi, egziabehere yibarkehe. teru sehuf new.

  ReplyDelete
 10. You guys ( Protestant tehadiso) yo say that you don't to believe on decreed fasting. We oriental orthodox fast this fast thinking that we will be forgiven from our sins. Fasting and prayer are our path of repentance!
  Amen

  ReplyDelete
  Replies
  1. የጌታ ፍቅርFebruary 13, 2014 at 5:58 AM

   1ኛ፤በነገራችን ላይ እኔ ወንድ ሳልሆን ሴት ነኝ፡፡ ጥርት ያልኩ የኦርቶዶክስ ልጅ ኢየሱስን በልቤ ዙፋን ላይ ያነገስኩት፤ ጌታዬና አምላኬም አባቴም ነህ ብዬ የተቀበልኩት፡፡ 2ኛ፤ አዎ! በቤተክርስቲያኔ ዉስጥ የሚካሄደዉን ክህደት Protest አደርጋለሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስና መድሃኔዓለምን ደባል ታቦት የሚል ቅጽል መሰጠቱን እንደዚሁም የሐሰት ወንጌል የሚያስተምሩ አድር ባይ ሰባኪዎችንም እንደ ጳዉሎስ (ወደ ገላቲያ ሰዎች) አጥብቄ አወግዛለሁ፤ ለክርስቶስ ክብር እስካስፈለገ ድረስ ቤተክርስቲያን የማያቋርጥ ተሀድሶ ብታደርግ ምንድርነዉ ክፋቱ? ተሀድሶስ ስድብነቱ ምኑ ላይ ነዉ? በወግ ተጠርንቆ መኖርስ ክርስትና ነዉን? በክርስቶስ እናምናለን እያላቸሁ ገና መዳናችሁን እንኩዋን ያልተረዳችሁ የምታሳዝኑ መናፍቃን መሆናችሁስ ለትምህርታችሁ ህዳሴ አያስፈልግም ትላላችሁን? እነዚህ ሁሉ የፊታችን ሁዳዴ ጾም አጀንዳ ይሁኑልን፤ የጌታችን ፀጋና በረከተ አይለየን፤ አሜን፡፡

   Delete
  2. Geta yebakesh! Geta abezetu yebarkesh!

   Delete
 11. keep up good job. May God bless you abundantly for telling the truth.

  ReplyDelete
 12. Yegeta Fikir, good job.

  ReplyDelete
 13. Geta Yibarkachu! Yesus geta new!

  ReplyDelete
 14. Be blessed brother

  ReplyDelete
 15. የጌታ ፍቅር
  አንቺ ልጅ ገረምሽኝ፡፡ አሁን ስላንቺ ጾታ የጠየቀ የለ ወንድ ሆንሽ ሴት ምን ያስቀባጥርሻል፡፡ ሁለተኛ እንዳታወሪ ዝም በይ፡፡
  ወደ ዋናው ቁመነገር ስገባ "ጥርት ያልኩ የኦርቶዶክስ ልጅ ኢየሱስን በልቤ ዙፋን ላይ ያነገስኩት፤ ጌታዬና አምላኬም አባቴም ነህ ብዬ የተቀበልኩት፡፡" ብለሽ መናገርሽ ገረመኝ፤ለምን ብትይኝ እንደዛ ከሆንሽ ታዲያ አባሰላማ ብሎግ ላይ ምን ለጠፈሽ፡፡እነሱ እንኳ በብሎጋቸው ላይ የአባቶቻችንን ፎቶግራፍ መለጠፋቸው ሊሸሽጋቸው እንዳልቻለ አምነው በተውበት ሰዓት አንቺን እዚህ መን አመጣሽ፡፡ ብልሹ አሰራሮችን ለመቃወምስ መጠጊያ ሊሆነን የሚገባው የመናፍቃን ቤት ነው እንዴ፡፡ የቤተከርስቲያናችንን ቀኖናዎች ከማይቀበሉ እንዲያውም ቤተክርስቲያንን ለማፍረስና የጭፈራ አዳራሽ ለማድረግ ጠዋት ማታ ከሚታትሩ የጥንተ-ጠላት የዲያብሎስ ማደሪያ ከሆኑ ከመናፍቃን ስር ምን ወሸቀሽ፡፡ የነነዌ ጾምም ሆነ የሁዳዴ ጾም በቤተክርስቲያናችን በቀኖና የተደነገገ መሆኑን አታውቂም ነበር እንዴ፡፡ ለመሆኑ መናፍቃንና ፀረ-ማርያሞች የቱ ቀኖናቸው ነው ጾምን በአዋጅ የሚደነግገው፡፡ የቱ ህጋቸው ነው ሁለት ወር ጹሙ የሚለው፡፡ ልቦናሽን አረጋግተሽ አስቢ፤ከሁለት ያጣሽ ከርታታ የምትሆኝ ሰው ነሽና ምክንያቱም በቤተክርስቲያናችን ውስጥ መኖር የሚቻለው አምኖ ህግና ስርዓት አክብሮ በቀኖናዎች ተወስኖ ነው እንጂ እነሱን እየተቃወሙ አይደለም፡፡ አውሮፓውያን እምነት የለሽና ተስፋቢሶች ሆነው የቀሩት እንዳንቺ ባለ አመለካከት ተጉዘው መጨረሻ መዳረሻቸው ፈጽሞ እምነትን መርሳትና ክህደት የለየት አለማዊነትን መላበስ በመሆኑ ነው፡፡
  "ለክርስቶስ ክብር እስካስፈለገ ድረስ ቤተክርስቲያን የማያቋርጥ ተሀድሶ ብታደርግ ምንድርነዉ ክፋቱ? ተሀድሶስ ስድብነቱ ምኑ ላይ ነዉ? " ላልሽው ወንጌላችን ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ይላል እንጂ ክርስቶስን ለማክበር ከፈለጋችሁ ራሳችሁን ከፍከፍ አድርጉ እሱ ያከበራቸውን ናቁ አንቋሽሹ አይልም፡፡ እናም ቤተክርስቲናችን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ አምላክነቱ ቅዱሳንንም እንደ ተሰጣቸው የቅድስና ክብር መጠን ታከብራዋለች እንጂ እንደ ተሀድሶ ክርስቶስ የመሰረታትን ቤተክርስቲያን አፍርሰን የአውሬው መልእክተኞች እነ ሉተር ባመጡት ፍልስፍና እንተካት፤ ወንጌሏንም መንፈስ ቅዱስ በሚገልጠው እውቀት ሳይሆን ስጋና ደም በገለጠልን ፍልስፍና ለኛም በሚመች አተረጓጎም እናስኪደው አትልም ፡፡ በዶግማዎቿም ምንም ተሀድሶ አያስፈልጋትም፡፡ መጽሐፋችን ዘመኑን ዋጁ እንዳለ ዘመኑን እየዋጀች እስከዛሬ የደረሰችው ቤተክርስቲያናችን መሰረቷ የክርስቶስ ደም ነውና አንቺና መሰሎችሽ የጥፋት ልጆች ሆናችሁ ትጠፋላችሁ እንጂ እሷ ለዘላለም ትኖራለች፡፡ የናንተን አይነት የሞት ተሀድሶ ሳይሆን የልጆቿን ህይወት እያደሰች ዘመናትን ትሻገራለች አትድከሙ፡፡ ለራሳችሁ ግን የእምነትና አመለካከት ተሀድሶ እንደሚያስፈልጋችሁ ልብ በሉ፡፡
  የተሀድሶ ክፋቱና ስድብነቱን ንገሩኝ ካልሽ
  1. በራሱ እምነት ሳይሆን በአውሮፓውያን የፕሮቴስታንት አዝማቾቹ የሚመራ የከሀዲዎችና የቅጥረኞች ስብስብ መሆኑ
  2. ቅዱሳን ሊከበሩ አይገባም፤ምምለድም አይችሉም የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ የኑፋቄ ትምህርት ስለሚያስተምር
  3. ክርስቶስ የመሰረተውን ክህነት እንደማያስፈልግና ሰውሁሉ ካህን እንደሆነ የሚያስተምር መሆኑ
  4. የድንግል ማርምን የአምላክ እናትነት ክዶ፤ዘላለማዊ ድንግልናዋን ክዶ፤በቃና ዘገሊላ ሰርግቤት የተገለጠውን አማላጅነቷን ክዶ የሚያስተምርዬከሀዲዎች ስብስብ በመሆኑ
  5. ከሁሉም በላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስን ከአምላክነት ክብሩ አውርዶ አማለጅ በማለት አምላክ አልባ የሚያደርግና መዳናችንን ሁሉ ፉርሽ የሚደርግ ትምህርት የሚስተምር የአውሬው መልእክተኛ መሆኑና ሌሎችም የተሀድሶን ክፋትና ስድብነት ሊገልጡ ይችላሉ፡፡
  ሌላው ነገር "እነዚህ ሁሉ የፊታችን ሁዳዴ ጾም አጀንዳ ይሁኑልን: ያልሽውን ሀሳብ ካሁኑ አጀንዳሽን ቀይሪ፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን በዓቢይ ጾም ካንቺጋር ልንነታረክ ሳይሆን ከአምላካችን ጋር ልንገናኝበት ነው እየተዘጋጀን ያለነው፡፡ ውስጥሽ ለው ክፉ መንፈስ ለማይረባ ክርክርና ጭቅችቅ ካሁኑ እያዘጋጀሽ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ቤተክርስቲያን ልጅ ብቲሆን ኖሮ በጾሙ ወራት ለአርምሞ፤ ለስግደት፤ ለጸሎትና ለእንባ እንጂ ለጉንች አልፋ ንትርክ እንድንዘጋጅ አትጋብዢንም ነበር፤ ከእኛ ወገን እንዳልሆንሽ ይሄ ራሱ በቂ ማስረጃ ነውና በቤተክርስቲን ጉያ ውስጥ ከተሸሸጉትና ከሚወጉዋት የውስጥ ጡት ነካሽ መናፍቃን ወገንም ከሆንሽ በቶሎ በንስሀ ብልመለሺ ካልሆነም ወደመሰሎችሽ አዳራሽ ብትሄጂ መልካም ነው እልሻለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ME EOTC ሆይ! ይህንን ያህል ያንተከተከህ ምንድርነዉ? ዋሽቼ ከሆነ የዋሸሁበትን በጨዋ ደንብ መግለፅ ነዉ እንጂ "ሰዉ ሁሉ የተፈጠረዉ እምቤታችንን ለማመስገን ነዉ " ብለህ ታምናለህ በማለቴ ይህንን ያህል የስድብ ናዳ ልታወርድ አይገባም፡፡ ከፈለግህ ብዙ አሰቃቂ እምነቶችህን ልደረድርልህ እችላለሁ፡፡ አንተ እንደምትለዉ ፃድቃንና ሰማዕታትን የማላከብር አይደለሁም፡፡ እንከዋን እነሱን አንተንም አከብራለሁ፡፡ እኔ ያልኩት የነሱ ሁሉ ጌታ የሆነዉና እነሱም የተሰዉለት ጌታ ክብር ቅድሚያ ይሰጠዉ፡፡ እሱ ብቻዉን መከበርና መመለክ አለበት እንጂ ደባል መሆን የለበትም ነዉ ያልኩት፡፡ ጉዳዩ ሳየገባህ ቀረቶ ሳይሆን የሃይማኖት ፖሊቲካዉ የምድራዊ ፉክክሩ ብሶብህ ስለሆነ የሁዳዴ ጽሙ እናንተን ሁሉ ቢመለከትልኝ ደስ ይለኛል፡፡ አንተም በፖሊቲካህ ቀጥል፡፡ ለእናት ቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ አያሌ ክርስቲያኖች ስላሉ ስለእናንተና ስለቤተክርስቲያናችን ፀሎታችንን በጾሙ ዉስጥ እንቀጥላለን፡፡ አንተንም የናዝሬቱ ኢየሱስ ያስብህ፡፡አሜን!!

   Delete
 16. Elelelelelelelelelelellelelelleleelel des yilal

  ReplyDelete
  Replies
  1. ME EOTC ሆይ! ይህንን ያህል ያንተከተከህ ምንድርነዉ? ዋሽቼ ከሆነ የዋሸሁበትን በጨዋ ደንብ መግለፅ ነዉ እንጂ "ሰዉ ሁሉ የተፈጠረዉ እምቤታችንን ለማመስገን ነዉ " ብለህ ታምናለህ በማለቴ ይህንን ያህል የስድብ ናዳ ልታወርድ አይገባም፡፡ ከፈለግህ ብዙ አሰቃቂ እምነቶችህን ልደረድርልህ እችላለሁ፡፡ አንተ እንደምትለዉ ፃድቃንና ሰማዕታትን የማላከብር አይደለሁም፡፡ እንከዋን እነሱን አንተንም አከብራለሁ፡፡ እኔ ያልኩት የነሱ ሁሉ ጌታ የሆነዉና እነሱም የተሰዉለት ጌታ ክብር ቅድሚያ ይሰጠዉ፡፡ እሱ ብቻዉን መከበርና መመለክ አለበት እንጂ ደባል መሆን የለበትም ነዉ ያልኩት፡፡ ጉዳዩ ሳየገባህ ቀረቶ ሳይሆን የሃይማኖት ፖሊቲካዉ የምድራዊ ፉክክሩ ብሶብህ ስለሆነ የሁዳዴ ጽሙ እናንተን ሁሉ ቢመለከትልኝ ደስ ይለኛል፡፡ አንተም በፖሊቲካህ ቀጥል፡፡ ለእናት ቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ አያሌ ክርስቲያኖች ስላሉ ስለእናንተና ስለቤተክርስቲያናችን ፀሎታችንን በጾሙ ዉስጥ እንቀጥላለን፡፡ አንተንም የናዝሬቱ ኢየሱስ ያስብህ፡፡አሜን!!

   Delete
 17. ይህ የመናፍቃን ድረገጽ ነው፡፡ በማህበረ ቅዱሳን ላይ የምትዋሹትን አቁሙ ሌቦች ናችሁ፡፡ ለቤተክርስቲያን ጠላቶች ናችሁ፡፡

  ReplyDelete
 18. To Sami Demekt
  please think befor you write.God will help you to open your mind. Pray hard to understand.first of all who is lying?

  ReplyDelete