Tuesday, February 4, 2014

የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን

Read in PDF

ከታላቁ የእስራኤል ነቢይና መስፍን ከሙሴ ቀጥሎ ሕዝበ እስራኤልን የመራውና ወደምድረ ርስት ያስገባው ኢያሱ የተናገረው ይህ ቃል በዚያ ዘመን ለነበሩትና በእግዚአብሔር ላይ የአሕዛብ ጣዖታትን ደርበው ከግብጽ ምድር ባወጣቸው አምላክ ላይ ላመነዘሩት ሕዝበ እስራኤል ያስተላለፈው ወሳኝ መልእክት ዛሬ ላለነውም በእግዚአብሔር ላይ ደብለን ሌሎችን አማልክት የምናመልከውን ይመለከታል፡፡
የኦርቶዶክሳውያን ትልቁ ችግራችን የምናመልከው እግዚአብሔርን ብቻ አለመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔርን እናመልካለን ብንልም ከጥንት ያልነበረና ከጊዜ በኋላ ሕዝቡ እያደረገ ያለውን የተሳሳተ ልምምድ ከማስተካከል ይልቅ በዚያው እንዲገፉበት ለማድረግ የሚታወቁና የማይታወቁ ቅዱሳንን ስም እየለዋወጥን በአክብሮት ስም አምልኮት እየፈጸምን እንገኛለን፡፡ በዘመናችን እንኳን ስንቱን ስም እየለዋወጥን የእግዚአብሔርን ክብር በቅዱሳን ስም ለሰይጣን ሰጠን? ለማስተዋስ ያህል፦

በ1980ዎቹ ኡራኤል ገናና ስም ሆኖ ነበር፡፡ በዚህ ስም የእግዚአብሔርን ክብርና አምልኮት ለእርሱ ሊገባ የሚገባውን መባና ስጦታ የኡራኤልን ስም የተዋሰው መንፈስ ሲወስድ ቆየ፡፡ በዚያ ወቅት አንዳንድ ደብሮች ገቢያቸውን ለማሳደግ ኡራኤልን ደባል አድርገው ነበር፡፡ ወዲያው ደግሞ የቦረዳ ዋሻ ሚካኤል የሚል ስም ብቅ ብሎ ነበር፡፡ ማቅም በሐመር መጽሔቱ ላይ ወሬውን አናፍሶት ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙም አልቆየ እርሱም ለተረኛው ስም ለደብረ ሊባኖሱ ለአባ ሀብተ ማርያም ስፍራውን ለቀቀ፡፡ የአባ ሀብተ ማርያም ስም ግን የሚፈለገውን ያህል ትርፍ ስላላስገኘ ጠላት ሰይጣን ላዘጋጀው ሌላ ስም ቦታውን እንዲተው አደረገ፡፡ በዚሁ መሰረት መጥምቁ ዮሐንስ የሚለውን ስም ጠላት ሊጠቀምበት ፈለገና ሸንኮራ ዮሐንስ በሚለው ስም እንደገና መጣ፡፡ ኡራኤልና የቦረዳው ሚካኤል አባ ሀብተ ማርያም የሚሉት ስሞች ግን ቀስ በቀስ እየተረሱና ዝናቸው እየወረደ ሄደ፡፡

ሰው ሁሉ ተረኛ ወደሆነው ወደሸንኮራ ዮሐንስ ይተም ጀመር፡፡ ትንሽ ትልቁ ሸንኮራ ዮሐንስ ይል ጀመር፡፡ ዮሀንስ መጥምቅ “እርሱ ሊለቅ እኔ ላንስ ይገባል” ያለውን ቃሉን ማን ሰምቶት አያ! አንተ መብለጥ ነው ያለብህ የሚለው የበዛ ነበር የሚመስለው፡፡ በጠበሉ ዳንኩ የሚለው ሁሉ ዮሀንስ ዮሀንስ እንጂ እግዚአብሔርን ጨርሶ ረሳ፡፡ ግን የሸንኮራው ዮሐንስም ነፈሰበትና ዝናውን ለሌላው ተረኛ ስም ለቀቀ፡፡  
ከዚያ በኋላማ በስንቱ የቅዱሳን ስም ጠላት ሰይጣን የእግዚአብሔርን ክብርና አምልኮ ለራሱ ወሰደ፡፡ ክርስቶስ ሰምራ፣ ጻድቃኔ ማርያም፣ ኩክ የለሽ ማርያም፣ አርሴማ የተባሉትን ስሞች ጠላት እያፈራረቀ በመጠቀም በከፍተኛ ደረጃ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር የሚነጥልባቸውና ለእርሱ የሚያሰግድባቸው ስሞች ሆኑ፡፡ አንዳንድ ስሞችን የሰይጣን ፈረስ የሆኑ አንዳንድ ደብተሮች ለማስተዋወቅ ቢሞክሩም ወዲያው “ነቄ” ይባልና ብዙም ሳይርቅ ይከሽፋል፡፡ ለምሳሌ ኮተቤ አካባቢ የተሞከረችው መግደላዊት ማርያም፣ እንዲሁም ታቦቷ ቤት ካልተሰራልኝ አልገባ አለች የተባለችው የቃሊቲዋ ማርያም፣ በቅርቡ በመስቀል ወረደ ስም ድራማ የተሰራበትና ተለባብሶ የታለፈው ደብር ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እነጻድቃኔ ማርያም እነኩክ የለሽ ማርያም ዝናቸው ሙሉ በሙሉ ያልከሰመ ቢሆንም አርሴማ የተባለው ስም ግን ከአናት ጉብ ብሏል፡፡
አርሴማ በአሁኑ ጊዜ ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገር ዝነኛ ስም ሆኖ ወጥቷል፡፡ ሴቱ ወንዱ አርሴማ አርሴማ እያለ ነው፡፡ አርሴማ የሚለው ስም ዝነኛ መሆኑን ተከትሎ ብዙ ደብሮች ገቢያቸውን ለማሳደግ አርሴማን ደባል እያደረጉ ናቸው፡፡ በአንድ ከተማ ያሉ የአንዳንድ አድባራት ካህናትማ እኛጋ ነው መግባት ያለባት በሚል ጠብ ውስጥ እየገቡ ነው፡፡ ለመሆኑ አርሴማ ማናት? ከመቼስ ጀምሮ ነው እንዲህ የታወቀችው? እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ታሪኳም ሆነ ስሟ ታዋቂ አልነበረም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ዝነኛ ሆናለች፡፡ የእርሷም ተራ ደርሶ በሌላው ተረኛ ስም እስክትተካ ድረስ፡፡ 
ግን ለምን? ህዝቡ ለእንዲህ ያለ ሰይጣናዊ አሰራር እስከመቼ ተላልፎ ይሰጣል? የፈጠረውን አምላክ፣ ስለኃጢአቱ የሞተለትንና ነጻ ያወጣውን ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስን ትቶ በቅዱሳን ስም ለሚሰራው ለሰይጣን የሚሰግደውና የሚገዛውስ እስከመቼ ነው? በዚህ ውስጥ የሠይጣንን ሐሣብ በማገልገል ላይ ያሉና የቅዱሳኑን ስም በማስተዋወቅ ስም ቢዝነሳቸውን ያጧጧፉ የጉዞ ማህበራት በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ የሚያሳዝነው ግን በሚፈራረቁ ስሞች ቅዱሳንን ያከበረ መስሎት ከመጣው አዲስ ስም ጋር በፍቅር የሚከንፈው ለነፍሱ ዕረፍት ያጣውና በመንከራተት ላይ የሚገኘው የዋሁ ምእመን ነው፡፡
ኧረ እናስተውል አያ! አሁን በያዝነው መንገድ ቅዱሳንን እያከበርን እኮ አይደለም፡፡ ቅዱሳን በሰሩት መልካም ስራ ከመታወስና ከታሪካቸው ከመማር በቀር በስማቸው አሁን እየተደረገ ያለውን አምልኮ ማድረግ የተከለከለ ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሔር ቅዱሳንም አጥብቀው የሚቃወሙት አምልኮ ባእድ ነው፡፡ ቅዱሳን በዚህ ምድር በነበሩ ጊዜ ራሳቸውን ዝቅ ሲያደርጉና ክብርን ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሰጡ ነው የምናየው፡፡ ካንቀላፉ በኋላ ታዲያ የተዉትን ክብር መልሰው ይወስዳሉ ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል? በፍጹም አይቻልም!!
ጠላት ዲያብሎስ ታዲያ ለምን እንዲህ ያደርጋል? ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ በዲያብሎስነቱ ማንም ስለማይቀበለው በቅዱሳን ስም ቢመጣ ብዙዎችን ማሳት እችላለሁ ብሎ ነው የእመቤታችንን የቅዱሳን መላእክትን የጻድቃንንና የሰማዕታትን ስም እየተዋሰ የሚሠራው፡፡ ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።” ተብሎ በተጻፈው መሰረት የሆነ ነው (2ቆሮ. 11፡12-15)፡፡ 
ወገኔ ሆይ የምታመልከውን ዛሬ ምረጥ! በቅዱሳን ስም ለሚያወናብድህ መንፈስ አትገዛ፡፡ በቅዱሳን ስም የምታደርገውን ሁሉ ቅዱሳን እንደማይቀበሉህ እወቅ፡፡
ሐዋርያው ጴጥሮስ በራእይ በመጣለት መልእክት ምሪት ወደቆርኔሌዎስ በሄደ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ከእግሩ በታች ሰግዶለት ነበር፡፡ ጴጥሮስ ግን ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።” (የሐዋ. 10፡26)፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ሲል የመለሰው ጴጥሮስ ዛሬ ካንቀላፋ በኋላ በስሙ የሚደረገውን አያውቅም እንጂ የሚያውቅበት ዕድል ቢኖር ግን እንዲህ የሚያደርጉትን ለቆርኔሌዎስ ከሰጠው ምላሽ የበለጠ ይናገራቸውና ይገስጻቸው ነበር፡፡
ጳውሎስና በርናባስም በልስጥራን ካደረጉት ድንቅ የተነሣ ሊያመልኳቸው የፈለጉትን ሰዎች “እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።” (የሀዋ. 14፡15) ብለው በመገስጽ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ አስተምረዋቸዋል፡፡ ዛሬ በስማቸው የሚደረገውን ቢያዩ “ይህማ ለቅዱሳን የሚገባ ክብር ነው” ብለው የሚቀበሉ ይመስለን ይሆን? በፍጹም አያደርጉትም፡፡
ሐዋርያው ዮሐንስ ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።” (ራእይ 19፡10)፡፡
“ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።” (ራእይ 22፡8-9)፡፡ ብሏል፡፡ ዛሬ በጌታ መልአክ ስም ተመሳሳይ ድርጊት ብንፈጽም የአክብሮት ስግደት ነውና ችግር የለውም የሚል ይመስለን ይሆን? በፍጹም እንዲህ አያደርግም፡፡ ተቀባዩ ግን የጌታ መልአክ ስላልሆነና በስሙ የሚነግደው ሰይጣን ስለሆነ ይህን ሐቅ እንዳናስተውልና የአክብሮት ነው እንድንል ያደርገናል፡፡ ነገር ግን የጌታ መልአክ ተገልጾልን ይህን ብናደርግማ ለዮሐንስ ከሰጠው ምላሽ የበለጠ እንጂ የተለየ ምላሽ አይሰጠንም፡፡
ወገኖቼ እባካችሁ በቅዱሳን ስም ሰይጣን እያደረገ ያለውን ክፉ ነገር እንንቃበት፡፡ በቅዱሳን ስም እያደረግን ያለውን ሁሉ የሚቀበለው ሰይጣን ሲሆን በዚህ ድርጊታችን ደግሞ እግዚአብሔርን እናስቀናዋለን? እርሱ እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ ብሏል፡፡ በእርሱ ላይ ደርበን በቅዱሳን ስም ሌላውን ስናመልክ ያዝናል? ስለዚህ ቅዱሳንን አከበርናቸው እንጂ መቼ አመለክናቸው በማለት ራሳችንን አናታልል? ከቅዱሳን ሕይወት ክብርንና አምልኮትን ለጌታ ብቻ መስጠትንና ለእርሱ ብቻ ኖሮ ማለፍን እንማር እንጂ እያከበርናቸው ነው በሚል ፈሊጥ በስማቸው የሚነግደውን ሰይጣን ስናመልከው እንዳንገኝ እንጠንቀቅ፡፡ ስለዚህ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን፡፡

35 comments:

 1. seytann yemitamelkew ante rash sathon atkerm. wegegna neh ebakih bileh bileh degimo be egziabher, bkedusan ena beseyitan mekakel yalewn liyunet legna le orthodoxawuyan litastemren yikejelihal. asking neh. yilk lezih tseyaf tegbarh nisiha giba. yegnan legna tewow. atdkem endet endeminitsedik anten kaseletenuh menafikan yilk bejigu enredawalen. seyitan mallet egiziabher yakeberachew kidusan sikeberu yemikena yemibesach, new. gira gebagn ante rash seyitan tihon ende? min yitawokal yih keysi memchaw eko ayitawokim!!! sew kehonk wodelibunah temelsina nisiha giba.

  ReplyDelete
 2. This post seems Ato Begashaw's sibket. The sentence arrangement, the words used etc are topical of him. The bulushit doma go boldly to your sugure dandies and mamis who hire u to destroy our church leave us we know what we are worshiping and have enough likawunts (intelectuals ) to teach us. Dedeb ahiya.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የደንቆሮ ለቅሶ አስመሰልከው አጻጻፍህ ሲያስጠላ

   Delete
 3. this is not your business zim belachu seytanawi kinat yaderebachu chefenoch nachu. min agebachu enante eski yerasachun eweku egna alkebeden mekari ayasfelegenim abatochachin kibir yegbachew ena hulunim neger be agebabu astemerewnal enam atdekemu misemachu yelem misemachu kagegnachu demo yaw yenante aynetun seytan yetewaresewin new enam zimmmmmmmmm belu.

  ReplyDelete
 4. በአብዛኛው በጥቅስ ሳይሆን በሎጂክ(አመክንዮ)ስለመጣህ በእሱው እመጣብሀለሁ!!!ሆኖም ለመላእክት የጸጋ ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት የጠቀስከው ጥቅስ ስላለ እጄ ላይ ካገኘሁዋቸው ጥቅሶች ውስጥ ለመላእክት የጸጋ ስግደት እንደሚገባ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ልጠቁም፡ዘፍ 19 ቁ1፣ዘኁ 22ቁ31፣ኢያ 5 ቁ13፣መሳፍ 13ቁ19፣ዳን 8ቁ 15፣ወዘተ ካስፈለገ ጨምሬ መምጣት እችላለሁ!!!ግን ይሄን ያህል መልስ ለመቆፈር የሚያስገድድ ጽሁፍ ጽፈሀል ብየ ስለማላምን ለጊዜው ጥይት ሳላባክን ሎጅክን በሎጅክ ልበል!!!ጀመርኩ…….
  1. ጸሀፊው ማምለክን ከማክበር ለመለየት እንዴት እንደተሳነው አልገባኝም!!!ቅዱሳንም ሆነ መላእክት በሰሩት በጎ ስራ ፈጣሪያቸውን አስደስተው ነፍሳቸውን ጠቅመዋልና እኛም አሰረ-ፍኖታቸውን(ምሳሌነታቸውን) ተከትለን በምግባር በሃይማኖት ጸንተን እንድንኖር፣ አማልጅነታቸውና ተራዳኢነታቸው እንዳይለየን፣ ጻድቁን በጻድቁ ስም እየተቀበልን መኖራችን፣ወዘተ የመሳሰሉ ፈጣሪን ከፍጡር የለዩ ድርጊቶች እንዴት ተደርጎ የአምላክነትን ስራ እንደሚወስዱ አይገባኝም!!እንዴት የእ/ርን ስም ጠርተን አማልዱን የምንላቸው ቅዱሳን በርኩስ መንፈስ እንደሚመሰሉም ግራ ነው!!!!!እውነት የአብርሃም፣የይስሀቅ፣የያእቆብ አምላክ ተራዳን ማለት ባእድ አምልኮ ነው የሚል መጽሀፍ ካለ አሳዩንና ስህተታችንን እንመን!!
  2. እኛ የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር ህብረት እንዳላቸውና እ/ር ለቅዱሳኑ የገባውን ቃል የሚያጥፍ ዋሾ አምላክ እንዳልሆነ ስለምናምን በተገባላቸው ቃልኪዳን እንዲያማልዱን ስማቸውን እንጠራለን!!!አናፍርም!!ቅ/ሚካኤል ከእ/ር አማልደን ተብሎ የቅ/ሚካኤል ስም ሲጠራ መልስ የሚሰጠው ሰይጣን ነው ብሎ መናገር ድፍረት ነው!!ክህደት ነው!!የሚካኤልን ተውት የእ/ር ስም ሲጠራ መልስ የሚሰጥ ሰይጣን አለ ማለት ሰይጣንን ማጀገን ነው!!!እኛ የምናመልከው እ/ር ስሙ ሲጠራ ሰይጣናት የሚንቀጠቀጡለት ነው!!!ሚካኤልም ረድኤተ እ/ርን አጋዥ አድርጎ በውጊያም በክርክርም ያሸነፈው ስለሆነ ሰይጣን ይንቀጠቀጥለታል!!!
  3. እናንተ ትክክል ናችሁ ብለን ብንነሳ እንኩዋ “የክብሩ ተጠሪዎች”(ቅዱሳን ነን ለማለት ይመስለኛል) የሚለው የእናንተ አዳራሽ ከእኛ በቅዱሳን ስም የተሰሙ አብያተክርስቲያናት በምን እንደሚበልጥ፣ “የህያዋን ሰራዊቶች” ከሚለው ጸያፍ ዘይቤን ከሚጠቀም አዳራሻችሁ የእኛ በሰራዊተ- መላእክት አለቆች በነቅ/ሚካኤልና ገብርኤል ስም የተሰየመ ቤ/ክ በምን እንደሚለይ፣ “የተዋጀች የእ/ር ቤ/ክ” ከሚለው ስያሜያችሁ የእኛ መድሀኔዓለም ቤ/ክ የሚለው ቃል ምን እንደሚጎለው፣ “ኮንፈረንስ” ከሚለው ባእድ ቁዋንቁዋ ‘ንግስ’ የሚለው ሀገርኛ ሃይማኖታዊ አገላለጽ በምን መልኩ እምደሚያንስ ብታስረዱን ጥሩ ነው!!
  4. ጸሀፊውም በቅዱሳኑ እና በመላእክት ስም የሚጠሩት አብያተክርስቲያናት አይመቹኝም ካልክ ዘለህ የነቀፋ ቃል ከመናገርህ በፊት በኢየሱስ፣በአማኑኤል፣በመድሃኒዓለም፣በስላሴ ስም ወደሚጠሩት ኦርቶዶክሳዊ አብያተክርስቲያናት መሄድ እንደሚገባ ብትናገር ትንሽ ልቤን ታራራው ነበር!!!ነገር ግን ያንተ ድርሻ የመሰለህ ማጥላላት ብቻ ነው መሰለኝ የት መሄድ እንደሌለብን እንጅ የት መሄድ እንዳለብን አትናገርም!!እስኪ እባክህ የአርሴማ ይቅር 6ኪሎ አካባቢ የሚገኘው ኢየሱስ ቤ/ክ ለመሄድ ሞክር!!ያለበለዚያ በ2 እግር አታንክስብን!!አንዱን እርገጥ!!ቆንጻይ አትሁን!!!ቁንጽልነት ለሃሜት እንጅ ለእውቀት አይረዳም!!
  5. ስለ አርሴማ ለመናገር ያህል ዘመነ ሰማእታት ተብሎ በሚታወቀው ዘመን ማለትም ንጉስ ቆንጠስጢኖስ ከመነሳቱ በፊት በዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መስክራ ሰማእትነት የተቀበለች የአርመኒያ ሰማእት ነች!!ታዲያ የኢየሱስ ነን እያሉ የሚመጻደቁ ሰዎች ስለኢየሱስ አምላክነት መስክራ ሰማእትነት የተቀበለችው ክርስቲያን የምስክርነት ገድል መነገር የክርስቶስን አምላክነት እንደመካድ አድርገው መረዳታቸው ያስገርመኛል!!!የማላላ እና የማንዴላ ቀን በሚከበርበት ዓለም የአንዲት ሰማእት ገድል ቀን ተቆርጦለት መነገር የሚያመው ክርስቶሳዊ ነኝ ባይ ሰው ሲያጋጥም ወይ ግሩም ከማለት ውጭ ምን ይባላል!!ለዚያውም ጣሊያን የገደላቸው “ሰማእታት” በየአመቱ የካቲት 12 ቀን እንደብሄራዊ ቀን ታውጆ በሚከበርባት ሀገር!!
  6. ልመለስወደጉዳያችን-በአርሴማም ሆነ በሚካኤል ቤ/ክ መስዋእቱ አንድ ነው!!!ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ!!!ቅዳሴውና ቁርባኑም ማእከል የሚያደርገው ክርስቶስን ነው!!ስለቅዱሳኑ የሚደረግ ነገር ቢኖር በቅዳሴ መሀል የሚነበቡ የመጽሀፍ ቅዱስ ምንባቦች ከእለቱ ታሪክ ጋር የሚጣጣሙ እንዲሆን ይደረጋል!!!ከቅዳሴው ውጭ ባለው መርሀግብር በእለቱ የሚታሰበው ጻድቅ ገድልም ሆነ ድርሳን ተነቦ ከመልአኩ/ከጻድቁ/ከሰማእቱ ረድኤት በረከት ያካፍለን ይባልና እለቱን በሚመለከተው የስብከት መርሀግብር ይቁዋጫል!!!በዚህም በእለቱ ከተደረሰው ቃለ እ/ር ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ ለእ/ር የሚደረስ ነው ማለት ነው!!!ማህሌቱም ቢሆን ከዚህ የተለየ አይደለም!!ይሄን ሁሉ ስናደርግ አምላካችንን እ/ር፣ ቅዱሳኑን ከአምላካቸው እ/ር የሚያማልዱ የተቀደሱ ፍጡራን እንደሆኑ በማመን ስለሆነ አልተሳሳትንም!!ለሁሉም የሚገባውን ለይተን ነው የሰጠነው!!!ክብር ለሚገባው ክብር-አምልኮ ለሚገባው አምልኮ!!ኑ!!እዩና እመኑ!!!
  አዎ አልተሳሳትንም!!የምናመልከውን መርጠናል!!!የምናመልከው ቅዱሳን አባቶቻችን የሚያመልኩትን ነው!!ስሙም እግዚአብሄር-የአብርሃም፣የይስሀቅ፣የያዕቆብ አምላክ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. I visit this site to read the response of Hiruy! which is very clear and Biblical.God Bless you!

   Delete
  2. ውድ ህሩይ! ጥሩ የሚመስሉ መረጃዎች ያለህ ትመስላለህ፤ነገር ግን ማነው ያ “ፕሮቴስታንታዊ ጅሃድ በኦርቶዶክስ ላይ ሲፋፋም…” የሚለውን ዘባራቂ አስታወስከኝ፡፡ ለምን በለኝማ፡፡ ሲጀመር ሙታን በዚህ ምድር ላይ ምንም ዕድል ፈንታ የላቸውም፤እንኳን ሊያማልዱን! ያንተ ችግር መሠረቱ ነው፤መሠረቱ የተመሰረተው በዓለቱ (እውነት) ላይ አይደለም እውነት ለመናገር! በ”ተረት” ላይ ነው፤እንደነ “ተአምረ ማርያም ያሉ ተረቶች”፡፡ይህንን ደግሞ በተደጋጋሚ በዚህ ብሎግ ላይ ያነሳነው ነው፡፡

   Delete
  3. Question for Hiruy - why do we need the intercession of the saints, don't we all just need the blood of our lord and savior Jesus Christ to be saved including saints? Why do you always want us to be dependent on other saints when we all have one saviour?

   Delete
  4. የቅዱሳን አማላጅነት እና የኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ልዩነት!!

   አንዳንድ ወንድሞች ነገረ ቅዱሳንን ከነገረ ክርስቶስ ጋር ይቀላቀልባቸዋል፡፡ከሚያነሱዋቸው ሐሳቦች አንዱና ዋነኛውም “ጻድቃን፣ ሰማዕታት እና ቅዱሳን መላእክት ብቃት ያላቸው አማላጆች አይደሉም፤ ይልቁንም ብቃት ያለው አማላጅ (ጠበቃ) ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው” የሚል ይገኝበታል፡፡ነገር ግን ወንድሞቼ የክርስቶስ መካከለኛነትና የቅዱሳን አማላጅነት ልዩነቱ የገባቸው አይመስልም፡፡
   ቤተክርስቲያናችን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በመላእክትና በቅዱሳን አማላጅነት ታምናለች፣ ታስተምራለችም፡፡ ይኼንን ትምህርት የማያምኑ ወንድሞቻችን ግን ለ“ትምህርታቸው” እንደ ማስረጃ ከሚያቀርቡዋቸው ጥቅሶች መካከል “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፣ እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /1ዮሐ.2፡1/” እና “በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም ሰው የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /1ጢሞ.2፡5/” የሚሉ ይገኙበታል፡፡
   ቤተክርስቲያናችን በእነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦች ላይ ያላት እምነት የሚከተለውን ነው፡፡

   1. የኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃነትና የቅዱሳን ጠበቃነት ፈጽመው የማይገናኙ ነገሮች ናቸው፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃችን ነው” ስንል አስታራቂነቱን ፣ ቤዛነቱን መናገራችን ነው፡፡ይህም ማለት እያንዳንዳችን በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ገዛ መንገዳችን ስናዘነብል ጌታ የሁላችንን በደል በመሸከም ዕዳችንን ከፍሎ ከአባቱ ጋር ጠበቃ በመሆን አስታርቆናል /ኢሳ.53፡6/፡፡ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ብቸኛው መካከለኛ (ወልድ ዋሕድ) ነው፡፡አባቱን ያረካ ብቸኛው መሥዋዕት በመሆንም ለምናምን ለኛ በእኛ ፈንታ በመሞት ጠበቃ ሆነልን፡፡ስለዚህ “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን”፡፡ምክንያቱም ከየትኛውም ዐይነት ኃጢአት መንጻት የምንችለው በጻድቁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነውና፡፡

   የቅዱሳን አማላጅነት ግን ኃጢአትን ከማንጻት እና ከቤዛነት ጋር ፈጽሞ የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡እነሱ መካከለኛም አይደሉም ፤ ሊሆኑም አይችሉም፡፡እነሱ መካከለኛ መሆን ቢችሉ ኖሮ በእነ ይስሐቅ፣ በእነ ኢሳይያስ ፣ በእነ ድንግል ማርያም አማካኝነት በዳንን ነበር፡፡ የእነሱ አማላጅነት በእኛ ፈንታ በክርስቶስ ፊት የሚያቀርቡት ጸሎት ብቻ ነው፡፡ምናልባት ከእናንተ መካከል “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው /ሮሜ.8፡34 እና ዕብ.7፡25/ ተብሎ በደማቅ ቀለም ተጽፎአል” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡እውነት ነው!! ነገር ግን ይህንን ሐሳብ ለመረዳት መጀመርያ የኢየሱስ ክርሰቶስ ሊቀካህንነትን ማወቅ ይጠይቃል፡፡

   የብሉይ ኪዳኑ ሊቀካህን በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት በመግባት ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፡፡ይህም ማለት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ሰዓት ስለ ሕዝቡም ይማልድ ነበር፡፡የሐዲስ ኪዳኑ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፡፡ስለዚህ “ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል” ሲባል ዛሬውኑ ተሰቅሎ ያድናል ማለት እንዳልሆነ ሁሉ “ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳል” ሲባልም በመስቀል ላይ ሆኖ “ጌታ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ያለው ቃል ዛሬ ለእኛም ይሠራል ማለት ነው እንጂ አሁንም ይማልዳል ማለት አይደለም፡፡ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “ሊቀ ካህናት ሲል ብትሰማው ዘወትር የሚያገለግል አይምሰልህ፤ ራሱን አንድ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋ …(ጳውሎስ) ሁል ጊዜ ቆሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ … ራሱን አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡አንድ ጊዜ ሰው እንደሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፤ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ባገለገለም ጊዜ በማገልገል ሥራ ጸንቶ አልኖረም /የዕብራውያን መልእክት ትርጓሜ ድርሳን 13፡184-190/” ብሎአል፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሁል ጊዜ ይለምናል” ብሎ ማሰብ ክብር ይግባውና ጌታን ደካማ ማድረግ ነው፡፡ምክንያቱም እንደኛ ኃይል የሌለው ነው ሁል ጊዜ የሚለምነው፡፡ አንድም ባለማወቅ ሁል ጊዜ እሱን መስቀል ነው፡፡

   2. የቅዱሳን አማላጅነት ከኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ፍጹም የተለየና ጸሎት ብቻ እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ይህን ዐይነቱ ጸሎት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ የሚደግፈው ጸሎት ነው፡፡ “እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ /ያዕ.5፡16/” እንዲል፡፡ ቅዱሳን ራሳቸው “ስለኛ ጸለዩ /1ተሰ.3፡1፣ ዕብ.13፡18 ኤፌ.6፡18/” ብለዋል፡፡ታድያ እነሱ እንኳን የእኛ ጸሎት እየፈለጉ እኛ የእነሱን አንፈልግም እንበልን? እንደኛ ተጋድሎአቸውን ያልጨረሱ ወንድሞቻችንን እንኳን እንዲጸልዩልን እየጠየቅን “ከመውጣቴም (ከመሞቴም) በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ /2ጴጥ.1፡15/” ያሉንንና በገነት ከክርስቶስ ጋራ ያሉትን ቅዱሳን እንዲጸልዩልን መጠየቅ አይገባንምን? ከምድር ወደ ገነት ከሄዱ በኋላስ ይህን ባለሟልነታቸው አጥተውታልን? ወይስ “የእነሱን ጸሎት መጠየቅ የሚቻለው ወደ ክርስቶስ እቅፍ ከሄዱ በኋላ ሳይሆን በዚህ ምድር ሳሉ ብቻ ነው” ተብሎ ተነግሮናል? ሰዎች እንዲጸልዩልን ከጠየቅንስ መላእክትን መጠየቅ አይገባምን?

   3. እግዚአብሔር ፃድቅ የሆኑ ሰዎች ስለ ሌሎች ይማልዱ ዘንድ ጠይቆአል፤ እንደሚችሉ አረጋግጦኣል፤ ይህ እዲደረግም ፈቅዶአል፡፡ለምሳሌ፡ አብርሃም ስለ አቤሜሌክ፣ ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ፣ አብርሃም ስለ ሰዶም ሰዎች፣ ሙሴ ስለ ሕዝበ እስራኤል ያቀረቡት ምልጃ ይጠቀሳል፡፡እነዚህ በምደር ሳሉ ያቀረቡት ምልጃ ሲሆን ወደ ገነት ከሄዱ በኋላ ያቀረቡ ደግሞ ዳዊት ስለ ሰሎሞን /1ነገ.11፡12-13፣31-34፣ መዝ.132፡10/፣ ጴጥሮስ ስለ ምእመናን /2ጴጥ.1፡15/፣ ሰማዕታት መከራ ስለሚደርስባቸው ምእመናን /ራዕ.6፡10/…ይገኙበታል፡፡
   ጸሎት ብቻ የሆነው የቅዱሳን አማላጅነት እንደ ጥብቅና ከተቆጠረ እና ምንም ተቀባይነት የሌለው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው ስለሌላው የሚጸልየው ጸሎትም አላስፈላጊ ጥብቅና ነው፡፡
   ይህ ግን ፈጽሞ የተሳሳተ አካሄድ እና እንግዳ ትምህርት ነው፡፡እግዚአብሔር እያንዳንዱ አማኝ (ከዚህ ምድር የተለየውም ያልተለየውም) ስለሌላው እንዲጸልይ የፈቀደው አንዱ ለሌላው ያለውን ፍቅር የሚገልጽበት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ በዚህ ምድር ያለንና በገነት ያሉት የክርስቶስ ብልቶች በጸሎት ድልድይ እንገናኛለን፡፡
   ስለዚህ የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለችና፤
   የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ እግዚአብሔር ይህን ዐይነት ጸሎት ፈቅዶአልና፤
   በቅዱሳን አማላጅነት እናምናለን፣ የሚመጣውን ሕይወት እናምናለንና፤ እነሱም ሕያዋን ናቸውና፤
   በቅዱሳን አማላጅነት እናምናለን፣ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንድነት እናምናለንና፤ ሁላችንም (ከዚህ ምድር የተለዩትም ያልተለየንም) የአንድ ክርስቶስ ብልቶች እንደሆንን እናምናለንና!!!!

   Delete
  5. @Anonymous February 7, 2014 at 7:18 AM Egziabhar yebarkot, betam telek timihirt new lastewalew sew. Egnam orthodoxawiyan yehinin tenkiken yawekn aymeslegnim

   Delete
  6. እንደ ሌሎቹ በጭፍን ከመሳደብና የጥላቻ መልስ ከመስጠት ይልቅ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም ሎጂካዊ መልስ ለመስጠት ስለሞከርክ አደንቅሃለሁ። ለምሳሌ"የቅዱሳንን ምልጃ እንጠይቃለን፣ እግዚአብሔር ይህን ዐይነት ጸሎት ፈቅዶአልና" ካልክ በኋላ የመፅሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ወይም ጥቅስ ለመስጠት አልቻልክም፤ ሙታን ስለ እኛ/ሕያዋን እንድፀልዩ እግዚአብሔር አላዘዘምና። በደብተራዎች ተፅፈው በየቤተክርስቲያኑና በየመንገዱ የሚሸቃቀጡትን መጽሐፎች ሳይሆን ዋናውን መፅሐፍ ቅዱስ በተለይም አዲስ ኪዳንን ደጋግመህ ቢታነብ ሚስጢሩ የሚገባህ ይመስላልና በርታ! እግዚአብሔር መንፈሳዊ ዓይኖችህን ይክፈትልህ

   Delete
 5. Indeed! bless you!!May God open the eyes of the people who are under the judgement as they are giving their back to Jesus and worship Satan's agent used those names as a cover!!!Satan is a deceiver!!!Jesus is life and only way!!!

  ReplyDelete
 6. i love it the ethiopian orthodox church is out of apostles teaching . The church is exit another way.

  ReplyDelete
 7. God bless you my brother.

  ReplyDelete
 8. good. this is interesting and biblical. be blessed

  ReplyDelete
 9. same, same boring 'nufake' by protestant menafkan. we know what we worship and we know what we respect. it is you that becomes very much confusednot we orthodoxies.you will live protesting the whole life while giving the proper respect to saints and the proper worship to our lord, god Jesus Christ. the bible says ' egziabeher bekidusanu endetegelete atawukumn????????' and 'ye tsadikanmetasebya lezelalem yinoral'. knowing this bibilical words, we keep on respecting.YOU PROTESTANTS ARE AGAINST THE BIBLE THAT IS FACT AND WE DO NOT LISTEN YOU.

  ReplyDelete
 10. መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ!!

  ReplyDelete
 11. Yes! This is DEMONIC! Everyone should be aware of this DEVILISH act and come back to the RIGHT way of the BIBLE! Indeed, today most of the Ethiopian Orthodox church members started to read the bile, that's why so many movements are raising and this is God's hand! I wish the people pray for the church to restore that right way back to the church and avoid this PUZZLE that makes us far apart from seeing God!

  ReplyDelete
 12. this is 100% correct

  ReplyDelete
 13. Bertu Geta yibarkachu Agelgilot malet sile kiristos bertito mastemar new yezihi zemen zera yaiqoboch begeta aserarachew eye temeta new bertu betselot tenkiru egziabher agelgilotachun yibarkew

  ReplyDelete
 14. Did People Really listen? this is a word of God. it should be respected and accepted. please please leave with it.

  ReplyDelete
 15. We don't worship the saints, we respect them and we believe in their intercession since they have been loyal till death to GOD and GOD want their name to be raises high. That is why miracles in their name happen!

  The work of the demons is clear! What is the difference between pente spirit and zare sprit!

  ReplyDelete
 16. ከሎጂክ ወደ ጥቅስ ልምጣና ይህን ልበል…….ጥቅስን በጥቅስ……
  1. የእስራኤል መስፍን የሆነው ኢያሱ፡ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እ/ርን እናመልካለን” የሚለውን ጥቅስ ተውሰህ ለመላእክት የሚደረግ ስግደት የአምልኮ ያህል እንደሚቆጠር አትተሀል!!!ምንያረጋል ኢያሱ ራሱ ካንተ ጋር አልቆመም!!!መጽ.ኢያሱ 5ቁ13 እንዲህ ይመሰክርብሀል “……እርሱም አይደለሁም እኔ የእ/ር ሠራዊት አለቃ ሆኘ አሁን መጥቻለሁ አለ. ኢያሱም ‘ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና’ ጌታየ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው አለው. የእ/ር ሰራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ አለው” የምታመልኩትን ምረጡ ያለው ኢያሱ ለመልአኩ በስህተት ሰገደ ብለን አናምንም!!!ለመልአኩ በግንባሩ መደፋቱም መልአኩን ለማክበር እንጅ ለማምለክ እንዳልሆነ እናውቃለን!!!ዛሬም ኢያሱን ተከትለን እንዲሁ ስናደርግ አምላክ ከመልአክ ለይተን ነው!!!የአንዱን ላንዱ ሳንሰጥ፣ሳንቀላቅል!!
  2. ወንጌላዊው ዮሐንስ፡በራእይ 19ቁ10 እና 22ቁ8 ….በመልአኩ እግር ፊት ሰገድኩለት እሱ ግን አትስገድልኝ፣ ሁለታችንም የእ/ር ባሪያዎች ነን አለኝ….የሚለውን ጥሬ ንባብ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት አቅርበኸዋል!!!ተሳስተሀል!!(ሀ)ወንጌሉን፣መልእክታቱን፣ራእዩን የጻፈው ዮሐንስ ለመልአኩ የሰገደው ባለማወቅ ነው ማለት ይሄን ሁሉ የጻፈውን ዮሐንስ ለማን መስገድ እንዳለበት እንኩዋ የማያውቅ አዲስ ምእመን ማስመሰል ነው!!!ዮሐንስ የሰገደው መስገድ ስለሚገባው ነው!!!(ለ)መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ስግደት የበላይና የበታች መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ዮሐንስ በክብር እንደበለጠው አውቆ ነው!!!ለትህትና!!!(ሐ)መልአኩ በምእራፍ 19 ቁ 10 እንደተገለጸው ዮሐንስን አትስገድልኝ ቢለውም ዮሐንስ ግን በምእራፍ 22 ቁ 8’ም ዳግመኛ ለመልአኩ ሲሰግድ እናገኘዋለን!!ዮሐንስን ያህል የጌታ ወዳጅ(ፍቁረ-እግዚእ) ተብሎ የተነገረለትና በጰራቅሊጦስ መንፈስቅዱስ የወረደበት አባት ለመልአክ መስገድ ስህተት መሆኑ ጠፍቶ፣ እየተነገረው ጭምር ከአንዴም ሁለቴ ሰገደ ማለት ቅድስናውን መጠራጠር ይሆናል!!!ስለሆነም መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ለትህትና ነው ስንል እናምናለን!!!
  3. የሞቱ ቅዱሳን ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም የምትሉ ሰዎች አላችሁ!!!እሺ ቅዱሳኑስ ይሁኑ ታዲያ መላእክት እኮ አይሞቱም!!!ስለታናናሾች የአብን ፊት ያያሉ እንጅ-በማቴ 18ቁ 10 እንደተጻፈው!በዘካርያስ 1 ቁ 13 የመልአኩ ምልጃ እንዲህ ተጽፉዋል “አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ 70 አመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተማዎች የማትምራቸው እስከመቼ ነው አለው.እ/ርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው” ታዲያ ሳንለምነው እንዲህ የሚማልድልን መልአክ ብንለምነውማ ምን ያህል ይማልድልን!!ሰአሉ ለነ ሚካኤል ወገብርኤል እንበላቸውማ!!!
  4.የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር በመንፈስ እንደሚገናኙ ደግሞ ይሄው!!!የሞቱ ቅዱሳን “እ/ር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነሱ እንደማያፍር” በዕብ 11 ቁ 16 ተጽፉዋል!!!የሞቱ ቅዱሳን አላዋቂዎች ሳይሆኑ ወደፍጹምነት የተሸጋገሩ ‘ፍጹማን’ መሆናቸው በዕብ 12 ቁ 22 ሰፍሮልናል!!!ጌታም ከአመታት በፊት በሞት የተለዩትን አብርሃምን፣ይስሀቅንና ያዕቆብን ጠቅሶ “የህያዋን አምላክ ነኝ” ሲል በማቴ 22 ቁ 32 ገልጹዋል!!!ጌታችን በስጋ ስለሞተው አብርሃም በዮሀንስ 8 ቁ 56 ሲናገር፡ “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴትን አደረገ፤አየም ደስ አለው” ይላል!!!በአጸደ ነፍስ ያለው አብርሃም የጌታን ቀን አይቶ የተደሰተው በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር ካለነው ጋር ህብረት ስላላቸው ነው!! ዮሐንስ በራዕዩ ምዕራፍ 8 ቁ 3 “የዕጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእ/ር ፊት ወጣ” ይለናል!!መላእክት ጸሎታችንን ያሳርጋሉ!!!አእርጉ ጸሎተነ የምንላቸውም ለዚሁ ነው-እንደ ቅ/ያሬድ-እንደ አባ ጎዮርጊስ ዘጋስጫ!!ሙሴስ በዘጸአት 32 ቁ 13 “በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ይስሀቅንና እስራኤልን አስብ” ብሎ በአጸደነፍስ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ስም ጌታውን ሲማጸን ከሞቱ ቅዱሳን ህብረት ስላለን አይደለምን!!!ነው እንጅ!!!
  5. ይሄን ሁሉ ስንል ባለቤቱን ረስተን አይደለም!!!በቀጥታም እሱን ማረን እንለዋለን-እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በምህላ-መሀረነ አብ በማስታኮት!!!ስማን፣ተማለደን፣ታረቀን እንለዋለን!!!ግን እንደሌሎቹ አማልደን አንለውም!!!ሌሎቹ የሚያማልደን ጌታ ነው እያሉ ቤዛነቱን እንደአማላጅነት ስለሚወስዱት ነው እኛ ቅዱሳንን አማልዱን ስንል አምላክ ያደረግናቸው የሚመስላቸው!!! አምላካችን አንድ ነው!!!የሃይማኖታችን መሰረትም እሱ-ለዚህም ነው ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን ስንል የሃይማኖት ጸሎታችንን የምንጀምረው!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Hiruy ሂሩዪ፥ እባክሕን ሁልጊዜ በመከታተል እነዚህን ከሀዲዎች አስታግስልን። እኛንም እንዲህ አስተምረን። እኔ ሁልጊዜ የቤክ ውድከት የሚመኙ ሰዎች ምን እያከዱላት እንደሆነ ለማዎቅ እና እንዳንተ እይነት ወንድሞች የምጸቱትን መልስ ለማንበብ ነው ይህን የመናፍክ ብሎግ የምጎበኝው። እግዚአብኄር ጸጋውን ያብዛልህ።

   Delete
 17. እግዚአብሔር አብርሃምን፦ «ከአገርህ፥ ከዘመዶችህ፥ ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።» ካለው በኋላ ተስፋውን ነግሮታል። ከተስፋውም መካካል «ስምህንም አከብረዋለሁ፤የሚል ይገኛል። ዘፍ ፲፪፥፪። ይህ ልዑለ ባህርይ እግዚአብሔር የሚያከብረው የሚያሰከብረው ስም በእውነት የተባረከና የተቀደሰ ነው።

  ፬፥፬ እግዚአብሔር በክብር የጠራው ነው፤

  የነቢያት አለቃ ሙሴ የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር። ሙሴ ቅዱስ ጳውሎስ እንደመሰከረለት፦ የንጉሥ የልጅ ልጅ መባልን በእምነት እንቢ ያለ፥ ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን የመረጠ፥ የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት ከግብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት አንደሚሆን ያወቀ፥ዋጋውን አሻግሮ የተመለከተ፥ የንጉሡን ቁጣ ሳይፈራ የግብፅን ሀገር በእምነት የተወ፥ ከሚያየው ይልቅ የማይታየውን ሊፈራ የወደደ ሰው ነው። ዕብ ፲፩፥

  ሙሴ በጎቹን ወደ ምድረ በዳ ነዳ፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ ወጣ። እግዚአብሔርም የደብረ ሲናን ሐመልማል ተዋህዶ በእሳት ነበልባል አምሳል ተገለጠለት። ሐመልማል የእመቤታችን፥ ነደ እሳት የመለኰት ምሳሌዎች ናቸው። ሙሴ ነበልባልና ሐመልማል ሳይጠፋፉ ተዋህደው ባየ ጊዜ ተደነቀ። «ቊጥቋጦው ስለምን አልተቃጠለም?ልሂድና ይህን ታላቅ ራእይ ልይ፤» አለ። እግዚአብሔርም እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደመጣ ባየ ጊዜ፦ «ሙሴ፥ ሙሴ ሆይ፥» ብሎ ጠራው ዘጸ ፫፥፩-፬። «ሆይ» የሚለው ቃል ቃለ አክብሮ ነው። ለፍፃሜው ሐመልማለ ሲና በምትባል በእመቤታችን አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ በመወለድ ሐዋርያትን፣ ሰብዓ አርድዕትን እና ቅዱሳት አንስትን ለሰማያዊ ግብር እንደሚጠራቸው ያመለክታል።

  እግዚአብሔር ነቢዩ ሳሙኤልንም በክብር ጠርቶታል። የስእለት ልጅ ነበር፤ ጡት ከጣለበት ጊዜ ጀምሮ ያደገው በእግዚአብሔር ቤት በእግዚአብሔር ፊት ነው። ያ ዘመን የእግዚአብሔር ድምፅ ከአገልጋዮችም ከተገልጋዮችም የራቀበት ዘመን ነበር፤ ሳሙኤል ግን ገና ብላቴና ሳለ የበፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር። እናቱም ትንሽ መደረቢያ ሠራችለት፤ በየዓመቱም መሥዋዕት ለመሠዋት ከባልዋ ጋር ስትወጣ ትወስድለት ነበር። ሊቀ ካህናቱ ዔሊም መክነው ያገኙትን ልጃቸውን በእምነት ለእግዚአብሔር በመስጠታቸው «በምትክ ዘር ይስጣችሁ፤» ብሎ ባረካቸው። እግዚአብሔርም በምትኩ ሦስት ወንዶች እና ሁለት ሴቶችን ሰጣቸው። ብላቴናው ሳሙኤልም በእግዚአብሔር ፊት አደገ ፪ኛ ሳሙ ፪፥፲፭-፳፮።

  የእግዚአብሔር መብራት ገና ሳይጠፋ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ነበር። በዚህን ጊዜ ነው፥ እግዚአብሔር በታቦቱ አድሮ «ሳሙኤል፥ ሳሙኤል ሆይ፥» እያለ በአንድ ሌሊት አራት ጊዜ መላልሶ የጠራው። እርሱ ግን እግዚአብሔርን ገና በድምፅ ስላላወቀው ፥ ሊቀ ካህናቱ ዔሊ የጠራው መስሎት፦ «እነሆ፥ የጠራኸኝ፤» እያለ ተመላልሶ ነበር። ዔሊም እግዚአብሔር ብላቴናውን በክብር እንደጠራው አስተውሎ፦ «ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠራህም፦ አቤቱ ባሪያህ ይሰማል ተናገር በለው።» ሲል መከረው። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በእስራኤል ሊያደርገው ያሰበውን ምሥጢር ሁሉ ለብላቴናው ነግሮታል። ሳሙኤልም እሰኪነጋ ተኛ፥ማልዶም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት ደጅ ከፈተ። ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ። ዔሊ ግን «ልጄ ሳሙኤል ሆይ፥» በማለት ስሙን በክብር ከጠራ በኋላ «እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? ከእኔ አትሸሽግ፤» አለው። በእግዚአብሔርም ስም አማጸነው። ሳሙኤልም አንዳችም ሳይሸሽግ ነገሩን ሁሉ ነገረው። በዚህን ጊዜ ዔሊ «እርሱ እግዚአብሔር ነው፥የወደደውን ደስ ያሰኘውን ያድርግ፤» አለ። ፩ኛ ሳሙ ፫፥፩-፲፰።

  ነቢዩ ኤርምያስም፦ «ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል፦ ኤርምያስ ሆይ! ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም የሎሚ በትር እያለሁ፥ አልሁ። እግዚአብሔርም፥ የተናገርሁትን እፈጽመው ዘንድ እተጋለሁና መልካም አይተሃል አለኝ፤» ብሏል። የሎሚ በትር የተባለች እመቤታችን ናት። ሎሚ መዓዛ አለው ፥ ይህም ለመዓዛ ድንግልናዋ ምሳሌ ነው። ኤር ፩፥፲፩። እግዚአብሔር ነቢዩ ሕዝቅኤልንም ለነቢይነት በጠራው ጊዜ፦ «የሰው ልጅ ሆይ! በእግርህ ቁም እኔም እናገራለሁ፤ --- የስው ልጅ ሆይ እኔን ወደ አስመረሩኝ ወደ እስራኤል ቤት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ዐመፁብኝ። እነርሱ ፊታቸው የከፋ፥ ልባቸው የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው። --- አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኲርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤--- ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና። --- አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የምነግርህን ሰማ፤ ---- አፍህን ክፈት፥ የምሰጥህንም ብላ። ---- የሰው ልጅ ሆይ! ያገኘኸውን ብላ፤ ይህን መጽሐፍ ብላ፤ ሄደህም ለእስራኤል ልጆች ተናገር። ---- የሰው ልጅ ሆይ! አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ። --- የሰው ልጅ ሆይ!ተነሥተህ ወደ እስራኤል ቤት ሂድና ግባ፥ ቃሌንም ንገራቸው።» ብሎታል። ሕዝ ፪፥፩-፲ ፤ ፫፥፩-፬፤ እርሱም፦ «እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ፤» ብሏል። እግዚአብሔር ነቢዩ ሕዝቅኤልን እስከ መጨረሻው ድረስ ያነጋገረው «የሰው ልጅ ሆይ! » እያለ ነው። ይኸውም በመጨረሻው ዘመን (ዓመተ ዓለም፥ ዓመተ ፍዳ፥ ዓመተ ኲነኔ ሲፈጸም) በተዋህዶ ሰው ሆኖ እንደሚወለድ ሲገልጥለት ነው።

  ፬፥፭፦ ቅዱሳን መላእክት በክብር የጠሩት ነው፤
  Post a Comment

  ReplyDelete
 18. ነገረ መላእክት ክፍል አንድ
  የተከበራችሁ አንባብያን ባለፈው ዝግጅታችን ቅዱሳን ?ተፈጥሮአቸውን፤አማላጅነታቸውን፤ጸጋቸውን ፤ክብራቸውን ፤በአጠቃላይ በቅዱሳን መላእከት ዙሪያ ቅድሰት ቤተክርስቲያን ያላትን አስተምሮ እና

  መናፍቃን ስለቅዱሳን መላእክት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ለመዳሰስ እንሞክራለን ብለን በገባነው ቃል መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ይዘን እንቀርባለን አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ያድለን በስነፍጥረት ትምህርት ከ22 ነገደ ፍጥረታት መካከል አንዱ ነገድ የመላእክት ነገድ ነው (1) ።
  እነዚህም በቅድሰትቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት መላእክት ቅዱሳን ይባላሉ ለመሆኑ ቅዱሳን መላእእክት ለምን ቅዱስ ተባሉ ? መላእክት ማለት ምንማለት ነው?ተፈጥሮአቸውን፤ አማላጅነታቸውን፤ ጸጋቸውን ፤ክብራቸውን ፤በአጠቃላይ በቅዱሳን መላእከት ዙሪያ ቅድሰት ቤተክርስቲያን ያላትን አስተምሮ እና መናፍቃን ስለቅዱሳን መላእክት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ለመዳሰስ እንሞክራለን አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን በረከቱን ያድለን አሜን
  1. ለምን ቅዱስ ተባሉ
  ቅዱሳ መላእክት ለምን ቅዱስ ተባሉ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ቅዱስ የሚለውን ቃል አስቀድሞ መመለስ ግድ ይላል ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ቅዱስ ፣ማለት ፣ክቡር ፤ምስጉን ፣ልዩ ፤ምርጥ፣ ንጹህ ፣ጽሩይ ማለት ሲሆን ቅዱሳን የሚለው ቃል ደግሞ ቅዱስ፡(ሳን፡ሳት፡ድስት)1 ለሚለው ቃል የብዙ ቁጥር መጠሪያ ሲሆን፤ቅዱሳት(2) ስንል ለስም ፤ለሀገር ማቴ4፥5፤ለመጻህፍት ሮሜ 1፥2፤ለሰዎችዳን7፥27፤ለመላእክት ዳን4፥9፤ለንዋየ ቅዱሳት ፤የሚቀጸል ሲሆን ለሁሉም እንደየአግባቡ ይተረጎማል ።ቅዱስ የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ወዳጆቹ አገልጋዮቹ ለእርሱ የተለዩ የተመረጡ የከበሩት በሙሉ ቅዱሳን ይባላሉ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ለርስቱ የተለዩ ለክብሩ የተመረጡት ግሩማን ንጹሐን ኃያላን ረቂቃን መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን ። ቅዱሳን መላእክትን ቅዱስ ስንል የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡራን መስጠታችን አይደለም።
  እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል ቅድስና የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ እርሱን እንደ አምላክነቱ እንደጌተነቱ ለእርሱ የሚገባውን ክብር እናቀርባለን ኢሳ 57፥15 ።በዚህ መሰረት እግዚአብሔር በባህሪው ንጹሕ ስለሆነ ንጹሐ ባህሪ ይባላል ፤ክቡር ስለሆነ የክብር አምላክ ይባላል፤ምስጉን ስለሆነ የምስጋና ጌታ ይባላል፤ጽሩይ ስለሆነ ጹሩየ ባሕሪ ይባላል ።ስለዚህ የቅድስና መሰረት በባህሪው ቅዱስ የሆነው አምላካችን በቅድስናው የጸና በመሆኑ ወዶና ፈቅዶ የቅድስናን ጸጋ ለፍጡራን እንዲደርሳቸው አድርጓል ይህም ይታወቅ ዘንድ ”እኔ ቅዱስ ነኝ እና ቅዱሳን ሁኑ ” ዘሌ19፥2 .1ጴጥ1፥17 ሲል ማዘዙ በጸጋ (በስጦታ)ቅዱሳን እንዲባሉ ወስኗል ።ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲእህ ሲል መስክሯል ”ዳሩ ግን፦እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቹ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም በኑሮአቹሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ”በማለት ለፍጥረታት የተሰጠውን የጸጋ ቅድስና በምግባር በሃይማኖት እንዲጠብቁት አባታዊ ምክሩን አስተላልፎአል።
  ቅዱሳን መላእክት ስንል የተቀደሱ ፥ የተመሰገኑ፥ የተመረጡ፥ ንጹሓን፥ የከበሩ መልክተኞች ፥አገልጋዮች ማለታችን ነው።ስለምን ይህ ክብር ተሰጣቸው ብንል በሃይማኖታቸው፥ በተፈጥሮአቸው ምክንያት ነው፤የቅዱሳን ክብር እግዚአብሔር አክብሮአቸዋል ።በአንጸሩም በጥርጥር ምክንያት ከክብራቸው የተዋረዱ ፥ጸጋቸውን የተገፈፉ በሥራቸው ውዱቃን የሆኑ ሰራዊተ አጋንንት ደግሞ እርኩሳን መላእክት ይባላሉ። 2ጴጥ 2፥4”እግዚአብሔር ኃጥያትን ለአደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጣሉ አሳልፎ ሰጣቸው ።”
  2. የመላእክት ተፈጥሮ
  መላእክት በቀዳማይ ዕለት ከተፈጠሩት 8 ፍጥረታት መካካል አንዱ በመሆናቸው ተፈጥሮአቸው” እምኅበ አልቦ ”አካላዊ ብርሃን ፈጥሮአቸዋል ስለዚህ መንፈሳውያን ረቂቃን በመናቸው ስጋና አጥንት የላቸውም በመጽሐፍ”መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ”ዕብ 1፩፥፮፲፬ ።ቅዱሳን መላእክት ስለተልዕኮአቸውና አግልገሎታቸው ከእሳት እና ከንፋስ ተፈጥረዋል የሚሉ ሊቃውንት አሉ ዕብ 1፥14 እና መዝ103፥4”መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አግልጋዮቹን የእሳት ነበልባል” ይህም ነፋስ ፈጣን ነው፣ መላእክትም ፈጣኖች ናቸው ።እሳት ብሩህ ነው መላእክትም፣ ብሩሃነ አእምሮ ናቸው ።እሳትእና ነፋስ ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው መላእክትም ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው ።ቅዱሳን መላእክት ሲፈጠሩ በነገድ መቶ በከተማ አሰር ሆነው ለባውያን ፤ነባቢያን ፤ህያዋን ሆነው ተፈጥረዋል ።(3)
  3. ቅዱሳን መላእክት መቼ ተፈጠሩ ?
  ቅዱሳን መላእከት በቀዳማይ ዕለት እሑድ ለይኩን ብርሃን ባለ ጊዜ ስጋ የሌላቸው ረቂቃን ሆነው ተፈጥረዋል ።ክቡር ዳዊትም ”መላእክት ሁሉ አመስግኑት ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ብርሃን ሁሉ አመስግኑት እርሱ ብሎአልእና ሁሉም እርሱም አዝዞአልእና ተፈጠሩም ”መዝ148፥2-5 ሲቀሌምንጦስም”በመጀመሪያው ቀን እሑድ ሰማይን እና መላእክትን ሁሉ ፈጠርኵዋቸው ይህንንም ለሙሴ አልነገርኩም ”ይላል ስለዚህ ለምስጋና እና ለቅዳሴ የተፈጠሩት መላእክት በመጀመሪያው ቀን ሲል በፍጥረት የመጀመሪያ ዕለት በዕለተ እሑድ መፈጠራቸውን ልናስተውል ይገባል።(4)
  4. የቅዱሳን መላእክት ባህርይ
  የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካካል አንዱ ስለትንሳኤ ሙታን ያስተማረው ትምህርት አንዱ ነው።ሰዱቃውያንም ስለትንሳኤ ከጠየቁት ጥያቄ አንዲቱ ሴትሰባት ባሎች ነበሯት ከእነሱ በመንግስተ ሰማያት ለማን ሚስት ትሆናለች ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸው መልስ እንዲህ የሚልነበር”በትንሣኤስ እንደሰማይ መላእክትበሰማይአያገቡም አይጋቡምም” በማለት መመለሱ የቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ሕያዋን፥ ለባውያን፥ ሰማያውያን፥ መንፈሳውያን ፥ብርሃናውያን መሆናቸውን ያሳያል ።ሉቃ24፥39 ይቆየን

  አስረጅ ፥ 1. አባ ጎርጎርዮስ የቤክ ታሪክ
  2. አለቃኪ ዳነወልድ ክፍሌ ስዋሰወ ግእዝ መዝገበ ቃላት
  3. በኅሩይ ኤርአሚያስ መዝገበ ታሪክ አንደኛ መጽሐፍ
  4. መጽሐፈ ቀለሚንጦስ
  የቅዱሳን መላእክት ተራዳሂነት እና አማላጅነት አይለየን።

  ReplyDelete
 19. እስቲ እኔ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ። በጣም ስለምትወድዋቸው ሰዎች ትፀልዩላቸዋላችሁ? ለምሳሌ ለልጆቻችሁ ፣ ለእናት አባቶቻችሁ፣ ለሚስቶቻችሁ፣ ብቻ ለሌሎች ሰዎች ሊሆን ይችላል ። ምን ብላችሁ እንደምትፀለዩ ልጠይቃችሁ አይደለም ። ግን እናንተ ከሞታችሁ በዃላ እግዚአብሔር በህይወት ዘመናችሁ ስለወዳጆቻቸችሁ የፀለያችሁትን ፀሎት እና ምልጃ የሚረሳ ወይም የማይፈፅም ይመስላችሁዋል። እስቲ አስረዱኝ።

  ReplyDelete
 20. Thank you Hiruy. good replay
  Mamleken makber yetlyale neger new. We worship God but thru Kidosan we get to him too. You sound like protestant

  ReplyDelete
 21. How a man saying he knows a bible and orthodox church doesn't differentiate " Yekidusanin Kibir" and "Amliko". The man is either totally taken by protestants or he is deaf or just a boy who cannot identity things. So childish way of writing.

  ReplyDelete
 22. አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ያድለን በስነፍጥረት ትምህርት ከ22 ነገደ ፍጥረታት መካከል አንዱ ነገድ የመላእክት ነገድ ነው (1) ።
  እነዚህም በቅድሰትቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት መላእክት ቅዱሳን ይባላሉ ለመሆኑ ቅዱሳን መላእእክት ለምን ቅዱስ ተባሉ ? መላእክት ማለት ምንማለት ነው?ተፈጥሮአቸውን፤ አማላጅነታቸውን፤ ጸጋቸውን ፤ክብራቸውን ፤በአጠቃላይ በቅዱሳን መላእከት ዙሪያ ቅድሰት ቤተክርስቲያን ያላትን አስተምሮ እና መናፍቃን ስለቅዱሳን መላእክት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ለመዳሰስ እንሞክራለን አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን በረከቱን ያድለን አሜን
  1. ለምን ቅዱስ ተባሉ
  ቅዱሳ መላእክት ለምን ቅዱስ ተባሉ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ቅዱስ የሚለውን ቃል አስቀድሞ መመለስ ግድ ይላል ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ቅዱስ ፣ማለት ፣ክቡር ፤ምስጉን ፣ልዩ ፤ምርጥ፣ ንጹህ ፣ጽሩይ ማለት ሲሆን ቅዱሳን የሚለው ቃል ደግሞ ቅዱስ፡(ሳን፡ሳት፡ድስት)1 ለሚለው ቃል የብዙ ቁጥር መጠሪያ ሲሆን፤ቅዱሳት(2) ስንል ለስም ፤ለሀገር ማቴ4፥5፤ለመጻህፍት ሮሜ 1፥2፤ለሰዎችዳን7፥27፤ለመላእክት ዳን4፥9፤ለንዋየ ቅዱሳት ፤የሚቀጸል ሲሆን ለሁሉም እንደየአግባቡ ይተረጎማል ።ቅዱስ የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ወዳጆቹ አገልጋዮቹ ለእርሱ የተለዩ የተመረጡ የከበሩት በሙሉ ቅዱሳን ይባላሉ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ለርስቱ የተለዩ ለክብሩ የተመረጡት ግሩማን ንጹሐን ኃያላን ረቂቃን መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን ። ቅዱሳን መላእክትን ቅዱስ ስንል የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡራን መስጠታችን አይደለም።
  እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል ቅድስና የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ እርሱን እንደ አምላክነቱ እንደጌተነቱ ለእርሱ የሚገባውን ክብር እናቀርባለን ኢሳ 57፥15 ።በዚህ መሰረት እግዚአብሔር በባህሪው ንጹሕ ስለሆነ ንጹሐ ባህሪ ይባላል ፤ክቡር ስለሆነ የክብር አምላክ ይባላል፤ምስጉን ስለሆነ የምስጋና ጌታ ይባላል፤ጽሩይ ስለሆነ ጹሩየ ባሕሪ ይባላል ።ስለዚህ የቅድስና መሰረት በባህሪው ቅዱስ የሆነው አምላካችን በቅድስናው የጸና በመሆኑ ወዶና ፈቅዶ የቅድስናን ጸጋ ለፍጡራን እንዲደርሳቸው አድርጓል ይህም ይታወቅ ዘንድ ”እኔ ቅዱስ ነኝ እና ቅዱሳን ሁኑ ” ዘሌ19፥2 .1ጴጥ1፥17 ሲል ማዘዙ በጸጋ (በስጦታ)ቅዱሳን እንዲባሉ ወስኗል ።ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲእህ ሲል መስክሯል ”ዳሩ ግን፦እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቹ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም በኑሮአቹሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ”በማለት ለፍጥረታት የተሰጠውን የጸጋ ቅድስና በምግባር በሃይማኖት እንዲጠብቁት አባታዊ ምክሩን አስተላልፎአል።
  ቅዱሳን መላእክት ስንል የተቀደሱ ፥ የተመሰገኑ፥ የተመረጡ፥ ንጹሓን፥ የከበሩ መልክተኞች ፥አገልጋዮች ማለታችን ነው።ስለምን ይህ ክብር ተሰጣቸው ብንል በሃይማኖታቸው፥ በተፈጥሮአቸው ምክንያት ነው፤የቅዱሳን ክብር እግዚአብሔር አክብሮአቸዋል ።በአንጸሩም በጥርጥር ምክንያት ከክብራቸው የተዋረዱ ፥ጸጋቸውን የተገፈፉ በሥራቸው ውዱቃን የሆኑ ሰራዊተ አጋንንት ደግሞ እርኩሳን መላእክት ይባላሉ። 2ጴጥ 2፥4”እግዚአብሔር ኃጥያትን ለአደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጣሉ አሳልፎ ሰጣቸው ።”
  2. የመላእክት ተፈጥሮ
  መላእክት በቀዳማይ ዕለት ከተፈጠሩት 8 ፍጥረታት መካካል አንዱ በመሆናቸው ተፈጥሮአቸው” እምኅበ አልቦ ”አካላዊ ብርሃን ፈጥሮአቸዋል ስለዚህ መንፈሳውያን ረቂቃን በመናቸው ስጋና አጥንት የላቸውም በመጽሐፍ”መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ”ዕብ 1፩፥፮፲፬ ።ቅዱሳን መላእክት ስለተልዕኮአቸውና አግልገሎታቸው ከእሳት እና ከንፋስ ተፈጥረዋል የሚሉ ሊቃውንት አሉ ዕብ 1፥14 እና መዝ103፥4”መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አግልጋዮቹን የእሳት ነበልባል” ይህም ነፋስ ፈጣን ነው፣ መላእክትም ፈጣኖች ናቸው ።እሳት ብሩህ ነው መላእክትም፣ ብሩሃነ አእምሮ ናቸው ።እሳትእና ነፋስ ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው መላእክትም ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው ።ቅዱሳን መላእክት ሲፈጠሩ በነገድ መቶ በከተማ አሰር ሆነው ለባውያን ፤ነባቢያን ፤ህያዋን ሆነው ተፈጥረዋል ።(3)
  3. ቅዱሳን መላእክት መቼ ተፈጠሩ ?
  ቅዱሳን መላእከት በቀዳማይ ዕለት እሑድ ለይኩን ብርሃን ባለ ጊዜ ስጋ የሌላቸው ረቂቃን ሆነው ተፈጥረዋል ።ክቡር ዳዊትም ”መላእክት ሁሉ አመስግኑት ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ብርሃን ሁሉ አመስግኑት እርሱ ብሎአልእና ሁሉም እርሱም አዝዞአልእና ተፈጠሩም ”መዝ148፥2-5 ሲቀሌምንጦስም”በመጀመሪያው ቀን እሑድ ሰማይን እና መላእክትን ሁሉ ፈጠርኵዋቸው ይህንንም ለሙሴ አልነገርኩም ”ይላል ስለዚህ ለምስጋና እና ለቅዳሴ የተፈጠሩት መላእክት በመጀመሪያው ቀን ሲል በፍጥረት የመጀመሪያ ዕለት በዕለተ እሑድ መፈጠራቸውን ልናስተውል ይገባል።(4)
  4. የቅዱሳን መላእክት ባህርይ
  የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካካል አንዱ ስለትንሳኤ ሙታን ያስተማረው ትምህርት አንዱ ነው።ሰዱቃውያንም ስለትንሳኤ ከጠየቁት ጥያቄ አንዲቱ ሴትሰባት ባሎች ነበሯት ከእነሱ በመንግስተ ሰማያት ለማን ሚስት ትሆናለች ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸው መልስ እንዲህ የሚልነበር”በትንሣኤስ እንደሰማይ መላእክትበሰማይአያገቡም አይጋቡምም” በማለት መመለሱ የቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ሕያዋን፥ ለባውያን፥ ሰማያውያን፥ መንፈሳውያን ፥ብርሃናውያን መሆናቸውን ያሳያል ።ሉቃ24፥39 ይቆየን

  አስረጅ ፥ 1. አባ ጎርጎርዮስ የቤክ ታሪክ
  2. አለቃኪ ዳነወልድ ክፍሌ ስዋሰወ ግእዝ መዝገበ ቃላት
  3. በኅሩይ ኤርአሚያስ መዝገበ ታሪክ አንደኛ መጽሐፍ
  4. መጽሐፈ ቀለሚንጦስ
  የቅዱሳን መላእክት ተራዳሂነት እና አማላጅነት አይለየን።

  ReplyDelete
 23. We need more news regarding to our church. We do not trust hara zetwahido All we have supported the law that proposed by Federal affairs of Ethiopia. Please write more to give us awarness about this topic. hara provided for readers negative side of the law

  ReplyDelete
 24. ጓዶች እኔስ ፈራሁ!!

  አንዳችን የለላዉን ሀሳብ ሳኒሬዳ ለተቃውሞ ብቻ ቸኩለን ክርከርና ትዕቢት እንድሁም እልሄኝነት የተሞላበት አንዳችን ለላውን ለማሸነፍ ስንታገል መስመር እንዳንስት እንጠንቀቅ፡፡

  "በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፡፡..... (1ኛጢሞ. 6፥4)" ትዕቢት በጣም መጥፎና ልብን የሚያደነድን እንዳናስተውል የሚያደርግ ሓጥአት ነው፡፡ እናውቃለን የተሻልን ነን አንበል፡፡ የተሻለና ፍጹም የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡

  "በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤.....(2ኛቆሮ.13፥5)" የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።

  ጓዶች let's examine ourselves, let's ask ourselves where we are? let's see ourselves according to the word of GOD. Lets pray the lord and he may reveal us the truth. unless and otherwise we are wasting time, we are pushing our self to hell. GOD said "You find me when you seek me with all your heart." So let's seek for him. Because the truth is with him.

  "Christianity is not religion, Christianity is Christ !!"

  Let God may help us !!

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም አዝናለሁ!! ይህ ሁሉ የምልጃ ጋጋታ ምንድርነዉ? እዉነት ጌታችን ጨካኝና ልመናችንን የማይሰማ ሆኖ ነዉ? በስሜ አንዳች ብትለምኑ ይሰጣችኋል፤ ድጅ ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ እናንት ክፎዎች ስትሆኑ.. . .. ጌታ ደግሞ አብዝቶ አንደሚሰጣችሁ አታዉቁምን? እያለ አባትነቱን እያረጋገጠልን በቀጥታ እንድንለምነዉ ራሱ እየለመነን ይህንን ፍቅር መገፍተርና አማላጅ መደርደር አያሳዝነዉምን? ወይስ በቃሉ የማይገኝ ጌታ ነዉ ያለን እስቲ አስረዱኝ ወይም ሰይጣን እየተጫወተብን ነዉ? ሌላዉ ደግሞ አንዴ የተማርኩት ነገር አስር ጊዜ ስህተትም ቢሆን አልተዉም አለዚያ ፕሮቴስታንት እባላለሁ ብለዉ ጌታን የሚያስቀኑ አሉ. አቶ ህሩይም ብዕርዎን ለጌታችን ክብር ያዉሉት. እስቲ ስለፍቅሩ ከልብዎ ያስቡና እርሱ ራሱ ምን ያህል እንዳዘነ ይነገርዎታል. ክብር ሁሉ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን.

   Delete
 25. T o anonymous Feb.4, 2014 @11:38 and Feb 5,2014@12:18 are you really Orthodox Christian were did you grow up in Christian family? What do you think when you say”Dedeb, Ahiiya to any human created by almighty GOD. Are you really sure you are Ethiopian ORTHODOX? Shame on you. God have Mercy on you. I wonder if you understand anything about being Ethiopian Orthodox.

  ReplyDelete